ዳንኤል እና ዮሐንስ። የሁለቱ ትንቢቶች ትልቅ ትስስር አላቸው
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
አዎ፤ ዳንኤል እና በሕብረት አገልግለዋል። መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው እግዚአብሔር መሆኑን አትርሱ። ሰዎች የእርሱን ሃሳብ እያደመጡ የጻፉ ጸሃፊዎች ናቸው።
ዳንኤል እና ዮሐንስ
ዳንኤል በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ በነበሩ ፖለቲካዊ መንግስታት ውስጥ የባቢሎንን ሚስጥራት ማለትም የክርስቶስ ተቃዋሚውን መንፈስ ሲከታተል ነበር። ከዚያም ዳንኤል ይህ የአሕዛብ ስሕተት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልኮ ሲገባ አየ።
ዮሐንስ ደግሞ የባቢሎን ሚስጥራት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲየንን ወደ ባቢሎናውያን ሚስጥራት እንዴት እንደቀየሯት እያሳየ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን ታሪክ ይገልጣል። እናት ቤተክርስቲያን የሆነችዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲየን ፕሮቴስታንት ልጆቿን ታበላሻቸዋለች፤ እነርሱም ልክ እንደ እርሷ ጋለሞታዎች ናቸው።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
ጋለሞታ ለባሏ ታማኝ ያልሆነች ሴት ናት። ቤተክርስቲያኖች እምነታቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል አይደለም፤ የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ኢየሱስ ነው፤ እርሱም የቤተክርስቲያን ባል ነው። ራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያለችው በተክርስቲያን ኢየሱስን ገፍታ አስወጥታው ኢየሱስ በደጅ ቆሞ ያንኳኳል። በስተመጨረሻ ምዕራፍ 18 ውስጥ ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር ይሰማዋል፡- “ሕዝቤ ሆይ ከመካከሏ ውጡ”።
ስለዚህ በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያን ሰው ሄዶ የሚጠለልባት ቦታ ሳትሆን ሰው በስሕተት የሚጠመድባት አደገኛ ቦታ መሆኗ ነው የተገለጠው።
ማቴዎስ 25 ውስጥ ቆነጃጅቱ ንጹህ ሴቶች በሙሉ ማለትም የዳኑ ክርስቲያኖች እንቅልፍ መተኛታቸውን ይናገራል። ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው ጥሪ በመጣ ጊዜ ሕይወታቸውን እንዲያስተካክሉ (ከዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ጋጠወጥነት) ካሉበት ቤተክርስቲያን “እንዲወጡ” ይነገራቸዋል። የትኛዋም ቤተክርስቲያን ጌታ ሲመጣ እንድንቀበለው ልታዘጋጀን ብቁ አይደለችም።
ዳንኤል እና ዮሐንስ በመጽሐፋቸው ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ እየተተካኩት ስለመጡት የባቢሎን ሚስጥራት ፖንቲፎች ጽፈዋል። የመጀመሪያው አመጸኛ የባቤልን ግምብ የሰራው ናምሩድ ነው። የባቢሎን ካሕናት የእርሱ ተተኪዎች ሲሆኑ በአሕዛብ ዘንድ የመጀመሪያዎቹ የጣኦት አምልኮ ካሕናት እንደመሆናቸው ታላቅ ክብር እና ተሰሚነት ነበራቸው። የባቢሎን ሊቀ ካሕናት ፖንቲፍ ወይም ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ይባላል። በሰዎች እና በአማልክት መካከል ታላቁ ድልድይ ሰሪ ወይም በምድር ላይ አማልክትን ወክሎ የቆመው ብቸኛ ሰው የአማልክትን ሚስጥረት የመተርጎም ብቃት አለው ተብሎ ይታመናል። የባቤል ግምብ ዓላማው በምድር እና በሰማይ መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት ነው።
ፔትር ሮማ በአሕዛብ ዘንድ ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ የቆየና የአማልክትን ፈቃድ የሚገልት ታላቁ ተርጓሚ ተብሎ ሲጠበቅ የቆየ ሰው ነው። ለዚህ በ380 ዓ.ም አካባቢ ፖፖቹ የሮማው ጴጥሮስ ተተኪዎች ነን ማለት የጀመሩት። (ፔትር ሮማ ከሚለው ስም ጋር በጣም ይቀራረባል።) ጴጥሮስ ወደ ሮም ሄዶ ባያውቅም ይህ ውሸት ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ከተነገረ ሰዎች ውሸትን እውነት አድርገው መቀበላቸው አይቀርም።
ራዕይ 17፡8 … አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ …
ይህ ጥቅስ የሚነግረን ስለ ፖፕ መተካካት ነው። ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ከሆነ ፖፕ ሁልጊዜም ነበረ ማለት ነው።
“አሁንም የለም”። ፖፑ ይሞታል።
“ነገር ግን እንዳለ”። አዲስ ፖፕ ይመረጣል ማለት ነው።
በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ፖንቲፍ ተብዬ መጠራት አለብኝ አለ፤ ይህን የፈለገው የሮማ መንግስትን እያፈራረሱ በነበሩ ባርቤሪያኖች መካከል መከበር ፈልጎ ነው። እስከ ዛሬም ድረስ የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ፖንቲፍ በሚባል ማዕረግ ነው የሚጠራው (ፖንቲፍ ማለት የባቢሎን ሚስጥራ ሊቀካሕናት ነው)።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዳንኤል የባቢሎን ፖንቲፎችን መተካካት ከአሕዛብ ቤተመቅደሶች ጀምሮ በአራት የአሕዛብ መንግስታት በኩል ተከታትሎ እስከ ሮማ ካቶሊክ ፖፕ መተካካት ድረስ ተከታትሎ ጽፏል። ከዚያ በኋላ ዮሐንስ ደግሞ ባለፉት 2,000 ውስጥ የቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ ተጽእኖ ያደረጉትን ፖፖች ተከታትሎ ጽፏል። የፖፖች መተካካት በምድር ላይ ከነበሩ ስርወ መንግስቶች ሁሉ በርዝመት አንደኛ ነው።
ባቢሎን ውስጥ ናቡከደነጾር የአሕዛብን ታሪክ በአንድ ሰው ምስል መልክ አየ።
አሕዛብ ሁልጊዜ ዓለምን በሙሉ አንድ ሰው እንዲመራ ይፈልጉ ነበር።
ባቢሎን የወርቁ ራስ ነው፤ ይህም የወርቅ ራስ ብዙ የአረማውያን ጥበብ የተሞላ ራስ ነው።
በክረምት አጋማሽ የፀሃይ አምላክ መወለድ።
እናት እና ልጅን ማምለክ።
ሚስጥራትን ካርዲናሎች እንዲመሩ ማድረግ።
የስላሴ አማልክት።
የምንቀደስበት የሁዳዴ ጾም።
የኢሽታር እንቁላሎች እና የኢሽታር ጥንቸሎች ለፀደይ ወቅት በዓል። የሮማ ካቶሊኮች ይህንን በቀላሉ የፋሲካ እንቁላሎች እና የፋሲካ ጥንቸሎች አድርገው ለወጡ (ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ሃሳብ ነው)። ሂዩ ሄፍነት ፐሌይቦች ለተባለው የብልግና ክለቡ ሴቶች እንደ ጥንቸል እንዲለብሱ ለምን እንዳደረገ ጠይቁ። እስካሁን ድረስ የምንበላሸው ከባቢሎናውያን ካሕናት በተቀበልናቸው እንግዳ ትምሕርቶች ነው። የወርቅ ራስ እንደመሆናቸው ያን ያህል ብልጥ ናቸው።
መናዘዣ ቦታ። ሰዎች ሐጥያታቸውን ለባቢሎናውያን ካሕናት ከተናዘዙ በኋላ እነዚህ ካሕናት ሐጥያታችሁን እናጋልጣለን ብለው ሰዎቹን በማስፈራራት ገንዘብ አምጡ ብለው ማስገደድ እና በሌላም መንገድ ሊጫወቱባቸው ይችላሉ። በዚህ መንገድ ካሕናቱ በሕዝቡ ላይ ስልጣን ይዘው ተቆጣጣሪ ሆነውባቸው ነበር።
የባቢሎን ካሕናት በሕዝቡ እና በአምላካቸው መካከል ቆመናል ይላሉ። ስለዚህ ሕዝቡ ለካሕናቱ ተገዥ ነበሩ።
ከለዳውያን ካሕናት ብቻ የሰማይ ቁልፍ እንዳላቸው ይታመናል። እነርሱም የባቢሎን ካሕናት ሆኑ።
ዛሬ ደግሞ ፖፑ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍትላችሁ ለፖፑ ከታዘዛችሁ ብቻ ነው ይላል። በ1302 ዓ.ም ፖፑ “Unam Sanctam” የሚል አዋጅ አወጀ፤ ይህም ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን የለም ማለት ነው። ብዙ የፕሮቴስታንት ፓስተሮች ይህን እምነት ይከተላሉ። “ከኔ ቤተክርስቲያን ብትወጡ ጠፍታችኋል”። ለዚህ ነው ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ሲሉ ምንም የማይከብዳቸው ነገር ግን ቤተክርስቲያናቸውን ለመተቸት በጭራሽ የማይደፍሩት።
ኤል ባር ተብሎ የተጠራ ብቸኛው ሰው ናምሩድ ነው። ይህም እግዚአብሔር ወልድ ማለት ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን “እግዚአብሔር ወልድ” ያለቸው በስላሴ ትምሕርት ምክንያት ነው፤ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ይህንን ስድብ ኮርጀው ለኢየሱስ አደረጉት። ይህ ሁሉ ደግሞ “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳ ባልተገኘበት ነው።
ጣኦታት። የአሕዛብ ቤተመቅደሶች ውስጣቸው በሃውልቶች የተሞሉ ናቸው፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያኖችም ልክ እንደዚሁ።
ካቶሊኮች በፑርጋቶሪ ያምናሉ፤ ለሙታን ይጸልያሉ፤ ወደ ሞቱ ቅዱሳን ይጸልያሉ።
ሴት አምላክን ማምለው ማርያምን ማምለክ ሆኖ ተለወጠ።
የጸሎት መቁጠሪያ እና ሻማዎች ከጥንት ጀምሮ ከጣኦት አምላኪዎች የመጡ ልማዶች ናቸው።
ብዙ የአሕዛብ መንግስታት በተነሱና በወደቁ ቁጥር እነዚህ ባቢሎናውያን ሃሳቦች ከአሕዛብ ብዙ ልማዶችን እየጨመሩ ሄደዋል። የግሪክ ፍልስፍና የአሕዛብ ስሕተቶችን ትክክለኛ አድርጎ ለማቅረብ እጅግ የረቀቁ ክርክሮችን ያቀርባል። የግሪክ ፈላስፋዎች እጅግ የሚኮሩበት ችሎታ አላቸው፤ ትክክለኛም ይሁን የተሳሳተ ሃሳብ ይዘው በጥሩ ክርክር ማሳመን ይችላሉ።
ዳንኤል ምዕራፍ 2 ውስጥ የተጻፈው የአሕዛብ ምስል ባቢሎናውያን ካሕናት ቂሮስ ባቢሎንን በገዛ ጊዜ እንዴት እንደተቃወሙት እና እንዴት ሸሽተው ጴርጋሞን ውስጥ እንደሰፈሩ ያሳያል። ሜዶናውያን እና ፋርሶች የመጀመሪያዎቹ ዓለም አቀፍ መንግስት ነበሩ፤ ከእነርሱም የባቢሎን ካሕናት በአንድ ብቸኛ ራስ የሚመራ ጨካኝ እና ዓለምን በሙሉ የሚገዛ ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዴት እንደሚመሰርቱ ተምረዋል።
ግሪክ ፋርስን አሸነፈች፤ የባቢሎን ካሕናትም ከግሪክ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን የስላሴ አስተምሕሮ እና ፑርጋቶሪ እንዴት አድርገው በክርክር እውነት አስመስለው ማቅረብ እንደሚችሉ ተምረዋል።
ታላቁ አሊግዛንደር በዘመተበት ጦርነት ሁሉ ድል አድራጊ ከመሆኑ የተነሳ በምዕራቡ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አምላክ ተቆጥሮ ተመልኳል። በምስራቅ የፋርስ መንግስት ውስጥ ብዙውን ጊዜ ንጉስ እንደ አምላክ ይመለክ ነበር።
በ133 ዓመተ ዓለም የጴርጋሞን መንግስት ባቢሎናውያን ካሕናቱን ይዞ ለሮም ተሰጠ፤ በ63 ዓመተ ዓለም ዩልየስ ቄሳር ጉቦ ከፍሎ የባቢሎን ሚስጥራት ፖንቲፍ ለመሆን በቃ። ቄሳር የሮም ፈላጭ ቆራጭ ሆነና ከሞተ በኋላ አምላክ ነው ተብሎ ተመለከ። ከዚያ ወዲያ የባቢሎን ፖንቲፍ ዝነኛ ሆነ። የሮማ ነገስታት ይህንን ማዕረግ እና የቄሳር አምልኮ በ379 ዓ.ም ቴዎዶሲየስ እስኪነግስ ድረስ እየተጠቀሙበት ቆዩ። ቴዎዶሲየስ ግን ክርስቲያን ስለ ነበረ የባቢሎን ፖንቲፍ መሆንን እምቢ አለ።
በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ፖንቲፍ ተብዬ መጠራት አለብኝ ብሎ ፖንቲፍ ብለው እንዲጠሩት አዘዘ፤ ምክንያቱም ይህ ማዕረግ የሮማ መንግስትን እያፈራረሱ በነበሩት የአሕዛብ ነገዶች ዘንድ ከበሬታን ያጎናጽፈዋል። በዚህ መንገድ የሮማ መንግስት በፈራረሰ ጊዜ ሳትፈርስ ጸንታ የቆመችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የባቢሎን ሚስጥራት ሾልከው ገቡ። በአገዛዙ እንደ ብረት የጠነከረው (በብረት እግር የተመሰለው) የጨካኙ የሮማ መንግስት መንፈስ በባርቤሪያውያን እጅ በ476 ዓ.ም ተደመሰሰ። ከዚያ ወዲያ ግን በሮማ መንግስት ፍርስራሽ ላይ ከሙታን ተነስቶ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሆነ፤ የታሪክ ምሑራንም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ክርስትና የተነሳ ጣኦት አምልኮ ብለው ይገልጻሉ። ዳንኤል የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በአሕዛብ ምስሉ እግር ውስጥ እንዳሉ የብረት ስብርባሪዎች ነው ያያት። እግሮቹ የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክን ይወክላሉ። ይህንኑ ታሪክ ዮሐንስ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ብሎ ይገልጻል። በታሪክ ውስጥ በተለያዩ ዘመናት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አልፋለች።
በብሉይ ኪዳን ዘመናት ውስጥ የእግዚአብሔር ማዳን በሕግ እንዲኖሩ ለተባሉ አይሁዶች ተሰጥቷቸው ነበር። አሕዛብ የአይሁድን እምነት ካልተከተሉ በቀር መዳን አልተፈቀደላቸውም ነበር። እንደ ጥሩ ምሳሌ መጥቀስ የምንችለው የሳባ ንግስትን ነው፤ እርሷም ከሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ለመስማት ብላ ከአፍሪካ ተነስታ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች።
ስለዚህ የመዳን “ቀይ ክር” ከአሕዛብ ምስሉ ውጭ ነበረ፤ ምክንያቱም አይሁዶች ሕይወታቸውን የሚኖሩት ከአሕዛብ ተለይተው ነበር።
እግዚአብሔር ግን አይሁዶች ኢየሱስን በቀራንዮ እንደሚገድሉት አስቀድሞ አውቋል።
ስለዚህ በመስቀሉ እግዚአብሔር አዲስ እቅድ ጀመረ፤ እርሱም አዲስ ኪዳን ነው።
መዳን ከአይሁድ ወደ አሕዛብ ተሸጋገረ።
መዳን ወደ አሕዛብ ምስሉ በእግሮቹ በኩል ገባ።
ይህ ምስል መዳን ከአይሁድ እንደነበረ፣ ከአሕዛብ ውጭ እንደነበረ እና፤ ከዚያም በምስሉ እግሮች በኩል ወደ አሕዛብ እንደተሸጋገረ ያሳያል፤ እግሮቹ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
ዳንኤል 2፡41 እግሮቹና ጣቶቹም እኩሉ ሸክላ እኩሉም ብረት ሆኖ እንዳየህ፣ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግስት ይሆናል፤ ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ የብረት ብርታት ለእርሱ ይሆናል።
ሸክላው በውስጡ እርጥበት አለው።
ሸክላ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ነው የሚወክላት፤ ሸክላው ከምስሉ ውስጥ ሕይወት ሊያበቅል የሚችል ብቸኛው ክፍል ነው።
እርጥብ ሸክላ ምን ማለት ነው?
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት …
ኢየሱስ እኛ እንድናደርገው ያዘዘን እግር የማጠብ ስርዓት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያለችውን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን በሙሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን ውሃ በመታዘዝ እንዴት እንደምትነጻ ይገልጻል።
ለዚህ ነው ጴጥሮስ እጆቹን እና ራሱን ሊታጠብ ያልቻለው። ባቢሎን፣ ፋርሶች፣ እና ሜዶናውያን ከብዙ ዓመታት በፊት አልፈዋል። መንግስታቸውም ከምድር ገጽ ላይ ጠፍቷል። ስለዚህ ወደ ፊት ሊገለጡ ያላቸው ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክሉ እግሮች ብቻ ነበሩ ከአለማመን እና ከሐጥያት በእግዚአብሔር ቃል ሊታጠቡ የቻሉት። ጴጥሮስ አይሁድ እንደመሆኑ በሰዓቱ ይህን ሚስጥር ሊገነዘብ አልቻለም፤ ምክንያቱም አሕዛብን ይንቅ ነበር። ነገር ግን አሕዛብ ለሆነው ለቆርኔሌዎስ ሊመሰክር በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር እርኩስ የነበሩ እንስሳት አሁን ንጹህ መሆናቸውን በራዕይ ሶስት ጊዜ አሳየው። ይህን ያደረገው የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ኃይል ነው። የተናቁት እና እርኩስ የነበሩ አሕዛብ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል።
ሸክላው መጽሐፍ ቅዱስን የምታምነዋን ቤተክርስቲያን ይወክላል። የብረት ስብርባሪዎች ደግሞ ዲኖሚኔሽናዊቷ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት፤ እርሷም አሁን ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልካ በመግባት በፓስተሮች አመለካከት እና በሰው መሪነት ስር ወደ ባርነት እየመራቻቸው ነው። ፓስቶሮቹ ከሚከተሉት ልዩ ልዩ አመለካከት ብዛት የተነሳ ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽኖች አሉ።
በቅርብ እጅ ሳይነካው በሚመጣው ድንጋይ አማካኝነት 10ሩ የእግር ጣቶች ሲደመሰሱ ማለትም ጌታ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ነጥቆ ሊወስዳት ሲመጣ ይህ ሁሉ መንፈሳዊ አረንቋ ይጠፋል። በዚያ ጊዜ ቀሪዎቹ ቤተክርስቲያን ተመላላሽ ሰዎች ይህ ሁሉ በክፋት የተሞላ የዚህ ዓለም ሥርዓት ወደሚጠፋበት ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ።
10ሩ የእግር ጣቶች ወታደራዊ ኃይላቸውን ለመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ የሚሰጡ እና ዓለምን እንዲገዛ የሚያግዙት 10 ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ናቸው።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
እንደ ነገስታት ስልጣን። መንግስትን ያልተቀበሉ፤ ዘውድ ያልጫኑ ናቸው ነገር ግን እንደ ነገስታት ስልጣን አላቸው። እነዚህ ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።
ኮቪድ-19ን ቻይና ውስጥ በጥቂት ወራት ተቆጣጥረውታል፤ ይህንም ሊያደርጉ የቻሉት በፈላጭ ቆራጭነታቸው ነው። ሕዝቡ እቤት አንቀመጥም ቢሉ የቤታቸውን በር በይደው ያሽጉባቸዋል። ቻያናዎች መንግስታቸው ሙሉ በሙሉ አምባገነን እና አፋኝ ጨቋኝ ነው። እንዲህም ሆኖ ግን ኮሮና ቫይረስን ማስወገድ ችሏል። አውሮፓ እና አሜሪካ ግን ዴሞክራሲያዊ መንግስታት በመሆናቸው በጣም ጨቋኞች አይደሉም፤ ኮሮና ቫይረስም በሃገራቸው ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ተሰራጨ።
ስለዚህ አስቸኳይ አደጋ ባለበት ሰዓት አዋጪው የመንግስት አይነት ፈላጭ ቆራጭ መንግስት መሆኑን 2020 ዓ.ም አሳይቶናል።
ስለዚህ በዓለም ዙርያ ወደፊት የፈላጭ ቆራጭነት መንፈስ እየጨመረ ይሄዳል።
አውሮፓ ውስጥ አሁን ብቸኛው ፈላጭ ቆራጭ ፖፑ ነው።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
ወደ ኢየሱስ የሚመጡ ሰዎች ለጥሪያቸው ታማኝ መሆን አለባቸው።
ይህም ጥሪ በቃሉ ውስጥ የሚጠራን የእግዚአብሔር ድምጽ ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
በ1769 በጥንቃቄ ታርሞ የተዘጋጀው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ስሕተት የሌለበት ፍጹም መመሪያችን ነው። የኢየሱስን ሃሳብ በሙሉ ይነግረናል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አገኘንበት የምትሉ ከሆነ በኢየሱስ አስተሳሰብ ውስጥ ስሕተት አገኘን ማለታችሁ ነውና በክርስቶስ ሙሽራ አካል የመሆን እድል ፈንታ የላችሁም።
ማቴዎስ ምዕራፍ 16 ውስጥ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጥቶታል። በኋላ ግን ባለማስተዋል ኢየሱስን እየተቃወመ ተናገረ። ኢየሱስም ጴጥሮስን ሰይጣን አለው።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ስትቃወሙ ምን መሆናችሁ ነው?
ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተጻፈው ለእያንዳንዱ ቃል ታማኝ መሆን አለብን።
ምሳሌ 30፡5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤
አትርሱ። መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አይደለም።
እግዚአብሔር ሰዎችን እንደ ጸሐፊ ነው የተጠቀመባቸው፤ የተጻፉት ሃሳቦች ግን ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ነው የመነጩት።
ደግሞም እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እንግሊዝኛ በሰው ጥበብ ዘመን የተረጎሙትን ሰዎች በትክክል እንዲተረጉሙ ጥበብን በመስጠት መርቷቸዋል።
አሁን በምንኖርበት የንስር ዘመን የተሰጠን ሥራ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃሎች መተርጎም ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት መረዳት ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ በዙፋኑ ዙርያ ስላሉ አራት ሕያዋን ፍጥረታት ወይም ክቡር ዘበኞች ተጽፏል።
ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
ዓይኖች ማስተዋልን ይወክላሉ።
እነዚህ መናፍስት ወደፊት የሚሆነውን ያውቃሉ (ከመሆኑ በፊት ቀድመው ማየት ይችላሉ) ደግሞም ከዚህ በፊት የሆነውን በሙሉ ያውቃሉ። በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሰይጣን ለማታለል እና ለማስመሰል ያደረገውን ነገር ሁሉ ሚስጥሩን ያውቁበታል።
በጣም ብዙ ያውቃሉ። ስለዚህ ማንም ሊያታልላቸው አይችልም።
ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
የአንበሳው ዘመን የቃሉን እውነት አየ፤ የቃሉ እውነትም የይሁዳ ነገድ አንበሳ ነው፤ ያም ዘመን በሐዋርያት የተሰበከውን እና የተጻፈውን ቃል አይቷል።
የጥጃው ዘመን ከ312 እስከ 1520 ዓ.ም ድረስ የዘለቀውን የ900 ዓመታት የጨለማ ዘመን ይወክላል፤ በዚያም ዘመን በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት የስላሴ አስተምሕሮ ወደ ቤተክርስቲያን ከገባ በኋላ ከአስር ሚሊዮን በላይ ቅዱሳን ተገድለዋል። ጥጃው ወደ ብርቱ በሬነት ለማደግ ረጅም ጊዜ አግኝቷል። በአደባባይ በእንጨት ላይ ታስረው ሲቃጠሉ መከራውን ለመቋቋም ብርታት ያስፈልጋቸው ነበር።
በሰው ዘመን ውስጥ ከ1520 እስከ 1906 ድረስ የሰው ጥበብ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተባረከ።
ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር መዳን በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ።
እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ቅድስናን እና የወንጌል ስርጭትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ በማምጣቱ ታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት ሊጀመር ችሏል።
ታላላቅ ሰዓሊዎች፣ ቀራጺዎች፣ ሙዚቀኞች፣ ገጣሚዎች፣ እና ደራሲዎች ተነስተዋል። ከሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ሁሉ በውበት አንደኛ የሆነው እንቁ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ በ1604 ተጀምሮ በ1611 ተጠናቅቆ ታተመ፤ ከዚያም በኋላ በ1769 ዓ.ም እንደገና በጥንቃቄ ተመርምሮ አጻጻፉ ዘመናዊ እንግሊዝኛ እንዲሆን ተደርጓል። ከዚያ በኋላ ለዓለም አቀፉ የወንጌል ስርጭት ዘመን የጀርባ አጥንት ሆኖ አገልግሏል።
ከ1947 እስከ 1965 ዓ.ም አሜሪካ ውስጥ ዊልያም ብራንሐም በንስ ዘመን አስደናቂ እይታ አማካኝነት ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ገልጧል። ስለዚህ አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ተምሳሌቶች እና ሚስጥራት ምን ማለት እንደሆኑ መረዳት እንችላለን። በዚህም መንገድ የጥንቷ በአንበሳው ዘመን የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ታምን ወደ ነበረችበት እምነት መመለስ እንችላለን።
ይህም ሁሉ የሚሆነው ፍሬው ከተክሉ ላይ የሚታጨድበት የመከር ወቅት እየደረሰ ስለሆነ እንድንዘጋጅ ነው። የመጨርሻው ዘመን ሙሽራ ጌታ በአየር ላይ ለመቀበል እንደ መከር ከምድር ላይ ታጭዳ ወደ ሰማይ ትነሳለች።
መከሩ የሚመጣው በስተመጨረሻ የሚታጨደው ፍሬ ልክ መጀመሪያ የተዘራውን ዘር በሚመስልበት ጊዜ ነው።
በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚኖሩ አማኞች እምነታቸው ልክ እንደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አማኞች መሆን አለበት።
እኛ ልክ እንደ ጥንቶቹ ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለብን።
ሳይንቲስቶች ስለ አተም ያላቸው እውቀት ጨምሯል፤ ቴክኖሎጂም መጥቋል። ልክ እንደ ንስር ሰው አየሩን በአውሮፕላን አቋርጦታል።
ዳንኤል የጻፈው ሚስጥር እስከ መጨረሻው ዘመን ታትሞ እንደተዘጋ ጽፏል።
ዳንኤል 12፡4 ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።
ዮሐንስ ደግሞ እነዚህን የመጽፍ ቅዱስ ሚስጥራት ማን እንደሚገልጥልን ነግሮናል። የሚገልጥልን ለሰባተኛው እና ለመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የተላከው መልአክ ወይም መልእክተኛ ነው።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
በእውነትም ዮሐንስ እና ዳንኤል በብዙ ዘመናት ተለያይተው ቢኖሩም እንኳ በመልእክቶቻቸው ግን ተባብረው በአንድነት ሰርተዋል።