ዳንኤል ምዕራፍ 8፡13 – 27 ከይስሐቅ እስከ ኢየሱስ። ከዚያም የአውሬው መነሳት



First published on the 7th of April 2021 — Last updated on the 7th of April 2021

እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር የገባው ቃልኪዳን የአብራሐምን ዘር ወይም ልጁን ይስሐቅን የሚያካትት ነበር።

አብራሐም ልጅ እንደሚወልድ ቃል ተገብቶለት ነበር፤ ይህም ልክ ከ25 ዓመታት በኋላ ነው የተወለደው። ስለዚህ የይስሐቅ መወለድ ለአብራሐም የተገባው ቃል በፍጥረታዊው ዓለም መፈጸሙን ያመለክታል። የእርሱም መወለድ ለአብራሐም እንደሚወለድለው ቃል የተገባለት መንፈሳዊው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣ የሚያመለክት ነው።

ኢየሱስ ሁል ጊዜ ማንም ሰው ማድረግ የማይችለውን ነገር ነው የሚያደርገው።

ስለዚህ ኢየሱስ ከአንድ ጊዜ በላይ ነው የሚመጣው።

የመጀመሪያ ምጻቱ ለሕዝቡ በቀራንዮ ተራራ ላይ ለመሞት ነው።

ታላቅ ሚስጥር የሆነው ሁለተኛው ምጻቱ ደግሞ ሙሽራይቱን ከምድር ላይ ለመውሰድ ነው።

ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ ምድር ከመድረሱ በፊት ሙሽራይቱ ከእርሱ ጋር በአየር ላይ እንድትሆን በሚስጥር ነጥቆ ይወስዳታል።

ሙሽራይቱን ለሰርግ እራት ግብዣ ወደ ሰማይ ይዟት ይሄዳል።

ይህ የመጨረሻዎቹ የዓለም ክስተቶች እንዲጀምሩ ያደርጋል። ሁለቱ ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ በዚያን ጊዜ ወንጌልን ለአይሁድ ሲሰብኩ ዓለም ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ትገባለች።

የመጨረሻው አውሬ ፖፕ እና የፖፑ ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ ሰራዊት አይሁዶችን ከማጥፋታቸው በፊት ኢየሱስ ሙሽራይቱን በሰማይ ትቶ 144,000 አይሁዶችን ከጥፋት ለማዳን በሚስጥር ወደ ምድር ይመለሳል። ይህም የማዳን ኃይል ሲገለጥ 144,000ዎቹ አይሁዶች ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን ያምናሉ።

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲመለስ ሁለቱ ነብያት እና 144,000ዎቹ አይሁዶች ይገደላሉ። ከዚያ በኋላ ግን ኢየሱስ እና ሙሽራይቱ ለመጨረሻው የአርማጌዶን ጦርነት ወደ ምድር ሲመለሱ ለሙሽራይቱ ጥበቃ ለማድረግ ከሙታን ይነሳሉ። ይህም ኢየሱስ የክርስቶስ ተቃዋሚውን ሰራዊት ለማጥፋት ለሶስተኛ ጊዜ የሚመለስበት ምጻት ነው።

ከአይሁዶች መረዳት አንጻር ወንጌሉን አንቀበልም ባሉ ጊዜ ቃል የተገባላቸው ልጅ ሲሞት ታሪካቸው በቀራንዮ ያበቃ ይመስላል። ከዚያ በኋላ ወደ ተስፋይቱ ምድር ተመልሰው እስኪገቡ ድረስ ለሁለት ሺ ዓመታት ስደተኞች ሆነው በዓለም ዙርያ ሲንከራተቱ አሳልፈዋል። ቤተክርስቲያን ወይም ሙሽራይቱ በዳግም ምጻት ወይም በመነጠቅ ጊዜ ታላቁ መከራ ሲጀምር ምድርን ለቅቃ ትሄዳለች። ተቋርጦ የነበረው የነበረው የአይሁድ ታሪክ የዚያን ጊዜ በድንገት ይቀጥላል። በቀጣዮቹ 3½ ዓመታት ውስጥ በታላቁ መከራ ዘመን አይሁዶች ቀስ በቀስ ወንጌሉን ይቀበላሉ። በስተመጨረሻ አርማጌዶን በሚባል ከባድ ደም መፋሰስ በሚሆንበት ጦርነት ውስጥ ጠላት ድምጥማጡ ይጠፋል።

እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር ያደረገው ቃልኪዳን ልጁን ይስሐቅን የሚመለከት ነው።

ስለዚህ የአይሁድ ሕዝብ ህልውና የሚጀምረው ይስሐቅ የአብራሐም ዘር ሆኖ ሲወለድ ነው። አብራሐም ልጅ ባይወልድ ኖሮ እርሱ ከሞተ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎት የነበረው ቃልኪዳን ዋጋቢስ ሆኖ ይቀር ነበር።

ስለዚህ ከይስሐቅ መወለድ በኋላ የአይሁድ ሕዝብ ረጅሙን ታሪካዊ ጉዞዋቸውን ጀመሩ።

ይህ ሕዝብ እግዚአብሔር መሲሁ በእነርሱ በኩል ይመጣ ዘንድ የመረጠው ሕዝብ ነው።

የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር የኢየሱስ መምጣት ከይስሐቅ መወለድ ይልቅ የተወሳሰበ ነው፤ ምክንቱም ከአንድ በላይ የሆኑ መምጣቶችን የሚያካትት ነው። በመጀመሪያ ኢየሱስ መሲህ ሆኖ መጣ፤ እርሱንም አንቀበልህም ብለው ገደሉት።

ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ሊነጥቅ ሲመጣ አይሁዶች አያዩትም፤ ነገር ግን በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ አይሁዶች ተመልሰው ወደ እግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ይገባሉ፤ ከእነርሱም መካከል በመከራ ውስጥ ያልጠፉት በታላቁ መከራ ማብቂያ ላይ ይደሰታሉ።

ኢየሱስ ወደ አርማጌዶን በሚመጣበት በሶስተኛው ምጻቱ ጊዜ ታላቁ መከራ ያበቃል።

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብቻውን የመጀመሪያውን ምጻት እና ከ2,000 ዓመታ በኋላ የሚመጣውን ታላቁን መከራ በአንዴ ሊገልጽ ይችላል። በነዚህ በሁለቱም ምጻቶች ውስጥ አይሁዶች አሉበት።

ኢሳይያስ 61፡1 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።

2 የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤

የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት በሙሴ ሕግ ውስጥ እውቅና ያልነበረው የረቢዎቹ፣ የፈሪሳውያን፣ የምኩራቦች፣ እና የሰዱቃውያን ሰው ሰራሽ አገዛዝ ያስጨነቀውን የአይሁድ ሕዝብ ለመፈወስና ነጻ ለማውጣት ነበረ።

ነገር ግን የመጀመሪያው ምጻቱ የተወደደችዋ ዓመት በአርማጌዶን ጦርነት ከሚያበቃው ከበቀል ዘመን ወይም ከታላቁ መከራ ጋር የተያያዘች ናት። ይህም የሚሆነው እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ ከምትሄድበት ከዳግም ምጻቱ በኋላ ነው።

ኢየሱስ በመጀመሪያ ምጻቱ ወቅት ይህን ትንቢት በፈጸመ ጊዜ የቃሉን ሁለተኛ አጋማሽ ሳያነበው ትቶ ነው ያለፈው።

ሉቃስ 4፡19 የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ

ስለ በቀል ቀን ምንም አልተጠቀሰም።

ሉቃስ 4፡21 እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር።

ይህ ቁልፍ ነጥብ ነው።

አንድ ጥቅስ በ2,000 ዓመታት ያህል የተነጣጠሉ ሁለት ክስተቶችን ሊገልጽ ይችላል።

ከጥቅሱ ውስጥ የትኛው ክፍል ስለ መጀመሪያ ምጻቱ እንደሚናገር ኢየሱሰ በትክክል አውቋል። ስለዚህ ቀሪውን የጥቅሱን ክፍል ሳያነበው አለፈው፤ ምክንያቱም ክፍሉ የሚናገረው ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የሚፈጸም ትንቢት ነበረ። እግዚአብሔር ግን አንድን ቀን እንደ አንድ ሺ ዓመት ስለሚያይ በእግዚአብሔር እይታ ሁለቱ ክስተቶች በመካከላቸው የነበረው ክፍተት የሁለት ቀናት ብቻ ነበር። ስለዚህ በአንድ ጥቅስ ስለ ሁለቱም መናገር አስቸጋሪ አይደለም።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

በ2,000 ዓመታት የተነጣጠሉ ሁለት ክስተቶችን የሚገልጽ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እነሆ፡-

ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።

6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

መጥምቁ ዮሐንስ የዚህን ትንቢት ግማሽ ብቻ ነው የፈጸመው።

መልአኩ ለመጥምቁ ዮሐንስ አባት ለዘካርያስ እንዲህ አለ፡-

ሉቃስ 1፡17 እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።

ሕጉን ይጠብቁ የነበሩት አመጸኞቹ አይሁዳውያን አባቶች እውነትን ለማግኘት ጻድቅ ልጆቻቸው እና የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ወደተቀበሉት ወደ ወንጌሉ ጥበብ መመለስ አለባቸው።

ሕጻናት ሆነው የጀመሩት ደቀመዛሙርት በኢየሱስ ትምሕርት አድገው የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባቶች ለመሆን በቁ።

“ታላቁ እና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን” ታላቁ መከራ ነው። “እርግማኑ” በታላቁ መከራ ወቅት ምድርን ከሚያጠፋት የኑክሊየር ቦምብ ፍንዳታ በኋላ አየሩ ላይ የሚቆየው ሬድዮአክቲቭ ጨረር ነው።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡12 የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ … ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤

ይህ ቃል ከምድር በላይ ከፍ ብለው ወደ ምድር እየመጡ ሳሉ አየር ላይ የሚፈነዱትን የኑክሊየር ሚሳኤሎች በትክክል ይገልጻቸዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሒሮሺማ ከተማ ላይ የወደቀው አቶሚክ ቦምብ በ600 ሜትር ከፍታ ላይ ነበር የፈነዳው። ይህም ቦምብ ዓይን በሚያጠፋ ድምቀት የሚነድድ የእሳት ኳስ ሲሆን ያገኘውን ነገር ሁሉ የሚያቀልጥና ብን አድርጎ የሚያጠፋ ነበረ።

የኑክሊየር ቦምቦች የአውዳሚነት ኃይላቸው እንዲጨምር የሚፈነዱት ከመሬት ሁለት ወይም ሶስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ሳሉ ነው። ሊቀዘቅዝ ወይም ሞቆ ሊያቃጥል የሚችለው ከባቢ አየር፣ በጭስ እና በሰደድ እሳት ሊቃጠል ወይም በከተሞች እና በፋብሪካዎች ሊበከል የሚችለው አየር፣ አንዳንዴም ንጹህ እና ደስ የሚል ወይም በነፋስ በበረዶ ወይም እና በአውሎ ነፋስ ሊናወጥ የሚችለው አየር - ፍጥረታዊ ሰማይ የሚባለው እርሱ ነው። (እግዚአብሔር እና መላእክት የሚኖሩት ከፍ ባለውና በዓይን በማይታየው መንፈሳዊ ሰማይ ውስጥ ነው።)

ታላቁ መከራ እና የኑክሊየር ጥፋት ከመጀመሩ በፊት ለክርስቲያኖች ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እና ወደ ሐዋርያዊ የቤተክርስቲያን አባቶች እምነት የሚመልሰን የዘመን መጨረሻ ነብይ እንደሚላክልን ቃል ተገብቶልናል። ለዚህ አገልግሎት ብቁ ሆኖ የተገኘው አሜሪካዊው ሰባኪ ዊልያም ብራንሐም ብቻ ነበረ።

ስለዚህ ይህ በሚልክያስ 4፡6 የተጻፈው ጥቅስ በ2,000 ዓመታት የተነጣጠሉ ሁለት ክስተቶችን ነው የሚገልጸው።

እስቲ ወደ አብራሐም ጥሪ እንመለስ (መጀመሪያ ስሙ አብራም ነበረ)፤ አብራሐም የተጠራው ከክርስቶስ 2,000 ዓመታት በፊት ነበረ።

ዘፍጥረት 12፡1 እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።

2 ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥

እግዚአብሔር አብራሐምን ሲጠራው ትኩረት ያደረገው የአብራሐም ዘር በሆኑት በአይሁድ ሕዝብ ላይ ነበር።

ትኩረቱ በአብራሐም ላይ ብቻ አልነበረም፤ ከእርሱ በሚወለደው ወንድ ልጅ ወይም ዘር በሚገኘው ሕዝብ ጭምር እንጂ።

ዘፍጥረት 12፡7 እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው።

ስለዚህ አብራሐም ልጅ እንደሚወልድ እግዚአብሔር ቃል ገባለት። ለአብራሐም ዘርም ምድር፤ የእሥራኤል ምድር እንደሚሰጠው ቃል ተገባለት።

አብራሐም ልጅ ባይወልድ ኖሮ ከእርሱ ሕዝብ አይወጣም ነበር።

ስለዚህ ቃልኪዳኑ ተፈጻሚነት ያገኘው ከ25 ዓመታት በኋላ ይስሐቅ በስጋ ሲወለድ ነው።

ቃልኪዳኑ ውስጥ ሌላው የተካተተ ነገር የተስፋ ምድር ነው (ይህም ከምድር ስፋት ላይ 1% ብቻ የሚሆን መሬት ነው)። ኋላ በሙሴ ሕግ መሰረት በቤተመቅደስ ፍጹም ያልሆኑ መስዋእቶች ይቀርቡ ነበር፤ ነገር ግን እነዚህ መስዋእቶች ሕዝቡን ሊለውጧቸው አልቻሉም። ሕጉ በመልካም ሥራ ለመዳን እንዲሞክሩ ለሰዎች ከባድ ቀምበር ጫነባቸው። አይሁዶች ደግሞ በራስ ወዳድነት እና በሃብት ፍቅር ተጠምደው ቀሩ።

የተስፋው ልጅ፡- ይስሐቅ። የተስፋይቱ ምድር፡- እሥራኤል። ዋናው ትኩረት በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ ነው።

ስለዚህ ሕጉ ውስጥ የተሻለ ኪዳን እንደሚመጣ ተስፋ ተሰቷል፤ ለዚህም የተሻለ ተስፋ ሕጉ እንደ ጥላ አመልካች ነበረ። ሕጉ ጊዜያዊ መሰረት ነበረ። ቤተመቅደሱ አስደናቂ ሕንጻ ቢሆንም ሁለት ጊዜ ፈርሷል።

ይህ የፍጥረታዊ ተስፋ ኪዳን የተቆረጠለት ዕድሜ ምን ያህል ነበረ?

ይህ ኪዳን የጀመረው ተስፋ ከተሰጠው ከይስሐቅ መወለድ ሲሆን ለአይሁዶች ተስፋ ምድር ሰጣቸው፤ እነርሱም መሲሁ እስኪመጣ ድረስ በዚያ ምድር ተደላድለው እንዲቀመጡ ተወሰነላቸው።

ጊዜው ሲደርስ አይሁዶች ሕግ ተሰጣቸው። ሕጉ ግን ውጤታማ አልነበረም። ሊቀ ካሕናቱ ቀያፋ በኢየሱስ ላይ በፈረደበት ጊዜ የክሕነት ልብሱን ሲቀድድ ሕጉ አበቃለት።

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።

ሊቀ ካሕናቱ አሮን የተለየ የክሕነት ልብስ ነበረው፤ ይህም ልብስ በአንገቱ ዙርያ በቀላል እንዳይቀደድ ጠንከር ተደርጎ የተሰራ ነበር።

ዘጸአት 28፡30 በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።

31 የኤፉዱንም ቀሚስ ሁሉ ሰማያዊ አድርገው።

32 ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።

ጥሩር ማለት ደረትን እና ጀርባን የሚሸፍን የብረት ልብስ ነው።

ስለዚህ ሊቀካሕናቱ ልብሱን በመቅደዱ ሕጉን አፍርሷል፤ በዚያን ጊዜም የሕጉ ዘመን ተጠናቀቀ። ይህን ተከትሎ የሕጉ ዘመን ማብቃቱን ለማመልከት እግዚአብሔር የቤተመቅደሱን መጋረጃ ቀደደው።

ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

ከላይ ጀምሮ መቀደዱ የቀደደው እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል።

አይሁድ በልባቸው ከሞላው ጥላቻ የተነሳ መሲሁን ለመግደል በመነሳታቸው ሕጉን አፈረሱት።

የሕይወት ራስ በሆነው በኢየሱስ ፈንታ የሞት መልእክተኛ የሆነውን በርባን መረጡ።

ፍጥረታዊ የሆነው የተስፋ ልጅ ይስሐቅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ መንፈሳዊ የሆነው የተስፋ ልጅ ኢየሱስ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ለእሥራኤል ሕዝብ አዳኝ የሆነውን መሲሁን እንዲወልዱ የተሰጠ ጊዜ ነበረ። ኢየሱስ ሰዎችን ማዳን የሚችለው ስለ ሐጥያታቸው ከሞተ ብቻ ነው። ስለዚህ አይሁዶች ኢየሱስን መግደል ነበረባቸው።

ይህ በመካከል ያለ ጊዜ ምን ያህል እንደሚረዝም ለዳንኤል ተገልጦለታል፤ ጊዜውም 2,300 ቀናት ነው።

መሲሁን ከገደሉት በኋላ አይሁዶች ከእግዚአብሔር እቅድ ወጥተው ወደቁ። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ለመመስረት ወደ አሕዛብ ዘወር አለ።

በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን ማለት ባለ 360 ቀናት ዓመት ሊሆን ይችላል።

ያዕቆብ የላባ ልጅ የሆነችዋን ራሔልን ሊያገባ ፈለገ። እርሷን ማግባት ከፈለገ ለሰባት ዓመታት ማገልገል እንዳለበት ላባ ነገረው። ሰባቱን ዓመታት ላባ አንድ ሳምንት ብሎ ነው የጠራው።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ይወክላል።

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

የታላቁ መከራ ዘመን 42 ወራት ወይም 1,260 ቀናት ተብሏል።

ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።

13 በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፥ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፥ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፥ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እያንዳንዱ ወር 30 ቀናት ብቻ ናቸው ያሉት። እያንዳንዳቸው 30 ቀናት በሆኑ ወራት መሰረት 42 ወራት ውስጥ 1,260 ቀናት አሉ።

ስለዚህ በ12 ወራቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመት 12 x 30 = 360 ቀና አሉት።

 

ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጅ ወይም የአብራሐም ፍጥረታዊ ዘር ነው።

ነገር ግን ይስሐቅ የአብራሐም ታላቁ የተስፋ ዘር የሆነው ለየኢየሱስ ጥላ ነው።

ሊቀካሕናቱ ቀያፋ ሕጉን አፈረሰው፤ ስለዚህ አዲስ ቃልኪዳን አስፈለገ።

አዲሱ መንፈሳዊ ቃልኪዳን የጸደቀው ኢየሱስ ሲሞት እና መንፈስ ቅዱስ ከስጋዊ አካሉ ለቆ ሲሆድ ነው።

የመዳንን ተስፋዎች መፈጸም የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም የሞተውና ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል የወረደው እርሱ ነው። መሞት እና ከዚያም ሞትን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም። ሰማያዊውን ቤተቅደስ ከሐጥት ማንጻት የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። (ሉሲፈር ሐጥያትን በጀመረ ሰዓት በሰማያት ነበረ።) የኢየሱስ ደም ብቻ በሰማይ ያለውን የፍርድ ዙፋን ወደ ምሕረት ዙፋን መለወጥ የሚችለው።

የአዲስ ሰማይና የአዲስ ምድር ተስፋ መሰረቱ የተጣለው በቀራንዮ ነው።

ስለዚህ ቀራንዮ ለሰው ዘሮች የአዲስ ታሪክ መነሻ ቦታ ነው። በቀራንዮ ኢየሱስ ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔር መንግስት መሰረት ጣለ።

ከፍጥረታዊው የተስፋ ልጅ ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ መዳን ወደ አይሁድ ሕዝብ በሕጉ በኩል መጥቶ ነበረ።

ከመንፈሳዊው የተስፋ ልጅ ከኢየሱስ ሞት ጀምሮ መዳን በጸጋ ወደ አሕዛብ መጣ።

ይህ እውነት ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ናቡከደነጾር ባየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ ተገልጧል።

 

 

መስቀሉ መዳን ከአይሁድ ወደ አሕዛብ “የተሸጋገረበት” መሸጋገሪያ ነው።

ስለዚህ ቀራንዮ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከሁሉ የሚበልጥ ክስተት ሆነ።

ዳንኤል 8፡13 ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ለተናገረው ለቅዱሱም ሁለተኛው ቅዱስ፦ ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፥ መቅደሱና ሠራዊቱም ይረገጡ ዘንድ ስለሚሰጥና ስለሚያጠፋ ኃጢአት የሆነው ራእይ እስከ መቼ ይሆናል? አለው።

ይህ ጥቅስ አራት ነገሮችን በተመለከተ ነው የሚናገረው።

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በየዕለቱ ቤተመቅደሱ ውስጥ የሚቀርበው መስዋእት ዋጋ ቢስ ሆኗል፤ ምክንያቱም የመጨረሻው መስዋእት ኢየሱስ ነው።

አመጻ ማለት የእግዚአብሔርን ቃል መተላለፍ ነው ወይም አለመታዘዝ ነው።

የአይሁዶች አመጽ የእግዚአብሔርን ቃል የፈጸመውን መሲሃቸውን አለመቀበላቸው ነው።

የቤተመቅደስ መስዋእታቸው ዋጋቢስ ከተደረገ በኋላ በጥቂት አመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ፈረሰ፤ ከዚያም አነርሱ ደግሞ ለ2,000 ዓመታት ያህል ተሰደዱ። ቤተመቅደስ በሌለበት ቤተመቅደሱን ያማከለ እምነት ይዞ መጠበቅ ትልቅ መንፈሳዊ መከራ ነው። ይህም የአመጻቸው ውጤት ነው።

ቤተመቅደሱ በ70 ዓመተ ምሕረት በሮማዊው ጀነራል ታይተስ አማካኝነት ፈረሰ ወይም ተረገጠ።

አለማመን በዝቶ ከ2,000 ዓመታት በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ጣራውን ይነካል፤ በዚያም ጊዜ የመጨረሻው ፖፕ ዓለም አቀፋዊውን ወታደራዊ ሰራዊቱን ሰብስቦ ኢየሩሳሌምን እና እሥራኤልን ሊያጠፋ ይነሳል። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ይመጣና ያጠፋዋል፤ የሰራዊቱም ይረገጣሉ፤ ደማቸውም የፈረሶች ልጓም ጋ እስኪደርስ ድረስ ይጎርፋል።

ራዕይ 14፡19 መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፥ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር ቍጣ መጥመቂያ ጣለ።

20 የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፥ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።

አንድ ማይል ስምንት ምዕራፍ ያህል ነው። ስለዚህ በደም የተነከሩት እሬሳዎች ሲረፈረፉ 200 ማይል ያህል ቦታ ይሸፍናሉ።

ሕዝቅኤል 39፡4 አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።

5 አንተ በምድር ፊት ላይ ትወድቃለህ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

አንድ መልአክ በጨለማ ቀን ፀሃይ ውስጥ ቆሞ ጥምብ አንሳዎችን ይጠራቸዋል።

ራዕይ 19፡17-18 አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፥ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፦ መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

እነዚህ ሰዎች የኖሩት ለስጋቸው ምኞት ብቻ ነው።

በአርማጌዶን ጦርነት ውስጥ የሚሞቱት እነዚህ ሁሉ ሰዎች እነማን ናቸው? የመጨረሻው አውሬ ፖፕ እና የእርሱ ሰራዊት ናቸው። እነዚህ ሁሉ ብዙ ሰራዊት ኢየሱስ መጥቶ እስኪረግጣቸው ነው የሚጠብቁት።

ራዕይ 19፡19 በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።

ሕዝቅኤል 39፡12 ምድሩንም ያጸዱ ዘንድ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ይቀብሩአቸዋል፥

አውሬዎቹ እና ጥምብ አንሳዎቹ የእሬሳዎቹን ስጋ በልተው ከጠገቡ በኋላ በሕይወት የተረፉት አይሁድ የሺ ዓመቱን የሰላም መንግስት የመጀመሪያ ሰባት ወራት የሚያሳልፉት ሙታንን በመቅበር ነው። ይህ ብዙ ደም እና አውሬዎች ከበሉዋቸው እሬሳዎች ተርፎ ምድር ላይ የሚቀረው ሁሉ ለአፈሩ ማዳበሪያ ሆኖ ያገለግላል።

አይሁዶች ኢየሱስን እንደ ሰው አንቀበልህም ብለውታል። ትልቁ ሐጥያታቸውም ይህ ነው። እግዚአብሔርም እንደ ሕዝብ ከራሱ የወይራ ዛፍ ላይ ቆርጦ ጣላቸው። በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሳቸው በሮማውያን እጅ ፈረሰ። ቤተመቅደሱ በነበረበት ቦታ ዛሬ የቆመው የኦማር መስጊድ ነው፤ ይህም የጥፋት እርኩሰት ነው። አይሁዶች በ2,000ዎቹ የቤተክርስቲያን ዓመታት ውስጥ ከርስታቸው ተፈናቅለው በስደት ነው የቆዩት። በተፈጥሯቸው የበረሃ ወይራ የነበሩ አሕዛብ በእግዚአብሔር የወይራ ዛፍ ውስጥ በጸጋው አማካኝነት ገቡ።

ታሪክ ራሱን ይደግማል።

በመጨረሻ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል አልቀበልም ትላለች፤ ኢየሱስን በደጅ ቆሞ ያንኳኳል።

ራዕይ 3፡14 ሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

17 … ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

እምነታችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ከሆነ በኋላ ከእግዚአብሔር ተለይተናል ማለት ነው።

ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይስማማም።

የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች እና የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት።

ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን ልማዶች መንፈሳዊ ምድረ በዳ ናቸው፤ ምክንያቱም በልማዶች ውስጥ የዘላለም ሕይወት የለም።

አብረቅራቂ ነገሮች፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞች እና ቄንጦች ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሐርት ውጭ የምትሄደዋን ቤተክርስቲያን ኪሳራ ለመደበቅ የሚያገለግሉ ስስ ሽፋኖች ናቸው።

ከዚያ በኋላ የወይራ ዛፉ ላይ ተገጥሞ የነበረው የአሕዛብ ቅንጫፍ እግዚአብሔር ሰብሮ ይጥላል። ስለዚህ በስተመጨረሻ የአይሁዶች ቅርንጫድ ወደ ወይራው ዛፍ ተመልሶ ይገባል፤ በዚያም ጊዜ 144,000 አይሁዶችን ያፈራል።

አይሁዶች ቤተመቅደሱ ውስጥ ያቀርቡ የነበረው ዕለታዊው መስዋእት በክርስቶስ መስዋእትነት ተተክቷል።

61-0618 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 2

ክርስቶስ መጥቶ ለሶስት ዓመት ተኩል ሰበከ፤ ትንቢትም ተናገረ፤ ከዚያም በኋላ ዕለታዊው መስዋእት ተቋረጠ፤

61-0308 መጠባበቅ

ዮሐንስ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ወጥቶ ቆሞ እየሰበከ ነበር። ካሕናቱም ከወንዙ ማዶ እንዲህ አሉ፡- “ዕለታዊው መስዋእት በመቅደሱ መቅረቡ የሚቋረጥበት ቀን ይመጣል እያልከኝ ነው፤ ከዚያም በኋላ መስዋእትም ሆነ ቁርባንም አይቀርብም?”

እርሱም እንዲህ አለ፡- “አንድ የሚመጣ አለ፤ እርሱም የመጨረሻው መስዋእት ሆኖ ይቀርባል።”

ስለዚህ እውነተኛው መስዋእት ኢየሱስ ነው።

65-0220 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ሥፍራ

አንድ ቀን በዚያ ቆሞ ሲሰብክ ነበረ። ካሕናቱም ከወንዙ ማዶ ቆመው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፡- “ዕለታዊው መስዋእት የሚቋረጥበት አንድ ቀን ይመጣል ማለትህ ነው? የሰራነው ይህ ትልቅ ቤተመቅደስ፣ ይህ ያቋቋምነው ትልቅ ዲኖሚኔሽን ሁሉ ከንቱ ይሆናል ማለትህ ነው?”

እርሱም እንዲህ አለ፡- “ይህ ሁሉ የሚጠፋበት ቀን ይመጣል።”

“ሊሆን አይችልም። አንተ ሐሰተኛ ነብይ ነህ!”

እርሱም ዙርያውን ተመለከተ። እንዲህም አለ፡- “እነሆ ተመልከቱ! እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ሥፍራ ይኸው። እርሱም በጉ ነው፤ የዓለምን ሐጥያት የሚያስወግድ እውነተኛው የእግዚአብሔር በግ።” “የዓለምን ሐጥያት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በፍ ይኸው” ብሎ ተናገረ እንጂ “ይኸው ሜተዲስቱ፣ ይኸው ባፕቲስቱ፤ ወይም ይኸው ካቶሊኩ” አላለም።

መዳን የምንችልበት መጠጊያችን የእግዚአብሔር በግ ብቻ ነው። መዳን በእርሱ ብቻ ነው እንጂ በየትኛዋም ቤተክርስቲያን አይደለም፤ ሰው በየትኛውም የእምነት መግለጫ፣ በየትኛውም ሕዝብ፣ በየትኞቹም አባቶች ወይም በየትኛውም የተቀደሰ ስፍራ መዳን የለም። እግዚአብሔር ለማዳን ስሙን በሰው ላይ ያኖረው ቅዱስ አምላክ በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ነው፤ እርሱም ለሐጥያተኞች መዳን የሚያስፈልገውን ዋጋ ከፍሏል። መዳን የሚገኘው በእርሱ ዘንድ ብቻ ነው። እኔ የቆምኩበት ዓለት እርሱ ነው።

 

መዳን በክርስቶስ ነው። የትኛዋም ቤተክርስቲያን ማንንም ማዳን አትችልም።

61-0730M ገብርኤል ለዳንኤል የሰጠው መመሪያ

ልብ በሉ ልክ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” እንደሚለው ቃል ድርብ ትርጉም አለው። ልክ እሥራኤል ተጠርቶ እንደወጣው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅም ኢየሱስም ተጠርቶ ወጥቷል።

ከዚህ በታች ያለው ጥቅስ ለእሥራኤልም ለአሕዛብም ድርብ ትርጉም አለው።

ዳንኤል 8፡12 ሠራዊቱም ከኃጢአት የተነሣ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ተሰጠው፤ እርሱም እውነትን ወደ ምድሩ ጣለ፥ አደረገም ተከናወነም።

ሕዝቡ በሙሉ ኢየሱስን ሲቃወሙ እና ይገደል ሲሉ ነበሩ።

የእርሱ ሞት በየዕለቱ ቤተመቅደሱ ውስጥ መስዋእት ሆነው የሚቀርቡት በጎች እንዳይቀርቡ አደረገ፤ ምክንያቱም ከኢየሱስ ሞት በኋላ ትርጉም የላቸውም።

የአይሁዶች ሐጥያት መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም ማለታቸውና የመጽሐፉ ቃል በፊታቸው እየተፈጸመ ማየት አልመቻላቸው ነው።

61-0730E ገብርኤል ዳንኤልን የጎበኘበት ስድስት ዓላማዎች

እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ያለውን ጉዳይ እስኪጨርስ ድረስ እሥራኤል ታውራ ነበር። ወደ ሐጥያት እና የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ መተላለፍ ገቡ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛ ወደ ወይራ ዛፉ ውስጥ እንገባ ዘንድ እግዚአብሔር የእነርሱን ዓይን አሳወረ።

እግዚአብሔር ለናንተ እና ለእኔ ብሎ በዓላማ ነው እነርሱን ያሳወራቸው። እነርሱም ማየት አይችሉም ምክንያቱም እግዚአብሔር አሳውሯቸዋል። እሥራኤልም በሙሉ እውነተኛ እሥራኤል ይድናል። መልአኩ ምን አለ? ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። “የእሥራኤልን አመጻ ለመፈጸም። የእሥራኤል አመጻ ሁሉ የሚወገድበት ቀን እንደሚመጣ ልነግርህ መጥቻቸለው።” እግዚአብሔር ያንን የበረሃ ወይራ ቅርንጫፍ ይቆርጥና እውነተኞቹን ቅርንጫፎች መልሶ ያስገባቸዋል።

የአሕዛብ ቤተክርስቲያንም የአይሁድ ሕዝብ ያደረጉትን ዓይነት ተመሳሳይ አመጻ ታደርጋለች። አይሁዶች ኢየሱስ እንደ ሰው ሆኖ በተገለጠበት ጊዜ አንቀበልህም አሉት። አሕዛብ ደግሞ ኢየሱስ እንደተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ ሲመጣ አንቀበልህም ይሉታል፤ በእርሱ ፈንታ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮዎች ይከተላሉ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዋ ዲኖሚኔሽን ስትሆን እናት ቤተክርስቲያን ተብላለች።

61-0806 የዳንኤል ሰባኛ ሱባኤ

እንቅልፍ የተኙትን አይሁድም እንዲሁም ሌሎች ሕዝቦች ሊገዛ የሚዘረጋው የሮም ኃይል … ሁላችንም ሮማዊ እንሆናለን፤ አለዚያ ምንም አይደለንም።

የቤተክርስቲያን ዕለታዊ መስዋእት በየቀኑ ለራስ መሞት የራሳችንን ፈቃድ መስዊያ ላይ ማቅረብ ነው፤ የዛኔ የእግዚአብሔር ፈቃድ በእኛ ውስጥ ይሰራል።

ማቴዎስ 16፡24 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

59-0612 የሕይወት ዘመናችን በሙሉ

የክርስትና ሕይወት የሁል ጊዜ መስዋእት ነው ብዬ አምናለው

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት (አርባ ስድስት ቀናት ብቻ ሳይሆን ቀን በቀን) ይከተለኝ”። አርባ ስድስት ቀናት ብቻ ሳይሆን በየቀኑ … የክርስቲያን ሕይወት የማያቋርጥ መስዋእትነት ነው።

ክርስቲያን ሕይወቱን መስዋእት እያደረገ መኖር ያስደስተዋል። ደግሞም በስስት ወይም በግድ አይደለም፤ እግዚአብሔርን እየወደደ ነው የሚያደርገው፤ ማድረግ በመቻሉም ደስ ይለዋል። ጌታ ኢየሱስን ማገልገል ታላቅ ደስታ ነው። ለጌታ መስዋእት መሆን ታላቅ ደስታ ነው። እግዚአብሔርን ማምለክ ደስታ ነው። ስለ እግዚአብሔር መንግስት አክራሪ ተብሎ መሰደብ ክብር ነው። ከስሕተት ፈቀቅ ማለት እና ስለ እውነት መቆም ታላቅ ደስታ ነው። እግዚአብሔርን ማመስገን ደስታ ነው። ከዚህ ዓለም ክፉ ነገሮች መራቅ ደስታ ነው። ከክፉ ነገሮች መጾም ደስታ ነው። ሁል ጊዜ መጾም ነው፤ ይህም ፍጹም ጾም ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ውስጣችሁ ይገባና ፍላጎታችሁን ይለውጠዋል።

“ሁዳዴ” በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለ46 ቀናት የሚጾሙበት ወቅት ነው።

53-1201 በእግዚአብሔር የተዘጋጀ መንገድ

እየደጋገማችሁ ወደ ኋላ በመንሸራተት ወደ ዓለም ልትመለሱ ትችላላችሁ፤ ስለዚህ ጸንታችሁ ለመቆየት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ያስፈልጋችኋል።

ጳውሎስ “ዕለት ዕለት እሞታለው” አለ።

ጳውሎስ ዕለት ዕለት መሞት ካስፈለገው እኔማ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅ ሆኜ ለመቆየት ምነኛ የበለጠ ዕለት ዕለት መሞት ያስፈልገኝ ይሆን። ሁላችንም ይህንኑ ማድረግ ያስፈልገናል፤ ሁላችንም ለእኔነት መሞት አለብን። ይህም የእግዚአብሔር መንገድ ነው።

ዕለታዊ መስዋእታችን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ይኖር ዘንድ እኛ ለራሳችን የምንሞተው ሞት ነው።

54-0516 ጥያቄዎች እና መልሶች፤ የሕጉ ጥላነት

ሁላችሁም ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለመሆን አትመኙም? መንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ በስርዓት የሚገለጡባት እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያን፤ ሁሉም ነገር በትክክለኛው መንገድ የሚገለጥባት ቤተክርስቲያን ውስጥ ብትሆኑ ደስ አይላችሁም? እንደዚያ ቢሆን በጣም ደስ አይልም? ስለዚህ መስዋእት መሰዋት አለባችሁ ግን ገንዘብ አይደለም የምትሰዉት። ስለዚህ ምንድነው የምትሰዉት? የምትሰዉት አንዳንዶቹን ሃሳቦቻችሁን ነውለጸሎት ጊዜ በመስጠት የተወሰነ ሰዓታችሁን ትሰዋላችሁ። ደግሞም ካስፈለገ ግትር የሆነ ፈቃዳችሁን ለመስበርና ትሁት ለመሆን የራሳችሁን ፈቃድ መስዋእት አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። አያችሁ? የክርስትና ሕይወት ሙሉ በሙሉ መስዋእትነት ነው። “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” ገብቷችኋል? መቼ መቼ ነው መስዋእት የምትሆኑት? በየቀኑ። ጳውሎስ “ዕለት ዕለት እሞታለው” አለ።

ነገር ግን ብዙ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ይህንን ዓይቱን ዕለታዊ መስዋእትነት ይቃወሙታል።

በዚህ ገንዘብ ወዳድ በሆነው ዓለም ውስጥ የተነሳው “የብልጽግና ወንጌል” አንዱ ነው።

ይህ ትምሕርት ከሰው ምኞት ጋር የተቀላቀለ ስለሆነ ለማመን ቀላለት ነው ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ እኛ መስማት የምንፈልገውንና ጆሮዋችንን የሚበላንን ነገር ነው የሚያስተምረው። ስለዚህ በዚህ ትምሕርት ዘና ብለን እንቅልፋችንን መተኛት እንችላለን።

የባርነት እና የፍርሃት ወንጌል። እግዚአብሔር ወደ እኔ አይመለከትም ምክንያቱም እርሱን የሚያስደስት ነገር መስራት አልቻልኩም። ከዚህ የበለጠ ጥረት ማድረግ አለብኝ። ይህ ዓይነቱ ወንጌል በስራ ተጠምደን ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ ጊዜ እንድናጣ ያደርጋል። ስራዎች በሙሉ የሚደረጉት በፍርሃት አነሳሽነት ነው። ይህም ሰዎችን መቆጣጠሪያ ዘዴ ነው።

በስራ እና በጥረት ላይ የተመሰረተ የራስ ጽድቅ። ይህ ደግሞ የሌሎችን እውቅና እና ክብር ለማግኘት የሚደረግ ጥረት ነው።

የበደለኛነት ስሜት ወንጌል። ብዙ ጥረት ባደርግም እንኳ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ብቁ አይደለሁም። ይህ ዓይነቱ እምነት በብዙ እስራት የተተበተበ፣ በራስ ወዳድነት የታነቀ የውሸት እምነት ነው። የሲኦል ፍርሃት፤ የመንግስተ ሰማያት ተስፋ። እራስን ከጥፋት ለማዳን መጨነቅ።

በስራ ለተወጠረው ሕይወቴ የኢየሱስን ወንጌል እንደ ማስታገሻ ክኒን (ወይም እንደ ቫይታሚን ሲ እንክብል) መውሰድ። ብዙ መልካም እና ታላላቅ ስራዎች ስላሉብኝ ምንም ጊዜ የለኝም። ስለዚህ ክርስቶስ የሕይወቴ ዋና ማዕከል አይደለም፤ ነገር ግን አልፎ አልፎ ነገሮች ሲጠምሙብኝ የእርሱ ድጋፍ ያስፈልገኛል።

የራሴ ፍላጎቶችና ሃላፊነቶች ይቀድማሉ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ በሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጠዋለው።

የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች አብዛኞቹ ከእነዚህ ወጥመዶች በአንዱ ተጠምደዋል።

መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለመከተል የቆረጡ በጣም ጥቂት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል ጓደኞችን ማጣት እና ተቀባይነትን ማጣት የመሳሰሉ መስዋእትነቶች ይጠይቃል።

የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ ምዕራፍ 4

በ1ኛ ቆሮንቶስ 9፡24 ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡-

“በእሽቅድድም ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።”

በጥንት ግሪክ ውስጥ ለኦሎምፒክ ሩጫ አሸናፊ የሚሰጠው ሽልማት ከወይራ ቅርንጫፍ የተጎነጎነ አክሊል ነው። ስለ ክርስቶስ ሰማእት ለሆነው ሰው የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው አክሊል ግን የንግስና ዘውድ ነው። ኢየሱስ ሲናገር የሕይወት አክሊል ይለዋል። አንዱ ዘውድ ለታገሉ ሰዎች ሲሆን ሌላኛው ግን ሕይወታቸውን ለሰጡ ነው። ሁለቱም የማይጠፉ አክሊሎች ናቸው። አይበሰብሱም። የዓለማዊውን ሕይወት ሩጫ ያሸነፉ ሰዎች ዓለም የሰጠቻቸው ቲፎዞ እና አድናቆት በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀዝቅዞ ይጠፋባቸዋል። ክብራቸው ይደበዝዛል። በየዕለቱ በመታገል ወይም ደማቸውን በማፍሰሰው ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ግን የሕይወት አክሊልን ይቀበላሉ።

ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ይህ ከሲኦል መዳን ማለት አይደለም። ከሲኦል የዳናችሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ንሰሃ በገባችሁ ሰዓት ነው። ይህ መዳን ግን የዳኑ ክርስቲያኖችን ወደ ታላቁ መከራ እየነዳቸው ካለው ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆነው የቤተክርስቲያኖች እምነት እና ትምሕርት ነው።

ማቴዎስ 24፡13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

እስከ መጨረሻው መጽሐፍ ቅዱስን ብንከተል ከታላቁ መከራ እንድናለን።

 

አሁን ደግሞ በቀራንዮ መስቀል ዕለት የተጠናቀቀውን የ2,300 ቀናት ትንቢት እናያለን። አስቸጋሪ የሆነብን ነገር የትንቢቱ ቀናት መች እንደጀመሩ ማወቅ ነው።

ዳንኤል 8፡14 እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።

61-0618 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 2

በዚህ ርዕስ ክርክር የነበረበት ወቅት ነበረ። ከአርባኛው ቀን፤ መጽደሱ ከሚነጻበት ከመጀመሪያው ቀን ወይም ክርስቶስ በቀራንዮ ከተሰቀለበት ቀን አንስቶ እስከ እርገቱ ድረስ አርባ ቀናት ነበሩ።

54-0515 ጥያቄዎችና መልሶች

ተቀምጦ የመጠበቅ ፕሮግመ የለም። ብዙ ተሳስታችኋል። “ቆዩ” ማለት “ጸልዩ” ማለት አይደለም፤ “ጠብቁ” ማለት ነው። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ከስቅለቱ፣ ከመቅደሱ መንጻት በኋላ፣ ከስርየት ቀን በኋላ ከትንሳኤ በኋላ …

 

በመጽሐፍ ቅዱስ አቆጣጠር አንድ ዓመት 360 ቀናት ነው። እኛ በሮማውያን ወይም በአሕዛብ አቆጣጠር ስለምንጠቀም አንድ ዓመት 365.24 ነው እንላለን። የእኛ አንድ ዓመት በ5.24 ቀናት ይረዝማል።

ስለዚህ በ69 ዓመታት ውስጥ 5.24 x 69 = 361 ተጨማሪ ቀናት ይኖሩናል። ይህም በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የአይሁዶች ዓመት አንድ ተጨማሪ ዓመት ነው።

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ 70 ዓመታት = ከእኛ ዘመናዊ የአሕዛብ 69 ዓመታ ጋር እኩል ናቸው።

ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየ70 ዓመቱ ከእኛ አቆጣጠር ላይ 1 ዓመት ስንቀንስ ነው አቆጣጠራችን ከመጽሐፍ ቅዱስ አቆጣጠር ጋር የሚገጥምልን።

2,300 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት / 70 = 33 ዓመታት።

2,300 – 33 = 2,267 ዘመናዊ ወይም የአሕዛብና የሮማውያን ዓመታት።

ቀኖች የሚቆጠሩት አንድ ንጉስ በዙፋን ተቀምጦ መግዛት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነበር።

ከሮማያን ነገስታት ሁሉ ዝነኛው አውግስጦስ ነበረ፤ እርሱም በ14 ዓ.ም ሞተ። እርሱ በማደጎ ያሳደገው ልጁ ጢባርዮስ ከ14 ዓ.ም ጀምሮ ነገሰ። የሮማ ምክር ቤት እርሱን ንጉስ አድርጎ የሾመው በዚያ ዓመት ነበረ።

ሉቃስ 3፡1 ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥ …

2 … የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ መጣ።

ስለዚህ 14 + 15 = 29 ዓ.ም መጥምቁ ዮሐንስ መስበክ የጀመረበት ዓመት ነው።

ከጥቂት ወራት በኋላ ጥቅምት አካባቢ ኢየሱስ ሊጠመቅ ወደ ዮሐንስ መጣ። በዚያ ጊዜ 29 ዓ.ም ወደ መጠናቀቂያው እየተቃረበ ነበር።

ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር

ቀኖቹ በትክክል ይገጣጠማሉ። ጊዜው 30 ዓ.ም የነበረ ሲሆን ኢየሱስም ዕድሜው 30 አካባቢ ነበር።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በዜሮ ዓ.ም መወለዱን ያረጋግጥልናል። ካላንደራችንም የሚጀምረው ከዚያው ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ለሶስት ዓመት ተኩል ያህል ካገለገለ በኋላ በሚያዝያ ወር 33 ዓ.ም ሞተ።

ከዜሮ ዓመት ለመጀመር 33 ዓመታት እንቀንስ።

2,267 – 33 = 2,234 ዓመተ ዓለም፤ ይህም ይስሐቅ የተወለደበት ዓመት ነው።

 

ይህንን ዓመት ለማረጋገጥ ስንፈልግ ብዙ የታሪክ ምሑራን ሰሎሞን መንገስ የጀመረው በ970 ዓመተ ዓለም ነው እንደሚሉ እናገኛለን።

ይህንን ቀን በትክክል ለማግኘት አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን 970 ዓመተ ዓለምን ወደ ትክክለኛው እንደሚቀርብ አድርገን መቀበል እንችላለን።

ዓመታቱን ከይስሐቅ መወለድ ጀምረን ሰሎሞን ቤተመቅደሱን መገንባት እስከጀመረበት ዓመት ድረስ እንቁጠር።

ለአሰራር እንዲቀለን ዓመታቱን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዓመት እንቆጥርና ከዚያ በኋላ ወደ ዘመናዊው የአሕዛብ ዓመታት እንቀይራቸዋለን።

ዘፍጥረት 25፡26 ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።

ያዕቆብ በተወለደ ጊዜ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበር።

ዘፍጥረት 41፡46 ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፥ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።

ዘፍጥረት 41፡47 በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ።

48 በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመት እህል ሁሉ ሰበሰበ፥ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ።

7ቱ የጥጋብ ዓመታት ሲያልቁ ዮሴፍ ዕድሜው 30 + 7 = 37 ዓመት ነበረ።

ዮሴፍ በሰጠው ትርጓሜ መሰረት የፈርኦን ሕልም 7 መልካም የበረከት ዓመታት እና 7 የረሃብ ዓመታት እንደሚመጡ ያሳያል።

ዘፍጥረት 41፡29 እነሆ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ፤

30 ደግሞ ከዚህ በኋላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል፥ በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል፤ ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል፤

ረሃቡ ከጀመረ በኋላ የዮሴፍ ወንድሞች ምግብ ፍለጋ ወደ ግብጽ መጡ። ዮሴፍም ረሃቡ እስኪያበቃ ድረስ ገና 5 ዓመታት እንደሚቀረው ተናገረ።

ዘፍጥረት 45፡11 በዚያም … እመግብሃለሁ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና።

ከረሃቡ ዓመታት ላይ ሁለት ዓመታት ስላለፉ ዮሴፍ ዕድሜው 37 + 2 = 39 ዓመት ነበር።

የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸውን ያዕቆብን ሊያመጡ ሄዱ፤ እርሱም በፈርኦን ፊት በቆመ ጊዜ የ130 ዓመት ሰው ነበረ።

 

ዘፍጥረት 47፡8 ፈርዖንም ያዕቆብን፦ የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው? አለው።

9 ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤

ስለዚህ ዮሴፍ 39 ዓመቱ በነበረ ጊዜ ያዕቆብ 130 ዓመቱ ነበረ።

ስለዚህ ዮሴፍ ሲወለድ ያዕቆብ 91 ዓመቱ ነበር።

ያዕቆብ በተወለደ ጊዜ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበረ። ከይስሐቅ መወለድ በኋላ 60 ዓመታት አልፈዋል።

ዮሴፍ ሲወለድ ያዕቆብ 91 ዓመቱ ነበረ። 60 + 90 = 151 ዓመታት ከይስሐቅ መወለድ በኋላ አልፈዋል።

ዘፍጥረት 50፡26 ዮሴፍም በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ፤

151 + 110 = 261 ዓመታት ከይስሐቅ መወለድ አንስቶ እስከ ዮሴፍ መሞት ድረስ አልፈዋል።

እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከዘሩ ጋር ቃልኪዳን ባደረገ ጊዜ በአብራሐም ወገብ ውስጥ የነበረው የመጨረሻው የአብራሐም ዘር ትውልድ ዮሴፍ ነበረ። ስለዚህ ቃልኪዳኑ ከአብራሐም፣ ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ፣ እና ከዮሴፍ ጋር ነበር።

 

ዕብራውያን 7፡9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤

10 መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና።

እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከዘሩ ጋር ቃኪዳን ባደረገ ጊዜ የ12ቱ ነገዶች አባቶች ሌዊ እና ወንድሞቹ በቅድመ አያታቸው በአብራሐም ወገብ ውስጥ ነበሩ።

ዮሴፍ ሲሞት ከአብራሐም ጋር የተደረገው ቃል ኪዳን ተጠናቀቀ።

ዘፍጥረት 15፡13 አብራምንም አለው፦ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ፤ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።

ግብጽ ውስጥ የነበሩ አይሁዶች ዮሴፍ በሕይወት ሳለ ግብጾች አላስጨነቋቸውም።

ግብጾቹ አይሁዶችን ማስጨነቅ የጀመሩት ዮሴፍን የማያውቅ ፈርኦን ከተነሳ በኋላ ነው። ይህም የሆነው ከ30 ዓመታት በኋላ ነው።

ዘጸአት 1፡8 በግብፅም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ።

ዘጸአት 1፡11 በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።

ዘጸአት 12፡41 እንዲህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ሠራዊት ሁሉ ከግብፅ ምድር ወጣ።

አይሁዶች ከግብጽ ከመውጣታቸው በፊት ግብጽ ውስጥ 30 ዓመታት በሰላም 400 ዓመታት ደግሞ በጭንቀት በባርነት አሳልፈዋል።

261 + 430 = 691 ዓመታት ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ አይሁዶች ከግብጽ እስኪወጡ ድረስ አልፈዋል።

1ኛ ነገስት 6፡1 የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

691 + 480 = ይስሐቅ ከተወለደ 1,171 በኋላ ሰሎሞን ቤተመቅደሱን መስራት ጀመረ።

1,171 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታትን ወደ እኛ ረዘም ያሉ ዓመታት ስንቀይር ፡- 1,171/70 = 1,154 ዓመታት እናገኛለን።

ስለዚህ 1,171 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት = 1,171 – 17 = 1,154 የእኛ ዓመታት።

ከይስሐቅ መወለድ ማለትም ከ2,234 ዓመተ ዓለም - 1,154 = 1,080 ዓመተ ዓለም ሲሆን ይህም 970 ዓመተ ዓለም ላይ ሊደርስ 110 ዓመታት ይቀሩታል።

ሆኖም በመሳፍንት ዘመን ለ111 ዓመታት በዙርያቸው ባሉ የአሕዛብ ነገዶች ተጨቁነው አሳልፈዋል።

ጠላቶቻቸው እየገዙዋቸው ስለነበረ እግዚአብሔር እነዚህን ዓመታት አልቆጠራቸውም። ይህም አይሁዳውያን በተስፋይቱ ምድራቸው ውስጥ በራሳቸው ሕግ እየኖሩ አልነበሩ ማለት ነው። በወታደራዊ ቀምበር እና ጭቆና ስር ሆነው በእግዚአብሔር በማያምኑ ጠላቶቻቸው እየተገዙ ነበር። ይህም ልክ ግብጽ ውስጥ ለግብጻውያን ባሪያ እንደነበሩበት ጊዜ ማለት ነው። ስለዚህ ግብጽ ውስጥ ከነበሩበት ባርነት አላመለጡም ነበር ምክንያቱም በፊት ግብጽ ውስጥ በባርነት ነበሩ ከዚያ በኋላ ግን እሥራኤል ውስጥ በባርነት ይኖሩ ነበር።

መሳፍንት 3፡8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በመስጴጦምያ ንጉሥ በኵሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኵሰርሰቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት።

መሳፍንት 3፡14 የእስራኤልም ልጆች ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎም አሥራ ስምንት ዓመት ተገዙለት።

መሳፍንት 4፡3 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሀያ ዓመት ያህል እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።

መሳፍንት 6፡1 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።

መሳፍንት 10፡7 የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በፍልስጥኤማውያንና በአሞን ልጆች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።

8 በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።

መሳፍንት 13፡1 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።

8 + 18 + 20 + 7 + 18 + 40 = 111 ዓመታት፤ እነዚህ ዓመታት በጠላቶቻቸው የተገዙባቸውና ጠላቶቻቸውን ያገለገሉባቸው ዓመታት ስለሆኑ አልተቆጠሩም።

ወደ አሕዛብ ዓመት ስንቀይረው ፡- 111 – 2 = 109 ዓመታት።

1080 – 109 = 971 ዓመተ ዓለም ሰሎሞን ቤተመቅደሱን መገንባት የጀመረበት ዓመት ነው።

ስለዚህ ሰሎሞን ቤተመቅደሱን መገንባት ከመጀመሩ በፊት ሶስት ዓመታት አልፈው ከሆነ ከዚያ ሶሰት ዓመታት ቀድሞ ነው መንገስ የጀመረው ማለት ነው፤ ማለትም በ971 + 3 = 974 ዓመተ ዓለም፤ ይህም የታሪክ ምሑራን ሰሎሞን ቤተመቅደሱን መገንባት የጀመረበት ዓመት ብለው ከሚገምቱት ዓመት ጋር በጣም ይቀራረባል።

ስለዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አቆጣጠር የትንቢቱ 2,300 ዓመታት የተጀመሩት ፍጥረታዊው የተስፋ ልጅ ከተወለደበት ዓመት ሆኖ የተጠናቀቁት ደግሞ መንፈሳዊው የአብራሐም ዘር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሞት ነው።

ዳንኤል 8፡15 እኔም ዳንኤል ራእዩን ባየሁ ጊዜ ማስተዋሉን ፈለግሁ፤ እነሆም፥ የሰው ምስያ በፊቴ ቆሞ ነበር።

ዳንኤል 8፡16 በኡባልም ወንዝ መካከል፦ ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ።

እነዚህን ራዕዮች መንፈስ ቅዱስ ካልገለጠልን በቀር ከታሪክ እንዲሁም ከቀሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማይጋጭ መልኩ መረዳት አንችልም።

ዳንኤል 8፡17 እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ።

ወደ ዘመን መጨረሻ ተቃርበን ከሆነ እነዚህ ትንቢቶች ግልጽ እየሆኑልን ይሄዳሉ።

እነዚህ ትንቢቶች ሚስጥር እንደሆኑ ከቀሩ ወደ ዘመን መጨረሻ አልቀረብንም ማለት ነው።

ነገር ግን እሥራኤል በ1948 ዓ.ም በይፋ መንግስት ሆና ተቋቁማለች። ከጥንታዊው ግዛቷ አብዛኛውን መሬት በ1967 ዓ.ም ተቆጣጥራለች። በ2018 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና ሰጠ። እስራኤል ወደ ሃገሯ ተመልሳለች፤ ስለዚህ ያቆጠቆጠችው በለስ ወደ መጨረሻው ዘመን መቅረባችንን በግልጽ የምታሳይ ምልክት ናት።

እግዚአብሔር ወደ አይሁዳውያን በሚመለስበት ጊዜ ቤተክርስቲያንን በንጥቀት ከምድር ያስወግዳታል።

አይሁዶች ወደ ሃገራቸው ከገቡ ወዲህ በግልጽ እንደምናየው እግዚአብሔር ትኩረቱን ወደ አይሁድ እየመለሰ ነው።

ዳንኤል 8፡18 ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ።

እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከዘሩ ጋር ቃልኪዳን በገባ ጊዜ አብራሐም ከባድ እንቅልፍ ወድቆበት ነበር።

ዳንኤልም መረዳትን ሊቀበል ሲል ከባድ እንቅልፍ ወደቀበት።

ዳንኤል 8፡19 እንዲህም አለኝ፦ እነሆ፥ በመቅሠፍቱ በመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን አስታውቅሃለሁ፤ ይህ ለተወሰነው ለፍጻሜ ዘመን ነውና።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። ድንግል ሴት ንጹህ ሴት ናት። ይህም የዳነች ቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው። ስለዚህ የአስሩ ቆነጃጅት ምሳሌ የዳኑ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ይወክላል፤ እነዚህም በመንፈስ የተሞሉ እና ያልተሞሉ ክርስቲያኖች በሙሉ ናቸው።

በምሳሌው መሰረት በመጨረሻው ዘመን ሁላቸውም እንቅልፍ ተኝተዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ለሰዎች መገለጥ ሊሰጥ ሲመጣ ሰዎች እንቅልፍ ይወድቅባቸዋል።

ዳንኤል 8፡20 ባየኸው በአውራው በግ ላይ የነበሩ ሁለቱ ቀንዶች እነርሱ የሜዶንና የፋርስ ነገሥታት ናቸው።

 

 

ቀይ ቀለም ያለበት ቦታ ከታላቁ የፋርስ ንጉስ ከቂሮስ ጋር በመተባበር ሜዶናውያን የሚያስተዳድሩት ግዛት ነው።

አረንጓዴው የፋርስ መንግስት ግዛት ነው።

ዳንኤል 8፡21 አውራውም ፍየል የግሪክ ንጉሥ ነው፤ በዓይኖቹም መካከል ያለው ታላቁ ቀንድ መጀመሪያው ንጉሥ ነው።

ከዚያ በኋላ ታላቁ አሊግዛንደር ከግሪክ መጣ፤ እርሱም ከምዕራባውያን ወገን ለመጀመሪያ ጊዜ እራሱን አምላክ አድርጎ የሰየመ ንጉስ ነው። የስኬቶቹ አስደናቂነትና ብዛት ብዙ ሰዎች እርሱ አምላክ ነው ብለው እንዲያምኑ አደረጋቸው።

ዳንኤል 8፡22 እርሱም በተሰበረ ጊዜ በእርሱ ፋንታ አራቱ እንደ ተነሡ፥ እንዲሁ ከወገኑ አራት መንግሥታት ይነሣሉ፥ ነገር ግን በኃይል አይተካከሉትም።

ለ20 ዓመታት ያህል ከባድ እልቂት የተፈጸመበት ጦርነት ከተዋጉ በኋላ አራቱ የሊግዛንደር ጀነራሎች ግዛቱን ለአራት ተከፋፈሉ። እያንዳንዳቸው አሊግዛንደር ይዞ ከነበረው የመጀመሪያ ግዛት ከፊሉን ይዘው ነገሱ። አራቱም ጀነራሎች እራሳቸውን ሰው-አምላክ ነን ብለው አወጁ።

 

 

ከዳንኤል አንጻር ከዚህ ግዛት ውስጥ ትኩረት የሚስበው ቦታ ከጴርጋሞን ከተማ ዙርያ ያለው ትንሽ ቦታ ሲሆን ይህም ቂሮስ ባቢሎንን ካሸነፈ በኋላ የባቢሎን ካሕናት ሚስጥራዊ ሐይማኖታቸውን እንደገና የመሰረቱበት ሥፍራ ነው። ይህም ትንሽ ግዛት እጅግ ባለጸጋ ወደ ሆነው የጴርጋሞን መንግስትነት አደገ፤ የጴርጋሞንም ንጉስ ባቢሎን ሚስጥር ካሕናት አማካኝነት ካሕን-ንጉስ፣ ሰው-አምላክ እና ፖንቲፍ ተብሎ እውቅና ተሰጠው።

በ133 ዓመተ ዓለም እጅግ ሃብታም የሆነችዋ የጴርጋሞን መንግስት ለሮም ተሰጠች። በ63 ዓመተ ዓለም ሮማዊው ንጉስ ዩልየስ ፖንቲፍ ሆነ፤ ከሞተም በኋላ ሰው ሆኖ እንደ አምላክ የተመለከ የመጀመሪያው ሰው ሊሆን ችሏል። በዚህም መንገድ የባቢሎናውያን ሚስጥር በሮማ መንግስት ውስጥ ተደላድሎ ተቀመጠ። በ450 ዓ.ም የሮም ጳጳስ ፖንቲፍ ወይም ፖፕ የተባለውን ማዕረግ ተቀበለ። ስለዚህ የባቢሎናውያን ሚስጥር ወደ ሮማ ካቶሊክ መንፈሳዊ መንግስት ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም በዓለም ዙርያ የገንዘብ እና የፖለቲካ ኃይል ሆና ተስፋፋች።

ታላቁ አሊግዛንደር እንደ አምላክ ለመቆጠር የመጀመሪያው ሰው ባይሆንም እራሱን አምላክ ማድረጉ ግን ለግሪካውያን ነገስታት እና ለሮማውያን ነገስታት እንዲሁም ለሌሎች መሪዎች ምሳሌ ትቶ አልፏል።

በ1302 ፖፕ ቦኒፌስ 7ኛው የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባል መሆን አስፈላጊ ነው አለ። የፖፑ ስልጣን የቤተክርስቲያን ዋና ራስ መሆኑን አወጀ። ስለዚህ ሁሉም ሰው የቤተክርስቲያን አባል ለመሆንና የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ለፖፑ መገዛት አለበት። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን እና የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ወይም ለመዳን እያንዳንዱ ሰው ለፖፑ መገዛት ግድ ሆነበት። በዚህም ምክንያት በምድር ላይ ፖፑ በእግዚአብሔር ቦታ ተቀመጠ። መዳንም የሚገኘው ለፖፑ በመታዘዝ ሆነ።

በጨለማው ዘመን ውስጥ ፖፑ የስርየት ወረቀቶችን ይሸጥ ነበር፤ ይህም ፖፑ ሐጥያትን ይቅር የማለት ስልጣን አለው ለማለት ነው። በዚህም መንገድ ፖፑ እራሱን በእግዚአብሔር ቦታ አስቀመጠ።

በ1870 ፖፑ ፍጹም የማልሳሳት ሰው ነኝ ብሎ ስለ ራሱ አወጀ፤ ስለዚህ በምድር ላይ ራሱን አምላክ አደረገ። ነገር ግን የማይሳሳተው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ስለዚህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሃብታም እና ኃይለኛ ድርጅት ሆናለች፤ ወደ ፊትም የዓለም ሁሉ ገዢ የመሆን እቅድ አላት።

ዳንኤል 8፡23 በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቈቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል።

በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ ክፋት ጽዋውን ይሞላል። ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ እንደተጻፈው ሐይማኖተኛ እና አሳሳች የሆነ ነጭ ፈረስ ማለትም ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ ሆኖ በ860 ዓ.ም ተሹሟል። ይህን ሹመት የተቀበለ ፖፕ በ1310 ዓ.ም ዘውዱን ባለ ሶስት ድርብ አደረገው። ከዚያ በኋላ የሮማ ካቶሊክ ፖለቲካዊ ኃይል የሆነው ቀይ ፈረስ በጨለማው ዘመን እና በተሃድሶው ዘመን ደግሞ በጸረ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በ1500ዎቹ የማርቲን ሉተርን ተሃድሶ በመቃወም ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የካቶሊክ ተቃዋሚዎችን ገድሏል። በየዘመናቱ የካቶሊክ ፖፕ ተጽእኖ እያደገ ሄዶ በአሁኑ ሰዓት በዓለም ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ፖፑ ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ሰው ሆኗል። ከዚያ በኋላ የገንዘብን ኃይል የሚወክለው ጥቁር ፈረስ ቫቲካንን ከዓለም ሃብታም ድርጅቶች ውስጥ አንደኛ ያደርጋታል። በዚህም የቤተክርስቲያኒቱ እርኩሰት ጫፍ ላይ ይደርሳል።

ከዚያም በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ ዲያብሎስ የፖፕ ስልጣን ላይ የሚቀመጥ ሰው ውስጥ ይገባል።

ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።

የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ በተለመደው መንገድ በካርዲናሎች ምክር ቤት ተመርጦ አይደለም ፖፕ የሚሆነው። በቀስታ መጥቶ በማታለል ነው ወደ ፖፕ ስልጣን ላይ የሚወጣው። ፊተ ጨካኝ ንጉስ። እንዲህ ዓይነቱን ሰው መቃወም ቀላል አይሆንም።

እንቆቅልሽ የሚያስተውል። ጥልቅ ሚስጥር ያላቸው ነገር ግን ሰዎችን የሚያሳስቱ ንግግሮችን ይናገራል። ሰላማዊ ሰው የመምሰል ችሎታ አለው፤ ስለዚህ በዚህ ችሎታው ተጠቅሞ በሚፈጥረው ሰላም ብዙዎችን ያታልላል።

ሰላም የማይፈልግ ማነው? ሰላምን ሲያሰፍን ሰው ሁሉ ይደነቅበታል። ነገር ግን ሰላሙ ጊዜያዊ ሰላም ነው።

1ኛ ተሰሎንቄ 5፡3 ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።

ዳንኤል 8፡24 ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም፤ በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል፤ ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል።

የመጨረሻው ፖፕ (ምናልባት ዳግማዊ ጴጥሮስ) ታላቅ ሐይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ እና የገንዘብ ኃይል ይኖረዋል። ነገር ግን ወታደራዊ ኃይል ይጎድለዋል። ስለዚህ ወታደራዊ ኃይልን ከአስር ፈላጭ ቆራጮች ያገኛል።

ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።

እንደ ነገስታት ስልጣን። የንጉስ ዓይነት ስልጣን አላቸው ግን ዘውድ አልጫኑም። እነዚህ 10 ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።

ይህ መልእክት በተጻፈበት በ2019 ዓ.ም አውሮፓ ውስጥ ፖፑ ብቸኛው ፈላጭ ቆራጭ ነው።

“አንድ ሰዓት” ማለት የታላቁ መከራ 3½ ዓመት አጭር ጊዜ ነው።

ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።

አንድ ሃሳብ። አስር ፈላጭ ቆራጮች ማለትም ዳንኤል ባየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ ያሉት አስር የእግር ጣቶች ሁላቸውም ለመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ይታዘዛሉ። እነዚህ አስር ፈላጭ ቆራጮች ወታደራዊ ኃይላቸውን ለፖፑ ይሰጣሉ። አስር የጦር ሰራዊቶችን በዓለም ዙርያ ማሰማራት ዓለምን ለመቆጣጠር አመቺ ስልት ነው። የትም ቦታ ብጥብጥ ቢነሳ በአቅራቢያው ያለው ወታደራዊ ኃይል ብጥብጡን ወይም ተቃውሞውን ጨፍልቆ ጸጥ ያሰኘዋል።

ይህ ስልት በጣም አዋጪ ነው፤ ምክንያቱም አሜሪካ ካለችበት ተነስታ ወደ ሌላ የዓለም ክፍል ወታደራዊ ኃይሏን ለማዝመት 6 ወራት ይፈጅባታል። እንደዚያም ሆኖ እንኳ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል በአንድ ጊዜ ሁለት ቦታ መሰማራት ይከብደዋል።

የክርስቶስ ተቃዋሚ በየስፍራው ባሰማራቸው ጦር ሰራዊቶች አማካኝነት የሚቃወሙትን በፍጥነት መቆጣጠር ይችላል። ሰነፎቹን ቆነጃጅት ማለትም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ስትነጠቅ ንጥቀት ያመለጣቸውን ክርስቲያኖች ይገድላቸዋል።

ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ዓለም አቀፍ የገንዘብ፣ የፖለቲካ እና ሐይማኖታዊ ኃይል ለማግኘት በአንድነት ይጣመራሉ። ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ስኬት መኮረጅ ነው። አውሬው የሮማ ካቶሊክ ሐይማኖት ነው። የአውሬው ምስል ማለት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ድርጅታዊ አሰራር የሚኮርጁ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ሕብረት ነው። በአሁኑ ሰዓት አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባገነን መሪ ፖፑ ነው። የፕሮቴስታንት ፓስተሮችም ቤተክርስቲያናቸውን እንደ አምባገነን መሪ ነው የሚያስተዳድሯቸው። ይህም አንድ ግለሰብ ብቻውን ቤተክርስቲያን የሚመራበት ፖሊሲ ነው። ዲኖሚኔሽናዊ ፖሊሲዎችን የሚቃወሙ ሰዎች በስተመጨረሻ ይገደላሉ።

“ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል”

እነዚህ አይሁዶች ናቸው። ቫቲካን የዓለምን ሁሉ ወርቅ ማግኘት የምትችልበት መንገድ አላት። አይሁዶች በእስቶክ ኤክስቼንጅ ገበያ ውስጥ ያለው ገንዘብ በእጃቸው ነው። የተሰወሩ እንቆቅልሾችን በመረዳት የመጨረሻው ፖፕ ከአይሁዶች ጋር ኢኮኖሚያዊ ቃልኪዳን ያደርጋል። ከዚያ ገንዘባቸውን በሙሉ ከወሰደ በኋላ ቃልኪዳኑን ያፈርሳል። በዚህ መንገድ አይሁዶችን በወታደራዊ ኃይል ከማጥቃቱ በፊት በኢኮኖሚ ያደቅቃቸዋል።

ዳንኤል 8፡25 በመታለሉ ተንኰልን በእጁ ያከናውናል፤ በልቡም ይታበያል፥ ታምነውም የሚኖሩትን ብዙዎችን ያጠፋል፤ በአለቆቹም አለቃ ላይ ይቋቋማል፤ ያለ እጅም ይሰበራል።

“ተንኮል” የእጅ ሥራ ነው። የፋብሪካ ምርት። ዓለም ወደ ኪሳራ ውስጥ እየወደቀች ባለችበት ሰዓት ለብዙዎች የሥራ ዕድሎችን ይከፍታል።

ራዕይ 13፡17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።

ነገር ግን ሥራ ማግኘት ከፈለጋችሁ የዚህ የአንድ ዓለም መንግስት ወይም አንድ የዓለም ሐይማኖት አባል መሆን ግዴታችሁ ነው።

ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ የሰው ኃይል ሊያስቆመው አይችልም። በምድር ላይ እራሱን እንደ እግዚአብሔር በዙፋን ያስቀምጣል። እርሱን ሊያጠፋው የሚችለው ጌታ በአርማጌዶን ጦርነት ጊዜ ተመልሶ ሲመጣ ብቻ ነው።

ዳንኤል 8፡26 የተነገረውም የማታውና የጥዋቱ ራእይ እውነተኛ ነው፤ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ ስለሚሆን ራእዩን ዝጋ።

ይህንን ራዕይ መረዳት የምንችለው በመጨረሻው ዘመን ብቻ ነው።

የአይሁዶች ቀን ከሌላው ሃገር አቆጣጠር ይለያል። ሲመሽ ይጀምራል፤ ከዚያም ሌሊት ይሆናል፤ ከዚያም ቀን ይነጋል።

ነገር ግን “ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ” ተብሎ ተጽፏል። ስለ ሌሊቱ ምንም አልተባለም። ለምን?

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ምንድርን ምንም ነገር ሳይጠቀም ነው የፈጠራት። እግዚአብሔር ምድርን ለሰው ኑሮ ምቹ እንድትሆን አድርጎ በፈጠራት ጊዜ የተወሰነ የጊዜ መለኪያ መርጦ ቀን ብሎ ጠራው።

ዘፍጥረት 1፡5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።

ቀንም ሌሊትም ነበረ፤ እግዚአብሔር ግን ለሌሊቱ ትኩረት አልሰጠውም። ጨለማ ማለት የብርሃን አለመኖር ብቻ ነው።

እግዚአብሔር የብርሃንን አለመኖር ጊዜን የመፍጠር አካል አድርጎ አልቆጠረውም።

እግዚአብሔር ቀን ብሎ በሚቆጥረው ጊዜ ውስጥ የሚያስበው ብርሃንን ብቻ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔርን ልናገለግል ስንሞክር እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስሕተቶች ውስጥ የምንንከባለልበትን ወቅት ከአገልግሎት አይቆጥርልንም፤ ምክንያቱም ስሕተት ውስጥ ስንሆን ብርሃን በሌለበት ነው የምንመላለሰው። እግዚአብሔርን የምናገለግለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ስናምን እና ስንመላለስ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ያለን ብርሃን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ስለ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ብዙም አልተጨነቀም። ኢየሱስ ሐዋርያትን አሰለጠናቸው፤ እነርሱም እውነቱን በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ጽፈው አስቀመጡ። ሐዋርያት የመጨረሻው ሐዋርያ ዮሐንስ በ100 ዓ.ም አካባቢ እስኪሞት ድረስ ቤተክርስቲያንን በስነ ሥርዓት ጠብቀው አቆዩ። ከዚያ በኋላ ዓለም ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ስትገባ እውነት ቀስ በቀስ እየደበዘዘች እንደምትጠፋ እግዚአብሔር አውቋል። ከዚያ በኋላ የተሃድሶ እና የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲሁም የጴንጤ ቆስጤያዊ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ መምጣት ቤተክርስቲያንን መልሶ ያነቃቃታል፤ ሆኖም ግን ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች እና ስሕተቶች ከቤተክርስቲያን ቶሎ ሳይወገዱ ይቆያሉ።

ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ነብይ ዊልያም ብራንሐም ከ1947 እስከ 1965 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት የሚገልጡ ስብከቶቹን በድምጽ ቀርጾ አስቀመጠ። ይህ የዘመን መጨረሻ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መገለጥ እግዚአብሔር ትልቅ ትኩረት የሰጠበት ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱ የዘመኑ መጨረሻ ስሕተት በቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ የሚበዛበት ጊዜ ነው። የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን (ልጆች) ወደ አዲስ ኪዳን ሐዋርያት (ወደ አባቶች) እምነት መመለስ አለባት። የቃሉን ሙሉ እውነት የያዙር ሐዋርያት ብቻ ነበሩ። ቃሉ ደግሞ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ሕጻናት (የመጨረሻ ዘመን ክርስቲያኖች) ወደ እኔ እንዲመጡ (ትክክለኛው የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት) አትከልክሏቸው ነው ያለው እንጂ ወደ ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች እና ወደ ልማዶቻቸው እንዲሁም አስተምሕሮዋቸው ይሂዱ አላለም።

ማቴዎስ 19፡14 ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤

ዛሬ ቤተክርስቲያኖች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንዲከተሉ አይፈቅዱም። ቤተክርስቲያኖች እረኛው ፓስተሩ ነው ይላሉ፤ ነገር ግን ይህ እውነት መሆኑን የሚመሰክር አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም። “ፓስተሮች” አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሱት ነገር ብሉይ ኪዳን ውስጥ በትንቢታዊ ቃል ስድስት ጊዜ ተወግዘዋል። አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ መጠቀስ ለፓስተሩ ቤተክርስቲያን ላይ ምንም ስልጣን አይሰጠውም።

ነገር ግን ሰዎች ከቤተክርስቲያን ልማድ ጋር አንስማማም ቢሉ እና ፓስተሩን ቢቃወሙ ከቤተክርስቲያን ይባረራሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በትክክል መከተል የሚፈልጉ ሰዎች በዘመኑ መጨረሻ ኢየሱስ በቃሉ እንደተናገረው የእውነት መከራ ይቀበላሉ።

ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን መገለጥ የሌሊት ብርሃን ነው።

ታላቁ መከራ የሌሊት ጨለማ ሰዓት ነው።

የንጋቱ ብርሃን የ1,000 ዓመቱ የሰላም መንግስት ነው።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ “ማታ እና ጥዋት” ሲል ስለ መጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን እየተናገረ ነው። በማታ የሚበራው ብርሃን ለመጨረሻዋ ዘመን ሙሽራ የሐዋርያትን አዲስ ኪዳናዊ እውነት ያበራላታል። ከዚያ በኋላ ንጥቀት ሲመጣ ከምድር ተነጥቃ ወደ ሰማይ ትሄዳለች።

ሙሽራይቱ በሰማይ በሚደረገው የበጉ ሰርግ ላይ ስለምትገኝ ታላቁ መከራ ምድርን በሚያስጨንቅበት ሰዓት አትገኝም።

ከዚያ በኋላ በታላቁ መከራ መጨረሻ ኢየሱስ ለአርማጌዶን ጦርነት ሲመለስ ሙሽራይቱ አብራው ትመጣለች፤ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ አውሬውን ያጠፋውና የ1,000 መንግስት ይመሰርታል፤ ይህም መንግስት ለምድር የንጋት ብርሃን ነው ምክንያቱም በምድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ሰላምን ያመጣል።

ስለዚህ “ማታ እና ጥዋት” ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ምሽት ውስጥ አታልፍም ማለት ነው።

ዳንኤል 8፡26 የተነገረውም የማታውና የጥዋቱ ራእይ እውነተኛ ነው፤ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ ስለሚሆን ራእዩን ዝጋ።

ይህ ትንቢት የእውነተኛዋን ቤተክርስቲያን መጨረሻ ነው ሚገልጠው።

ከፊል የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እና ከፊል የቤተክርስቲያን ልማዶችና ስሕተቶች ብቻ የሚሰበክበት ጊዜ ስለሆነ ግራ የሚያጋባ ዘመን ነው፤ ይህም ክርስቲያኖችን እንዲድኑ ያስችላቸዋል ግን ከታላቁ መከራ ማምለጥ አያስችላቸውም። እውነተኛዋ ሙሽራ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ እውነቶች በምሽት ከሚበራው ብርሃን መልእክተኛ ትማራለች። ወደ ሰማይ ተነጥቃ ስለምትሄድ ከታላቁ መከራ ሌሊት ታመልጣለች። ከዚያ በኋላ የ1,000 ዓመቱ መንግስት ሲጀምር ለሚፈነጥቀው ንጋት ተመልሳ ትመጣለች።

ዘካርያስ 14፡6 በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።

በመጨረሻ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ለመዳን የሚበቃ ብርሃን ብቻ ስለሚኖር በጣም ከባድ ጨለማ አይሆንም። ነገር ግን ያለው ብርሃን ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ለመረዳት የሚበቃ አይደለም፤ ስለዚህ ድብዝዝ ያለ እና በደምብ የማይደምቅ ብርሃን ነው። ይህ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ፤ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች አሉ፤ አፈ ታሪኮች አሉ ብለው የሚያምኑ ክርስቲያኖች ያሉበት ግራ የሚያጋባ ዘመን ነው።

ቃሉ ግን ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው በተናገሩ ሰዓት ሳያውቁት ኢየሱስ ስሕተት አለበት ማለታቸው ነው። ኢየሱስ ግን ፍጹም ነው።

ስለዚህ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስም ፍጹም ነው።

አንድ ቀን የእግዚአብሔር ቃል ይፈርድብናል።

7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።

ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ በቆመበት ቆመን ከሆነ ለአጭር ጊዜ ፈንጥቆ የዳኑ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ያለውን ጨለማ የሚገፍፈው የብርሃን ጮራ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን መረዳት እንድንችል ያግዘናል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት በቂ ብርሃን ስለሆነ የእግዚአብሔር ቃል ፍጹም መሆኑን እንድንገነዘብ ይረዳናል።

ብርሃን ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተየተጻፈውን ቃል የመረዳት ችሎታ ነው።

ዳንኤል 8፡27 እኔም ዳንኤል ተኛሁ፥ አያሌም ቀን ታመምሁ፤ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ የንጉሡን ሥራ እሠራ ነበር፤ ስለ ራእዩም አደንቅ ነበር፥ የሚያስተውለው ግን አልነበረም።

ራዕይ ለማየት የሚያበቃ መንፈሳዊነት በአካልም አድካሚ ነው። ስጋችን በእግዚአብሔር መንፈስ ፊት ሲቀርብ በጣም ይደክማል። ነገር ግን ለእኛ የተሰጠን ታላቅ ክብር ደግሞ ዳንኤል በሰዓቱ ሊያስተውል ያልቻለውን ሚስጥር እግዚአብሔር በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ መግለጡ ነው።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23