ዳንኤል 9፡27 ኪዳን ያደረገው ማነው? እግዚአብሔር ወይስ የክርስቶስ ተቃዋሚ? የቀሩት ዓመታት 7 ወይም 3½?



First published on the 22nd of April 2021 — Last updated on the 22nd of April 2021

አይሁዶች ባቢሎን ውስጥ ተማርከው ከቆዩ በኋላ የተመለሱበትን ሁኔታ በአጭሩ እንመልከት።

የፋርስ ንጉስ ቂሮስ አይሁዶች ቤተመቅደሱን በ536 ዓመተ ዓለም እንዲሰሩ ፈቀደ።

ኢያሱ እና ዘሩባቤል መሰረቱን ጣሉ፤ ከዚያ በኋላ ጠላቶቻቸው ለ17 ዓመታት አስቆሟቸው።

በስተመጨረሻ የፋርስ ንጉስ ዳርዮስ ቤተመቅደሱን ሰርተው እንዲጨርሱ ፈቀደላቸው፤ እነርሱም በሐጌ እና በዘካርያስ ትንቢት እየተበረታቱ በ516 ዓመተ ዓለም ሰርተው ጨረሱ። ሁለተኛው ቤተመቅደስ ተሰርቶ ተጠናቀቀ።

56 ዓመታት ካለፉ በኋላ በንጉስ አርጤክስስ የመጀመሪያ ዓመት ማለትም ከ460 – 459 ዓመተ ዓለም አካባቢ ዕዝራ የቤተመቅደሱን እቃዎች ወደ ቤተመቅደሱ ይዞ መጣ። በዚህ ጊዜ ቤተመቅደሱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ነበር።

ዕዝራ የ5ኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ ማርቲን ሉተርን ይወክላል፤ ሉተር ወደ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መልሶ አምጥቷል (ከሐጥያታችን ንሰሐ ስንገባ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በማመን እንድናለን)። የጻድቃን ሰማዕታትን ምስል ማምለክ እን በመልካም ስራ መዳን የሚባሉ ቆሻሾች ሁሉ ከአዲሲቷ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠርገው ተወገዱ።

ከዚያም 13 ዓመታት ካለፉ በኋላ ነህምያ በ52 ቀናት ውስጥ የኢየሩሳሌም አጥር ሰራ።

በዚያ ዘመን አንድ ከተማ ከተማ የሚባለው በሕንጻዎቹ ዙርያ ጠንካራ ግምብ አጥር ካለ ብቻ ነው። ይህ ግምብ አጥር በከተማው ውስጥ ለሚኖሩት ሰዎች ብርታታቸው ነው፤ ለሕዝቡ ጥበቃም ጭምር ነው።

ነህምያ የ6ኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ ጆን ዌስሊ ይወክላል፤ ጆን ዌስሊ ቅድስና እና የወንድማማች መዋደድ እንዲሁም የወንጌል ስርጭት የተባሉትን ታላላቆቹን የክርስትና ግምብ አጥሮች ሰርቷል። ይህም ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲጀመር ታላቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ዌስሊ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ተቀብሏል፤ ይህም ልምምድ በ1738 ዓ.ም ዌስሊ “የሮሜ መልእክት መግቢያ” የሚለውን የማርቲን ሉተርን መጽሐፍ እያነበበ ሳለ ልቡ ውስጥ “ለየት ያለ ሙቀት” እንዲሰማው አድርጎታል።

በ1739 ዌስሊ ቤተክርስቲያን ለማይሄዱ ሰዎች ውጭ ሜዳ ላይ በሚደረገው አገልግሎት ከጆርጅ ዊትፊልድ ጋር ተባበረ።

ዌስሊ ከቤተክርስቲያን ውጭ ሜዳ ላይ ለ52 ዓመታት ሰብኮ ከዚያ በኋላ በ1791 ሞተ።

ዌስሊ ትኩረት ያደረገው አምኖ በጸጋ ስለ መዳን እና በቅድስና ስለመኖር ነው። ከቤተክርስቲያን ውጭ ስላሉ ሐጥያተኞች ልቡ ይቃጠል ነበር።

ከዚያም በ1792 ዊልያም ኬሪ የእንግሊዝ ባፕቲስት ሚሽነሪ ሶሳይቲ የሚባለውን አገልግሎት ጀመረና ከ1793 ጀምሮ ቀሪ ዕድሜውን ሕንድ ውስጥ አሳለፈ። ይህንም ተከትሎ ወርቃማው የፊልደልፊያ ወይም የወንድማማች መዋደድ የወንጌል ስርጭት ዘመን ተጀመረ። ይህ የወንድማማች መዋደድ ወንጌልን ወደ አሕዛብ ይዞ መሄድን በዚያውም ራስን ለሞት አደጋ ማጋለጥን ያካትታል፤ ብዙውን ጊዜ ሰባኪዎች በሄዱበት የምድር ወገብ አካባቢ በሽታዎች ባይገድላቸው እንኳ ሕዝቡ ይገድሏቸው ነበር። ይህን ያህል የተሰጡ ነበሩ።

 

 

ትንቢቶችን ስናጠና የሚከተሉትን እውነታዎች ማሰብ አለብን።

አንድ ቀን አንድን ዓመት ሊወክል ይችላል።

የትንቢት ወይም የአይሁድ አንድ ዓመት ርዝመቱ 360 ቀናት ነው።

እያንዳንዱ 70 የአይሁድ ዓመት በእኛ በአሕዛብ አቆጣጠር 69 ዓመት ነው።

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

ሳምንት ወይም ሱባኤ ማለት 7 ዓመት ነው፤ ስለዚህ በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመት ነው።

ነገር ግን እነዚህ እውነታዎች በባለ 360 ቀኑ የአይሁድ ዓመት ውስጥ እንጂ በባለ 365.24 ቀኑ የአሕዛብ ዓመት ውስጥ አይሰሩም።

ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።

3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።

1,260 ቀናት = 42 ወራት። ስለዚህ 1 ወር = 30 ቀናት።

ዳንኤል 9፡24 … በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።

በየዓመቱ እኛ አሕዛት 5.2422 ትርፍ ቀናት አሉን።

ስለዚህ በ69 ዓመታት ውስጥ እኛ አሕዛብ 5.2422 x 69 = 361.7 ትርፍ ቀናት ይኖሩናል፤ ይህም አንድ ባለ 360 ቀናት የአይሁድ ዓመት ይሞላል።

[99.5% ትክክለኛ በሆነ ስሌት ሲታሰብ በ70 የአይሁድ ዓመታት ውስጥ 1.7 ትርፍ ቀን ማግኘት ማለት በ490 ዓመታት ውስጥ ከሁለት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ ብቻ ማትረፍ ነው። ስለዚህ ትንሽ ስሕተት በዚህ ጥናት ውስጥ ያሉትን ዓመታት ቁጥር በምናሰላበት ጊዜ የጎላ ችግር አያመጣም።]

በ70 የዓይሁድ ዓመታት ውስጥ እኛ 69 ዓመታት ይኖረናል።

ስለዚህ በ490 የአይሁድ ዓመታት ውስጥ እኛ 490/70 = የእኛ የአሕዛብ ዓመታት በ7 ዓመት ያንሳሉ።

የአይሁድ 490 ዓመታት 490 – 7 = 483 የአሕዛብ ዓመታት።

ስለዚህ አይሁዶች 483 የአሕዛብ ዓመታት ይቀሯቸዋል።

 

እነዚህ 483 ዓመታት ወደ ኋላ መቆጠር የሚጀምሩት ከመች ጀምሮ ነው?

 

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

የኢየሩሳሌም አጥር እንደገና እንዲሰራ ይህንን ትዕዛዝ የሰጠው ማነው?

ልብ በሉ። አጥሩ እንዲሰራ ይህ ትዕዛዝ ከመውጣቱ 70 ዓመታት አስቀድሞ ነው ቤተመቅደሱ የተሰራው።

አንድ ቦታ ከተማ ተብሎ የሚቆጠረው በዙርያው ግምብ አጥር ሲኖረው ብቻ ነበር።

ኢየሩሳሌምም ከተማ እንድትባል በፈረሰው አጥሯ ምትክ አዲስ አጥር ያስፈልጋት ነበር።

ነህምያ 2፡1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ ግን በፊቱ ያለ ኃዘን እኖር ነበር።

ነህምያ 2፡5 ንጉሡንም፦ ንጉሡን ደስ ቢያሰኝህ፥ ባሪያህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ እሠራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባቶቼ መቃብር ከተማ ስደደኝ አልሁት።

ነህምያ ኢየሩሳሌምን እንደ ከተማ አድርጎ ሊሰራት የሚችለው አጥሯን ከሰራ ብቻ ነው። አጥሯ ነው ከተማ የሚያደርጋት።

አርጤክስስ የነገሰው መች ነው? በ465 ዓመተ ዓለም

የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ቀዳማዊ - ዊኪፔድያ (Wikipedia)

en.wikipedia.org › wiki › Artaxerxes_I_of_Persia

የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ቀዳማዊ

አርጤክስስ ቀዳማዊ የአካሜኒድ መንግስት ስድስተኛው ንጉሰ ነገስት ነበረ፤ የነገሰውም ከ465 – 424 ዓመተ ዓለም ነው።

የነገሰበት 20ኛ ዓመት መች ነበረ?

ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ ቀዮቹ ቁጥሮች አርጤክስስ የነገሰባቸውን ዓመታት ያመለክታሉ።

 

 

ስለዚህ በእኛ የዘመን አቆጣጠር የአርጤክስስ 20ኛ ዓመት በ446 ዓመተ ዓለም ነው።

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

የመጀመሪያዎቹ 69 ሳምንታት (69 x 7 = 483 የአይሁድ ዓመታት) በሁለት ክፍለ ጊዜዎች ተከፍለዋል።

ዶ/ር እስኮፊልድ እንደጻፈው ሚልክያስ የተነበየው በ397 ዓመተ ዓለም ነው።

 

 

ስለዚህ ከ446 እስከ 397 ዓመተ ዓለም አይሁዶች 7 ሳምንታት ነበሯቸው (7 x 7 = 49 የአይሁድ ዓመታት) በእነዚያም ዓመታት ነብይ መጥቶ ይናገረናል ብለው መጠበቅ ይችላሉ።

ከዚያ በኋላ 62ቱ ሳምንታት ተከትለው ይመጣሉ (62 x 7 = 434 የአይሁድ ዓመታት) በእነዚህም ዓመታት ውስጥ ነብይ አልተነሳም።

ነብይ ያልተሳበት ዘመን ያበቃው መጥምቁ ዮሐንስ በ29 ዓ.ም በተገለጠ ጊዜ ነው።

ዮሐንስ 29 ዓ.ም ማለቂያ አካባቢ 30 ዓ.ም ሊገባ ትንሽ ሲቀረው ኢየሱስን አጠመቀ።

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ካጠመቀበት ጊዜ ጀምሮ ዓመታቱ 49 + 434 = 483 የአይሁድ ዓመታት ይሆናሉ።

ይህም እኩል ይሆናል 483 – 7 = 476 የአሕዛብ ዓመታት።

446 ዓመተ ዓለም ሲደመር 30 ዓ.ም = 476 ዓመታት።

ስለዚህ በ30 ዓ.ም አካባቢ የተከሰተ ነገር ይኖር እንደሆን መጠየቅ አለብን።

ሉቃስ 3፡1 ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥

ዓመታት የሚቆጠሩት ከሮማ ገዥ ንግስና ጋር ተያይዞ ነበር። አውግስጦስ ቄሳር በ14 ዓ.ም ሞተ ከዚያም በኋላ ወዲያው እርሱ በማደጎ ያሳደገውን ልጁን ጢባርዮስን ምክር ቤቱ ገዥ ወይም ቄሳር አድርጎ ሾመ።

አውግስጦስ - ዊኪፔድያ

en.wikipedia.org › wiki › Augustus

 

የቄሳር አልጋ ወራሽ -

አውግስጦስ (Imperator Caesar Divi filius አውግስጦስ፡ መስከረም 23 ዓመተ ዓለም - ነሐሴ 19 ቀን 14 ዓ.ም) ሮማዊ ባለ ስልጣን እና ወታደራዊ መሪ የነበረ ሰው ሲሆን የመጀመሪያው የሮማ መንግስት ንጉሰ ነገስት በመሆን ከ27 ዓመተ ዓለም እስከ ሞተበት ቀን እስከ 14 ዓ.ም ነግሷል።

 

የጢባርዮስ 15ኛ ዓመት ማለት 14 + 15 = 29፤ ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን የጀመረው በ29 ዓ.ም ነው።

በዚያም ዓመት መጨረሻ አካባቢ ኢየሱስን አጠመቀ። የ29 ዓ.ም ወራት እያለቀ ስለነበረ ጊዜው የ30 ዓ.ም መግቢያ ነበር።

ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር

ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ዮርዳኖስ መጥቶ በተጠመቀ ጊዜ ዓመቱ የ69ኛው ሱባኤ መጨረሻ ነበረ።

አንድ ሱባኤ ብቻ ቀርቶ ነበር።

የቀረው አንድ ሱባኤ ማለት 7 ዓመት ነው።

በሴት ማሕጸን ውስጥ የሕይወትን ዘር የሚያስቀምጥ ሁሉ የሕጻኑ አባት ነው።

ይህንን ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።

በሌላ አነጋገር መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው፤ እርሱም ለራሱ ማደሪያ መኖሪያ የሚሆን ስጋዊ አካል እያዘጋጀ ነበር።

በስጋ አካል ሰው ሆኖ የተገለጠው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። (መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ እንኳ “እግዚአብሔር ወልድ” አይልም)።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” ተብሎ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።

እግዚአብሔር “እግዚአብሔር አብ” ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር የሚኖርበት ሰብአዊ “የእግዚአብሔር ልጅ” ሲኖር ብቻ ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

መንፈስ ቅዱስ እንዴት በኢየሱስ ላይ ቅባት ሆኖ እንደ ወረደበት ልብ በሉ። መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሱ ውስጥ አልገባም።

ሉቃስ 3፡22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው። ስለዚህ በአደባባይ ሊቀባው በወረደ ጊዜ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ነው አጽንኦት ሰጥቶበት የተናገረው።

አለቃው መሲህ።

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ

መሲህ ማለት የተቀባ ነው።

አለቃ ማለት የንጉስ ልጅ ነው።

በ3½ አገልግሎቱ ማብቂያ ላይ ኢየሱስ በ33 ዓ.ም ኢየሱስ እንደ ንጉስ ሆኖ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ስለዚህ አለቃው መሲህ የሚለው ቃል የሚናገረው ስለዚያ ቀን አይደለም።

ዘካርያስ 9፡9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

ማቴዎስ 21፡5 ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤

መጥምቁ ዮሐንስ በ29 ዓ.ም ነብይ ሆኖ ብቅ አለ።

በዚያም ዓመት ማለቂያ አካባቢ 30 ዓ.ም ሊጀምር ሲቀርብ ኢየሱስ ተጠምቆ በአደባባይ አለቃው መሲህ ማለትም የንጉሱ “ልጅ” ሆኖ ተቀባ።

1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።

 

ዳንኤል 9፡26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤

ኢየሱስ ተጠመቀ፤ ማለትም ከዚያን ቀን ጀምሮ አይሁዶች አንድ ሱባኤ ወይም 7 ዓመታት ብቻ ቀራቸው።

ነገር ግን በሱባኤው እኩሌታ ከ3½ ዓመት አገልግሎት በኋላ ተገደለ።

ወደ ፊት በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ለአይሁዶች የሚቀራቸው 3½ ዓመት ይፈጸማል።

 

 

ያለ ነብይ 62 ሱባኤዎችን ካሳለፉ በኋላ መጥምቁ ዮሐንስ የተባለ ነብይ በ29 ዓ.ም ብቅ አለ፤ ኢየሱስም በ29 ዓ.ም ወደ 30 ዓ.ም መግቢያ አካባቢ አገልግሎቱን ጀመረ። ከዚያም 3½ ዓመታት በኋላ አገልግሎቱ ተቋረጠ።

ሮማዊው ጀነራል ቬስፓሲያን በ66 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን እንዲያምበረክክ በንጉሱ ኔሮ ተልኮ ነበር።

ወደ 69 ዓ.ም ማለቂያ አካባቢ ቤስፓሲያን የሮማ ገዥ ሆኖ የተሾመ ጊዜ እሥራኤልን ትቶ ሄደና ልጁን ጀነራል ታይተስን በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን እንዲያንበረክክ አዘዘው። ስለዚህ ታይተስ አባቱ በ70 ዓ.ም የሮም ገዥ ስለሆነ እርሱ አለቃ ነበር። የሮማ ጀነራል እና አለቃ የሆነው ታይተስ ቤተመቅደሱን እና ከተማይቱን አፈራርሶ 1,100,000 አይሁዶችን ገደለ፤ 90,000 አይሁዶችን ባርያ አደረገ።

“የሚመጣው አለቃ ሕዝብ”።

የኢየሩሳሌምን ከተማ በ70 ዓ.ም ያፈረሱት ሮማውያን ናቸው። ስለዚህ በዘመን መጨረሻ የሚነሳው የክርስቶስ ተቃዋሚም ሮማዊ፣ የሮማ ካቶሊክ ነው የሚሆነው።

ካቶሊኮች ጴጥሮስ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን የመሰረቷት የሐዋርያት አለቃ ነበር ይላሉ።

ፖፑ “የሐዋርያት አለቃ ተወካይ” (Vicar of the Prince of the Apostles) ይባላል። ከዚህም የተነሳ ፖፑ በጴጥሮስ ቦታ ስለሚቆም ፖፑ አለቃ ይሆናል። (Vicar ማለት በአንድ ሰው ምትክ ማለት ነው)።

ስለዚህ “የሚመጣው አለቃ” ሮማዊ ነው የሚሆነው፤ ማለትም የሮማ ካቶሊክ ፖፕ።

 

ኢየሱስ የ3½ ዓመት አገልግሎት አገልግሏል።

ይህን ለማረጋገጥ የዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የተጻፉትን በዓላት መመልከት አለብን።

የ3½ ዓመታት አገልግሎት ለማገልገል ኢየሱስ አራት የፋሲካ በዓሎች ላይ መገኘት አለበት።

ፋሲካ ብዙውን ጊዜ በሚያዚያ ወር ነበር የሚከበረው።

ስለዚህ ኢየሱስ ጥቅምት ወር 29 ዓ.ም አካባቢ ተጠምቆ ከሆነ ጊዜው ከፋሲካ 6 ወራት ያህል ቀደም ብሎ ነበር ማለት ነው።

ዮሐንስ 2፡13 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ (30 ዓ.ም)

ዮሐንስ 13፡1 ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ … (33 ዓ.ም)

 

 

ዮሐንስ 6፡4 የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር (32 ዓ.ም)

ለ31 ዓ.ም ያልተጠቀሰ አንድ ፋሲካ አለ።

ፋሲካ ሁልጊዜ የአይሁድ ዓመት የመጀመሪያ በዓል ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ማንኛውም ሌላ በዓል ላይ መገኘቱ ተጽፎ ከሆነ ፋሲካ ከዚያ ቀን ቀድሞ አልፏል ማለት ነው።

ዮሐንስ 4፡35 እናንተ፦ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል …

የገብስ መከር ሚያዚያ ውስጥ ነው። የስንዴ መከር ደግሞ ግንቦት ውስጥ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ከሳምራውያን ጋር ሲነጋገር የነበረው በክረምት ታህሳስ አካባቢ ነው።

ዮሐንስ 5፡1 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ …

በዓሉም የትኛው በዓል እንደሆነ ተጽፏል። ነገር ግን የፋሲካ በዓሉ ከሁሉም በዓላት ቀድሞ ነው የሚመጣው። ስለዚህ ይህ ሌላ በዓል ቢሆን የ31 ዓ.ም ፋሲካ ከዚህ በዓል ቀድሞ ተከብሮ አልፏል ማለት ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ በአራት ፋሲካዎች ላይ ተገኝቷል።

ይህም አገልግሎቱ ለ3½ ተኩል እንደነበረ ማረጋገጫ ነው።

የሞተው በ33 ዓ.ም ነው።

 

ስለዚህ ኢየሱስ በ29 ዓ.ም ማለቂያ አካባቢ አገልግሎቱን ሲጀምር አይሁዳውያን 7 ዓመታት (አንድ ሱባኤ) ይቀራቸው ነበር።

ኢየሱስ የሰባት ዓመታት አገልግሎቱን ቢጨርስ ኖሮ የ1,000 ዓመቱን የሰላም መንግስት ወዲያው ይመሰርት ነበር።

ነገር ግን ከ3½ ዓመት በኋላ ተገደለ፤ በ33 ዓ.ም የተገደለበትም ጊዜ የመጨረሻው ሱባኤ እኩሌታ ነበር።

ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤

በሱባኤው እኩሌታ ሲገደል የብሉይ ኪዳን ሕግ ከመስዋእቶቹ ጋር አበቃ።

ሌዋውያን 10፡6 ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን፦ እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ራሳችሁን አትንጩ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤

ሕጉ ሊቀካሕናቱ አሮን (እንዲሁም በሊቀካሕናትነት የሚከተሉት ልጆቹ) ልብሱን መቅደድ እንደማይፈቀድለት ይገልጻል።

ሊቀካሕናቱ ቀያፋ ግን ኢየሱስን እየመረመረው በነበረበት ሰዓት ልብሱን ቀደደ።

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል … አለ።

በዚህም ምክንያት ሕጉ አከተመ።

እግዚአብሔርም የቤተመቅደሱን ውስጠኛ መጋረጃ በመቅደድ ምላሽ ሰጠ።

ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥

ስለዚህ የቤተመቅደሱ ሕግ እና መስዋእቶቹ በቀራንዮ መስቀል አበቁ።

ኢየሱስ ሲሞት መንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደሱን ለቆ ወጣ፤ ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ለመጀመር የበዓለ ሃምሳ ዕለት ወረደ። የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚጠናቀቀው በንጥቀት ነው፤ በዚያን ጊዜ ቤተክርስቲያን ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ትነጠቃለች።

 

 

በዚያ ጊዜ ኢየሱስ ከምሕረት ዙፋን ላይ ስለሚነሳ ከዚያ በኋላ ለሐጥያተኛ አሕዛቦች በታላቁ መከራ ውስጥ ምሕረት አይኖርም።

እግዚአብሔር ግን ለአይሁዳውያን ምሕረት ያደርጋል ምክንያቱም 70 ሱባኤ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶ ነበር፤ ከሰባውም ሱባኤ ውስጥ ያልተጠቀሙበት የአንድ ሱባኤ እኩሌታ ወይም 3½ ዓመት ይቀራቸዋል። በዚያ ጊዜ ውስጥ ነው ሙሴ እና ኤልያስ 144,000ዎቹን አይሁዶች በመጥራት ከመሲሃቸው ከኢየሱስ ጋር የሚያስተዋውቋቸው።

ስለዚህ የ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሚስጥር በሁለቱ የሰባኛው ሱባኤ እኩሌታዎች መካከል መግባታቸው ነው።

እነዚህ ሁለቱ የሱባኤ እኩሌታዎች በ2,000 ዓመታት ያህል ተለያይተዋል።

ስለዚህ የቤተክርስቲያን ዘመናት በሰባኛው ሱባኤ ሁለት እኩሌታዎች መካከል “አካፋይ ዘመን” ናቸው።

 

ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤

ይህ ጥቅስ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።

በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው መረዳት የሚከተለው ነው።

ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚ በታላቁ መከራ ውስጥ ምድርን ለ7 ዓመታት ይገዛል ይላሉ፤ በዚያም ጊዜ አይሁዶች ቤተመቅደሱን እንደገና እንዲሰሩ ለመፍቀድ ከእነርሱ ጋር ቃልኪዳን ያደርጋል።

ከዚያ በኋላ በ7ቱ ዓመታት አጋማሽ ላይ እራሱን እንደ እግዚአብሔር አድርጎ ቤተመቅደሱ ውስጥ በመቀመጥ ቃልኪዳኑን ያፈርሳል ይላሉ። ከዚያም በኋላ ቀሪው የታላቁ መከራ ግማሽ ዘመን በጣም የከፋ ይሆናል። የታላቁ መከራ የመጀመሪያ አጋማሽ ብዙም አስጨናቂ አይደለም ይላሉ።

የታላቁ መከራ የመጀመሪያ አጋማሽ ብዙም አያስጨንቅም የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

“እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃልኪዳን ለአንድ ሱባኤ ያደርጋል”።

ቃልኪዳን አያደርግም። ይህን ቃልኪዳን ጽኑ ያደርገዋል ወይም ያጸናዋል እንጂ።

ይህም ቃልኪዳኑ ከዚያ አስቀድሞ ተደርጎ እንደነበረ ያመለክታል።

ቤተክርስቲያኖች ይህንን መመለስ አይችሉም ምክንያቱም የክርስቶስ ተቃዋሚ መጀመሪያ ቃልኪዳን ማድረግ ከዚያም ቃልኪዳኑን ለ7 ዓመታት ማጽናት ካለበት በምድር ላይ ከ7 ዓመት በላይ መቆየት ግድ ሊሆንበት ነው።

የክርስቶስ ተቃዋሚ በምድር ላይ ከ7 ዓመታት በላይ እንደሚቆይ የሚናገር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

ቃልኪዳኑን ከማጽናቱ በፊት መጀመሪያ ቃልኪዳን እንደሚያደርግ የተጻፈ ቃል የለም።

ቃልኪዳኑን ከ3½ ዓመት በኋላ የሚያፈርሰው ከሆነ ሊያጸናው አይችልም።

የጸና ቃልኪዳን ሊፈርስ አይችልም።

ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱ አፈታት ችግር አለበት።

 

መጽሐፍ ቅዱስ ቃልኪዳኑን ያፈርሳል አይልም። ያላለውን ነው እንዳለ ተቆጥሮ የተወሰደው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው መስዋእቱን ያስቀራል ነው።

 

ስለዚህ ቃልኪደኑ ለ7 ዓመታት ይጸናል፤ በዚያው ጊዜው ውስጥ ግን ከ3½ ዓመታት በኋላ የቤተመቅደሱ መስዋእት ይቋረጣል።

 

ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤

 

 

እግዚአብሔር ለአይሁዶች የ70 ሱባኤ ጊዜ ሰጥቷቸው ነበር ግን በ70ኛው ሱባኤ ውስጥ እኩሌታው ላይ እግዚአብሔር በቀራንዮ አማካኝነት የቤተመቅደሱ መስዋእቶች እንዲቋረጡ አደረገ።

ስለዚህ አይሁዶች መሲሁን በመግደላቸው የመጨረሻ 7 ዓመታቸውን በራሳቸው እጅ ያጡ ይመስላል።

ዳንኤል ግን እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ለ7 ዓመት እንዳጸናው ይናገራል።

ስለዚህ አይሁዶች ሙለውን 7 ዓመታቸውን ያገኛሉ፤ ነገር ግን 7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እስኪጠናቀቁ ድረስ መጠበቅ አለባቸው።

7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የመጨረሻውን ሱባኤ ለሁለት በመክፈል ሁለተኛውን የሱባኤውን አጋማሽ በብዙ ዓመታት ወደፊት ገፉት። አይሁዶች መሲሁን ሲገድሉ ራሳቸው ላይ ጥፋት አመጡ፤ ከዚያም በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሳቸው በሮማውያን እጅ ፈረሰ፤ ከዚህም የተነሳ መስዋእት እያቀረቡ መቀጠል አልቻሉም። አይሁዶች ይህን የተቋረጠባቸውን ፕሮግራም ወደፊት ይቀጥሉታል ግን የሚቀጥሉት በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ነው፤ ከእነርሱም መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት በታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

5ኛው ማሕተም እንደሚገልጸው አይሁድ በመሆናቸው ምክንያት የተገደሉት አይሁዶች በሰማይ ነጭ ልብስ ይሰጣቸዋል።

 

አንድ ሰው ቃልኪዳኑን ለ7 መታት ማጽናት እና በቤተመቅደስ ውስጥ መስዋእቶቹን ማስቆም አለበት።

ቃልኪዳኑን ኋላ የሚያፈርሰው ከሆነ ሊያጸናው አይችልም።

ይህን ሊያደርግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

እና ይህ ቃልኪዳን መች ነበር የተደረገው?

ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤

እግዚአብሔር ቃልኪዳን ያደረገው ከአብራም ጋር (ኋላ ስሙን አብራሐም አለው) እና ከመንፈሳዊ ዘሩ (ከክርስቶስ) ጋር ነው።

በፊት ዘሩ የሚለው ዘሮቹ ወይም አይሁዶች ማለት ይመስለን ነበር። ይህ ስሕተት ነው።

ቃልኪዳንን ስለ ማጽናት የሚናገር ሌላ ቃል አንድ ጊዜ ብቻ ይገኛል።

ገላትያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ።

ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፡- ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፡- ለዘርህም ይላል፣ እርሱም ክርስቶስ።

ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።

እግዚአብሔር ይህንን ቃልኪዳን የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር በሆነው በክርስቶስ አጸናው።

ቃልኪዳኑ ከአይሁዶች እና ዘግይቶ ከመጣው ሕግ ጋር አንዳችም የሚያያዘው ነገር አልነበረም።

አይሁዶች የእሥራኤልን ግዛት እስከ ኤፍራጥስ ድረስ አልተቆጣጠሩም፤ ነገር ግን በ1,000 ዓመት የሰላም መንግስት ጊዜ ይቆጣጠራሉ።

 

 

ስለዚህ በቀራንዮ የጸናው እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከመንፈሳዊ ዘሩ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን ምን ነበር?

የቤተመቅደሱ መስዋእቶች በሱባኤው እኩሌታ ቃልኪዳኑ በጸና ጊዜ መቋረጣቸውን ልብ በሉ። ቃልኪዳኑ አልፈረሰም።

ሕጉ ተሻረ ወይም አበቃ።

ነገር ግን ሕጉ ከቃልኪዳኑ ጋር ምንም የሚያያዘው ነገር የለውም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 15 ውስጥ የተደረገው ቃልኪዳን ምን ነበር?

እንዴት ነው ቀራንዮ ላይ የጸናው?

ቤተክርስቲያን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በሐዋርያት አገልግሎት አማካኝነት እውነቱን ተቀብላ ነበር ነገር ግን በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፋባት። ከዚያ በኋላ ሶስት የተሃድሶ ደረጃዎች ይመጣሉ። ይህም ለእግዚአብሔር አስቸጋሪ ወቅት ነበር ምክንያቱም ቤተክርስቲያንን ወደ ሐዋርያዊ እምነት ሊመልሷት የሚችሉ ሐዋርያት በምድር ላይ አልነበሩም።

7 ቅርንጫፎች ያሉት መቅረዝ ከበዓለ ሃምሳ ቀን ጀምሮ የኢዲስ ኪዳን መጻሐፍትን በጻፉት ሐዋርያት መሪነት ስር የነበረውን የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።

ሐዋርያት በነበሩ ጊዜ ቤተክርስቲያን መሆን የምትችለውን ያህል በጣም ጥሩ ነበረች።

ሐዋርያት የሰሩትን ስራ ማሻሻል አንችልም፤ የምንችለው ወደ እነርሱ ለመመለስ መሞከር ብቻ ነው።

 

 

ይህ የመጀመሪያዎቹን አራት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል፤ በዚህም ዘመን ውስጥ እውነት እየደበዘዘ ሄደ፤ በተለይም በሶስተኛው እና በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ።

 

 

አሁን ደግሞ የእውነትን ተሃድሶ እናያለን። እግዚአብሔር ትልቅ ትኩረት የሰጠበት ጉዳይ ይህ ነው።

5ኛ ዘመን። ሉተር ጀርመኒ ውስጥ ተነሳ። በእምነት መዳንን አስተማረ።

6ኛ ዘመን። ዌስሊ እንግሊዝ ውስጥ ተነሳ። ቅድስናን አስተማረ። የወንድማማች መዋደድ። ታላቁ የወንጌል ስርጭት የተደረገበትን ዘመን አስጀመረ።

7ኛ ዘመን። ጴንጤቆስጤያዊ መነቃቃት በአሜሪካ። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ተሃድሶ። ይህ ግን ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም።

 

 

ኢየሱስ እግዚአብሔርን በመንፈስ እና በእውነት ማምለክ እንዳለብን ተናግሯል።

7ኛ ዘመን ወደ 1ኛ ዘመን መመለሻ ነው።

ዊልያም ብራንሐም የመጀመሪያውን ሐዋርያት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የሰበኩትን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን ይመልሳል።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

 

 

ስለዚህ 5ኛ፣ 6ኛ፣ እና 7ኛ ዘመናት ሶስቱ ቁልፍ የሆኑ የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ዘመናት ናቸው፤ ቤተክርስቲያንም ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ትመለሳለች።

ዘፍጥረት 15፡9 እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው።

ሶስት ዓመት የሆናቸው ሶስት እንስሳት።

“ሶስት” የሚለው ሶስቱን (5፣ 6፣ እና 7) እውነት በተሃድሶ ተመልሶ የመጣባቸውን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል።

ሁለቱ ወፎች መዳንን እና ፈውስን ይወክላሉ። እነዚህም ሐጥያተኛ ሰው የሚያስፈልጉት ሁለት ታላላቅ ነገሮች ናቸው።

ዘፍጥረት 15፡10 እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልከፈለም።

እንስሳቱ እያንዳንዱ ለሁለት ተሰንጠቀው ግምሽ ግማሽ ትይዩ ተደርገው ነበር የተቀመጡት።

ይህም ፊት ለፊት እየተያዩ የተቀመጡትን የእግዚአብሔር ቃል ሁለት ግማሾች ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳንን ይወክላል፤ እነዚህ ሁለት ኪዳኖችም የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ መካከል ላይ ባሉት አራት ወንጌሎች ተለያይተዋል። በአራቱ ወንጌሎች ውስጥ ምን እየተከናወነ እንደነበር የሚያውቀው ኢየሱስ ብቻ ነበር።

ብሉይ ኪዳን ትርጉሙን የሚያገኘው በቀራንዮ ነው አዲስ ኪዳን ደግሞ ብርታቱና ጽናቱ የሚመነጨው ከቀራንዮ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ልጆም መዳን ያቀደው ሙሉው እቅድ በክርስቶስ ሕይወት እና ሞት ነው የተጠቀለለው።

ወፎቹ ለሁለት አልተሰነጠቁም።

መዳንን እና ፈውስን ከራንዮ መለየት አይቻልም። ሁለቱም ከቀራንዮ ይገኛሉ።

ቀራንዮ በጸጋ በእምነት አማካኝነት የሚገኘውን የእግዚአብሔር የማዳን መልካም ዜና ያለማቋረጥ የሚያሰራጭ ዋይፋይ ነው።

የይለፍ ቃሉን ካገኛችሁ በማንኛውም ጊዜ ከየትኛውም ቦታ ሆናችሁ የቀራንዮን የስርጭት ጣብያ ማግኘት ትችላላችሁ።

የይለፍ ቃሉ ከልብ የሆነ ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነው።

ዘፍጥረት 15፡11 አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።

አሞራዎች በመጀመሪያው ምሳሌ ውስጥ መንገድ ዳር የወደቀውን ዘር የበሉ ጠላቶች ናቸው፤ ይህም ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ የተጻፈው የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን የሚወክለው የዘሪው ምሳሌ ነው።

ማቴዎስ 13፡4 እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።

ሶስተኛው ምሳሌ ውስጥ ትንሽ ቁጥቋጦ ሆኖ በመቅረት ፈንታ ያለልክ የሚያድግ ዛፍ እናገኛለን። አሞራዎቹ (ጠላት) መጥተው ቅርንጫፎቹ ላይ ያርፋሉ፤ የዚህችንም የተደራጀች ቤተክርስቲያን የአመራር ስልጣን ይቆናጠጣሉ።

ቤተክርስቲያኒቱ በሽማግሌዎች የምትተዳደር የቤት ውስጥ ትንሽ ቤተክርስቲያን ሆና ብትቀር ይሻላት ነበር።

ነገር ግን የኒቅያ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የስላሴ ትምሕርት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የስቅለት አርብ እንዲሁም የተደራጀ ሐይማኖት፤ የሮም ጳጳስ የቤተክርስቲያኖች ራስ እንዲሆንና እንደ ክሪስማስ የመሳሰሉ ሰው ሰራሽ ሃሳቦች ትልቅ ድርጅት የሆነችዋን ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩዋት መንገድ ከፈተ።

ማቴዎስ 13፡31 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤

እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ትንሽ እንድትሆን ነበር የታሰበው፤ ይህም የስልጣን እና የገንዘብ ፍቅርን ለመከላከል ይጠቅም ነበር።

ማቴዎስ 13፡32 እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።

እያንዳንዱ የሐይማኖት ድርጅት በመጽሐፍ ቅዱስ የማይታወቅ ሰው ሰራሽ የስልጣን ተዋረድ አለው፤ በዚህ ተዋረድ ውስጥል ስልጣን ለሚወዱ ሰዎች ቦታ ይሰጣቸዋል።

 

 

ፕሮቴስታንቶችም ኋላ ከአሮን ሹመት ጋር የሚሄድ ባለ አምስት ቢሮ አገልግሎት አደራጅተው ሰዎችን ከሕዝቡ በላይ ከፍ አደረጓቸው፤ ይህም ሕዝቡን ለመግዛትና ለመጨቆን ይጠቅማቸዋል። ከዚያም ፓስተሩ መጽሐፍ ቅዱስ ያልፈቀደለትን ከሁሉ በላይ ከፍ የሚልበትን ስልጣን ይቆናጠጣል፤ ከዚያ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ይላል። ራስ የመሆን ስልጣን ግን የክርስቶስ ብቻ ነው።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

ስለዚህ ነብዩ አብራም እነዚህን የዲኖሚኔሽን አሞራዎች አባረራቸው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደተጻፈው የሐዋርያት ትምሕርት መመላለስ የተሳሳቱ መሪዎችን ያባርራቸዋል። አዲስ ኪዳን ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ አልሾመውም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን የምትሰበሰበው በሰዎች ቤት ውስጥ ነበር።

ሮሜ 16፡3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤

5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

 

ዘፍጥረት 15፡12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤

“ፀሃይ እየገባች ነበር”። የምሽት ሰዓት ነበር። እውነት ተመልሶ በመጣ ጊዜ በምሽት ብርሃን ይሆናል።

“አብራም አንቀላፋ”። ይህ የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ነው። አብራም ምንም ማድረግ አያስፈልገውም። አብራሐምን የራሱ ሥራ ሊያድነው አይችልም። እንቅልፉን ተኝቶ ሁሉን ለእግዚአብሔር መተው ብቻ ነው ያለበት። እግዚአብሔር ከእናንተ ምንም እገዛ ሳይቀበል የመዳናቹን ስራ ይሰራዋል።

የታላቅ ጨለማ ድንጋጤ። የሐጥያታችን ጨለማ። እንቅልፍ የሞት ተምሳሌት ነው። ከሞት በኋላ የሐጥያታችንን ዋጋ የምንከፍልበት አስፈሪ ሰዓት ይመጣል።

 

ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።

“ፀሃይ ገባች”። በዲኖሚኔሽናዊ ዘመን ውስጥ ግራ የሚያጋባ የምሽት ብርሃን ይወጣል።

ብዙዎች መዳን በእምነት በጸጋው አማካኝነት መሆኑን በተረዱ ጊዜ ቤተክርስቲያኖች ጥቂት ብርሃን ያገኛሉ።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ልማዶቻቸው አማካኝነት ብዙ ጨለማ ይፈጥራሉ።

ስላሴ። እንድናከብር ያልታዘዝነው ክሪስማስ። የስቅለት አርብ። የእሁድ ሰንበት። ሔዋን የዛፍ ፍሬ በላች። የሰባት ዓመት መከራ። የ1963ቱ ደመና የጌታ ምጻት ነው ወይም የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ መውረድ ነው። ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳተው ፍጹሙ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው።

ዘካርያስ 14፡7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።

ግን ደግሞ እውነትም አለ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ሐዋርያዊ አባቶች ወዳስተማሩት እውነት ይመለሳሉ።

“ጨለማ”። የሐጥያት ዋጋ በሚከፈልበት ሰዓት የሚሆን የሞት ድንጋጤ።

“የምድጃ ጢስ”። እሳቱ የሚመጣው ከሲኦል ጉድጓድ ነው። ይህም የሐጥያተኞች አስፈሪ ዕድል ፈንታ ነው።

“የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ”።

ቀራንዮ ላይ የበዓለ ሃምሳ ቀን በተጀመረችው በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እና በብሉይ ኪዳን መካከል አራት ወንጌሎች አሉ።

እነዚህ ወንጌሎች ስለ ሐጥያታችን ዋጋ ሊከፍል በመስቀል ላይ ስለሞተው ስለ ክርስቶስ ይነግሩናል። እርሱም በሞተ ጊዜ ቅዱስ የሆነው መንፈሱ በሁለቱ ኪዳኖች መካከል አልፎ ሄደና ጉድጓድ እና ጨለማ ወደሆነው ሲኦል ውስጥ እንደ እሳት ነበልባል ወርዶ በዚያ ዲያብሎስን አሸነፈ። የሲኦልን እና የሞትን ቆልፍ ይዞ በተመለሰ ጊዜም እኛን ስለ ማዳን ከገባበት ጦርነት ውስጥ ድል አድራጊ ሆኖ ተመለሰ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ የማዳን እቅዱን ሙሉ በሙሉ በእጁ አስገባ፤ ሰይጣንም ክፉኛ ተሸነፈ።

እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ከአብራሐም ጋር በሶስት ተምሳሌቶች አማካኝነት አደረገ።

እግዚአብሔር መከራ በተቀበለ እና ሞቶ ወደ ሲኦል በመውረድ ሰይጣንን ባሸነፈው ጊዜ ቃልኪዳኑን በቀራንዮ መስቀል ላይ አጸናው። ከዚያ በኋላ ከሞት ተነሳ።

የነፍሳችን መዳን ተረጋገጠ። የሕጉ መስዋእቶች ተሻሩ።

ነገር ግን ቃልኪዳኑ ለ7 ዓመታት ክፍለ ጊዜ ነው የሚጸናው።

ኢየሱስ 3½ ዓመት ጨርሷል፤ ስለዚህ ለአይሁዶች በታላቁ መከራ ጊዜ የሚቀራቸው የ3½ ጊዜ አለ።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23