ዳንኤል ምዕራፍ 7፡ የዱር አራዊት ያሉበት ሁለተኛ ራዕይ በአሕዛብ ምስሉ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ያሳያል
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዳንኤል 7፡2 ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ በሌሊት በራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በታላቁ ባሕር ላይ ይጋጩ ነበር።
ነፋሳት የሚያመለክቱት ግጭቶችንና ጦርነቶችን ነው። አንድ ሃገር ሌሎች ሃገሮችን ሁሉ ማንበርከክ እና መግዛት በመፈለጓ እና በአሕዛብ ግፈኝነት የተነሳ ዓለም ሁልጊዜ በግጭትና በጦርነት እንደተሞላች ናት። ይህም አንድ ሰው በሌሎች ላይ የበላይ የመሆን ፍላጉቱ መገለጫ ነው። የሰማይ ነፋሳት በሚለው ውስጥ “ሰማይ” መንፈሳዊ ክልል ነው። ስለዚህ ይህ ራዕይ በሃገሮች መካከል የሚደረገውን ጦርነት መንፈሳዊ ገጽታውን ይገልጣል። ከግኡዙ ዓለም በስተጀርባ በሰዎች ዓይን በማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ጦርነቶቹ ይቀጥላሉ። እኛ የምናየው ግኡዝ የሆነውን መገለጫቸውን ብቻ ነው።
የአሕዛብ ሃገሮችን የሃይል ጥማት ትግል የሚቀሰቅሰው መንፈስ አስቀያሚ መንፈስ ነው።
ዳንኤል 7፡3 አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች።
ባሕር የሚወክለው በፋሽን፣ በሰዎች አመለካከት፣ ልማድ እና በግል የሃብትና የስልጣን ጥማት ሞገዶች ወዲያ እና ወዲህ የሚንገላታውን የሚፍገመገመውን እረፍተ ቢስ ሕዝብ ነው።
ዳንኤል መጀመሪያ እነዚህን አራት መንግስታት ማለትም ባቢሎን፣ ፋርስ፣ ግሪክ፣ እና ሮም የአንድ ሰው ምስል ሆነው ነበር ያያቸው። ባቢሎን የወርቁ ራስ ነው። ፋርስ ከብር የተሰሩት ክንዶች እና ደረት ናቸው። ግሪክ ሆዱ እና ታፋው ነው። ሮም ደግሞ ከብረት የተሰሩት ሁለቱ እግሮች ናቸው።
ብረቶቹ በጥንካሬ እየጨመሩ ቢሄዱም እንኳ በዋጋቸው ግን እየወደቁ ነው የሄዱት።
ይህም እኛ አሕዛብ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆንን ይገልጻል። ለገንዘብ እና ለስልጣን ተስገብግበን ስንሻማ ባሕርያችን ጠንካራ ይሆናል ግን ሰብዓዊነታችን እየጠፋ ይሄዳል።
በሁለተኛው ራዕይ ውስጥ ዳንኤል እነዚህኑ አራት መንግስታት በጨካኝ አውሬዎች ተመስለው አያቸው። ይህም የአሕዛብ መንግስታትን ጨካኝነት እና አውሬያዊ ግፈኛ ባህሪያቸውን ያሳያል። የእባቡ የአውሬነት ባህርይ በኤደን ገነት ውስጥ በሔዋን በኩል ወደ ሰው ዘር ተላልፏል። ቀየን ወንድሙን የገደለ ነፍሰ ገዳይ ሆነ ከዚያም ደግሞ በታሪክ ውስጥ እግዚአብሔርን ሊዋሽ የሞከረ ሰው ሆነ። “የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” ወንድሙ የት እንደደረሰ እንደማያውም ሊያስመስል መሞከሩ ነው።
ዳንኤል በራዕይ እንዳየው የአሕዛብ መንግስታትን ለመግደል እና ለመግዛት የሚያነሳሳቸው ይህ የአውሬነት ባህርይ ነው።
ዳንኤል 7፡4 መጀመሪያይቱ አንበሳ ትመስል ነበር፥ የንስርም ክንፍ ነበራት፤ ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፥ ከምድርም ከፍ ከፍ ተደረገች፥ እንደ ሰውም በሁለት እግር እንድትቆም ተደረገች፥ የሰውም ልብ ተሰጣት።
የመጀመሪያው መንግስት ባቢሎን ሲሆን የሚገኝበትም ቦታ በኤፍራጠስ እና በጤግሮስ ወንዞች መካከል ነው፤ ይህም የዛሬዋ ኢራቅ የምትገኝበት ቦታ ነው። ከዚህ በታች ባለው ካርታ ውስጥ ሜዲተራንያን ባሕር፣ ቀይ ባሕር፣ እና የፋርስ ባሕረ ሰላጤ በሰማያ ቀለም የተቀቡት ቦታዎች ናቸው። የባቢሎን መንግስት ዳር ድንበሮች በዚህ ካርታ ውስጥ ቀዮቹ መስመሮች ናቸው።
አንበሳ የአራዊት ንጉስ ነው። ናቡከደነጾር በባቢሎን ዙርያ ያሉትን ግዛቶች ሁሉ አንበርክኮ የገዛ ታላቅ ጦረኛ ንጉስ ነበረ። ባቢሎንን በዓለም ሁሉ ታላቅ ከተማ እና ታላቅ የንግድ ማዕከል አድርጎ ሰራት። እኛ አሕዛቦች ሞኝነታችን ስልጣን፣ ታዋቂነት፣ ሃብት እና ትልልቅ የሚያምሩ ሕንጻዎች የሕይወት ዋነኛ ቁምነገር ናቸው ብለን ማሰባችን ነው።
ባቢሎን በወርቅ ራስ እና በጨካኝ አንበሳ ነው የተመሰለችው። ወርቃማ ግን አደገኛ። የሐሰተኛ ሐይማኖት መልክ ይህ ነው።
ክንፎች ወፍን ወደ ላይ ለመብረር ያስችሏታል፤ ደግሞም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመስማት ወደ ሰማይ የመውጣት ምሳሌ ናቸው። ስለዚህ ወፎች በሰማይ እና በምድር መካከል ያለውን ግንኙነት ያመለክታሉ። ንስር የወፎች ንጉስ ነው፤ ከብዙዎቹ ወፎች በላይ ከፍ ብሎ ነው የሚበርረው።
ስለዚህ በምድር ላይ የሚመላለሰው ፖለቲካዊ ንጉስ (አንበሳው) የአየሩ (ንስር) መንፈሳዊ አረማዊ ሊቀካሕናት ወይም ፖንቲፍ ነው፤ ምክንያቱም ከፍ ብሎ መብረር እና ወደ እግዚአብሔር መጠጋት ይችላል። ይህም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ የሃገሩ ጦረኛ ፖለቲካኛ መሪ እንዲሁም የሐይማኖታዊ ማሕበረሰቡ መንፈሳዊ ሊቀካሕናት ወይም ፖንቲፍ እንዲሆን አስችሎታል (ሐይማኖታዊ ማሕበረሰብ ማለት ዛሬ ቤተክርስቲያን እንደምንለው ነው)።
ስለዚህ የባቢሎን መንፈስ ቤተክርስቲያን እና መንግስትን በአንድነት አጣምሮ ይይዛል።
አንድ ሰው ማለትም ናቡከደነጾር ንጉስም የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናትም ነበረ። ይኸው አንድ ሰው ሕዝቡ እንዴት መኖር እናዳለባቸው የሚነግራቸው ፖለቲከኛ መሪ እና ምን ማመን እንዳለባቸው የሚነግራቸው ሐይማኖተኛ መሪ ጭምር ነበር።
አንድ ሰው በሌሎች ሰዎች ላይ ይህን ሁሉ ስልጣን መያዙ በጣም ይበዛል።
ይህም ፖለቲካ ውስጥ ጥልቅ እያሉ ለሚገቡ የወንጌል አገልጋዮች ማስጠንቀቂያ ነው።
ይህ የባቢሎን ሚስጥር ሐይማኖት እንደመሆኑ ባቢሎናዊ ሐይማኖት እውነትን እንደሚቃወም እናውቃለን።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ንጉስ የካሕንን ሥራ እንዲሰራ እግዚአብሔር ፈቅዶ አያውቅም። ቤተክርስቲያን እና መንግስት ተለያየተው መቆም አለባቸው። አንበሳ ክንፍ ሲኖረው ከተፈጥሮ ባህርዩ ውጭ ይሆናል። ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው የፖለቲካ እና የሐይማኖት አገልጋይ መሆኑ ጠማማነት ነው።
ለምሳሌ ከኢጣሊያ የድሮ ሰንደቅ ዓላማዎች አንዱን ተመልከቱ። ክንፍ ያለው አንበሳ ሰይፍ ወይም ጩቤ (ለመግደል) ይዞ ከጭንቅላቱ በላይ ደግሞ የቅዱሳን ዓይን ክብ መስመር ይታያል።
ይህም የሚያሳየን ቅዱስ ነፍሰ ገዳይ - ወይም ሐይማኖታዊ ገዳይ ነው። ፖፑ ለመስቀል ዘመቻ ያሰማራቸውን “ክርስቲያኖች” አስቡ። ሄደው በእግዚአብሔር ስም ሰዎችን ገደሉ፤ ዘረፉ፤ አስገድደው ደፈሩ። የሰሩት ግፍ እና ነውር ቀፋፊውን የመስቀል ዘመቻ ታሪክ ጥላሸት ቀብቶታል። ፖፑ ደግሞ የመዳን መንገድ በመስቀል ዘመቻ ውስጥ መሳተፍ ነው ብሎ አሳምኗቸዋል። ብዙዎቹ ጋሻቸው ላይ ቀይ መስቀል አድርገው ነበር (ሰንደቅ ዓላማቸውም ላይ ቀይ መስቀል አለበት) እና አብዛኞቹ ከሸሚዛቻ በላይ በለበሱት መደረቢያ ደረት ላይ ትልቅ ቀይ መስቀል ምልክት አድርገው ነበር። የሚያሳዝነው ከደረታቸው ላይ የነበረው መስቀል በልባቸው ውስጥ የነበረውን ዲያብሎስ ሊደብቀው አልቻለም። እነዚህ የመስቀል ዘማቾች ሐይማኖተኛ ጂሃዲስቶች ነበሩ። በእግዚአብሔር ስም ሰዎችን ገደሉ። ዋናው ዓላማቸው መዝረፍ እና መሬት መያዝ ስነበረ ስራቸው ሁሉ ሐይማኖታዊ ጥመት ነበር።
ይህም ድሮ የፈጸሙት ግፍ የዛሬዎቹ ሙስሊም ጂሃድ ሽብርተኞች በበቀል እንዲዘምቱ አነሳስቷቸዋል። አሁን ሙስሊሞቹም መግደል እና መዝረፍ የመዳን መንገድ ነው ብለው ያስባሉ።
የፖፕ ጆን 23ኛውን ባክ ተመልከቱ (በስልጣን የቆየው ከ1410 እስከ 1415 ዓ.ም ነበር)። ይህም ባጅ ባለ ክንፍ አንበሳ አለበት።
ስለዚህ እራሳቸው ሳይክዱ እንደሚያሳዩን ሐይማኖታዊ ስሕተትን የሚወክለው ባለ ክንፉ አንበሳ ወደ ኢጣሊያ ገብቶ ፖፑን ተቆጣጥሮታል። ቢያንስ አሁን የት እንዳለ እናውቃለን።
ሶስቱ አይሁዳውያን ለተቀረጸ ምስል በመስገድ አናምንም ባሉ ጊዜ ናቡከደነጾር በእቶን እሳት ውስጥ ጥሎዋቸው ሊገድላቸው ሞከረ።
የመጀመሪያው የአሕዛብ መንግስት ሰዎች የአንድን ቅዱስ ሰው ምስል እንዲያመልኩ አስገደዳቸው። የመጨረሻው የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመን ሰዎች አንድን ቅዱስ ሰው እንዲያመልኩ ያስገድዳቸዋል። ወይ ፖፑን ወይ ዊልያም ብራንሐም በአሁኑ ሰዓት በተከታዮቻቸው ዘንድ የእግዚአብሔር ድምጽ ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፤ ስለዚህ በፍጹም የማይሳሳቱ ሰዎች እንደሆኑ እና ንግግራቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንደሆነ ይቆጠራል። የብራንሐም አገልግሎት በእውነት ታላቅ ነበረ፤ ነገር ግን እርሱን የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ማለት አሳዛኝ ስሕተት ነው።
ስለዚህ የባቢሎንን እምነት አልቀበልም በሚሉ ሰዎች ላይ ሐይማኖታዊ ስደት የተጀመረው ባቢሎን ውስጥ ነው። ይህም ስደት ዓላማው ሰዎች እውነተን መከተል ትተው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ስሕተትን እንዲያመልኩ ማስገደድ ነው። ፖለቲከኛው ንጉስ ናቡከደነጾር ሰማይ እና ምድርን የሚያገናኝ ድልድይ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። የንስሩ ክንፎች የሚያመለክቱት ናቡከደነጾር ሊቀ ካሕናት ወይም ፖንቲፍ እንደመሆኑ በመንፈስ ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ በመብረር አማልክት የሚናገሩትን ሰምቶ የአማልክት ፈቃድ ምን እንደሆነ ለሕዝቡ ለማሳወቅ ወደ ምድር መመለስ እንደሚችል ነው።
ከባቢሎን ሚስጥራት አንዱ የፖለቲካ ራስ የሆነው ሰው ለሕዝቡ መንፈሳዊ ራስ ጭምር መሆኑ ነው።
ስለዚህ አማኞች ይህ ከፍ ያለ ቅዱስ ሰው በእነርሱ እና በእግዚአብሔር መካከል እንዲቆምላቸው ያስፈልጋል ብለው እንዲያምኑ ይገደዳሉ።
ይህ መንፈሳዊ የሆነ እና “ከፍ ብሎ የሚበር” ሰው ብቻ ነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያውቀው። ሌላ የትኛውም ግለሰብ በግሎ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አይችልም። በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ለሚቆመው ቅዱስ ሰው መገዛት አስፈላጊ ነው ተብሎ ይታመናል። የባቢሎን ሐይማኖት መሰረቱ ይህ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ናቡከደነጾር በአንበሳ የተመሰለ የራሱን ፈቃድ በሕዝቡ ላይ የሚጭን ንጉስ ነው። ይህ የባቢሎን መንፈስ ባህርይ ነው፡- የባቦሎን አሰራር ኃይልን በመጠቀም ፖለቲካን እና ሐይማኖትን በአንድ ቀላቅሎ ሕዝብን ለአንድ ግለሰብ ፈቃድ ተገዥ ማድረግ ነው። ዛሬ ፖንቲፍ ተብሎ የሚጠራውን ፖፑን አስቡ። ይህ ሰው ፖለቲካ ውስጥ የተዘፈቀ የሐይማኖት መሪ ነው።
ስለዚህ ዳንኤል ተከታትሎ የሚያሳየን የባቢሎን ሚስጥራት እንዴት አድርገው ወደ ሮም እንደገቡ እና በስተመጨረሻ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የባቢሎን ሚስጥር ለተባለችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሰረት እንደሆኗት ነው። ናቡከደነጾር በራሱ ክብር እና በትዕቢት የተሞላ ሰው ነበረ። “ይህች እኔ በብርታቴ ጉልበት ያሰራኋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችምን?” የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት ናቡከደነጾር ያሰራቸው ታላላቅ ሕንጻዎች የጥንት መንግስታት ካሰሯቸው በቁጥር ሁለት እጥፍ ይበልጣሉ። ባቢሎን ውስጥ ትልቁ የንግድ ስራ የሸክላ ጡብ ሰርቶ በፀሃይ ማድረቅ ነው ምክንያቱም ግምብ የሚሰሩበት ድንጋይ አልነበራቸውም። እኛ አሕዛቦችም ስኬታማ ስንሆን ልባችን ልክ እንደዚሁ አይደለም በትዕቢት የሚሚላው? በጣም አስደናቂ ሰዎች እንደሆንን አድርገን ነው ስለ ራሳችን የምናስበው።
እግዚአብሔር ግን ናቡከደነጾርን ወደ ዱር አሳደደው፤ በዚያም ናቡከደነጾር እንደ ዱር እንስሳ ሆኖ ኖረ፤ ይህም የእርሱ ክፉ መንግስት ምን እንደሚመስል ያሳያል። ዳንኤል መጀመሪያ ባየው ራዕይ ውስጥ ናቡከደነጾር የአሕዛብ ምስል ራስ ሆኖ ነበር የተመሰለው። ስለዚህ በእርሱ ላይ በተቃውሞ የተነሱበትን ወይም ለእርሱ አልታዘዝ ያሉትን ሁሉ በግፍ የመግደል ፍላጎቱ ከፍተኛ ነበር። አካል ወይም ሕዝቡ ራስን መታዘዝ አለባቸው። ናቡከደነጾር ሕዝቡ ሁሉ እንዲታዘዙለት ግድ የሚል አምባገነን ንጉስ ነው፤ ባይታዘዙለት ደግሞ ጉዳቸው ፈላ። ይህ አውሬያዊ ባህርይ በፋርስ መንግስት ወደ ግሪክ መንግስት እና ወደ ሮም መንግስት ተላልፎ በስተመጨረሻ ከሮማ መንግስት ፍርስራሽ ላይ የተነሳችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥም ተጋብቷል። አካል ከራስ በሚመጡ ሃሳቦች ቁጥጥር ነው የሚንቀሳቀሰው።
ናቡከደነጾር አውሬ ሆኖ ሰባት ዓመት አለፈበት፤ ይህም ለአረማዊው የሮማ መንግስት የሚገዙትን ያልዳኑ ጨካኝ አሕዛቦች መንፈስ ኋላም በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ አማኞች በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በግፍና በጭካኔ እየተሰደዱ በሚኖሩበት ዘመን ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚታዘዙትን አውሬያዊ ባህርይ ያላቸውን ሕዝብ የሚያመለክት ምሳሌ ነው።
ከዚያም እግዚአብሔር ክንፎቹን ሰበረ። ከዚያ ወዲያ ናቡከደነጾር እራሱን በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የቆመ ድልድይ ወይም ሊቀካሕናት አድርጎ ማየት አቆመ። ይነግስ ዘንድ እግዚአብሔር የፈቀደለት ተራ ሰው ነበረ እንጂ ሌላ ምንም አልነበረም። ለንግስና መመረጡ በመንፈሳዊነትም ይሁን በሌላ መንገድ ከሌሎች ሰዎች በምንም እንዲበልጥ አላደረገውም። ነገር ግን ስኬቱ እና የነበረው ኃይል ናቸው ያባለጉት።
ስለዚህ እርሱም በሕይወቱ የእግዚአብሔር ጸጋ የሚያስፈልገው ሐጥያተኛ ነበር። ከዚህም የተነሳ ከማንም የተለየ ሰው አልነበረም። እግዚአብሔር ብቻ ነው ታላቅ።
በመንፈሳዊ እይታ በእግዚአብሔር ፊት የትኛውም ሰው ከየትኛውም ሰው አይበልጥም፤ ምክንያቱም እኛ ሰዎች ራሳችንን ከሉሎች ከፍ የምናደርግበት ክንፍ የለንም። እግዚአብሔር ከእኛ ከአሕዛቦች የሚፈልገው አስተሳሰብ ይህ ነው፤ እንዲህ ዓይነት አቋም ሲኖረን ብቻ ነው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ ለዳግም ምጻቱ ዝግጁ መሆን የምንችለው።
ዳንኤል 7፡5 እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፤ እንደዚህም፦ ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ ተባለላት።
አውሬይቱ በአንድ ወገን ስትነሳ አንድ ትከሻዋ ከሌላ ትከሻዋ በላይ ከፍ ይላል። ሜዶናውያን በመጀመሪያ ወደ ሥልጣን ወጡ። በመጀመሪያ ትንሽ ግዛት የነበረችዋ የፋርስ ንጉስ ቂሮስ (ቀጣዩ ካርታ ውስጥ በነጭ ሞላላ ቅርጽ የተመለከተችዋ) የሜዶናዊው ንጉስ የልጅ ልጅ ነበረ። ከዚያ በኋላ ፋርሶች ቂሮስ በተባለው በታላቁ ንጉሳቸው መሪነት የሜዶናውያንን ግዛት ተቆጣጠሩ፤ ነገር ግን ንጉሱ ለሜዶናውያን ደግ ሆነላቸው፤ ስለዚህ ፋርሶች ሜዶናውያንን እንደ አጋር ሕዝቦች ተቀበሏቸው። በፋርስ እና በሜዶናውያን መንግስት አጋርነት ውስጥ የበላይ የሆነውን ስፍራ ፋርሶች ነበሩ የያዙት፤ ግዛታቸውም ካርታው ላይ በቡናማ ቀለም ምልክት የተደረገባቸውን ቦታዎች ናቸው። ድብ በአንድ ጎኑ ጋደም ካለ በአንድ በኩል ብቻ ነው መማታት የሚችለው፤ ወደ ፊት ለፊቱ ብቻ እንጂ ወደ ኋላው መሰንዘር አይችልም። ስለዚህ ድቡ ከሰሜን ወደ ደቡብ ራሱን ወደ ሰሜን አድርጎ ተጋድሞ ከሆነ (ታላቁ ድብ ሰማዩ ላይ በስተ ሰሜን ያሉትን ከዋክብት የሚገዛ የከዋክብት ስብስብ ነው - “አርክቲክ” የሚለውን ቃል ያገኘነው ከዚህ ታላቅ ድብ ስም ነው) ከዚያ በአንድ ጎኑ ጀርባውን ወደ ምስራቅ አድርጎ ቢነሳ ወደ ምዕራብ እና በስተደቡብ ወደ ግብጽ ሲሰነዝር ዳንኤል ያየው ነበር። በጥርሶቹ መካከል ያሉት ሶስት የጎድን አጥንቶች የተቆጣጠራቸውን ሶሰት ቁልፍ ግዛቶች ይወክላሉ። ለምን ሶስት ብቻ? ቂሮስ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ መንግስት በመሰረተ ጊዜ ብዙ ግዛቶችን ተቆጣጥሯል። በስተምስራቅ እስከ ሕንድ ድንበር ድረስ ግዛቱን አስፋፍቷል። ድቡ ጀርባውን ወደ ምስራቅ አድርጎ በመጋደሙ ዳንኤል ይህን ሁሉ እንዳላየ ያልፈዋል።
ለምን?
ለዳንኤል ትልቁ ጉዳይ የፋርስ መንግስት ግዛት ምን ያህል ትልቅ መሆኑ አይደለም፤ ዳንኤል ትኩረቱን ያደረገው የባቢሎንን ሚስጥራት ጠብቆ ለማቆየትና ለማስፋፋት የሚያገለግለውን ግዛት ለማሳየት ነው። እነዚህ የባቢሎን ሚስጥራት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስት ክርስትናን በርዘው ያበላሻሉ። እነዚህ ሚስጥራት ጥንታዊ የእውነት ጠላቶች ነበሩ፤ ዳንኤልም እንዴት እንደሚዛመቱ እየተከታተለ ነበር። ስለ ጠላታችን በሚገባ ማወቅ አለብን።
በ538 ዓመተ ዓለም ባቢሎን በሜዶናዊው ዳርዮስ እጅ የወደቀች ጊዜ የባቢሎናውያን ሚስጥራት ፖንቲፍ ወይም ሊቀካሕናት መዝገቦቹን በሙሉ ይዞ ወደ ምዕራብ ሸሸ። ሜዶናውያን እና ፋርሶች ከባቢሎን በስተ ምስራቅ ነበሩ፤ ስለዚህ ወደ ምስራቅ መሄድ አስፈላጊ አልነበረም። ሐይማኖት ከጥንትም ጀምሮ ገንዘብ የሚያስገኝ ሥራ ነው፤ ስለዚህ መሪው እርሱን ከሚከተሉት ሕዝብ ሃብት እና ስልጣን ያገኛል። ስለዚህ ፖንቲፉ ሚስጥራቱን የሚሰራበት ሌላ አዲስ ከተማ ፈለገ። ወዲያ ወዲህ ሲዞር ከቆየ በኋላ ጴርጋሞስ በምትባል ትንሽ ከተማ ተቀመጠ (የከተማይቱ ስም ጴርጋሞን ነው፤ በግሪክ ሲጻፍ ግን ጴርጋሞስ ነው) ይህችም ከተማ ትንሹ እስያ ውስጥ ነው የምትገኘው። ትንሹ እስያ በጣም ሃብታም ሃገር ነበር። ፋርሶች በስተ ምዕራብ በኩል ወርቅ የሚያገኙት ሳርዲስ ከምትባለው የትንሹ እስያ ከተማ ነበር። ትንሹ እስያ ውስጥ ብዙ የንግድ መስመሮች ነበሩ ስለዚህ አካባቢው ለብልጽግና ምቹ ነበር። ፖንቲፉ የባቢሎንን ሚስጥራት ለማስፋፋት እንዲችል ሃብት እና ፖለቲካዊ ኃይል ያስፈልገው ነበር። ሆኖም ግን ጴርጋሞን ከዚያ ዘመን ጀምሮ ለቀጣዮቹ 200 ዓመታት የፋርስ መንግስት ዘመን ታዋቂ አልሆነችም። ከዚያም ግሪካዊው ንጉስ አሌግዛንደር የፋርስን መንግስት አሸንፎ ወዲያው እርሱ ራሱ ሞተ። የእርሱን መሞት ተከትሎ ከተነሳው የሃያ ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ አራት ጨካኝ የግሪክ ጀነራሎች መንግስቱን ተከፋፈሉት። በ301 ዓመተ ዓለም ጀነራል ላይሲማከስ በዚያ ዘመን ትሬስ ይባል የነበረውን በጴርጋሞን ዙርያ ያለውን ግዛት ተቆጣጠረ። ጴርጋሞስ እየተስፋፋችና ሄዳ ታላቅ ከተማ ሆነች። ከዚያ በኃላ የትሬስ መንግስት ወደቀና የጴርጋሞን መንግስት በቦታው ተተክቶ ትንሹ እስያ ውስጥ ያሉትን አብዛኞቹን ግዛቶች ተቆጣጠረ። የባቢሎን ፖንቲፍ የልጅ ልጆች ይህንን ዕድል ተጠቅመው ከ281 ዓመተ ዓለም ጀምሮ ካለመታወቅ በመውጣት በጴርጋሞን መንግስት ውስጥ ነገስታት-ካሕናት ሆኑ፤ የመጀመሪያው ንጉሳቸውም አቲከስ ቀዳማዊ ነበረ።
ስለዚህ በድቡ አፍ ውስጥ ያለው አንድ የጎድን አጥንት የባቢሎን ሚስጥራት የፈለቁበትን የባቢሎንን መንግስት ይወክላል። ሁለተኛው የጎድን አጥንት የጴርጋሞንን መንግስት እና በዙርያው ያለውን የሊድያ መንግስት (የፋርስ መንግስት በሚገዛበት ዘመን ትንሹ እስያ ሊድያ ነበር የሚባለው) ያም ሥፍራ የባቢሎን ሚስጥራት በድብቅ ሲጠናከሩ ስር ሲሰዱ የቆዩበት ቦታ ነው። ከዚያ በኋላ በግሪክ መንግስት ዘመን ጴርጋሞን ስትበለጽግ የባቢሎን ሚስጥራት ጴርጋሞን ውስጥ በፍጥነት ተስፋፍተው ተቀባይነትን አገኙ።
የባቢሎን ሚስጥራት የሄዱበት አቅጣጫ ከባቢሎን ወደ ጴርጋሞን ነው።
ቂሮስ እነዚህን ሁለቱንም ግዛቶች ተቆጣጥሯቸው ነበር።
ሶስተኛው የጎድን አጥንትስ?
የፐርሺያዊው ንጉስ የቂሮስ ልጅ ካምቢሰስ ግብጽን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ሃገሩ ወደ ፋርስ ሲመለስ ሞተ። ስለዚህ ሶስተኛው የጎድን አጥንት ግብጽ ነበረች።
ብዙ የግብጽ አረማዊ እምነቶችና ብዙ የተስፋፉ የግብጽ ጣኦት አምልኮዎች በባቢሎን ሚስጥራት ውስጥ ተካተው የባቢሎን ሚስጥራት እና የግብጽ አረማዊነት ድብልቅ ሆነዋል። በተመሳሳይ መንገድ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እሥራኤል በስተሰሜን በባቢሎን (የዚህን ዘመን የዲኖሚኔሽኖች እና የቤተክርስቲያኖች ሐይማኖታዊ ስሕተት በምትወክለው) እና በስተ ደቡብ (ዓለማዊነትን በምትወክለው) በግብጽ ተከብባ ነበር፤ ስለዚህ አይሁዶች በእነዚህ ሁለት ተጽእኖዎች ተከበው ነበር። ዛሬም ክርስቲያኖች በዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ሐይማኖታዊ ስሕተት እና በዓለማዊነት መስህብ ተከበው ነው የሚኖሩት።
አብዛኛዎቹ የባቢሎን ሚስጥራት ከግብጽ እምነቶች ጋር ተቀላቅለዋል። በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ሁለቱ ታላላቅ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ግብጽ እና ባቢሎን ናቸው። ባቢሎናውያንም ብዙ አረማዊ ሃሳቦችን ከግብጾች ተቀብለው በእምነታቸው ውስጥ አካተዋል። በ274 ዓመተ ዓለም የሮማ ገዥ ኦሬልያን ከግብጻውያን አምልኮ ውስጥ የፀሃይ አምላክን የማምለክ ልማድን ወስዶ በባቢሎን ሚስጥራት ውስጥ በማካተት ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ ልደት ቀን ነው ብሎ አወጀ ምክንያቱም ያ ቀን በክረምት ወቅት አጋማሽ እና የፀሃይዋ ሙቀት መጨመር የሚጀምርበት ጊዜ ስለነበረ ነው።
በ350 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ ዲሴምበር 25ን የእግዚአብሔር ልጅ ልደት ቀን ነው ብሎ አወጀ፤ ይህም ዛሬ ክሪስማስ የተባለው በዓል ሆነ። ስለዚህ ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓል ነው የሚያከብሩት። መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናከብር አልጠየቀንም። ዲሴምበር 25 ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ ቀን አይደለም፤ ደግሞም ጌታ የተወ
አንድን ቀን በየዓመቱ ማክበር የጌዜ ብክነት መሆኑን ጳውሎስ በመልእከቱ በግልጽ ጽፏል።
ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
25ኛ ቀን። 12ኛ ወር። የክሪስማስ ወቅት። በየዓመቱ።
ገላትያ 4፡11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
ክሪስማስንም ሆነ በሮማ ካላንደር ላይ ያሉ ሌሎች ቀናትን ብናከብር ጳውሎስ ጊዜ እያባከናችሁ ናቸው ነው የሚለን።
ግብጻውያን አማልክቶቻቸው ስላሴ እንደሆኑ ያምናሉ፤ የስላሴ አካላትም አይሲስ፣ ኦረስ፣ እና ሴብ ናቸው። መሰዊያቸው ላይ የሶስቱ አማልክት ስም የመጀመሪያ ፊደሎች ተጽፈዋል። ይህ ልማድ በባቢሎን ሚስጥራትም ውስጥ ተቀባይነት አግኝቶ እስከ ዛሬ ድረስ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በሜተዲስት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ አለ።
የግብጻውያን የፀሃይ አምልኮ የሚወከለው በክብ ቂጣ ሲሆን ክቡ ቂጣ የፀሃይዋን ቅርጽ ይወክላል። ካሕናቱ ይህንን ክብ ቂጣ ይዘው ሰዎችን በአፋቸው ያጎርሳሉ። ቂጣው አይቆረስም። ይህ ቂጣ ወደ ባቢሎን ሚስጥራት ውስጥ ገብቶ ዛሬ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በፕሮቴስታንት አንግሊካን ቤተክርስቲያን ውስጥ ስርዓተ ቅዳሴ ላይ የተገኙ ሰዎች በጌታ እራት አገልግሎት ላይ የሚቀበሉት ቂጣ ያልተቆረሰ ክብ ቂጣ ነው።
ፕሮቴስታንቶች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው።
ኢየሱስ ከመጨረሻው እራት በኋላ ለተደረገው ስርዓት የተጠቀመውን ቂጣ ቆርሶታል።
ግብጻውያን በፀሃይ አምልኮዋቸው ውስጥ ጫፉ ሾጠጥ ያለ ረጅም የድንጋይ ሃውልት ይጠቀሙ ነበር፤ ምክንያቱም ሃውልቱ ወደ ሰማይ ያመለክታል ደግሞም በፀሃይ ጥላ እንደሚሰራ ሰዓትም ያገለግላል። ዛሬ ቫቲካን ከተማ ውስጥ ባለው የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ትልቅ ሃውልት ቆሟል፤ ይህም በባቢሎን ሚስጥራት ውስጥ ግብጽ ምን እንዳበረከተች ማስረጃ ነው።
ስለዚህ ለአብዛኞቹ የባቢሎን ሚስጥራት መነሻ የሆነችው ግብጽ የድቡ አፍ ውስጥ ሶስተኛው የጎድን አጥንት ናት።
ዳንኤል 7፡6 ከዚህም በኋላ፥ እነሆ፥ ነብር የምትመስል በጀርባዋም ላይ አራት የወፍ ክንፎች የነበሩአት ሌላ አውሬ አየሁ፤ ለአውሬይቱም አራት ራሶች ነበሩአት፥ ግዛትም ተሰጣት።
ግሪኮች የፋርስን መንግስት ነው ወስደው የነገሱት፤ ከዚያም አስር ዓመት በፈጀ ፈጣን ወታደራዊ ዘመቻ ግዛታቸውን እስከ ሕንድ ድረስ አሰፉ። ነብር በፈጣን ሩጫው የሚታወቅ አውሬ ነው። ታላቁ ንጉስ አሌግዛንደር ሲሞት ጀነራሉቹ ለሃያ ዓመታት እርስ በርሳቸው ሲዋጉ ቆይተው በስተመጨረሻ የተረፉ አራት ጀነራሎች ግዛቱን ለአራት ተከፋፈሉ። ካሳንደር ግሪክን ያዘ፤ ፕቶለሜይ ግብጽን ተቆጣጠረ፤ ሴሊዩከስ ሶርያን እና በምስራቅ በኩል ከግዛቱ የተረፉ አካባቢዎችን ተረከበ። የትሬስ መንግስት የተባለው ትንሽ ግዛት ለላይሲማከስ ተሰጠው፤ እርሱንም ከጊዜ በኋላ ሴሊዩከስ ገደለው።
ላይሲማከስ ትንሹ እስያ ውስጥ የባቢሎን ሚስጥራት ሲፈለፈሉበት የነበረውን የጴርጋሞንን ከተማ የሚያጠቃልለውን ግዛት ያዘ።
ዳንኤል ሐይማኖታዊ ስሕተትን በዘመናት ውስጥ ሲከታተል ካየበት እይታ አንጻር ከአሌግዛንደር ግዛት ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም እንኳ በጣም አስፈላጊውን ክፍል የተቆጣጠረው ላይሲማከስ ነበር፤ ከዚህ በታች ያለው ካርታ ላይ ጥቁር ቀለም የተቀባውን ክፍል። ነገር ግን የባቢሎን ሚስጥራት ግን ከ133 ዓመተ ዓለም በኋላ ወደ ሮማውያን ነገስታት ከመሻገራቸው በፊት በጴርጋሞን ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል። ሮም ግሪክን ባሸነፈች ጊዜ ዩልየስ ቄሳር ፖንቲፍ የሚባለውን ሹመት ወሰደ። ከዚያ በኋላ እስከ 382 ዓ.ም ድረስ አረማዊ የሮም ነገስታት ፖንቲፍ የሚባለው ማዕረግ ተሰጣቸው፤ በ382 ዓ.ም ክርስቲያን የሆነው የሮማ ንጉስ ቴዎዶሲየስ ፖንቲፍ የሚባለውን ማዕረግ የሮም ጳጳስ ለነበረው ለዳማሰስ ሰጠው። ቴዎዶሲየስ ክርስቲያን እንደመሆኑ መጠን የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት መሆን አልፈለገም።
ራዕይ 2፡12 በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፦
13 የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።
“ሰይጣን የሚኖርበት”። ሰይጣንን በሰዎች ልብ ውስጥ ሲያነግሱት ዲያብሎስ የባቢሎንን ሚስጥራት እንዲከተሉ ያደርጋቸዋል። የባቢሎን ሚስጥራት እውነትን ይቃወማሉ። በጣም አደገኞች እና የብዙዎችን እምነት የሚያጠፉ ናቸው።
አንቲጳስ የሚለው ስም አንቲ እን ፓፓስ (አባት) ከሚሉ ቃላት ነው የተገኘው፤ ፖፕ የሚለው ቃል ድግሞ የተገኘው ከዚህ ቃል ነው። አንቲ ማለት ተቃራኒ ሲሆን አንቲጳስ ፖፑን የሚቃወም ሰው ነበረ። ስለ እምነቱም ተገደለ። እርሱ ማንድ እንደሆነ በውል የሚያውቅ ሰው የለም። ከሰው አመለካከት አንጻር ፖፑን የሚቃወም ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ነበረ። እግዚአብሔር ግን በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ስሙን መዝግቦለታል፤ ይህም ደግሞ በየትኛውም የሰው ታሪክ መዝገብ ውስጥ ከመመዝገብ ይበልጣል።
ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።
ኒቆ ማለት ማንበርከክ ነው። ምዕመናንን (በቤተክርስቲያን ውስጥ የሉትን ሕዝብ) ማንበርከክ መግዛት።
እንዴት? አንድን ቅዱስ ሰው ከጉባኤው በላይ ከፍ በማድረግ ሕዝቡ ለዚህ ሰው ፈቃድ እንዲገዙ ማድረግ ነው። ይህም በመንፈስ ከሌሎች ሰዎች በላይ ከፍ የሚል የካሕን አገልግሎት ስርዓትን በድጋሚ እንዲካሄድ ያደርጋል (ክንፍ ተጠቅሞ ከሰዎች ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ በመብረር) ከዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ግለሰቦች መካከል የሚቆም ሰው ይኖራል። በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል አንድም ሰው መኖር የለበትም።
እግዚአብሔር የእውነት በልብህ ውስጥ የሚኖር ከሆነ በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል ሰው ሊኖር አይችልም። ስለዚህ እውነተኛው ሕብረት በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል ብቻ ነው።
የኢጣልያ ስም በእንግሊዝኛ ተጽፎ ፊደሎቹ ቦታቸው ሲቀያየሩ “ሌይቲ” (ITALY – LAITY) ማለትም ምዕመናን የሚል ትርጉም ይሰጣሉ። አረማዊቷ ሮም ኢጣልያን ተቆጣጠረች። ከዚያም ፖፑ ደግሞ ሌይቲውን ማለትም በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ምዕመናን ተቆጣጠረ።
ፖፑ ቤተክርስቲያኖችን በደምብም መቆጣጠር የሚችለው ቤተክርስቲያኖች እያንዳንዳቸው በቄስ ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ነው። ከዚያ በኋላ ከፖፑ የሚጠበቅበት ለእያንዳንዱ ቄስ ምን ማድረግ እንዳለበት መንገር ብቻ ነው፤ ቄሱም ደግሞ ሕዝቡ ፖፑ የሚፈልገውን እንዲያደርጉ ለማዘዝ በሕዝቡ ላይ ስልጣን አለው።
ፕሮቴስታንቶች ይህንን የካቶሊክ ስርዓት በመኮረጅ ሕዝቡን ለመቆጣጠር በእያንዳንዱ ጉባኤ ላይ ፓስተር ሾሙ። ፓስተር ወይም እረኛ የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚገኘው። ኤፌሶን ውስጥ ከአምስቱ አገልግሎቶች አራተኛው ሆኖ ተጠቅሷል። ስለዚህ ፓስተር ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን የለውም።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ፓስተር ወይም እረኛ የሚለውን ቃል ስምንት ጊዜ ጠቅሶታል። ከስምንቱ ውስጥ ስድስቱን ጊዜ እየነቀፈ ነው የጻፈው።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላሉ የአገልግሎት ምደባዎች ሲጽፍ ፓስተሮችን ጭራሽም አልጠቀሳቸውም። በቤተክርስቲያን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር አስተማሪዎች ያስፈልጋሉ ምክንያቱም ፓስተሮች ብዙዎቹን ትምሕርቶቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ተጠቅመው ማሳየት አይችሉም።
ለምሳሌ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑን ፓስተሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አይችሉም።
ሰዎች ፓስተሩ እረኛ ነው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ይህንን አይልም። ይህ የሰዎች ፈጠራ እና ልማድ ብቻ ነው።
የፓስተሩ አገልግሎት ሰዎችን በግል ችግራቸው፣ በቤተሰብ ችግር፣ በሥራ ችግር ውስጥ መርዳት እና ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ሕብረት ለማጠናከር ማገዝ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚያስተምር የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ነው ሰዎችን በአስተምሕሮ መሰረት የሚያስይዛቸው።
በምስራቅ ሃገሮች ፋርስ ውስጥ ንጉሱ እንደ አምላክ ይመለክ ነበር። በምዕራቡ ዓለም ይህ አልተደረገም። አሌግዛንደር ፋርስን ባሸነፈ ጊዜ ፋርሶች አሌግዛንደርን እንደ አምላክ ማምለክ ጀመሩ። እርሱ ደግሞ በሕይወቱ መጨረሻ አካባቢ ግሪኮችም እንደ አምላክ እንዲያመልኩት አስገደደ። ስለዚህ አሌግዛንደር በስፋት እንደ አምላክ የተመለከ የመጀመሪያው ምዕራባዊ ንጉስ ሆነ። አሌግዛንደር አራት ጀነራሎች ግዛቱን ቆራርሰው በተከፋፈሉ ጊዜ ብዙዎቹን የአሌግዛንደር ሃሳቦች በመከተል እራሳቸውን እንደ አምላክ ቆጥረው ሕዝብ እንዲያመልካቸው አድርገዋል። ስለዚህ እያንዳንዱ ንጉስ በመንግስቱ እና በሰማይ መካከል አገናኝ ድልድይ ሆነ።
ይህን የሚያመለክተው እነዚህን መሪዎች ወደ ሰማይ ከፍ በሚያደርጓቸው አራት ክንፎች ነው።
ነገር ግን ክንፎቻቸው የወፍ ክንፍ ነበሩ እንጂ የንስር ክንፍ አልነበሩም። ሰዎች ራሳቸውን አማልክት ባደረጉ ጊዜ ባሕርያቸው መልካም አልነበረም። እያንዳንዱ በምድር ላይ እንደ አምላክ ተቆጥረው ነበር፤ ነገር ግን አምላክነታቸው እውቅና ያገኘው በግዛታቸው ድንበር ውስጥ ብቻ ነው። ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች ሶስት ተቀናቃኝ አማልክት ነበሩ። ስለዚህ አራቱ አማልክት በፊት እንደነበረው አንድ ብቸኛ አምላክ እንደ አሌግዛንደር አስገራሚዎች አልሆኑም። አሌግዛንደር ከሁላቸውም በላይ ደምቆ ነበረ።
ነገር ግን እነዚህ አራት ሰዎች መሪን እንደ አምላክ የማምለክን ሃሳብ ወደ ምዕራቡ ዓለም ይዘው መጡ። ይህ ሁሉ የባቢሎን ሚስጥር አካል ነው።
የባቢሎን ሚስጥራት ጴርጋሞን ውስጥ ሳይጠፉ ቆይተዋል ነገር ግን ከጴርጋሞን በኋላ በዓለም ዙርያ ሁሉ እንዲስፋፉ ተለቅ ያለ ኃይል ያለው ድጋፍ ያስፈልጋቸው ነበር። ስለዚህ ፖንቲፍም የጴርጋሞን ንጉስም የነበረው አታለስ 3ኛው በ133 ዓመተ ዓለም በኑዛዜው መንግስቱን ለሮማውያን ሰጠ።
ይህ ንጉስ ወራሽ አልነበረውም ግን በጣም ሃብታም ነበረ (ልክ እንደ ዛሬዎቹ የሐይማኖት መሪዎች)። እርሱ ከሞተ በኋላ ተፎካካሪ ቡድኖች ሃብቱን እና ስልጣኑን ለመያዝ ሲሉ የእርስ በርስ ጦርነት እንደሚጀምሩ አውቋል። ስለዚህ ይህ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይከፈት ብሎ በኑዛዜው ውስት መንግስቱን ለሮም ሰጠ። ሮማውያን ግሪኮችን እና ሰሜን አፍሪካ ውስጥ ካረታጄንያኖችን እንደማሸነፋቸው መጠን በኃይል ከሌሎች በላይ እያደጉ መምጣታቸውን በትክክል አስተውሏል።
የባቢሎን ሚስጥራት ከባቢሎን ወደ ጴርጋሞን ሄደው ከዚያው አረማዊ ወደ ሆነችው ሮም ተሸጋገሩ።
በዚያ ጊዜ ጴርጋሞንን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ሮም በብዛት የተጋዘው የትንሹ እስያ ሃብት ነው ሮማውያንን ምግባረ ብልሹ ያደረጋቸው። በ63 ዓመተ ዓለም ዩልየስ ቄሳር ጉቦ ከፍሎ የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት የመሆንን ስልጣን ወሰደ።
ከዚያ በኋላ የጦር ሰራዊት ይዞ ወደ ጋውል (ፈረንሳይ) በመሄድ የነበረበትን እዳ ለመክፈል ሃገሪቱን ዘረፈ። ሮም ውስጥ ወደ ከፍተኛ ስልጣን ሲወጣ የባቢሎን ሚስጥራት ክብር ከእርሱ ጋር አብሮ ከፍ አለ። ከዚያ ወዲያ በምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ በላይ ኃያል ሰው ሆነ። የባቢሎን ሚስጥራት የበላይ ጠባቂያቸው የምድር ኃያል ሰው ሆነ።
ዳንኤል 7፡7 ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።
ይህ አስፈሪ አውሬ ጠማማነትን ነው የሚያሳየው። በምድር ላይ ካሉ አራዊት የትኛውንም አይመስልም። የዳንኤል ራዕይ ውስጥ የነበሩት የብረት እግሮች በዚህ ምስል ውስጥ የአውሬው ጥርሶች ሆነው መጡ።
የሮማ መንግስት የሚቃወሙትን ሁሉ ፈጭቶ ያደቃል።
እያንዳንዱ አረማዊ የሮማ ንጉስ ፖንቲፍ የተባለውን ማዕረግ ተጠቅሞበታል። በምስራቅ አዲስ የሮማ ንጉስ የነበረው ቴዎዶሲየስ ቀዳማዊ በ379 ዓ.ም ተሾመ። በ382 ዓ.ም ክርስቲያን ነኝ አለና ፖንቲፍ የሚለውን የማዕረግ ስም አልቀበልም አለ። ቴዎዶሲየስ በ395 ዓ.ም በሞተ ጊዜ የሮማ መንግስትነ በሁለት ክፍል ከፍሎ ነው የሞተው፤ በዚህም ድርጊቱ ዳንኤል በአሕዛብ ምስል ያየው ትንቢታዊ ራዕይ ተፈጽሟል።
ይህ አውሬ ከሮማ መንግስት ግዛት ውስጥ ምዕራባዊውን ግማሽ ነው የሚወክለው ምክንያቱም የባቢሎን ሚስጥራት ወደ ሮማ በተሸጋገሩ ጊዜ ሄደው የሮማ መንግስት ምዕራባዊ ግዛት ውስጥ ነው የተቀመጡት።
በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ፖንቲፍ የሚባለው ማዕረግ ለፖፑ እንዲሆን አደረገ። ይህንንም በማድረጉ በባርቤሪያውያን ወራሪዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ጨመረለት።
በ452 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ አቲላ ዘሃን ሮምን ማጥቃት እንዲያቆም ብዙ ገንዘብ ሰጠው። አቲላ ሮምን ሳያጠቃ ወደ ኋላ የተመለሰበት ዋነኛው ምክንያት ግን የምግብ እጥረት እና በዙርያው ከነበረው ሃገር የመጣ ወረርሽኝ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ፖፑ ከአቲላ ጋር ያደረገው ይህ ድርድር ለፖፑ በሕዝቡ ፊት ትልቅ ሞገስ ሰጥቶታል። ፖንቲፍ እንደመሆኑ የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት ሆኗል፤ ከዚህም የተነሳ የተዋቡ የክሕነት ልብሶቹን ለብሶ መሃይምና ሃይማኖተኛ የነበሩ ብዙ ባርቤርያውያንን ሊያስገርማቸው ችሏል።
ዳንኤል 7፡7 ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።
ለምንድነው ሮም ከሌሎቹ ሶስት መንግስታት ልዩ የሆነችው?
ሌሎቹ ሶስት መንግስታት ጠንከር ያለ መንግስት መጥቶ ሲያሸንፋቸው ጠፍተው ቀሩ። ሮም ግን ከእርሷ በበለጠ ጠንካራ መንግስት አልተሸነፈችም፤ በዚያ ፈንታ ብዙ የባርቤርያውያን ሰራዊት መጥቶ ነው የተቆጣጠራት።
ከዚያ በኋላ የሮማ መንግስት ሲወድቅ እና ሲጠፋ የሮም ኃይል መንግስት ከመሆን ተለውጦ መንፈሱ መልኩን ቀየረና በአረማውያን የጣኦት አምልኮ ልማዶች ላይ የተመሰረተች ቤተክርስቲያን ሆኖ አንሰራራ።
ቤተክርስቲያን ከሆነች በኋላ ሮም ሶስት ነገዶችን በመጨፍጨፍ ባርቤሪያውያን ገዢዎቿን አሸነፈች፡- እነርሱም ሄሩሊዎች፣ ቫንዳሎች፣ እና ኦስትሮጎቶች ናቸው። ይህም የተደረገው በታላቁ ጀነራላቸው ቤሊሳሪየስ እና ናርሰስ የሚመራውን የኮንስታንቲኖፕል ሰራዊትን በመጠቀም ነው። ከዚያም ፖፑ ብዙ ነገዶችን ወደ ሮማ ካቶሊክ እምነት ለወጣቸው። የሮም ቤተክርስቲያን በሚያስገርም ሁኔታ ታላቅ ኃያል ድርጅት ሆና ተነሳች። ነገር ግን አረማዊ ልማዶቿ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ እየራቁ የሚሄዱ ጠማማ ትምሕርቶች ምክንያት ሆነዋል።
ዳንኤል 7፡7 ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።
ምዕራባዊውን የሮማ ግዛት የተቀራመቱት ነገዶች ከአስር በላይ በመሆናቸው ይህ ቃል ለመረዳት ትንሽ አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን በዚህ ራዕይ ውስጥ ዳንኤል የሚከታተለው የባቢሎን ሚስጥራትን መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ዩልየስ ቄሳር ከሞተ በኋላ እንደ ጴርጋሞን የመሳሰሉ የሮማ ግዛት ምስራቃዊ ክፍሎች ዩልየስ ቄሳርን እንደ አምላክ ማምለክ ጀመሩ። ከዚያም በኋላ በ27 ዓመተ ዓለም የወንድሙ የልጅ ልጅ አውግስጦስ ቄሳር የመጀመሪያው የሮም ንጉስ ሆነ።
እርሱንም በሕይወት ሳለ ጴርጋሞን ከተማ ውስጥ አምላክ ነው ብለው ያመልኩት ነበር። በዚህም መንገድ ሰውን እንደ አምላክ የማምለክ ልማድ ወደ ሮም መንግስት ውስጥ ገባ። የባቢሎን ሚስጥራት ሮም ውስጥ ስር መስደድ ጀመሩ። ሶስተኛው ንጉስ ካሊጉላ ደግሞ አምላክ መሆኑን እራሱም ጭምር ያምን ነበር። በዚህ መንገድ ሰውን እንደ አምላክ የማምለክ አስተምሕሮ ሮም ውስጥ ተደላድሎ ተቀመጠ። ይህ አስተሳሰብ ከነገስታቱ አልፎ ኋላ ወደ ፖፑ ደረሰ።
ነገስታት እና ገዥዎች እየመጡ በፖፑ እግር ስር መደፋት እንዲሁም ጫማውን መሳም ጀመሩ። ስለዚህ ዳንኤል ትኩረቱን ያደረገው የሮማ ግዛትን የተቀራመቱት ነገዶች ላይ ብቻ ሳይሆን የሮማ ካቶሊክ ወደ ታላቅ ስልጣን እንድትወጣ ትልቅ ሚና በተጫወቱት ላይ ጭምር ነው። አረማዊው የሮማ መንፈስ እንዲሞትና ከሞትም ተነስቶ እንዲያንሰራራ አስተዋጽኦ ያደረጉ አስር ነገዶች አሉ፤ የሮማ መንግስት መንፈስ እንደ መንግስት ሞቶ እንደ ተደራጀ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ከሞት ተነሳ።
የመጀመሪያው ነገድ ከሌሎቹ ሁሉ አስፈሪ የሆነው የሃን ነገድ ነው። የዚህ ነገድ አባላት ጠንካራ ቀስት ያላቸው ሲሆኑ ፈረስ ላይ ተቀምጠው ነበር የሚዋጉት። ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሰውን ባለ ቀስት ፈረሰኛ ማለትም ሐሰተኛ አስተማሪ ሆኖ የሚነሳውን የሮማ ቤተክርስቲያን የሚወክሉ ናቸው። ስለዚህ ቀስተኞቹ የሃን ነገድ አባላት የሮማ መንግስትን ማፈራረስ ጀመሩ፤ ከዚያም ሳያውቁ ፖፑ ወደ ስልጣን እንዲወጣ ድጋፍ አደረጉ። ከማእከላዊ እስያ መጥተው የሮማ መንግስት ድንበር ላይ ተሰልፈው የነበሩትን የባርቤርያን ነገዶች ወደ ሮማ ግዛት ውስጥ አባረው አስገቡ። ስለዚህ ዋነኞቹ የለውጥ መንስኤዎች የሃን ነገድ አባላት ነበሩ።
በ378 ዓ.ም የሃን ነገዶች ለመጀመሪያ ጊዜ በምስራቃዊው የሮማ ግዛት ተገኝተው ጎት የሚባሉት ነገዶች ቫለንስ የተባለውን የምስራቃዊ ሮማ ግዛት ንጉስ እንዲገድሉ እና 20,000 ሮማውያን ወታደሮችን እንዲጨፈጭፉ ረድተዋል፤ ይህም ሮም ከሃኒባል ጋር ከገጠመችው ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ አደጋ በሮም ላይ የደረሰበት ወቅት ነው። ይህ ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊጠቅማት የሚችለው እንዴት ነው? ቴዎዶሲየስ ቀዳማዊ በቫለንስ ቦታ ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ የሮማ ምስራቃዊ ግዛት ንጉስ ሆኖ ተሹሞ ነበር፤ እርሱም ከጊዜ በኋላ ፖንቲፍ የሚለውን ማዕረግ አልፈልግም አለ። ቀጥሎም ፖፑ ከእርሱ በስልጣን እንደሚበልጥ በማመን የሮማ ጳጳስ ለዳማሰስ በ382 ዓ.ም ፖንቲፍ የሚለውን ማዕረግ ሰጠው። በዚህም መንገድ የባቢሎን ሚስጥራት ዋነኛው ራስ የነበረውን የሮማ ንጉስ ቢያጡም ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መግባት ችለዋል።
ፖፕ ሊዮ ካናገረው በኋላ አቲላ በቀጣዩ ዓመት ሞተ። ይህም ለፖፕ ሊዮ የሃኖችን ጨካኝና ኃይኛ ንጉስ በሰላም ያናገረ ሰው የሚል ትልቅ ክብር ጨመረለት። ይህን ከመሰለ ዝና ጋር ልትወዳደር የምትችል ሌላ ቤተክርስቲያን አልነበረችም። ከአቲላ ሞት በኋላ የሃን ነገዶች ኃይላቸው ተዳከመ። የሃን ነገዶች ፖንቲፍ የነበረውን ንጉስ ቫለንስ በመግደል ቴዎዶሲየስ ቀጣዩ ንጉስ እንዲሆን በር ከፈቱ፤ እርሱም ፖንቲፍ መሆንን እምቢ አለ። በሮማ ግዛት ውስጥ ቀጣዩ ኃያል ሰው ፖፑ ነበር። ስለዚህ ፖፕ የተባለው ማዕረግ ለፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ተሰጠ፤ ይህም ማዕረግ ፖፑ የሃን ንጉስ የሆነውን አቲላ ፊት ለፊት እንዲጋፈጥ አስችሎል፤ በዚያውም ፖፑን ዝነኛ አድርጎታል።
ቴዎዶሲየስ በ395 ዓ.ም ሲሞት አንድ ትልቅ ስሕተት ሰራ። የሮማ ግዛትን እርስ በርስ ለሚጣሉት ሁለት ሰነፍ ልጆቹ ግማሽ ግማሽ አካፈለ። ይህ ውሳኔ ምዕራባዊውን የሮማ ግዛት በጣም አዳከመው። ምዕራባዊው ግዛት መውደቅ ጀመረ። ምዕራባዊው ግዛት ውስጥ አንድ ጥሩ ጀነራል አቲየስ ነበረ፤ እርሱም አንድ ባርቤሪያዊ ነገድን ለማሸነፍ በሌላ ባርቤርያዊ ነገድ ይጠቀም ነበር። የተጠቀመው ስልት ከፋፍሎ መግዛት ነው። አቲየስ የአቲላን ሃኖች ለማሸነፍ ብሎ ከጎቶች ጋር ተባበረ ግን ሃኖችን ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም፤ ምክንያቱም ኋላ ሌሎችን ባርቤርያውያን ለማሸነፍ የሃኖች ድጋፍ ያስፈልገኝ ይሆናል ብሎ አስቧል። ይህም የምዕራባዊውን ሮም ገዥ ተጠራጣሪ አደረገውና አቲየስን ገደለው። ከዚያ በኋላ ምዕራባዊው ግዛት በብዙ ብጥብጥ ተናወጠ።
አንድ ጠንካራ ሰው ፖፕ ሆኖ የሚያስተዳድራት የሮማ ቤተክርስቲያን ባርቤሪያውያን እንደፈለጉ ወረራ በሚያደርጉበት፤ በሚገድሉበትና በሚዘርፉበት ነውጥ ውስጥ ብቸኛዋ የተረጋጋች ተቋም ነበረች። ቀደም ብሎ ጸረ ካቶሊክ የነበሩ ሰዎች ምግብ፣ አመራር፣ እና መንፈሳዊ ምሪት ፍለጋ ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መመልከት ጀመሩ። የተሾሙ ባለስልጣናት የከተማ አስተዳደር አገልግሎት በመስጠት እየተንገዳገዱ በነበረበት ሰዓት የሮማ ጳጳሶች ጊዜው ያመጣላቸውን ዕድል ተጠቅመው ተነሱና የሮም ከተማን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ማከናወን ጀመሩ።
ሃኖች ንጉስ ቫለንስን ለማስወገድ ድጋፍ አደረጉ። በእርሱም ቦታ ንጉስ ቴዎዶሲየስ ተተካ፤ ነገር ግን ቴዎዶሲየስ ባለማስተዋል የሮማ ግዛትን ለሁለተ ከፈለ፤ ይህም ውሳኔ በምዕራብ ያለውን መንግስት አዳከመ። የምዕራቡ ነገስታት አቅማቸው እየተዳከመ ሲመጣ በዚያው የሮም ከተማ ውስጥ የሮማ ጳጳሳት ኃይል እየተጠናከረ ሄደ፤ እነርሱም ሕዝባዊ አስተዳደሩን ቀስ በቀስ እየወረሱ ሙሉ በሙሉ ያዙ። ምዕራባዊው ግዛት ቀውስ ውስጥ እየወደቀ ባለበት ሰዓት የሮም ጳጳሳት በሮም ከተማ ሕዝባዊ አስተዳደር ውስጥ ያሳዩት ብቃት ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ለአመራር ወደ ሮማ ካቶሊክ እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል።
ስለዚህ ሃኖች የሮማ ግዛትን ብትንትኗን አወጡ፤ በዚያው እግረ መንገዳቸውን ባልተጠበቀ መንገድ ለፖፑ ስልጣን መጠናከር ታላቅ ድጋፍ አደረጉ።
ዳንኤል 7፡8 ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።
ባርቤሪያውያን የሮማ ግዛትን እንደ ቅርጫ ተቀራመቱ። አቲላ ከሞተ በኋላ ሃኖች ተበታተኑ።
ከእነርሱ ተገንጥለው ከወጡት ቡድኖች መካከል ሄሩሊ የተባሉት ባርቤሪያዊው ኦዶዋሰር ንጉሳቸው እንዲሆን መረጡ። እርሱም በሮማ ግዛት ውስጥ የጦር ጀነራል ነበረ። በ476 ዓ.ም ኦዶዋሰር እራሱን የኢጣልያ ንጉስ ብሎ አወጀ፤ ከዚያ ጊዜ ምዕራባዊው የሮማ ግዛት ጠፋ። ኦዶዋሰር ብቃት ያለው መሪ ነበረ፤ ነገር ግን አንድ ትልቅ ችግር ነበረበት፤ ይህም በካቶሊክ የስላሴ ትምሕርት አላምንም ማለቱ ነው። የኦዶዋሰር ነገድ እምነታቸው አሪያን ነበረ፤ ይህም ስለ ክርስቲያኖች አምላክ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተለየ አመለካከት የሚከተሉ ሰዎች እምነት ነው። ይህም እምነት በፖፑ ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም።
ሄሩሊዎች መናፍቅ ተብለው ተወገዙ፤ እንዲገደሉም ተወሰነባቸው። የስላሴ እምነት የባቢሎን ሚስጥራት መሰረት ነው፤ ስለዚህ ፖፑ የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ የስላሴን እምነት ለማስከበር እርምጃ ይወስዳል። ሚስጥራት ግልጽና ቁርጥ ያለ ማብራሪያ አያስፈልጋቸውም። ሚስጥራት የሚለመልሙት ብዥታ በሞላባቸው ጽንሰ ሃሳቦች አማካኝነት ነው።
እኛ ሰዎች የምናምንበትን ነገር በስዕል የማየት ፍላጎት አለን።
እንድንታለል ካስፈለገ የሚቀርብልን ብዥታ የሞላበት ስዕል ነው።
ስለዚህ እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር የሆኑ ሶስት አካላት ሶስት አምላክ አይሆኑም ግን አንድ አምላክ ናቸው። የሰው አእምሮ አንዳችም ግልጽ የሆነ መረዳት ሳያገኝ በሶስት እና በአንድ መካከል እየወላወለ ይቆያል። ስሕተትን ለማሰራጨት ይህ ብዥታ በጣም ጠቃሚ ነው፤ በተለይም ሰዎች እንደ ስላሴ የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላትን ሲያምኑ። ብዥ ያሉ ምስሎች ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲርቁ ያደርጋሉ።
“እግዚአብሔር ወልድ” የሚለው ስያሜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለው ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስያሜ ነው። ለምን? ይህን ጥያቄ በቁምነገር የሚያስብበት ሰው አለ? አንድም ሶስትም የሚል ብዥ ያለ ትምሕርት በሚሰጥበት ሁኔታ እቅጩን መናገር ቀርቷል። ማንኛውም ሊጠጋጋ የሚችል ግምት ሁሉ ተቀባይነት አለው። የባቢሎን ሚስጥራት ወጥመድ ይዞናል፤ ከዚህም የተነሳ የምናምነውን ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልገን ማሰብ አቁመናል። ነገር ግን እምነታችንን ለመግለጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን መጠቀም እንችላለን በሚለው ሃሳብ ደንዝዘናል።
ስለዚህ የሚያነሱበት ተቃውሞ ሳያደናቅፈው ፖፑ ወደ ስልጣን ይወጣ ዘንድ እነዚህ በስላሴ የማያምኑ መናፍቃን ከኢጣሊያ እንዴት ነው የተወገዱት? ናቡከደነጾርን እና የእቶን እሳቱን ታስታውሳላችሁ? ናቡከደነጾር የሁሉ አለቃ ነበረ፤ ስለዚህ በእርሱ ሃሳብ የማይስማሙትን ሁሉ አይፈልጋቸውም ነበር።
ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ የነበረው ንጉስ ዜኖ ድንቅ ሃሳብ መጣለት። ቲዎዶሪክ የኦስትሮጎቶች ንጉስ ነበረ፤ እርሱም ባልካንስ የሚባል ቦታ ከኢጣልያ እና ከምስራቃዊው የሮማ ግዛት መካከል ይኖር ነበረ። ብዙ ጊዜ ምስራቃዊው የሮማ ግዛት ላይ ወረራ እያካሄደ ይረብሻቸው ነበረ። ስለዚህ ዜኖ ቲዎዶሪክ ወደ ኢጣልያ ገብቶ ሃገሪቱን በመቆጣጠር ሄሩለሊዎችን እንዲጨፈጭፍ ጋበዘው። ኦስትሮጎቶች ከባድ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በ493 ዓ.ም ኦዶዋሰር ሞተ፤ ሄሩሊዎችም ተደመሰሱ። አንድ የባርቤርያውያን ቀንድ ተነቀለ። ነገር ግን ቲዎዶሪክ እና ኦስትሮጎቶች አሪያኖች በመሆናቸው ሁሉ ነገር ሰላም ሆኖ ሊቀጥል አልቻለም። ኢጣልያ በስላሴ የምታምን ሃገር እንድትሆንና ከስሕተት ትምሕርት የጸዳች ሃገር እንድትሆን ኦስትሮጎቶችን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው?
በስላሴ አጥብቆ የሚያምነው ጀስቲንያን በ527 የኮንስታንቲኖፕል ንጉስ ሆነ።
አርያኖች ተብለው የሚታወቁት ቫንዳሎች ለኢጣልያ የምግብ ምንጭ የሆነውን ሰሜን አፍሪካ ተቆጣጠሩ። ቫንዳሎች ታላቅ የባሕር ኃይል ነበራቸው፤ ስለዚህ ሜዲተራንያን ባሕር ላይ እንደ ባሕር ዘራፊዎች ይንቀሳቀሱ ነበር። ጀስቲንያን ሰራዊቱን በባሕር ላይ ወደ ኢጣልያ መላክ ፈለገ፤ ስለዚህ ኢጣልያን ከመውረሩ በፊት ሰሜን አፍሪካን መቆጣጠርና የቫንዳሎችን የባሕር ኃይል መምታት ፈለገ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነትም ጊዜ የተባበሩት ኃይላት ይህንኑ ነው ያደረጉት። ኢጣልያ ላይ ጥቃት ከመሰንዘራቸው በፊት በሮሜል መሪነት ሰሜን አፍሪካ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩትን ጀርመኖች ማሸነፍ ያስፈልጋቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ኢጣልያ ውስጥ የነበሩት ጀርመኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር የሚችሉት፤ ስለዚህ ከኢጣልያ የእግር ጣት ጫፍ ጀምረው እስከ ላይ ድረስ ጥቃት ሰነዘሩ።
ቤሊሳሪየስ ዝነኛ የጦር ጀነራል ነበር። የምስራቃዊው የሮማ ግዛት ዋና ከተማ ከነረችው ከኮንስታንቲኖፕል ተነስቶ በመርከብ በመሄድ በ533 ዓ.ም ሰሜን አፍሪካ ደረሰና በ534 ቫንዳሎችን አሸነፋቸው። ይህ ፈጣን ድል አሳሳቸ ነበረ። ወደ ኮንስታንቲኖፕል ሲመለስ ሰሜን አፍሪካ ውስጥ የነበሩት ሙር የተባሉ ሕዝብ አመጹ፤ ከዚያም በኋላ ለብዙ ዓመታት ብቃት በሌላቸው መሪዎች አማካኝነት አሸናፊው ያልለየለት ጦርነት ሲደረግ ቆየ። ከዚህ ጦርነት ሰሜን አፍሪካ ለረጅም ጊዜ ሳታገግም በመቆየቷ ኢጣሊያ እና አውሮፓ በምግብ እጥረት የተነሳ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ላይ ወደቁ።
ነገር ግን አንድ የማያጠራጥር ውጤት ተገኝቷል። በስላሴ የማያምኑት ቫንዳሎች ተጨፍጭፈው አልቀዋል። ስለዚህ ሁለተኛው ቀንድ ተሰበረ ማለት ነው።
ይህም በ535 ዓ.ም ቤሊሳሪየስ ከሰሜን አፍሪካ ተነስቶ በመርከብ ወደ ኢጣልያ በመሄድ ኢጣሊያን ሲገዙ የነበሩትን በስላሴ የማያምኑ ኦስትሮጎቶችን ለመውጋት በር ከፍቶለታል።
ነገር ግን ይህ ጦርነት 20 ዓመታት የሚፈጅ ታላቅ ትግል ሆነ። ጦርነቶቹ ኢጣልያ ውስጥ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለማቋረጥ ሲያተራምሱ ነበር። ሮም ተከብባ አምስት ጊዜ ተይዛ ነበር። ቤሊሳሪየስ ፋርሶችን ለመዋጋት ተጠርቶ ወደ ኮንስታንቲኖፕል ተመለሰ። ንጉስ ጀስቲንያን ግሪካውያን ቅጥረኛ ወታደሮችን ተጠቅሞ ገጠሮችን ሁሉ ዘረፈ። በስተመጨረሻ ናርሰስ የተባለ ሽማግሌ ጀነራል ወደ ኢጣልያ ተላከ። ኦስትሮጎቶችን ከማሸነፉ በፊት መጀመሪያ የሎምባርድ ባርቤሪያውያን እንዲያግዙት ጥሪ አቀረበ። ጥቂት የቀሩት ኦስትሮጎቶች በራሳቸው ጥያቄ ከኢጣልያ ለቀው ወጡ። ኢጣልያ ወረሽኝ፣ ረሃብ እና ቸነፈር አሰቃያት። ሚላን እና ሮም ፍርስርሳቸው ወጣ። ቫንዳሎችን እና ኦስትሮጎቶችን የማስወገዱ ሥራ የየሚያስከፍለው ዋጋ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ኢጣልያ እና አውሮፓ በሙሉ ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ሊገቡ ችለዋል።
ነገር ግን ጀነራል ናርሰስ ሎምባርዶችን ወደ መጡበት በመለሳቸው ጊዜ ኢጣልያ ውስጥ የነበራቸው አጭር ቆይታ አስደስቷቸው ስነበረ ሲወጡ ተመልሰው ለመምጣትና ኢጣልያን ለራሳቸው ለመግዛት ወስነው ነበር የሄዱት።
ነገር ግን ሶስተኛው የአሪያን ቀንድ ተሰብሯል ስለዚህ ኢጣልያ ውስጥ የነበረው የስላሴ እምነት የሚቃወመው አልነበረም።
ባርቢሪያውያን ወደ አውሮፓ እና ሰሜን አፍሪካ እየገሰገሱ በገቡ ጊዜ ብዙ ሰዎች ንብረታቸውን ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰጥተው ነበር፤ የሰጡትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሕዝቡ በባርቤርያውያን እጅ ከመውደው እንድታድናቸው ተስፋ አድርገው ነው። በ600 ዓ.ም በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ከሁሉም ትልቋ የመሬት ባለንብረት ቤተክርስቲያን ነበረች። የፖፑ ስልጣን በስፋት እውቅና እያገኘ ሄደ። በቤተክርስቲያን እጅ የገቡትን መሬቶች ለማስተዳደር በፖፑ አማካኝነት በጣም ጥሩ ሕዝባዊ የአስተዳደር ስርዓት ተዘረጋ።
ኦስትሮጎቶች ከኢጣልያ ከተወገዱ ከአስራ ስድስት ዓመታት በኋላ ጨካኞቹ የሎምባርድ ባርቤርያውያን ነገዶች በ568 ወረራ አደረጉና ከኢጣልያ ላይ ዛሬ ሎምባርዲ ተብላ የምትጠራዋን ቦታ ጨምሮ ትልቅ ግዛት ቆርሰው ወሰዱ። በዚያው ዓመት ፍራንኮች ጋውልን ይዘው ነበር፤ እርሷም ዛሬ ፈረንሳይ ተብላ የምትጠራው ሃገር ናት። በ739 ዓ.ም ሎምባርዶች ሮምን ተቆጣጠሩና ዘረፏት። ፖፑም ተስፋ ቆረጠና ወደ ፈረንሳይ በመሄድ ከፍራንኮች ጋር ውል ተዋዋለ።
በውሉ መሰረትም ፍራንኮች የመረጡትን ንጉስ ፖፑ ይሾምላቸውና ያጸድቅላቸዋል። ለዚህም ውለታ ምላሽ ፍራንኮች ሮምን ከሎምባርዶች ጥቃት ይከላከላሉ። ክሎቪስ የተባለው የፍራንኮች ንጉስ በርገንዲያዊ በሆነችው ሚስቱ ተጽእኖ ወደ ካቶሊክነት ተለወጠ። የክሎቪስ ልጅ ፔፒን ሎምባርዶችን ከሮም አባረራቸው፤ በስተመጨረሻም ሻርለሜን የተባለው የልጅ ልጁ በነገሰ ጊዜ ሎምባርዶችን አሸንፎ ወደ መንግስቱ ውስጥ ጠቅልሎ አካተታቸው።
ከሎምባርዶች የመጣው ስጋት ፖፑ ወደ ካቶሊክ ፍራንኮች እንዲጠጋ አድርጎት ነበረ። ፖፑ የፍራንኮችን ንጉስ መሾሙ አውሮፓ ውስጥ ሌሎችን ነገስታት ሁሉ ለመሾም ሰበብ ፈጠረለት። ስለዚህ ባርቤርያውያን መሪዎች ፖፑ ከሾማቸው በኋላ በሕዝባቸው ዘንድ ተቀባይነት ስለሚያገኙ ብለው ከየፖፑ ጋር ወዳጅ መሆንን በመፈለጋቸው የተነሳ በእነርሱ ዘንድ የፖፑ ተጽእኖ እየጨመረ ሄደ።
ሎምባርዶች ፖፑ ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ ካለው ሮማዊ ገዥ ጥበቃ እንዲርቅ እና ፍራንኮች ከተባሉ ባርቤሪያውያን ነገዶች ጋር ድርድር እንዲያደርግ በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ከኢጣሊያ በስተ ሰሜን ይኖሩ የነበሩት ፍራንኮች ከባርቤሪያውያን ነገዶች ሁሉ ኃይለኞች ነበሩ።
ፍራንኮች ድጋፍ እያደረጉለት ሳለ የትኛውም ነገድ ፖፑ ላይ አደጋ ሊጥልበት አልቻለም።
በ800 ዓ.ም ሊዮ 3ኛው የተባለው ፖፕ ሻርለሜንን የሆሊ ሮማን ኤምፓየር ንጉስ አድርጎ ሾመው፤ ይህም ለፖፑ ትልቅ ክብር እና ነገስታትን የመሾም ወይም የመቀባት ስልጣን ጨምሮለታል።
ሌሎችም ነገዶች ፖፑ ንጉሳቸውን እንዲሾምላቸው ፈለጉ። ከዚህም የተነሳ የፖፑ ስልጣን እያደገ ሄደ።
በ1130 ፖፕ ኤነሰንት 3ኛው አውሮፓ ውስጥ ኃይለኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰብ ሆነ። በ700 ዓ.ም አካባቢ ሙስሊሞች ሰሜን አፍሪካን እና አብዛኛውን የመካከለኛው ምስራቅ ሃገሮች በመቆጣጠራቸው ምክንያት ገንዘብ፣ ስልጣን፣ እና ንግድ ከሜዲተራንያን አካባቢ ሸሽቶ ወደ ሰሜን እና ወደ ምዕራባዊ አውሮፓ ፈቀቅ እያለ ነበር። ገዳሞች በሰሜን እና በምዕራብ አውሮፓ ወደ ባርቤሪያውያን ግዛቶች ውስጥ ሰርገው ገቡ። ዋነኛው ገዳም ክላኒ ሲሆን የተገነባውም በበርገንዲያውያን ነገዶች ግዛት ውስጥ ነው (የዛሬዋ ምሥራቅ ፈረንሳይ ውስጥ የምትገኘው በርገንዲ ግዛት)። የክላኒ ገዳም ተጽእኖ እየተስፋፋ ሄደ፤ እንደ ክላኒ ሮማ ካቶሊክ የሆኑ ገዳሞችም ስኬታማ እየሆኑ ሄዱ። አዳዲስ ገዳሞች ፖፑን እንደ ራስ በመሾም ራሳቸውን አስከበሩ። የካቶሊክ ገዳሞች አውሮፓ ውስጥ እየተስፋፉ በሄዱ መጠን ባርቤሪያውያን ነገዶች ወደ ካቶሎክ ክርስቲያንነት እየተለወጡ የፖፑም ተጽእኖ እየሰፋ ሄደ።
አረማውያኑ አንግሎ-ሳክሰኖች ኢንግላንድን ወረሩና ካቶሊክ ያልሆኑትን ክርስቲያኖች ወደ ምዕራብ ወደ ዌልስ ገፉዋቸው። አንግሎ-ሳክሰኖች በ664 ዓ.ም በዊትቢ ሲኖዶስ የካቶሊክ እምነትን ተቀበሉ። ካቶሊኮች የአዮና ደሴት ላይ እስኮትላንድ አጠገብ ኮሉምባ በተባለ ሰው የተሰሩትን የአየርላንድ ገዳሞች ለመፎካከር ብለው ብዙ ገዳሞችን ከፈቱ። አረማውያን ቅዱስ ጴጥሮስን የሰማይ ደጅ ጠባቂ አድርገው በማሰብ የሚሰጡትን አክብሮት በመጠቀም የካቶሊክ ገዳሞች የባርቤሪያውያን ነገድ መሪዎችን ድጋፍ አገኙ፤ በተጨማሪም የኮሉምባ ገዳሞች የሰሩትን ብዙ መልካም ሥራዎች ዋጋ ለማሳጣት ሞከሩ።
በዚህም መንገድ የአንግሎ-ሳክሰን ገዳሞች የሌሎችን ገዳሞች ተቃውሞ አፍነው የፖፑን ስልጣን እና ተጽእኖ በሰሜን እና በምዕራብ አውሮፓ አስፋፉ።
በምዕራብ አውሮፓ እስፔይን ውስጥ ቪሲጎት ፖርቹጋል ውስጥ ደግሞ ሱዌቪ የተባሉ ነገዶች ሰፍረው ነበር። እነዚህ ነገዶች በመጀመሪያ አሪያን ነበሩ፤ ከባርቤሪያውያን ነገዶች ውስጥ ወደ ካቶሊክ የተለወጡት የመመጀመሪያዎቹ ሱዌቪዎች ናቸው። ከሰሜን አፍሪካ የመጡት አረቦች እና ሙር የተባሉ ነገዶች እስፔይን እና ፖርቹጋልን ገዙ፤ ነገር ግን ከቪሲጎት እና ከሱዌቪ ነገዶች የተረፉ ሰዎች ለብዙ መቶ ዓመታት ሲዋጉ ቆይተው አረቦችን እና ሙር ነገዶችን አሸነፉዋቸው። እስፔይን በሙስሊሞች በተያዘች ጊዜ ቪሲጎት እና ሱዌቪ ካቶሊክ መሆን ጠቅሟቸዋል ምክንያቱም ካቶሊክ በመሆናቸው ፈረንሳይ ውስጥ ያሉትን የካቶሊክ ፍራንኮችን ድጋፍ እንዲሁም የፖፑን ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። ከዚያም ኮለምበስ በ1492 ወደ አሜሪካ በመርከብ ከሄደ በኋላ አሜሪካ ውስጥ የነበሩትን የኢንካዎች እና የአዝቴኮች ሃብት ለመዝረፍ እስፔይኖች ወደ ምዕራብ ፖርቹጋሎች ደግሞ ወደ ምሥራቅ ሄዱ። በዚህ መንገድ እስፔይን እና ፖርቹጋል የቀረውን ዓለም ለካቶሊክ እና ተጽእኖ ክፍት በማድረጋቸው የፖፑ ስልጣን በዓለም ዙርያ ሁሉ እየሰፋ ሄደ።
የሮማ መንግስትን በማፈራረስ አስር ባርቤሪያውያን ነገዶች ሚና በመጫወት ተሳክቶላቸው ነበር፤ ነገር ግን አስበውትም ሆነ ሳያስቡት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኢጣልያ ውስጥ ከዚያም አውሮፓ ውስጥ እንዲሁም ከባሕር ማዶ ባሎ ብዙ ሃገሮች ላይ በዓለም ዙርያ ኃይሏ እንዲጠናከር አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ዳንኤል 7፡8 ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።
እንደ ሰው ዓይኖች። ሰዎች ለነገሮች ያላቸው አመለካከት። ሰዎች የስልጣን እና የሃብት ፍቅር አላቸው። ሰዎች አስፈላጊ ብለው የሚያስቡት ዓለማዊ ስኬት እና ስልጣን ነው።
ፖፕ ግሪጎሪ 7ኛው (1073-1085) የሚከተሉትን ንግግሮች ተናግሯል፡-
ፖፑ በምድር ላይ በማንም ሊመዘን አይችልም።
የሮማ ቤተክርስቲያን ተሳስታ አታውቅም፤ ስሕተት ልትሰራም አትችልም።
የተወገዙ ካቶሊኮች መናፍቃን ናቸው ተብለው ይፈረድባቸዋል፤ ስለዚህ ተሰቃይተውና በእሳት ተቃጥለው መሞት ይገባቸዋል።
ፖፑ ከእግዚአብሔር ልጅ ጋር እኩል ነው።
ፖፑ ሊሳሳት የማይችል ፍጹም ሰው ነው።
ፖፕ አርባን ዳግማዊ የመጀመሪያውን የመስቀል ዘመቻ በ1095 አስጀመረ፤ ለዘማቾችም ፓለስታይን ሄዳችሁ ሙስሊሞችን ከገደላችሁ የዘላለም ሕይወት ታገኛላችሁ የሚል ተስፋ ሰጣቸው። ኢየሩሳሌም ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሙስሊሞችም ተገደሉ።
ፖፕ ኤነሰንት 3ኛው (1190-1216) ፖፑ የክርስቶስ ወኪል ነው ብሎ ተናገረ። ፖፑ በክርስቶስ ቦታ ይቆማል። ፖፑ ለአራተኛ ጊዜ የላከው የመስቀል ዘመቻ በ1204 ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከተማይቱን ከሙስሊሞች ቁጥጥር ነጻ በማውጣት ፈንታ ኮንስታንቲኖፕልን በማጥቃት ከተማይቱን ከክርስቲያኖች እጅ ነጠቃት።
በ1209 ፖፕ ኤነሰንት ካቶሊክ ባልሆኑነት የአልቢጀንስ ክርስቲያኖች ላይ ደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ ጥቃት ሰነዘረ። ከዚያ በኋላ በቀጣዮቹ ሃያ ዓመታት ውስጥ ብዙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ተደርገዋል።
በ1302 ፖፕ ቦኒፌስ 7ኛው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን የለም ብሎ አወጀ። ለፖፑ ከታዘዛችሁ ብቻ ነው ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የምትችሉት።
ፖፕ ሲክስተስ 4ኛው (1471-1484)። ይህ ፖፕ ሮም ውስጥ መሸታ ቤቶች እንዲከፈቱ ሕጋዊ ፈቃድ ሰጠ፤ ከመሸታ ቤቶቹም በዓመት 30,000 ዱካት ገቢ ያገኝ ነበር። ለሞቱ ሰዎች የሃጥያት ማስተሰርያ ይሸጥ ነበር። ለሟች ዘመዶች አሁን ክፈሉላቸውና የሞቱ ዘመዶቻችሁ ከፖርጋቶሪ ይወጣሉ። ጸሎት አያድናችሁም፤ የሚያድናችሁ ገንዘብ ብቻ ነው።
በ1478 ፖፑ የእስፓኒሽ ኢንክዊዚሽን የተባለውን ዘመቻ በመባረክ መናፍቃን እና መናፍቃን በመሆን የተጠረጠሩ ሰዎችን ማሰር፣ ዘግናኝ በሆነ መንገድ ማሰቃየትን፣ እና መግደልን ፈቀደ። የዚህ ሐይማኖታዊ የግድያ ስርዓት በአስፈሪ ሁኔታ የተዋጣለት በመሆኑ ሒትለር ካዘጋጃቻው የሞት ካምፖች አይተናነስም ነበር።
ፖፕ አሌግዛንደር 6ኛው (1492-1503) ከባሕር ማዶ ካለው የአሜሪካ አዲስ ዓለም በባሮች ጉልበት የተገኘውን ሃብት ለእስፔይን እና ለፖርቹጋል አካፈለ።
ፖፕ ፓየስ 5ኛው (1556-1562) ካቶሊክ መሆንን እምቢ ባሉ ሰዎች ላይ የተደረገውን ችሎት በሙሉ ተከታትሎ እነርሱን በሚያሰቃዩበት ክፍል ውስጥ ገብቶ ፕሮቴስታንት ስለሆኑ ብቻ በሁላቸውም ላይ ሞት ፈርዶባቸዋል። ፖፑ የራሱን ጦር ሰራዊት ወደ ፈረንሳይ በመላክ ካቶሊክ አንሆንም ያሉት የሁገኖት ነገዶች ሁሉ ላይ ፈረንሳይ ውስጥ በተከፈተው ሐይማኖታዊ ጦርነት ላይ ድጋፍ በማድረግ ሁገኖት እስረኞችን በሙሉ እንዲገድሏቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል።
በ1570 ዓ.ም በቅዱስ በርተሎሜዎስ በዓል ዋዜማ ፓሪስ ውስጥ 3,000 የሁገኖት ሰዎች ሲገደሉ ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው ሮም ውስጥ የምስጋና ዝማሬ መርቷል።
በቀጣዮቹ ሳምንታት ፈረንሳይ ውስጥ 50,000 ሁገኖት ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕጻናት ሲገደሉ የፖፑ ደስታ እየጨመረ ሄዷል።
ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው በ1582 ዓ.ም የቀን አቆጣጠር ከተፈጥሮ ኡደቶች ወደ ኋላ ቀርቷል በማለት ከጥቅምት ወር ላይ 10 ቀናት ቀንሶ እስከማስተካከል ድረስ ስልጣኑን ተጠቅሞበታል። ዛሬ ዓለም በሙሉ ይህንን የቀን መቁጠሪያ ወይም ካላንደር መከተሉ ፖፑ በዓለም ሕዝብ ዘንድ ያለውን ስልጣን ይመሰክራል።
የጀሱት ፖፕ ሊዮ 13ኛው (1878-1903) እንዲህ ብሎ ተናግሯል፡- “መናፍቃንን እንድንገድል መንፈስ ቅዱስ አይፈልግም የሚል ሰው ሁሉ የተረገመ ይሁን”።
በየዘመናቱ ስልጣን ላይ የተቀመጠ የካቶሊክ ፖፕ በስልጣን ዘመኑ ከተናገራቸው ንግግሮች በጥቂቱ እነዚህ ናቸው።
እነዚህ ንግግሮች ምን ያህል ስልጣን እንደሚወዱ የሚያሳዩ ናቸው።
ከእነዚህ ንግግሮች በስተጀርባ ያለው መንፈስ የክርስቶስን መንፈስ የሚያንጸባርቅ አይደለም።
ስለዚህ የትኛውን መንፈስ ነው የሚያንጸባርቀው?
ዳንኤል 7፡9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።
ትዕይንቱ ወዲያው ወደ ፍርድ ቀን ይሸጋገራል። በሰዎች ሕግ ላይ የተመሰረተ ፍርድ የሚደረግበት የነገስታትና የዳኞች ዙፋን ሁሉ ይወድቃል። እግዚአብሔር ሲፈርድ ፍርዱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ ነው የሚሆነው። ዳኞች የሚለብሱትን ነጭ የሱፍ ጸጉር በራሱ ላይ ይለብሳል። ዳኛ በራሱ ላይ የሚለብሰው ነጭ ጸጉር ለሃገሪቱ ሕግ መገዛቱን ያመለክታል። ይህኛው ዳኛ ግን የሚገዛው ለእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።
ዳንኤል የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኃይል ስትነሳ ያያል፤ ከዚያ ቀጥሎ ያየው የፍርድ ቀን ነው።
ይህም ማለት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የተሰራጨው የካቶሊክ ልማድ ነው የሰው ዘርን ሁሉ ጠራርጎ ወደ እግዚአብሔር ፍርድ የሚወስዳቸው።
ዳንኤል 7፡10 የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር፤ ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር፤ ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።
አስር ጊዜ አስር 100 ነው። ባሏን በምታገለግለው በእያንዳንዷ ሙሽራ አንጻር 100 ሐጥያተኞች አሉ። ከሙሽራይቱ ይልቅ የሐጥያተኞች ቁጥር በብዙ ይበልጣል። የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችው እውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን በፍርድ ቀን ከክርስቶስ ጋረ ትቀመጣለች። ሚስት ባሏን ታገለግላለች፤ ባል የሚስቱ ራስ ነውና። እውነተኛ አማኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ከመቶ ሰዎች መካከል አንድ እውነተኛ አማኝ ይገኛል። አንድ በመቶ! ስለዚህ ሰዎች በስተመጨረሻ ለሰሩት ሥራ ሁሉ ተጠያቂ ይሆናሉ። ያመኑት ስሕተት እና የሰሩት ጥፋት ሁሉ በፍርድ ቀን ይጠየቁበታል።
ዳንኤል 7፡16 በዚያም ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ ስለዚህ ሁሉ እውነቱን ጠየቅሁት፤ እርሱም ነገረኝ፥ የነገሩንም ፍቺ አስታወቀኝ።
ዳንኤል 7፡17 እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው።
ዳንኤል 7፡18 ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።
ዓለም በምግባረ ብልሹ እና ጨካኝ መሪዎቿ እየተመራች ትቆያለች። ነገር ግን እነዚህ ክፉ ነገስታት ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው የሚቆዩት። በስተመጨረሻ መጽሐፍ ቅዱስን በታማኝነት ሲታዘዙ የነበሩ ዳግመኛ የተወለዱ ክርስቲያኖች ምድርን ይወርሳሉ።
ዛሬ በዚህ ዓለም ዘንድ የተመሰገኑ ሰዎች ሰዎች ናቸው የሚመሩት፤ ወደ ፊት ግን አሁን የተገፉ ሰዎች ናቸው የሚነግሱት።
የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ።
ዳንኤል 7፡19 ከዚህም በኋላ ከቀሩት ሁሉ ተለይታ እጅግ ስለምታስፈራው፥ ጥርሶችዋም የብረት ጥፍሮችዋም የናስ ስለሆኑት፥ ስለምትበላውና ስለምታደቅቀው የቀረውንም በእግርዋ ስለምትረግጠው ስለ አራተኛይቱ አውሬ፥
ይህ ምዕራብ አውሮፓን የተቆጣጠረ ክፉ የሮማ መንግስት ነው። ዳንኤል ስለ ምስራቃዊው የሮማ ግዛት ብዙም ትኩረት አይሰጥም። ምከንያቱም የባቢሎን ሚስጥራት ወደ ምዕራብ ነው የሄዱት እንጂ ወደ ምስራቅ አይደለም።
ዳንኤል 7፡20 በራስዋም ላይ ስለ ነበሩ ስለ አሥር ቀንዶች፥ በኋላም ስለ ወጣው፥ በፊቱም ሦስቱ ስለ ወደቁ፥ ዓይኖችና ትዕቢት የተናገረ አፍ ስለ ነበሩት፥ መልኩም ከሌሎች ስለ በለጠ ስለ ሌላው ቀንድ እውነቱን ለማወቅ ፈቀድሁ።
ይህ አውሬ አንድ ራስ ብቻ ነው ያለው።
ስለዚህ ይህ አውሬ የሐንስ በራዕይ ምዕራፍ 13 እና 17 ውስጥ ያየው አውሬ አይደለም።
አውሬው ሰባት ራሶች ነበሩት። ዳንኤል ያየው አውሬ አረማዊው የሮማ መንግስት ነው። ዮሐንስ ያየው አውሬ ደግሞ በሰባቱ የሮም ተራሮች ላይ የምትቀመጠዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። ይህች ቤተክርስቲያን ከጋለሞታ እናታቸው ወጥተው ጋለሞታ ለሆኑት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ሁሉ እናት የሆነች ጋለሞታ ናት።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የሚወክለው ትንሹ ቀንድ ከሌሎቼ ባርቤርያውያን ነገዶች ሁሉ ይልቅ ብርቱ ሆኖ ተገኘ።
አውሮፓ ውስጥ በብሔር የተመሰረቱ መንግስታት ሲነሱ የባርቤሪያውያን ነገዶች እየጠፉ ሄዱ። ከሃን ነገድ የሆነው አቲላ የሮማ ግዛትን አንቀጥቅጦ እንደነበር ሁሉ የናፖልዮን ሽብር ደግሞ አውሮፓን በሙሉ ማንቀጥቀጥ ጀመረ። ናፖልዮንን ለመዋጋት በተለያየ ስፍራ ያሉ ሕዝቦች እንደ አንድ ሃገር መሰብሰብ ጀመሩ። ከናፖልዮን በኋላ አውሮፓ በብዙ ሃገሮች ተከፋፈለች፤ ባርቤርያውያንም የታሪክ ትዝታ ሆነው ቀረው። ናፖልዮን ፖፑን አሰረ፤ ኋላም በ1870 ዓ.ም ኢጣልያ ነጻ ስትወጣ ፖፑ ቫቲካን ውስጥ ቀረ። ስለዚህ እንደ ባርቤርያውያን ነገዶች የካቶሊክ ቤተክርስቲያንም የጠፋች ይመስል ነበር። ነገር ግን የሮም መንፈስ ሊጠፋ ከቀረበበት በማንሰራራት የታወቀ ነው። በ1929 ዓ.ም የኢጣልያ አምባገነን ገዢ ሙሶሊኒ ለቫቲካን እራሷን የቻለች ሃገር እንድትሆን እውቅና ሰጠ። ስለዚህ ቫቲካን በዓለም ላይ ከሁሉ ትንሸዋ መንግስት ወይም ሃገር ሆነች። ማለትም ዳንኤል በራዕይ ያየው ትንሹ ቀንድ።
በዚያ ጊዜ ፖፑ በራሱ ሃገሮችን ለመግዛትና ለመቆጣጠር መሞከር ትቶ ነበር፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ የገንዘብ አቅሙን በፍጥነት በመጨመር ፖለቲካዊ እና ሐይማኖታዊ ኃይሉን አጠናክሮ ተነሳ። በአሁኑ ሰዓት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙርያ ፖለቲካዊ እና መንፈሳዊ የስልጣን እውቅና አግኝታ ታላቅ ተጽእኖ በማድረግ ትንቀሳቀሳለች። ባርቤርያውያን ነገዶች ጠፍተዋል፤ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን እስከ ዛሬ ድረስ አለች።
ዳንኤል 7፡21 እነሆም፥ ያ ቀንድ ከቅዱሳን ጋር ሲዋጋ አየሁ፥ … አሸነፋቸውም።
በ400 ዓ.ም አካባቢ ኦጋስተን የተባለው የካቶሊክ ጳጳስ መናፍቃንን ማሳደድ ችግር የለውም ብሎ አወጀ፤ መናፍቃን ማለት ከፖፑ ጋር አልስማማም ያሉ ሰዎች ናቸው። አንዳንድ የታሪክ ምሑራን ኦጋስተንን የአሳዳጆች አለቃ ይሉታል።
በ450 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ እንዲህ አለ፡- ኦጋስተን ሲናገር መናፍቃንን መግደል ትችላላችሁ ማለቱ ነው።
ከዚያ በኋላ ግድያው ተጀመረ። ይህም ግድያ በጨለማው ዘመን ውስጥ ለ1,000 ዘለቀ፤ ከዚያም አልፎ ሉተር ያመጣውን ተሃድሶ ለማዳፈን ሲባል በካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተደረገው ጸረ ተሃድሶ ዘመቻ ውስጥም ግድያው ቀጠለ።
በስተመጨረሻም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ስለተቃወሙ ብቻ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጨፈጨፉ። በአንዳንድ ሥፍራዎች ለምሳሌ በደቡብ ፈረንሳይ አልቢጀንሶች ሙሉ በሙሉ ጠፉ። ዋልደንሶች ወደ አልፕስ ተራሮች ሸሽተው በዚያ ኖሩ። ሁገኖት የተባሉት ነገዶች እና ሌሎች ክርስቲያኖች ባሕር አቋትተው ወደ አሜሪካ ሄዱ።
ዳንኤል 7፡22 በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ
በስተመጨረሻ ግን እግዚአብሔር ቅን ፍርድ በመፍረድ ሁሉን ያስተካክላል። በምድር ላይ የሰይጣን ውሸት ለጊዜው ሊሰለጥን ይችላል፤ ስለዚህ ቅዱሳን መታገስ አለባቸው። በስተመጨረሻ እግዚአብሔር የራሱን እርምጃ ይወስዳል። እኛም በእምነት ጸንተን መቆም አለብን።
ዳንኤል 7፡23 እንዲህም አለ፦ አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፤ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዲኖሚኔሽናዊው የሐይማኖት ስርዓት እና ፕሮቴስታንት ልጆቿ ዓለምን ይቆጣጠራሉ። ይህንን ትልቅ ሐይማኖታዊ ስርዓት የሚቃወሙ አማኞች ተረግጠው ይሰባበሩና ይበታተናሉ። ዳንኤል በራዕይ ባየው የአሕዛብ ምስል እግር ውስጥ ያለው ሸክላ ተሰብሮ ነበር። ሸክላው የሚወክለው እውነተኞቹን አማኞች ነው። ብረቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ነው የሚወክለው። በመጀመሪያው የጌታ እራት አገልግሎት ላይ እንጀራው ተቆርሶ ነበር። እንጀራ የክርስቶስን አካል ወይም ቤተክርስቲያንን ይወክላል።
አረማዊው የሮማ መንፈስ በመጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ነበረ፤ በዚያን ጊዜም እውነተኛ አማኞችን ይቃወም እና ያሳድድ ነበር። ይህ አረማዊ መንፈስ በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት በ325 ዓ.ም ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገባ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ጀመረች።
ዳንኤል 7፡24 አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከእነርሱም በኋላ ሌላ ይነሣል፥ እርሱም ከፊተኞች የተለየ ይሆናል፥ ሦስቱንም ነገሥታት ያዋርዳል።
ፖፑ በስላሴ ከማያምኑ አሪያን መናፍቃኖች ተቃውሞ ነጻ ሆኖ ኢጣልያ ውስጥ እንዲገዛ ለማመቻቸት ሶስቱ አሪያን ነገዶች ማለትም ሄሩሊ፣ ቫንዳሎች፣ እና ኦስትሮጎቶች ሙሉ በሙሉ መጥፋት ነበረባቸው። ከዚያ በኋላ በቀጣዮቹ 900 የጨለማ ዘመን ዓመታት ውስጥ የስላሴ አስተምሕሮ ላይ ተቃውሞ አልተነሳም። ስለዚህ የስላሴ አስተምሕሮ ያለምንም ጥያቄ ተቀባይነትን አገኘ። እስከ ዛሬ ድረስ የሆነ ሰው በስላሴ አላምንም ብሎ ሲናገር ሲሰሙ ሰዎች ይደነግጣሉ።
ጳጳሶቹ ከሌሎች ነገዶች የተለዩ ናቸው። የሮማ መንግስት ግዛቶችን በሙሉ ተቆጣጥረው ነበረ። ነገር ግን በስተመጨረሻ ፖፑ በቫቲካን ከተማ ብቻ ተወስኖ ቀረ፤ ይዞዋቸው የነበሩ ግዛቶችን ሁሉ ለቀቀ። ከዚያው ከቫቲካን ሆኖ መንፈሳዊ መንግስቱን በማስፋት በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነችዋ ቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ተገለጠ። ከአንድ ቢሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሕዝብ መንፈሳዊ መሪ እንደመሆኑ መጠን በዓለም ላይ እጅግ በጣም ትልቅ ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያደርጋል። ፖፑ እጅግ ብዙ ገንዘብ እና ንብረቶች አሉት። ካለው መንፈሳዊ ክብር እና ስልጣን የተነሳ በዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። የፖፑ መንግስት ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ውስጥ ያሉትን መሳሪያዎች በመጠቀም የሰዎችን ልብ እና አእምሮ ለመቆጣጠር ሳይታክት ይሰራል። ደግሞም ዓለምን በሙሉ ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረቱ በአስደናቂ ፍጥነት እየተሳካለት ይገኛል።
ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።
“በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል”። ፖፑ ከሚናገረው ንግግር ውስጥ አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል የለበትም።
ግልጽ የሆነው ምሳሌ ለቤተክርስቲያን ገንዘብ በመክፈል የሰራችሁት ሐጥያት ይሰረይላችኋል የሚለው ንግግሩ ነው። ንሰሃ ስንገባ እና ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል የኢየሱስ ደም ብቻ ነው ለሐጥያታችን ማስተሰርያ የሚሆንልን።
ከዚያ በኋላ ጳጳሳቱ ሰዎች ሙስሊሞችን በመግደል መዳንን እንዲያገኙ ተስፋ በመስጠት በመስቀል ዘመቻዎች ውስጥ እንዲሳተፉ አበረታቷቸው። ይህ ፈጽሞ ከክርስትና እውነት ያፈነገጠ ትምሕርት ነው።
ሌላ ምሳሌ ብንመለከት ደግሞ ፖፑ እግዚአብሔርን ስላሴ አድርጎታል፤ ይህንንም በማድረጉ እግዚአብሔርን ስም አሳጥቶታል። ሶስት ሰዎች አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ ክርስቲያኖች ሶስቱን የማዕረግ መጠሪያዎች አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ይዘው የእግዚአብሔር ስም ናቸው ሲሉ እየተሞኙ ነው። ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ስም ናን እንደሆነ አያውቁም።
ዛሬ የውሃ ጥምቀት በብዙ የተለያዩ መንገዶች ይፈጸማል። በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያላገኘው የጥምቀት ዓይነት በኢሱስ ክርስቶስ ስም ማጥመቅ ነው። ይህ ጥምቀት አንድ መለኮት በሶስት አካላት ከሚለው የስላሴ ጽንሰ ሃሳብ ጋር አይገጥምም። ሆኖም ግን ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ቁጥር 38 ውስጥ ያጠመቀው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው። የሚገርመው ነገር ደግሞ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጴጥሮስን ታላቁና የመጀመሪያው ፖፕ አድርጋ መቁጠሯ ነው። እንዲህም ሆኖ ግን የጴጥሮስን መመሪያ አይከተሉም።
ፖፑ እኛ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የምንችለው ለእርሱ ከታዘዝን ብቻ ነው ብሎ መናገሩ ኢየሱስ የመዳን መንገድ እኔ ብቻ ነኝ፤ ደግሞም ወደ ሰማይ መግቢያው በር እኔ ብቻ ነኝ ብሎ ከተናገረው ቃል ፊት ለፊት ይቃረናል።
“ቅዱሳንን ይሰባብራል”። በ450 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ የሮማ ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን መግደል ጀመረ።
በጨለማው ዘመን እና ጸረ ተሃድሶ ዘመቻ በተደረገበት ዘመን ከአስር ሚሊዮን በላይ የሮማ ካቶሊክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ተገድለዋል። እያደጉ የነበሩ ክርስቲያን ማሕበረሰቦች ተጨፍጭፈዋል። ክርስቲያኖች ወደ አልፕስ ተራሮች ውስጥ ገብተው እንዲደበቁ ወይም ባሕር አቋርጠው እንዲሰደዱ ተገደዋል።
ከዚያ ቀጥሎ በቫቲካን መሪነት የተጀመረው በዘግናኝ መንገድ ሰዎችን እያሰቃዩ የሚመረምሩበት ኢንክዊዚሽን የተባለ ስርዓት ተጀመረ፤ በተለይም እስፔይን ውስጥ የተደረገው ዘስፓኒሽ ኢንክዊዚሽን። እነዚህ አሰቃቂ የመግደያ ማሽኖች እንደ ሒትለር የመሳሰሉ ክፉ ጨካኝ አምባገነን መሪዎች ፖላንድ ውስጥ እስታሊን ደግሞ ራሺያ ውስጥ ማኦ ቻይና ውስጥ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ያዘጋጁዋቸውን የሞት ካምፖች ያስታውሱናል። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ለዘጅም ዘመን ሳይቋረጥ ከቆየው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስደት የተነሳ ብዙ መከራ ደርሶባታል።
“ዘመናትን ይለውጣል”። ካላንደራችን የተለወጠው በሮም ነው። በ45 ዓመተ ዓለም ዩልየስ ቄሳስ የወራቱን አቆጣጠር ከወቅቱ ጋር አብሮ እንዲሄድ ለማድረግ 90 ቀኖችን ጨመረ። ከዚያ በፊት ፌብሩዋሪ ውስጥ 23 ቀናት ተጨምረው ነበር፤ እርሱ ደግሞ በኖቬምበር እና ዲሴምበር መካከል 67 ቀናትን ጨመረ። ስለዚህ 45 ዓመተ ዓለም 445 ቀናትን የፈጀ ዓመት ስለነበረ አደናጋሪ ዓመት ሆኗል።
ደግሞም በየአራት ዓመቱ በዓመት ላይ አንድ ተጨማሪ ቀን የመጨመርን ልማድም አስጀመረ።
ይህ ሮማዊው ዩልየስ ቄሳር ነው።
ነገር ግን ከዩልየስ ቄሳር በኋላ ካላንደሩ በየ 128 ዓመታቱ ከወቅቶች በ 1 ቀን ወደ ኋላ እየቀረ ነበር።
በ1582 ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው ካላንደሩ ከወቅቶች ጋር እኩል እንዲሄድ በማለት ከኦክቶበር ላይ 10 ቀናችን ቀነሰ። እርሱም በእያንዳንዱ መቶኛ ዓመት ላይ ዓመቱ ያለቀሪ በ400 መካፈል ካልቻለ ጳጉሜ ስድስት ቀናት እንዳይሆን አደረገ። ስለዚህ በፈረንጆች አቆጣጠር 1900 ዓ.ም ላይ ጳጉሜ ስድስት ቀናት አልሆነም 2000 ዓ.ም ላይ ግን ስድስት ቀን ነበረ።
ይህ የሮማ ካቶሊክ ግሪጎሪያን ካላንደር ነው።
ፖፑ የጌታ እራት (ካቶሊኮች ቅዱስ ቁርባን ይሉታል) የሚደረግበትን ሰዓት ከምሽት (ከእራት በኋላ) ወደ ጠዋት ቀየረው ምክነያቱም ለብዙ ሰዎች ጠዋት ይመቻቸዋል። ፕሮቴስታንቶች የካቶሊክን ምሳሌ ተከትለው የጌታ እራት ሳይሆን የጌታ ቁርስ ፕሮግራም ያደርጋሉ።
ፖፑ የሰንበትን ቀን ከቅዳሜ ወደ እሁድ ቀየረ። ፕሮቴስታንቶች ይህንንም ተከተሉ።
ግን ይህ ሁሉ ስሕተት ነው።
በእሁድ ጠዋት የቤተክርስቲያን የአምልኮ ጊዜ ማድረግ መልካም ነው፤ ምክንያቱም የጥንቷ ቤተክርስቲያንም የአምልኮ ጊዜዋ እሁድ ጠዋት ነበር፤ ነገር ግን ይህ እሁድን ሰንበት አያደርገውም።
ሰንበት ማለት እረፍት ነው። እውነተኛው እረፍት ከሐጥያታችን ማረፍ ሲሆን ይህም በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀን ኢየሱስ በእኛ ውስጥ እየኖረ ሕይወታችንን ካልተቆጣጠረ በቀር ሊፈጸም አይችልም። በዚያ ጊዜ ብቻ ነው ከቀደሙ ሐጥያቶቻችን ማረፍ የምንችለው። ከዚያ በኋላ ከመዳናችን በፊት እንመላለስበት ወደነበረው የሐጥያት ስራ አንሄድም። በተመሳሳይ መንገድ እግዚአብሔርም ዓለምን ከፈጠረ በኋላ በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ስላረፈ ከዚያ ወዲያ ሁለተኛ ወደ መፍጠር ስራ አልተመለሰም። ቅዳሜ የእረፍት ወይም የሰንበት ቀን ከሆነ ሥራ ትሰራላችሁ፤ ከዚያ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ታርፋላችሁ፤ ከዚያም እንደገና ወደ ሥራ ትመለሳላችሁ። እግዚአብሔር ያረፈበት እረፍት ግን እንዲህ አይደለም።
እሁድ የምናመልክበት እና ስለ እግዚአብሔር የምንማርበት ቀን ነው። የሰንበት ቀናችን እሁድ አይደለም፤ የሰንበት ቀናችን የምንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ተቀብለን ከቀደሙ የሐጥያት ሥራዎቻችን ያረፍንበት ቀን ነው። ስለዚህ ወደ ቀደመው ሰካራምነትና ጠጪነታችን፣ አጫሽነታችን፣ ቁማርተኝነታችን፣ ውሸታምነታችን እና ወደ አታላይነታችን፣ ወዘተ. አንመለስም።
ዕብራውያን 4፡10 ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
የኢየሱስን ልደት እንድናከብር አልተጠየቅንም። በ350 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ ዲሴምበር 25 የእግዚአብሔር ልጅ ልደት እንዲሆን አወጀ። ይህ በ274 ዓ.ም በአረማዊው የሮም አምባገነን ንጉስ ኦሬልያን ከታወጀው ሮማውያን የፀሃይን አምላክ የልደት ቀን ከሚያከብሩበት ቀን የተኮረጀ ድርጊት ነው፤ ኦሬልያን የፀሃይ አምላክን ልደት ቀን ያወጀው የሮምን ጳጳስ አንገቱን ቆርጦ ከገደለ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
“ሕግን ይለውጣል”።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከምታደርጋቸው ነገሮች ውስጥ አብዛኘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን ያደርጋሉ።
ለምሳሌ ፑርጋቶሪ የሚባል ቦታ አለ የሚል ትምሕርት ፈጠሩ፤ የሆነ ሰው ለሐጥያታችሁ ገንዘብ እስኪከፍል ድረስ ነፍሳችሁ ፑርጋቶሪ ውስጥ ትቆያለች።
የጌታ እራት (ወይም ቅዱስ ቁርባን) ላይ ለሕዝቡ ያልተቆረሰ ክብ ቂጣ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ከወይኑ አንዳችም አያቀምሷቸውም።
ይህ ቂጣ እውነተኛው የጌታ ሥጋ ነው ብለው ያምናሉ፤ ወይኑ ደግሞ የኢየሱስ ደም እራሱ ነው ይላሉ።
በትምሕርታቸው መሰረት ለፖፑ ካልታዘዛችሁ አትድኑም።
ሐጥያታችሁን ለካሕን መናዘዝ አለባችሁ።
ቤተክርስቲያኖቻቸው ውስት ብዙ ጣኦታት እና የተቀረጹ ምስሎች ይገኛሉ።
ካሕናት ሚስት ማግባት አይፈቀድላቸውም።
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የአዋልድ መጻሕፍት የተባሉ መጻፎችን ጨምረዋል።
ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካርዲናሎች፣ እና ፖፕ ያሉበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የስልጣን ተዋረድ ፈጥረዋል።
የማርያም አምልኮ።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የፈጠረቻቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሕግጋት ብዛት ማለቂያ የላቸውም።
ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።
ይህ ከባድ ዓረፍተ ነገር ነው። “ዘመን” ዓመት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። “ዘመናት” ደግሞ ሁለት ዓመታት ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ “እኩሌታ ዘመን” ግማሽ ዓመት ነው።
ይህ አተረጓጎም ትክክል ከሆነ ዘመን፣ ዘመናት እና እኩሌታ ዘመን ሲደመሩ ሶስት ዓመት ተኩል ይሆናሉ፤ ይህም 42 ወራት ወይም 1,260 ቀናት ተብሎ የተተቀሰው የታላቁ መከራ ዘመን ርዝማኔ ነው።
ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደ ድርጅት ታላቁ መከራ እስኪጀምር ድረስ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ትቃወማለች። በዚያ ጊዜ ኢየሱስ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ነጥቆ ይወስዳታል። ከዚያ በኋላ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ዓለምን ይቆጣጠራል፤ ነገር ግን እውነተኛይቱ ሙሽራ በምድር ላይ ስለማትኖር በክርስቶስ ተቃዋሚው የጥፋት ኃይል ስር አትሆንም።
ስለዚህ የሶስት ዓመት ከግማሹ ታላቅ መከራ እስኪጀምር ድረስ ነው ሮማዊው አውሬ ክርስቲያኖችን የሚያሳድዳቸው።
ይህ ቃል ከዳንኤል ምዕራፍ 9 ጋርም ይያያዛል።
ይህ ቃል ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ተቃዋሚ ነጻ የምትሆነው በዳግም ምጻት ጊዜ መሆኑን በመግለጥ ተመሳሳይ ድምዳሜ ይሰጠናል። ነገር ግን ጠለቅ ያለ መረዳትም ይጨምርልናል።
በ538 ዓመተ ዓለም በኃላ ቂሮስ አይሁዶች ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመሉ ከባቢሎን የለቀቃቸው ጊዜ ነበረ። ጠላቶቻቸው ለ17 ዓመታት ከዘገዩዋቸው በኋላ በ21 ዓመታት ውስጥ ቤተመቅደሱን ሰርተው ጨረሱ። ከሃምሳ ስድስት ዓመታት በኋላ ዕዝራ መዝገቡን ወደ ቤተመቅደሱ መለሰው፤ ከተጨማሪ 13 ዓመታት በኋላ ደግሞ ነህምያ የኢየሩሳሌምን አጥር በ52 ቀናት ውስጥ ሰርቶ ጨረሰ። ይህ ዓመት 446 ዓመተ ዓለም ነበረ።
ዶክተር እስኮፊልድ ነብዩ ሚልክያስ የገለገለው በ397 ዓመተ ዓለም ነው ይላል። ይህም ዓመት የኢየሩሳሌም አጥር እንዲሰራ ትዕዛዝ ከወጣ ከ49 ዓመታት በኋላ ነበር።
ከዚያ በኋላ የዝምታ ጊዜ ሆነ። መጥምቁ ዮሐንስ እስኪመጣ ጊዜ ድረስ ሌሎች ነብያት አልተነሱም።
ዮሐንስ ኢየሱስን ለ7 ዓመት አገልግሎት አጠመቀው፤ ነገር ግን ይህ የአገልግሎት ዘመን በሶስት ዓመት ከግማሽ ላይ ተቋረጠ። ቀሪው ሶስት ዓመት ተኩል በታላቁ መከራ ዘመን ለሚመጡት ለሁለቱ ነብያት ነው።
ስለዚህ የመጨረሻ ሳምንት በተባለው በ7ቱ ዓመታት እኩሌታ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት የሚሞሉት ሰባቱሳቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው።
አሁንም ወደ ዳንኤል ትንቢት ተመልሰን እንይ።
ዳንኤል 9፡24… በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።
ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
ነህምያ 2፡1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ ግን በፊቱ ያለ ኃዘን እኖር ነበር።
ነህምያ 2፡8 በቤቱም አጠገብ ላለው ለግንብ በሮች፥ ለከተማውም ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ለንጉሡ ዱር ጠባቂ ለአሳፍ ደብዳቤ ይሰጠኝ አልሁት። ንጉሡም በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነችው እንደ አምላኬ እጅ ሰጠኝ።
አርጤክስስ በ465 ዓመተ ዓለም ነገሰ። የንግስናው የመጀመሪያ ዓመት 465 ዓመተ ዓለም ከሆነ 20ኛ ዓመቱ 446 ዓመተ ዓለም ነው።
የኢየሩሳሌምን አጥር ለማደስ ለነህምያ ትዕዛዝ የተሰጠው በ446 ዓመተ ዓለም ነው (በዚያ ዘመን አንድ ቦታ በዙርያው አጥር ከሌለው በቀር እንደ ከተማ አይቆጠርም ነበር)።
የመስዋእቱ በግ የሚታጠብበትን ስርዓት በሆነው በጥምቀቱ ሰዓት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለሕዝቡ የጠቆመው መጥምቁ ዮሐንስ ነበር፤ ይህንንም ያደረገው መንፈስ ቅዱስ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ብሎ ሲናገር በሰማ ጊዜ ነው፤ ቢዚያም ሰዓት መንፈስ ቅዱስ መጣና ኢየሱስ የተቀባው መሲህ መሆኑን ለሰዎች ለመግለጥ በእርሱ ላይ አረፈበት። የሰማይ ንጉስ ልጅ በእርግጥም ጌታ ነው። ይህ የሆነው ኢየሱስ የ30 ዓመት ሰው በነበረ ጊዜ ስለሆነ ያ ዓመት በእኛ የዘመን አቆጣጠር 30 ዓ.ም ነው።
ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር
ይህ አምስት መቶ ዓመታት የፈጀ በመሃል የነበረ የጊዜ ርዝመት በሁለት ክፍለ ጊዜዎች ተከፍሏል። አንድ ቀንን እንደ አንድ ዓመት ስንቆጥር የሰባት ሳምነትታትን ጊዜ ያህላል፤ ማለትም 7 x 7 ቀናት እኩል ይሆናል 49 ቀናት። አንድ ቀን አንድ ዓመት ከሆነ አይሁዶች እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ነህምያ እና ሚልክያስ በመሳሰሉ በተቀቡ ሰዎች በመጨረሻዎቹ ነብያት አማካኝነት የሚነጋገርበት 49 ቀናት ይቀሩ ነበር ማለት ነው። እነዚህም ዓመታት ሲቆጠሩ እስከ 397 ዓመተ ዓለም ይደርሳሉ። ከዚያ በኋላ የነበሩትን 434 ዓመታት የታሪክ ምሑራን “የዝምታ ጊዜ” ይሏቸዋል ምክንያቱም እግዚአብሔር ዝም ያለበት ጊዜ ነበር፤ አይሁዶችን ለመምራት አንድም ነብይ አልተላከም። ስድሳ እና ሁለት ሳምነት ማለት 62 x 7 ቀናት፤ ማለትም 434 ቀናት ናቸው፤ ይህም 434 ዓመታት ማለት ነው። ስለዚህ አይሁዳውያን አጭር ዘመን ነበራቸው (በዚህ ትንቢት ውስጥ ዘመን ማለት እንደ 7 ሳምንታት ነው የተቆጠረው) በዚህም አጭር ዘመን ውስጥ በነብያት አማካኝነት መለኮታዊ ምሪት ሲያገኙ ቆይተዋል፤ ከዚያ በኋላ ግን በጣም ረጅም ጊዜ (“ዘመናት” በዚህ ትንቢት ውስጥ 62 ሳምንታት ተብለዋል) ይህም አይሁዳውያን ያለ ነብይ ያለ መለኮታዊ ምሪት በራሳቸው ፈቃድ እንዲኖሩ የተተዉበት ዘመን ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ የተጠመቀበት ዓመት ከ 70 ሳምንታቸው ውስጥ 7 + 62 ሳምንታቸውን ጨርሰዋል።
በዚያ ጊዜ አይሁዶች የሺህ ዓመቱ መንግስት ሊመሰረትና እነርሱ ዓለምን በሙሉ ሊገዙ የቀራቸው አንድ ሳምንት ብቻ (7 ቀናት ወይም 7 ዓመታት) ነበር።
[የአሕዛብ አንድ ዓመት 365.24 ቀን ነው። የአይሁዶች ዓመት ግን 360 ቀን ነው።]
ስለዚህ 70 የአይሁድ ዓመታት 69 የአሕዛብ ዓመታት ነው የሚሆኑት።
የ490 ዓመታት ትንቢት = 70 x 7። ስለዚህ በአሕዛብ ዘመን አቆጣጠር ከዚህ ቁጥር ላይ 7 ዓመታት መቀነስ አለብን።
490 የአይሁድ ዓመታት = 483 የአሕዛብ ዓመታት።
በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን ማለት አንድ ዓመት ነው።
ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፡-
ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።
ዳንኤል 9፡26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።
በመጨረሻ የሚመጣው የክርስቶስ ተቃዋሚ አለቃ ሕዝቦች (ሮማውያን) ኢየሩሳሌምን እና ቤተመቅደሱን ያፈርሳሉ። ስለዚህ ዋነኛው የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚመጣው ከሮም ነው፤ እርሱም የመጨረሻው ፖፕ ነው።
መሲሁ በእስራኤል ከተገለጠ በኋላ ሶስት ዓመት ከግማሽ አገልግሎ ተሰቀለ። ከዚህም የተነሳ የመጨረሻው ሳምንት ለሁለት ተከፈለ። በመጀመሪያው ግማሽ ሳምንት ውስጥ ኢየሱስ አገለገለና ከዚያም ለ2,000 ዓመታት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ከአይሁድ ወደ አሕዛብ ዘወር አለ። የኢየሱስ ዳግም ምጻት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ ነው የሚሆነው ፤ በዚያን ጊዜም እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ይወስዳታል። ይህም ከሆነ በኋላ አይሁድን በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ለመምራት የሙሴ እና የኤልያስ አገልግሎት ይጀምራል፤ ይህም የአይሁድ ሕዝብ ሳይጨርሱ የቀረባቸው ግማሽ ሳምንት ነው።
ስለዚህ “የዘመን እኩሌታ” የተባሉት ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በ70ኛው ሳምንት የመጀመሪያ አጋማሽ (የኢየሱስ አገልግሎት) እና የ70ኛው ዓመት ኋለኛ አጋማሽ ማለትም የሙሴ እና የኤልያስ አገልግሎት መካከል የሚገኙት የዘመን ክፍተት ናቸው። የቤተክርስቲያን ዘመናት የአይሁድን ዘመን የመጨረሻ ሳምንት በሁለት ግማሾች ከፈሉ፤ ከዚያም በሁለቱ የሳምንት አጋማሾች መካከል ያለውን ክፍተት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይሞሏቸዋል።
ዳንኤል 7፡25 ልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።
የባቢሎን ሚስጥራት የስሕተት መንፈስ ከፋርስ መንግስት ጀምሮ በግሪክ መንግስት አልፎ በሮማ መንግሰት በኩል ነው የመጣው (የሮማ መንግስት ክርስቶስን ገድሏል፤ ቀጥሎ ደግሞ በመጀመሪያዎቹ ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እስከ 312 ዓ.ም ድረስ የጥንቶቹን ክርስቲያኖች ገድሏል)፤ ከዚያም በኋላ የባቢሎን ሚስጥራት የስሕተት መንፈስ በዲኖሚኔሽናዊ አሰራሩ አማካኝተን ክርስቲያኖችን ለማሳት እና ለመግደል በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት አንሰራርቷል። ቤተክርስቲያንን በአንድ አምባገነን ግለሰብ መምራት የማሳሳት እና የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን የማጥፋት ዘመቻውን የቤተክርስቲያን ዘመናት እስኪጠናቀቁ እና ቤተክርስቲያን እስክትነጠቅ ድረስ ይቀጥላል።
ስለዚህ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀስቃሽነት የሚመሩ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች እስከ “ዘመን እኩሌታ” (ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት) እስኪጠናቀቁ ድረስ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ይቃወማሉ፤ ያፍናሉ። ከዚያ በኋላ ሁለቱ አይሁዳውያን ነብያት ይገለጣሉ፤ ኢየሱስ በምድር ላይ ለሚተዋቸው ሰዎች ወዲያው የሶስት ዓመት ከግማሹ የታላቁ መከራ ዘመን ይጀምራል።
“የሚመጣው አለቃ ሕዝብ ከተማይቱን እና ቤተመቅደሱን ያፈርሳሉ”።
የክርስቶስ ተቃዋሚው አለቃ ይመጣና በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ይነግሳል። የእርሱ ሕዝብ በ70 ዓ.ም የኢየሩሳሌምን ከተማ እና ቤተመቅደሱን (የሰሎሞንን ቤተመቅደስ) አፍረሰዋል። ይህ የማፍረስ ተልዕኮ የተፈጸመው በሮማዊው ጀነራል ታይተስ ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚው ሕዝብ እነዚህ ከሆኑ የወደፊቱ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚነሳው ከሮም መሆን አለበት።
በ135 ዓ.ም ሐድሪያን የተባለው የሮማ ገዥ ባር-ኮክበ የተባለውነ የአይሁዶች የተቃውሞ አመጽ ደምስሷል፤ ከዚያም በኋላ ኢየሩሳሌም በጥማድ በሬዎች አረሰ። ቤተመቅደሱም የኢየሩሳሌም ከተማም በሮማውያን እጅ ነው የጠፉት።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
“እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤”
ይህ የሚናገረው ቃል ኪዳን ስለ ማድረግ አይደለም። ይህ የሚናገረው አስቀድሞ የተደረገ ቃል ኪዳንን ስለ ማጽናት ነው።
“እርሱም” የሚለው ቃል የሚናገረው ስለ እግዚአብሔር ነው እንጂ ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ አይደለም።
እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር ያደረገውን ቃልኪዳን በክርስቶስ አጸናው።
ቃልኪዳን ከተደረገ በኋላ ነው ቃልኪዳን የሚጸናው።
(የጸና ቃልኪዳን ሊፈርስ አይችልም።)
1ኛ ዜና 16፡16 ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።
እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር ቃል ኪዳን ገባ፤ ይህንንም ቃል ኪዳን በኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት፣ እና ትንሳኤ አጸናው ወይም አረጋገጠው።
የክርስቶስ ተቃዋሚ መጀመሪያ ከአይሁዶች ጋር ቃልኪዳን ያደርጋል፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ ያጸናዋል የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። የክርስቶስ ተቃዋሚ ክፉ እንደመሆኑ ቃልኪዳን ያፈርሳል እንጂ አያጸናም።
“በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል”።
ኢየሱስ ከሶስት ዓመት ተኩል አገልግሎት በኋላ በተሰቀለበት ሰዓት እግዚአብሔር የቤተመቅደሱን ቅድስተ ቅዱሳን ለቅቆ ሲወጣ የቤተመቅደሱ መጋረጃው ተቀደደ፤ ከዚያ በኋላ የቤተመቅደስ አምልኮ ቀረ። የእግዚአብሔር በግ ለሐጥያት ለአንዴ እና ለዘላለም የሚበቃ መስዋእት ሆኖ በመቅረቡ እሥራኤሎች በተደጋጋሚ ያቀርቧቸው የነበሩ የበጎች መስዋእቶች ከዚያ በኋላ ቀሩ።
በ70 ዓ.ም ሮማዊው ጀነራል ቤተመቅደሱን እና የኢየሩሳሌምን ከተማ አፈራረሰ። በ132 እና 135 ዓ.ም ሃድሪያን የተባለው የሮማ ገዥ 580,000 አይሁዶችን ገድሎ የቀሩትን ከሃገራቸው አባረራቸው። ቤተመቅደሱ በነበረበት ቦታ አየልያ ካፒቶሊና የተባለ አረማዊ ቤተመቅደስ ሰራበት። ከዚያ በኋላ በ691 ዓ.ም ሙስሊሞች ቤተመቅደሱ ነበረበት ብለው በገመቱበት ቦታ ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለውን መስጊዳቸውን ሰሩበት። ስለዚህ እግዚአብሔር ቤተመቅደሱ የነበረበት ስፍራ በመንፈስ ውድማ ሆኖ እንዲቀር አደረገ። እስከዛሬም እንደዚያው ነው።
ፖፑን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አድርጎ ለማጽናት በስላሴ የማያምኑ ሶስት ባርቤሪያውያን ነገዶችን ጨፍጭፎ ማጥፋት በ533 እና 552 ዓ.ም መካከል ኢጣልያ እና ሰሜን አፍሪካ ሙሉ በሙሉ እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል። ይህም ውድመት በአውሮፓ ውስጥ ሁሉ ተሰራጭቶ የጨለማው ዘመን እንዲጀምር መንስኤ ሆኗል።
በ1929 የሮማ ካቶሊክ መናገሻ የሆነችዋን ቫቲካን ሙሶሊኒ የከተማ መንግስት እንድትሆን እውቅና ሰጣት። በዚያው ዓመት ዓለም በሙሉ በታላቅ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ኪሳራ ተመታ።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን እምቢ እያሉ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎችን እና ልማዶችን ሲቀበሉ በዲኖሚኔሽናዊ ክርስትና ውስጥ ያለው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ከሮም ተነስቶ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተሰራጭቷል፤ ስለዚህ እውነተኛ እምነት እየጠፋ ይሄዳል።
እምነት የሚመጣው መጽሐፍ ቅዱስን ከማመን ብቻ ነው።
ዳንኤል 7፡26 ነገር ግን ፍርድ ይሆናል፥ እስከ ፍጻሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል።
የሐይማኖት ስሕተት ለዘላለም አይቀጥልም። በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ስላለማመናቸውና ስለ ሐጥያታቸው መልስ ይሰጣሉ።
ዳንኤል 7፡27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።
እግዚአብሔርን የምናገለግለው ቃሉን በመታዘዝ ነው እንጂ የቤተክርስቲያን ልማዶችን በመከተል አይደለም፤ የቤተክርስቲያን ልማዶች ምንም ያህል ተቀባይነት ያገኙ ቢሆኑም እንኳ ልንከተላቸው አይገባም።