ዳንኤል ምዕራፍ 2. የብረት እና ሸክላ እግሮች
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዳንኤል አራት የአሕዛብ መንግስታትን የሚወክል የአሕዛብ ምስል በራዕይ አየ። እግሮቹ በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚያልፍ የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ይወክላሉ።
ዳንኤል በዚህ የአሕዛብ ምስል ላይ ተመርኩዞ ጠለቅ ያለ ትንቢታዊ መልእክት አስተላልፏል። በ600 ዓመተ ዓለም አካባቢ ታላቁ የባቢሎን ንጉስ እና ካሕን (ብልህ ሃሳቦችን የሚያፈልቀው የወርቁ ራስ) በከዋክብት ንባብ ላይ የተመሰረተ ትንበያ፣ በክረምት አጋማሽ ላይ የሚከበር የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን፣ የኢሽታር እንቁላሎች፣ እና አንድ ሰው ሆኖ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ እና የገንዘብ ኃይልን በአንድ ላይ አጣምሮ በመያዝ ሐይማኖታዊ አምልኮዎች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ የሚሰጥ ፖለቲካዊ ንጉስ የመሳሰሉ ሃሳቦችን አመነጨ።
በሆነ መንገድ እነዚህ ሃሳቦች ወደ ምዕራቡ ዓለም ተሰራጭተው ቤተክርስቲያንን ተቆጣጥረዋል።
እነዚህ ሃሳቦች ብርማ በሆነው የፋርሶች የመንግስት አወቃቀር እና ግዛት የማስፋት ስልት አማካኝነት ድጋፍ አግኝተዋል። የአሕዛብ ምስሉ ላይ እንዳሉት እጆች ፋርሶች ብዙ ሕዝቦችን ወደ መጀመሪያው ዓለም አቀፍ ግዛትና መንግስት ውስጥ ጠቅልለው ያዙ። ከዚያ በኋላ ሐይማኖታዊ ስሕተት በግሪክ ፍልስፍና ብልሃት ተጠቅሞ ተስፋፋና በስተመጨረሻ ያለምንም እፍረት የጣኦት አምልኮ ሃሳቦችን ከክርስትና እምነት ጋር አጋባ።
ዝነኛው ዩልየስ ቄሳር ፐንቲፍም ሮማዊ ፈላጭ ቆራጭም በሆነ ጊዜ የባቢሎን ሚስጥራት የሮማ መንግስት ውስጥ ገብተው ተደላደሉ። የብረቱ እግር የሚወክለው ተቃዋሚዎቻቸውን የመደምሰስ ኃይል ያላቸውን የሮማ ወታደራዊ ሰራዊት ነው። ለዕድሜ ልክ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ለመቀመጥ ዋነኛው ዘዴ ተቃዋሚዎችን በሙሉ ማጥፋት ነው። አሕዛብ የሆኑት የሮማ ነገስታት ፖንቲፍ በሚለው ማዕረግ መጠራት ጀመሩ፤ ፖነቲፍ ማለት የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀ ካሕን ነው። እነዚህ ሃሳቦች ኋላ ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰተት ብለው ገበቡ፤ ከዚያም ክርስትና እና የባዕድ አምልኮ ሲጋቡ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የባቢሎን ሚስጥር ሆነች።
በቀድሞ ዘመን መዳን ለአይሁድ ብቻ ነበረ እንጂ ለአሕዛብ አልነበረም።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነገረው ትንቢት የሴቲቱ ዘር ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ይገልጻል። እርሱም ያለ ሰብዓዊ አባት ከድንግል ሴት ብቻ ተወለደ። ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጭ የተወለደ ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው።
ዘፍጥረት 3፡15 በአንተ (በእባቡ) እና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።
ሔዋን የተቀጣችው ስላረገዘች መሆኑን ልብ በሉ።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጭ የተወለደው ብቸኛው ሰው ኢየሱስ በግብረ ስጋ ግንኙነት አማካኝነት በተወለዱት ሕዝብ እጅ ተገደለ። ልጅ መውለድ በጣም አስጨናቂ ነገር ነው። ከዝሙት ጋር የተያያዙ ወንጀሎች እና ሐጥያቶች እንዲሁም አከራካሪ ጉዳዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዜና ማሰራጫዎች ላይ ትልቅ ርዕሶች ናቸው። ስለ መጀመሪያው ሐጥያት በተመለከተ ቤተክርስቲያኖች ያላስተዋሉት አንድ ነገር አለ። እርግዝና ከሔዋን ውድቀት ጋር የተያያዘ ክስተት ነው።
በኢየሱስ እና በሰይጣን መካከል የተደረገው ታላቅ ጦርነት የተፈጸመው በቀራንዮ ነው። አይሁዶች ኢየሱስን ሰቀሉትና መዳን ወደ አሕዛብ ተሸጋገረ። (መስቀል ይህ መዳን ወደ አሕዛብ መሸጋገሩን የሚያሳይ ምልክት ነው)። መስቀሉ የሚገኘው በአሕዛብ ምስሉ ተረከዝ አካባቢ ነው። የመዳን ቀይ ክር ወደ አሕዛብ ምስል የገባው በተረከዙ በኩል ነው።
ስለዚህ የአሕዛብ ምስሉ እግሮች በተለይም አሕዛብን የሚመለከተውን የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ይወክላል።
በ378 ዓ.ም ቴዎዶሲየስ ክርስቲያን የሮማ ገዥ በሆነ ጊዜ ፖንቲፍ የሚለውን ማዕረግ አልቀበልም አለ። የሮማ መንግስት በባርቤሪያውያን ወራሪዎች እና ስደተኞች ጫና በዝቶበት ወደቀ። በዚያ የውድቀት ጊዜ የሮም ጳጳስ ፖንቲፍ የሚለውን ማዕረግ ለራሱ ወሰዶ እስከ ዛሬ ድረስ እየተጠቀመበት ነው። በጠንካራ ብረት የተወከለው የሮማ መንግስት ሲፈራርስ የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ወይም ፖንቲፍ አውሮፓ ውስጥ በሚኖሩ ባርቤሪያውያን ላይ በስልጣን ከፍ ከፍ አለባቸው።
ቤተክርስቲያንን ለባርቤሪያውያን ምቹ ለማድረግ ተብሎ ብዙ የባዕድ አምልኮ ሃሳቦች ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው እንዲገቡ ተደረገ።
ከእነዚህ ሃሳቦች ውስጥ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ ያጌጠ የገና ዛፍ፣ የፋሲካ እንቁላሎች እና የፋሲካ ጥንቸሎች፤ የቤተክርስቲያን ጉልላቶች፣ የሁዳዴ ጾም እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
ቤተክርስቲያንም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሃሳቦችን ማመን እየተላመደች መጣች።
ነገር ግን የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ሃሳቦችን እየፈጠሩ አንዳቸው ከሌላቸው ይለያያሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሃሳቦችን መቀበል አረማውያንን ወደ ቤተክርስቲያን ለማስገባት ጥሩ ዘዴ ተደርጎ ተቆጠረ፤ ነገር ግን እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሃሳቦች እየበዙ ሲሄዱ ሰዎች ዲኖሚኔሽን በሚባሉ የተለያዩ ቡድኖች መከፋፈልና መለያየት ጀመሩ። እያንዳንዱ ቡድን እኔ ነኝ ትክክለኛ ይላል። እያንዳንዱ ቡድን በአንድ መሪ መመራት ጀመረ፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኑ ሊያድግ የሚችለው በአንድ መሪ ሲመራ ነው። የሮም ብረት እግር መንፈስ ሐይማኖተኛ ሰውንም ልክ እንደ ቄሳር የቤተክርስቲያን ራስ መሆን አለብኝ እንዲል አደረገው። ስልጣን የሚወድ የቤተክርስቲያን ራስ ብዙም ሳይቆይ ፈላጭ ቆራጭ ይሆናል። የሮም ጳጳስ በይፋ የቤተክርስቲያን ራስ ሆነ። ዛሬ አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባ ገነን መሪ ፖፑ ነው።
በብረት እግሮች የተወከለው አራተኛው መንግስት በዙሪያው ያሉትን ሕዝቦች ሰባብሮ በስልጣን ያደገው የአሕዛቡ ሮማ መንግስት ነው። በስተመጨረሻ ባርቤሪያውያን የሮማ መንግስትን ደመሰሱት። ሮም ግን ከተደመሰሰች በኋላ በአውሮፓ ላይ የነበራትን ፖለቲካዊ ስልጣን በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኩል የገንዘብ ኃይል በመያዝ መልሳ አገኘችው።
ሮም እንደ ፍጥረታዊ መንግስት ይዛ የነበረው ስልጣን ግልባጩ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኩል መንፈሳዊ መንግስት ሆኖ ቀጠለ።
ዳንኤል 2፡40 አራተኛውም መንግሥት ሁሉን እንደሚቀጠቅጥና እንደሚያደቅቅ ብረት ይበረታል፤ እነዚህንም ሁሉ እንደሚፈጭ ብረት ይቀጠቅጣል ይፈጭማል።
ስለዚህ ሰይጣን ቤተክርስቲያንን ኃይል አሳጣት። የዲኖሚኔሽን መንፈስ በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩ አመለካከቶች በሚገኙበት ቦታ ቤተክርስቲያንን በቀላሉ ይገነጣጥሏታል። የተለያዩት ቡድኖች እርስ በራሳቸን እያጠቁ እስር በራሳቸውን አቆሰሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለው የስላሴ ትምሕርት በፈጠረው ጭቅጭቅ ሰዎች ተገዳድለውበታል። በጨለማው ዘመን ውስጥ በቤተክርስቲያን የነበረው የስልጣን ፉክክር ብዙ ሰዎች እንዲገደሉ እና በግፍ እንዲሰቃዩ ምክንያት ሆኗል፤ የተገደሉት እና የተሰቃዩት ሰዎች መከራ እና ሞት የደረሰባቸው ከተደራጀችዋ ቤተክርስቲያን ጋር መተባበር አንፈልግም በማለታቸው ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የገንዘብ እና የፖለቲካ ኃይል ሆና ነው የተነሳችው፤ ይህም በምስሉ እግሮች ውስጥ በሚገኘው የብረት ስብርባሪ ነው የተመሰለው። ብረት ጠንካራ ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምዕራቡ ዓለም በርዝመቱ ከሁሉ የሚበልጥ ያልተቋረጠ የስልጣን ሽግግር ታሪክ አላት። ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ፖፕ ሲሞት ሌላ ፖፕ እየተተካ እስከ ዛሬ ቆይቷል። ስለዚህ ጠንካሮች ናቸው።
ሳይጠፉ ለመቆየት የሚያዋጣ ዘዴ ሆኖ የተገኘው አንድ ግለሰብን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ ማስቀመጥ ነው፤ በተለይም ሶስት አካል ያሉት ስላሴ መለኮት ነው ብለው ሲያስተምሩ። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ከካቶሊክ ተነጥለው ወጥተዋል ግን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሳትፈርስ የቆየችባቸው ዘዴዎች ፕሮቴስታንቶችንም ስበዋቸዋል፤ ስለዚህ ፕሮቴስታንቶችም ሳይጠፉ ለመቆየት እንዲረዳቸው አንዳንድ ቁልፍ የሆኑ የካቶሊክ ሃሳቦችን ተከትለው እየተጠቀሙባቸው ነው። “ፓስተር” አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፤ በኤርምያስ ትንቢት ውስጥ ደግሞ ስድስት ጊዜ ተወግዟል። ሆኖም ግን ይህ የአገልግሎት ዘርፍ የቤተክርስቲያን ራስ እና የአስራት ገንዘብ ሰብሳቢ ሆኗል። (ይሁዳ ትዝ አይላችሁም?) በገንዘብ ፍቅር እና በስልጣን ፍቅር ተጠምዳ ቤተክርስቲያን በፓስተሮቿ ምክንያት 45,000 ዓይነት ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ወዳልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ተሰነጣጥቃለች። እያንዳንዱ እኔ ነኝ ትክክለኛ ይላል። የአሕዛብ ምስሉ ወደ ሁለት እግር ከተከፈለ በኋላ እግሮቹ ደግሞ ወደ አስር ጣቶች ተከፋፍለዋል። መከፋፈል ወይም መሰነጣጠቅ የአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች ባህርይ ነው።
የገንዘብ ፍቅር እና በሕዝብ ላይ ባለ ስልጣን የመሆን ፍቅር የዲኖሚኒሽናዊ ስርዓት ጠንካራ ብረት ነው፤ ይህም ሰዎች “ፓስተር” ነኝ ወይም ጳጳስ፣ ወይም ካርዲናል ወይም ፖፕ ነኝ እንዲሉ ያደርጋቸዋል። ብቻ ዋና የሚፈልጉት ነገር የአንድ ቤተክርስቲያን ራስ መሆን ነው።
ገንዘብ እና ስልጣን የሰውን ገዥነት ያጠናክራሉ። እያንዳንዱ መሪ ለራሱ መንግስትን ሲመሰርትና ሲያስፋፋ ዲኖሚኔሽናዊ ድርጅቶችን ጠንካራ እና ውጤታማ ያደረጋቸው ይህ ብረት የገንዘብ እና የስልጣን ፍቅር ነው።
ዳንኤል 2፡41 እግሮቹና ጣቶቹም እኩሉ ሸክላ እኩሉም ብረት ሆኖ እንዳየህ፥ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየሁ፥ የብረት ብርታት ለእርሱ ይሆናል።
ነገር ግን መከፋፈል የሚፈጠረው አንዳንድ ሰዎች ፓስተሩን ትተው ኢየሱስን እና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመከተላቸው ነው።
የቤተክርስቲያን ራስ መሆን ያለበት ክርስቶስ ነው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
ስለዚህ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ስራውን የሚሰራ አንድ ነገር አለ፤ እርሱም ሸክላ ነው።
የአሕዛብ ምስሉ ከተሰራባቸው ብረቶች መካከል ሕይወትን ማብቀል የሚችለው ሸክላው ብቻ ነው። ስለዚህ ምንጊዜም ቢሆን ከተደራጁ የቤተክርስቲያን ስርዓቶች ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን እና ኢየሱስን የሚያስቀድሙ ክርስቲያኖች ይኖራሉ። እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ብቻ ያምናሉ እንጂ ገንዘብ፣ ዝና፣ ወይም ስልጣን ምንም አይገርማቸውም። በቸኛው ፍላጎታቸው መጽሐፍ ቅዱስን መከተል ነው።
ሸክላ ሕይወትን ያበቅል ዘንድ እርጥብ መሆን አለበት።
መጽሐፍ ቅዱስ “የሸክላ ጭቃ” ይላል። ይህ እርጥብ ሸክላ ነው፤ ማለትም በውሃ የታጠበ እና በሸክላ ሰሪው እጅ የተፈለገውን ቅርጽ መያዝ የሚችል ነው።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ የሚጠቅሱ ክርስቲያኖች እውነተኛ ቤተክርስቲያን ወይም የሙሽራይቱ አካል ናቸው። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ እንደ ክሪስማስ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት፣ ዲኖሚኔሽን የመሳሰሉ ሃሳቦችን ሳይሆን የሚያምኑት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ነው። እነርሱ በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው ታጥበው መንጻት የሚችሉት።
ከመጨረሻው እራት በኋላ ያልተለመደ ነገር ተደረገ።
ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜ እግር ላይ ያልተለመደ ትኩረት አደረገ።
ጴጥሮስ ሊቃወም ሞከረ፤ ኢየስስ ግን ጴጥሮስ እግሩን መታጠብ እንደሚያስፈልገው አስጠንቅቆ ነገረው። ከዚያም ጴጥሮስ ኢየሱስ ራሱን፣ እጆቹን፣ እና እግሮቹን በሙሉ እንዲያጥብለት ፈለገ። ኢየሱስ ግን አይሆንም አለው። እግሮቹ ብቻ ናቸው መታጠብ የሚያስፈልጋቸው።
ኢየሱስ አንድ ነገር ሊያስተምራቸው ፈልጓል፤ እነርሱ ግን አልገባቸውም።
ዮሐንስ 13፡8 ጴጥሮስም፦ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም፦ ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።
9 ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
10 ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።
ኢየሱስ ስለ ይሁዳ እና ሐጥያት ታጥቦ እንደሚወገድ እየተናገረ ነበር።
ይህ ድርጊት በውሃ ከእግር ላይ አቧራ አጥቦ ከማስወገድ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ምክንያቱም አቧራ ለማስወገድ መታጠብ ከሆነ ወደ ቤት ሲገቡ ታጥበዋል። በዚህ ሰዓት ግን ገብተው እራት በልተው ተነስተዋል። እግራቸውን ታጥበው አቧራ ያራገፉት የቤቱ በር ላይ ነበር።
ደግሞም ትሕትናን ከማስተማር ጋር ምንም የሚያገናኘውም ነገር የለም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ለጴጥሮስ አሁን የማድርገውን አታውቅም ብሎታል። ጴጥሮስ የሚጋበው ከጊዜ በኋላ ነው።
ዮሐንስ 13፡5 በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
7 ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
ጴጥሮስ ኋላ የሚማረው ትልቅ ትምሕርት ምንድነው?
እግዚአብሔር ሶስት ጊዜ እርኩስ እንስሳትን አርዶ ስለ መብላት ራዕይ አሳየው። ቀስ ብሎ ጴጥሮስ ይህ ራዕይ ትርጉሙ አይሁዶች የሚጸየፏቸው እርኩስ የሆኑት አሕዛብም በወንጌሉ አማካኝነት እንደሚድኑ መሆኑን ተረዳ።
የሐዋርያት ሥራ 10፡10 ተርቦም ሊበላ ወደደ፤ ሲያዘጋጁለት ሳሉም ተመስጦ መጣበት፤
11 ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤
12 በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።
13 ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚልም ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
14 ጴጥሮስ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ አንዳች ርኵስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና አለ።
15 ደግሞም ሁለተኛ፦ እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
16 ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፥ ወዲያውም ዕቃው ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ጴጥሮስ የተማረው ትልቅ ትምሕርት ይህ ነው።
ወንጌል ለአሕዛብ መድረስ አለበት።
ዳንኤል ባየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ እርጥቡ ሸክላ የዳኑትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት አሕዛብ ናቸው። እነርሱ እርጥብ ሸክላ ናቸው ምክንያቱም በቃሉ ውሃ ታጥበዋል። ሐዋርያት የእግዚአብሔርን ቃል፣ የመዳንን ወንጌል ለአሕዛብ ማድረስ አለባቸው።
ከአሕዛብ ምስሉ ውስጥ የቤተክርስቲያን ዘመናትን የሚወክሉት እግሮቹ ብቻ ናቸው መታጠብ የሚችሉት።
የባቢሎንን መንግስት የሚወክለው ራስ በታሪክ ውስጥ ሞቶ ካለፈ ብዙ ዘመን ሆኖታል። ባቢሎን በ539 ዓመተ ዓለም በፋርስ እና ሜዶን ተሸንፋለች።
የፋርስ እና የሜዶናውያንን መንግስት የሚወክሉት እጆችም ከብዙ ዘመን በፊት አልፈዋል። እነርሱ ደግሞ በ331 ዓመተ ዓለም በታላቁ አሊግዛንደር ተሸንፈዋል።
በ1960 ዓ.ም የራሺያ መሪ ክሩሼቭ የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ ንዴቱን መቆጣጠር አቅቶት ንግግር በሚያደርግበት መድረክ ላይ ጫማውን አውልቆ ፑልፒቱን በጫማው ደብድቧል።
ይህ ድርጊት የዓለም ሁሉ ትኩረት ወደ እግር እንዲሆን አድርጓል።
ጫማ ሲወልቅ እግር ይገለጣል።
በዘመን መጨረሻ ላይ የአሕዛብ ምስሉ ውስጥ በእግሮች የተመሰሉትን ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት በተመለከተ መገለጥ ማግኘት አለብን።
ወንድም ብራንሐም የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ሚስጥር በ1960 ገልጦ አስተምሯል።
ራዕይ 1፡20 በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፥ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
መላእክት መልእክተኞች ናቸው። እያንዳንዱ መብራት አንድ የቤተክርስቲያን ዘመንን ይወክላል።
እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ሕዝቡን የሚመራ የተቀባ መልእከተኛ ተልኮለታል።
ጳውሎስ፣ አይሬንየስ፣ ማርቲን፣ ኮሉምባ፣ ማርቲን ሉተር፣ ጆን ዌስሊ፣ ዊልያም ብራንሐም።
እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር በየዘመናቱ ሰዎች እውነትን ያገኙ ዘንድ እንዲያስተምሯቸው የላካቸው የእምነት አርበኞች ናቸው።
ብልጣሶር በደገሰው ድግስ ላይ የመጀመሪያው የባቢሎን መንግስት አበቃ።
ዳንኤል 5፡5 በዚያም ሰዓት የሰው እጅ ጣቶች ወጥተው በንጉሡ ቤት በተለሰነው ግንብ ላይ በመቅረዙ አንጻር ጻፉ፤ ንጉሡም የሚጽፉትን ጣቶች አየ።
እጅ መጣችና በመቅረዙ አንጻር ግድግዳው ላይ በባቢሎናውያን ሚስጥራት የተመሰረተው የመጀመሪያው የአሕዛብ መንግስት መውደቁን ጻፈች።
መቅረዙ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ነው የሚወክለው።
በመቅረዙ አንጻር ከመቅረዙ ውጭ ማለት ነው።
በሌላ አነጋገር የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲጠናቀቁ የእጅ ጽሕፈቱ በዘመን ግድግዳ ላይ ይጻፋል።
የባቢሎን ሚስጥር ማለትም የሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን እና ፕሮቴስታንት ልጆቿ የመጨረሻው የአሕዛብ መንግስት የሚጠናቀቅበት ታላቁ መከራ ውስጥ እንዲጠፉ ተፈርዶባቸዋል።
በመጀመሪያው የአሕዘብ መንግስት ማለትም በባቢሎን መንግስት ዘመን ነብዩ ዳንኤል በምሳሌ ተጠቅሞ የአሕዛብን ታሪክ ገልጧል። የእነዚህን ምሳሌዎች ትርጉም ማወቅ ባለመቻላችን የተነሳ ብዙ እውነት ተሰውሮብናል።
ዳንኤል 12፡4 ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።
በዘመን መጨረሻ በመጨረሻዎቹ የአሕዛብ መንግስታት ዘመን እውቀት እጅግ በሚበዛበት ጊዜ እግዚአብሔር ዊልያም ብራንሐም የሚባል ነብይ አስነስቶ በ1963 ዓ.ም የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር ይገልጣል። እነዚህ ሚስጥራት የዳንኤልን ትንቢት ለመተርጎም እና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ለማስተዋል ይረዱናል።
በ1960 የታየው የክሩሼቭ ጫማ “የዘመኑ ምልክት” ነው፤ ትርጉሙም በአሕዛብ ምስሉ እግሮች የተመሰለው የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ዘመናት ወደ መጠናቀቂያቸው እየቀረቡ መሆኑን ነው።
የቃሉ ሚስጥራት መገለጥ ወደ መጨረሻው ዘመን እየደረስን መሆናችንን ያመለክታል። በሰባተኛው ወይም በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ነን።
እግዚአብሔር ትኩረቱ የምስሉ እግሮች ውስጥ ያለው ሸክላ ላይ ነው። ሸክላ ሰው ሰራሽ ልማዶችን እና የዲኖሚኔሽናዊ ድርጅቶች ትዕዛዛት የማይከተሉ ክርስቲያኖችን ይወክላል።
የጥንቶቹ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ የሚተዳደሩት በሽማግሌዎች እንጂ በአንድ ግለሰብ አልነበረም።
እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነበር የሚያምኑት።
ዳንኤል 2፡42 የእግሮቹም ጣቶች እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ እንደ ነበሩ፥ እንዲሁ መንግሥቱ እኩሉ ብርቱ እኩሉ ደካማ ይሆናል።
የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ብረት በጣም ጠንካራ እና እየተስፋፋ የሚሄድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለመከተል የሚፈልጉ ግለሰቦች ለስላሳ ሸክላ ትልቅ ቤተክርስቲያን ለመገንባት የሚያዋጣ ዘዴ አይደለም። እነዚህ ግለሰቦች ጥቂት ስለሚሆኑ ይበታተኑ እና የሚያስተውላቸውም የለም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ብዙውን ጊዜ የምትሰበሰበው በሰዎች ቤት ውስጥ ነበር።
ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች በመጠየቃቸው ምክንያት ከዋናዎቹ ቤተክርስቲያኖች ተገፍተው የወጡ ሸክላዎች ታዋቂነት ካገኙት ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑት የቤተክርስቲያን ትምሕርቶች ተለይተው ከመሄድ በቀር ሌላ አማራጭ የላቸውም። ከዋናዎቹ ቤተክርስቲያኖች ጋር ሲነጻጸሩ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች እውነተኛ ቤተክርስቲያን በጣም ደካማ ትሆናለች።
አስር የእግር ጣቶች።
ይህ ዮሐንስ በራዕይ ካየው ባለ ሰባት ራስ እና ባለ አስር ቀንድ አውሬ ጋር የተያያዘ ነው።
ዮሐንስ ማየት የጀመረው በምድረ በዳ ውስጥ በሆነ ጊዜ ነው፤ ምድረ በዳ በቤተክርስቲያን ቡድኖች ውስጥ የማይፈለጉ የተገፉ ሰዎች የሚገኙበት የብቸኝነት ስፍራ ነው።
ራዕይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
አስሩ ቀንዶች እንደ ነገስታት ስልጣን አላቸው። እነዚህ ነገስታት ዘውድ አልጫኑም ግን የንጉስ ስልጣን አላቸው። እነዚህ ሰዎች ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።
በመጨረሻው ዘመን አስር ኃይለኛ ፈላጭ ቆራጮች ይነሳሉ። እነዚህ ፈላጭ ቆራጮች የሚነሱባቸው ሃገሮች በዮሐንስ ዘመን አልነበሩም።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
ነገር ግን እነዚህ አስር ፈላጭ ቆራጮች በታላቁ መከራ ዘመን ለአጭር ጊዜ ተባብረው ለመግዛት አንድ ይሆናሉ። አውሬው ወይም ሰይጣን ሊቀመጥበት የሚፈልገው ስልጣን የፖፑ ስልጣን ነው። ዳንኤል ስለ ታናሽ ቀንድ ወይም ታናሽ ስልጣን ትንቢት ተናግሯል።
ዳንኤል 8፡9 በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ የመርከቦችም ሲሶው ጠፋ።
ፖፑ የሚኖርባት ሮም ከተማ ውስጥ ያለችው ቫቲካን ከተማ በምድር ላይ ከሁሉ ትንሽዋ መንግስት ናት። ቫቲካን ከተማ ትንሽ ከመሆኗ በተጨማሪ ሮም የተቆረቆረችባቸው የመጀመሪያዎቹ ሰባት ኮረብታዎች አጠገብ ነው የምትገኘው፤ ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ተመልከቱ።
ቫቲካን ከተማ 800 ዜጎች ሲኖሯት ስፋቷ አንዲ ኪሎ ሜትር ካሬ ብቻ ነው።
እንዲህም ሆኖ ግን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ካሉ ድርጅቶች ሁሉ በሃብት አንደኛ ናት።
ሰይጣን በስተመጨረሻ የሚጠቀመው ቫቲካንን ነው፤ ምክንያቱም ቫቲካንን ከያዘ ብዙ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ እና የገንዘብ ኃይል እና ተጽእኖ ማድረግ ይችላል።
ሰይጣን በሰማይ እኛን መክሰስ ይችላል።
የሙሽራይቱ አካል የሆኑ ክርስቲያኖች አዲሱን የማይሞተውን አካላቸውን ከለበሱ በኋላ ሐጥያት ስለማይሰሩ ከዚያ ወዲያ ሰይጣን ሊከስሳቸው አይችልም። ከዚያ በኋላ ክርስቶስ እንደ ሊቀ መልአኩ ሚካኤል ሆኖ በመገለጥ ሰይጣንን ከሰማይ ያባርረዋል።
ራዕይ 12፡7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥
8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።
9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
ሙሽራይቱ እራት ለመብላት ወደ ሰርጉ ግብዣ ትሄዳለች። ሰነፎቹ ቆነጃጅት እና ዓለም ግን ለአውሬው እራት ሊሆኑ ይሄዳሉ።
ስለዚህ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ ስትሄድ ሰይጣን ወደ ምድር ተወርውሮ ስለሚወድቅ ምድር ላይ የሚያርፍበት ስፍራ ይፈልጋል።
በዚህ ጊዜ ነው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዓለም ሁሉ አንደኛ ሃብታም ቤተክርስቲያን ስለመሆኗ ዋጋ የምትከፍለው፤ ምክንየቱም የሰይጣን ዓይን በእርሷ ላይ ይሆናል።
ራዕይ 12፡12 ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።
ሰይጣን ዓለምን ለመቆጣጠር እና ሙሉ በሙሉ ለመግዛት የታላቁ መከራ ዘመን ሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ብቻ ነው ያለው። ያም ጊዜ ለዓለም እጅግ አስጨናቂ ጊዜ ይሆናል።
ሰይጣን የሆነ ሰው ውስጥ ይገባ እና እንደ ፖፕ ሆኖ ስልጣን ይይዛል። ምናልባትም ራሱን ፖፕ ጴጥሮስ ዳግማዊ ብሎ ይጠራ ይሆናል።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ከሁሉ ይበልጥ ታላቅ የሐይማኖት ድርጅት ስለ መመስረቷ የምትከፍለው ዋጋ ይህ ነው። ሰይጣን አዲስ መኖሪያ በሚፈልግበት ጊዜ ሃብታምነታቸው በቀላሉ የሰይጣን ዓይን ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።
ሮምን የመሰረታት ሮሙለስ ነበር። የሮም የመጀመሪያ ገዥ ኦጋስተስ ነበር። የሮም የመጨረሻ ገዥ ደግሞ ሮሙለስ ኦጋስተለስ ነበር። ስለዚህ የመጨረሻው ገዥ ከመጀመሪያው ገዥ ጋር ስሙ አንድ ዓይነት ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነበር ትላለች። ስለዚህ ፖፕ ጴጥሮስ ዳግማዊ ነኝ የሚል ፖፕ ሲመጣ ልብ በሉ። ይህ ሲሆን በሕይወት ኖራችሁ ካያችሁ ታላቁ መከራ ውስጥ ገብታችኋል ወይም ታላቁ መከራ ሊጀምር በጣም ቀርቧል ማለት ነው።
ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።
የመጨረሻው ፖፕ በፊት እንደተለመደው በካርዲናሎች ምክር ቤት ተመርጦ አይደለም ወደ ስልጣን የሚወጣው።
በሆነ ተንኮል ተጠቅሞ ስልጣኑን ነጥቆ ነው የሚወስደው።
ዳንኤል ያየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ ያሉት አስር ጣቶች ራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ የተጠቀሰው የአውሬው 10 ቀንዶች ናቸው።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
በተለያየ የዓለም ክፍል የሚኖሩ እነዚህ አስር ፈላጭ ቆራጮች ወታደራዊ ኃይላቸውን ለመጨረሻው ፖፕ ይሰጣሉ።
ይህ ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ኃይልን በአንድነት አጣምሮ የያዘ ሰው እነዚህን አስር ፈላጭ ቆራጮች ፈጽሞ ሙሉ በሙሉ ስለሚቆጣጠራቸው በአንድነት የእርሱን ራዕይ ተካፍለው ለእርሱ ዓለምን ሁሉ የሚገዛበት ወታደራዊ ኃይል ሆነው ለማገልገል ራሳቸውን ይሰጡታል።
አሜሪካ በዓለም ላይ ችግር ወደ ተፈጠረበት ራቅ ወዳለ ሃገር ጦር ሰራዊቷን ለማንቀሳቀስ ወራት ይፈጅባታል። ነገር ግን በዓለም ላይ በልዩ ልዩ ስፍራ የተቀመጡ አስር ፈላጭ ቆራጮች ሲኖሩ ቀላል ነው። በማንኛውም ሰዓት ችግር ቢፈጠር ከአስሩ መካከል ችግር በተፈጠረበት ቦታ በቅርበት የሚገኘው ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል የተፈጠረውን ነውጥ ጸጥ ለማሰኘት ሊዘምት ይችላል።
ዳንኤል 2፡43 ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶችን ቀላቅለው የሚያስተምሩት ትልልቅ ቤተክርስቲያናዊ ድርጅቶች የቤተክርስቲያን ዓለም ላይ ገዥ ይሆናሉ። ብረጥ ጠንካራ እና ገዥ ነው። ነገር ግን ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አለብን የሚሉ ግለሰቦች (ሸክላዎች) አይታጡም፤ እነዚህ ግለሰቦች ከዲኖሚኔሽናዊ ድርጅቶች ጋር መስማማት አይችሉም። ደግሞም በታላላቆቹ የቤተክርስቲያን ድርጅቶችም ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። ሸክላ እና ብረት በእርግጥ ሊደባለቁ አይችሉም።
መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል የሚፈልጉ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ልማዶች እና አመለካከቶች አይመሰጡም።
1961-0806 የዳንኤል ሰባኛ ሱባኤ
በእርኩሰት ጫፍ ላይ አጥፊው እንደሚመጣ አስተወሉ፤ የእርኩሰት ጫፍ… እርኩሰት ምንድነው? “እድፋምነት።” አያችሁ? ጥፋትስ ምንድነው? “ማፈራረስ፤ ማውደም ነው።” የእርኩሰት ጫፍ ሲደርስ አጥፊው ያጠፋል። አያችሁ? የሮማ ኃይል እንቅልፍ የተኙ ቆነጃጅትን ሁሉ ሊገዛ መምጣቱ፤ አይሁድም ይሁኑ ሌሎች… ሁላችንም ሮማውያን እንሆናለን አለዚያ እንጠፋለን። እርሱም ቃልኪዳኑን በሱባኤው እኩሌታ ያፈርሰዋል።
የእርኩሰት ጫፍ … እርኩሰቱ የመጣው በኢየሱስ ዘመን ሮማውያን ፕሮፓጋንዳቸውን ይዘው በመጡ ጊዜ ከሆነ አሁንም እንደገና ሮማውያን ናቸው የሚሆኑት -- አሁንም በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጸም እርኩሰት ነው የሚሆነው … ጥፋት እስከ ፍጻሜው ድረስ ተቀጥሯል… እርሱ ምንድነው የሚያደርገው? እስከ ፍጻሜው ድረስ ይቀጥለዋል። ያም ፍጻሜው ይሆናል።
ዳንኤል 2፡44 በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ … መንግሥት ያስነሣል፤
የአስሩ ፈላጭ ቆራጮች መነሳት ከጌታ ምጻት በፊት ከምናያቸው የመጨረሻ ምልክቶች መካከል አንዱ ነው።
እንደ ራሺያ፣ ቱርክ፣ እና ኢራን የመሳሰሉ ሃገሮች ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄዳቸው አስገራሚ ነገር ነው፤ ሆኖም ግን እውነታው ከምርጫ በኋላ የሚተዳደሩት በአንድ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ነው። ኢራን የምትመራው በተመረጠው ፕሬዚዳንት ሳይሆን ከሙስሊም የሐይማኖት መሪዎች መካከል ከፍተኛ ስልጣን ላይ በሚቀመጥ ሰው ነው። አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባ ገነን መሪ ፖፑ ነው።
የፈላጭ ቆራጮች እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ ፈላጭ ቆራጮች መነሳት ዘመኑን የሚያሳይ ምልክት ነው።
በዚሁ ጊዜ ቤተክርስቲያን ደግሞ ችግር ውስጥ ናት።
ድንግል ወይም ቆንጆ ማለት የዳኑ ክርስቲያኖችን የምትወክል ንጹህ ሴት ናት።
ማቴዎስ 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
3 ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤
4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
በመጨረሻ ልባሞቹም ሰነፎቹም ክርስቲያኖች እንቅልፍ ይተኛሉ።
ማነው እንቅልፍ የሚያስተኛቸው? የሚያዳምጧቸው ሰባኪዎች ናቸው።
1963-0320 ሶስተኛው ማሕተም
ዛሬ መምጣት የነበረባቸው መነቃቃቶች ለዚህ ነው … ዲኖሚኔሽናዊ መነቃቃቶችን አይተናል፤ እውነተኛ መነቃቃት ግን አላየንም። በፍጹም በጭራሽ። አይተን አናውቅም። መነቃቃት አይተን እናውቃለን እንዳትሉ። አላየንም። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያን አባላት አሏቸው በየቦታው፤ ነገር ግን አንድም ጊዜ የትም ቦታ መነቃቃት ሲሆን አይተው አያውቁም። በፍጹም። ሙሽራይቱ መነቃቃት ሆኖላት አያውቅም። አያችሁ? መነቃቃት ሆኖ አያውቅም፤ ሙሽራይቱን ሊያነቃ የሚችል የእግዚአብሔር ኃይል መገለጥ ሲሆን አይተን አናውቅም። አያችሁ? እስካሁን እየተጠባበቅን ነን። ሙሽራይቱን እንደገና ለማንቃት እነዚያ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ማሰማት አለባቸው። እርሱም ይልካል። ምክንያቱም ቃል ገብቷል። ስለዚህ አሁን ተመልከቱ። አሁን ሞታለች።
ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በዝርዝር ያልተገለጡት ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን የሚያሰሙት ብርቱው መልአክ ቅዱሳንን ከሙታን ካስነሳ በኋላ ነው።
1964-0119 ሻሎም
ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ብቻ ናቸው ለመነጠቅ የሚያስፈልገውን እምነት ከትንሳኤ በኋላ ለሙሽራይቱ መስጠት የሚችሉት። በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሞቱ ቅዱሳን ወደ ሰማይ ተነጥቀው መሄድ የሚችሉት ከሙታን ከተነሱ በኋላ ነው።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
ሙታን እና ሕያዋን በአንድነት ነው የሚነጠቁት። ወደ ሰማይ መነጠቅ ለመነጠቅ የሚሆነው እምነት በተግባር ሲገለጥ ነው። አሁን በዚሁ በሚሞት አካል ውስጥ ሆኖ ለመነጠቅ የሚሆነው እምነት አለኝ ብሎ መናገር ሐሰተኛ ዜና እንደማውራት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
በሕይወቱ የመጨረሻ ወር ላይ እንኳ ወንድም ብራንሐም በራዕይ 6፡1 ውስጥ የተጠቀሰው በጎድጓድ እና ታላቁ ድምጽ (መልእክቱ) እና ድምጹ (ሙታንን የሚያስነሳው የብርቱው መልአክ ድምጽ) እና መለከቱ (ለመነጠቅ ጊዜ የሚነፋው መለከት) ይገለጣሉ ብሎ ሲጠባበቅ ነበር።
1965-1127E
ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ታላቅ ድምጽ የሚለው ወንድም ብራንሐም ከ1947 – 1965 ድረስ መልእክት የሰበከበትን ዓመታት አይደለም። እርሱ ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር ያውቅ ነበር እኛ ግን አላወቅንም። በዚያ ዘመን ብዙዎቻችን ገና አልተወለድንም ነበር።
ታላቁ ድምጽ የሚመጣው ሙሽራዋ ጥቅሶቹን ወስዳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ስታመሳክርና መልእክቱ እውነተኛ መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገናኘት ስታረጋግጥ ነው። የመልእክቱን አስተምሕሮዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ በመስበክ እውነተኛነታቸውን ስናረጋግጥ የዚያን ጊዜ ታላቁ ድምጽ ይመጣል። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው እንጂ የእኛ ቃል አይደለም።
1965-0429
እውነተኛዋ ሙሽራ ቃሉን በመጠበቅ የእግዚአብሔርን ትኩረት ትስባለች።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በከፊል መጽሐፍ ቅዱሳዊ (ትኩስ) በከፊል ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ (ቀዝቀዛ) ይሆናል። ይህ ለብ ያልን እንድንሆን ስለሚያደርገን እግዚአብሔር ይተፋናል።
16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
እግዚአብሔር የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ከአፉ ይተፋታል፤ አፉ ማለት ቃሉ ነው።
ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተቶች አሉበት ይላሉ፤ በትክክል ያልተተረጎሙ ክፍሎች አሉት ይላሉ። ደግሞም ለመረዳት ያስቸገሩዋቸው ከባድ ጥቅሶች ምንም የማይጠቅሙ ዝርዝር ጉዳዮች ናቸው ይላሉ። ይህ የክርስትና እስራት ነው።
ብረት ከሌሎች አተሞች ሁሉ የበለጠ ጠንካራ የመተሳሰር ጉልበት እንዳለው ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሚሰነዝሩበት ማንኛውም ትችት ተመሳሳይ ትችት ኢየሱስ ላይ እየሰነዘሩ ነው።
ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወሰኑ ክፍሎችን አንቀበልም ሲሉ ኢየሱስን እራሱን አንቀበለውም እያሉ ነው።
ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲጠሉ እግዚአብሔርም ቤተክርስቲያኖችን እየጠላቸው ነው።
ዛሬ ተስፋ ያለው ለግለሰቦች ብቻ ነው።
ኢየሱስ ከየቤተክርስቲያኑ ተገፍቶ ወጥቶ በደጅ ቆሞ ውስጥ ላሉ ግለሰቦች ጥሪ እያቀረበ ነው።
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
ዛሬ በአሕዛብ ምስል እግር ውስጥ ያለው ሸክላ የሚወክለው እምነታቸውን ከመጽፍ ቅዱስ መርምረው ማረጋገጥ የሚፈልጉ ግለሰቦችን ነው። እነዚህ ግለሰቦች የጥንቷ ቤተክርስቲያን ማመን ይፈልጋሉ። እውነተኛ ክርስትና ይህ ነው።