የቤተክርስቲያን ዘመናት - ኤፌሶን፤ የመጀመሪያው ዘመን፤ ከ33ዓ.ም. - 170ዓ.ም.
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በሰገነት ውስጥ ተሰብስበው በነበሩ አማኞች እና በእግዚአብሔር መካከል አንድም ሰው ጣልቃ ሳይገባ በመለኮታዊ ኃይል ብቻ ነበር የተወለደችው። በእያንዳንዱ አናት ላይ መለኮታዊ የእሳት ልሳን ባረፈባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በቀጥታ በእያንዳንዳቸው ውስጥ ገብቶ የነበሩበትን ቤት ሞላው። የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እንዲህ ነበር የተወለደችው።
የሐዋርያት ሥራ 2፡1 በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
2 ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
ባለ ሰባት ቅርንጫፉ መቅረዝ በ2000 ዓመታት የሰው ታሪክ ውስጥ የሚነሱትን ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ነው የሚወክለው። የመጀመሪያው የኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን የተጀመረው በጴንጤ ቆስጤ እለት እግዚአብሔር መካከለኛውን መቅረዝ በለኮሰው ጊዜ ነው። ይህች የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን ፍጹም የሆነች ቤተክርስቲያን ነበረች። እውነተኛ ቤተክርስቲያን ምን መምሰል እንዳለባት ማሳያ የምትሆነው ይህች ቤተክርስቲያን ብቻ ናት። የአዲስ ኪዳን አስተምህሮዎች የክርስትና አስተሳሰባችን ሁሉ ዋነኛ መሰረት መሆን አለባቸው። በአዲስ ኪዳን ከተገለጠው እምነት የተለየ ነገር በሙሉ ከእውነተኛው መንገድ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ፈቀቅ ማለታችንን ያመለክታል። ከመንገዱ ፈቀቅ ካልን መልካም ቦታ ላይ አይደለንም። ከተጻፈልን ቃል ውጭ የሚያፈነግጥ ማንኛውም እንቅስቃሴ ሁሉ ጀማሪውና ፈጻሚው ሰይጣን ነው።
እስቲህ የዚያን አስደናቂ ወጣት ንጉስ የኢዮስያስን ምሳሌነት እንመልከት።
2ኛ ዜና 34፡1 ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።
2 በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፥ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።
እግዚአብሔር ለመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በጴንጤ ቆስጤ እለት ያደረገውን ነገር በተመሳሳይ መንገድ መስዋእቶቹን በበላው መለኮታዊ እሳት የሰሎሞንን ቤተ መቅደስ በቀባ ጊዜ አድርጓል።
2ኛ ዜና 7፡1 ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን በላ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ።
2 የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም።
ነገር ግን የአይሁድ ሕዝብ በማዕረግ ከእነርሱ ከፍ ያሉ በአሮን ክሕነት የተሸሙ ካሕናት በላያቸው ነበሩዋቸው። ሕዝቡ እግዚአብሔርን ሊያመልኩ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ በእግዚአብሔርና በእነርሱ መካከል ካሕናቱ ሲኖሩ ነበር። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ይህ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ተሹሞ የነበረ ክሕነት ውጤታማ አልሆነም። በሰዎች ላይ የተመሰረተ ነገር ሁሉ ይወድቃል። በስተመጨረሻም እግዚአብሔር በ33 ዓ.ም. በስቅለት ሰዓት የመቅደሱን መጋረጃ በመቅደድ የመቅደስ አምልኮ ስርዓትና የመቅደሱ የክሕነት አገልግሎት ማብቃቱን በግልጥ አመለከተ። ነገር ግን ካሕናቱ በሕዝቡ ላይ የነበራቸውን ስልጣንና አሥራት መቀበላቸውን በራሳቸው ፈቃድ ቀጠሉ፤ በሕይወታቸው የነበራቸው ብቸኛው ፍላጎት ሰዎችን መግዛት ነበርና። አይሁድን መግዛት ቀጠሉ፤ ሕዝቡን ኃይል በሌለው የአምልኮ መልክ ማታለል ተሳካላቸው። ነገር ግን ይህን ማታለላቸውን መቀጠል የቻሉት እግዚአብሔር መቅደሱን በ70 ዓ.ም. እስኪያፈርሰው ድረስ ብቻ ነበር። መቅደሱን ባፈረሰው ጊዜ የራሳቸውን ጥቅም ያሳድዱ የነበሩ ካሕናትም አብረው ጠፍተዋል። ከዚያ ወዲያ ከእግዚአብሔር ተለይቶ የሄደው መንፈስ የሌለው ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውም በማታለል መቀጠል አልቻለም።
የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ልዩ ሆና ነው የተጀመረችው።
በሕዝቡ እና በእግዚአብሔር መካከል መሪ ሆነው የገቡ ሰዎች አልነበሩም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉንም ክርስቲያን አማኞች ወንጌልን ወደ ሐጢያተኛው ዓለም ይዘው ይሄዱ ዘንድ፤ በስፍራ ሁሉ በየአቅጣጫው እንዲስፋፉ ነገር ግን ሐዋርያዊ መነሻቸውን እንዳይረሱ ካሕናት አድርጎ ሾማቸው። ሐጥያተኞች ንሰሃ ሲገቡ እነርሱም ወደዚህ ክሕነት ይቀላቀሉ ነበር። ስለዚህ አንድም ክርስቲያን በእግዚአብሔር እና በሌላ ክርስቲያን መካከል አይቆምም ነበር። አሕዝብ በብዛት ስለ ክርስቲያኖች የሚሰጡት አስተያየት እንዲህ የሚል ነበር፡- “ታያላችሁ እነዚህ ክርስቲያኖች እንዴት እንደሚዋደዱ?” ክርስቲያን በእግዚአብሔር እና ባልዳነ ሰው መካከል መቆም እና ወደሚያድናቸው ጌታ ማመልከት ይችላል። ነገር ግን ሐጢያተኞቹ ንሰሃ ከገቡ በኋላ የንጉስ ካሕናትን ስለሚቀላቀሉ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር እኩል ናቸው።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት … ናችሁ፤
ወንድማማችነት መሰረቱ እኩልነት ነው። ሁላችንም ከእርስ በርሳችን መማማር እንችላለን። ማንም ከማንም አይበልጥም።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡17 ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ…።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡5 እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ሲጠቅስ ለቃሉ እውቅና በመስጠት አንዳችን ለሌላችን እንገዛለን። የእግዚአብሔርን ቃል መቀበላችንን እናሳያለን እንጂ እኛ ትክክል መሆናችንን ለማስረዳት አንሞክርም። ከሌሎች የተሻላ ስጦታ ወይም ችሎታ ካለህ ያንን የሰጠህ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ከሌሎች የተሻለ ሰው አያደርግህም። ችሎታህ ከሌሎች የበለጠው እግዚአብሔር ስለሰጠህ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ማንኛውንም ስጦታ ሲሰጥህ ሌሎችን ለማገልገል እንድትጠቀምበት ይጠብቅብሃል እንጂ ራስህን በሌሎች ላይ ገዥ እንድታደርግበት አይደለም። ደግሞም ማንም ሰው እኛ ከምናምነው ወይም ከምናደርገው ነገር የተለየ ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲያሳየን፤ ያሳየን ሰው ማንም ይሁን ማን ወዲያው ለእግዚአብሔር ቃል እንገዛለን።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ከመጀመረያው ጀምሮ ሁለት የወይን ሃረጎች ሲያደጉ ነበር።
አንደኛው የወይን ሃረግ ከኢየሱስ ጋር ሕብረታቸውን ማሳደግ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን እና ሃሳባቸው ሌሎች ሰዎች በሚናገሩት እንዳይቀረጽ የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ናቸው። ይህ እግዚአብሔርን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ቃል መሰረት እና በራስ ሕሊና በመመራት የማምለክ ነጻነት ማንም በድርጅት ሊያዋቅረው የማይችለው እሳት ሆነ። በተለያዩ ቦታዎች እንደ ሰደድ እሳት ነደደ፤ ደግሞም በአንድ ቦታ ሲዳፈን ሌላ ቦታ ይቀጣጠላል። ብዙውን ጊዜ በኤልያስ ዘመን ተደብቀው እግዚአብሔርን ያመልኩ እንደነበሩት እንደ 7000 ሺዎቹ ሌላው ሰው አያውቃቸውም። የስደት ብዛት ክርስቲያኖች ራሳቸውን በአደባባይ ሳይገለጡ እንዲኖሩ አደረጋቸው። ነገር ግን በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ በቃሉ የተጻፈውን ብቻ ለመታዘዝ የሚፈልጉ እግዚአብሔር ያስነሳቸው ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ብዙውን ጊዜ ሰው የማያውቃቸው ትሁታን ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ፍላጎታቸው የተራራውን ስብከት የሕይወት መመሪያቸው አድርገው በጸጥታ እግዚአብሔርን በማምለክ መልካም ሥራን መስራት ነው።
የየትኛውም ታላቅ ሰው ስልጣን የእግዚአብሔርን ቃል ስልጣን እንዲተካ አይፈቀድለትም ነበር።
ይኸኛው የወይን ሃረግ እስዛሬም ድረስ አለ። እነዚህ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ሕብረት ሊያደርጉ ይችላሉ ነገር ግን ኢየሱስን እና ቃሉን ብቻ መታዘዝ ስለሚፈልጉ የቤተክርስቲያን ወገን አይደሉም፤ ከዚህ የተነሳ ሰው ባይፈልጋቸውም ባያከብራቸውም አይፈሩም። በራሳቸው የማሰብ ነጻነትን እና አንድ ሃሳብ በእርግጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚስማማ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ከዚያም ሃሳቡን የሚቀበሉት የሆነ ሰው እውነት ነው ስላለ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚመሰክርለት ነው። በእነርሱ እና በእግዚአብሔር መካከል ሰው ሲቆም አይመቻቸውም፤ በተለይም ደገሞ ሰው ሁሉ ድክመት እንዳለበት ስለሚገነዘቡ። በእርሷ እና በባሏ መካከል ሰው እንዲገባ የምትፈልግ ሙሽራ የለችም። የትኛዋም ሙሽራ ለባሏ እንጂ ለሌላ ሰው ቃል መገዛት አትፈልግም። ልክ እንደዚሁ የእግዚአብሔር ሙሽሮችም ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚገዙት።
ሮሜ 3፡12 በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም።
ኤርምያስ 17፡5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።
ክርስቲያኖች በመሪዎቻቸው ሲነተማመኑ ዓይኖቻቸውን ከእግዚአብሔር ላይ ያነሳሉ። ከዚያም እግዚአብሔርን እንደምናገለግል ይመስለናል ነገር ግን እርግማን እየተቀበልን ነን። የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ዘመን አሁን ያለንበት ዘመን ትልቁ እርግማን ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው። የዛን ጊዜ የእውነት እርግማን ውስጥ መሆናችን ይታወቀናል።
ከዚያም ደግሞ ሌላ ሐሰተኛ የወይን ሃረግ በቀለ፤ እርሱም በሰዎች ዘንድ ገናና የሆነችዋ ቤተክርስቲያን ናት። የዚህች ሰዎች ያደራጁዋት ቤተክርስቲያን መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎማቸውን እና በብልሃት የፈጠሩት ሰውኛ አስተሳሰባቸውን ለሕዝቡ አስተላለፉ። ይህ ሐሰተኛ የወይን ሃረግ የተመሰረተው አንድን ቅዱስ ሰው እንደ መሪ መከተል እና ምን እንዲያምኑ እንዲነግራቸው በሚፈልጉ ሰዎች ነው። ሰይጣን ያለማቋረጥ መሪዎችን በመጠቀም ሰዎችን ለመግዛትና ከአዲስ ኪዳን ትምሕርት ያፈነገጡ ሐሳቦችን እንዲያምኑ ለማድረግ ይሞክራል። እነዚህ ሰዎች ዋስትናቸው የኢየሱስ በመሆናቸው ሳይሆን የቤተክርስቲያን በመሆናቸው ነው። ዛሬ ሁሉም እኛ ትክክል ነን የሚሉ ከ45000 በላይ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖችና የቤተክርስቲያን ድርጅቶች ሲኖሩ ሁሉም ግን እውር ተብለው ነው የተገለጹት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከእነዚህ በድርጅት ከተዋቀሩ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ በእድሜ ቀደምት፣ ታላቅ እና በቀላሉ ተለይታ የምትታወቅ ናት። በዓለም ላይ በርዝመቱ አንደኛ የሆነ ያልተቋረጠ የአምባገነን መሪዎች መተካካት የታየው በዚህች ቤተክርስቲያን ነው። ሕዝቡ መሪያቸው በሚለው ሁሉ መስማማት አለባቸው፤ ፖፕ ወይም ጳጳስ ተብሎ የሚጠራው መሪያቸው በአስተሳሰቡና በንግግሩ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ጳጳሳት ጋር ቢቃረንም እንኳ በፍጹም አይሳሳትም ተብሎ ይታመናል።
ክርስቲያኖች ከሚያደርጉት የበጎ አድራጎት ሥራ አንጻር ሁለቱም የወይን ሃረጎች ድንቅ ሥራ ሰርተዋል። ይህም የበጎ አድራጎት ሥራ ክርስትናን ስኬታማ ለማድረግ የሚጠቅም ታላቅ መሳሪያ ነው። ወላጅ የሌላቸውን ልጆች፣ መበለቶችን፣ ምስኪኖችና ድሆችን ረድተዋል። እንደ ድርቅ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የበሽታ ወረርሽኝ እና ጦርነት የመሳሰሉ አደጋዎች በሚፈጠሩ ጊዜ ማሕበራዊ አገልግሎቶቻቸው ተገልጠዋል። ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውንና ቁሳቁስ በልግስና ሰጥተዋል።
ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን ከመሰረቱ እና አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ ሐዋርያት ሁሉ አለፉ። እነርሱም ሐዋርያት ያስተማሩትን እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን ትምሕርት በሚከተሉ የሽማግሌዎች ቡድን የሚመሩ ቤተክርስቲያኖችን መሰረቱ። የዳኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ካሕናት ነበሩ፤ በዚህም የወንድማማች እኩልነት ከሕዝቡ በላይ ከፍ የሚል በአሮን ክሕነት የተሾመ ልዩ ሰው አልነበረም። ልክ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሰባኪዎች የሚያመለክቱት ወደ ክርስቶስ እና ወደተጻፈው ቃል እንጂ ወደራሳቸው አልነበረም።
ዮሐንስ 1፡35 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥
36 ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።
37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
አንድ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ሲናገር ብትሰማ የንግግሩን ቃላት ስላደመጥክ ብቻ እርሱን ሰማኸው ማለት አይደለም። ሲናገር ሰማኸው የሚባለው ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ስትከተለው ነው።
ነገር ግን ብርሃን ባለበት ጥላዎችም አሉ። ሰይጣን በአምስቱ የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ በሚሰማሩ አገልጋዮች አማካኝነት ጥቂት ሰዎችን በሌሎች ሰዎች እና በእግዚአብሔር መካከል ከፍ ለማድረግ ያለማቋረጥ ሲተጋ ቆይቷል። እንደ ሰይጣን አመለካከት በአንተ እና በእግዚአብሔር ቃል መካከል የሆነ ሰው ያስፈልጋል። እነዚህ አገልጋዮች የቤተክርስቲያን መሪ ለመሆን ተቀባይነትን አግኝተው ከተሳካላቸው በኋላ ቀስ በቀስ ሰዎችን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ከተጻፈው እንዲርቁ ያደርጉዋቸዋል። ክርስቲያኖቹ የእግዚአብሔርን ቃል በንቃት መጠበቅ ሲያቆሙ እና ቸል ሲሉ የሰዎች አመለካከት እና የሰዎች ገዥነት በእግዚአብሔር ቃል ዘር መካከል እንደ አረም ተዘራ። የቤተክርስቲያን መሪ የሆነ ሰውን ለመቃወም ከመሞከር ይልቅ ከእርሱ ጋር መስማማት ይቀላል፤ በተለይም የገዥነት ባሕርያ ያለው ሰው ሲሆን። ከእርሱ ጋር ስትስማማ ተቀባይነትን እንዳገኘህ እንዲሰማህ ያድግሃል። ከእርሱ ጋር አልስማማም ካልክ ደግሞ ማንም እንደማይፈልግህ እንዲሰማህ ያደርግሃል። ስለዚህ በስሜታዊነት እና በቤተክርስቲያን ጥላ ስር የመኖር ፍላጎታችንን በመጠቀም ይገዛናል እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም።
የአሕዛብ ሐይማኖቶች ብዙውን ጊዜ ሞያተኛ ካሕናት አሉዋቸው።
ታላቁ እስክንድር ከሰራቸው አስደናቂ ጀብዱዎች የተነሳ በምሥራቅ ሃሮች በቀላሉ እንደ አምላክ ተቆጥሮ ይመለክ ነበር፤ ምዕራባውያን ደግሞ እያንገራገሩም ቢሆን ለአምላክነቱ እውቅና ሰጥተዋል። ምሥራቃውያን ቃየን የኖረበት ሃገር አካባቢ መሪዎቻቸውን እንደ አማልክት ያመልኳቸው ነበር። ምዕራባውያን ግን እንዲህ አይነት ልማድ አልነበራቸውም። እስክንድር ከግሪክ ተነስቶ ወደ ምስራቅ ሄዶ ግብጽ ውስጥ “የአምላክ ልጅ” ተብሎ ተቀባይነትን ያገኘ የመጀመሪያ ምዕራባዊ ሰው ነው። አምላካቸው አሙን ራ ነበረ፤ እርሱም አምላክ የሆነ በውትድና ጀብዱ ነበር። ፋርስን አሸነፈ፤ አፍጋኒስታን ሄዶ ያለምንም ርህራሄ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ሕጻናትን በጅምላ በመጨፍጨፍ እና በብልጣብልጥነት የአፍጋኒስታንን ገዥ ሴት ልጅ አግብቶ አፍጋኒስታንን በመቆጣጠርና በማረጋጋት የተሳካለት ብቸኛው ሰው ሆነ። ከዚያም ራሱን “አምላክ” ብሎ ጠራ፤ ያውም ለምዕራባውያን ተከታዮቹም ጭምር። ምዕራባዊ ግሪኮች ተገደው ቢያመልኩትም እርሱ ግን ወደ ምዕራብ አልተመለሰም። አምላክነቱን ባወጀ በአራት ዓመት ውስጥ ባልታወቀ ሁኔታ ባቢሎን ውስጥ ሞተ። ኢየሱስ አምላክም የእግዚአብሔር ልጅም ሆኖ ያገለገለው ግን ለሦስት ዓመት ተኩል ብቻ ነበር። ስለዚህ እስክንድር ከምዕራባውያን ገዥዎች ሁሉ ይበልጥ ዝነኛ በመሆኑ አምላክ ነኝ ማለቱና ግሪክ ውስጥ ያሉ ሕዝብ እንዲያመልኩት መፈለጉ እድሜውን አሳጥሮ ከአራት ዓመት በላይ እንዳይኖር አደረገው። ከኢየሱስ ክርስቶስ ልትበልጡ አትችሉም። ማንም ሰው ከኢየሱስ ጋር መወዳደር የለበትም፤ ሊወዳደር ቢያስብ በሕይወቱ ላይ ፈርዶ ነው የሚወዳደረው። እግዚአብሔር ማንም ሰው እንዲፎካከረው አይፈልግም። እኛ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ለመወዳደር ብቁ አይደለንም።
ከእስክንድር ጀነራሎች አራቱ የእስክንድርን ስልጣን ወረሱ ግን በእስክንድር ምትክ አምላክነታቸውን ቢያውጁም እንኳ የምዕራቡን ዓለም ሊያንበረክኩ አልቻሉም። አራቱ ጀነራሎች ከሞቱ በኋላ የነገስታት ወደ አምላክነት የመለወጥ ሃሳብ በጴርጋሞን ከተማ በስተቀር በምዕራባውያን ዘንድ እየመነመነ ሄደ። ቂሮስ ባቢሎንን የተቆጣጠረ ጊዜ የባቢሎን አሕዛብ ካሕናት ስሙ አታለስ በሚባል ፖንቲፍ ወይም ሊቀካህናቸው ሥር ሆነው ወደ ጴርጋሞን ሸሹ።
እስክንድር ከሞተ በኋላ ከጀነራሎቹ አንዱ ላይሲማከስ ጴርጋሞንን ተቆጣጠረና ልክ እንደ እስክንድር አምላክ ነኝ አለ። የጴርጋሞን ግዛት በለጸገች።
ላይሲማከስ በተገደለ ጊዜ ባቢሎናዊው የጴርጋሞን ሊቀ ካሕናት በጴርጋሞን ላይ ነገሰ፤ ከዚያ እርሱም ልክ እንደ ላይሲማከስ አምላክ ነኝ በማለቱ ወደ አምላክነት የተለወጡ ነገስታት ያሉበት የአታሊድ ሥርወ መንግስት ተመሰረተ። እነዚህ አምላክ ነኝ የሚሉ ነገስታት ተቀባይነታቸው በአካባቢያቸው ብቻ ነበር።
እስክንድርስ ብዙ የጦር ሜዳ ጀብዱዎች ሰርቶ ነው ብዙ ትኩረት ወደ ራሱ ሊስብ የቻለው፤ እነርሱ ግን ምንም ስላልሰሩ የብዙዎችን ቀልብ ማግኘት አልቻሉም። ግሪኮች እጅግ ብልሆችና ስህተታቸውን በብልሃት አለባብሰው፤ በፍልስፍና እና በጥበብ በበለጸገ ክርክራቸው ስህተት እንዳልሆነ የማሳየት ችሎታ የተካኑ ሰዎች ናቸው። በተራቀቀ አስተሳሰባቸው አማካይነት የባቢሎንን ምስጢራት አሰማምረው በየስፍራው አስፋፉ፤ ከዚያም በ133 ዓ.ም. የመጨረሻው የጴርጋሞን አምላክ-ንጉስ አታለስ 3ኛው ሲሞት እነዚህ ምስጢራትና የያዙዋቸው መሪ የሆነ ሰው አምላክ ነው የሚሉ ሃሳቦች ለሮም ተላለፉ። የባቢሎን ምስጢራት በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ክብር የነበራቸው ሲሆን ሮም ውስጥ ግን አንድም ዝነኛ የሆነ ሊቀ ካሕን ወይም ፖንቲፍ ስላልነበረ ማንም አላስተዋላቸውም። ከዚያም ዩልየስ ቄሳር ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዓመተ ዓለም በሮም ውስጥ የባበሎናውያን ምስጢራት ፖንቲፍ ለመሆን ጉቦ የሚከፍልበት ብዙ ገንዘብ ተበደረ። የፖነቲፉ አስገራሚ አልባሳትና ብዙ ክንዋኔዎች ያሉት የባቢሎናውያን ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች በአሕዛብ ዘንድ ለክሕነት ታላቅ ከበሬታ አስገኙ። ከሮማ ገዥዎች ሁሉ ዝነኛ በሆነው በዩልየስ ቄሳር አማካኝነት የባቢሎናውያን ምሥራቃዊ ምስጢራት ከፍ ያለ ክብርና ስልጣንን ተጎናጸፉ። የጴርጋሞን ከተማ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ29 ዓመተ ዓለም ቄሳርን ከሞተ በኋላ አምላክ አድርጋ ሾመችው።
ስለዚህ ዩልየስ ቄሳር በሮም ውስጥ አምላክ ተደርጎ የተመለከ የመጀመሪያው ሰው ሆነ። የስሙ የመጀመሪያ ፊደሎች በእንግሊዝኛ ሲጻፉ J C ስለሆኑ ከኢየሱስ ስም መነሻ ፊደሎች ጋር ማለትም Jesus Christ ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ቄሳር ሲሞት የእሕቱን የልጅ ልጅ አውግጦስን በራሱ ቦታ ተካ።
ንጉሱ አውግስጦስ በሕይወት ሳለ በጴርጋሞን ውስጥ አምላክ ተደርጎ ተመለከ። እርሱ የባቢሎናውያን ምስጢራት ፖንቲፍ ስለነበረ በሮማ ግዛት ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ሕዝቦች ወደ አንድነት ማምጫ ይሆን ዘንድ ንጉስን አምላክ አድርጎ የማምለክ ልማድ በአንድ ጊዜ ተስፋፋ። በ400 ዓ.ም. የሮማ ጳጳስ ይህንን የፖንቲፍ ማዕረግ ስለወሰደ የባቢሎናውያን ምስጢራት ሊቀ ካሕን እና ፖፕ መሆን ችሏል። እንግዲህ የባቢሎን ምስጢራት እንደዚህ ይፋዊ በሆነ መንገድ ነው ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የገቡትና ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ባቢሎን ምስጢር የለወጧት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልክ እንደ አሕዛብ ከምእመኑ እና ከጉባኤው በላይ ከፍ የሚሉ ሞያተኛ ካሕናት ኖሩዋት።
ከሕዝቡ በላይ ካሕናትን ይሾሙ ዘንድ ሰይጣን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አስተማረ፤ በዚህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወደ ብሉይ ኪዳኑ የአሮን ክሕነት እንድትመለስ አደረጋት። እነርሱም ከካሕናቱ በላይ ጳጳሳትን በመሾም ስርዓቱ ላይ ለውጥ አደረጉ።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አወቃቀሯ በአጠቃላይ የሮማ ግዛትን ንጉሳዊ አስተዳደር የተከተለ ነው፤ በዚህም ስርዓት አንድ ጳጳስ አንዲትን ከተማ እና በዙሪያዋ ያሉ ግዛቶችን ያስተዳድራል። በትልቅ ከተማ የሚቀመጥ የአውራጃ ጳጳስ በአውራጃው ካሉት ሌሎች ጳጳሳት በላይ የበለጡ መብቶች አሉት። በትልቅ ከተማ የሚቀመጡ ጳጳሳት የአውራጃ ጳጳሳትን የሚያስተዳድሩ ሊቀ ጳጳሳት ሆኑ። በ700 ዓ.ም. አካባቢ ከሊቀ ጳጳሳቱ በስልጣን የሚበልጡ ካርዲናሎች በስልጣን ተዋረዱ ውስጥ ብቅ አሉ።
እንግዲህ ማእከላዊ መዋቅር ባላት ድርጅት ውስጥ ታላቅ ስልጣን በተጎናጸፈው በፖፑ ገዥነት ስር ይህን የመሰለ እጅግ የተወሳሰበ የቤተክርስቲያን የስልጣን ተዋረደ ተመሰረተ። የዚህ ግዙፍ ድርጅት እድገት አስቀድሞ የታቀደበት አለነበረም፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱ ለሁኔታዎች ምላሽ በሰጠች ቁጥር ባልታሰበ መጠን እየጨመረ ሄደ፤ ጳጳሳቱም በክርስቲያኖች ላይ ስልጣንን ለመቆናጠጥ ግፊት በሚያደርጉ ብልሃተኛ ሰዎች እጅ ውስጥ እንዲሁም ይህንን እድገት ለመግታት አቅም የሌላቸው ሰዎች እጅ ውስ ገቡ።
ይህች የሮማ ግዛትን የመፈራረስ ቀውስ ተቋቁማ ያለፈች በማዕከላዊነት የተዋቀረች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ድርጅት በሌሎች ካቶሊካዊ ባልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ በእግዚአብሔር እና በክርስቲያኖች መካከል እንዲቆሙ ከፍ በተደረጉ አምስት አገልግሎቶች አማካኝነት ምሳሌነቷ ተኮርጇል። ለብቃት እና ቅልጥፍና ሲባል አንድ ሰው የነዚህ የአምስት አገልግሎቶች ራስ እንዲሆን አስፈልጓል። ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሰው ፓስተር የሚለው ቃል ትርጉሙ ብዙም ግልጽ ባለመሆኑ ያለ ምንም ተቀናቃኝ የእያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ሰተት ብሎ መግባት ችሏል። ከዚያም በከተሞች ውስጥ ኤጲስ ቆጶሳት ከፓስተሮች በላይ ተሸሙ። ከዚያም እነዚህ ሐይማኖታዊ ድርጅቶች እያደጉ ሲመጡ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እና ፓትሪያርኮች ተጨመሩ። ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ዴሞክራሲ ከመመራት ይልቅ ማዕከላዊ በሆነ የአንድ ሰው መሪነትና ስልጣን ስር መተዳደር ጀመረች። በመንፈስ የሆነ ነጻነት ጠፍቶ በሰው ግትር አመራር ተተካ።
እግዚአብሔር አይሁዳውያንን በአሕዛብ ተጽእኖ እንዳይረክሱ በማሰብ ከሌሎች ሕዝቦች ተለይተው እንዲኖሩ መረጣቸው። አይሁድ የመጽሐፉ ሕዝብ እንዲሆኑ ተጠሩ። ከአንድ ቅዱስ መጽሐፍ ጋር ብቻ ጽኑ ቁርኝት የነበረው ሌላ ጥንታዊ ሐይማኖት የለም። አዲስ ኪዳንን ብቻ አጥብቀው የያዙና የቤተክርስቲያን የስልጣን ተዋረድ ያላበጁ ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ የሰው ዓይን ውስጥ አይገቡም ነበር። እያደጉ የመጡት የተደራጁ ሐይማኖቶች ግን የታሪክ ጸሐፊዎችን ዓይንና ትኩረት ሁሉ ስበዋል።
ለተወሰኑ አሕዛብ የአይሁድ እምነት የሚስባቸው አይሁድ አንድ አምላክ ብቻ አለ ብለው ማመናቸው ነው። ለሌሎች አሕዛብ ደግሞ የአሕዛብ እምነት የሚስባቸው አሕዛብ በልዩ ልዩ ሥላሴዎቻቸው ማመናቸው ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ማንነት በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች ቤተክርስቲያንን ይሰነጣጥቋት ነበር፤ ዛሬም እንደዚያው ነው።
አይሁድ የተመረጡት የሚያስመርጣቸው መልካምነት ተገኝቶባቸው አልነበረም። ይም ምርጫ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበረ። እኛ ሰዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመረዳት የሚበቃ ልቦና የለንም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ስሕተት ለእግዚአብሔር ፈቃድ ጸንታ አለመገዛቷ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ይመራቸው ዘንድ ራሳቸውን አልሰጡም። ማድረግ የሚገባቸውን የሰው መሪ እንድነግራቸው ፈለጉ።
እውነተኛዋ የወይን ሃረግ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ትልቅ ትኩረት እንደሚሻ ጉዳይ ትይዘው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ በመንድ የሚመራ መንፈሳዊ ኮምፓሳቸው ነበር። በቀጣዮቹም ነውጥ የሞላባቸው ክፍለ ዘመናት የታሪክ እንቅስቃሴዎች እየተመሩ የቆዩት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለው መለኮታዊ ትምሕርት እና የተጻፈው ቃል እንዳይስፋፋ ለመቃወም በሚነሱ ተንኮል በሞላባቸው የሰይጣን አቅዶች መካከል በሚደረግ ትግል ነው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ጥብቅ የሆነ ትስስርና ወንድማማችነት ውስጥ ንብረትን በጋራ በመጠቀም እንዲሁም ገንዘብን ለእያንዳንዱ እንደሚያስፈልገው መጠን በማከፋፈል የምትኖር አንድ አካል ነበረች። ልብሶች ተበጣጥሰው እስኪያልቁ ድረስ ይለበሱ ነበር። ሰዎች የነበራቸውን ትርፍ ልብስ ለሌለው በነጻ ይሰጣሉ። ቁሳቁሶችን ሁሉ ይከፋፈላሉ። ኑሮዋቸው በቁጠባ ነበር። ክርስቶስ በሐጥያተኛ ሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ግድግዳ ብቻ አልነበረም ያፈረሰው፤ በአንድ ሰው እና በሌላ ሰው መካከል የነበረውንም ጭምር እንጂ።
ክርስቲያኖች ተቃውሞ እና ስደት ይጋፈጡ ነበር። ነገር ግን መከራው እምነታቸውን አጠነከረው። ስደት ሲበታትናቸው የቤተክርስቲያን ድንበር እየሰፋ ሔደ። የጥንቱ ክርስትና ውስጥ ወንዶችም ሴቶችም ለእምነታቸው ሊሞቱ ፈቃደኛ ስለነበሩ የዚያ ዘመን መለያው የወንጌል ስርጭት የተጧጧፈበት ጊዜ መሆኑ ነበረ።
የጥንት ክርስትና ለቦቅባቆች አይመችም ነበር። ማንም እግዚአብሔር ካልጠራው በቀር ሊተባበራቸው አይደፍርም ነበር። የሚገጥሟቸው ተግዳሮች በጣም ከባድ የኑሮ ዘይቤያቸውም በጣም ጥብቅ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 5፡13 ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፥
እነዚህ የጥንት ቤተክርስቲያኖች ሰው በራሱ ረክቶ ተደላደሎ የሚተኛባቸው ቤተክርስቲያኖች አልነበሩም።
የክርስትና እምነት የተስፋፋው በሰው አቅም ሊታለፉ በማይቻሉ እንግዳ በሆኑ እና አጋጣሚ በሚመስሉ ሁኔታዎች እያለፈ ነው። እግዚአብሔር የራሱን ፈቃድ ይፈጽም ነበር፤ የማንንም ሰው ወይም የድርጅት ድጋፍ ሳይጠይቅ በራሱ ነበር የሚፈጽመው። በንሰሐ የሐጥያት ስርየት ማግኘት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሕዝብ ፊት እየመሰከሩ መጠመቅና ከክርስቶስ ጋር በአደባባይ መሰለፍ በሕይወት መኖር አደገኛ በሆነበት ዘመን ውስጥ መኖር የሰለቻቸው መሞትም የሚያስፈራቸውን ሰዎች በጣም ይስባቸው ነበር። ያለ ሐጥያት የመኖር ፍላጎታቸው እና የተከተሉ ጥብቅ የሥነ ምግባር ሥርዓት እግዚአብሔርን ሲከተሉ በሕሊናቸው እየተመሩ እንዲኖሩ አስቻላቸው። ይህም ውስጣዊ ሰላምን ሰጣቸው።
ጥምቀት ክርስቲያኖችን ከዓለም የሚለይ የአደባባይ እርምጃ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።
ወደ መንግስተ ሰማይ እንገባ ዘንድ ከሐጢያታችን ሊፈታን የሚችለው ብቸኛ ቁልፍ በጴጥሮስ እጅ ነበር። ያም ቁልፍ የንሰሐ ትምሕርት ነው።
ሐጥያታችሁ ይሰረይላችሁ ዘንድ ንሰሐ ግቡ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ታውቁ ዘንድ በውሃ ተጠመቁ። የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ባሕርያቱን የሚገልጡት ብዙ ስሞቹ አሁን ሰው ሆነዋል፤ እኛም ብቸኛው የሚያስፈልገን ሰው በሆነ ጊዜ የተሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለውን ስሙን ማወቅ ነው።
ማቴዎስ 16፡19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ (እኔ ኢየሱስ)፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
ጴጥሮስ ለሙሽራዋ ወደ ሰማይ መግቢያ በር በመክፈት ከሐጥያታችን ፈታን፤ እኛም መግባት የምንችለው ንሰሐ ብንገባ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብንጠመቅ ብቻ ነው። በኢየሱስ ስም መጠመቅን በማስተዋወቅ ጴጥሮስ መጥምቁ ዮሐንስ በንሰሐ ጥምቀት ከፍቶት የነበረውን የሰማይ መግቢያ ቆለፈው። ዮሐንስ ያጠምቅ የነበረው የአዳኙን ስም ከማወቁ በፊት ነበር።
ጥምቀት የሞት፣ የቀብር እና የትንሳኤ ተምሳሌት ነበር። ዮሐንስ በሕይወት ሳለ ኢየሱስ ገና አልሞተም ነበር።
ሮሜ 6፡3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?
4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
5 ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤
ይህን በመሰለ መንገድ ጴጥሮስ ቁልፉን በመጠምዘዝ ከዚያ ጊዜ በኋላ የማይጠቅመውን የዮሐንስን ጥምቀት ዘጋው፤ የዮሐንስ ጥምቀት ጊዜያዊ እርምጃ ነበር።
ለአሕዛብ እንዲያስተምር የተላከው ታላቅ ሐዋርያ ጳውሎስ በመጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ የቤተክርስቲያንን ትምሕርት እያዘጋጀ በነበረ ሰዓት እነዚህን ሁኔታዎች ማስተዋል እጅግ አስፈላጊ ነበር።
ስለዚህ ጳውሎስ የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኖች መሰረት የሆነችዋ የኤፌሶን ቤተክርስቲያን መልእክተኛ እንደመሆኑ ጴጥሮስ ያደረገውን እያጸደቀ የዮሐንስን ጥምቀት በመዝጋት የጴጥሮስን ጥምቀት አጸና።
የሐዋረያት ሥራ 19፡1 አጵሎስም በቆሮንቶስ ሳለ ጳውሎስ በላይኛው አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፥
2 አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ፦ ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት።
3 እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ በዮሐንስ ጥምቀት አሉት።
4 ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው።
5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
እነዚህ በኤፌሶን የነበሩ ደቀ መዛሙርት በዮሐንስ ጥምቀት ተጠምቀዋል። ጳውሎስ ያለምንም ማንገራገር እንዲህ ነበር ያላቸው፡- “ጴጥሮስ በኢየሱስ ስም እንዳጠመቀው ካልተጠመቃችሁ ጥምቀታችሁ ዋጋ የለውም፤ እንደገና በትክክል መጠመቅ አለባችሁ”። እኛ እንድንመለስ የሚያስፈልገን ወደ እንደዚህ አይነቱ የነጳውሎስ ትምሕርት ነው።
ቆላስይስ 3፡17 እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
ጥምቀት አንድን ሰው ከውሃ ሥር የመቅበር ድርጊት ነው፤ በሚቀበርበትም ሰዓት በሚጠመቀው ሰው ላይ የጴጥሮስም ቃላት በሚሰማ ድምጽ ይነገርበታል። ስለዚህ በኢየሱስ ስም ማጥመቅ አስፈላጊ ነው።
ነገር ግን ንሰሐ እና በኢየሱስ ስም መጠመቅ ለሙሽራይቱ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍትላት ቁልፍ በመሆኑ ከፍተኛ የሰይጣን ጥቃት የሚሰነዘረው በዚህ ቁልፍ ላይ ነው። ዳግመኛ ወደ መወለድ የሚመራ፤ ኢየሱስን የግል አዳኝ አድርገው የሚቀበሉበትና ኢየሱስም ግለሰቡን ከሐጢያት መልሶ ሕይወቱን የሚቆጣጠርበት ከልብ የሆነ ንሰሐን የማይሰብኩ ቤተክርስቲያኖች ተነሱ። ከዚያም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ነው በማለት እግዚአብሔር የተጠራበት ሰብዓዊ ስሙ ላይ ሳይቀር ጥቃት ተሰነዘረ። በዚህም የተነሳ የኢየሱስ ስም ከውሃ ጥምቀት ላይ ተወገደ። ወዲያው በጥምቀት ስረዓት ውስጥ በኢየሱስ ስም ቦታ ሶስት የማዕረግ መጠሪያዎች ተተኩ።
ማቴዎስ 28፡18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።
ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው።
ማቴዎስ 28፡19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
ስልጣን ሁሉ ለኢየሱስ ተሰጥቶታል። መማር እንዳለብን ሁለት ጊዜ ተናግሯል። ስለዚህ እዚህ ውስጥ ጥልቅ ሚስጥር አለ ማለት ነው።
በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም (ነጠላ) እያጠመቃችሁዋቸው።
እግዚአብሔር በስብዕና ሦስት ከሆነ የአብ ስም ያህዌ ነው። የወልድ ስም ኢየሱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የለውም። ስለዚህ ሰሦስቱ ሁለት ስም ብቻ አለ። ከዚህም ብሶ ደግሞ ኢየሱስ ለሦስቱ አንድ ስም ብቻ መጠቀም አለብን አለ። ይህ ደግሞ አይቻልም።
“ሥላሴ” “ሦስትነት በአንድነት” “አንድ ህልውና” “አንድ ማንነት” እነዚህ አባባሎች በግሪክ ፍልስፍና ውስጥ እናገኛቸዋለን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኛቸውም።
ስለዚህ ጴጥሮስ የመለኮት ሙላት በክርስቶስ በአካል ተገልጦ እንደሚኖር አስተውሏል።
ቆላስይስ 2፡8 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
አብ ከአይሁድ ሕዝብ በላይ ይኖር የነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። መንፈሱም በክርስቶስ ውስጥ በአካል ኖረ፤ በዚህም አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ።
ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
እግዚአብሔር እንደ አብ ከአይሁድ በላይ ነበረ። ከዚያም ከአይሁድ ጋር በመኖር ወልድ ወይም ልጅ ሆነ ይህም በመሞት የሐጥያትን ዋጋ ለመክፈል ነው።ከዚያ በኋላ ነው በሞት ጊዜ የኢየሱስን አካል ለቆ የሄደው መንፈስ ቅዱስ ከሐጥያታችን ንሰሃ ስንገባ ወደ እኛ መጥቶ በውስጣችን መኖር የቻለው።
ዮሐንስ 14፡17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
ክርስቲያኖች ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ 2፡38 ኢየሱስ በማቴዎስ 28፡19 ከተናገረው ጋር ተጋጭቷል በማለት ታላቅ ስሕተት ሰሩ፤ ከዚያም ኢየሱስ በተናገረው መመራትን መረጡ። ነገር ግን ኢየሱስ ሲናገር ለጥምቀት አንድ ስም መጠቀም እንዳለባቸው እንጂ ሦስት የማዕረግ መጠሪያዎች እንዲጠቀሙ አልነገራቸውም። ስለዚህ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ስም ጠፋባቸው ምክንያቱም በሥላሴነት ለሚያምኑት መለኮት ውስጥ ላሉ ለሦስት ሰዎች የሚሆን አንድ ስም የለም። ደግሞም ጴጥሮስ ለመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ክርስቲያኖች የመንግስተ ሰማያትን ደጅ የከፈተበትን የንሰሃ እና የኢየሱስ ስም ጥምቀት ቁልፍን አንቀበልም ይላሉ። ሐዋርያትን ለማረም መሞከር ያለ አቅም መንጠራራት ነው። ወደ እነርሱ ትምሕርት ብንመለስ ይሻለናል።
አብ እና መንፈስ ቅዱስ አልሞቱልንም። አልተቀበሩም -- መንፈስን እንዴት አድርጋችሁ ትቀብራላችሁ? -- ደግሞም ከሞትም አልተነሱም። ስለዚህ ጥምቀት ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ምክንያቱም ጥምቀት የሚያያዘው ከኢየሱስ ሞት፣ ቀብር እና ትንሳኤ ጋር ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ ሙላት በክርስቶስ ውስጥ ነበረ ከዚያም ሲሞት ደግሞ ተለየው። የሞተው እና የተቀበረው የኢየሱስ ሥጋ ወይም አስከሬን ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ነው። ኢየሱስ እንደ እኛ እንደ ሰው ሞተ። ሮሜ 6፡3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?
የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በዋነኝነት አይሁድ ነበሩ፤ ስለዚህ ክርስቲያኖች በመጀመሪያ አይሁድ ነበሩ። በ50 ዓ.ም. ክሎዲየስ የተባለ የሮም ንጉስ አይዶችን ከሮም ሲያባርራቸው ክርስቲያኖችም አብረው ተባረሩ። ይህም የማንም ተቃውሞ ወይም ትችት የሌለበት አማራጭ የሆነ የሮማ ካቶሊካዊ ክርስትና ጽንሰ ሃሳብ እንዲመጣ በር ከፈተ። በ54 ዓ.ም. ክሎዲየስ ሲሞት ተባርረው የነበሩት ክርስቲያኖች እንዲመለሱ በተፈቀደላቸው ጊዜ ሁለት የክርስትና ቅርንጫፎች ነበሩ። አንደኛው ጳውሎስ ያስተማረውን የሐዋርያት ትምሕርት የሚከተል ሲሆን ሌላኛው ቅርንጫፍ ደግሞ የወንጌሉን ቅርጽ በመለወጥ የሮማ ካቶሊካዊ እምነት ያደረገ ነበረ። ሮም ውስጥ የገነነውም ይኸኛው ቅርንጫፍ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 18፡1 ከዚህም በኋላ ጳውሎስ ከአቴና ወጥቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ።
2 በወገኑም የጳንጦስ ሰው የሚሆን አቂላ የሚሉትን አንድ አይሁዳዊ አገኘ፤ እርሱም ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ መጥቶ ነበር፥ አይሁድ ከሮሜ ይወጡ ዘንድ ቀላውዴዎስ አዞ ነበርና፤ ወደ እነርሱ ቀረበ፥
ንጉስ ኔሮ በ64 ዓ.ም. እና በሞተበት በ68 ዓ.ም. መካከል በሮም ከተማ ውስጥ በተነሳው ታላቅ እሳት ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖችን በጭካኔ ማሳደድና መግደል ጀመረ። ኔሮ በሞተበት ሰዓት ብዙዎቹ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ወይ ሞተዋል ወይ ደግሞ ከሮማ ግዛት ድንበር ርቀው ሄደዋል።
ኔሮ አሰቃቂ ስደት ባስነሳበት ወቅት በ66 ዓ.ም. ጄነራል ቬስፓሲያንን ኢየሩሳሌምን እንዲቆጣጠር ላከው፤ ይህም ሐዋርያው ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ከተገደለ ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው። በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች ሸሹ። የጥንት ክርስቲያን ታሪክ ጸሃፊዎች እንደሚሉት አንዳንዶቹ በቅርበት ወዳለችው ፔላ ወደምትባለው ከተማ ሄዱ። በኢየሩሳሌም ላይ በ70 ዓ.ም የመጣው የመጨረሻው ውድመት በሮም ካለችው ቤተክርስቲያን በልጣ ትታይ የነበረችውን የኢየሩሳሌምን ቤተክርስቲያን ከምድረ ገጽ አጠፋት። ስለዚህ ሰዎች ተነስተው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ውጭ ሌላ ትምሕርት ለማስተማር እና ብዙዎችን ቀስ በቀስ ለማሳት እድል አገኙ።
ስደት የጥንቷን ቤተክርስቲያን አንድ አድርጓት ነበር። እነርሱም ወኅኒ እንዳይገቡ በድብቅ ያመልኩ ነበር። በግልጽ በአደባባይ መንቀሳቀስ አስጊ ነበር።
የጥንት ቤተክርስቲያኖች የግለሰቦች መኖሪያ የነበሩ ሲሆን ጉባኤው በቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ብቻ ቤቶቹ ውስጣቸው ትንሽ ለውጥ ይደረግበት ነበር።
ቤተክርስቲያኖች በከተማ ውስጥ በቀላሉ ተለይተው የሚታወቁ ሕንጻዎች የሆኑት ለመጀመሪያ ጊዜ በ312 ዓ.ም ነው። ይህም የሆነው ንጉስ ኮንስታንቲን የክርስቲያኖችን ስደት ባስቆመ ጊዜ ነው።
CHURCH AGE BOOK - EPHESIAN CHURCH AGE
ማድረግ የሚያስፈልጋችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል የተንቀሳቀሰበትን ጊዜ ማስታወስ ብቻ ነው… የዚያን ጊዜ ክርስቲያኖች … በቤቶች ውስጥ ነው ያመለኩት ወይም በአሮጌ መጋዘኖች ውስጥ። እነርሱም እውነተኛውን ሕይወት አጣጥመውታል። ነገር ግን የሚያማማሩ ሕንጻዎችን ለመስራት በቂ ገንዘብ ያገኙት ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው… ። ከዚያ በኋላ በሰው የሚመራ እንቅስቃሴ ተጀመረ።
የክርስትና እንቅስቃሴ በግለሰቦች ቤት ውስጥ በደስታ ተጀመረ። የአዲስ ኪዳን ዘመን ሲጀመር “የቤተክርስቲያን” ሕንጻዎች አስፈላጊ አልነበሩም። ሰዎችን በቤተክርስቲያን ሕንጻ ውስጥ ሰብስቦ ማደራጀት አንድ ሰው መሪ እንዲሆን እና ሰው ሰራሽ ሕጎች እና እምነቶች እንዲሰለጥኑ በር ይከፍታል። ሰይጣን ይህንን ዘዴ ሁል ጊዜ ይጠቀምበታል በተለይም በዚህ ዘመን። ሰይጣን በጣም ንቁ ያልሆኑ ሰዎች የማያስተውሉትን ለውጥ ትንሽ በትንሽ እና ቀስ በቀስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያመጣል።
የመጀመሪያዋን የቤተክርስቲያን ዘመን የምትወክለውንና የቀጣይ የቤተክርስቲያን ዘመናት መሰረት የሆነችውን የኤፌሶንን ቤተክርስቲያን ለመመስረት ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች ወደ ሚሊጢን ከተማ ሰበሰባቸው። ሚሊጢን በዚያ አካባቢ እንደ ዘመናዊ ከተሞች በዘጠና ዲግሪ የሚታጠፉ እና እርስ በርሳቸውን የሚያቋርጡ መንገዶች በብሉ ፕሪንት የተሰሩበት የመጀመሪያ ከተማ ነው። ስለዚህ ይህ ከተማ ለጳውሎስ የኤፌሶንን የቤተክርስቲያን ዘመን እና የቀጣዮቹን የቤተክርስቲያን ዘመናት ለመምራት የሚሆን ብሉ ፕሪንት ለማዘጋጀት ሁነኛ ቦታ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡27 የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።
28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
ሰዎች መሪ ለመሆን ቀስ በቀስ ይጀምራሉ፤ -- ከዚያም የሽማግሌዎች ሕብረት ሳይሆን አንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ ይሆንና “ተከተሉኝ” ይላል ።
ከስትሮንግስ ኮንኮርዳንስ፡-
“overseer” በግሪክ ኤጲስቆጶስ ሲሆን ተቆጣጣሪ ማለት ነው።
ስለዚህ ሽማግሌዎች የቤተክርስቲያን ኤጲስቆጶሳት እና ተቆጣጣሪዎች ናቸው።
ከስትሮንግስ ኮንኮርዳንስ፡-
“presbuterion” ፕሬስቢተሪዮን የሽማግሌዎች ሕብረት ማለት ነው።
ስለዚህ ፕሬስቢተር፣ ተቆጣጣሪ፣ ኤጲስቆጶስ እነዚህ ቃላት አንዱ በሌላው ቦታ ተተክተው ያገለግላሉ።ፊልጵስዩስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
በፊልጵስዩስ ከተማ ብዙ ኤጲስቆጶሳት ነበሩ። እነዚህም ሰዎች በዚያ ያለችው ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ወይም ተቆጣጣሪዎች ነበሩ።
የሽማግሌዎች ሕብረት መንጋውን ማብላት እንዳለባቸው ጴጥሮስም አረጋግጧል። ጴጥሮስ ራሱን ሐዋርያ ከማለት ይልቅ ሽማግሌ ነው የሚለው።
ለራሱ ታላቅ የአገልግሎት ቦታ ወይም ማዕረግ አልፈለገም። ጴጥሮስ ትኩረት ያደረገው በመሪነት ውስጥ ባለው እኩልነት እንጂ አንድ ሰው በሌሎች ላይ ከፍ በማለቱ አይደለም፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን አንድን ካሕን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጋ ስትሾም ደግሞም ጳጳስን የካሕናት ራስ ስታደርግ ያሰበችው አንድን ሰው ከሌሎች በላይ ከፍ ማድረግ ነው። ይህም የኒቆላውያን ትምሕርት ነው - ማለትም አንድን ቅዱስ ሰው ከሕዝብ በላይ ከፍ ማድረግ።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ጴጥሮስ አሥራት የፓስተሩ ነው አላለም።
ጳውሎስ የትኞቹ አገልግሎቶች ቤተክርስቲያንን መምራት እንዳለባቸው የጻፈውን ተመልከቱ።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
ሦስት አገልግሎቶች ብቻ ናቸው የተጠቀሱት። ሐዋርያት እውነትን መሰረቱ ስለዚህ የእነርሱ አገልግሎት ከሁሉም የሚበልጠው አገልግሎት ነው። ትምሕርቶቻቸውም አነርሱ ከመሞታቸው በፊት በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ተጻፉ። አዲስ ኪዳንን ስናነብ ከሐዋርያት ጋር በቀጥታ እየተማከርን ነው።
እግዚአብሔር ለነብይ በቀጥታ ይናገራል፤ ግን ነብይ በሁለተኛ ደረጃ ነው የሚመጣው ምክንያቱም ነብይ ትምሕርት ቢያስተምር ሐዋርያቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ ጻፉት ብቻ ነው የሚመልሰን። ነብይ እንደተጻፈው ቃል መናገር አለበት።
አስተማሪዎች ሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው ያሉት። አስተማሪው መገለጡን የሚያገኘው ከነብይ ነው፤ ከዚያም ይህንን መገለጥ ሐዋርያት ከጻፉት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማመሳከር ማረጋገጥ አለበት። አስተማሪም ይሁን ነብይ ሐዋርያት የጻፉትን መቃረን አይችልም። ልብ በሉ፡- ጳውሎስ እዚህጋ ፓስተሮችን ጭራሽም አይጠቅስም።
የሐዋርያት ሥራ 15፡6 ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።
ይህ ዘዴ ሁሌ መቀጠል ነበረበት። ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጽፈው ያስቀመጡት እስከ ዛሬም ድረስ በእጃችን አለ። ስለዚህ ዛሬ የአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ሐዋርያት የጻፉትን አዲስ ኪዳን ቢያነቡ እራሳቸውን ሐዋርያትን አግኝተው ከማናገር ጋር እኩል ነው።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ የትም ቦታ ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ተብሎ አልጠራም።
ፓሰተር የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ እርሱም ከአምስቱ አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ ሆኖ። ስለዚህ ፓስተር ቤተክርስቲያንን እንዲገዛ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስልጣን አልተሰጠውም። ፓስተር የተለያዩ አይነት ሰባኪዎች ቡድን አባል ነው፤ ይህም ቡድን ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩዋት የሽማግሌዎች ሕብረት ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።
ስለዚህ ሽማግሌዎች ሁሉ ሰባኪዎች አይደሉም። ነገር ግን ሽማግሌዎች ሁሉ እኩል ናቸው። ጴጥሮስ ሐዋርያ ሆኖ ሳለ ለሽማግሌዎች መልዕክት ሲጽፍ ራሱን ሽማግሌ ብሎ ነው የጠራው። የአምስቱ አገልግሎቶች አካል ያልሆነ ሽማግሌ ባይሆንም እንኳ ለጉባኤው ጠቃሚ ምክር መስጠት ይችላል።
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡13 እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ።
እዚህ ቃል ውስጥ ምክር ከትምሕርት የሚለይ ይመስላል፤ በዚህም ምክንያት ለምሳሌ የማበረታቻ ንግግር ብቻ ይመስላል። ማንኛውም ሽማግሌ ሰባኪ ባይሆንም እንኳ መምከርና ማበረታታት ይችላል።
ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር የሽማግሌዎች ሕብረት እያንዳንዱን አጥቢያ ቤተክርስቲያን እንዲቆጣጠሩ እና እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ለሐዋርያት ትምሕርት ታማኝ ሆነው ይቀጥሉ ዘንድ እንዲጠብቋቸው ፈለገ። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጳጳስ የሚለው ስም እንደ ቤተክርስቲያን መሪ አብዝቶ መጠቀስ ጀመረ።
የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት ሐዋርያት ከሞቱ ከሁለት ትውልዶች እንኳ ሳያልፉ እንዴት እንደሆነ በግልጽ ባልታወቀ መንገድ ጳጳስ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ብቅ አለ። የአሕዛብ መቅደሶች ሁሉ አንድ መሪ ወይም ካሕን አላቸው እርሱም የጉባኤው ራስ ነው። ክርስቲያኖች ቀስ በቀስ ይህን የአሕዛብ አርአያነት መከተል ጀመሩ። አንጾኪያ በቤተክርስቲያን ታሪኳ ትልቅ ሥፍራ ያላት ሃገር ነበረች። በ117 ዓ.ም. አካባቢ የሞተው የአንጾኪያው ኢግናሺየስ የአንጾኪያ ጳጳስ ነኝ አለ፤ ደግሞም የአንድ ከተማ ጳጳስ በምድር ላይ የእግዚአብሔር ተወካይ ነው ስለዚህ “እንደ ራሱ እንደ ጌታ ማየት አለብን” አለ።
ጳጳስ በከተማ ውስጥ የአንድ ቤተክርስቲያን ራስ መሆኑ የክርስቲያኖችን ቀልብ የሳበ አዲስ ሐሳብ ነበር። ይህንንም መንገድ ብዙሃኑ ተከተሉት። እንደዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በማይደግፈው መንገድ ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ ይሆን ዘንድ ከፍ ማድረግ፤ ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ መሾም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ እንዲሁም ከዚያ በኋላ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ማወዳደር ሙሉ በሙሉ ስሕተት ነው። ክርስቲያኖች ስሕተትን ለመዋጋት ይህ ከሁሉ የተሻለ መንገድ መስሎዋቸው የኒቆላውያንን ትምሕርት ያበረታቱ ነበር፤ የኒቆላውያን ትምሕርት አንድን ቅዱስ ሰው ከቤተክርስቲያን በላይ ከፍ ማድረግ ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጳጳሳት ከሽማግሌዎች በላይ እንደሆኑ ተቆጠረ። በሕዝቡ እና በእግዚአብሔር መካከል የሚቆም የአሮን አይነት ክሕነት ተጀመረ። ቤተክርስቲያን በጣም ቸልተኛ ከመሆኗ የተነሳ ይህንን ስሕተት ትኩረት ሰጥታ በጊዜው አልቀረፈችውም።
ክርስቲያኖች ሐዋርያት ባስተማሩት ትምሕርት መሰረት የእምነታቸውን ዝርዝር ጉዳዮች አጥብቀው ከመያዝ ግድ የለሽ ሆነው ተዘናጉ። በሰው መሪነት ላይ የሚደረገው ትኩረት ቀስ ቀስ እያለ ነው ሾልኮ የገባው። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቤተክርስቲያናት የሐዋርያትን ትምሕርት ሲረሱ (ወይም እውነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው ለማግኘት በጣም ሲሰንፉ) ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ለመቀበል ፈቀዱ። ዛሬም እንደዚሁ ነው።
ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ጊዜ ኤጲስቆጶስ መምረጥ ሊከብድ ይችላል። የሮሙ ፋቢያን የተመረጠው አናቱ ላይ እርግብ ስላረፈችበት ነበር።
ቤተክርስቲያንም ይህ የመንፈስ ቅዱስ ምርጫ መሰላት።
ነገር ግን የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን በ170 ዓ.ም. አካባቢ ሲጠናቀቅ በከተማ ውስጥ ላሉ ቤተክርስቲያኖች ጳጳሳት ራስ መሆናቸው የተለመደ አሰራር ነበረ። ሽማግሌዎች በማዕረግ ከጳጳሱ እንደሚያንሱ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር። ሽማግሌዎች ተፈላጊነታቸውን እያጡ ሄዱ። የቤተክርስቲያን አመራር በማዕረግና በስልጣን እና በሰዎች የስልጣን ጥማት ተያዘ።
ቤተክርስቲያን ልክ እንደ ሮማ መንግስት ራስዋን ዓለም አቀፍ ድርጅት አድርጋ ቆጠረች።
ቤተክርስቲያን የእድገት አቅጣጫዋን አካባቢዋና በዙሪያዋ ያሉ ሁኔታዎች እንዲወስኑላት ፈቀደች። ለማሕበራዊ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ድርጅት ሆነች። ቤተክርስቲያን ኢየሱስን የሚወድዱ ግለሰቦች ስብስብ ጥምቀት፣ የጌታ እራት፣ እግር መተጣጠብ እና በቃሉ ላይ ያለቸው እምነት ብቻ አንድ ያደረጋቸው ሰዎች ሕብረት መሆኗ ቀርቶ በሰዎች ትዕዛዝ የምትንቀሳቀስ ድርጅት ሆነች።
ሮማውያን በአስተዳደር የተካኑ ሰዎች ናቸው፤ ስለዚህ ማንኛውም ድርጅት እነሱ ባበጁት ቀልጣፋ የአስተዳደር ስርዓት ውስጥ ገባ።
ቤተክርስቲያንም ለምሳሌ ድሆችን በማብላት ና በሌሎች ተግባራዊና ድርጅታዊ አሰራሯ ሮማዊ እየሆነች መጣች።
የተለያዩ ቦታዎችና የተለያዩ ባህሎች አንድ አይነት እንዲሆኑ ተደረገ። ስለዚህ ይህን የአሰራርና የፖሊሲ አንድነት ለማስጠበቅ ሲባል በሕብረቶች መካከል የሚመላለሱ ባለስልጣኖች ተመደቡ።
በ170 ዓ.ም. እያንዳንዱ ሕብረተሰብ የተወሰነ ስልጣን ባላቸው ሹሞች ሲሆን ከእነዚህ በላይ ደግሞ አንድ ጳጳስ ይሾማል፤ ይህም ጳጳስ ማሕበረሰቡን ይወክላል። ማሕበረሰቦቹ በሙሉ የአንድ ሕዋአቀፍ ወይም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነበሩ (ቤተክርስቲያን ካቶሊክ ተብላ የተጠራቸው ለመጀመሪያ ጊዜ “ካቶሊክ” የሚለውን ቃል በተጠቀመው ኢግናሺየስ በተባለ ሰው ነበር)። የጳጳሳት መማክርት ጉባኤ ተሰብስቦ በመወያየት የብዙ ማሕበረሰቦችን አመለካከት ይነጋገሩበታል፤ ውሳኔም ያስተላልፋሉ። ቀስ በቀስ የዚህ መማክርት ጉባኤ ውሳኔዎች ከእግዚአብሔር ቃል ፈቀቅ ማለት ጀመሩ።
ጳጳሶቹ የተለያዩትን ቦታዎች የሚመሩ ራሶች ስለሆኑ የተለያዩ አካባቢዎች እምነታቸው ተመሳሳይ ሊሆን ችሏል። ወዲያው ጳጳሶቹ ከመንግስት ጋር እንደሚታገል ፓርቲ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኑ።
በቤተክርስቲያኖች መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳይቋረጥ ተግተው የሚሰሩት ሹሞች የአንድነት አስጠባቂ በመሆን በጣም አስፈላጊ ሰዎች ሆኑ፤ ከዚያም እንደ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ራስነት አስፈላጊ ሰዎች ሆኑ።
እነዚህ ሰዎች በተጨማሪ ሮም ዓለምን በሙሉ የምታስተዳድርበትን አደረጃጀት አስተዋሉና ቤተክርስቲያንም የሮማን ግዛትን ልታስተዳድርና ተልዕኮዋን ልትፈጽም የምትችልበት ዘዴ ጥብቅ ሕግና ሥርዓትን በማስፈጸም መሆኑን ተረዱ። ጠበቅ ያለ ድርጅታዊ መሪ እና ተቆጣጣሪ በሌለበት “ኑፋቄ” ሊያሸንፍ የሚችልበት ትልቅ አደጋ ነበረ።
ይህ የሰው ጥበብ ያመጣው ውድቀት ነው። በእርሻ ውስጥ ሁልጊዜ በሰብል መካከል እንደማይጠፋ የሆነውን ኑፋቄን ወይም የአስተምህሮ ስሕተትን ለመዋጋት ብላ ቤተክርስቲያን ራሷ ሌላ ትልቅ ስሕተት ይዛ መጣች፤ ይህም ስሕተት የኒቆላውያን ትምሕርት ወይም ሰውን መሪ ማድረግ ነው።
ይህ አሰራር ተመስርቶ ከጸና በኋላ እና ብዙ ቅን ክርስቲያኖችም ቤተክርስቲያንን ለመምራት ጳጳስ ያስፈልጋል ብለው ካመኑ በኋላ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የቤተክርስቲያን አደረጃጀት ተጨማሪ የአስተምሕሮ ስሕተቶች ቤተክርስቲያንን እንዲቆጣጠሩዋት በር ከፈተ። የመጀመሪያው የሐዋርያት ብርሃንም እየደበዘዘ ሄደ።
መጽሐፍ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ራስ ብሎ የሚጠቅሰው ማንን ነው?
ኤፌሶን 5፡22 ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤
23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
24 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።
SEVEN CHURCH AGES BOOK CHAPTER 5 PERGAMOS AGE DOCTRINE OF NICOLAITANES
በኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ኒቆላውያን የሚል ቃል መጥቀሴንና ከሁለት የግሪክ ቃላት የተመሰረተ ቃል መሆኑን መጥቀሴን ታስታውሳላችሁ፡- ኒቃዎ ማለት መግዛት ሲሆን ላዎ ማለት ደግሞ ምዕመናን ማለት ነው።
ስለዚህ ኒቆላውያን ማለት “ምዕመናንን መግዛት” ማት ነው።
ይህ ክፋቱ ምንድነው? ይህ አሰራር ክፉ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን በተመረጡና በፖለቲካዊ አስተሳሰብ ተሞልተው በሚንቀሳቀሱ መሪዎች እጅ አሳልፎ አልሰጠም። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን አደራ የሰጠው በእግዚአብሔር ለተመረጡ፣ በመንፈስ ለተሞሉ በቃሉ እየኖሩ ሕዝቡን ቃል ለሚመግቡ ሰዎች ነው።
እግዚአብሔር ብዙሃኑ በጥቂት ቅዱሳን ካሕናት ይመሩ ዘንድ ሕዝቡን በሁለት መደብ ለያይቶ አላስቀመጠም።
መሪዎች በእርግጥ ቅዱስ መሆን ያስፈልጋቸዋል፤ ግን ደግሞ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ መላው ጉባኤ ቅዱሳን መሆን አለባቸው።
ከዚህም በተጨማሪ ቃሉ ውስጥ አንድም ቦታ ካሕናት፣ አገልጋዮች ወይም እንደ እነርሱ ያሉ ሰዎች በሰዎች እና በእግዚአብሔር መካከል እንደሚቆሙ ወይም ሰዎች እግዚአብሔርን ሲያመልኩ ከእግዚአብሔር ጋር ተራርቀው እንደሚለያዩ የተጻፈ የለም። እግዚአብሔር ሁሉም እንዲወዱትና አብረው እንዲያመልኩት ነው የሚፈልገው።
የኒቆላውያን ትምሕርት ይህንን ጽንሰ ሃሳብ አጥፍቶ በቦታው አገልጋዮችን ከሕዝቡ በማለያየት መሪዎችን በአገልጋይ ፈንታ የሕዝቡ ጌታ ያደርጋቸዋል።
ይህ ትምሕርት በመጀመሪያው ዘመን ውስጥ እንደ አደራረግ ነው የተጀመረው። ችግሩ በሁለት ቃላት ውስጥ ያለ ይመስላል፡ “ሽማግሌዎች” (ፕሬስቢተርስ) እና “ተቆጣጣሪዎች” (ቢሸፕስ)። መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሽማግሌዎች መኖራቸውን ቢያሳይም አንዳንዶች ግን (ኢግናሺየስ ከእነርሱ መካከል አለበት) ጳጳስነት ከሌሎቹ ሁሉ የላቀ መሆኑን ወይም ከፍ ያለ ስልጣን እና የሽማግሌዎች ተቆጣጣሪ እንደሆነ ማስተማር ጀመሩ።
እውነቱ ግን ምን መሰላችሁ፡- “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ግለሰቡን የሚወክል ሲሆን “ጳጳስ” ግን የዚህኑ ሰው ሥራውን ያመለክታል። ሽማግሌ ሰውየው ነው፤ ጳጳስ ደግሞ ሥራው ነው። “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ሁልጊዜም የሚያመለክተው ሰው በጌታ ሆኖ ያሳለፋቸውን ዓመታት እንጂ መመረጡን ወይም መሾሙን ወዘተ… አይደለም፤ በጌታ መሸምገሉን እንጂ። ምራቁን የዋጠ፣ የበሰለ፣ የተማረ እንጂ ጀማሪ ወይም አዲስ ያልሆነ በልምዱ እና በረጅም ጊዜ አቋሙ የተነሳ አስተማማኝ መሆኑን ያስመሰከረ ሰው ነው።
… ነገር ግን ጳጳሳቱ ጳውሎስ የጻፈውን መልዕክት መከተል አልፈለጉም፤ በዚያ ፈንታ በሐዋትያት ሥራ 20 ጳውሎስ ሽማግሌዎችን ከኤፌሶን ወደ ሚሊጢን የጠራበትን ታሪክ አነበቡ። ቁጥር 17 ላይ ቃሉ “ሽማግሌዎች” ተጠሩ ይልና ቁጥር 28 ላይ ደግሞ “ጳጳሳት” (ተቆጣጣሪዎች) ይላቸዋል። እነዚህ ጳጳሳት ግን (ፖለቲከኞች እና የስልጣን ጥመኞች መሆናቸው ግልጽ ነው) ጳውሎስ “ተቆጣጣሪዎች” ሲል ለአንድ ለሚያገለግሉባት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ ሃላፊነት የተሰጣቸው ለማለት አይደለም ብለው መከራከር ጀመሩ።
ለእነርሱ ጳጳስ ማለት ከአንድ ቤተክርስቲያን አልፎ የብዙ አጥቢያዎች ተቆጣጣሪ ነው የሚል ሰፋ ያለ ትርጉም ያለው ቃል ሆነ። ይህ አይነቱ ትርጓሜ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ ታሪካዊ መነሻ የለውም፤ የሚገርመው ግን ፖሊካርፕን እንኳ የሚያህል አቋም ያለው ሰው እንኳ ሳይቀር በዚህ ትርጓሜ ተስቧል።
ሲደራጁ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ቃል ይለያሉ፤ በዚህም ራሳቸውን መንፈሳዊ ግልሙትና ውስጥ ይከታሉ።
PERGAMEAN CHURCH.AGE - CHURCH.AGE.BOOK CPT.5
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በእያንዳንዱ ዘመን የሆነው ይኸው ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን ነጻ ያወጣል። እነርሱም በደሙ ታጥበው ይወጣሉ፤ በቃሉ ይቀደሳሉ፤ በጥምቀት ውሃ ውስጥ ያልፋሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላሉ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የመጀመሪያው ፍቅር ይቀዘቅዛል፤ ከዚያም የሆነ ሰው መደራጀት እንዳለባቸው እና እንዳይበታተኑ ለራሳቸው ስም ማስጠራት እንዳለባቸው ያስባል። እነርሱም በሁለተኛው ትውልድ አንዳንዴ ከዚያም በፊት ፈጥነው ራሳቸውን ያደራጃሉ። ከዚያ በኋላ የአምልኮ መልክ ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣቸው የላቸውም። ሙት ናቸው። ራሳቸውን ከሐይማኖታዊ አቋም እና ከውጫዊ ስርዓት ጋር አዳቅለዋል እንጂ በውስጣቸው ሕይወት የለም።
ራዕይ 2፡1 በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦
ጳውሎስ ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን ዋነኛው መልዓክ ወይም መልዕክተኛ ነው። ነገር ግን በዚህ ታላቅ ኮከብ ብዙ ከመደነቃችን በፊት ኢየሱስ ሌሎችም ስድስት ከዋክብት መኖራቸውን ያስታውሰናል፤ እነዚህ ሰባት ታላላቅ ሰዎች ሁላቸውም ታላቅ ኃይል እና ተጽእኖ ሊኖራቸው የቻለው በኢየሱስ ኃያል ቀኝ እጅ ውስጥ ስለተያዙ ብቻ ነው።
ማቴዎስ 26፡64 ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።
የቤተክርስቲያን ዘመን መልዕክተኛ ታላቅ ቢሆንም (ሁሉም ደግሞ ታላላቅ ነበሩ) ከኢየሱስ ጋር ሲወዳደሩ በእጁ ውስጥ ያሉ ከዋክብት ብቻ ናቸው። ስለዚህ እርሱ ከሁላቸውም እጅግ በጣም ይበልጣል። ከከዋክብት ሁሉ ደማቅ የሆነው ኮከብ ፀሃይ ስትወጣ ይደበዝዛል። ከከዋክብት ሁሉ ደማቅ የሆነው ኮከብ ወይም መልዕክተኛ በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ፊት ይደበዝዛል። የጽድቅ ፀሃይ የሆነው ኢየሱስ በሕዝቡ ልብ ውስጥ ሲበራ የእግዚአብሔር ቃል ብቻውን በውስጣቸው ደማቅ ብርሃን ይሆናል።
ሚልክያስ 4፡2 ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።
ዮሐንስ ሁለቱን ደቀመዛሙርቱን ወደ ኢየሱስ እንዳመለከታቸው ስለዚህ መልዕክተኞች ሁሉ ማድረግ የሚችሉት ሰዎችን ወደተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ማመልከት ነው።
ዮሐንስ 1፡35 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥
36 ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።
37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
ከሁሉም የሚለየው መልዕክተኛ ጳውሎስ ብቻ ነው ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲጽፍ ሃላፊነት ስለተሰጠው ነው። ደግሞ ማንም ጳውሎስን ለመቃረን መነሳት የለበትም።
ገላትያ 1፡8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
10 ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።
ጳውሎስ ማንንም ሰው ወይም መሪ ለማስደሰት አልሞከረም። እርሱ የእግዚአብሔርን ቃል ይጽፋል እንጂ ከዛ ውጭ ምንም አያውቅም።
በመቅረዞቹ መካከል ሲራመድ የሚታየው ኢየሱስ ብቻ ነው። አንድም ሰው በመቅረዞቹ መካከል አይታይም።
እያንዳንዱ መልእክተኛ በተጠራበት ዘመን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። ኢየሱስ ደግሞ በሰባቱም ዘመናት ውስጥ አለ። ስለዚህ እያንዳንዱ መልእክተኛ ወይም ኮከብ ወደ ኢየሱስ እንዲያመለክት ሃላፊነት ተሰጥቶታል ምክንያቱም በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ክርስቲያኖችን አጽንቶ የሚጠብቀው ኢየሱስ ብቻ ነው።
መልእክተኛ ወደ መዳረሻው የሚያመለክት ጠቋሚ ነው። መዳረሻው ኢየሱስ ነው፤ እርሱም የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ከኢየሱስ ጋር በጌትነቱ እና በአዳኝነቱ በግል ያለህ ልምምድ፣ እንዲሁም የተጻፈውን ቃል የምታምንበትና የምትከተልበት የመሰጠት መጠን የወደፊት መንፈሳዊ ሕይወትህን ይወስነዋል። መንፈሳዊ ሕይወትህ ልምላሜው አባል በሆንክበት ቤተክርስቲያን አይወሰንም።
ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
በቤተክርስቲያን ውስጥ የቡድን መዳን የለም። መዳን በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል ብቻ ያለ የግል ጉዳይ ነው። ይህ ቃል ሰዎች በስንፍና እና በቸልተኛነት ተደላድለው ስለመቀመጣቸው አይናገርም።
ሮሜ 14፡12 እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
ቤተክርስቲያንህ ልትደግፍህ ወይም እንቅፋት ልትሆንብህ ትችላለች፤ ልታድንህ ግን አትችልም። ለሕይወትህና ለእምነትህ በእግዚአብሔር ፊት ብቻህን ነው መልስ የምትሰጠው። እርሱም የሚፈርድብህ በቃሉ እንጂ ከአንድ ሰው አንደበት በተወሰደ ጥቅስ አይደለም።
ዮሐንስ 12፡48 የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።
በርትቶ መስራት የጥንቷ ቤተክርስቲያን መታወቂያዋ ነበረ።
የሐዋርያት ሥራ 17፡10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤
11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
የሰሙትን ሁሉ አንድ በአንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ይፈትኑ ነበር። እንደዚህ አይነቱን አማኝ አንድ ስህተት አልፎት ሊሄድ አይችልም። እነርሱ አንድንም ሰው እንኳ አላመኑም፤ ከዚያ ይልቅ የተባለውን ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አመካኝነት ይመዝኑ ነበር።
ራዕይ 2፡2 ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
ቤተክርስቲያን በጥሩ አጀማመር ተነሳች። እነርሱም የሚያስከፍላቸውን ዋጋ ሳይተምኑ በደስታ ዘለው ገቡ። ከባድ ሥራ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች አላስፈሩዋቸውም። ወንጌልን ለማሰራጨት ለፉ፤ ስደትና መከራ ድካማቸውን ከንቱ ሲያደርግባቸውም በትዕግስት ያሳልፉ ነበር። ለአንበሳ ተጥለው ዘግናኝ አሟሟት ሊሞቱ ሲጠባበቁ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር በመዘመር አሕዛብን አስገርመዋል፤ አንበሳ ሲቦጫጭቃቸው በስቃይ በሚጮሁት ጩኸት መዝሙራቸው ቢቋረጥም ሰው መሆናቸውን ብቻ ነው የሚመሰክረው። እነዚህ ሰዎች ተራ ሰዎች ናቸው ግን ነፍሳቸውን በስቃይ እስኪሰዉለት ድረስ ውድ የሆነ ነገር አግኝተዋል። አሕዛብም ከክርስቲያኖቹ ጋር ሲነጻጸሩ ከራሳቸው ሃሰተኛ አማልክት ጋር ያላቸው ቁርኝት ምንም ጥልቀት እንደሌለው ራሳቸውን ታዝበዋል። በዚህም መስዋእትነት እነዚህ ሰማዕታት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስቶስ መልሰዋል።
ልፋት የሚለው ቃል በጫና ውስጥ ሆኖ ብዙ መድከምን ያሳስባል። እነርሱ የሐዋርያት ትምሕርት እንዳይበረዝ ለመጠበቅ ብዙ ለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ ለእነርሱ የመጨረሻ የእውነት መመዘኛ ነው። ነገር ግን በዙሪያቸው ሁሉ ከተጻፈው ቃል የሚያፈነግጥ የራሳቸው የግል አመለካከት የሚመስጣቸው ሰዎች ነበሩ። ይህም ከሁለት አማራጮች አንዱን የመቀበል ጉዳይ ነው፡ ሰዎች ከፍ ያደረጉት አንድ መሪ የተናገረውን ቃ ለመቀበል መምረጥ ወይ ደግሞ የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ ለመጽናት መምረጥ።
በመጀመሪያ ክርስቲያኖች በጣም ጽኑ አቋም ነበራቸው። ሐዋርያት የተናገሩትን ብቻ ነበር የሚያምኑት። እነዚህም የሐዋርያት ትምሕርቶች ተሰባስበው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሆኑ። ሐዋርያት ሰሞቱ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ማመን ቀጠሉ። ማንኛውም መሪ በአዲስ ኪዳን ከተጻፈው ውጭ ሌላ ነገር ቢናገር በቀላሉ ውሸታም ይሉታል።
ስደት በታተናቸው ነገር ግን በየደረሱበት ሐዋርያት የጻፉትን ያስተምሩ ነበር። ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል ተሰራጨ፤ ሰዎችም ከኢየሱስ ጋር ጠለቅ ያለ ሕብረት ውስጥ ስለገቡ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ ሆነ። የጥንት ሰባኪዎች ጠንቃቃ መሆን ግዴታቸው ነበር ሐዋርያት የተናገሩትን ከተናገርክ በመልካም ይቀበሉሃል። አንዳች ልዩ ነገር ከተናገርክ ውሸታም ነበር የሚሉህ። በሁለቱ መካከል አንዳችም አልነበረም።
ለጥንት ክርስቲያኖች ዋነኛ ፍቅራቸው ኢየሱስ ሲሆን ቃሉ ደግሞ የመጨረሻ የእውነት መመዘኛቸው ነበረ። እንደ ሙሽራ ለባላቸው ሙሉ በሙሉ ይገዙ ነበር። ከኢየሱስ በቀር የማንም ቃል አይሰሙም ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተጻፈው ለእያንዳንዱ ቃል ታላቅ አክብሮት ነበራቸው። ምክንያቱ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ እራሱ በጽሑፍ መልክ ነው።
ኤፌሶን 5፡31 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
33 ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሰዎችን የመከተል ፍላጎት አልነበራትም። አንዴ ኢየሱስን በፍቅር ከወደዳችሁት ሌላ ሰው በእምነታችሁ ላይ ምንም ተጽእኖ አይኖረውም። በአእምሮዋችሁ ውስጥ የሚቀሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብቻ ናቸው።
ራዕይ 2፡3 ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።
ቀደም ባለው ጥቅስ ውስጥ እንዳየነው የአዲስ ኪዳንን የሐዋርያት ትምሕርት ለመጠበቅ ለፍተዋል። አሁን ደግሞ የኢየሱስን ስም ለመጠበቅም መልፋት ኖረባቸው። የብሉይ ኪዳን አይሁዶች ሁሉን ቻዩ አምላክ ሰው ሆኖ ሊመጣ እንደሚችል ማመን አቅቷቸዋል። አይሁድ በዚህ ምክንያት ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ወደ ምድር ወርዶ በሰው ውስጥ ማደሩን እና ኢየሱስ በተባለ ሰው ውስጥ መገለጡን አላመኑም። ከዚያ በኋላ የዚህ ግልባጭ የሆነ ችግር ተፈጠረ። ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ የአሕዛብ ክርስቲያኖች ኢየሱስ የተባለው ሰው ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር መሆኑን ማመን ፈተና ሆነባቸው። ለሰው አእምሮ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎ ማየት ከባድ አልነበረም። ቀስ በቀስ ግን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ ለእርሱ አባት የሆነ ሰማይ ውስጥ ሌላ ማለትም እግዚአብሔር አብ አለ የሚለው ሃሳብ እየተጠናከረ መጣ። በመጀመሪያ ጊዜ ሃሳቡ ድብዝዝ ያለ ነበር ግን ኋላ ስለ እግዚአብሔር ባህርይ ብዙ የሰው መላምቶች እንዲሰነዘሩ በር ከፈተ። እነዚህም ክርስቲያኖች ቀስ በቀስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው እውነት እየራቁ ሄዱ።
ከግሪክ ፍልስፍና የመጡ ቃላትን እየተጠቀሙ መከራከር ጀመሩ፤ ደግሞም ትራያድ “triad” ሦስትነት የሚለውን ፕሌቶ የተባለ የግሪክ ፈላስፋ የፈጠረውን ቃል ይዘው መጡ። ይህም ቀስ በቀስ እያደገ “Trinity” ትሪኒቲ ወይም ሥላሴ የሚለውን ቃል ወለደ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ባዕድ የሆኑ ቃላት እየሾለኩ ገቡ፤ ኋላም “ሦስት አካላት ያሉት መለኮት” የሚል (መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ) አባባል ይዘው መጡ፤ ይህም አባባል ኢየሱስ በሚለው ስም ለወከል የማይችል ሆነ።
እንግዲህ በዚያ ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት ሐረጎች ነበሩ፡ እነርሱም፡-- የኢየሱስን ስም አጥብቆ የያዘው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ያመነው እውነተኛው ሐረግ እና ሐሰተኛው ሐረግ ናቸው።
CHURCH AGES BOOK THE EPHESIAN CHURCH AGE
“…ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም”። እነዚህ አማኞች ሲደክሙ የነበሩት ስለ ጳውሎስ አልነበረም፤ ወይም ደግሞ ስለ ድርጅት አልነበረም። ለየትኛውም አይነት ድርጅት ወይም ስማቸውን ለሚያስጠሩበት ፕሮግራም ራሳቸውን አልሰጡም። የጌታ አገልጋዮች እንጂ የድርጅት ተላላኪዎች አልነበሩም።
የትኛውም የድርጅት ተወካይ እውነተኛ የግል አስተያየት መስጠት አይችልም። መናገር የሚችሉት ድርጅቱ እንዲናገሩ የሚፈቅድላቸውን ብቻ ነው፤ ወይም ድርጅቱ እንዲናገሩ የሚጠብቅባቸውን ብቻ ነው።
አንድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የመጡ ሃሳቦችን መቀበል የሚወድ ሐሰተኛ ሐረግ ደግሞ በዚያው ዘመን እያደገ ነበር፤ ይህም ሐረግ ኢየሱስ በሚለው ስም የማይጠራ ብዙ አካላት ያሉት መለኮት ጽንሰ ሃሳብ ፈጠረ።
ጦርነቱ ተጀመረ። ሁለቱ ዘሮች ተተከሉ።
ራዕይ 2፡4 ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።
ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እውነተኛው ሐረግ ቸልተኛ መሆን ጀመረ። እጅግ በጣም ተዘናጉ። ስኬታቸው ሲበዛ ነቅተው መጠበቅ ላይ ሰነፉ። ለጊዜው ነገሮች ተረጋጉ። ስደትም እየበረደ ሄደ። ከዚያም አጥብቆ በመጽሐፍ ቅዱስ መመራት ብዙም አስፈላጊ አይደለም የሚል ላላ ያለ አቋም መጣ። ለመጽሐፍ ቅዱስም የነበራቸው ጥልቅ ፍቅር ቀዘቀዘ። በጥቂቱ ማመቻመች ተጀመረ። በዙሪያ ካለው ማሕበረሰብ እምነትና ልማዶች ጋር ለመመሳሰል የሚደረገው ጫና ጠነከረ። ለመጽሐፍ ቅዱስ የነበራቸው የቀደመው ጽኑ ፍቅር ቀነሰ። ከዚያ ወዲያ አንድ ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ካልተገኘ እውነት አይደለም ብሎ መሟገት ቀረ።
በሁሉ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ የመጣ አንድ ሃሳብ ነበረ፤ እርሱም ቤተክርስቲያንን የሚመራ አንድ ብቃት ያለው ሰው የምናምነውን የሚነግረን ብናገኝ ሕይወታችንን ቀለል ያደርግልናል የሚል ነው። ከዚያ በኋላ ለራሳችን ማሰብ አይጠበቅብንም።
የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ከመከተል ይልቅ የሰውን አመራር መከተል በጣም ይቀላል።
ነገር ግን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የተዘሩ ትንንሽ የስሕተት ዘሮች በኋለኞች ዘመናት አድገው ጸረ መጽሐፍ ቅዱስ የሆነ፤ እውነትን ውጦ የሚያጠፋ በስተመጨረሻም መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት የሌለው ፍጹም መጽሐፍ መሆኑን ማንም ማመን እስኪያቅተው ድረስ የሰውን አእምሮ ሁሉ የሚበክል የክርስትና አይነትን እንደሚያስከትል ማንም አልጠረጠረም። በኤደን ገነት ውስጥ በሔዋን ላይ እንደሆነባት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጥቅስ እንኳ ባይታመን ይህ ብቻ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ በቂ ነው። እስቲ ዛሬ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ እያንዳንዱ ቃል እውነት መሆኑን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ፈልጉ። እንደዚህ አይነቱን ክርስቲያን ለማግኘት ብዙ ትደክማላችሁ።
ሳይንስ የአዝጋሚ ለውጥ ንድፈ ሃሳብ (የኤቮልዩሽን ቲዮሪ) እውነት ነው ብሎ ይናገራል፤ በዚህም የተነሳ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የዘፍጥረት መጀመሪያ ምዕራፎችን እንደ ተረት ያያሉ።
በናቡከደነጾር ሃውልት ላይ ያለውን የአሕዛብ ምስል ታስታውሳላችሁ? ዓለቱ መጣና የሐውልቱን እግር መታው፤ የምስሉንም የዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሃሳብ ሰባበረው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰውን አመለካከት የማይጨምር አንድ ክርስቲያን ፈልጋችሁ ለማግኘት ሞክሩ። ብዙ አይደሉም። ሳይንስ የቢግ ባንግ ቲዮሪ እውነት ነው ይላል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሊፈጥረን አያስፈልገንም። የሳይንሱ ዓለም አራቱን የተፈጥሮ ኃይላት ከኤቮልዩሽን ቲዮሪ ጋር እንደምንም ለማገጣጠም እየተሟሟተ ነው ግን አልተሳካላቸውም። (ሰለዚህ የሳይንሱ ዓለምም በሚመጣው ዓለት በኢየሱስ ዳግም ምጻት ተመቶ ይሰባበራል።) ስለዚህ ሳይንቲስቶስ እግዚአብሔር አያስፈልገንም ይላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስንም የምር እውነት አድርገን መቀበል የለብንም ይላሉ። ብዙ ሚሊየኖች ይህን ሃሳብ በቀላሉ ይቀበላሉ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰባኪዎች በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንድ ጥቅሶች ከመጀመሪያዎቹ ቋንቋዎች በትክክል አልተተረጎሙም ብለው ይናገራሉ። ለዘመናዊ አንባቢዎች መጽሐፍ ቅዱስ የጸሐፊዎቹ የግል አመለካከት ሆኗል። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርስ በሚጋጩ ሃሳቦች እንደተሞላ ያምናሉ። በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በተዘራው የጥርጣሬ ዘር አሁን የሞት መኸር እየታጨደ ነው።
ምሳሌ 30፡5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤
ማቴዎስ 4፡4 እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 … የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
አማኝ እያንዳንዱን ቃል ማመን እና መታዘዝ አለበት። እግዚአብሔር የምንፈልጋቸውን ጥቅሶች ብቻ እንድንመርጥ አልፈቀደልንም። ከእምነትህ ጋር የማይስማማ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቢኖር የአንተ እምነት ስሕተት አለበት ማለት ነው።
ራዕይ 2፡5 እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።
ብዙዎች በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ በከተሞቻቸው ውስጥ ካሉት መሪዎች ጋር እንዲስማሙ ከታላላቅ ሰዎች ለሚመጡ ጫናዎች እጅ እየሰጡ ነበር። ሕዝቡ ከሐዋርያት ትምሕርት ይልቅ የሰው መሪዎችን እያደመጡ ስለነበረ እግዚአብሔር በ70 ዓ.ም. ከዮሐንስ በቀር ሐዋርያትን ሁሉ አስወገደ።
በዚህም ምክንያት ሰዎችን እንደ መሪ የመከተል ዝንባሌ ጨመረ። ስሕተት ከፈለግን እግዚአብሔር ስሕተት ይሰጠናል። አይሁድ ንጉስ ካልተሰጠን ሲሉ እግዚአብሔር ንጉስ ሳኦልን ሰጣቸው፤ እርሱም ብዙ ነገር አበላሸባቸው ምክንያቱም አይሁድ በንጉስ ይተዳደሩ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም።
ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።
አይሁድ የተስፋይቱን ምድር መውረስ እንደማይችሉ ባሰቡ ጊዜ እግዚአብሔር በምድረበዳ 40 ዓመት እንዲባዝኑ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው።
ዘኁልቁ 14፡33 ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ።
ክርስቲያኖች ለመረዳት የሚከብዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አካባቢ ይባዝናሉ ወይም ቸል ይሉዋቸዋል፤ የብዙዎቹን ጥቅሶች መንፈሳዊ ትርጉም ስለማያውቁ በመንፈስ ይቅበዘበዛሉ። እነዚህን ጥቅሶች እንደ ስሕተት ወይም እንደማያስፈልጉ ይቆጥሩዋቸዋል። ይህም ጠለቅ ያለውን ትርጉም ፍለጋ እንዳንደክም ቀለል ያለ ማምለጫ መንገድ ነው።
• ኢየሱስ በማመንዘር የተያዘችውን ሴት ይዘው መጥተው ሲጠይቁት ለምንድነው ሁለት ጊዜ ምድር ላይ በጣቱ የጻፈው? ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን ጥያቄ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚበቃ እውቀት የላቸውም። ሰዎቹ ስለ ሕጉ እየጠየቁ ነበር፤ እርሱም ይህንን ዘዴ ተጠቅሞ ስለ እግዚአብሔር መለኮት እንዲሁም ስለ ሕግ እና ስለ ፀጋ ጠለቅ ያለ ትምሕርት እየሰጣቸው ነበር።
• ሉቃስ የጻፈው የኢየሱስን የዘር ሃረግ በዳዊት እና በዮሴፍ መካከል ለምንድነው ማቴዎስ ውስጥ ከምናገኘው የትውልድ ዝርዝር የተለየው? አንዱ የዮሴፍ የዘር ሃረግ ሲሆን ሌላኛው የማርያም ነው። ሁለት የዘር ሃረግ ያስፈለገው ለምንድነው?
• የኢየሱስን የዘር ሃረግ ለምንድነው ሁለቱ ወንጌሎች ብቻ የመዘገቡት?
• ሉቃስ በጻፈው የዘር ሃረግ ውስጥ በዳዊት እና በዮሴፍ መካከል ያሉ ትውልዶች በቁጥራቸው ማቴዎስ ከጻፈው በአሥራ ሶስት የበለጡት ለምንድነው?
• በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ካሉት ሰባት ቤተክርስቲያናት ውስጥ ስድስቱ የከተሞቻቸውን ስም ይዘዋል። (በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንደምናየው) ሦስተኛዋ ቤተክርስቲያን ግን የስሟ መጨረሻ ላይ የግሪክ ድምጽ አላት፤ ፔርጋመም በመሆን ፈንታ ፔርጋመስ ትባላለች። ለምንድነው? ይህ ጥያቄ መጀመሪያ የተነሳው በ1850 ዓ.ም. ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችሁ እስካሁንም ድሮ ሰዎች እንደነበራቸው ትንሽ ነው? ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ ሳይንሳዊ እውቀት እንደ ሮኬት ተተኩሷል። ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው እውቀት ግን እንደ ኤሊ እየተንፏቀቀ ነው። የሆነ ችግር አለ።
• ማቴዎስ እና ማርቆስ በኢየሱስ መቃብር አጠገብ አንድ መልአክ ብቻ ነው የሚጠቅሱት። ለምን? ሉቃስና ዮሐንስ ግን ሁለት ነበሩ ይላሉ። በዚህ አማካኝነት አራቱ ወንጌሎች ምን ሊነግሩን እየሞከሩ ነው?
• ዮሐንስ እንደሚነግረን ማርያም ወደ መቃብሩ ስትመጣ ኢየሱስ እንዳትነኪኝ ብሏታል።
ዮሐንስ 20፡16 ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ፦ ረቡኒ አለችው፤ ትርጓሜውም፦ መምህር ሆይ ማለት ነው።
17 ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።
• ሆኖም ግን ማቴዎስ ሴቶች ኢየሱስን እግሩን መንካት እንደሚፈቀድላቸው ይናገራል።
ማቴዎስ 28፡5 መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤
9 እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።
መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ ብዙ ክርስቲያኖች እንቆቅልሽ የሚሆንባቸው እንደዚህ አይነት ምስጢሮች ሞልተውበታል። ተጠራጣሪዎች እነዚህን ጥቅሶች በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይቃረናል ይላሉ። በዚህም መንገድ ተጠራጣሪዎች እነዚህን ክርስቲያኖች በክርክር ያሸንፋሉ። ብዙ ክርስቲያኖች የሜሴጅ አማኞችን ጨምሮ ለምንድነው እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ የማይችሉት? በቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው አማካኝነት በጨለማ እንዲቆዩ ስለተደረጉ ነው። መሪዎቻቸውም ደግሞ መልሱን አያውቁም
ስለዚህ ገና ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡን ተቆጣጥረው እውነት እስኪረሳ ድረስ በጨለማ መንገድ ሲነዱዋቸው ቆይተዋል።
ኒቆላውያንነት የሚለው ቃል የመጣው “ኒቆ” ማለትም “መግዛት” እና “ሌዎስ” ማለትም “ምዕመናን” በሌላ አነጋገር ጉባኤው ነው። ምዕመናንን መግዛት ሮም ውስጥ የተዋጣለት ዘዴ ነበር። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዓለም ትልቋ ቤተክርስቲያን ወደ መሆን እያደገች ስትመጣ መሪዋም አምባገነን ፖፕ ወይም ሊቀ ጳጳስ ሆነ። ዛሬ ፖፑ በምዕራብ አውሮፓ ብቸኛው አምባገነን መሪ ነው። ሮም ግን ኢጣሊያ ውስጥ ናት። ሮም ውስጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ በመንገስ ተደላድላ ተመሰረተች።
ራዕይ 2፡7 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።
ስዕል ስታዩ በአንድ ጊዜ ልትመለከቱት ትችላላችሁ። በአንድ ምልከታ ማየት ይቻላል። ትምሕርትን ግን በአንድ አፍታ ልታደምጡ አትችሉም ምክንያቱም ንግግር ቃሉቱ በሙሉ ተብለው እስኪያልቁ ድረስ ጊዜ ይፈልጋል። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ሊነግረን የሚፈልገውን ቀስ በቀስ ሲገልጥልን መስማት እንድንችል ለጆሮ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል። ከገሃዱ ዓለም ጋር ያለን ግንኙነት 80 በመቶው የሚመጣው በዓይናችን በኩል ሲሆን 15 በመቶው ብቻ ነው በጆሮዋችን በኩል። ስለዚህ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ለሰይጣን ዓይናችንን እንዲጠቀም እድል ይሰጠዋል። ሰይጣን በዓይን አምሮት፣ በዚህ ዓለም አብረቅራቂ ነገር፣ በትልልቅ አስደናቂ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎች እና በቅንጦት ኑሮ ያታልለናል። የሃብታምነት ምኞት ለትርፍ እንድንስገበገብ ያደርገናል።
እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እንድናዳምጥ በመጠይቅ በትሕትና ወደ እኛ ይመጣል። ከዚያም እኛ ደግሞ እግዚአብሔር የቃሉን ምስጢር ሊገልጥልን እስኪወድ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ አለብን። እውነት ጊዜ ይፈልጋል። ተክሎች በራሳቸው ጊዜ ነው የሚያድጉት። ፍሬ ቀስ ብሎ ነው የሚበስለው።
ዛሬ የሜሴጅ ሰባኪዎች ወደ ፊት የሚሆኑ ክስተቶችን አልፈዋል ይላሉ። ክስተቶች ግን በራሳቸው ትክክለኛ ጊዜ ነው የሚገለጡት። እኛ ማድረግ የምንችለው ነገር ቢኖር በችኩሎች ስብከት ላለመታለል በጣም መጠንቀቅ ነው። ከእግዚአብሔር ጊዜ መቅደም ጊዜን ማባከን ነው።
እግዚአብሔር የሚናገረው ለሁሉም ቤተክርስቲያኖች ነው። እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን የመጀመሪያውን ዘመን መምሰል አለበት ምክንያቱም እግዚአብሔር ሌላ እቅድ የለውም። እያንድንዱ ዘመን ከመጀመሪያው ዘመን ምን ያህል ማፈንገጡ እየታየ ነው የሚፈረድበት። እኛ ያለንበት የሎዶቂያ ቤተክርስቲያን ዘመን የመጨረሻው ወሳኙ ዘመን ነው። እግዚአብሔር ወደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እንድንመለስና እንደነሱ እንድንሆን ይጠብቅብናል። ከዚያ የኛ የቤተክርስቲያን ዘመን በመሃሉ ታላቁ መከራ ይገባበታል። በእምነታቸው የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን የማይመስሉ እጅግ ከባድ ትምሕርት ሊማሩ ነው። 6 ሚሊየን አይሁድ ያለቁበት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጭፍጨፋ የታላቁ መከራ ቅምሻ ነው፤ ልክ አንድ ሚሊየን ያህል አይሁድ እንደተገደሉበት የ70 ዓ.ም. የኢየሩሳሌም ውድመት።
እየተስፋፋ የመጣውን በቤተክርስቲያኖች በስም መከፋፈል እና የሰውን መሪ የቤተክርስቲየን ራስ እንዲሆን ከፍ ለማድረግ ብለው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ከሚንቁ ጋር አልተባበርም ለሚሉ ግለሰቦች በገነት የሚጠብቃቸው ሽልማት በምድር ላይ የሚገጥማቸውን መገፋትና እንግልት በብዙ ይበልጠዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ዛፍ ነው። እርሱ ብቻ ነው የዘላለም ሕይወት የሚሰጥ። እርሱ በሰው መልክ የተገለጠው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለዚህ በምድር ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መቆየት ከፈለክ የክርስቶስ መንፈስ በውስጥህ ሲኖር ብቻ ነው የምትችለው። ከዚያ ላንተ ድርሻ ሆኖ የተሰጠህ መንፈስ ቅዱስ ወደ ገነት ይወስድሃል ምክንያቱም የታላቁ መንፈስ ቅዱስ አካል የኢየሱስ አካል ትሆናለህ። ስለ እርሱ በምድር ብትቆም ከእርሱ ጋር በሰማይ ትቆማለህ። ከዚህ የተሻለ ፍጻሜ አይኖርም።
ግን እያንዳንዱ ዘመን የራሱን ዘመን ስሕተት ማሸነፍ አለበት።
የመጀመሪያው ዘመን ጥፋት ፈጽመው መጽሐፍ ቅዱስን ባይከተሉ ችግር እንደሌለው ማመን መጀመራቸው ነው። እግዚአብሔርን እናገለግላለን ለሚሉ ለሰው መሪዎች አመለካከትና ፈቃድ መታዘዝ እግዚአብሔር የሚፈልገው አገልግሎት ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ። ለቤተክርስቲያን አባልነት ታማኝ መሆን እና በቤተክርስቲያን አባልነትና ከቤተክርስቲያን ሁሌ ባለመቅረት መደገፍና መታመን ተጀመረ። እነዚህ ነገሮች በራሳቸው መጥፎ አይመስሉም ነግር ግን እያስከተሉ የነበረው ውጤት የሰዎችን ዓይን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዞር በማድረግ ክርስቲያኖች ስለ ቤተክርስቲያናቸው አመራር መልስ ሲሰጡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳይጠቅሱ ማድረግ ነው። “ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው” “አሥራት የሚገባው ለባስተሩ ነው” “ፓስተሩ ይረዳሃል” እነዚህ እስከዛሬ ድረስ የምንጠቀማቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አባባሎች ናቸው። ስለዚህ ጸረ መጽሐፍ ቅዱስ የሆነ ድርጅት እያደገ ሰዎችንም ከመጽሐፍ ቅዱስ አርቆ ይዞ እየሄደ ነበር። መጀመሪያ ብዙም ጉዳት ያለው አይመስልም ነበር። ስለዚህ እነዚህ ሃሳቦች ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው ገቡ። ሰዎች በጣም ከመዘናጋታቸው የተነሳ ፓስተር የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንዴ ብቻ መጠቀሱን እንዲሁም የቤተክርስቲያን ራስ የመሆን ስልጣንም እንኳ እንዳልተሰጠው አላስተዋሉም።
ሐዋርያት የሞቱለትን እምነት ከጊዜ በኋላ ዞር ብሎ የሚያየው ጠፋ።
ሐዋርያት ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ እንደሆነና ቤተክርስቲያንም በሽማግሌዎች ሕብረት መመራት እንዳለባት አስተምረዋል። መንፈሳዊ ጉበኞችም እነዚህ አዳዲስ ሃሳቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ መሆናቸውን ለማረጋገት በስፍራቸው አልተገኙም። ሰዎች ምንም አይደርስብንም ብለው አስበው በብልጣሶር ድግስ ላይ ሲዝናኑ እንደነበረው ሁሉ ነቅቶ መጠበቅ ቀረና ሰዎች ትኩረታቸውን መደሰት እና በቁሳዊው ዓለም መበልጸግ ላይ አደረጉ። ለቤተክርስቲያን ምን እንድታምን የሚነግራትን አንድን ሰው መሪ አድርጋ መከተል በጣም ቀለላት።
ጳውሎስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሰዎች ሰው እንዲመራቸው የመፈለግ ዝንባሌያቸውን ለማጥፈት ሲታገል ነበር። ሰው እንዲመራን መፈለግ በተፈጥሮ ያለብን ድክመት ነው።
በቀሎኤ ቤት የሚሰባሰቡት አማኞች ወይም ቤተክርስቲያን ሌሎቹ ከእነርሱ ጋር የጀመሩትን ውድድር በተመለከተ ለጳውሎስ ቅሬታ አቀረቡ። እነዚያም ራሳቸውን የጳውሎስ ቤተክርስቲያን፣ የአጵሎስ ቤተክርስቲያን የኬፋ ቤተክርስቲያን እያሉ ይጠሩ ነበር፤ ቤተክርስቲያን የእነዚህ ትልልቅ ሰዎች የሆነች ይመስል እና ደግሞ ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከሌላው የሚበልጥ ከሆነ እነርሱ በዚያች ቤተክርስቲያን አባል በመሆናቸው ከሌሎች ሊበልጡ ይፈልጋሉ።
እስከ ዛሬ ድረስ የሉተር ቤተክርስቲያን አለ፣ የዌስሊ ቤተክርስቲያን አለ፣ የዊሊያም ብራንሃም ቤተክርስቲያን አለ፣ የሜሴጅ ቤተክርስቲያን አለ። ቤተክርስቲያኖች በፓስተራቸው ስም እየተጠሩ ነው። ይህ አሳዛኝ ስሕተት ለሁለት ሺ ዓመታት ዘልቋል። እጅግ ከባድ እን በጣም ተላላፊ የሆነ ቫይረስ ነው። በሰው መሪነት ላይ መጣበቅ የቤተክርስቲያን ውድቀት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 1፡11 ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና።
12 ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ።
13 ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?
ጳውሎስ አንድ ሰው እንኳ በእርሱ ስም ቢጠመቅ በጣም ያስደነግጠዋል። ዛሬ ግን ይህ እየሆነ ነው፤ ሰዎች በዊሊያም ብራንሃም ስም ወይም በጌታ ብራንሃም ክርስቶስ ስም እየተጠመቁ ነው። ስለዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ስሕተት የተጀመረው አንድ ሰው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን በመሆኑ ነው፤ ያም ስሕተት ፈጽሞ አልጠፋም።
የእውነትን አንድ ገጽታ ብቻ ያለልክ የማጉላት አደጋ አለ (አንድ ሰው ብቻ ቤተክርስቲያንን በብቃት እንዲመራ ከፍ መደረጉ) እና ሌሎች እውነቶችን ቸል ማለት (መጽሐፍ ቅዱስ የሽማግሌዎች ሕብረት ቤተክርስቲያንን እንዲመራ ማለቱን)።
በአሁኑ ሰዓት እጅግ ብዙ ሰዎች የሚሰበሰቡበትን ትልቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻ መስራት እና በአንድ ሰው መመራት ትልቅ ትኩረት ይሰጠዋል። ይህ ቀልጣፋ አመራር ነው ግን ሰውን ሁሉ በስሕተት ወጥመድ ውስጥ ያስቀራል። ነገር ግን በጥንቷ ቤተክርስቲያን ሰዎች በየቤቱ ይሰበሰቡ እንደነበረ እንዘነጋለን፤ ቤት ውስጥ ሲሰበሰቡ አንድም ሰው ሕብረቱ ላይ ሊነግስበት አይችልም ምክንያቱም እያንዳንዱ ቤት ትልቅ ሕብረቶችን ሊይዝ አይችልም። በየቤቱ ሲሰበሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መወያያት እንዲሁም ከአንድ ራሱን ትልቅ ማድረግ ከሚፈልግ ሰው ገዥነት ነጻ ወጥተው በቃሉ መኖር ይችላሉ።
ስለዚህ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እውነተኛ አማኞች እግዚብሔር የሚጠላውን ከፍ ያለውን የሰው አመራር መዋጋት ነበረባቸው። ዛሬ እኛም ልክ እንደ እነርሱ ይህንን ስሕተት መዋጋት አለብን። ግን የእኛ ችግር ከእነርሱም የባሰ ነው። እኛ ከዚያ ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ቃሉን ባለመታዘዛቸው በተፈጠረ ትንሽ ቀዳዳ ሾልኮ የገባውን የስሕተት እባብ መዋጋት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ስድስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ባለመታዘዝ የተጠራቀመ ትልቅ ክፍተት ውስጥ የገቡ ትልልቅ እባቦችን ሁሉ መዋጋት ይጠበቅብናል።
ፊልጵስዩስ 2፡12 ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
ባለህበት ቤተክርስቲያን ተመችቶህና በግድየለሽነት ተደላድለህ እየኖርክ ከሆነ የጎደለብህ ነገር አለ። ተጠንቀቅ።
ሉቃስ 21፡34 ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤
35 በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና።
36 እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ።
ወጥመድ የተደበቀ አሽክላ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳናይ የሚያሳውሩንን ስሕተቶች እግዚአብሔር ካልገለጠልን ከባድ ችግር ውስጥ እንገባለን።
የሰውን አመለካከት በማዳመጥ ቤተክርስቲያን ለተሰጣት አደራ ታማኝ ሳትሆን ቀረች፤ ስትጀምር ከተመሰረተችባቸው መርሆችም ራቀች። ዛሬም ተመሳሳይ ስሕተት እንሰራለን። የኤፌሶን የወደብ ከተማ ወደ ወደቡ ከሚፈስሰው ወንዝ የሚመጣ ጭቃ ወደቡን ሞልቶት ከተማይቱ ጠፋች የባሕሩ ጠረፍም ከከተማይቱ ርቆ ሄደ። ልክ እንደዚያው ቀስ በቀስ ሰዎች ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል እየራቁ ሲሄዱ የሰው አመራር እና የሰዎች አስተሳሰብ አእምሮዋቸውን እየሞላው ሄደ። የመጀመሪው ዘመን ዋነኛ ስሕተት ሽማግሌ ካሕን ተብሎ መጠራቱ እና የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ራስ መደረጉ ነው።
ከዚያም በእያንዳንዱ ከተማ እና በዙሪያው ላሉ አጥቢያዎች ሁሉ ራስ የሚሆን ጳጳስ በመሾም ይህ ብልሹ ስርዓት እንዲጠናከር ተደረገ።
በዚህም መንገድ በቀጣይነት በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ለሚመጡ ስሕተቶች በር ተከፈተ።
አንዳንድ ሰዎች ለሮማ ግዛት ውድቀት የሆነው ዋነኛው መንስኤ የተፈጠረው እጅግ በጣም መልካም በሆነው ንጉስ በማርከስ ኦሬሊየስ ዘመን ነው ብለው ያስባሉ። እርሱም ከተጠናወተው ክርስቲያኖችን የማሳደድ አባዜ በስተቀር መልካም ሰው ነበር ይላሉ። በታሪክ ከተከሰቱ ወረርሽኞች ሁሉ እጅግ የከፋው የአንቶኒ ወረርሽን በሮማ ግዛት ውስጥ ከ165 እስከ 180 ዓ.ም. ተስፋፋ። ይህ ወረርሽኝ ሮም ጦርነት ላይ እያለች ሰራዊቱ አንድ ላይ በተሰበሰበበት ነበር የተነሳው። በሰራዊቱ መካከል በመሰራጨትና መሪዎቻቸውን በመግደል የቁጥር ብልጫቸውን አመነመነው። የሕዝብ ቁጥርም በእጅጉ ቀነሰ። በግዛቱ ውስጥ የሕዝብ ቁጥር መመናመን ማለት ደግሞ እህል የሚያመርቱ ሰዎች ቁጥርም ይቀንሳል ማለት ነው። ይህም የከተሞችን ውድቀት ያስከትላል (ምክንያቱም ከተሞች እንዲያድጉ ብዙ የእርሻ ምርት ያስፈልጋቸዋል) ደግሞም በአጠቃላይ የሕዝብ ብዛትም እንዳያድግ ያደርጋል። በአጭሩ ሮም ግዛቶችዋን ሁሉ የሚጠብቁላት በቂ ወታደሮች አይኖሩዋትም ማለት ነው።
ይህም ከዓመታት በኋላ ድንበሮቻቸውን ለማስጠበቅ የሚበቃ ገንዘብ እና የሰው ኃይል በጠፋ ጊዜ ለሚመጣው ለምዕራባዊ ሮማ ግዛት ታላቅ ውድቀት መሰረት አበጀ።
በዚህ በታላቁ ወረርሽኝ መካከል የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ተፈጽሞ ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የጀመረበትን ጊዜ ለማመልከት በ170 ዓ.ም. አካባቢ መስመር ልናሰምር እንችላለን።
ኑሮ ከባድ ነበረ። ይህም ቤተክርስቲያን ከአዲስ ኪዳኑ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ምሳሌ ርቃ የመሄዷ ውጤት ነው።