ገና / ክሪስማስ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
“ክሪስማስ” የሚለው ቃል እና ዲሴምበር 25 የሚለው ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጠቀሱም፡፡ የዚህ በዓል አመጣጥ እና ታሪክ ውስጥ ምን ያህሉ ከሰዎች ወግ እና ልማድ የመነጨ እና እርባና ቢስ ሊሆን ይችላል? ምን ያህሉስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ እና ሊታመን የሚገባው ነው?
ክሪስማስ በሰዎች ልብ ውስጥ ጥልቅ ስሜት ይቀሰቅሳል፡፡ በብዙዎችም ዘንድ የተቀደሰ ወቅት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሌሎች ደግሞ የመጠጥ ፌሽታ እና የስካር ወቅት አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የቤተሰብ ግንኙነትን የሚያጠናክርና የደስታ ጊዜ ቢሆንም፤ በመንገዶቻችን ላይ በሚደርሱ አደጋዎች ምከንያት ከባድ ሐዘን የሚፈጠርበት ወቅትም ነው፡፡ ወቅቱ ሰዎች ስጦታን የሚለዋወጡበት፤ ብዙ ገንዘብ የሚያወጡበት እንደመሆኑ በዓመቱ ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ሲሆን፤ ይህንን ወቅት ተከትሎ ከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ የሚፈጠርበት የጃንዋሪ ወር ይመጣል፡፡ ብዙ ሰዎች በክሪስማስ ስጦታ ላይ ከመጠን ያለፈ ገንዘብ የማውጣት ግዴታ ያለባቸው ይመስላቸዋል፡፡
ሕዝቡ በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እጦት እና በብዙ የባዕድ እምነቶች አፈታሪክ የተተበተበ ከመሆኑ የተነሳ ይህንን ድርብ የስሜት መጋረጃ መግፈፍ ቀላል ሥራ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ከተከተሉት ልማድ ውስጥ የትኛው በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የተመሰረተ የትኛው ደግሞ በሰዎች ብልሃት የተፈጠረ ተረት መሆኑን እንመልከት።
የምንድነው እግዚአብሔር ምን ማመን እንዳለብን በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል የነገረንን ስንከተል ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ የተመሰረቱ እምነቶች በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም፤ በብዙ ሰዎች ቤት ውስጥም ከመጻሕፍት ሁሉ የማይነበብ መጽሐፍ ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ሐይማኖት ማለት ሰው በራሱ መንገዶች እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚሞክርበት ሥርዓት ነው፡፡ ሰዎች ደግሞ በብዛት እነዚህን ሰው ሰራሽ ልማዶች በጣም ከመውደዳቸው የተነሳ ሐይማኖት እውነትን ተክቶ፤ የግል ልምምዶች የእግዚአብሔርን ቃል ቦታ ነጥቀው ቆይተዋል። ስለዚህ እውነትን ፍለጋ ተነስተናል።
ኢየሱስ የተወለደበት ትክክለኛ ዓመት አጨቃጫቂ ነው፤ የተለያዩ የታሪክ ጸሐፊዎች በ7 ዓመተ ዓለም እና በ1 ዓመተ ምሕረት መካከል ባሉት ዓመታት ውስጥ ነው ይላሉ። ብዙዎቹ በ4 ዓመተ ዓለም ነው ብለው ይስማሉ። ስለዚህ ኢየሱስ የተወለደበት ዓመቱ ራሱ አጨቃጫቂ ከመሆኑ አንጻር ቀኑን የመወሰኑ ጉዳይ ደግሞ ምን ያህል ግምት እንደሚበዛበት ማሰብ አያቅተንም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን የልደት ቀን የማይጠቅስ ከሆነ እኛ መገመት አለብን ወይ?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእግዚአብሔር የሚያምን አንድ ሰው እንኳ የራሱን ልደት ካላከበረ የክርስቶስን የልደት ቀን በማክበር ለእግዚአብሔር ውለታ ልንሰራለት እየሞከርን ነውን? መዳን ከእግዚአብሔር ሲሆን በቃሉ በማመን እንዴት መዳን እንደምንችል ሊያስተምረን ከላይ ወርዷል፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ለማስደሰት ብሎ የራሱን ስርዓቶች እና ወጎች በመፍጠር በራሱ ትህትና ሲመላለስ ሐይማኖት ይወለዳል። በጣም የሚያሳዝነው ግን ሐይማኖት ውስጥ መዳን የለም፡፡ እግዚአብሔር በሰዎች አስተሳሰብ አይደነቅም፡፡
“ክሪስማስ” (Christ’s Mass) የሚለው ቃል Cristemasse ከሞለው የሚድል ኢንግሊሽ ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል ደግሞ Crīstesmæsse ከሚል ኦልድ ኢንግሊሽ ቃል ነው የመጣው፤ ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሁፍ ውስጥ የተገኘው በ1038 ዓ.ም. ነበር።
ስለዚህ “ክሪስማስ” የሚለው ቃል ከ1038 ዓ.ም. በፊት ጽሁፍ ውስጥ አልተገኘም፡፡ ከዚያ ዓመትም በፊት “ክሪስማስ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሎ ይሆናል ግን ጥቅም ላይ መዋሉን የሚያረጋግጥ ሰነድ የለም፡፡ “ክራይስትስ-ማስ” የሚለው ቃል እራሱ በዓሉ የሮማ ካቶሊክ በዓል መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡
ፕሮቴስታንቶች “ማስ” ተብለው የሚጠሩ የካቶሊክ የቅዳሴ ሥርዓቶችን በሙሉ አይቀበሉም፡፡ ክሪስማስን ብቻ ግን ተቀብለዋል። ለምን?
ይሁዳ 1፡3 …ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
አሁን እኛ በምንኖርበት የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ትክክለኛውን አቅጣጫ ማግኘት የሚቻለው ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ኢየሱስ ራሱ ያስተማራቸውና የእውነትን ቃል በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት የጻፉት ሐዋርያት ወዳስተማሩት ትምሕርት ስንመለስ ብቻ ነው፡፡ የአረማውያንን ባህል የምንከተል ከሆነ አቅጣጫችንን እንስታለን፤ ምክንያቱም እነርሱ የሚያምኑት ነገር ሁሉ አንዳችም ዘላለማዊ ፋይዳ የለውም፡፡ “ክሪስማስ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዴም እንኳ አልተጠቀሰም፤ እንዲሁም የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን አላመነችበትም፡፡ ዲሴምበር 25 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እውቅና የተሰጠው ቀን አይደለም፡፡
ገላትያ 4፡9 …እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ?
10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
ሐዋርያው ጳውሎስ ከዓመቱ ውስጥ ለአንድ ቀን የተለየ ቲፎዞ አልነበረም፡፡
ክሪስማስ ወይም የገና በዓል በዘመናት ውስጥ ከተለያዩ ባህሎች የተለያዩ ሃሳቦች እየተዋሰ የመጣ ወግ ነው፡፡ ክሪስማስ ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰቡ ልዩ ልዩ ሃሳቦች ጥርቅም ነው፡፡ በዚህ ልማድ ላይ የተደረጉ የቅርብ ጊዜ ጭማሪዎችን እንመልከት፡፡
http://www.reindeerland.org/santa-claus/history-of-santa-claus.htm
የሳንታ ክሎስ አጀማመርና ታሪክ - የሳንታ ክሎስ ስም አመጣጥ
“የሳንታ ክሎስ ታሪከ የሚጀምረው ከበርካታ መቶ ዓመታት በፊት ነው፡፡ የሳንታ ክሎስ ታሪክ የሚጀምረው ኒኮላስ በተባለውና በኋላም ሴንት ኒኮላስ ወይም ቅዱስ ኒኮላስ የሕፃናት ጠባቂ በተባለው ሰው ነው፡፡ የሲንተርክላስ ወይም ሴይንት ኒኮላስ (ቅዱስ ኒኮላስ) ክብረ በዓል ደቾች በዲሴምበር 6 ይከበራል፡፡ በዓሉ ዋዜማ (ዲሴምበር 5) ሰዎች ስጦታ በመለዋወጥ ሲንተርክላስን ያከብራሉ፡፡ የዋዜማ ምሽት “ሲንተርክላስቮንድ” (sinterklaasavond) የሚባል ሲሆን የሚከበረውም በተለይ ለልጆች ተብሎ ነው፡፡ አሜሪካ ውስጥ ሲንተርክላስ ሚለው ስም ተለውጦ ሳንታ ክሎስ ሆነ፡፡”
ሳንታ በዲሴምበር 5 ለልጆች ስጦታዎችን ይሰጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህንን ሐሳብ እጅግ ከመውደዳቸን የተነሳ አፍነን ወስደነው ወደዲሴምበር 24 ምሽት ወደ ክሪስማስ ዋዜማ አመጣነው፤ ይህም የመጀመሪያ ትክክለኛ ቀኑ አልነበረም፡፡
ሳንታ በመጀመሪያ ለልጆች ስጦታ የሚሰጥና ሰው ነበር እንጂ ከኢየሱስ ልደት ጋር ምንም የሚያዛምደው ነገር አልነበረም፡፡
የሳንታ ክሎስ አጀማመርና ታሪክ - ሲንተርክላስ ወይም ሲንተር ክላስ
“ከደቾች ሲንተርክላስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ዘመናዊ ባህሎችና ታሪኮች ‘Sint Nicolaas en zijn knecht’ (Saint Nicholas and his helper) በሚል ርዕስ በ1850 ዓ.ም. ጃን ሼንክማን (1806-1863) የባለ የልጆችን መጽሐፍ ይጽፍ የነበረ አስተማሪ ከጻፈው መጽሐፍ የመነጩ ናቸው። ይህ መጽሐፍ ነው ሲንተርክላስ ከቤቶች ጣሪያ በላይ እየጋለበ በጭስ ማውጫ በኩል ስጦታዎችን እየጣለ ያልፋል የሚለውን ሃሳብ ያስተዋወቀው፡፡”
ኒኮላስ በእውነትም የነበረ ሰው እና ለተወሰኑ ልጆች ስጦታ ያበረክት የነበረ ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚበሩ አጋዘኖችን በመጋለብ በጣሪያ ላይ መብረርና በጭስ ማውጫ ውስጥ ወደ ላይና ወደታች መመላለሱ ታሪኩ እንዴት በሰዎች ልቦና ውስጥ በፈጠራ እና በማጣፈጫዎች ቅርጹ እንደተለወጠ ያሳያል፡፡ ለልጆች ስጦታ መስጠትን የሚቃወም ማንም የለም፡፡ ስለዚህ ክሪስማስ ለሕጻናት ካለን ፍቅር ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ስለሆነ ሰዎች በቀላሉ የሚላቀቁት በዓል አይደለም። ታዲያ እውነቱን የምናረጋግጠው እንዴት ነው? ስሜታችንን እና ልማዶቻችንን ወይስ መጽሐፍ ቅዱስን በመከተል?
ሴንት ኒኮላስ የሚለው ስም ደስ ሊል ይችላል፡፡ ሰውየው ለልጆች ስጦታ ያበረከተ ነበር፡፡ በበበረት ውስጥ በግርግም ተኝቶ ለነበረው ለሕጻኑ ኢየሱስ ስጦታ ከሰጡት ሰብዓ ሰገል ጋር አይመሳሰልምን? በመሆኑም ሰዎች ይህንን ለልጆች ስጦታ የመስጠትን ልማድ የክሪስማስ አካል አድርገውታል፡፡ ከልጆችም አልፎለቤተሰብ አባላት፣ ለጓደኞች፣ ለስራ ሸሪኮችና ለደንበኞች ወዘተ ስጦታ መስጠትም ተጀመረ፡፡
ግን ቆይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ እኮ በማቴዎስ ምዕራፍ 2 ቁጥር 11 ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ገቡ እንጂ ወደ በረት ውስጥ ገቡ አይልም፡፡ ስለዚህ ሰብዓ ሰገል ኢየሱስ በተወለደበት ሰዓት አልተገኙም፡፡
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ይህ የሆነው ኢየሱስ ተወልዶ ሁለት ዓመታት ያህል ካለፉት በኋላ ነው፡፡ በመጡ ሰዓት ዮሴፍ እንኳ አልነበረም፡፡
ይህ እውነት ቢታወቅ ደግሞ በገና/በክሪስማስ ሰሞን ለሚጧጧፈው ንግድ ያሰጋል፡፡ በልደቱ ቀን ምንም ዓይነት ስጦታ አልነበረም፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሁለት ዓመታት ካለፉ በኋላ ሲሆን በወቅቱ እርሱ ሕፃን አልነበረም። (ሄሮድስ ለዚህ ነው ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ያስገደለው)፡፡
የንግዱ ዓለም ሰዎች በክሪስማስ ወቅት ከሚያወጡት ወጪ ትልቅ ድጎማ ያገኛል። በዚህ ዘመን ሰዎች የሚያመልኩት አምላክ ገንዘብ በመሆኑ ትልልቅ ንግድ የሚጧጧፍበትን ወቅት ለመቃወም አንደፍርም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ ሲገቡ የሚያሳዩ የገና ካርዶችን ሁልጊዜ ያሳትማሉ፡፡ ኢየሱስ የተወለደበትን ወቅት የሚያሳዩ ትወናዎች ውስጥ ሁልጊዜ እረኞች በበረት ውስጥ ይገኛሉ (ይህ ትክክል ነው) ደግሞም ሦስት ሰብዓ ሰገልም አብረው በረት ውስጥ ይታያሉ (ይህ ግን እውነት አይደለም)፡፡ የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን እውነቱና ሐሰቱ ተደበላልቆባታል፡፡ ስህተት ለረጅም ጊዜ ሲደጋገም ሰዎች ቆይተው እንደ እውነት ያምኑታል፡፡
“ዓመታት አለፉና በ1931 ዓ.ም ሃደን ኤች. ሳንድብሎም የተባለ ሰዓሊ ለኮካ ኮላ ድርጅት ተቀጥሮ መስራት ጀመረ፡፡ ከ1931-1964 ድረስ ይህ ሰው በያመቱ በክሪስማስ (ገና) ወቅት ቀይ ኮት የለበሰ የሳንታ ምስል እየሳለ ለኮካ ኮላ የገና ማስታወቂያ ዘመቻ ሲጠቀምበት ቆየ፡፡ እነዚህ ሃደን ኤች. ሳንድብሎም የሚስላቸው የሳንታ ስዕሎች ከጓደኞቹ መካከል ድምቡሽቡሽ ፊት ያለውን ሰው ፊት ምስል በመጠቀም የክሪስማስና የደስታና የፌሽታ መንፈስ በስዕሎቹ ውስጥ ለማሳየት ችለዋል፡፡ ምስሎቹ የሕዝቡን ቀልብ በመግዛታቸው የሳንታ ክሎስ ታሪክ ላይ ሊጨመሩ በቅተዋል፡፡
ከአፈ ታሪክ እንደምንሰማው የደቹ ሲንተርክላስ አረንጓዴ ጃኬት ይለብስ ነበር፡፡ ስሙ ወደ ሳንታ ክሎስ ተለወጠና ጃኬቱም ከአረንጓዴ ወደ ቀይ ተቀየረ፡፡
የኮካ ቆርቆሮዎች የንግድ መለያቸው ደማቅ ቀይ በመሆኑ የኮካላ ካምፓኒ የሳንታ ክሎስ ጃኬት ቀይ እንዲሆን አዘዘ፡፡
ስለዚህ አሁን ኮካኮላ በእምነታችን ውስጥ የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ ይሁዳ በመልእክቱ “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት” እንድንጋደል ከሰጠን ምክር ምን ያህል ርቀን እንደሄድን እናንተው አስቡ፡፡
የክሪስማስ ካርዶች ለመጀመሪያ ጊዜ የታተሙት በ1843 እንግሊዝ ውስጥ ሲሆን እያንዳንዳቸው የ1 ሽልንግ ዋጋ ነበራቸው፡፡ ያን ጊዜ ሽያጭ ላይ አክስረዋቸው ነበር፡፡ በ1860 በብዛት ሲታተሙ የማሳተሚያ ወጭ መበቀነሱ ንግዱ እያደገ ሊመጣ ችሏል፡፡ በ2012 ዓ.ም. እንግሊዝ ውስጥ የተሸጡት 900 ሚሊዮን የክሪስማስ 364 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ገቢ አስገኝተዋል፡፡ እንግዲህ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ እንግሊዝ የክሪስማስ ካርድ ስጦታዎችንና የደረቁ ፍራፍሬዎችን ሽያጭ ንግድ አስተዋወቀች (የደረቁ ፍራፍሬዎች የሚሸጡት በጊዜው ፍሪጅ ስላልነበረ ነው፡፡)
የንግስት ቪክቶሪያ ባለቤት ልዑል አልበርት ዘመናዊውን የክሪስማስ በዓል አከባበር ባህል ከጀርመኒ ነው ወደ እንግሊዝ ይዞ የመጣው፡፡ እንግሊዞችም ንግስቲቱ ከባሏ የተቀበለችውን ልማድ ወዲያ በጉጉት ተከትለውታል፡፡ በ1848 Illustrated London News የተባለ ጋዜጣ ንጉሳውያን ቤተሰቡ ቪክቶሪያና አልበርት ከልጆቻቸው ጋር በጥድ ዛፍ ዙሪያ ቆመው የሚያሳየውን ምስል አተመ፡፡ ከዚያ በኋላም ወዲያው የገና ዛፍ ክሪስማስ በዓል በተከበረ ቁጥር የግድ አስፈላጊ የሆነ የበዓሉ አካል ሆኖ ቀረ፡፡ በ2013 ብቻ እንግሊዝ ውስጥ 6 ሚሊዮን የገና ዛፎች ተሽጠዋል፡፡
የገና ብስኩቶች የለንደን ጣፋጭ ምግቦች አምራች በነበረው ቶም ስሚዝ በ1847 ተፈጠሩ፡፡ በ2013 ስዋንቴክስ የተባለ የእንግሊዝ ካምፓኒ 25 ሚሊዮን ብስኩቶች ሸጠ።
በ1850 የእንግሊዝ ግዛት የዓለምን አንድ አራተኛ የሚሆን ክፍል ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ በመሆኑም ንግስት ቪክቶሪያ የተቀበለችሁ የክሪስማስ አከባበር ልማድ ወዲያ በዓለም ዙሪያ ተስፋፋ፤ በተለይም ደግሞ በዓሉ ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ የንግድ እድልን ይዞ ከመምጣቱ ጋር አንጻር በታላቅ ፍጥነት ሊሰራጭ ችሏል፡፡
ንግስቲቱ ለክሪስማስ ልማዶች ያሳየችው ፍቅር በመላው የእንግሊዝ ግዛቶች ሕዝቡ ውስጥ ለክሪስማስ ያላቸው ቦታ እንደገና እንዲያንሰራራ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከእንግሊዝ ግዛቶችም አልፎ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ተስፋፋ፡፡ ሌላው ቀርቶ ሙስሊሞችና ሂንዱዎች እንኳን ሳይቀሩ ክሪስማስን አክብረው እንደሚያውቁ ይታወቃል፡፡
“ክሪስማስ”መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡ ዲሴምበር 25ም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡
ክርስቲያኖች የዲሴምበር 25ን ቀን ከየት አመጡት?
ክርስቲያኖች እንዲህ አይነት ግምቶችን የጀመሩት በ220 ዓ.ም. ነው፡፡
ግምት 1፡- መንፈስ ቅዱስ በማርያም ላይ የጸለለው በዲሴምበር 25 ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ ግን አትጠይቁ፤ ምክንያቱም የለም፡፡ ነገር ግን ያ ዕለት ቀኑ እና ሌሊቱ ርዝማኔያቸው እኩል 12 ሰዓት የሚሆንበት የስፕሪንግ ኤክዊኖክስነበር፡፡ እንደነርሱ አመለካከት እግዚአብሔር እኩል ሰዓታት ያላቸው ቀናትና ምሽቶች ስለሚያስደንቁት (ለምን እንደሆነ አላውቅም) በዚያን ቀን ያሰበውን ሥራ አከናወነ፡፡
ግምት 2፡- እርግዝናዋ ዘጠኝ ወር እቅጩን ነው የፈጀው፤ በመሆኑም ኢየሱስ ዲሴምበር 25 እለት ተወለደ፡፡
ይህ ምንም ማስረጃ የሌለው ግምት ነው፡፡ እነዚህን መሰረት የሌላቸውን ግምቶች ዛሬ ክርስቲያኖች “እምነት” ይሏቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሌለ የዚህ ዘመን ክርስቲያኖች ያምኑታል፡፡ ብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ነገር ለምሳሌ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ መግባታቸውን አይነት ነገር እንዲያምኑ አትጠይቋቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ ገቡ አይልም፤ ስለዚህ ክርስቲያኖች ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ እንደገቡ ለማመን ምንም ችግር የለባቸውም፡፡ ወይ ግሩም።
እስቲ ቀኖቹን እንደምራቸው፡፡ ዘመናዊ ሕክምና እንደሚለው እርግዝና የሚቆየው ከመጨረሻው የወር አበባ መጀመሪያ አንስቶ ለ40 ሳምንታት ወይም ከፅንስ ከተቋጠረበት ቀን አንስቶ ለ38 ሳምንትታት ነው፡፡
38 x 7 = 266 ቀናት (አብዛኛውን ጊዜ እስከ 270 ቀናት ይራዘማል)፡፡
አሁን ከማርች 25 ጀምሮ እስከ ዲሴምበር 25 ያሉትን ቀናት እንደምር፡፡
7 + 30 + 31 + 30 + 31 + 31 + 30 + 31 + 30 + 25 = 276
ማርች ሜይ ጁላይ ሴፕቴምበር ኖቬምበር
በዘመናዊ አቆጣጠር እርግዝናዋ ከ6 እስከ 10 ቀናት ያህል ከመውለጃ ቀኗ ዘግይቷል፡፡
የእርግዝናን ርዝመት በትክክል ማወቅ አይቻልም ምክንያቱም ሁሌ በጥቂት ቀናት ከፍ ዝቅ ይላል፡፡ ትክክለኛው የኢየሱስ ልደት ቀን ለመወሰን ይህንን ዘዴ መጠቀም ጠቃሚ ወይም ትክክለኛ መልስ ሊሰጠን አይችልም፡፡ በተለይ ደግሞ ጽንሱ የተከሰተበትን ቀን ስለማናውቅ፡፡
ስለዚህ ሁለት ግምቶች ተባብረው ትልቅ የእምነት እርምጃ ይሆናሉ! ቀኑ ዲሴምበር 25 መሆን አለበት፡፡ ብዙም አያሳምንም አይደል?
ነገር ግን ይህ በግምት ከተቀመጡ በርካታ ቀናት አንዱ ሲሆን በወቅቱ ዲሴምበር 25 ወዲያው ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡ የአሌክሳንድሪያ ጳጳስ ክሌመንት ቀኑን አስልቶ ኖቬምበር 18 ነው ብሎ ነበር፡፡ ሌላ በ243 ዓ.ም. ማን እንደጻፈው የማይታወቅ ሰነድ ቀኑን ማርች 28 አድርጎታል፡፡ ፊትዝሜየር ደግሞ ቀኑ ዲሴምበር 11 ነው ብሎ ገምቷል፤ ወዘተ…
በ380 ዓ.ም. አንጾኪያ ውስጥ የነበረው ታዋቂ ሰባኪ ክራይሶስቶም ደግሞ የክርስቶስ የልደት ቀን ዲሴምበር 25 መሆኑን ብቻ እንደሰማ ይኸውም ከ10 ዓመታት በፊት (በ370 ዓ.ም) ተነግሮት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ክራይሶስቶም በ398 የኮንስታንቲኖፕል ጳጳስ ሆኖ ከተሸመ በኋላ እዚያ ሄዶ ክሪስማስን አክብሯል፡፡
ዌይሰር እንዳለው “ሮም ውስጥ ትክክለኛው የክርስቶስ ልደት ቀን እንደማይታወቅ በግልጽ የተነገረ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተለያዩ ቀኖች የልደት ቀኑ ተብለው ይቆጠሩ ነበር”፡፡
(F. Weiser, Handbook of Christian Feasts and Customs – New York: Harcourt, Brace, and Company, 1958, 61.).
ከ200 ዓ.ም. በኋላ የኢየሱስን የልደት ቀን የሚጠቁሙ ግምቶች መምጣት ጀመሩ፡፡ ምሁሩ ሉፒ የክርስቶስ ልደት በዚህ ወር ነው ብለው ሊቃውንት ከዓመቱ ወራት ውስጥ ያልጠቀሱት ወር እንደሌለ አሳይቷል
(Zaccaria, Dissertazioni ecc. del p. A.M. Lupi, Faenza, 1785, p. 219)፡፡
በቀደሙትና ክርስቲያን ጸሃፊዎች ለምሳሌ አይሬኒየስ (130-200) ወይም ተርቱሊያን (160-225) ጽሑፎች ውስጥ የልደት በዓልን ስለማክበር አንዴም እንኳ አልተጠቀሰም፡፡ የአሌክሳንድሪያው ኦሪጌን (165-264) በሮማውያን የልደት በዓል የማክበር ልማድ ላይ “የአረማውያን ልማድ” እያለ ይሳለቅ የነበረ ሲሆን፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሁለት ሰዎች ልደት ብቻ መጠቀሱን ያውታውሳል፤ እነርሱም ሄሮድስ እና ፈርኦን ናቸው፤ ሁለቱም ደግሞ በልደት ቀናቸው ግድያ ፈጽመዋል፡፡
ክሪስማስ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ይከበሩ ከነበሩ በዓላት አንዱ ስላልነበረ አይኒየስ እና ተርቱሊያን ከበዓላት ዝርዝሮቻቸው ውሰጥ አልመዘገቡትም፡፡ ኦሪጌን ነገስታት ልደታቸውን ማክበራቸውን በማየት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልደታቸውን የማክበር ልማድ የነበራቸው ጻድቃን ሳይሆኑ ኃጢአተኞች መሆናቸውን በአጽንኦት ይገልጻል (in Lev. Hom. viii in Migne, P.G., XII, 495)፤ አርኖቢየስም (VII, 32 in P.L., V, 1264) በአማልክት የልደት በዓላት ላይ ይሳለቃል…
የዲሴምበር 25 በዓል ወደ ግብፅ የደረሰው በ427 እና 433 ዓ.ም መካከል ነው፡፡
ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔዲያ
የካቶሊክ ኢንሳይክሎፔዲያ በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ በክሪስማስ የማያምኑ ታላላቅ ክርስቲያን መሪዎችን ይዘረዝራል፡፡ እነዚህ ሰዎች የኖሩት ከ130 እስከ 254 ዓ.ም ነው፡፡
የክርስቶስ ልደት ለመጀመሪያ ጊዜ ሮም ውስጥ በዲሴምበር 25 መከበሩ የተመዘገበው በ354 ዓ.ም. በተጻፈው ክሮኖግራፊ ነው (በፊሎካሊያን ካላንደር በ354)፤ ይህም ክሮኖግራፊ ዲሴምበር 25 የማይሸነፈው ፀሐይ እና የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን እንደሆነ ይጠቅሳል፡፡ ይህን መረጃ የያዘው ሰነድ በ336 አካባቢ በነበረ ካላንደር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
(Herman Wegman, Christian Worship in East and West, New York: Pueblo Publishing, 1985, 103).
ክሮኖግራፊው በዓመቱ ውስጥ በዓል የሚከበርላቸውን የተለያዩ ሰማዕታትን የበዓል ቀን መዝግቦ የያዘ የሮማ ቤተክርስቲያን ሰነድ ነው፡፡
የሮም ጳጳስ ዩልየስ በ350 ዓ.ም. አካባቢ ዲሴምበር 25ን ተቀበለ ምክንያቱም ይህ ቀን አረማውያን የአምላካቸውን ልደት የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ ልደት ማክበር ለክርስቲያኖች ሌላ አማራጭ በዓል ከመስጠቱም በላይ የአረማውያንን የፀሐይ አምላክ በዓል ከማክበር እንዲታቀቡ ያደርጋቸዋል፡፡ ዛሬ ብዙ ሙስሊሞች እና ሒንዱዎች ክሪስማስን ያከብራሉ ምክንያቱም ሐይማኖታቸው በዲሴምበር 25 ዕለት ሌላ አማራጭ በአል ስለማያቀርብላቸው ነው፡፡
ከ200 ዓ.ም. ጀምሮ ብዙ የተለያዩ ቀናት የክርስቶስ ልደት ቀን እንዲሆኑ ቢታሰብም በቀጣዮቹ 100 ዓመታት ውስጥ ቀስ በቀስ ዲሴምበር 25 የበለጠ ተቀባይነትን ቢያገኝም ጀጃንዋሪ 6ም ሌላ ተቀናቃኝ ቀን ነበር፡፡ በወቅቱ ያስፈልግ የነበረው ሁሉ አንድን ቀን እንዲቀበሉ የማስገደድ ማዕከላዊ ስልጣን ያላት ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡ አብያት ክርስቲያናት ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ቀን ይፋዊ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ አድርጎ ሊያጸድቅ የሚችል የሰው መሪ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ በመሆኑም የሮማው ጳጳስ ዩሊየስ ይህንን ቀን የማጽደቁን ሂደት ጀመረው፡፡
ክሪስማስን በትክክል ለመረዳት በሰባት ዘመናት የተከፋፈለውን እና በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ በሰባቱ አብያተክርስቲያናት የተወከለውን የቤተክርስቲያን ታሪክ መመልከት ያስፈልገናል፡፡
ራእይ 1፡11 እንዲሁም፡- የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ።
እነዚህ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ከጠፉ ረጅም ጊዜ አልፏል፡፡ እነዚህ ቤተክርስቲያኖች ባለፉት 2000 ዓመታት ውስጥ ለነበሩ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ጥልቅ የሆነ መልዕክት ከሌላቸው በስተቀር ለእኛ ብዙም ትርጉም አይኖራቸውም፡፡
እስቲ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም የሚደግፍ ማስረጃ ይኖር እንደሆን እንመልከት።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ ገዥ የነበረው አዲስ ኪዳንን የጻፉልን የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ትምሕርት፡፡ ሐዋርያቱ ቀጥታ ከኢየሱስ የተማሩ ሲሆኑ ትኩረታቸውም ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያምኑና ከሰዎች ልማድ እንዲርቁ ማድረግ ነበር፡፡ የሮማው ንጉሰ ነገስት የኔሮ አገዛዝ በ68 ዓ.ም. ከማብቃቱ በፊት ባሉት ዓመታት ውስጥ ያዕቆብ፣ ጳውሎስ እና እና ሌሎች ሐዋርያት ተገድለው ነበር፡፡ ከሐዋርያት ሁሉ ለረጅም ጊዜ በሕይወት የቆየውዮሐንስ ሲሆን የሞተውም በ100 ዓ.ም. አካባቢ ነበር፡፡ ከዚያም ሰዎች በራሳቸው ጥበብ ሲመኩ እራሳቸውን ከፍ ሲያደርጉ የሐዋርያት ተጽዕኖ እየቀነሰ መጣ፡፡
በቤተክርስቲያን ውስጥ “ዋና ሊሆን” የሚፈልገውን ዲዮጥራጢስን በተመለከተ 3ኛ ዮሐንስ ውስጥ ማስጠንቀቂያ ተጽፏል። “ነ ቀስ በቀስም እራሳቸውን ታላቅ ያደረጉ እና የብልጣብልጥ ሰዎች አመለካከት የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መተካት ጀመረ፡፡
3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።
የሰው አመራር የመጽሐፍ ቅዱስን ቦታ መተካት ጀመረ፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ኤፌሶን የምትባል ሲሆን ትርጉሙም “የተነጣጠረባት” ወይም “ዘና” ያለች ማለት ነው፡፡ በ200 ዓ.ም. የሐዋርያት ተጽዕኖ እና የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል በሰው አስተሳሰቦች እና በመሪዎች የግል ፍላጎት እና ጥላቻ ተተኩ፡፡
ከ200 ዓ.ም. ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቆ መከተል ቀረ፡፡
ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሰምርኔስ ዘመን ተጀመረ(ሰምርኔስ ማለት እሬት ወይም መራራነት እና ሞት ማለት ነው)፡፡ የሮማ ነገታት ክርስቲያኖችን በጭካኔ ያሳድዱ የነበረ ሲሆን፤ በሚላን ከተማ በታወጀው አዋጅ አማካኝነት በ313 ዓ.ም. ጭፍጨፋው እስከቆመበት ጊዜ ድረስ ከንጉስ ኮንስታንቲን በፊት 3 ሚሊዮን ያህል ክርስቲያኖች ተገድለዋል፡፡ ጭፍጨፋው ሲቆም ሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማለትም የጴርጋሞን ዘመን ጀመረ (ትርጉሙም ያገባች ማለት ነው)፡፡ ለአካላዊ ደህንነታቸው የከፈሉት የክርስትና ዋጋ ኮንስታንቲንን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው መቀበልና ይህ አንድ ሰው ብቻውን የሁሉም ቤተክርስቲያን ገዥ በመሆኑ ለእርሱ እምነቶች መገዛት ነበር፡፡ በዚህም ክርስትና በሰው መሪ የሚመራ መንግስት ካለው ፖለቲካ ጋር ጥብቅ ጋብቻ ፈጸመች፡፡
ስለዚህ የቤተክርስቲያንም ራስ ሰው ሆነ፡፡ ኮንስታንቲን ክርስቲያኖችና አረማውያን ሕብረት እንዲፈጥሩ ፈለገ፤ በዚህም ክርስትና ከአረማዊነት ጋር ጥብቅ ጋብቻ በመጋባት የአረማውያን በዓላት የክርስትና ስም እየተሰጣቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገቡ፡፡
በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ስለ ክሪስማስ ወይም ዲሴምበር 25 የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ የለም፡፡
በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ274 ዓ.ም. ዲሴምበር 25 በሮም ውስጥ በንጉሰ ነገስት ኦሬልያን አማካኝነት በሦስት ክፍል ተከፋፍለው የነበሩትን የሮማ ግዛቶች በድጋሚ በማዋሀድ ላገኘው ድል መታሰቢያነት የፀሐይ አምላክ የልደት ቀን ተደርጐ ታወጀ፡፡
በሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ350 ዓ.ም. አካባቢ የሮም ጳጳስ የነበረው ዩሊየስ ዲሴምበር 25ን ተቀበለው ምክንያቱም ቀኑ አረማውያን የአማልክቶቻቸውን የልደት ቀን በድምቀት የሚያከብሩበት እና ከክረምቱ ቀናት ሁሉ በጣም አጭሩ ቀን ወይም ዊንተር ሶልስቲስ የሚባለው ነበር። (በ1500ዎቹ ውስጥ ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው በካላንደሩ ላይ ባደረገው መጠነኛ ለውጥ ምክንያት የክረምቱ አጭር ቀን ወደ ዲሴምበር 21-22 ፈቀቅ ብሏል። እስካሁንም በእኛ ዘመን ዊንተር ሶልስቲስ) በ 350 ዓ.ም. አካባቢና ከዚያ በኋላ ክርስቲያኖች የፀሐይን አምላክ የልደት ቀን በቀላሉ ወደ አምላክ ልጅ የልደት ቀን የቀየሩት ሲሆን ክሪስማስም በአረማውያንና በክርስትና እምነቶች መካከል ከተደረገው ጋብቻ ውስጥ ተወለደ፡፡
በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሰው አመራር ቤተክርስቲያን ላይ እየሰለጠነ የመጣ ሲሆን፤ ኤጲስቆጶስ የሚለው ማዕረግም የአንድ ከተማ ቤተክርስቲያን መሪ ወደመሆን ከፍ ተደረገ፡፡ እያንዳንዱ ከተማም የራሱ የቤተክርስቲያን መሪ ማለትም ኤጲስቆጶስ ነበረው፡፡ ታሪክም ከዚያ በኋላ ሰዎችን የሮም ጳጳስ ወይም የአንጾኪያ ጳጳስ ወዘተ. እያለ ተቀበላቸው፡፡ ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጳጳስ የሚለው ቃል አጠቃቀሙ በዚህ መንገድ አልነበረም፡፡
ፊልጵስዩስ 1፡1የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
ኤጲስቆጶሳት በፊሊጵስዩስ ከተማ በብዙ ቁጥር ነው የተጠቀሱት፤ ፊልጵስዩስ የታላቁ እስክንድር አባት በነበረው በንጉስ ፊሊፕ ስም የተሰየመች ከተማ ናት፡፡
ስለዚህ በአንድ ከተማ ውስጥ በርካታ ኤጲስቆጶሳት እንደነበሩ ማየት እንችላለን፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡1-13 እንደተጻፈው የኤጲስቆጶስ መስፈርት ከዲያቆን ጋር አንድ አይነት ነው፡፡
በመሆኑም ኤጲስቆጶስ ማለት በቀላሉ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ነው፡፡ የአጥቢያ ሽማግሌዎች ኃላፊነት ስለለባቸው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ነበሩ፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ያስቀመጡት አሰራር ነበር፡፡ ጳውሎስም ጴጥሮስም ሽማግሌዎችን የአጥቢያ ቤተክርስቲያን መሪዎች አድርገው ነው እውቅና የሰጡዋቸው፡፡
የሐዋርያት ሥራ 20:17-28 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ (ጳውሎስ) የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤…
ቁጥር 28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
1ኛ ጴጥሮስ 5:1-3 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ …የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ስለዚህ የአጥቢያ ሽማግሌዎች እያንዳንዱን ሕብረት በሃላፊነት እንዲያስተዳድሩ ተመድበዋል፡፡ ይህም አሰራር አንድ ግለሰብ ጉባዔውን እንዳይቆጣጠር ይከለክላል፡፡
መጋቢ ወይም ፓስተር የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
ይህም መጋቢው ጉባዔውን እንዲቆጣጠር ፈቃድ አይሰጠውም፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሽማግሌዎች ብዙ ጊዜ መጠቀሱ ትክክለኛው አመራር የእነርሱ መሆኑን ያሳያል፡፡
በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የመጣው “የከተማ ጳጳስ” የሚለው ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት የራቀ ሐሳብ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እየራቁ የሰውን አመራር መቀበል ጀመሩ፡፡ በሁለተኛው ዘመን ማብቂያ እያንዳንዱ ከተማ አንድ ጳጳስ ወይም የቤተክርስቲያን መሪ ነበረው፡፡
ይህም ለሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መንገድ ጠረገ፤ በሦስተኛውም ዘመን አንድ ሰው ብቻ ማለትም ፖለቲካዊ መሪ ንጉስ የኮንስታንቲን የሁሉም ቤተክርስቲያናት መሪ ሆነ፡፡ ብዙ ነገሮች በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካለው ትምሕርት እየራቁ ሄዱ፡፡
ዓመታት ሲያልፉም ቀስ በቀስ የዲሴምበር 25 ተቀባይነትን እየጨመረ ሄደ፡፡
የሮም ቤተክርስቲያን ሆን ብላ “የፀሐይን ልደት በክርስቶስ ልደት” ለመቀየር ዲሴምበር 25 ስለመቀበልዋ የሚያረጋግጥ ቀጥተኛ ማስረጃ ባይኖርም፤ ከቤተክርስቲያን አባቶች ዘንድ ተጽፈው የተቀመጡ የሚከተለውን ሃሳብ የሚያስተላላፉ ስብከቶች አሉ፡፡
ለምሳሌ የሂፖው ኦጋስተን (354-430) በ202ኛው ስብከቱ ውስጥ እንዲሁም ታላቁ ሊዮ (440-461) [— PL 54 Sources chartiennes 22] ቀኑ የተመረጠው በእለቱ በአረማውያን ዘንድ በጣም ተወዳጅ የሆነ የበዓል ቀንን ተጽእኖ ለመቋቋም ተብሎ ነው ይላል፡፡
ክርስቲያኖች በዙሪያቸው ካሉ ማሕበረሰብ ውስጥ ጎልተው የሚወጡ አስተሳሰቦችን የመቅዳት አሳዛኝ ዝንባሌ አላቸው፡፡ የፋሲካ እንቁላል፣ የፋሲካ ጥንቸል ወይም የገና ዛፍን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ማስረጃ የለም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ክርስቲያኖች በደስታ ወደ እምነታቸው የቀላቀሏቸው የሚስቡ አመለካከቶች ናቸው፡፡ ከ312 ዓ.ም. በኋላም ሁኔታው እንዲሁ ቀጠለ፡፡ ኮንስታንቲን የክርስቲያኖችን ስደት በማስቆሙ የክርስቲያኖች ጀግና ሆነ፡፡ ኮንስታንቲን ክርስቲያኖች እና አረማውያን በአንድ ግዛት ስር በሕብረት እንዲኖሩ ፈለገ፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች በኮንስታንቲን ዘንድ ተወዳጅነትን ለማግኘት ብለው እምነታቸውን ከአረማውያን እምነት ጋር የሚያስተሳስር መንገድ መፈለግ ጀመሩ፡፡ “ከእርሷ ዘንድ ውጡ” (ራዕይ 18፡4) የሚለው ትዕዛዝ ቸል ተባለና እያመቻመቹ የአረማውያንን ሃሳቦች ወደ ክርስትና ማስገባት እንደ ብልህነት ተቆጠረ።
ስለዚህ በሦስተኛ የቤተክርስቲያን ዘመን ከክርስቶስ ከተወለደ 300 ዓመታት ካለፉ በኋላ ነው የእርሱን የልደት ቀን ለመወሰን ማሰብ የተጀመረው፡፡ የክረምት አጋማሽ በዲሴምበር ወር ውስጥ ያን ጊዜ ቄሳር ባዘጋጀው አዲስ ካላንደር ዲሴምበር 25 የነበረ ሲሆን ወቅቱ ብዙ ልዩ ልዩ የአረማውያን በዓላት የሚከበሩበት ጊዜ ነበር፡፡
ደግሞም ለበርካታ አረማውያን አገራትም የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ነበር፡፡
በአንድም ሆነ በሌላ ወቅቱ የበዓል ሰሞን ነበር፤ ስለዚህ ወቅቱ ለክርስቲያኖችም በዓላቸውን ለማክበር እንደ ጥሩ ጊዜ ተወስዷል፡፡
ስለዚህ የክረምቱን አጋማሽ የክርስቶስ ልደት ነው ብሎ ማክበሩ ክርስትናን ከአረማውያን ልማዶች ጋር በአንድነት አሰለፋት፡፡
ዴሴምበር 25 ከአረማውያን እምነት ጋር ለመቀራረብ ሆን ተብሎ የተመረጠ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ከአረማውያን እምነት ጋር ስለተቀራረበ በርካታ ጥቅሞችን ይዞ መጥቷል፡፡ አረማውያን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደቤታቸው እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ ከክርስትና ጋር የመጡ አዳዲስ ቃላትን ከመቀበል በቀር ከእምነታቸውም ውስጥ ብዙ ለውጥ እንዲያደርጉ አይጠበቅባቸውም። የፀሐይ አምላክ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ተቀይሯል፡፡ ይህም አረማውያኑን ክርስትና የተነሱ አረማውያን ለማድረግ በጣም ቀላል ዘዴ ሆነ፡፡ በሕይወታቸውና በእምነታቸው እምብዛም መለወጥ አላስፈለጋቸውም፡፡ ይህም ልክ የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ዓለማዊ ባህሪያትንና አለባበስን በመፍቀድ የአባላት ቁጥር እንደምታሳድገው ነው፡፡
በ312 ዓ.ም. ኮንስታንቲን ክርስትናን መቀበሉ ጴርጋሞን ተብሎ የሚታወቀውን ሦስተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን አስጀመረ (ጴርጋሞን፡- ሙሉ በሙሉ የተጋባች ማለት ነው)፡፡ የክርስቲያኖችን ጭፍጨፋ አስቆመ፤ በዚህም በወቅቱ በክርስቲያኖች ዘንድ እንደ ጀግና ይታይ ስለነበረ ክርስቲያኖችም የሱን አመራር ለመከተል ደስተኞች ነበሩ፡፡
የቤተክርስቲያንን መሪነት ለራሱ ወሰደ፤ ክርስቲያኖችና አረማውያን አንድ እንዲሆኑ በመፈለጉም የአረማውያን በዓላት የክርስትና ቅርጽና መልክ እየተሰጣቸው እንዲለወጡ አበረታታ፡፡ ቤተክርስቲያንና መንግስት በአንድ ሰው መሪነት ተዋሃዱ፡፡ ሐይማኖትና ፖለቲካ በአንድ ላይ ተዋህደው መሪዎች በሰዎች ላይ ከፍተኛ ሥልጣን እንዲኖራቸው አስቻሏቸው፡፡ የሮሙ ጳጳስ የሮማ ግዛት ዋና ከተማ ጳጳስ በመሆኑ ብቻ ከሌሎች የሚበልጥ ስልጣንና ክብርን አገኘ፡፡ በ312 ዓ.ም. ኮንስታንቲን የላተራንን ቤተመንግስት አዲስ የመኖሪያ ቤት አድርጐ ለሮማ ጳጳስ ሰጠው፤ ይህም ድርጊት የጳጳሱን ክብር በእጅጉ ጨምሮለታል፡፡ ለሮማው ጳጳስ ሲልቬስተር ኮንስታንቲን እጅግ ብዙ ሃብት የሰጠው ሲሆን ይህም በግልጽ ሲልቬስተር ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ለኮንስታንቲን እንዲታዘዝ አድርጐታል፡፡ የሮማው ጳጳስ ዲሴምበር 25ን የኢየሱስ ልደት አድርጐ ከተቀበለው ክብሩ እና ስልጣኑ እየጨመረ ከመሄዱ አንጻር ብዙዎች ይህንኑ እንዲያምኑ ሊያበረታታቸው ይችላል፡፡ በ350 ዓ.ም. አካባቢ የሮማው ጳጳስ ዩሊየስ ከተደረገበት ጫና የተነሳ ዲሴምበር 25ን የኢየሱስ ልደት አድርጐ ተቀበለ፡፡ ክርስትናል በአረማውያን የባህል ጫና ውስጥ እየሰጠመ ሄደ፡፡ እነዚህ የአረማውያን ልማዶች በአተገባበራቸው ምንም ሳይለመጡ ክርስቲያናዊ ስም ብቻ እየደረቡ ወደ ክርስትና ውስጥ ገቡ፡፡ ክርስትና ብዙ አረማዊ ልማዶችን እየተሞላ ተለወጠ። አረማዊነት ጥቂት ክርስቲያናዊ ስሞችን ከመቀበሉ በቀር እምብዛም አልተለወጠም፡፡
የሮም አምባገነን መሪ ዩልየስ ቄሳር በ45 ዓመተ ዓለም የካላንደር ለውጥ አደረገ። ካላንደሩ ከዓመቱ ወቅቶች ጋር እንዲገጣጠም በማሰብ 46 ዓመተ ዓለም ላይ 90 ቀናትን በመጨመር 445 ቀናት አደረገ፤ በዚያን ጊዜ የሮማውያን አንድ ዓመት 355 ቀናት ነበር። (በእርግጥ ብዙ ተቃውሞ ተነስቶ ነበር፡፡ የግራ መጋባት ዓመት ተብሎም ይጠራ ነበር)፡፡ በዚያ ወቅት የክረምት አጋማሽ ዲሴምበር 25 ላይ እንዲሆን ያደረገውም እርሱ ነው። ነገር ግን የቄሳር ካላንድር ከወቅቶቹ ጋር ሲነጻጸር በየ400 ዓመቱ በ3 ቀኖች ወደ ኋላ ይቀራል፡፡ በመሆኑም ዊንተር ሶልስቲስ ማለትም የክረምቱ አጭር ቀን ቀስ በቀስ ዲሴምበር ውስጥ ወደኋላ እየተንሸራተተ በ12 ቀናት ያህል እየቀደመ መምጣት ጀመረ፡፡ ይህንንም ችግር በ1582 ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው 10 ቀናትን ከካላንደሩ ላይ በማንሳት አስተካክሎ የክረምቱን አጋማሽ ከዲሴምበር 25 ጥቂት ቀናት ብቻ እንዲቀድም አድርጎታል፡፡ በመሆኑም እስከዛሬ የክረምት አጋማሽ ዲሴምበር 21 አካባቢ ሊሆን ችሏል፡፡
ይሁን እንጂ መሬት በዛቢያዋ ላይ ስትሽከረከር በመዋለለልዋ እና በዋልታዎች ላይ ያሉት የበረዶ ግግሮች እኩል ባለመሆናቸው (በሰሜን ዋልታ ካለው የበረዶ ግግር የደቡብ ዋልታ አስር እጥፍ ይበልጣል) እንዲሁም በመሬት ላይ ፕላኔቶች በሚፈጥሩት የስበት ተጽዕኖ እና የምድር ምሕዋር ትክክለኛ ክብ ባለመሆኑ የክረምት አጋማሽ የሚሆንበት ቀን በጥቂቱ ይለዋወጣል፡፡ ግሪጐሪ በየ100 ዓመቱ 1 ቀን የጨመረ ሲሆን ይህም በ400 መካፈል የሚችል ከሆነ ብቻ ነው፤ ለምሳሌ 1600፣ 2000 ወዘተ፡፡ በዚህም መሠረት በቄሳር ጊዜ ዲሴምበር 25 የነበረው የክረምት አጋማሽ ቀን አሁን ዲሴምበር 21 ሆኗል፡፡
ይህ የቀናት ለውጥ ለማንም ግድ አልሰጠውም፡፡ ሁሉም እንዳላወቀ ሰው ቸል ብሎታል፡፡
ነገር ግን የክረምት አጋማሽ ቀን ቀስ በቀስ በየ400 ዓመቱ በሦስት ቀናት እየተንሸራተተ ስለሚሄድ የክርስቶስን የልደት ቀን ዲሴምበር 25 ላይ አጽንቶ ማስቀረት ቀላሉ አማራጭ ተደርጎ ተወስዷል። ስለዚህ ይህ ቀን ከክረምት አጋማሽ ጋር ቢገጥምም በይገጥምም የክሪስማስ ቀን ተብሎ ተሰየመ።፡፡
የክረምት አጋማሽ በቄሳር ጊዜ ዲሴምበር 25 የነበረ ሲሆን ቀኑ ለብዙዎቹ አረማውያን ሃገራት የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ነበር፡፡
በአንግሎ-ሳክሰን እንግሊዝ ውስጥ ብዙውን ጊዜ አዲስ ዓመት ይጀምር የነበረው በዲሴምበር 25 ሲሆን ቀኑ በአረማውያን ዘመን አዲስ ዓመት መጀመሩን ያመለክት ነበር፡፡
“ሶልስቲስ” ማለት ፀሐይዋ (በላቲን ቋንቋ “ሶል”) በክረምት ቀኖቹ እያጠሩ በሚሄዱ ጊዜ ልትጠልቅ ስታዘቀዝቅ አድማሱጋ ቀጥ ብላ ትቆማለች፤ በዲሲምበር 21ም ለአንድ ቀን ቀጥ ብላ በመቆም ቀኑ ረጅም በሚሆንበት በበጋ ወራት ወደ ላይ መውጣት ቀጥታ ከአናት በላይ ትውላለች ማለት ነው፡፡ ይሁም ልክ በጦርነት ጊዜ እንደሚደረግ የሰላም ስምምነት ነው፤ ማለትም ወታደሮች ሁሉ ውጊያ ትተው ቀጥ ብለው እንደሚቆሙት ነው፡፡
ይሁን እንጂ አብዛኛው የምዕራብ አውሮፖ ሀገራት የሚቆጥሩትን ዓመት የሚጀምሩት በዲሴምበር 25 (የኢየሱስ ልደት)፣ በማርች 25 (የክርስቶስ ስጋ መልበስ) ወይም ፋሲካ፤ ለምሳሌ ፈረንሳይ ውስጥ (ለበለጠ ማብራሪያ ስለ ሊተርጂካል ዓመት የተጻፈውን መጣጥፍ ይመልከቱ)…
ሀገራት በ1500 ዓ.ም. አካባቢ አዲስ ዓመት የሚጀምርበትን ቀን ወደ ጃንዋሪ 1 መቀየር ጀመሩ፡፡
በሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሮማው ንጉሰ ነገስት የቤተክርስቲያን ራስ እና የመንግስት መሪ ሆነ፡፡ የሮም ግዛት በመጨረሻ በምዕራቡ አካባቢ በ476 ዓ.ም ሲወድቅ በወቅቱም የባርባሪያን ወራሪዎችን የሚቋቋም ኃይል ስላልነበረ በተፈጠረው የሥልጣን ክፍተት የተነሳ ሰዎችም የሮሙን ጳጳስ እንደ ቤተክርስቲያን መሪ መቀበል ጀመሩ፡፡ ሌላው ቀርቶ ባርባሪያኖች እንኳን በካቶሊክ ሐይማኖታዊ ስርዓት እና ጳጳሱ የጴጥሮስ ስልጣን ወራሽ ነኝ የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ አለኝ በማለቱ ተደንቀዋል፡፡ ስለዚህ በ600 ዓ.ም. አካባቢ 4ኛው የጥሬያኖን ዘመን ጀመር (ትያጥሮን፡- ጨቋኝ ሴት ማለት ነው)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ስትሆን እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ደግሞ የክርስቶስ ሙሽራ ተብላ ትጠራለች፡፡ ከ600 ዓ.ም. በኋላ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀስ በቀስ በሐይማኖታዊ አስተምህሮና በፖለቲካዊ አስተሳሰብ አውሮፓን መቆጣጠር መጨቆን ጀመረች፡፡
ስለዚህ በ1800 ዓ.ም. ሰዎች ጃንዋሪ 1ን እንደ አዲስ ዓመት ቀን፤ ዲሴምበር 21ን የክረምት አጋማሽ እና ዲሴምበር 25ን የክሪስማስ ቀን አድርገው ተቀበሉ ምክንያቱም እነዚህን ቀናት ሁሉ የሮማ ካሊክ ቤተክርስቲያን አጽድቃቸዋለች፡፡ በጨለማው ዘመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን የተቆጣጠረች ሲሆን ቤተክርስቲያኗ ለዩኒቨርስቲዎች ከፓሪስ በመጀመር እውቅና በመስጠት በመላው አውሮፓ ለመስፋፋት ችላለች፡፡ በነዚህ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የነበሩ ምሁራን ትምሕርት ለመማር ብቸኛ እድል ያገኙ ሲሆኑ እነርሱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስትምህሮ ተጽእኖ የተጫነው ልዩ የምሁራን ሕብረት ፈጥረው ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜም እነዚህ የተማሩ ሰዎች ነበሩ በመንግስትና በቤተክርስቲያን ውስጥ ሥልጣን የሚሰጣቸው፡፡ ስለዚህ ለረጅም ዘመን አውሮፓ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀምበር ስር ቆየች፡፡
አረማውያን መሪዎች ክርስትናን በመቀበል ተከታዮቻቸውም ይህንኑ እንዲያደርጉ በማስገደድ ክብርና ሥልጣን ማግኘት ቻሉ፡፡ አረማውያን መሪዎች በጣም አስቸጋሪ እና በአደጋ የተሞላ ሕይወት ይመሩ ስለነበር እድሜያቸው አጭር ነበር። ሮምን ሲያዩ ግን ሮም ረጅም ታሪክ የነበራት ደግሞም የተረጋጋ የሕግ ስርዓት እና የሰለጠነ የግብርናና እውቀት እና ኢንዱስትሪ ያላት መሆኗ ያስደንቃቸው ነበር፡፡ የፍራንኮች ንጉስ የነበረው ሻርለሜይን በ782 ዓመ. በአንድ ቀን ብቻ ወደ 4500 የሚጠጉ ሳክሰኖችን አንገታቸውን አስቆርጧል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለመጠመቅ እምቢ ስላሉ ነበር፡፡ እንግዲህ እያለ ክፍለ ዘመናት በሄዱ ቁጥር የአረማውያን ባህሎች ቀስ በቀስ እየጠፉ ሄዱ፡፡ እጅግ ጥቂት የሆኑ አረማውያን ብቻ እምነታቸውን ሳይቀይሩ በመቆየት ዲሴምበር 25 ላይ የፀሐይ አምላክን የልደት ቀን ያከብሩ ነበር፡፡ ብዙዎቹ አረማውያን ግን በግዴታ ክርስቲያን እንዲሆኑ ተደርገው ዲሴምበር 25 ላይ ክሪስማስን ያከብሩ ነበር፡፡
ስለዚህ የክረምት አጋማሽ ሁሌም ለአረማውያን የተለየ ቀን ነበረ ምክንያቱም ቀኑ የክረምት አጋማሽ ብቻ ሳይሆን ለአብዛኛዎቹ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ስለነበረ ነው፡፡ በእርግጥም ቀኑ አዲስ ዓመትን ለመጀመር ትክክለኛ ጊዜ ይመስላል፤ ምክንያቱም ቀኖቹ ረዘም እያሉ እና ሙቀታቸው እየጨመረ ይሄዳል። ይህም ማንኛውም ሰው ሊያስተውለው የሚችለው የተፈጥሮ ኡደት ላይ የሚከሰት ለውጥ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ አረማውያን ያልተማሩ ስለነበሩ ተፈጥሮ ላይ በሚያዩት ለውጥ በመመራት ቀኑ በጣም አጭር ሆኖ ፀሐይዋ በእኩለ ቀን ሰማዩ ላይ ዝቅ ስትል የአዲስ ዓመት መግቢያን ያመለክታል ብለው ይገነዘባሉ፡፡
ይሁን እንጂ ሮም የአዲስ ዓመት ቀንን ጃንዋሪ 1 ላይ ማክበርዋን ብትቀጥልም ይህን ዕለት ልዩ ቀን የሚያደርግም አንዳችም ተፈጥሮአዊ ምልክት የለም፡፡ አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሃገራት በ1500 እና በ1600 ዓ.ም. መካከል የሮምን የአዲስ ዓመት ቀን ጃንዋሪ 1ን ተቀበሉ፡፡ ሮም በአውሮፓ ውስጥ ስልጣን ስለነበራት ሌሎች ሃገሮች ዲሴምበር 25ን እንደ አዲስ ዓመት ቀን ማክበርነ እንዲተዉ ማሳመን ችላለች፡፡
የክረምት አጋማሽ ታዋቂ የሆነ የአረማውያን ባህል ነበረ፤ በዚህም ቀን አምላካቸው የተሰየፈበትና ሞቶ እንደ ልጅ በድጋሚ ተመልሶ የተወለደበትና የሕይወት ትንሳኤ ያገኘበት ጊዜ ነበር፡፡
ዩል የሚባል ዛፍ ግንድ ወይም ሾላ ተቆርጦ(ዩል ማለት በከለዳውያን “ትንሽ ልጅ” ማለት ነው) ከክረምት አጋማሽ በፊት በዲሴምበር ወር ውስጥ በምሽት ይቃጠላል (በመጀመሪያ ወደ ዲሴምበር 25 ነበር አሁን ከካላደሮች ለውጥ በኋላ ቀኑ ዲሴምበር 21 ሆኖ ቀርቷል)፡፡
በጣም ትልቅ የዩል ግንድ ለአሥራ ሁለት ቀናት የእሳት ማንደጃ ባለው ክፍል ውስጥ ይነድዳል (ክሪስማስን ለ12 ቀን የማክበር ልማድ የመጣው ከዚህ ነው) ከዚያ ሲነድ ቆይቶ ዲሴምበር 24 ላይ ያልቃል (ለዚህ ነው የክሪስማስ ዋዜማ ታላቅ ቀን የሆነው)። በቀጣዩ ቀን ከሙታን ትንሳኤን ለማብሰር በጌጣጌጥ ያሸበረቀ ዛፍ እዚያው ክፍል ውስጥ ያቆማሉ፡፡ የዩል ዛፍ (ብዙውን ጊዜ ትልቅ ዋርካ ወይም ሾላ) በጠላቶቹ ተቀልቶ የሞተውና በድጋሚ ሕፃን ሆኖ የተወለደውን አምላካቸውን የሚወክል ሲሆን ይህም በዲሴምበር 25 በክረምት አጋማሽ ላይ በተጌጠ ዛፍ ምሳሌነት ይገለጣል፡፡
የሚቃጣለው ግንድ የሾላ ዛፍ ሲሆን ዲሴምበር 25 ቦታውን ተክቶ ተጊጦ የሚቆመው ደግሞ የጥድ ዛፍ ነው ምክንያቱም በክረምቱ ሌሎች ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ረግፈው የሞቱ መስለው ሲታዩ ዓመቱን ሙሉ ደማቅ አረንጓዴ ሆኖ ለምልሞ የሚቆየው ይህ ዛፍ ብቻ ነው፡፡
እነዚህ ዛፎች የሞትና የዳግም ልደትን ሙሉ ኡደት በምሳሌነት ያሳያሉ፡፡ ይህም ማቆሚያ የሌለው የተፈጥሮ ኡደት ነው፡፡ እያንዳንዱ መጨረሻ አዲስ ጅማሬን ይጠቁማል፡፡
ዩል (Yule) የሚለው ቃል በከለዳውያን ቋንቋ ትንሽ ልጅ ማለት ነው፡፡
ዩል ወይም ዩልታይድ (የዩል ወቅት) የሰሜናዊው አውሮፓ ሕዝቦች የሚያከብሩት ሐይማኖታዊ ባዓል ሲሆን በኋላም ወደ ክርስትና ውስጥ በመግባት ከክሪስማስ ጋር እኩል የሚከበር በዓል ሆኗል (ዊኪፒዲያ)፡፡
የዩል ግንድ እነርሱ እንደሚፈልጉት ያህል ትልቅ ከሆነ ከክረምት አጋማሽ በፊት የአሮጌውን ዓመት መሞት ለማሳየት ለ12 ቀናት ይነድዳል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች እስከዛሬ የክሪስማስን 12 ቀናት ያከብራሉ፡፡ የገና ዛፍ ክርስትናን በግልጽ ከአረማውያን እምነት የሚያስተሳስር ሲሆን ኤርሚያስ የአሕዛብን ልማድ እንዳንከተል በግልጽ ያስጠነቅቀናል። ኤርምያስ እንዳለው የአሕዛብ ልማዶች የሚስቡና የሚያምሩ ቢሆኑም እንኳ ልንከተላቸው አይገባንም፡፡
ኤርምያስ 10፡2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- የአሕዛብን መንገድ አትማሩ…የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እንጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።
እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤
የሮማውያን የአዲስ ዓመት ዋዜማ የሚከበረው ክፉ መናፍስትን ለማባረር ከፍተኛ ጩኸት በመጮህ ነበር፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማ እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ሁካታ የተሞላ መሆኑ በአሕዛብ ልማድ መጠመዳችንንን ያረጋግጣል፡፡
የኤስተር በኒስ (የፋሲካ ጥንቸሎች) እና እንቁላሎችም ሌሎች የተጠመድናባቸው የአሕዛብ ልማዶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ ባይሆኑም ግን በሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ከአሕዛብ ዘንድ ወደ ቤተክርስቲያን ከገቡ በኋላ ቤተኛ ሆነው ቀርተዋል፤ ክርስቲያኖችም ያጌጡና በቀለማጽ ያሸበረቁ የአሕዛብ ልማዶችን በመኮረጅ እግዚአብሔርን ሊያስደስቱ የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡
ሆሊ የሚባል ጠንካራ ቅጠሎች ያሉት ዛፍ አለ፤ የዚህ ዛፍ ደማቅ አረንጓዴ ቅጠሎችና ብሩህ ቀይ ፍሬዎች ተጎንጉነው ለድሩድ ቀሳውስት እራሳቸው ላይ እንደ አክሊል ያገለግሊ ነበር። በጭንቅላታቸው ላይ የሚደፉት ክብ አክሊል የዓመቱን ኡደት እንዲሁም ሞትና ዳግም መወለድን ይወክላል፡፡ እስካሁን ድረስ ይህ ሆሊ ለክሪስማስ ማስጌጫነት የሚያገለግለው ለምንድነው? በክረምት አጋማሽ አረንጓዴ ሆሊ እና ሃረጎች የአሕዛብን ቤቶች ለማስጌጥ ያገለግላሉ። ይህ ልማድ እስካሁንም አልተቋረጠም፡፡
የአረማውያን ዊካ የጥንቆላ አሰራር እስካሁን ድረስ የዩልን ጊዜ እና የክረምት አጋማሽን በኢንተርኔት ያስተዋውቃል፡፡
የአረማውያን ልማዶች የሚስቡ ስለነበሩ ክርስቲያኖች ተቀበሉዋቸው፡፡ ይህ ጥበብ እንደጎደላቸው ያሳያል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው “ሕዝቤ ሆይ… ከእርሷ ዘንድ ውጡ” ይላል (ራዕይ 18፡4)፡፡ በአሕዛብ ልማዶች ተደሰቱ አይልም፡፡
ዲሴምበር 25 ትልቅ ቀን የሆነው እንዴት ነው?
ሰሜን አውሮፓ ውስጥ በክረምት ወቅት ከባድ በረዶ እና ብርድ ስላለ ሰዎች በጨለማና ቆሻሻ ቤታቸው ውስጥ ነበር ብዙ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት፡፡ በክረምት አጋማሽ ቄሳር ዲሴምበር 25 ላይ ያደረገው ግን ኋላ ወደ ዲሴምበር 21 በተመለሰው ቀን ፀሐይዋ በምህዋሯ የመጨረሻ ዝቅታ ላይ ትደርስና ከዚያ ተመልሳ በሰማዩ ላይ ከፍ ብላ በመውጣት ምድሩን ብሩህና ሞቃት ታደርጋለች፡፡ ይህም ለአረማውያን የአማልክቶቻቸውን ሞትና ትንሳኤ የሚያከብሩበት ወቅት መድረሱን የሚያበስር ግልፅ ምልክት ነው። ስለዚህ በጨለማ ቤታቸው ውስጥ ብርሃን እንዲኖር ሻማዎች ይለኮሳሉ፣ በበረዶ ምክንያት ከቤት መውጣት የማይችሉባቸውን አሰልቺ ቀናት ድብርት ለመዋጋት ምግብ መጠጥ እና እንደልብ መስከር ይዘወተራል፡፡ ከተለያዩ ሃገሮች የሆኑት አረማውያን ብዙ የተለያዩ አስገራሚ ልማዶች አሉዋቸው፡፡ ሰዎችም ከተለያዩ ምንጮች የሚወዱዋቸውን ሐሳቦችን ይቀዳሉ በተለይም የክረምት አጋማሽ ላይ በብዙ ሃገሮች ከሚከበሩ በዓሎች፡፡ የክሪስማስ (የገና) አጀማመሩ ክርስቲያኖች ከተለያዩ የአሕዛብ ልማዶችን ባደረጉት ኩረጃ ነው፡፡
ትልቅ ግዛትን ተቆጣጥራ የነበረችው ሮም ስለሆነች ወደ ሮም እናተኩር
ሳተርናሊያ የተባለው በዓል የሳተርንን አምላክ ለማክበር የሚደረግ በዓል ነበር፡፡ በዓሉም የሚከበረው በዲሴምበር 17 ነበር፡፡ ዩልየስ ቄሳር በ45 ዓመተ ዓለም ካላንደሩን በመቀየር በጃንዋሪ፣ በኦገስት እና በዲሴምበር ወራት ላይ 2 ቀናት በመጨመሩ ምክንያነት ይህ በዓል ወደ ዲሴምበር 19 ፈቀቅ ብሏል፡፡ ወግ አጥባቂዎች ግን ትክክለኛው ቀን 17 ነው ብለው ስለሚያምኑ ደስተኞች አልነበሩም፡፡ ኦጋስተስ ንጉሰ ነገስት ሲሆን ቀናትን በመጨመርና 18ኛውን ቀን በማካተት ሳተርናሊያ ለሦስት ቀናት እንዲከበር አደረገ፤ ማለትም ከ17 እስከ 19፡፡ በመቀጠል የመጣው ንጉሰ ነገስት ካሊጉላ ሁለት ቀናትን በመጨመር በአሉን ከ17 እስከ 21 አድርጎ አራዘመው፡፡ ከዚያም በኋላ እንደገና 2 ቀናት ተጨምረው ሳተርናሊያ ከዲሴምበር 17 እስከ 23 ሆነ፡፡ ወቅቱ በተለይም ዲሴምበር 23 የበርካታ ስጦታ መለዋወጫ ጊዜ ሆነ፡፡ ሳቱርናሊያ የስካር እና ልቅ ወሲባዊ ኃጢአት የሚፈጸምበት በዓል ነው። (አሁን የተለወጠ ነገር አለን? ለምንድነው እስካሁን ድረስ በዚህ ወቅት ስጦታዎችን የመግዛት አባዜ የተጠናወተን?)፡፡
በ260 ዓ.ም አካባቢ የሮማ ግዛት በመበታተን ላይ ነበረች፡፡ በ270 ዓ.ም. ኦሬሊያን የተባለ አንድ ብልህ ጀነራል የንጉሰ ነገስትነቱን ቦታ ያዘ፡፡ ምስራቃዊያን ግዛት ካሸነፈ በኋላ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ የምዕራቡንም ክፍል መልሶ ተቆጣጠረ፡፡ በዲሴምበር 274 ዓ.ም ወደ ሮም ሲመለስ ለሚወደው ለፀሐይ አምላክ አንድ የተለየ የበዓል ቀን በማወጅ ምስጋናውን ለማቅረብ ፈለገ፡፡ ዲሴምበር 25ን ከመረጠ በኋላ ያልተሸነፈው ፀሐይ የልደት ቀን እንዲሆን አወጀ፡፡ ዲሴምበር 25 የዓመቱ አጭር ቀን ከመሆኑ አንፃር እና ቀጣዮቹ ቀኖች እየረዘሙና እየደመቁ የሚሄዱ በመሆናቸው ሆን ብሎ የተደረገ ነው የቀኑ አመራረጥ፡፡ ይህም ውሳኔ የክረምት አጋማሽ በዓሎችን ከሚያከብሩ ሌሎች የአረማውያን ሀገራት ጋር እንዲገጣጠሙ አደረጋቸው፡፡ አብዛኛዎቹ የምዕራብ አውሮፓ ሃገሮች ዲሴምበር 25 የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ነው ብለው ይቀበሉ ስለነበር በብዙዎቹ ዘንድ ቀኑ በፊትም ታዋቂ የበዓል ቀን ነበር፡፡ ጃንዋሪ 1 የአዲስ ዓመት ቀን ተደርጐ ተቀባይነት ያገኘው ከ1500 ዓ.ም. በኋላ ነበር፡፡ ሮም እራሷ ጃነዋሪ 1ን የአዲስ ዓመት ቀን አድርጋ ማክበሩዋን ቀጠለች፡፡ ኋላም የፀሃይን አምላክ ልደት ማክበርም ተወዳጅነቱ እየጨመረ ሄደ ምክንያቱም ዲሴምበር 25 ቀድሞውንም ታዊቂ በዓል ነበር፤ለብዙዎችም የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ እና ተገድለው የነበሩ አማልክት የሚወለዱበትና የሕይወት ትንሳኤ የሚያገኙበት ጊዜነበር፡፡
በንጉሰ ነገስት ኮንስታንቲን ጊዜ (በ325 ዓ.ም. አካባቢ) እና በንጉሰ ነገስት ቴዎዶሲየስ (በ380 ዓ.ም. አካባቢ) ጊዜ አረማውያን ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጡ ለማበረታታት ወይም ለማስገደድ ቤተክርስቲያን ከአረማውያን በአላት ጋር ሕብረት ለመፍጠር ሞከረች፡፡ በመሆኑም ክርስትና የተለየዩ የአረማውያን እምነቶችን መገለጫ መቀበል ጀመረች፡፡
ይህ እንግዳ ሁኔታ ሊመስል ቢችልም ግን እስካሁን ድረስ ቤተክርስቲያን የዓለምን አስተሳሰቦች፣ ባህሪና አለባበስ እየተቀበለች ነው፡፡ እንደ ደች ሪፎርምድ ቸርች የመሳሰሉ ቤተክርስቲያኖች በፖለቲካ ውስጥ መጠመዳቸው እና በ1948 አፓርታይድን መደገፋቸው ቤተክርስቲያን ከዓለም ጋር በማይመች አካሄድ መጠላለፏን ከሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች አንዱ ነው፡፡ በጨለማው ዘመን በጳጳሱ ኧርባን ፈቃድ ግድያ፣ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር በመፈፀም ስግብግብነታቸውንና የእርኩሰት ፍላጐታቸውን በመስቀል ዘመቻ ወይም በቅዱስ ጦርነት ስም የሸፋፈኑት የመስቀል ዘማቾችስ ምን ይባላሉ? ጦርነት እጅግ አስከፊ ተግባር እንጂ ቅዱስ አይደለም፡፡ ማን ትክክል እንደሆነ በጦርነት አይወሰንም፤ ጦርነት ማን ሳይሞት እንደሚተርግ ብቻ ይወስናል እንጂ፡፡
እንግዲህ ቤተክርስቲያን ብዙውን ጊዜ ዓለማውያን ወደሚያመጡት ሃሳብ ስታዘነብል ቆይታለች ምክንያቱም ይህ ዝንባሌዋ በቀላሉ አባላትን ለማብዛት ጠቅሟታል፡፡ የዞዲያክ (የኮከብ ትንበያ) ምልክቶች ከ4000 ዓመታት በፊት ባቢሎናውያን ነበሩ የፈጠሩዋቸው፡፡ በዚህ ዘመን የወደፊት እጣ ፈንታችሁን ይገልጣሉ ተብለው የሚታመኑ የኮከብ ትንበያ ገጾችን ያላካተተ የጋዜጣ የለም፡፡ ብዙ ክርስቲያኖችም የኮከብ ትንበያዎችን ያነብባሉ ደግሞም ያምናሉ፡፡
በመሆኑም ክርስቲያኖች ወደ ዓለም እየተሳቡ ለራሳቸው ማመካኛ በመፍጠር እነዚህና ሌሎችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልምምዶችን ይቀበላሉ፡፡
የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን መፍቀድና ሰዎች ሳይጋቡ ወሲብን እየፈጸሙ እንዲኖሩ መፍቀድ ከዓለም የመጡ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት እያገኙ ያሉ የዓለም ጥበቦች ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ብሔራዊ ፓርቲው አፓርታይድን ሲያስተዋውቅ የፓርቲው ይፋዊ ቤተክርስቲያን የሆነችው ደች ሪፎርምድ ቸርች አፓርታይድ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ አረጋግጣ አቅርባለች፡፡ ኤፍ. ደብልዩ. ዴ ክለርክ አፓርታይድን ለማፍረስ በወኔ ሲነሳ ይህችው ቤተክርስቲያን ራሷ በድንገት አፓርታይድ ስህተት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ገልፃለች፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች በፖለቲካና በዓለም ተጽዕኖ እየተፍገመገሙ እንደሆነ እናያለን፡፡ ዓላማቸው ተቀባይነት ማግኘት ብቻ ነው፡፡
በ378 ዓ.ም. ቴዎዶሲየስ ንጉሰ ነገስት ከሆነ በኋላ በ381 ዓ.ም. አረማውያንን እንዲገደሉ የሚያዝ ጨካኝ ሕግ አወጣ፡፡ ስለዚህ አረማውያን ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው እምነታቸውን በበክርስቲያናዊ ቃላት መሸፈን ጀመሩ፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን የአረማውያን ጣኦታትና ሐውልቶች በታዋቂ ክርስቲያኖች ስም በመጠራት ሳይጠፉ መቅረት ችለዋል፡፡ ሐውልቱ ወይም ጣኦቱ ጁቢተር ቢሆን ይሰባብሩት ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጴጥሮስ ተብሎ ሲሰየም ማንም ሳይነካው መኖር ችሏል፡፡ የአረማውያን ቤተመቅደሶች ቤተክርስቲያን ሆኑ፡፡ ከባቢሎን ግምብ የተኮረጁ ጉልላቶች ወሳኝ የቤተክርስቲያን መዋቅር ሆነዋል፡፡
በዲሴምበር 25 ይከበር የነበረው የፀሐይ አምላክ ልደት የእግዚአብሔር ልጅ ልደት ሆኖ ተለወጠ፤ ኢየሱስ በዲሴምበር 25 ነው የተወለደው ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ፡፡
የክርስቶስን የልደት ቀን በዲሴምበር 25 ማክበርን በተመለከተ የሚናገር የመጀመሪያ ሰነድ በ354 ዓ.ም የተጻፈው ክሮኖግራፊ ነው፡፡ ይህ ሰነድ ሁለቱንም ማለትም የፀሐይ አምላክ ልደትንና የኢየሱስን ልደት መዝግቦ ይዟል፡፡ ስለዚህ ጊዜ እያለፈ ሲሄድም ዲሴምበር 25 የኢየሱስ የልደት ቀን ተደርጐ ተቀባይነት አገኘ፡፡ ብዙ ሰዎች ማንም መጽሐፍ ቅዱስን ፈትሾ ስለማይመረምር ብልጣ ብልጥ ሰዎች በጣም አሳማኝና በሆነና በሚስብ መንገድ ክርስትናን እና ጣኦት አምልኮን በአንድ ላይ ቀላቅለዋል፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ ብርሃናችን ነው፡፡ ብርሃንን በአግባቡ ካልያዙት ይጠፋል፡፡ በቀጣዩ የቤተክርስቲያን ዘመን ማለትም የትያጥሮን (ትርጓሜው ጨቋኝ ሴት ማለት ነው) ዘመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፖን ሁሉ ወደ ድቅድቅ ጨለማ ይዛ መግባቷ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡
ኢየሱስ የተወለደው በክረምት አጋማሽ ነውን?
ኢየሱስ “ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ” ብሏል (ማቴዎስ 24፡20)፤ ምክንያቱም በዲሴምበርና በጃንዋሪ ወራት ምሽቶቹ እጅግ የሚቆረጣጥም ብርድና ቅዝቃዜ ያላቸው ናቸው፡፡ ዮሴፍ በዚያ ከባድ የብርድ ወቅት በክረምት አጋማሽ ልትወልድ የደረሰች ነፍሰጡር ይዞ ማረፊያ በሌለበት በምሽት አይዞርም ነበር፡፡ እስራኤል ውስጥ ከኦክቶበር በኋላ እረኞች በምሽት ወቅት በጎቻቸውን አያሰማሩም ምክንያቱም በጣም ይቀዘቅዛል፡፡ ነገር ግን እረኞችና ከበጐቻቸው ጋር ነበሩ ኢየሱስን ለማምለክም መጥተዋል፡፡ ከወራት ሁሉ የክረምት አጋማሽን (ዲሴምበር በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ) የኢየሱስ የልደት ቀን አድርጐ መምረጥ እጅግ የማይመስል ነገር ነው፡፡
ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ አልገቡም፡፡ እነርሱ የገቡት ወደ ቤት ሲሆን ያገኙትም ኢየሱስንና ማርያምን ብቻ ነው፡፡ ዮሴፍ ስለመኖሩ አልተጠቀሰም፡፡ ነገር ገን የሮማውያን የክረምት አጋማሽ ስጦታ የመስጠት ከፍተኛ ፍላጐት ስጦታዎችን የመግዛት ግርግር እንዲኖር ግድ ይላል፡፡ የገንዘብ ፍቅር ሰብዓ ሰገል ስጦታቸውን ለመስጠት ወደ በረት ገብተዋል የሚል ወሬ ፈጥሮ አሰራጭቷል፡፡ በአሁኑ ዘመን የገና ስጦታ ትልቅ የንግድ ትርፍ ማግኛ ዘዴ ነው፤ ስለዚህ ጥሩ ክርስቲያኖች እንኳ ስጦታ ስለመግዛት ማመካኛ ሲፈልጉ ሰብዓ ሰገል ስጦታ ለመስጠት ወደ በረት ውስጥ ገብተዋል በሚለው ፈጠራ ሊያምኑ ችለዋል (ነገር ግን ይህ የሳተርናሊያ ልማድ ነው፤ ዲሴምበር 23 የሳተርናሊያ የመጨረሻ ቀን እንደመሆኑ ስጦታ መለዋወጫ ቀንም ነው)፡፡
ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል (ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት እንደገቡ) አያውቁም፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውን ያውቃሉ፡- ማለትም ሰብዓ ሰገል ወደ በረት እንደገቡ፤ እንዲሁም ሰብዓ ሰገል ሦስት እንደነበሩና ስማቸውም መልኪዮር፣ ጋስፓር እና ባልሳዛር እንደነበር፡፡ ይህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡
የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን (ሎዶቂያ) እውር ተብላ ብትጠቀስ ያስደንቃል? (ሎዶቂያ ማለት የሰዎች መብት ማለት ነው)፡፡
ራእይ 3፡14-17 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡-
በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ።
እንዲሁ ለብ ስላልህ…
ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
እውር ማለት ከአሕዛብ የመጡ ልማዶችን እየተከተልን መሆናችንን ማየት አልቻልንም ማለት ነው፡፡
የተራቆትህ፡፡ ለዚህ ዘመን ገላን የሚያጋልጥ የአለባበስ ፋሽን የሚከፋ አገላለጽ አይደለም፡፡
የሰዎች መብት፤ የፈለጉትን የማግባት መብት፡፡ ያ ሰው ከራስ ፆታ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም እንኳ፡፡
በአሁኑ ወቅት ሰዎች እንደፈለጉት ሆነው የመኖር መብት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን ማንኛውንም ዓይነት ገደብና ሕግ አይፈልጉም፡፡ ሌላው ቀርቶ ማምለጥ እንችላለን ብለን ካሰብን የትራፊክ ሕግን ለመታዘዝ እንኳ አንፈልግም፡፡ ሰዎች ጠጥተው መኪና መንዳት ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም በመንገዶቻችን ላይ በክሪስማስ ወቅት ብዙ ቤተሰቦች በመኪና አደጋ ወገኖቻቸውን አጥተው በሃዘን ይቀመጣሉ፡፡
እንዴት መኖርና እንዳለብን ሊነግረን መብት ያለው እግዚአብሔርስ?
ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ነው ወይ የቆምነው?