ዳንኤል 12፡10 – 13



First published on the 21st of April 2021 — Last updated on the 21st of April 2021

ዳንኤል 12፡10 ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ።

ሶስት ዋና ነጥቦች ተጠቅሰዋል። ያጠራሉ። ያነጣሉ። ይነጥራሉ።

ክፉዎች የትኞቹ እንደሆኑ እንዴት እናውቃን? ክፉዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን የማያስተውሉ ናቸው።

ክፉዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ምን ማለት እንደሆኑ ማብራራት የማይችሉ ሰዎች ናቸው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሲብራሩላቸው እንኳን መረዳት የማይችሉ ሰዎች።

የተቀበሉትን መገለጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሙሉ ተከታትሎ ለማየት ጥቅሶችን ለማገናኘት የሚያስፈልገው ጥበብ የጎደላቸው ሰዎች ናቸው ክፉዎች የተባሉት።

ጥበበኞች “ማወቅ አለብን” ይላሉ።

ክፉዎች ግን “ማወቅ ያስፈልገናል?” ይላሉ።

በስተመጨረሻ አስፈላጊው ነገር ታላላቅ ሥራዎችን መስራት ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለማስተዋል የሚያስፈልግ የማስተዋል ችሎታ ማዳበር ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ሃሳብ ይገልጻል።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡16 እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።

የክርስቶስ ልብ ካለን የእርሱን ሃሳብ መረዳት እንችላለን፤ ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ማስተዋል እንችላለን።

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ምንድነው?

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ከተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እውነትን የማስተዋል ችሎታችን ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የማወቅ ፍላጎት አለን?

አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያብራራልን የመረዳት ችሎታ አለን?

ልብ በሉ። እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ትኩረት የሰጠው ጉዳይ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተዋል ነው።

በመጨረሻው ዘመን ሙሽራይቱ የምትገኝበት ሶስት ሁኔታዎች አሉ።

 

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶቻችንንም ሆነ አመለካከቶቻችንን ከውስጣችን ቀጥቅጠን ማስወጣት አለብን። ወርቅ ሲቀጠቀጥ ነው ከውስጡ ጉድፎች የሚወገዱለት። አንጥረኛው የራሱን መልክ እንደ መስተዋት ወርቅ ውስጥ ማየት እስኪችል ድረስ ቅጥቀጣው ይቀጥላል። ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔርም መንፈሱ በእኛ ውስጥ እስከሚገለጥ ድረስ “እኔነታችንን” ከውስጣችን ይቀጠቅጠዋል። የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያምነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሰበሰብናቸውን የተሳሳቱ እምነቶች እና ልማዶች ሁሉ እርግፍ አድርገን መጣል አለብን።

 

ያነጡማል። ነጭ የጽድቅ ተምሳሌት ነው። ብቸኛው ጽድቃችን እግዚአብሔር ቃል ማመን ነው።

ከዚያ በኋላ ጠለቅ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ትርጉም ከወንድም ብራንሐም ትምሕርቶች ተከታትለን እንደገና መማር ያስፈልገናል። በፊት የነበሩንን የተሳሳቱ መረዳቶች ከአእምሮዋችን አስወግደን በትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መረዳት መተካት አለብን።

ራዕይ 19፡7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።

8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።

ሚስት ለሰርጓ ነጭ ልብስ ነው የምትለብሰው።

ለምን ነጭ? ይህ የእግዚአብሔር ትልቅ እቅድ ሚስጥር ነው።

ነጭ በቀስተ ደመና ውስጥ ያሉ ሰባት ቀለሞች በሙሉ ተደባልቀው አንድ ሲሆኑ የሚገኝ ቀለም ነው።

እግዚአብሔር ሰዎች ማየት የማይችሉት ትልቅ እቅድ አለው። እኛ ጻድቅ የምንሆነው እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ በመስራት ታላቅ እቅዱን በእኛ ሲፈጽም ብቻ ነው እንጂ የራሳችንን ውስን ፈቃድ ስንፈጽም አይደለም።

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ለማጥመቅ ብቁ እንዳልሆነ ገብቶታል።

ስለዚህ ኢየሱስ ለዮሐንስ ስለ ታላቁ እቅድ አስታወሰው።

ማቴዎስ 3፡15 ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።

ኢየሱስ ከመሰዋቱ በፊት መታጠብ የሚገባው የመስዋእቱ በግ ነበረ።

ስለዚህ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ውስጥ የተመደበበት ቦታ የት እንደሆነ ማወቅ አስፈለገው። ከዚያ በኋላ ዮሐንስ የሚያደርገው ነገር ሁሉ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚመደብ ነው። ዮሐንስ ሰዎችን ያጠመቀበት ጥምቀት ሳይቀር ኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚደረገው ጥምቀት ተተክቷል (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)።

ስለዚህ የዮሐንስ ጥምቀት ጊዜያዊ አገልግሎት ነበረ።

ነገር ግን ከአገልግሎቱ ውስጥ ዋነኛውና ትልቁ ሥራው የእግዚአብሔርን በግ ማጠብ ነበረ። ካልታጠበ በቀር ኢየሱስ መስዋእት ሆኖ መቅረብ አይችልም።

2ኛ ዜና 4፡6 ደግሞም አሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።

ኢየሱስ የተናገረው ስለ እውነተኛው ጽድቅ ነው።

ዮሐንስ ንጹህና ጻድቅ ሕይወት ነው የኖረው። ሆኖም ግን የዮሐንስ የግል ጽድቅ የእግዚአብሔርን ታላቅ እቅድ ማስፈጸም አይችልም።

በእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ ውስጥ የተሰጠውን ድርሻ ማወቅ ለዮሐንስ ትክክለኛ ጽድቁ ነው።

ስለ አብራሐም ሲናገር ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

ሮሜ 4፡5 … እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

አብራሐም ብቸኛ ልጁን ይስሐቅን መስዋእት አድርጎ ለማቅረብ ተነሳ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከሙታን እንደሚያስነሳለት አምኖ ነበር።

ስለዚህ የአብራሐም እምነት በእግዚአብሔር ትልቅ እቅድ ውስጥ ነበረ። ይህም እግዚአብሔር ሙታንን ማስነሳት መቻሉ ነው።

“ነጭ” ማለት የእግዚአብሔርን ታላቅ እቅድ ተረድተን እግዚአብሔር እቅዱን ለመፈጸም እኛ በማናውቀውና ባልጠበቅነው መንገድም እንኳ ቢሆን እንዲጠቀምብን እንፈቅደለታለን ማለት ነው።

ሮሜ 1፡17 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።

እያንዳንዱ ዘመን ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተወሰነ የተለየ የእምነት መጠን ተገልጦለታል። ስለዚህ እኛ በትናንትናው ዘመን እቅድ ውስጥ ልንንቀሳቀስ አንችልም።

የወደብ መብራት ጨረሩ በአንድ ቦታ ለብዙ ሰዓት አይቆይም።

በትናንትናው ነፋስ ዛሬ መሄድ የሚችል መርከብ የለም።

ስለዚህ እግዚአብሔር ዛሬ ከተገለጠው ቃሉ ውስጥ ምን እንድናውቅ ነው የሚፈልገው?

ዳንኤል 12፡13 አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ አንተም ታርፋለህ፥ በቀኑም መጨረሻ በዕጣ ክፍልህ ትቆማለህ።

“ዕጣው” እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የመደበለት ድርሻው ነው፤ ክርስቲያኑ በየትኛውም የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ቢኖርም እግዚአብሔር የመደበለት ድርሻ አለው። የምንኖርበትን ዘመን እና ሁኔታ መምረጥ አንችልም። እግዚአብሔር ነው የሚወስንልን። የእኛ ድርሻ እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ እንደሚፈልግ ማወቅ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጠው ዛሬውኑ ማመን ነው። እግዚአብሔር በወሰነልን መንገድ ሥራችንን በመስራት ውጤታማ መሆን ወይም በራሳችን መንገድ ለመስራት ሞክረን ከንቱ ሆነን መቅረት የእኛ ነጻ ምርጫ ነው።

ነጭ ብርሃን ሰባቱ የቀስተደመና ቀለሞች በአንድነት ሲዋሃዱ የሚገኝ ቀለም ነው።

ነጭ ብርሃን የሚገኘው ሰባቱም ቀለማት በአንድነት ሆነው ሲዋሃዱ ነው።

ስለዚህ “ነጭ” የሚለው ቃል ጠለቅ ያለ ወይም ተለቅ ያለ እቅድን ያመለክታል። ይህም ሰባቱን ቀለማት ወይም ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት በታላቅ እቅድ አንድ ያደርጋቸዋል።

በስተመጨረሻ ሙሽራይቱ የሰባቱንም ቤተክርስቲያን ዘመናት በሙሉ መረዳት ባገኘች ጊዜ እና በሰባቱ የቤተክርስቲያንን ዘመናት ውስጥ የነበረሩትን የቤተክርስቲያንን ታሪክ ክስተቶች እንደ ሰንሰለት አያይዛ ጠቅለል ያለ እውቀት ስታገኝ ነጭ ብርሃን ይበራል።

ስለዚህ “ያነጣሉ” የሚለው ቃል ከእኛ በፊት ከነበሩ ስድስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር መዋሃድ አለብን ማለት ነው።

ከዚያም ጋር ተያይዞ የእኛ ድርሻ ወይም ዕጣችን ወደ መጀመሪያው የቤተክስቲያን ዘመን መመለስ መሆኑን ማወቅ ያስፈልገናል።

ዕብራውያን 11፡40 ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።

 

ይነጥሩማል።

ይህ በግላችን የምንፈተነው ፈተና ነው። ትዕቢታችንን ረግጠን ያረጁ እምነቶቻችንን ለመጣል ፈቃደኞች ነን? አዲስ የተገለጡልንን የመጨረሻው ዘመን ነብይ ያመጣልንን የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳቶች ለመቀበል የሚበቃ የእውነት ፍቅር አለን?

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን የሚያመጡብንን ውግዘት ለመቋቋም የሚበቃ ብርታት አለን?

እነዚህ ሶስት እርምጃዎች ሙሽራይቱ ማስተዋል እንድትችል ይረዷታል።

በዘመን መጨረሻ በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ካለችው ሙሽራ ሶስት እርምጃዎች ይጠበቁባታል።

ራዕይ 3፡18 ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።

ከተገለጠው የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የሚመጣ መንፈሳዊ ልብስ።

እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ ለሙሽራይቱ ሲናገር ሶስት ነገሮች እንደሚያስፈልጉልን ገልጧል።

 

“በእሳት የነጠረውን ወርቅ ከእኔ ትገዛ ዘንድ”። የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ሐጥያታችንን ይዞ ወደ ሲኦል ወርዶ ዲያብሎስ ላይ በማራገፉ ብቸኛው በእሳት የተፈተነ ሰው እርሱ ነው።

ግዛ ማለት ዋጋውነ ክፈል ማለት ነው።

ይህም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛው ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ በማመን የተነሳ የሚመጣ የመገፋት እና የመወገዝ ዋጋ መክፈል ነው።

ኢየሱስ ራሱን የሚገልጠው ተሰውረው በነበሩ ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን በተገለጡ ሚስጥራት ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በመረዳት የምንማረው ብቻ ነው ንጹህ እውቀት። በብዙ ዘመናት ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ተፈትኗል፤ እስካሁንም ስለ እያንዳንዱ ዘመን ከመምጣቱ በፊት በትክክል ይተነብያል።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን በሙሉ እንደ ወረደ ማመን መለማመድ አለብን።

የእግዚአብሔር ቃል በእሳት ተፈትኖ አልፏል። ከእግዚአብሔር ቃል የተሻለ አስተማማኝ መሪ የለንም።

ግዛ። ዋጋውን ክፈል። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሐሰት ነው ብለው የሚቃወሙትን እውነት አድርጎ ማመን። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ስሕተት የሌለበት መጽሐፍ ቅዱስ ነው ብለን ማመን አለብን። የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ክርስቶስ አንዳችም ስሕተት የለበትም።

 

ነጭ ልብስ

አሁንም የምናየው የታላቁ እቅድ አካል ስለ መሆን ነው። በዚህ እቅድ ውስጥ የ2,000 ዕድሜ ያላት ቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የተሰጠንን ድርሻ መወጣት አለብን።

ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ አለብን።

 

“እንድታይም ዓይኖችህን እኔ በምሰጥህ ኩል ተኳል”።

እውነትን ፊት ለፊት ለማየት እና የቤተክርስቲያናችንን ፓስተር ለመጋፈጥ ብርታት ያስፈልገናል።

አዲስ ኪዳን ውስጥ የትም ቦታ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ሃላፊ የሆነበት ቃል የለም። ይህ የኒቆላውያን መንፈስ ነው።

ፓስተሩን ልትቃወሙ ብትሞክሩ በገቢ ምንጩ ላይ እንደመጣችሁበት ይቆጥራል። ከዚያ ችግር ውስጥ ትገባላችሁ። ስለዚህ ብርታት ያስፈልጋኋል።

ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ነጋዴዎችን ሰኞ ዕለት ከቤተመቅደስ አባረራቸው፤ እነርሱም ወዲያ ሐሙስ ዕለት ገደሉት።

(ኢየሱስ እሑድ ጠዋት ከሙታን ከመነሳቱ በፊት መቃብር ውስጥ ሶስት ሌሊት እንደሚቆይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ስቅለት አርብ” ነው የሚል ቃል የለም)።

ፓስተሩን ከገንዘቡ በቀላሉ ልትለዩት አትችሉም።

በዚህ ዘመን ሰባኪነት ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሙያ ነው። ጥሪ መሆኑ ቀርቷል።

በመከር ጊዜ የሚታጨደው ፍሬ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት።

 

 

ስለዚህ ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት።

መከር ማለት ፍሬው ከተክሉ ላይ የሚቀጠፍበት ወይም የሚታጨድበት ጊዜ ነው።

“የመከሩ ዝናብ” ወይም “ኋለኛው ዝናብ” የሙሽራይቱ አካላት ሰውነታቸውን የሚለውጡበትን እና ለመነጠቅ የሚያስፈልጋቸውን እምነት የሚቀበሉበትን እውቀት የሚሰጣቸውን ሰባቱን ነጎድጓዶች አስከትሎ ነው የሚመጣው።

ለመነጠቅ የሚያበቃቸውን እምነት ከተቀበሉ በኋላ አዲሱ አካላቸው ከምድር ላይ ተነጥቆ በመሄድ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል እና ከዚህ ዓለም ወጥተው ወደ ዘላለማዊው ዓለም ለመግባት ዝግጁ ይሆናሉ።

አዲሱ የማይሞተው አካላችሁን ከለበሳችሁ በኋላ ከዘመን ውጭ ወጥታችሁ ዘላለም ውስጥ ስለምትገቡ አታረጁም፤ አትሞቱምም ።

 

በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ በትንሳኤው እና በእርገቱ መካከል 40 ቀናት አልፈዋል።

በዳግም ምጻቱም ጊዜ ልክ እንደዚሁ ነው የሚሆነው።

የትምሕርት ዝናብ በ1947 ጀመረ፤ የጀመረው ወንድም ብራንሐም ስብከቶቹን በድምጽ ቀርጾ ሲያስቀምጥ ነው። ይህ የትምሕርት ዝናብ እስከ መጨረሻው ይቀጥላል።

 

 

ነገር ግን በመጨረሻው ወር ማለትም በትንሳኤ እና በመነጠቅ መካከል የሞቱ ቅዱሳን ከመቃብራቸው ከወጡ በኋላ የትምሕርቱ ዝናብ ከኋለኛው ወይም ከመከር ዝናብ ጋር ይደራረባል።

ኤርምያስ 5፡24 በልባቸውም፦ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም።

ሁሉም ነገር በተመደበለት ጊዜ ነው የሚከናወነው።

ኢዩኤል 2፡23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።

የትምሕርቱ ዝናብ እና የመከር ዝናብ የሚደራረቡት ለአንድ ወር ነው።

አሁን በመጠኑ ከወንድም ብራንሐም ስብከቶች ተምረናል። የእርሱ ስብከቶች ጠለቅ ያለ እውነት የያዙ ትምሕርቶች ናቸው፤ ነገር ግን ከትንሳኤ በኋላ ሌላም ተጨማሪ ትምሕርት ይመጣል። በዚያን ጊዜ አዲስ አካል እንዴት እንደምንለብስ ከሰባቱ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች እንማራለን። ደግሞም ከሙታን ተነስተው አዲስ አካል በለበሱ ቅዱሳን ፊት እንሆናለን።

በዚያን ጊዜ ምን ዓይነት ኑሮ እንደምንኖር በምናባችን መሳል እንኳ አንችልም።

የኢየሱስ እናት ማርያም ኢየሱስ ከተነሳ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስታየው ልታውቀው አልቻለችም። አትክልተኛ መስሏለት ነበር። እርሱ መሆኑን ያወቀችው ስሟን በጠራ ጊዜ ነው።

ዮሐንስ 20፡14 ይህንም ብላ ወደ ኋላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ኢየሱስም እንደ ሆነ አላወቀችም።

15 ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው።

16 ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ፦ ረቡኒ አለችው፤ ትርጓሜውም፦ መምህር ሆይ ማለት ነው።

51,0509 ምስክርነት

ኢየሱስ ከሙታን ተነሳ። ምስኪኖቹ ደቀመዛሙርቱ እረኛ እንደሌለው በግ ተበታትነው ነበር… እናቱ መቃብሩ አጠቀብ ቆማ ስታለቅስ ነበር። እዚያው በቆመችበት ሌሊቱ ነግቶ ወፎች በአካባቢው እየበረሩ ነበር። እርሱም “ማርያም” ብሎ ጠራት። እርሷም አወቀችው።

63-0320 ሶስተኛው ማሕተም

ሙሽራይቱ እስካሁን መነቃቃት አላገኘችም። አያችሁ? መነቃቃት አልመጣም፤ ሙሽራይቱን የሚያነቃቃ የእግዚአብሔር መገለጥ እስካሁን አልመጣም። አያችሁ? መነቃቃት እስኪመጣ እየተጠባበቅን ነን። ሙሽራይቱ እንደገና እንድትነቃቃ እነዚያ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች መምጣት አለባቸው። እርሱም ይልካቸዋል። እንደሚልካቸው ተስፋ ሰጥቷል። አሁን ልብ በሉ። ሞታለች።

በአሁኑ ሰዓት ሙሽራይቱ ሞታለች፤ ከባድ እንቅልፍ ተኝታለች።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ድንገተኛ የማንቂያ ድምጽ ሆነው ይመጣሉ።

 

ራዕይ 3፡19 እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።

እግዚአብሔር ሊያስተካክለን ሲፈልግ ይገስጸናል።

ከገሰጸን ከባድ ስሕተት ውስጥ ገብተናል ማለት ነው። ሲገስጸን ፓስተሩ ከሰበከን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ስሕተቶች ውስጥ ስንትና ስንት ስሕተቶችን እንደ ውሃ እየጠጣን እስክንቀበል ድረስ ምን ያህል እንደ ደነዘዝን ይነግረናል።

መጽሐፍ ቅዱስን በሰዎች ንግግር ጥቅስ ስለ መተካታችን ይገስጸናል። የጥንቷ ቤተክርስቲያን እንዲህ አድርጋ አታውቅም።

የሰው ንግግር ጥቅሶችን የእግዚአብሔር ድምጽ ስላልን ይገስጸናል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የትኞቹንም ሐዋርያት የእግዚአብሔር ድምጽ ናቸው አላለችም።

የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

እግዚአብሐየር በቃሉ በኩል ሲጣራ የእግዚአብሔርን ድምጽ በግልጽ ይሰማሉ

… ዛሬ የሚጠራችሁን የእግዚአብሔርን ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስን አድምጡ።

መገሰጽ ማለት እግዚአብሔር የተቀበልናቸውን ስሕተቶች ከእኛ ውስጥ ለማስወገድ ትልቅ ጥረት እያደረገ ነው ማለት ነው።

“ይገርፈዋል”።

የሜሴጅ ተከታዮች ብዙ የተሳሳተ ነገር ያምናሉ። ደህና አድርጎ የሚገርፈን ያስፈልገናል። ከዚያ በኋላ ብዙ ስሕተቶቻችንን ስናይ ልባችን ትሁት ይሆንና ዓይናችን በርቶ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ እናማራለን።

“እንግዲህ ቅና ንሰሐም ግባ”።

ቅና። ይህ ማለት ንሰሐ ለመግባት በጣም መፈለግ አለብን።

ይህ የሚያሳየው ብዙ ስሕተቶቸን ተቀብለን ማመናችንን ነው። ለመንፈሳዊ ጤናችን አደጋ የሆኑ ብዙ የተመረዙ ምግቦችን ስንበላ ቆይተናል።

ሰዎችን መሪ አድርገን ስለመከተላችን ንሰሐ መግባት ያስፈልገናል።

እምነታችንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማረጋገጥ ስላለመቻላችን ንሰሐ መግባት አለብን።

በጣም ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን ስላመንን ንሰሐ መግባት አለብን።

በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የሚሰጡ የተሳሳቱ ትምሕርቶችን ከዚህ በታች ተመልከቱ።

 

ዊልያም ብራንሐም ፍጹሙ፣ ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል ነው። (ሐሰት)

62-1007 የበሩ ቁልፍ

… እኔ ፍጹም እንደሆንኩ ይናገራሉ። እኔ የማላውቀው ነገር እንደሌለ … ኦህ፣ ስለ እኔ የሚናገሩትን አንዳንድ ነገር ብትሰሙ ራሳችሁን ያማችኋል።

 

ዊልያም ብራንሐም የሰው ልጅ ነው። (ሐሰት)

65-0725 በዘመን መጨረሻ ላይ የተቀቡት

“በዚያ በተወሰነው ቀን የሰው ልጅ ይገለጣል።” ራዕይ 10፡1 እስከ 7 እቤታችሁ ስትገቡ አንብቡት፤ “የሰባተኛው መልአክ መልእክት እና የማሕተሞቹ መፈታት።” ይህ ምንድነው? መልአኩ የሰው ልጅ አይደለም፤ ነገር ግን መልእክተኛው የሰውን ልጅ እየገለጠው ነው። አሁን ለይታችሁ ማየት ቻላችሁ? ለእናንተ ከባድ የሚመስላችሁ ይህ ነው፤ አያችሁ። የሰው ልጅ እራሱ ሳይሆን ሰባተኛው መልአክ፤ ሰባተኛው መልእክተኛ ነው የሰው ልጅን ለሕዝብ የሚገልጠው ፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ተመልሶ ዘር ሆኗልና አሁን እንደ በፊቱ በስጋ ዓይን አይታይም።

ወንድም ብራንሐም በትምሕርቱ ኢየሱስ በመጽፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ ባሳየ ጊዜ የሰው ልጅን ከመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ውስጥ እየገለጠ ነበረ።

 

ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰምተዋል። (ሐሰት)

ወንድም ብራንሐም “ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰምተዋል” አላለም።

 

የኢየሱስን አዲስ ስም እናውቃለን። (ሐሰት)

ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤

ማንም ሰው በሐጥያተኛ የስጋ አካል ውስጥ ሆኖ የኢየሱስን አዲስ ስም ሊያውቅ አይችልም። ሁላችንም ሐጥያታችንን ይቅር በሚለን በኢየሱስ ስም ነው የምንደገፈው።

አዲሱ የማይሞተው አካላችሁን ከለበሳችሁ በኋላ ሐጥያት ፈጽሞ አይነካችሁም። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው አዲሱን የኢየሱስ ስም ማወቅ የምትችሉት።

አዲሱ ስም ከተገለጠ በኋላ የኢየሱስን ስም አትጠቀሙትም።

 

ነጎድጓዶቹ ምን እንደተናገሩ እናውቃለን። (ሐሰት)

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

ነው።ሰባት ነጎድጓዶች በተከታታይ ቃላቸውን ተናገሩ … አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት በተከታታይ። ከዚያ የተናገሩትን ሰማያትም ሊጽፉ አልቻሉም፤ የተናገሩትን ሰማያትም ሊያውቁ አልቻሉም፤ በጭራሽ ምክንያቱም ከእነርሱ በኋላ የሚቀጥል ነገር የለም። ከዚያ በኋላ የጸጥታ ጊዜ ነው የሆነው። ይህ ሚስጥር ለመላእክት እንኳ አልተገለጠም። ለምን?

ይህንን ሚስጥር ሰይጣን ቢያገኘው ታላቅ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል። እርሱ አንድ የማያውቀው ነገር አለ። ምንም ነገር በራሱ መተርጎም አይችልም፤ የትኛውንም ስጦታ ኮርጆ ማስመሰል አይችልም (እየተማራችሁ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለው)። ይህንን ሊያውቅ አይችለም። ይህ ሚስጥር ቃሉ ውስጥ እንኳ አልተጻፈም። ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። መላእክትም ሆኑ የትኛውም ፍጥረት አያውቁትም። ቢያውቁና አንድ ነገር ትንፍሽ ብለው ቢናገሩ ሚስጥሩን ሊያባክኑ ይችላሉ፤ ስለዚህ ምንም ባለማወቃቸው የተነሳ ምንም መናገር አይችሉም።

የዚያ ማሕትም አንዱ ሚስጥር፤ ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ምንም እንከን አይወጣላቸውም፤ ምክንያቱም ማንም ስለ ነጎድጓዶቹ ቃል አያውቅም፤ ምክንያቱም ምንም አልተጻፈም። ስለዚህ አሁን የዘመን መጨረሻ ላይ ነን።

 

የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር ወርዷል። (ሐሰት)

64-0119 ሻሎም

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ

ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከአንድ ዓመት በኋላ ስለ መልአኩ መውረድ ገና ወደ ፊት ሊሆን እንዳለ አድርጎ ነበር የሚናገረው።

65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየችህ

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

ከመሞቱ አንድ ወር በፊት እንኳ ሙታንን የሚያስነሳው ብርቱ መልአክ ድምጹ ወደፊት ይመጣል ብሎ እየተጠባበቀ ነበር።

በተጨማሪ ደግሞ ስለ ምንነቱ ምንም የማናውቀው አንድ ነጎድጓድ አለ። ይህም ደግሞ የሚፈጸመው ወደ ፊት ነው።

 

ወንድም ብራንሐም በ1963 የታየው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ስር ቆሞ ነበር። (ሐሰት)

ደመናው ፎቶግራፍ የተነሳው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ደመናው በታየበት ሰዓት ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም።

 

 

ደመናውን የሰሩት 7ቱ መላእክት ደመናው ከታየ ከስምነት ቀናት በኋላ ነው ወደ ሳንሴት ፒክ ከተማ መጥተው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ወንድም ብራንሐምን የጎበኙት። ሳንሴት ፒክ ከፍላግስታፍ በ200 ማይል ርቀት ላይ ነው የሚገኘው። በዚያን ዕለት ሲመጡ ምንም ደመና አልሰሩም።

ደመናው እና የመላእክቱ ጉብኘት ሁለት የተለያዩ ክስተቶች ናቸው።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ደመናው ስር አልቆመም።

 

ክርስቶስ በሳንሴት ተራራ ላይ ወርዷል። (ሐሰት፤ የውሸት ዜና)

 

 

ደመናው ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ለ28 ደቂቃዎች ነው የቆየው።

ደመናው ወደ ሳንሴት ፒክ ከተማ አልመጣም።

ኢየሱስ በበረሃ አይመጣም።

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

ሳንሴት ፒክ ታላቁ የሶኖራ በረሃ ውስጥ ያለ ከተማ ነው።

 

 

ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ሳንሴት ፒክ ሊመጣ አይችልም።

ለሜሴጅ አማኞች ትልቅ ችግር የሚፈጥርባቸው ሁለት ደመናዎች መኖራቸው ነው።

 

 

ጴጥሮስ ከኢዩኤል ጠቅሶ እንዲህ አለ።

የሐዋርያት ሥራ 2፡19 ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤

“የጢስ ጭጋግ” የሚለው ቃል የሚናገረው ከፈነዳ ሮኬት ላይ ስለበነነው ጭስ ነው። ይህም ከትልቁ ደመና ኋላ በ20 ማይል ርቀት ላይ የታየውን ትንሽዬ ደመና የሚገልጽ ቃል ነው።

 

ዳንኤል 12፡11 የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኵሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

የጥፋት እርኩሰትን የሚፈጽመው ሰው ማነው?

ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥

የተቀደሰችው ስፍራ ማለት ቤተመቅደሱ የነበረበት ቦታ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ነበር የሚኖረው።

በ70 ዓ.ም የሮማ መንግስት ወደ ቤተመቅደሱ ውስጥ ገብቶ ቤተመቅደሱን እና ከተማይቱን አፈራረሰ።

የሮማ መንግስት ገዥ ፖንቲፍ የሚባል የማዕረግ መጠሪያ ነበረው፤ ይህም ማዕረግ የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀ ካሕናት ማዕረግ ነው።

በ382 ዓ.ም አካባቢ የምስራቁ የሮማ መንግስት ገዥ ይህንን ማዕረግ ፖፕ ለነበረው ለአጎቱ ለቴዎዶሲየስ ሰጠው። እርሱም የሮም ጳጳስ ሆኖ ሊሾም በፈለገ ጊዜ ሹመቱን ለመያዝ ብሎ ከ300 በላይ የሚሆኑ ተፎካካሪዎቹን ገድሏል።

 

 

ራዕይ 13፡1 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።

የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስማ ማነው? የሚለውን ጥያቄ ቤተክርስቲያኖች መመለስ አይችሉም።

ከዚህም የተነሳ ስላሴ ብለው የሚጠሩት አምላክ ስም የለውም። ይህ ከባድ ችግር ነው።

ራዕይ 13፡3 ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥

የአረማዊው ሮማ መንግስት ማዕከል ሮም ከተማ ውስጥ ካፒቶላይን የተባለው ኮረብታ ነው።

የሮማ መንግስት ከባርቤሪያውያን በደረሰበት ጥቃት ለሞት የሆነ ቁስል ቆሰለና መንግስቱ ፈራረሰ።

በ476 ዓ.ም የሮማ መንግስት በባርቤሪያውያን እጅ ሙሉ በሙሉ ወደመ።

ሮም መጀመሪያ የተመሰረተችባቸው ሰባቱ ኮረብታዎች እነዚህ ናቸው።

 

 

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ፖፑ በባርቤሪያውያን መካከል ንጉስ የመሾም ስልጣን አገኘ፤ ከዚህም የተነሳ በእነርሱ ላይ ያለው ተጽእኖ ጨመረ። የመንግስተ ሰማያትን በር ሊከፍትላቸው የሚችለው ጴጥሮስ ብቻ ነው ብሎ አለ። ጴጥሮስም ደግሞ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍትላቸው ለፖፑ ከታዘዙ እና ፖፑን ከረዱት ብቻ ነው አላቸው።

ስለዚህ ጨካኙ እና ምሕረት የለሹ የአረማዊ ሮም መንፈስ በወደቀችውና በፈራረሰው የሮም ከተማ ላይ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ እንደገና ተነሳ።

ፖፑ ካኤልያን ኮረብታ ላይ ባለው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ማዕከል በሆነው የላተራን ቤተመንግስት ውስጥ ተቀምጦ የሮም ገዥ አጥቶ የነበረውን ስልጣን በሙሉ በተቀዳጀ ጊዜ ለሞት የሆነው ቁስልም ተፈወሰ።

አንድ የታሪክ ምሑር የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ክርስትና የተነሳ አረማዊነት በማለት ይገልጻል።

 

 

ራዕይ 17፡10 ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።

ዩልየስ ቄሳር የሮማ ሪፓብሊክን ያጠፋ የዕድሜ ልክ ፈላጭ ቆራጭ ነበረ። ከዚያ በኋላ ቤተሰቦቹ አውግስጦስ፣ ጢባርዮስ፣ ካሊጉላ፣ እና ክሎዲየስ ነገሱ እና ሞቱ።

በ64 ዓ.ም ሮም ውስጥ ከተነሳው ታላቅ የእሳት አደጋ በኋላ ክሎዲየስ በማደጎ ያሳደገው ኔሮ በነገሰ ጊዜ ለእሳት አደጋው ክርስቲያኖችን ተጠያቂ በማድረግ በክርስቲያኖች ላይ ስደት አስነሳባቸው። ሐዋርያው ዮሐንስ በዚያ ጊዜ ተይዞ በፍጥሞ ደሴት ላይ ታሰረ፤ በዚያም ሆኖ ከፊሉን የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጻፈ።

“አንዱም አለ” የሚለው ኔሮን ነው የሚያመለክተው። ኔሮ በ68 ዓ.ም በሞተ ጊዜ ዮሐንስን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ተፈቱ።

በቄሳር ቤተሰብ ውስጥ የመጨረሻው ሰው ኔሮ ነው።

እስፔይናዊው ጀነራል ጋልባ ዙፋኑን ነጥቆ ይዞ ነበር ግን ከ7 ወራት በኋላ ተገደለ። አረማዊውን የሮማ ግዛት ማስተዳደር ከዚያ በኋላ ከባድ ሆነ። በ200 እና 285 ዓ.ም መካከል 30 ነገስታት ነፈራርቀዋል።

ኋላም ዮሐንስ እንደገና በንጉስ ዲዮክሌቲያን እጅ ታሰረ። ከዚያም የዮሐንስ ራዕይን ጽፎ ጨረሰ።

ኔሮ ክርስቲያኖችን ገደለ። ነገስታቱ አምላክ የሆኑ መስሏቸው አምልኮ ይገባናል አሉ። የመጨረሻው አረማዊ የሮማ ገዥ ዲዮክሌቲያን በጣም ከባድ የሆነ የአስር ዓመት ስደት አስነስቶ መጽሐፍ ቅዱስን ሁሉ ለማጥፋት ሞከረ።

ስምንት አዲስ ስርዓትን የሚያመለክት ቁጥር ነው። ስለዚህ ፖፑ የገዥነትን ስልጣን በወሰደ ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ አዲስ የአረማዊነት ስርዓት አስጀመረ።

ክርስቲያኖችን ገደሉ፤ ራሳቸውን እንደ አምላክ አድርገው ሐጥያትን ይቅር ማለት ጀመሩ። በጨለማው ዘመን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥፋት የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ።

ስለዚህ ፖፖቹ “ከሰባቱ” ውስጥ ነበሩ፤ ክርስቲያኖችን ከሚገድሉት፣ ለገንዘብ ከሚስገበገቡትና አምላክ የሆኑ ይመስል ሊመለኩ ከሚፈልጉት የቄሳር ቤተሰቦች ጋር አንድ ዓይነት ባህርይ አላቸው።

በአመራር ላይ የሮማ መንግስት የነበረው ስጋት ለራሱ አስጨናቂ ነበረ። ብቁ ከሆኑት መሪዎች በኋላ ይወለዱ የነበሩ ልጆች ምናምንቴዎችና የማይረቡ በመሆናቸው ችግሩ እየተባባሰ ሄደ።

ነገር ግን የካቶሊክ ፖፕ ደግሞ ከሮማ መንግስት መውደቅ በኋላ ከሮማ መንግስት ይልቅ ጠንካራ የሆነ የአመራር ስርዓት መሰረተ።

ቄሶች ወይም ካሕናት፣ ጳጳሶች፣ ካርዲናሎች፣ እና ፖፖች ማግባት አይፈቀድላቸውም። ስለዚህ አንድ ፖፕ ሲሞት ካርዲናሎቹ ከመካከላቸው ከፍተኛ ብቃት ያለውን ሰው በፖፑ ቦታ እንዲቀመጥ ይመርጣሉ። ስለዚህ ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ እና እየተበላሸ የሚሄድ ስርወ መንግስት አልተፈጠረም።

ራዕይ 17፡11 የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።

ካቶሊኮች የመጀመሪያው ፖፕ ጴጥሮስ ነበረ ይላሉ። ስለዚህ ካቶሊኮቹ እንሚሉት ከመጀመሪያውም ጀምሮ ቤተክርስቲያን ፖፕ ነበራት።

“የሌለውም” ማለት ፖፑ ይሞታል ማለት ነው።

ራዕይ 17፡9 … አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፣ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ …

“እንዳለ”። አዲስ ፖፕ ይመረጣል።

በምድር ላይ ያልተቋረጠ ረጅም ስርወ መንግስት የካቶሊክ ፖፕ መንግስት ነው።

እነርሱም አንድ ላይ የዘንዶው ጅራት ናቸው።

 

 

የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ስሕተትን ያስገቡ እና ከፕሮቴስታንቶች ዘንድ እውነትን ያጠፉት እነርሱ ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ነገር ሁሉ እርኩሰት ነው።

አጋንንታዊ አሰራር የሚሰለጥነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስፍራዎች ነው።

ሰይጣንን መቆጣጠር የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

 

 

61-1119 ፍጹም ብርታት በፍጹም ድካም ውስጥ

ወንድሜ ሆይ የሲኦል ክዳን ተከፍቷል (እውነቴን ነው።) የአጋንንት ኃይል እንደ እንፋሎት ከብዙ ቦታ እየመጣ ነው። ብዙ ሃገሮችን እየተቆጣጠረ ነው። ፖለቲካው ውስጥ ገብቶ ከውስጥ እስኪያበሰብስ ድረስ ተቆጣጥሮታል። ቤተክርስቲያኖችንም ከዲኖሚኔሽን በቀር ምንም እስከማያውቁ ድረስ ተቆጣጥሯቸዋል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና አሁን ደግሞ ሌሎቹ ቤተክርስቲያኖች ሕዝቡ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል እንዳያዩ አድርገዋቸዋል። ስለዚህ የአጋንንት አሰራር እንደ አዲስ ተስፋፍቷል፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ነግሰዋል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እርኩሰቶች በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተስፋፍተዋል።

ይህን ሐይማኖታዊ የአጋንንት ስራ የሚያንቀሳቅሰው ማነው?

ራዕይ 9፡1 አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

ሰይጣን ከሰማይ ተወርውሮ በሲኦል ወደሚገኘው አስቀያሚ መኖሪያው ወደቀ።

ኢሳይያስ 14፡12 አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ!

ራዕይ 9፡2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።

ጥልቁ ጉድጓድ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለም ማለት ነው። ሰባኪዎች በየጊዜው ለራሳቸው የሚመቻቸውን አዳዲስ ሃሳቦች ያፈልቃሉ። እነዚህ ሃሳቦች በየጊዜው እንደ አደገኛ ቫይረስ ይለዋወጣሉ።

የሲኦል እሳት። የአጉል ፍልስፍና እና በስሕተት የተተረጎሙ የሰው ጥቅሶች ጭስ ፀሃይን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ያጨልማሉ ምክንያቱም ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ትኩረት አይሰጡም (የሜሴጅ ፓስተሮች አሳስተው በተረጎሙት ጥቅስ መሰረት ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን ምርጫ ታሸንፋለች ብለው እንደነበር ልብ በሉ)። ከዚህም የተነሳ አየሩ ይጨልማል። ከአንድ የሜሴጅ ፓስተር ጋር ብትከራከሩ ወይም ሃሳቡን ባትቀበሉ ከሚፈጠረው ንዴት የተነሳ አየሩ እንዴት እንደሚከብድ ወይም እንደሚጨልም ማየት ትችላላችሁ።

ራዕይ 9፡3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።

የአጋንንት አሰራር ተለቋል። ፍጥረታዊ አንበጦች አረንጓዴ ተክሎችን ይበላሉ። እነዚህ አጋንንታዊ አንበጦች ግን መብላት አያስፈልጋቸውም።

ራዕይ 9፡4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።

ይህ አጋንንታዊ ሰራዊት ግን የሚያሰቃየው አእምሮዋቸው ባለበት በግምባራቸው ላይ የመንፈስ ቅዱስ ማሕተም የሌላቸውን ሰዎች ነው። አእምሮዋችን አንጎላችን ነው።

 

 

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት የሚበቃ ብርሃን ያበሩ ዘንድ በቂ ዘይት በመብራታቸው ውስጥ የሚኖራቸው ልባሞቹ ቆነጃጅት ብቻ ናቸው። ከአጋንንት ጥቃት ከብዙ የተሳሳተ ትምሕርቶቻቸው የምንተርፍበት ብቸኛው መከላከያችን መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መረዳት ብቻ ነው።

ስለዚህ እውነትን ያበላሹ እና ወደ ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን አመለካከት የለወጡ እነዚህ አጋንንት ንጉስ አላቸው።

ራዕይ 9፡10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።

ራዕዩ ውስጥ ያለው “ጅራት” እነርሱ የሚናገሩት “ተረት” ወይም ሐሰት ነው።

ተረታቸውን ወይም የሐሰት ትምሕርታቸውን ብታዳምጡ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ትገባላችሁ።

ራዕይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።

አብዶን እና አጶልዮን ትርጉማቸው አጥፊ ነው።

ንጉስ ዘውድ ይጭናል።

ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ የጫነው የመጀመሪያው ፖፕ ክሌመንት 5ኛው ነው፤ እርሱም በ1305 ዓ.ም ነበር ፖፕ ሆኖ የተሾመው።

ዘውዱ ባለሶስት ድርብ ነው፤ ማለትም እርሱ የሰማይ፣ የምድር እና ከምድር በታች አጋንንት የሚኖሩበት የፑርጋቶሪ ንጉስ ነው።

 

 

ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍተው ለፖፑ ለሚታዘዙ ሰዎች ብቻ ነው እያለ ፖፑ ያስተምር ነበር። ይህም ትምሕርት በ1302 ኡናም ሳንክተም የሚል ስም ተሰጥቶስ እንደ ሕግ ተደነገገ። ይህም ትርጉሙ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን የለም ማለት ነው።

ፖፑ ፑርጋቶሪ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ከፑርጋቶሪ እያስወጣ ስለ ሐጥያታቸው እንዲሰቃዩ ማድረግ ይችላል የሚል ትምሕርት መጣ። ስለዚህ ፖፑ ከምድር በታች ፑርጋቶሪ ውስጥ ያሉ አጋንንትን መቆጣጠር ይችላል አሉ።

ይህ ዓይነቱ አጸያፊ ውሸት መጽሐፍ ቅዱሳዊው መዳን ከሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ተፍቆ እንዲጠፋ አደረገ። ከዚህም የተነሳ መዳን የማይገኝ ነገር ሆነ። እነዚህም ጠማማ መሪዎች ማንንም ሰው ማዳን አልቻሉም።

ከስርየት ወረቀቶች ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ሮም ውስጥ ሲስቲን ቻፕል እና የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ሕንጻዎችን ለመገንባት ዋለ።

ከዚያ ወዲያ ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ በፖፑ ቁጥጥር ስር በመውደቃቸው ፑርጋቶሪ ውስጥ ሆነው የሚደረግላቸው የገንዘብ ክፍያም ሆነ በሰማይ የሚኖረው ቅዱስ ጴጥሮስ ምንም ሊያደርጉላቸው አልቻሉም።

የስርየት ወረቀት ለቫቲካን ግንባታ ብዙ ገንዘብ አስገኝቷል፤ ኋላ ግን ቤተክርስቲያን አቆመችው። ፖፕ ጆን ፖል 2ኛው የስርየት ወረቀትን በ2,000 ዓ.ም በፈቃደኝነት ለሚከፍሉ ሰዎች ክፍር አደረገ። ፖፕ ፖል 6ኛው በ1963 ወንድም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች ከገለጠ በኋላ በጭንቅላቱ ላይ ያደርግ የነበረውን ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ መጠቀም አቆመ። የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ ፈረሱ ላይ ተቀምጦ የሚጋልበው የክርስቶስ ተቃዋሚ ዘውድ ተሰጥቶታል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራሷ በዚህ መገለጥ ደንግጣለች።

 

የአይሁዶች ዓመት ርዝመቱ 360 ቀናት ነው።

የአሕዛብ ዓመት ርዝመቱ 365.24 ቀናት ነው።

ስለዚህ 70 የአይሁድ ዓመታት ለእኛ 69 ዓመታት ናቸው።

እኛ የምንከተለው የአሕዛብ ዘመን አቆጣጠር በሮማዊው አምባገነን ገዥ በዩልየስ ቄሳር የተዘጋጀ ነው፤ ከዚያ በኋላ በ1582 በሮማዊው ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው አማካኝነት ማስተካከያ ተደርጎበታል። ስለዚህ የካላንደራችን ዓመታት ሮማውያን ዓመታት ይባለሉ።

እያንዳንዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአይሁድ 70 ከአሕዛብ የሮም ዓመታት በአንድ ዓመት ይቀንሳል።

1,290 / 70 = 80

ስለዚህ በ1,290 ዓመታት ጊዜ ውስጥ እኛ አሕዛቦች የዓመቶቻችን ብዛት ከአይሁዳች በ18 ዓመታት ዝቅ ይላል።

1,290 የአይሁድ ዓመታት = 1,290 – 18 = 1,272 የሮም ዓመታት።

ኢየሱስ በ33 ዓ.ም ሞተ፤ በእርሱ ሞት ቤተመቅደሱ በደሙ ነጻ።

33 + 1,272 = 1,305

ስለዚህ በ1305 የጥፋት እርኩሰት የመጣው ፖፕ ክሌመንት 5ኛው ፖፕ በሆነ ጊዜ እና የፑርጋቶሪ ማለትም አጋንንት ከምድር በታች ለሚኖሩበት ክልል ንጉስ የሆነበትን ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ በጫነ ጊዜ ነው።

በዚህም መንገድ የካቶሊክ ሐይማኖት ሰው በእምነት በእግዚአብሔር ጸጋ የሚድንበትን እውነት ከሰዎች አእምሮ ውስጥ ፈጽሞ አጠፋ።

ይህ በአጋንንት አሰራር ላይ የተመሰረተ ዲኖሚኔሽናዊ ስርዓት በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ጭምር ውስጥ ተሰራጨ።

ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ጠፋ፤ ሰዎችም መጽሐፍ ቅዱስን የመማር ፍላጎታቸው ጠፋ።

በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ የነገሱት የሰው ንግግር ጥቅሶች እና እንደ ስላሴ፣ ክሪስማስ የመሳሰሉ የአሕዛብ ልማዶች ናቸው።

ጥፋቱ እየተስፋፋ ይሄዳል።

በ1870 ዓ.ም ፖፑ የማይሳሳት ፍጹም ሰው ነው ተብሎ ታወጀ።

ዛሬ ደግሞ የሜሴጅ ተከታዮች ወንድም ብራንሐም አይሳሳትም ይላሉ።

ፕሮቴስታንቶች የካቶሊክን ሃሳብ በተቀበሉ ቁጥር ጥፋቱ እየሰፋ ይሄዳል።

 

ዳንኤል 12፡12 የሚታገሥ፥ እስከ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀንም የሚደርስ ምስጉን ነው።

ታላቁ መከራ ለ1,260 ቀናት ነው የሚቆየው፤ ከዚያ በኋላ ሁለቱ ነብያት ይገደላሉ።

ቁጥር 12 የሚናገረው ከ75 ቀናት ወይም ከሁለት ወር ተኩል በኋላ ስለሚመጡ ሰዎች ነው።

ጌታ መንግስቱን እሥራኤል ውስጥ ከመመስረቱ በፊት የተወሰኑ ክስተቶች ይፈጸማሉ።

ለምሳሌ ኢየሱስን የሚቀበሉት 144,000 አይሁዶች ተገድለው ይቀበራሉ።

አምስተኛው ማሕተም ሲፈታ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የተገደሉ አይሁዳዊ ሰማዕታት ይታያሉ። እነርሱም ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ስትነጠቅ ሲያዩ ያሳደዳቸውን የክርስቶስ ተቃዋሚ ስርዓት ወደ ምድር ወርደው ይዋጉት ዘንድ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ ያቀርባሉ።

ራዕይ 6፡9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።

አምስተኛው ማሕተም። አምስት ጸጋን የሚወክል ቁጥር ነው። ስለ እምነታቸው የተገደሉትን አይሁዶች እግዚአብሔር ያድናቸዋል።

እነርሱም በኢየሱስ ምስክር ሳይሆን በራሳቸው ምስክር ነው የሚቆሙት።

ራዕይ 6፡10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።

ክርስቲያኖች የገደሉዋቸውን ሰዎች ይቅር ይላሉ። እነዚህ አይሁዶች ግን በቀል እንዲደረግላቸው ይጠይቃሉ።

ራዕይ 6፡11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።

እነዚህ ሰማዕታት ታላቁ መከራ እስኪጀምር ድረስ እንዲጠብቁ ተነገራቸው።

አይሁዶች የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው። አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔር ሙሽራ ናቸው።

አብረዋቸው አገልጋዮች የሚሆኑት 144,000 አይሁዶች መጀመሪያ በታላቁ መከራ ውስጥ ኢየሱስን ይቀበላሉ፤ ከዚያ በኋላ ይገደላሉ።

ከዚያ በኋላ ጌታ ከሙሽራይቱ ጋር ለአርማጌዶን ጦርነት ወደ ምድር ሲመለስ 144,000ው አይሁዶች ከሙታን ይነሳሉ።

“በኩራት” የሚለው ቃል ትንሳኤን የሚያመለክት ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡20 አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።

ራዕይ 14፡3 በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።

4 ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፥ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።

144,000ዎቹ ለሙሽራይቱ ጥበቃ የሚያደርጉ መንፈሳዊ ጃንደረቦች ናቸው።

ከዚያ በኋላ የአርማጌዶን ጦርነት መደረግ አለበት።

ይህ ሁሉ ጊዜ የሚወስድ ሲሆን በነዚያ 75 ቀናት ውስጥ ነው የሚከናወነው።

በዚያ ጊዜ የሚከናወኑ ሌሎች ክስተቶች በነዚያ 75 ቀናት ውስጥ ሊሆኑ ወይም ላይሆኑ ይችላሉ።

ኢየሱስ ለ1,000 ዓመት በምድር በሚነግስበት ሰዓት ከአርማጌዶን ጦርነት የሚተርፉ አንድ ሶስተኛ የአይሁድ ሕዝቦች የት መኖር እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ የእሥራኤል ድንበሮች ከየት እስከ የት እንደሆኑ መታወቅ አለበት።

አዲሱ ቤተመቅደስ ከአርማጌዶን ጦርነት ለሚተርፉት መሰራት አለበት፤ እነዚህ ሰዎች በዋነኝነት ወንጌሉን ሰምተው የማያውቁ አሕዛቦች ናቸው።

ይህ ቤተመቅደስ ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ በሰዎች ሊሰራ ይችላል ወይም ኢየሱስ በመለኮታዊ ኃይል ይሰራዋል።

 

 

ነገር ግን ሁለቱ ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ ከተገደሉ ከ75 ቀናት በኋላ የሺ ዓመቱ ሰላም ይጀምራል።

ዳንኤል 12፡13 አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ አንተም ታርፋለህ፥ በቀኑም መጨረሻ በዕጣ ክፍልህ ትቆማለህ።

“በዕጣ ክፍልህ”።

እያንዳንዱ ሰው በሆነ ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በወሰነው ዘመን ውስጥ ነው የሚወለደው።

ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው በምድር ለኖረበት ዘመን ተጠያቂ ነው።

እያንዳንዱ ዘመን ለሰዎች የራሱ የሆነ ፈተና ይዞ ነው የሚመጣው።

ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ለሚኖርበት ዘመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈልጎ ማግኘት አለበት።

አሁን እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን ስለ መረዳት ትኩረት እንድንሰጥ በሚፈልግበት በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ነን።

ትልቁ ጠላታችንን መታለል ነው።

ሙሽራይቱ “ማወቅ አለብን” ትላለች።

ሰነፎቹ ወይም የተታለሉት ቆነጃጅት ግን “ማወቅ አለብን ወይ?” ይላሉ።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23