የክርስቶስ ተቃዋሚ በመጀመሪያዎቹ 800 ዓመታት ውስጥ እንዴት እንዳደገና እንደተከናወነ - ክፍል 2

ራእይ 9፡2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።
3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው
4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።

 

ፍጥረታዊ አንበጦች የሚበሉት አረንጓዴ ተክሎችን ነው፡፡ አውዳሚ የሚያሰኛቸውም ይኸው ነው፡፡ እነዚህ ግን ፍጥረታዊ አንበጦች ሳይሆኑ አጋንንታዊ የጥፋት ኃይሎች ናቸው፡፡ በሕጻናት የኮሚክ መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ገጸባህሪያት ምን ያህል ሰይጣናዊ ገጽታ እንዳላቸው አስተውላችኋል? ይህ በእኛ ዘመን ጥልቁ የሲዖል ጉድጓድ መከፈቱን የሚያመለክት ማስረጃ ነው፡፡ የክፋት ኃይሎች ተፈትተው ተለቀዋል፡፡ እጅግ ክፉና ምህረት የለሽ የሆኑትን የጅሃድ አሸባሪዎች ተመልከቱ፡፡

 

ራእይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።
ንጉስ ዘውድ ይደፋል። ጳጳሱ ባለ ሦስት ተደራቢ ዘውድ ይደፋል።
ራእይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፡- ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።

 

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እናት ቤተክርስቲያን ናት። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ደግሞ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደ መውጣታቸው የሮማ ካቶሊክ ልጆች ናቸው፡፡

 

ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፡- እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።

 

ስለዚህ ፕሮቴስታንቶች ልክ እንደ ሮማ ካቶሊኮች ሁሉ የሰው አመራርና ልማዶችን ይመርጣሉ፡፡

ዳንኤል ያየው የአህዛብ ምስል የወርቅ ራስ የነበረው ሲሆን ይህም በታላቁ መሪያቸው በናቡከደነፆር የሚተዳደረው የባቢሎን መንግሥት ነው፡፡ ባቢሎን በሜዶናውያንና በፋርሶች አማካኝነት ከፈረሰች በኋላ የባቢሎን ሐይማኖታዊ ምስጢሮች ወደ በጴርጋሞን ከተማ ተዛውረዋል፡፡ በዚያም በፋርሶች መንግሥት(የምስሉ ደረትና ክንዶች) በኩል እንዲሁም በግሪኮች (የምስሉ ሆድና ጭኖች) መንግስት በኩል የባቢሎን ሐይማኖታዊ ምስጢር ከተላለፈ በኋላ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ133 የሮማ አገዛዝ አካል ሆኑ፤ በዚያም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዩሊየስ ቄሳር ፖንቲፍ ወይም ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ተብሎ ለመሰየም መንገዱን በጉቦ አማካኝነት አስተካከለ፡፡ ይህ ማዕረግ ቴዎዶሲየስ በ378 ዓ.ም. ንጉሰ ነገስት በሆነበት ጊዜ እስኪያስወግደው ድረስ የሮማ ንጉሰ ነገስቶች ሲጠሩበት ቆይተዋል፡፡ ቴዎዶሲየስ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ስላሰበ ንጉሰ ነገስትና የአረማዊያን ሊቀ ካህን ተብሎ መጠራትን አልተቀበለም፡፡

በጳጳሱ ሊዮ ጊዜ (ወደ 450 ዓ.ም. አካባቢ) ይህ ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ወይም ፖንቲፍ የሚለው ማዕረግ የጵጵስና አንዱ ክፍል ለመሆን የበቃ ሲሆን የዚህም ምክንያት የሮማን ግዛት እየተቆጣጠሩ በነበሩት አረማውያን መካከል ለጳጳሱ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ዳንኤል በሕልም ወዳየው የአሕዛብ ሃውልት ምስል ስንመለስ የባቢሎንን ምስጢራት የወረሱት የሮማውያን የብረት እግሮች ኋላ የብረት (የባቢሎን ምስጢር ማለትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን) እና የሸክላ (ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ክርስቲያኖች) ቅልቅል የሆኑት የቤተክርስቲያንን የ2000 ዓመታት ታሪክ ይወክላሉ። ይህም ታሪክ አንድ ድንጋይ (የኢየሱስ ዳግም ምጽአት) የምስሉን እግር እስኪመታው ድረስ ይዘልቃል።

የኢጣሊያ ካርታ የቅልጥም ቅርፅ ያለው ሲሆን የሲሲሊ ደሴት ደግሞ የዚህን እግር ጣቶች ሊመታ የተዘጋጀ ይመስላል። ዳንኤል በሕልም ካየው ምስል ጋር የሚገጣጠም መልክአ ምድር ይህ ሃገር ነው፡፡

map-italy

የሮም መንፈስ መሪን ከፍ ከፍ ማድረግ እና ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ የሰዎች ልማዶችን እንዲከተሉ ማድረግ ነው፡፡

የገና በዓል፣ ዲሴምበር 25፣ የገና ዛፍ፣ የፋሲካ እንቁላሎች
ሰው የቤተክርስቲያን መሪ በሆነበት ሁሉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የሰዎችን ወግ እና ልማድ መከተል ይመርጣሉ። በካቶሊክ እምነት ሁሌም ቤተክርስቲያንን የሚቆጣጠር አንድ ሰው ወይም ካህን አለ። ካህናትን የሚቆጣጠር ደግሞ ኤጲስቆጶስ፤ ከኤጲስቆጶሳት በላይ ካርዲናሎች፤ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ዋናው አለ፡፡ ሥላሴ በአረማውያን ዘንድ ዋነኛ እምነት ነበረ፡፡ ይህ በአብዛኛዎቹ የጥንት አረማውያን ዘንድ ዋነኛ የነበረ እምነት ሲሆን ጳጳሱም ይህንን እምነት በመቀበል የካቶሊክ እምነት በባርቤሪያውያን ዘንድ የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖረው አደረገ በስርዓተ ቅዳሴ ሰዓት (ፕሮቴስታንቶች ሕብረት ወይም የጌታ እራት የሚሉት) ካህናቱ ብቻ ወይኑን ይጠጣሉ፡፡ ሕዝቡ ቀጭን ክብ ቂጣ ይበላሉ (ግብጽ ውስጥ ይህ ክብ ቂጣ “ራ” ወይም “አሞን ራ” የተባለው የፀሐይ አምላክ ምልክት ነበር)፤.ነገርግን በፋሲካ እራት ጊዜ ኢየሱስ ዳቦ ነው የቆረሰው ፡፡

ከክርስቶስ ልደት 133 ዓመታት በፊት የሮማ ግዛት ብዙም ትልቅ አልነበረም፡፡ ካርታው ላይ አረንጓዴዎቹ ቀለሞች የሮማ ግዛት ምን ያህል እንደነበረ ያሳያሉ፡፡

IMG_5384 (Small)

በመቀጠልም በትንሽዋ እስያ ዉስጥ የሚገኘዉ የጴርጋሞን ግዛት ንጉስ አታለስ 3ኛው ሲሞት ግዛቱን ለሮም ሰጠ፡፡ ይህም የሮማን ግዛት በቆዳ ስፋት እጅግ ከማሳደጉ በላይ የጴርጋሞን አካባቢ በሃብት የበለጸገ እደ,ንደመሆኑ ሮምን እንድትበለጽግ አስችሏታል፡፡

 

ራእይ 12፡3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥

4 ጅራቱም (በራዕይ ላይ የተጠቀሰው ጅራት ሰዎችን ለማታለል የሚጠቀምበት ተረት ነው) የሰማይን ክዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው (ሦስት ዓይነት ስዎች አሉ፡- አይሁድ፣ አሕዛብና በከፊል አይሁድ በከፊል አሕዛብ የሆኑ ሳምራውያን፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚለው ቃል የሚያመላክተው አይሁድን ሲሆን ዲያብሎስ ሮምን ተጠቅሞ መሲሁን ገደለ፤ አይሁድም ኢየሱስ እንዲሰቀል አጥብቀው በመለመን እና ከሮም ጋር በመስማማት ዘላለማዊ ሕይወትን አጥተዋል፤ ስማቸው ከሕይወት መጽሐፍ ተሰርዞባቸዋል፡፡)፤ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻንዋን እንዲበላ (ሔሮድስ ኢየሱስን ለማጥፋት ብሎ ብዙ ሕጻናት እንዲገደሉ አዘዘ) ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ (ሮም ወደ እሥራኤል መጥታ በቅኝ ግዛት የተቆጣጠረቻት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዓመት ነበር)።

 

የጴርጋሞን ግዛት ወደ ሮም ግዛት ከተቀላቀለ በኋላ ታላቁ ፖምፔይ የተባለው ሮማዊ ጀነራል ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ66 እስከ 63 ባሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ የምስራቁን ክፍል ድል ለመንሳትና ለመግዛት በጳንጦስ፣ ሲሊሺያ በኩል (በአሁኑ ጊዜ ቱርክ ተብላ የምትታወቀው) እና ሶሪያ (ፍልስጤምን ጨምሮ) በማለፍ ገሰገሰ፡፡ እንዲህ ባለ መንገድ ሮም ፍልስጤምን ከተቆጣጠረች በኋላ ዘንዶው (ሮም) ኢየሱስ በተወለደበት ጊዜ ሊገድለው ተዘጋጅቶ ሲጠባበቅ ነበር፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዓመት ዩልየስ ቄሳር ፖንቲፌክስ ማክሲመስ (የባቢሎን ምስጢራት ሊቀ ካህን) ከሆነ በኋላ በሮም ውስጥ ብቻውን አንባገነን መሪ ለመሆን ፖንፔይንና ግብፅን አሸነፈ፡፡

IMG_5393 (Small)

የሮማው ጄነራል ፖምፔይ በካርታው ላይ የሚታዩትን ቀያዮቹን ክልሎች ወደ ሮም ግዛት ቀላቀላቸው፡፡
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዓመት ሮም ልክ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ፍልስጤምን ተቆጣጠረች፡፡
የሮም መንፈስ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያንም ሆነ ለሃገር ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ አንድ መሪ መሾም ነው፡፡
ሄሮድስ ቄሳርን ስለረዳው ለውለታው ምላሽ ቄሳር ሄሮድስን የአይሁድ ንጉስ አድርጐ ሾመው፡፡
ሄሮድስን የአይሁድ ንጉስ አድርጐ የሾመው ቄሳር ነው፡፡ ስለዚህ ሔሮድስ የአይሁድ ንጉስ ሆኖ ስለሚወለደው መሲህ ሲሰማ እጅግ ተደናገጠ፡፡ ለሥልጣኑም ስለሰጋ ኢየሱስን ለመግደልና ለንግስናው ተቀናቃኝ የሚሆንበትን ለማስወገድ ቆርጦ ተነሳ፡፡

 

ማቴዎስ 2፡16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

 

የባቢሎን ምስጢራት በመጀመሪያ ወደ ጴርጋሞን በመቀጠልም ወደ ሮም ገቡ፡፡
ዩልየስ ቄሳር ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዓመት ፖንቲፍ ወይም ጳጳስ ሆነ፡፡

 

ዳንኤል 7፡7ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።

 

IMG_7169 (Small)

ዳንኤል 7:8 ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ፤ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት። (የእግዚአብሔረ ቃል ሳይሆን የሰዎች ጥበብና ወግ)

IMG_7166 (Small)

ንጉሰ ነገስቱ ቴዎዶሲየስ በ395 ዓ.ም. ሲሞት መንግስቱን በሁለት ልጆቹ መካከል አካፈለ፡፡ በመንግስቱ ምዕራባዊ ክፍል ሮም ዋና ከተማ ሆነች፡፡ በምስራቁ ግዛት ደግሞ ኮንስታንቲኖፕል ዋና ከተማ ሆነች። ይህም ዳንኤል በህልሙ ያያቸውን ሁለቱን የሮም የብረት እግሮች ይወክላል፡፡

በቻይና ውስጥ የተፈጠረ ብጥብጥ ሚሊዮኖችን እንዲሰደዱ አደረገ፡፡ እነርሱም ከሃኖች ጋር ተጋጩ፤ ሃኖች ደግሞ ወደ ምዕራብ ተገፍተው ከእስያ ወጥተው ከሮማውያን ጋር እስኪላተሙ ደረስ ተሰደዱ። በዚህም ሌሎች ጎሳዎች ከሮም ጋር ተጋጭተው መሬት ማግኘት እና ሃብት መዝረፍ እንደሚችሉ ሲያውቁ ሮም ግዛት መፈራረስ ተጀመረ።

አቲላ በ 433 ዓ.ም. የሃኖች ንጉስ እንደሆነ፤ የመጀመሪያ እርምጃው እስያ አይታ የማታውቀው አይነት እጅግ ኃያልና አስፈሪ ሰራዊት ለመመስረት እንዲያስችለው ሕዝቦቹን ወደ አንድነት ማምጣት ነበር፡፡

አቲላ በ441 ዓ.ም. በሮም ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀመረ፤ ከዚያም በ453 ዓ.ም. እስኪሞት ድረስ በማውደምና በማጥፋት በጦርነት ተግባሩ ቀጠለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሃኖች በርካታ የጀርመን ጐሳዎችን ወደ ሮም ግዛት አሳደዱዋቸው፡፡ እነዚህ የጀርመን ጐሳዎችም ሃኖችን በመፍራት ከፊታቸው እየሸሹ ከሮማውያን ጋር መዋጋትን መርጡ፡፡

ብዙ ሌሎች ባርቤሪያን ነገዶች ምግብ፣ ገንዘብ እና መሬት ፍለጋ የሮማን ግዛት ወረሩ፡፡ ከሃኖች በኋላ የሮማን ግዛት በመከፋፈል ሌሎች ዘጠኝ ነገዶች የተሳተፉ ሲሆን፤ እነሱም ግዛቱን ከመቀራመት አልፈው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንድታንሰራራም ዋነኛው ሚና ተጫውተዋል፡፡

ዳንኤል በሕልሙ የሮማን ግዛት በጨካኝ አውሬ ተመስሎ ነበር ያየው፡፡ አውሬው አንድ ራስ እና አስር ቀንዶች ነበሩት፡፡ አስሩ ቀንዶች የሮማን ግዛት የሚቀራመቱት አስር የባርቤሪያን ነገዶችን የሚወክሉ ሲሆን እነዚሁ አሥር ነገዶች ለሮማ ካቶሊክን መነሳት ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ሦስት ቀንዶች ከተሰበሩ በኋላ በተነሳው ትንሽዬ ቀንድ ተወክላለች፡፡

የሄሩሊ ነገድ በኦዶዋሰር መሪነት በ476 ዓ.ም. ሮምን ድል አደረገ፤ ነገድ ግን እነርሱ አሪያን እንጂ ትሪኒታሪያን (በሥላሴ የሚያምኑ) አልነበሩም፡፡

ኦስትሮጎቶች፣ ሄሩሊዎች እና ቫንዳሎች ሁሉም በሥላሴ አያምኑም ነበር፡፡ በኮኒስታንቲኖፕል የተቀመጠው ንጉሰ ነገሥት የኦስትሮጎቱን ቲዮዶሪክ ሄሩሊዎን ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው ጠየቀው፡፡ ቲዮዶሪክም ከ489 ዓ.ም. ጀምሮ ኦዶዋሴርን እስከገደለበት 493 ዓ.ም. ድረስ እንደታዘዘው ሄሩሊዎችን ጨፈጨፈ፡፡ ሄሮሊዎችም ከምድር ገጽ ተወገዱ፡፡ ይህም የመጀመሪያው ቀንድ ተሰበረ ማለት ነው፡፡ ይህ በሥላሴ የማያምን ነገድ የተወገደው ጳጳሱ በሥላሴ ማመንን ለማስፋፋት የነበረውን ሃይማኖታዊ ዓላማ ያደናቅፍ ስለነበረ ነው፡፡

ሄሩሊዎች

Heruli

በዚህ መንገድ የመጀመሪያው በሥላሴ የማያምን ነገድ ከምድር ገጽ ተወገደ፤ ማለትም ከሦስቱ ቀንዶች አንዱ ከሥሩ ተነቀለ፡፡

ነገር ግን ኦስትሮጎቶችም በሥላሴ አያምኑም ነበር፤ በሰሜን አፍሪካ የሚኖሩት ቫንዳሎችም በሥላሴ አያምኑም ነበር፡፡

የኦስትሮጎቱ ቲዮዲሮክ ሲሞት በኮንስታንቲኖፕል የሚኖረው የሮማ ንጉሰ ነገስት በሥላሴ የማያምኑትን ኦስትሮጎቶች ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ፈለገ። ኢጣሊያን በቀጥታ ማጥቃት አልቻለም ምክንያቱም በመንገዱ ላይ ብዙ አስቸጋሪ ተራሮች ነበሩ፡፡ አሜሪካውያን በ2ኛው የዓለም ጦርነት እንዳደረጉት በመጀመሪያ ሰሜን አፍሪካን ለማንበርከክ ከዚያም ከሰሜን አፍሪካ ተነስቶ ኢጣሊያን ለመውረር ጄኔራል ቤሊሳሪየስን ከኮንስታንቲኖፕል ላከ። ጀነራል ቤሊሳሪየስም ሰሜን አፍሪካ ሄዶ በ533 እና 534 ዓ.ም. መካከል ቫንዳሎችን ከምድረ ገጽ አጠፋ፡፡

 

ቫንዳሎች

vandals

ጄኔራል ቤሊሳሪዬስ በመጀመሪያ ሰሜን አፍሪካን መቆጣጠር እና ከዚያ በመነሳት ወደ ኢጣሊያ በባህር ተሻግሮ ኦስትሮጎቶችን የማንበርከክ ስልት ነደፈ፡፡ እግረ መንገዱን በሥላሴ የማያምኑ ቫንዳሎችንም አጠፋቸው፡፡ ስለዚህ ጳጳሱን በኢጣሊያ ውስጥ የሃይማኖት መሪ ለማድረግ ሲባል ሁለተኛውም ቀንድ ተነቀለ፡፡

በመቀጠልም ቤሊሳሪየስ ኢጣሊያ ውስጥ የሚገኙትን በሥላሴ የማያምኑ ኦስትሮጎቶችን ለመውጋት በባሕር ተሻገረ።

 

ኦስትሮጎቶች

Ostrogoths

ከዚያ በመቀጠል ከ535 እስከ 554 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ኦስትሮጎቶችን ለማጥፋት ለ20 ዓመታት ተዋጋቸው፡፡
በሥላሴ የማያምኑት ኦስትሮጎቶች ጳጳሱን በኢጣሊያ ውስጥ ኃላፊ እንዲሆን ተዉለት። ቤሊሳሪዬስም በሰሜን አፍሪካ እና በኢጣሊያ ላይ ስኬታማ ወረራ አደረገ፡፡

ቤሊሳሪየስ ቫንዳሎችን እና ኦስትሮጎቶችንም ሙሉ በሙሉ አጠፋቸው። ስለዚህ በሥላሴ የማያምኑት ሦስቱም ነገዶች ጠፍተዋል፡፡

እንግዲህ ከዚህ ወዲያ የሥላሴ አስተምህሮ ያለ ምንም ተቀናቃኝ በጳጳሱ አማካኝነት ሊስፋፋ ይችላል፡፡
ከዚያም ሎምባርዶች ኢጣሊያን ወረሩ፡፡ በኮንስታንቲኖፕል የተቀመጠው ንጉሰ ነገስት ሎምባርዶችን ለመመከት የሚያስችል አቅም አልነበረውም፡፡

 

ጳጳሱ ፊቱን ወደ ፍራንኮች አዞረ፡፡ ሎምባርዶችን ካሸነፈለት ፒፕንን የፍራንኮች ንጉስ አድርጎ እንደሚሾመው ቃል ገባ። ፒፒንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ውለታ የሰራ መስሎት ሎምባርዶችን አሸንፎ ከሮም ዙሪያ ያለውን መሬት ለጳጳሱ አስረከበ፡፡ በመሆኑም ጳጳሱ በከፊል ኢጣሊያ ላይ ፖለቲካዊ ስልጣንን አገኘ፡፡ ስለዚህ ሦስቱ በሥላሴ የማያምኑ ቀንዶች (ባርቤሪያን ነገዶች) ከስራቸው ተነቀሉ (ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ)፤ መወገዳቸውም ትንሹ ቀንድ (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን) በስልጣን እንድትገለጥና ሥላሴ መኖሩን እና ቤተክርስቲያንን አንድ ሰው ብቻውን መቆጣጠር እንዳለበት ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን ጨምሮ ሁሉን እንድታሳምን መንገድ ከፈተላት፡፡

ትንሽ ቀንድ የሚወክለው በመጠን ትንሽ የሆነ ስልጣንን ነው፡፡

ቫቲካን በምድር ላይ አንድ ኪሎ ሜትር ካሬ ስፋት ያላት እና ከአንድ ሺህ በታች ዜጎች ያሏት ከአለም ትንሿ ሃገር ናት፡፡

ለማይክል ኤንጅሎ አስደናቂ የሥዕል ክህሎት ምስጋና ይግባውና ቫቲካን ውስጥ የሚገኘው የሲስታይን ጸሎት ቤት በዓለም ላይ ከሚገኙ እጅግ ታዋቂ የጸሎት ቤቶች አንዱ ነው፡፡ በስነ-ጥበብ ስም ሰውነትን አጋልጠው እርቃንን የሚያሳዩ አለባበሶች እና ራቁትነት ከፍተኛ ቦታ የተሰጣቸው ሲሆን ይህም ዳንኤል በሕልሙ ያየውን ምስል እንዲሁም በእርቃን ገላ እና በሃውልቶች የሚመሰጡትን የግሪኮች ተጽእኖ ያመለክታል።

 

ዘሌዋውያን 26፡1ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ

 

የኒቂያ ጉባኤ የተካሄደው በ325 ዓ.ም. ሲሆን በዚህ ወቅትም ንጉሰ ነገስት ኮንስታንቲን እራሱን የቤተክርስቲያን ራስ በማድረግ አውጇል፡፡ እርሱም ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ በሚኖርበት ጊዜ በሮም ውስጥ የተቀመጠው ጳጳስ በሮም ውስጥ ቀኝ እጁ ይሆንለት ዘንድ ፖለቲካዊ ስልጣን እና ብዙ ገንዘብ ሰጠው፡፡ በዚህ የኒቂያ ጉባኤ ላይ ስላሴን (በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል) የቤተክርስቲያኗ ይፋዊ አስተምህሮ እንዲሆን ተደረገ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉባኤው ለትንሳዔ በዓል ከአይሁድ የፋሲካ በዓል ቀን ጋር የማይገጥም ቀን መርጦ አጸደቀ፡፡

 

ራእይ 13፡2ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።

 

ንጉሰ ነገስት ኮንስታንቲኖፕል ለሮሙ ሊቀጳጳስ የሰጠው የላተራን ቤተመንግስት እስከ አሁን ድረስ የሮም ጳጳሳት ይፋዊ መቀመጫ ነው፡፡ በዚህ ቤተመንግስት ውስጥ ከኢጣሊያ አምባገነን መሪ ከሙሶሊኒ ጋር በ1929 በተፈረመው ስምምነት ቫቲካን እራሷን የቻለች መንግሥት እንድትሆንና ከቫቲካን ከተማ ውጭ የላተራን ቤተመንግስት እና ባሲልካ ከግዛቶቿ እንዲቆጠሩላት ተደርጓል፡፡

ስለ ሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አነሳስ እና በአለም መድረክ ላይ እንዴት ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን እንደቻለች እስኪ በአጭሩ እንመልከት፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ጳጳሱ የቤተክርስቲያን ራስ ነው በማለት የታወጀው በጳጳሱ ሊዮ አንደኛው ከ440-461 ዓ.ም. ሲሆን ይሁን እንጂ ይህ ስልጣን እውቅና ያገኘው በ1200 ዓ.ም. በኤነሰንት ሦስተኛው ጊዜ ነበር፤ እርሱም የጴጥሮስ ወራሽ በመሆን ሁሉንም ከፍተኛ ስልጣኖች ለራሱ ጠቅልሎ ያዘ፡፡

ብዙውን ጊዜ በጳጳሳቱ ፖለቲካዊ ዓላማዎች እና በመጋቢነት አገልግሎታቸው መካከል ግጭት ይፈጠር ነበር። በኃይል አንበርክከኸው ግዛቱን ለመውሰድ ሙከራ እያደረክ ሳለ ወንድምህን እንደራስህ አድርገህ መውደድ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

የጳጳሱን ከፍተኛ ስልጣን ለማጠናከር ትልልቅ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ መዋቅሮች ተዘረጉ፡፡ በ500 ዓ.ም. አካባቢ ይህ ሃይማኖታዊ-ፖለቲካዊ ስርዓት ለጳጳሱ የበለጠ ስልጣን ለመስጠት የሚያስችል ሆኖ በተገኘበት ጊዜ የሮሙ ጳጳስ የቤተክርስቲያን መሪዎች የሚጠሩበትን “ፓፓ” የሚለውን ማዕረግ ለራሱ ብቻ ወሰደ፡፡ በዚህ ማዕረግ መጠራት ሁሌም የሚቻል አልነበረም፤ ምክንያቱም በ1075 ዓ.ም. እንኳ ግሪጎሪ 7ኛው አንድ ጳጳስ ብቻ አለ ብሎ ይሟገት ነበር።
ሮም የተነሳችባቸው አጋጣሚዎች አብዛኞቹ ድንገተኛ እና ያተጠበቁ እንዲሁም ከጳጳሱ ቁጥጥር ውጭ ነበሩ። ደግሞም ብዙዎቹ አጋጣሚዎች እርስ በርሳቸው ያልተዛመዱ እና ለአንዳንድ ክስተቶች የሚሰጡ ምላሾች ብቻ ነበሩ።

የሮማ ቤተክርስቲያን አስገራሚ ባሕርይዋ በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ እራሷን እያመቻቸች የመቆየት ችሎታዋ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቀር እያደገ ሲመጣ ድንገተኛ የሆኑ ለውጦቿን እና ያልተያየዙ ክስተቶችን እንደ ሰንሰለት የተያያዙ እና ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሚያያይዙዋቸው ክስተቶች ተደርገው መተርጎም ጀመሩዝባቸው ፍቺ ነበራቸው ፡፡

የሮም ቤተክርስቲያን የሮማ ግዛትን ከሚያስተዳድሩ ንጉሰ ነገስቶች ጋር ለመስማማት ፈጣን ነበረች፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ የሮም መንግስትን አወቃቀር በቀላሉ ኮርጃለች። (ኒኮላይታኒዝም ማለት አንድን ቅዱስ ሰው እስኪመለክ ድረስ ከፍ ከፍ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህም ቄሳር ይመለክበት የነበረና ንጉሰ ነገስቶች እንደ አምላክ ይታዩ የነበረበት ሥርዓት ነው፡፡ የገዢውን ሥልጣን ለመደገፍ እጅግ የተወሳሰቡ ሥርዓቶች ይከናወናሉ፡፡ በቫቲካን ውስጥ በታላቁ መሰዊያ ላይ ከሚደረገው ከታላቁ ሥርዓተ ቅዳሴ ይበልጥ የተወሳሰበ ሥርዓት ለማግኘት ይቅርና ለማሰብ እንኳ አይቻልም፡፡ የሮማ ቤተክርስቲያን ጣዖት አምላኪዎች በቀላሉ እንዲቀበሏት የእነርሱን ልማዶች በፍጥነት ተቀበለች፤ አመጣጧንም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ለማያያዝ ብላ ሐዋርያዊ መተካካት የሚባል ሃሳብ ፈጠረች፤ በዚህም የተነሳ ማንም ሊቀናቀን የማይችለውን ክብር ለራሷ ወሰደች።)

የሮማ አገዛዝ በ476 ዓ.ም. በወደቀ ጊዜ ሮም ከጀርመን መንግስት ፖለቲካዊ የስልጣን ሽኩቻ እንዲሁም በ1400 ዓ.ም. አካባቢ ከተነሱት ብሔራዊ መንግስታት ጋር እራሷን አዛመደች፡፡ ዛሬ ደግሞ ከእስያ እና ከአፍሪካ እንዲሁም ከደቡብ አሜሪካ ዘመናዊ የሦስተኛ ዓለም ሃገሮች ጋር እራሷን እያጣጣመች ናት፡፡ የሮማ ቤተክርስቲያን በየዘመናቱ ራሷን እያስተካከለች በመዝለቅ ዝናን አትርፋለች፡፡
በ325 ዓ.ም. የሮሙ ሊቀጳጳስ ብዙም ትልቅ ስም አልነበረውም፡፡

ጵጵስናው የተጀመረው የሮሙ ጳጳስ ከጳጳስ የበለጠ መሆን ሲጀምርና ከመጀመሪያው የሮም ግዛት ጳጳስ የበለጠ ስልጣን ሲያገኝ ነው፡፡
ኦስትሮጎቶች ሮምን ይገዙ የነበሩትን በሥላሴ የማያምኑትን የሄሩሊ ነገዶች አጠፉ፡፡ ከ533-554 ዓ.ም. እጅግ ከፍተኛ ብቃት የነበረው ጀነራል ቤሊሳሪየስ በሰሜን አፍሪካ ውስጥ የነበሩትን ሚገኙትን ቫንዳሎች እና በኢጣሊያ ውስጥ የሚኖሩትን አስትሮጎቶችን አጥፍቷቸዋል፡፡ እነዚህ ሶስቱ የአሪያን ነገዶች በሥላሴ አላመኑም ነበር፡፡ በእነዚህ ነገዶች መጥፋት በሮማ ቤተክርስቲያን ላይ የነበረ መንፈሳዊ ተቃርኖ ተወገደ፡፡

ከ600-700 ዓ.ም. የሜዲትራኒያን ስልጣኔ ፈጽሞ የሚወድቅ እና ቤተክርስቲያኒቱንም ወደ ኪሳራ ይዟት የሚወርድ ይመስል ነበር። ይህም ቤሊሳሪዬስ ባካሄዳቸው ጦርነቶች አስከፊ ውጤቶች ምክንያት ነበር፡፡ አንዳንድ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት ቤሊሳሪየስ ባካሄዳቸው ጦርነቶች ወደ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ገድሏል፤ ከዚያም ተከትሎ የተከሰተው ረሀብ እና ወረርሽን ተጨማሪ 85 ሚሊዮን ሰዎችን ፈጅቷል፡፡ ይህም አሰቃቂ ክስተት የጨለማውን ዘመን በር ከፍቶ ተቀበለው፡፡ በዚህ ምክንያት አውሮፓ ከረጅም ዘመን በኋላ ተመልሳ እስክታገግም ድረስ ቀዝቃዛ፣ ጨለማ እና ቆሻሻ ሆና ቆየች።
ይህ የጨለማው ዘመን ቀውስ ሲሚያልፍ ጵጵስናውም በአውሮፓ ውስጥ ትልቅ የለውጥ ተጽእኖ ይዞ እንደመጣ ተቋም ብቅ አለ፡፡

በ1929 በተከሰተው ታላቅ የኢኮኖሚ ቀውስ ኪሳራ ሁሉም ላይ ሰጋት አምጥቶ ነበር። ቢሆንም ግን በዚሁ ጊዜ ነው በላተራን ከሙሶሊኒ ጋር በተፈረመ ስምምነት ቫቲካን ነጻነቷን ያገኘችው። ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እውቅና በመስጠት (የዳንኤል ሕልም ውስጥ የተገለጠው ታናሽ ቀንድ) ዓለም በሙሉ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ ወደቀች። ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን መሪነት መቀበል ለሚያስከትለው መንፈሳዊ ኪሳራ ተምሳሌት ነው፡፡ የሮማ ቤተክርስቲያን ወደ ስልጣን የመጣችበት ወቅት የጨለማው ዘመን ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ሮም ዓለምን ወደ ጨለማ እንድትመራ ተመድባለች፡፡
ማስረጃ ስለሌለ እና ብዙ ግምት ብቻ በመኖሩ የተነሳ ስለ ሮማ ቤተክርስቲያን መነሻ በግልጽ ባይታወቅም ይህች ቤተክርስቲያን ግን እንዴት ነገሮችን ተቋቁማ መቀጠል እንዳለባት ታውቅበታለች፡፡

በ49 ዓ.ም. ከአይሁድ መካከል ክርስቲያኖች ነበሩ። ጳውሎስ ከ61-63 ዓ.ም. ድረስ በሮም ጎብኝቷቸዋል፡፡ ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ ባይኖርም ጳውሎስ በ67 ዓ.ም. ሮም ውስጥ ነው የተገደለው ተብሎ ይታመናል፡፡

ሮም በ64 ዓ.ም. በተቃጠለችበት ጊዜ ኔሮ ክርስቲያኖቹን እና አይሁዶችን ተጠያቂ በማድረግ አይሁዶችን እና ክርስቲያኖችን (ክርስትና የአይሁድ እምነት ቅርንጫፍ ነው ብሎ አስቦ) በጭካኔ በማሳደድ ቤተክርስቲያንን ፈጽሞ አጠፋት ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ጥቃት አደረሰባቸው፡፡
በ36 ዓ.ም. አካባቢ ጁኒየስ እና አድሮኒከስ (ሮሜ 16፡7 አንድራኒቆስ እና ዩልያን) ወንጌልን ወደ ሮም ይዘው ሄዱ፡፡

በአይሁዶች መካከል ያለማቋረጥ ይደረግ የነበረው ክርክር እስከ 54 ዓ.ም. ድረስ በክላውዲየስ ዘመን ለ13 ዓመታት እንዲባረሩ አድርጓቸዋል።

የመጀመሪያዎቹ የክርስቲያን ቤተክርስቲያኖች ትንንሽ ማህበራት ሲሆኑ የነበራቸውንም ስልጣን በጋራ ይጠቀሙ ነበር፡፡

በ100 ዓ.ም. አካባቢ የመጨረሻው ሐዋርያ ዮሐንስ ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላም የሰዎች ስህተት ቀስ በቀስ ወደ ቤተክርስቲያን መግባት ጀመረ፡፡ ከ150 ዓ.ም. በኋላ ክርስቲያኖች የስልጣን ተዋረድ ላይ ማተኮር የጀመሩ ሲሆን ኤጲስቆጶስ የሚለው ማዕረግ ለሽማግሌዎች መስጠት ቀርቶ ለቤተክርስቲያን መሪዎች መስጠት ተጀመረ፡፡ ይህ ሃሳብ በምሥራቅ የሚኖሩ እራሳቸው ከማሰብ ይልቅ የሚያስቡላቸውን መሪ ሰዎች በሚፈልጉ ሰዎች ነበር የተጀመረው፡፡ ሮም ውስጥ ይህንኑ ሃሳብ ሂፖሊተስ በ200 ዓ.ም. ሮም ውስጥ ጀመረ፡፡

ከዚያም በኋላ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ለአንድ ከተማ የሚባል ሃሳብ መጣ፡፡ በዚህም ምክንያት አንዲት ከተማ ሙሉ በሙሉ በአንድ ሰው ሃይማኖታዊ ቁጥጥር ስር ወደቀች፡፡

 

ፊልጵስዩስ 1፡1  የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤

 

ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ኤጲስ ቆጶሳት ሰላምታ አቅርቦላቸዋል (ብዙ ናቸው)፡፡ እነርሱም ሽማግሌዎች ነበሩ፡፡

ወደ 220 ዓ.ም. አካባቢ ካሊስተስ የመጀመሪያው የሮም ኤጲስ ቆጶስ ጴጥሮስ ነበር የሚለውን ሐሳብ ይዞ መጣ፡፡ ጴጥሮስ ግን ወደ ሮም ሄዶ እንኳን አያውቅም፡፡ ናቡከደነፆር በምርኮ ወደ ባቢሎን በወሰዳቸው አይሁዶች መካከል እየሰራ ከባቢሎን ደብዳቤ ጽፎላቸዋል፡፡

በ240 ዓ.ም. ጴጥሮስ ክሌመንት ላይ እጁን በመጫን የሮም ኤጲስ ቆጶስ እንዳደረገውና በራሱ ወንበር ላይ እንደ ሾመው የሚጠቅስ ሐሳብ ተጀመረ፡፡ ይህንን በተመለከተ ምንም ዓይነት የታሪክ ማረጋገጫ የለም፡፡

በርካታ አነስተኛ የእምነት ክፍሎች ማቆጥቆጥ ጀመሩ፡፡ ብዙ ኑፋቄዎች ወይም የስህተት ትምሕርቶች ነበሩ፡፡ ከዚያ ሰዎች ኤጲስ ቆጶስ ብለው የሚጠሩት (በክብር ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጡት) እውነቱን የሚጠብቅላቸው መሪ እንደሚያስፈልጋቸው ይሰማቸው ጀመር፡፡

የከተሞች ኤጲስ ቆጶሳት እውነት ነው ብለው የሚያምኑትን ለማብራራት በሲኖዶስ ይገናኙ ነበር፡፡ ነገር ግን የሮም አውራጃ በውስጧ ብዙ ከተሞች ነበሩዋት። ስለዚህ እነዚህን ኤጲስ ቆጶሳት ማን ነው የሚመራቸው? የከተሞች ኤጲስ ቆጶሳት ሜትሮፖሊታን የሚባል የማእረግ ስም ከሮማ መንግስት በመኮረጅ በአውራጃ ውስጥ ያሉትን ጳጳሳት መቆጣጠር ጀመሩ፡፡

በ200 ዓ.ም. የካርቴጁ ተርቱሊያን የሐዋርያት መተካካት ማለት በሐዋርያ የጀመሩት ቤተክርስቲያኖች ብቻ እውነቱን ይዘዋል ማለት ነው አለ፡፡ ይህንን መስፈርት የሚያሟሉት ደግሞ የኢየሩሳሌም፣ አንጾኪያ፣ አሌክሳንድሪያ፣ ኤፌሶን፣ ሰምርኔስ፣ ፊልጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ፣ ቆሮንቶስ እና የሮም ቤተክርስቲያኖች ናቸው፡፡

ከነዚህ ቤተክርስቲያናት ውስጥ አራቱ ብቻ ማለትም ሮም፣ ኢየሩሳሌም፣ አንጾኪያ እና አሌክሳንድሪያ ብቻ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሊሆኑ ችለዋል፡፡

ሌሎቹ ቤተክርስቲያናት በጊዜ ሂደት ከመድረኩ ርቀዋል፡፡

በኋላ ኮንስታንቲኖፕል ስትገነባ የኮንስታንቲኖፕል ቤተክርስቲያንም ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን በቅታለች፡፡

ሮም በምዕራቡ የሮማ ግዛት ብቸኛዋ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡ ይህም ለሮም ቤተክርስቲያን በግዛቱ ግማሽ ውስጥ ተፎካካሪ ስላልነበራት ተስማምቷታል፡፡

East west empire

የምስራቅ ምእራብ ግዛት

ተርቱሊያን እንዲህ አለ፡- “ጴጥሮስ ቁልፎች ተሰጥተውታል፤ ስለዚህ እርሱ የመጀመሪያው ሐዋርያ ነው”፡፡ ይህም ጴጥሮስን የሐዋርያት አለቃ ከዚያም የሐዋርያት ንጉሥ ወደመሆን አሳድጎታል፡፡

ጴጥሮስ ሮም ውስጥ እንደነበረ እንኳን የሚገልጽ ምንም አይነት ታሪካዊ መረጃ የለም፤ ነገር ግን የሮማ ቤተክርስቲያን ለረጅም ዘመን ያለ ማቋረጥ ይህንኑ ከማወጁዋ የተነሳ ፕሮቴስታንቶች እንኳን ሳይቀሩ በአሁኑ ወቅት ጴጥሮስ ሮም ውስጥ አንደነበር ያምናሉ፡፡

በ200 ዓ.ም. አካባቢ ቪክቶር የተባለው የሮም ኤጲስ ቆጶስ ፋሲካን እንዴት ማክበር እንዳለባቸው ለትንሹ እስያ ሊነግራቸው ሞከረ፡፡

ካሊስተስ የሚባለው የሮም ኤጲስ ቆጶስ ለኃጥያት ራስን በራስ የመቅጣትን አስተምሕሮ በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ላይ ለመጫን ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ በ220 ዓ.ም. የጴጥሮስን ስልጣን ተጠቅሟል፡፡

ስቲቨን (እስጢፋኖስ) የተባለው የሮም ኤጲስ ቆጶስበ254 ዓ.ም. የጴጥሮስን ወንበር (ካቴድራ ፔትሪ) መያዙን አወጀ፤ ነገር ግን በዚያ ወቅት ቤተክርስቲን ገና ጠበቅ ባለ አወቃቀር አልተደራጀችም ነበር።

የኤጲስ ቆጶሳት መብቶች የሮም ኤጲስ ቆጶሳት እስከ ነበሩት እስከ ዳማስከስ (366-84) እና እስከ ሊዮ አንደኛው (440-61) ድረስ ብዙም አላደገም ነበር፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች የሮማ ቤተክርስቲያን መሪ ስልጣን ከፍ እንዲል ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ንጉሰ ነገስት ዴሺየስ (249-251) ክርስቲያኖችን ማሳደዱን እንደ አዲስ ጀመረ፤ እስከ 311 ድረስም አንዴ ሲያሳድድ አንዳንዴ ደግሞ ማሳደዱን ይተው ነበር፡፡ በዚህ የስደት ወቅት ሮም ዋነኛ ሰለባ ነበረች፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ዚስተስ እና ባልደረቦቹም ተገድለዋል፡፡

የፀሐይ አምላክ የልደት ቀን ዲሴምበር 25 እንዲሆን ያደረገው ኦሬሊያን (270-275 ዓ.ም.) የቤተክርስቲያን ክፉ አሳዳጅ የነበረ ሲሆን፣ ዲዮክሊቲያን ደግሞ ከ300 እስከ 311 ዓ.ም. ክርስትናን በተቀናጀ ዘዴ ለማጥፋት በወሰደው እርምጃ ብዙ ክሕደትን አስከትሏል፤ በዚህም ጊዜ ጳጳሱን ማርሴሊነስን ጨምሮ ብዙ ክርስቲያኖች እምነታቸውን ክደዋል፡፡

ከውጭ ዛቻ በበዛበት ሰዓት አንድነት መጠናከሩ፣ ሮም ለተሰደዱት ወንድሞች የገንዘብ እርዳታ በመላክ ለጋስነቷን ስላሳየች የጳጳሱ ሥልጣን ከፍ እያለ ሊሄድ ችሏል።

ኢየሩሳሌም በሐዋርያው ያዕቆብ አመራር ስር ሆና ታላቅ ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡ ነገር ግን ያዕቆብ በ62 ዓ.ም. የተገደለ ሲሆን ከዚያም በ70 ዓ.ም. ታይተስ ኢየሩሳሌምን አጥፍቷታል። ኢየሩሳሌም የሮም ዋነኛ ተቀናቃኝ ስለነበረች መጥፋቷ ለሮማ ቤተክርስቲያን ትልቅ እድልን ፈጥፎላታል፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ኢየሩሳሌም ውስጥ የምትገኘው ቤተክርስቲያን ከአመድ ወይም ከፍርስራሽ ላይ በመነሳት እንደገና ተጽእኖ ፈጣሪ ሆናለች፡፡ ያ ጊዜ እስኪደርስ ግን የሮምም ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆናለች፡፡

ሮም የሮማ ግዛት ግዛት ዋነኛ ከተማ ነበረች፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ከመንግስት ጋር በተለይም በሥልጣን ሥፍራ ካሉ ክርስቲያች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራት። ሮም ሌሎችን ቤተክርስቲያኖች ወክላ በመንግስት ዘንድ ጣልቃ የመግባት ብቃት ነበራት፡፡ ሮምብዙ ሃብት ሰበሰበች፤ ሃብቷንም ለሌሎችን ቤተክርስቲያኖችን ለመርዳት ተጠቀመችበት፡፡

በንጉሰ ነገስት ኔሮ፣ ዴሺየስ፣ እና ቨሌሪያን የግዛት የተሰዉት ሮማውያን ሰማዕታት ለሮማ ክብርን ጨምረውላታል፡፡

ልክ ከ200 ዓ.ም. በፊት የሮም ኤጲስ ቆጶስ ኢጣሊያ ውስጥ ብቸኛው ኤጲስ ቆጶስ ነበር፡፡

ከ313 ዓ.ም. ጀምሮ ግን የሮማ ኤጲስ ቆጶስ ክብር እና ተጽእኖ የማድረግ ብቃት የነበረው ቢሆንም ከኢጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ኤጲስ ቆጶስ ነበር።

ቤተክርስቲያን የተለያዩ እምነቶች እና ልምምዶችን የምታስተናግድ፣ ጠበቅ ያለ መዋቅር የሌላት ማሕበር ነበረች፡፡

ኮንስታንቲን ክርስትናን እንደ ተወዳጅ ሃይማኖት ቆጥሮ ተቀብሎታል፡፡

የሮማ ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ ብሎ ልዩ መብቶችን እና ስጦታዎችን በብዛት ሰጥቷታል፡፡

በቫቲካን ውስጥ የጴጥሮስ ጸሎት ቤት ተብሎ የሚታወቀውን ትልቅ እና እጅግ ያጌጠ ቤተክርስቲያን ገንብቷል፡፡ ጴጥሮስ ሮም ውስጥ እንደነበረ ለማሳመን ከፍተኛ የሆነ የማስታወቂያ (የህዝብ ግንኙነት) ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በ311-312 ዓ.ም. አካባቢ የላተራን ቤተመንግስትን ለኤጲስ ቆጶስ ሚልታደስ ሰጠ፡፡

ሲልቬስተር (314-335 ዓ.ም.) ከአዲሱ የጳጳሳት ቤተመንግስት አጠገብ በ314 ዓ.ም. ታላቁን የላተራን መቅደስ መገንባት ጀመረ፤ ይህም የላተራን ቤተመንግስት የሮም ጳጳስ ይፋዊ መቀመጫ ሆነ፡፡

የሮም ቤተክርስቲያን ሃብትና ንብረት ማካበት ጀመረች።

በ325 ዓ.ም. የሮማ ኤጲስ ቆጶስ በምዕራቡ የሮማ ግዛት ክፍል የንጉሰ ነገስቱ ዋነኛ ተጠሪ ወይም ተወካይ እንዲሆን ለማስቻል ኮንስታንቲን ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት እንዲደረግ አመቻቸ፡፡

ኮንስታንቲን ጨካኝ አምባገነን እና በክፋት የተሞላ ብልህ ንጉስ ነበር፡፡ መንግስቱን በንጉሳዊ ሐይማኖት ለማዋቀር ይፈልግ ነበር፡፡ ይህም ሐይማኖት የአገዛዝ መዋቅሩን አንድ የሚያደርግለት አምድ እንዲሆን ፈልጓል፡፡

ስለዚህ ቤተክርስቲያንን እንደፈለገች እንድትሆን ሊተዋት አላሰበም፡፡ ወደ አንድነት ሊያመጣት አሰበ፡፡ በ325 ዓ.ም. በተደረገው የኒቂያ ጉባዔ ላይም አርያኖች እግዚአብሔርን በሚመለከት ላነሱት ክርክር መፍትሄ ለመስጠት የራሱን ቀመር አስቀመጠ፡፡

ስነመለኮታዊ ግጭቶች በግዛቱ ውስጥ መከፋፈልን አስከተሉ፡፡ ነገስታቱም አንድነትን ያመጣል ብለው የሚያምኑትን ኃይል ሁሉ በአማራጭነት ተጠቀሙ፡፡ ጴጥሮስ ለተሰጠው ክብር ምስጋና ይግባና ሮም ከሁሉ የበላይ ሆነች፡፡

የአረማውያኑ “ፔትር ሮማ” ወይም የአማልክት ፈቃድ “ታላቁ አስተርጓሚ” የሮማው ጴጥሮስ ነው ተባለ፤ ይህም በአረማውያኖቹን ዘንድ ተቀባይነት የሚያስገኝ ሆነ፡፡

በ378 ዓ.ም. የሮሙ ኤጲስ ቆጶስ በምዕራቡ ክፍል የሚገኙ ኤጲስ ቆጶሳት ላይ ላቀረበው የሥልጣን ጥያቄ ንጉሰ ነገስቱ ግራቲያን የአዎንታ ምላሽ ሰጠው፡፡

በ379 ንጉሰ ነገስቱ ቲዎዶሲየስ ፖንቲፌስ ማክሲመስ ወይም የባቢሎናዊያን ምስጢራት ታላቁ ሊቀ ካህን የሚለውን ማዕረጉን ተወው፡፡

በ380 ቲዎዶሲየስና ሁለት ሌሎች ነገስታት ለሮማው ኤጲስ ቆጶስ የእውነተኛው እምነት የበላይ ጠባቂ ነው ብለው እውቅና ሰጡት፡፡ የሮማው ኤጲስ ቆጶስ ተከታዮችም ብቸኛዎቹ እውነተኛ የካቶሊክ ክርስቲያኖች ተብለው ተጠሩ፡፡

በ391 ቲዎዶሲየስ አንደኛው የአረማውያንን አምልኮ ያገደ ሲሆን ክርስትናም በመንግስት ዘንድ እውቅና የተሰጠው ሐይማኖት ሆነ፡፡
የሐይማኖት ጉዳዮችን በተመለከተ ቤተክርስቲያን የበላይ እንደሆነች ቲዎዶሲየስ እውቅና ሰጠ፡፡

ጀስቲኒያን (527-65) ሁለት ጳጳሳትን ከሥልጣን በማውረድ ፔላጊየስ የሚባለውንና ይህ ማዕረግ የማይገባውን ሰው ጳጳስ አድርጎ ሾመው፡፡

በ395 ሁለቱ የቲዎዶሲየስ ልጆች ግዛቱን ግማሽ ግማሽ ተካፍለው ተቆጣጠሩት፡፡ በ286 ዲዮክሌቲያን የመንግስቱን መቀመጫ ከሮም ወደ ሚላን አዘዋወረ፡፡ በሚላን የምትገኘዋ ቤተክርስቲያንም በአስደናቂ ሁኔታ ከፍ እያለች መጣች፡፡

በ402 የንጉስ መቀመጫ ወደ ራቬና ተዘዋወረ፡፡ ሮምም ወደ አውራጃ ከተማነት ዝቅ በማለት የሰሜናዊ ኢጣሊያ ግዛቶችን ለሚላን አስረከበች፡፡ ኮንስታንቲኖፕል በምስራቁ ክፍል ትልቁ ሐይማኖታዊ ባላንጣ ነበር፡፡

ዳማስከስ 1ኛው (366-84) የጳጳሱን የበላይነት ለማረጋገጥ እስከ ግሪጐሪ 1ኛው (590-604) ድረስ የቀጠለ መታገል ጀመረ፡፡ ጳጳሱ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፡፡

በ381 በኮንስታንቲኖፕል ከተማ በተደረገው 2ኛው ዓለም አአቀፍ የቤተክርስቲያኖች ጉባዔ ላይ ኮንስታንቲኖፕል ከአንጾኪያና ከአሌክሳድሪያ በላይ ተደርጋ ተሰየመች፡፡ ዳማስከስ የተባለው የሮም ጳጳስ አልተጋበዘም፤ እርሱም በ392 ዓ.ም. እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠ፡- የሮም የበላይነት በስብሰባ ውሳኔ የሚሰጣት ሳይሆን ከራሱ ከክርስቶስ ለጴጥሮስ በተሰጠው ሥልጣን አማካኝነት ነው፡፡

ዳማስከስ ሮምን የሐዋርያት ማዕከል ብሎ ጠራት፡፡ ሌሎቹን ዔጲስ ቆጶሳረወ ወንድሞች ከማለት ይልቅ ልጆች ብሎ ይጠራቸው ነበር፡፡ እራሱንም ሲጠቅስ “እኛ” የሚለውን የግርማዊነት ብዙ ቁጥር ይጠቀም ነበር፡፡

የኮንስቲኖፕል ኤጲስ ቆጶስ የነበረው የሥልጣን ጥማት ሮም የጵጵስናውን ከፍተኛ ቦታ ይገባኛል እንድትል አስገድዷታል፡፡

በ400 ዓ.ም. ሲሪሺየስ እራሱን ጳጳስ ብሎ ሰየመ፡፡

ኢነሰንት 1ኛው (401-17) “የጳጳሱ ውሣኔ በሁሉም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ላይ ተፈጻሚነት አለው” አለ፡፡

ቦኒፌስ 1ኛው (418-22) የሮማ ቤተክርስቲያን ራስ እንደሆነችና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት አባላት እንደሆኑ ገለጸ፡፡ ኤጲስ ቆጶሳትም እርሱ ላቆመው ስነስርዓት ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ገለጸ፡፡

ሮም የሮማው ጳጳስ የክርስትና እምነት ሁሉ ራስ ነው ማለቷን የኤፌሶን ጉባኤ በ431 ዓ.ም. ውድቅ አደረገ፡፡

ከዚያ በመቀጠል ስር ነቀል ለውጥ ተፈጠረ፡፡

ሊዮ 1ኛው (440-61) ፖንቲፌክስ ማክሲመስ የሚለውን ማዕረግ በመጠሪያነት የተጠቀመ የመጀመሪያው ጳጳስ ነበር ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ ማዕረግ እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን እንደገባ ግልጽ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ መጠሪያ ወደ ቤተክርቲያን ውስጥ በመግባቱ ጳጳሱ እስከዛሬ ፖንቲፍ ተብሎ ይጠራል፡፡

ሊዮ አንደኛው ጴጥሮስ የሐዋርያት እና የቤተክርስቲያን አለቃ እንዲሁም ክርስቶስን ለሚከተሉ ሁሉ አለቃ ነው ብሎ አወጀ፡፡ ቤተክርስቲያን ጳጳሱ እንደ ጴጥሮስ ሆኖ የሚሰራባት በጳጳሱ የምትገዛ ንጉሳዊ መንግስት ሆነች፡፡

ሊዮ ጳጳሱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተወካይ በመሆኑ ከሁሉ በላይ ሥልጣን አለው ብሎ ተናገረ፡፡

“የዓለም ቤተክርስቲያን በጴጥሮስ ዙፋን ስር በአንድ መሰባሰብ አለባት” (በላተራን ቤተመንግስት ውስጥ)።

በ445 ቫሌንቲንያን 3ኛው “የሮም ሥልጣን በሁሉም ላይ ገዢ ሕግ ይሆናል” አለ፡፡

ጳጳሱ በምዕራቡ ዓለም ተገዳዳሪ የሌለው ከፍተኛው ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን በምስራቁ ክፍል ኮንስታንቲኖፕል የቤተክርስቲያን መሪ ነኝ በማለቷ ገፍቶ መሄድ አልቻለም፡፡

በምስራቅ የንስጥሮስ ውዝግብን ተከትሎ አንዳንድ ወገኖች ከራሳቸው ፍላጎት በመነሳት ሮም በዓለም ቤተክርስቲያናት ላይ ሥልጣን አላት ብለው ፊታቸውን ወደ ሮም አዙረዋል፡፡

በመቀጠልም አረማውያን (ባርቤሪያውያን) መጡ።

በምዕራቡ ክፍል ሃኖች የጀርመን ጐሳዎችን ወደ ሮማ ግዛት ውስጥ አሳደዱ፡፡ ሮም በ410 በአላሪክ ተበዘበዘች፡፡ በ442 ስፔይን እና ሰሜን አፍሪካ በቪሲጐቶችና ቫንዳሎች ቁጥጥር ስር ወደቁ፡፡ የቤተክርስቲያን መዋቅርም ተፈረካከሰ፡፡

ከ20 ዓመታት በፊት የሮማ ጳጳስንን ጣልቃ ገብነት ይቃወሙ የነበሩ ኤጲስ ቆጶሳት አሁን እርዳታ ፍለጋ በፈቃዳቸው ፊታቸውን ወደ ሮም አዞሩ፡፡ ሊዮ ዓለም አቀፋዊቷን ቤተክርስቲያን እንደሚረዳ ተናገረ፡፡ ንጉሰ ነገስቱ የግዛቱን አንድነት ከሚጠብቅ ማንኛው ኃይል ጋር ስምምነት ለማድረግ በመፈለጉ ሊዮ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ድጋፍ ሰጠ፡፡

በ452 ጳጳሱ ሊዮ ከሮማ መንግስት ምክር ቤት ኤምባሲ ጋር በመሆን አቲላ ሮምን እንዳያጠፋት ለመነ፡፡ አቲላም ሮምን ከማጥፋት ተመለሰ፡፡ ይህ ለጳጳሱ ክብር እና ተደማጭነትን ጨመረለት፡፡ አቲላ ሮምን ከመውረር የተመለሰበት ዋነኛው ምክንያት ግን ደቡባዊ ኢጣሊያ ጥቂት ምግብና ብዙ ወረርሽን ስለነበራት ነው፡፡ ነገር ግን ሊዮ ምስጋናውን ተቀበለ፡፡

በ445 ሊዮ ቫንዳሎች ሮምን እንዳይወሯት ለመማፀን ሞከረ፡፡ እነርሱ ግን ከተማይቷን በመውረር ታይተስ የአይሁድን ቤተመቅደስ ባወደመበት ጊዜ ዘረፎ ያመጣውን መቅረዝ ሰረቁ፡፡

የሄሩሊው ኦዳሴር ሮምን ከ476-493 ድረስ የገዛ ሲሆን እርሱ ከተገደለ በኋላ በኦስትሮጐቱ ቲዎዶሪክ ተተክቷል፡፡ ቲዎዶሪክም ለጳጳሱ ጌላሲየስ (492-96) ጥበቃ አደረገለት፡፡

በርገንዲያኖችና ፍራንኮች ጋውልን (የአሁንዋ ፈረንሳይ) ወረሩ።

በምዕራቡ ክፍል የነበረው የጳጳሱ ሥልጣን ወደ ማዕከላዊውና ደቡባዊው ኢጣሊያ ክፍል እየጠበበ በመምጣቱ በኮንስታቲኖፕል ከሚመራው ምስራቃዊ ግዛት ጥበቃ ያስፈልገው ነበር፡፡ ሶሪያ ከከተዋማ ከአንጾኪያ ጋር ግብፅም ከከተማዋ ከአሌክሳንድሪያ ጋር ዋነኛ የምግብ አቅራቢዎች ሆነው ተነሱ፡፡ ኢየሩሳሌምም በድጋሚ ተገንብታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቤተክርስቲያን ሆነች፡፡ ሮም እያነሰች ሄደች፡፡

በ533 ጀስቲኒያን አሪያናዊነትን ማለትም በሥላሴ የማያምኑትን ባርቤሪያውያን ለማጥፋት ዘመቻ ጀመረ፡፡

ሮምን ያተረፏት ሶሪያን በ640 እና ግብፅን በ642 እንዲሁም ሰሜን አፍሪካን የተቆጣጠሩት ሙስሊሞች ነበሩ፡፡ ሙስሊሞቹ የሮማን ተቀናቃኞች ማለትም አንጾኪያ፣ ኢየሩሳሌም፣ አሌክሳንድሪያ እና ካርቴጅን አስወገዱላት፡፡ ሎምባርዶች በ568 ሰሜናዊውን ኢጣሊያ ወረሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የኮንስታንቲኖፕል ንጉሰ ነገስት በምሥራቅ ትልልቅ ችግሮች ስለገጠሙት በምዕራቡ ክፍል የመጡበትን ችግሮች ሊፈታ አልቻለም፡፡ ጳጳሱ ስቴፈን 2ኛው (752-57) የኮንስታንቲኖፕል ንጉሰ ነገስት ሊረዳው ባለመቻሉ ፊቱን ወደ ባርቤሪያውያኑ የፍራንክ ንጉስ ወደ ፒፒን አዞረ፡፡

ግሪጐሪ 1ኛው (590-601) በሮም መግቢያ ላይ ሎምባርዶቹን ከተጋፈጣቸው በኋላ በእንግሊዝ ውስጥ የሚገኙትን አንግሎ ሳክሰኖች ክርስቲያኖች አደረጋቸው፡፡ ለኮንስታንቲኖፕሉ ጳጳስም መልስ ሲሰጥ ከአባቶች (ከትልልቅ ከተሞች ኤጲስ ቆጶሳት) አንዳቸውም የዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ተቆጣጣሪ እንዳልሆኑ ገለጸለት፡፡ ይህ ሰው ድሆችን የሚረዳና በጳጳሱ ሥር ያሉትን ግዛቶች በብቃት የሚመራ ጠንካራ ሰው ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ለጳጳሱ ትልቅ ክብርን ጨመረለት፡፡ ሌሎች ጳጳሳት ዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን መሪ የላትም የሚለውን የግሪጐሪን ሃሳብ አልተቀበሉም፡፡

ሎምባርዶች ለመውረር ከመዛታቸው ጋር በኢጣሊያ ውስጥ የነበረው የሕዝብ አስተዳደር ወደቀ፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ የሮማ ቤተክርስቲያን ለድሆች ውሃ እና ምግብ አቅራቢ ሆነች፡፡ ቤተክርስቲያናዊ በደምብ እየተደራጁ ከመምጣታቸው ጋር የሮማ ቤተክርስቲያንም በግዛቷ ላይ ኃያል ሆነች፡፡ ግሪጐሪም ከሲሲሊ በቆሎ በመግዛት ለሮም የሚበላ ነገር ያቀረበላ ሲሆን በ591 እና 593 ሎምባርዶችን በገንዘብ ገዝቶ የራሱ አደረጋቸው፡፡ በመቀጠልም እንደ መሪ ለሚቆጥሩት የሃገሪቷ ወታደሮች ክፍያ ይከፍላቸው ጀመር፡፡ አሪያን የነበሩ ሎምባርዶችንም ወደ ካቶሊክ እምነት ቀየራቸው፡፡ እነርሱም ወደ ካቶሊክ አማኝነት የመለወጡ ሥራ በ680 ተጠናቀቀ፡፡ ከዚያም በስፔይን የሚገኙት ቪዝጐቶችም አሪያናዊነትን እርግፍ አድርገው ጣሉ፡፡

በ726 ዓ.ም. ሊዮ 3ኛው የምስል አምልኮን አጥብቆ በተቃወመ ጊዜ በምሥራቅ እና በምዕራብ መካከል እጅግ የመረረ መከፋፈል ሆነ፡፡ የሮማ ጳጳስ ለምስሎች ያለው ድጋፍ ጽኑ ነበር፡፡

ኢሊይሪያ እና ሲሲሊ የተባሉት የግሪክ ከተሞች እንዲሁም ደቡባዊ ኢጣሊያ (የሮም ዋነኛ የሐብት ምንጭ) በኮንስታንቲኖፕል ንጉሰ ነገስት አማካኝነት ከሮም ተወገዱ፡፡ ሮምም ከግዛቱ ሙሉ በሙሉ ተገለለች፡፡ ከዚያ ወዲያ በግዛቱ ውስጥ ዋነኛዋ ቤተክርስቲያን መሆንዋ ቀረ፡፡ በመቀጠልም ከ50 ዓመታት በኋላ ሎምባርዶች በድጋሚ ዘመቱ፡፡

አስቀድማ የተገለለችውና በየያዘችው ግዛትም አነስተኛ የሆነችው ሮም ከምዕራባዊ ባርቤሪያውያን መካከል ከፍራንኮች ጋር ድርድር እንድትጀምር ተገደደች፡፡ ስቴፈን 2ኛው (752-57) የፍራንኮችን ንጉስ ፒፒንን ለድርድር ጠራው። የኢጣሊያን ሰሜናዊ ግማሽ ግዛት እንዲሰጠው ፒፒንን ጠየቀው፡፡ ፒፒን ሎምባርዶችን አሸንፎ በ756 በሮም ዙሪያ ግዛት ቆርሶ ለጳጳሱ በሰጠው ጊዜም የጳጳሱ ግዛቶች በ756 ተመሰረቱ፡፡ በድንገትም ጳጳሱ የዚያ ግዛት ንጉስ ለመሆን ቻለ፡፡ ከባርቤሪያውያን ፍራንኮችን ጋር ባደረገው ውል ቢጠቀምም ከምስራቃዊ የኮንስታንቲኖፕል ንጉሰ ነገስት ጋር የነበረውን ግንኙነት ፈርሶበታል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሮማ ቤተክርስቲያን ፊትዋን ወደ ምዕራባውያኑ ባርቤሪያን ጐሳዎች አዞረች፡፡

በዚህ መንገድ ብዙ ክስተቶቹ የፈጠሩት ጫና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልቃ እንድትወጣ ረድተዋታል፡፡

ኮንስታንቲን እውቅናና ገንዘብ በመስጠት ቤተክርስቲያኒቷ በምስራቃዊ መንግስት ሥልጣን ሥር እንድትንቀሳቀስ አድርጎ ነበር፡፡ ለሮሙ ኤጲስ ቆጶስ ገንዘብ አብዝቶ መስጠቱ ኤጲስ ቆጶሱ ለኮንስታንቲን እንዲታዘዝ ቢያደርገውም ግን የገንዘቡ ብዛት ለሮማው ኤጲስ ቆጶስ በሕዝብ ፊት ታላቅ ከበሬታን እና ሞገስን ጨምሮለታል፡፡

ከግሪጐሪ 1ኛው ጀምሮ የሮም ቤተክርስቲያን ከኮንስቲያንቲኖፕል ጋር ለመፎካከር በመመኮር በሁለት ዓለሞች መካከል ትዋልል ነበር፡፡
ከ754 በኋላ ፊትዋን ወደ ምዕራብ አዞረች፡፡ የጴጥሮስ ተተኪና የቤተክርስቲያን ራስ በመሆን በባርቤሪያውያኑ መካከል ትልቅ ከበሬታን አተረፈች፡፡

በባርቤሪያውያን ነገዶች መካከልም የምትፈልገውን አዲስ ሥልጣን አገኘች፡፡

የፍራንኮች ንጉስ ሕጋዊነት ለማግኘት ሲል ጳጳሱ እንዲቀባው ይፈልግ ነበር፡፡ ጳጳሱም በዛ ክልል ከነበሩት ነገዶች ሁሉ ጠንካራ ከሆኑት ከፍራንኮች ወታደራዊ ጥበቃ ይፈልግ ነበር፡፡ የፈጠሩት ግንኙነት የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም ያስከበረ ነበር፡፡

በመሆኑም ከፍ የለ የሰው አመራር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትን የመካድ አካሄድ ለክርስቶስ ተቃዋሚ መነሳት መንገድ ከፈቱለት። ሌሎቹ መንገድ ከፋቾች ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ሥልጣን ጥማት እና ትልቅ ግዛትን የመግዛት፣ ግብር የማስገበር እና የቁሳቁሳዊ ሐብት ፍቅር ናቸው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ የሰዎችን አመለካከት ከፍ ለማድረግ መረጠች፡፡ ኒቆላውያን (“ኒቆ” ማለት ማንበርከክ ወይም ማሸነፍ ማለት ሲሆን ይህም ምዕመኑን እንዲሁም በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ የሚገኘውን ተራውን ሕዝብ ማንበርከክ መግዛት ማለት ነው)። ይህም የሚደረገው አንድን ቅዱስ ሰው ከፍ በማድረግና ሕዝቡም ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የሚችለው በእርሱ በኩል ብቻ እንደሆነ በማስተማር ሕዝቡ ለዚህ ቅዱስ ሰው ዝቅ ብለው እንዲገዙ በማድረግ ነው፡፡ ይህም አሰራር በመጀመሪያ ሐሳብ እና በየቦታው የሚሰራጭ ልምምድ ሲሆን በመቀጠልም የአምልኮ አቀራረብ ስርዓት ሆኖ ይወሰዳል። ከዚያ በይፋ ሁሉም ሊቀበለው የሚገባው አስተምሕሮ ሆነ፡፡ እነዚህ ሐሳቦች በመቀጠል የቤተክርስቲያኒቷ ሕግ በመሆን ከመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ አስፈላጊ ተደርገው ተቆጠሩ፡፡ እነዚህንም ሕጎች የተቃመ ሰው ሁሉ ጉዱ ፈላ፡፡

 

ራእይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።

 

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልምዶች ሾልከው ሲገቡ አይታለች፡፡

ከ70 እስከ 110 ዓ.ም. ገደማ የነበረው ታዋቂና ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች አንዱ የነበረው ኢግናቲየስ እራሱን በሶሪያ የምትገኘዋ የአንጾኪያ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሾመ፤ በዚሁ ማዕረግም ተቀባይነትን አገኘ።

ዊኪፔዲያ

በነዚህ ደብዳቤዎች ውስጥ ኢግናቲየስ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ “ንጉሳዊ ኤጲስ ቆጶስ” እንዲኖር የተከራከረ የጀመሪያው ሰው ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሦስት ደረጃ ያለው አገልግሎት አለ ብሎ ዘረዘረ፤ ይህም የኤጲስ ቆጶሳት፣ የሽማግሌዎች፣ እና የዲያቆናት አገልግሎት ነው፡፡ በኢግናቲየስ አስተሳሰብ ኤጲስ ቆጶስ የሚለው መጠሪያ ከሽማግሌዎች መካከል በሥልጣን ከፍ በማለት በሽማግሌዎች ላይ የበላይ ሆኖ በእግዚአብሔር ምትክ ለሚገዛ ለአንድ ግለሰብ ብቻ የተወሰነ ማዕረግ ነው፡፡

“ሊቀ ጳጳሱ በእግዚአብሔር ቦታ ይግዛ፤ ሽማግሌዎችም የሐዋርያትን መማክርት ጉባዔው ቦታ ይውሰዱ፤ እንዲሁም ዲያቆናት የኢየሱስ ክርስቶስ የአገልግሎት ሥፍራ ይሰጣቸው” (ለማግኔዢያኖች የተፃፈ መልዕክት 6.1)

ይህ አንድ ቅዱስ ሰው ከሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት ከፍ ባለ ስፍራ ማስቀመጥ የተጀመረበት የመጀመሪያው ማሳያ ነው፡፡

 

ዊኪፔዲያ

ኢግናቲየስ ይህን አይነት እርምጃ እንዲወስድ ያነሳሳው በከፊል የቤተክርስቲያን አንድነት ጉዳጥ ነበር፡፡ በአንጾኪያ ውስጥ መናፍቅ ወይም ሐሰተኛ ብሎ የሚቃወማቸው አስተምህሮዎች እና አንጃዎች ነበሩ፡፡ እርሱም በቤተክርስቲያን ላይ እንደ ባለ ሥልጣን የሚገዛ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ቢሰየም እና ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚታዘዙት ለእርሱ ቢታዘዙ በቤተክርስቲያን ውስጥ መከፋፈልን ለመከላከል ያስችላል ብሎ ያምን ነበር፡፡

ኢግናቲየስ በፊልጵስዩስ ላሉት እንዲህ ብሎ ጻፈ፡- “ለኤጲስ ቆጶሱ፣ ለሽማግሌዎች እና ለዲያቆናት ምክር ጆሮ ስጡ… ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ ምንም ነገር አታድርጉ፤ ሰውነታችሁን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆኑ አድርጋችሁ ጠብቁ፤ ለሕብረት ዋጋ ስጡ፣ መከፋፈልን ተጸየፉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን እንደ መሰለ እናንተም እርሱን ምሰሉ” (7.1-2)

በሰምርኔስ ላሉት በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ብሏል፡- “መከፋፈልን የተንኮል ምንጭ እንደሆነ ቆጥራችሁ ሽሹት፤ ኤጲስ ቆጶሱ ሳይስማማበት ከቤተክርስቲያን ጋር በተገናኘ ምንም ነገር እንዳታደርጉ... በዚህ መንገድ የምትሰሩት ሁሉ መልካምና ተቀባይነት ያለው ይሆናል፡፡” (6-9)
በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ይህ አመለካከት ቤተክርስቲያን በብዛት የምትከተለው አመለካከት አልነበረም፤ ይህ አመለካከት ለቤተክርስቲያን እንግዳ የሆነ አካሄድ ነበር፡፡

ኢግናቲየስ ፖሊካርፕን “የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ” ብሎ ቢጠቅሰውም (ለፖሊካርፕ በጻፈው መልዕክት)፤ ፖሊካርፕ ግን እራሱን የሚጠቅሰው “ፖሊካርፕና በሽማግሌነት አብረውት ያሉት” እያለ ብቻ ነበር (ለፊልጵስዩስ የተፃፈ መልዕክት)
ፖሊክራፕ ቤተክርስቲያንን ከሚመሩ በርካቶች መካከል አንዱ ነበር፤ “ንጉሳዊ” ኤጲስ ቆጶስ የሚባል ነገር በፊልጵስዩስ ውስጥ አልነበረም (ኤቨሬት ፈርገሰን፤ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ድምጽ Early Christians Speak 175)

ኢግናቲየስ በመልዕክቶቹ ውስጥ የሮም ኤጲስ ቆጶስ ብሎ ጠቅሶ አያውቅም። ይህም ክሌመንት እና ሄርማስ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በሮም ያለችው ቤተክርስቲያን በብዙ ሽማግሌዎች ትተዳደር እንደነበር ያቀረቡትን ማስረጃ ያጠናክራል (ፈርገሰን 174)።
በአይሬኒየስ እና በአሌግዛነድሪያው ክሌመንት ጽሑፎች ውስጥ እንደተገለጸው “ንጉሳዊ ኤጲስ ቆጶስ” የሚለው ሃሳብ በቤተክርስቲያናት ውስጥ ሄደ፤ ግን በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ አካባቢ ነው የተስፋፋው፡፡

በኢግናቲየስ ጊዜ የኤጲስ ቆጶስ ሥልጣን ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን የዘዘለ አልነበረም (ፈርገሰን 175)

የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አብያተ ክርስቲያናት እራሳቸውን የሚያስተዳድሩ የነበሩ ሲሆን፤ እያንዳንዳቸው የተዳደሩት በሽማግሌዎች ሕብረት ነበር (የሐዋርያት ሥራ 11፡30፤ 14፡23፤ ቲቶ 1፡5)። እነዚህን መሪዎች አዲስ ኪዳን “ኤጲስ ቆጶሳት”፣ “ሽማግሌዎች”፣ ወይም “መጋቢዎች” ብሎ ይጠራቸዋል፤ እነዚህንም መጠሪያዎች ሰዎቹ አትቢያ ቤተክርስቲያንን በመምራት አገልግሎት ወስጥ የተሰጣቸውን የሥራ ድርሻ ለመግለጽ ነው የተጠቀመባቸው (የሐዋርያት ሥራ 20፡17፣ 28፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡1-3)

ኢግናቲየስ ከአዲስ ኪዳን የቤተክርስቲያን አስተዳደር አሰራር ያፈነገጠ አካሄድን በማስተዋወቅ ከመጀመሪያዎቹ አንዱ ነበር፡፡

 

ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማፈንገጥ በአንድ ከተማ ውስጥ የምትገኝ ቤተክርስቲያንን በአንድ ሰው ቁጥጥር ስር ማድረግ ከ100 ዓ.ም. በኋላ ቀስ በቀስ በሮማ ግዛት ውስጥ እየተስፋፋ ሄዶ እያንዳንዱ ከተማ በአንድ ኤጲስ ቆጶስ መመራት አለበት የሚለው አቋም ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ ቀጠለ፡፡ ከጊዜያት በኋላም ይህንን አሰራር ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር በማነጻጸር ጥያቄ የሚያነሳ አልነበረም፡፡ ስለዚህም ተቀባይነት ያለው አሰራር ሆኖ ቀረ፡፡

 

የሚገርመው ነገር

ኢግናቲየስ ለፊልጵስዩስ እንደዚህ ብሎ ጻፈ፡- “ለኤጲስቆጶስ፣ ለሽማግሌዎች እና ለዲያቆናት ምክር ጆሮአችሁን ስጡ...ከኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ ውጭ ምንም ነገር አታድርጉ”...“ኤጲስ ቆጶሱ በእግዚአብሔር ቦታ ይግዛ…”

 

ስለዚህ ኢግናቲየስ በፊልጵስዩስ ከተማ ያሉ ክርስቲያኖችን የሚመራ አንድ ኤጲስ ቆጶስ የመሾም ልማድን አስጀመረ (ፊሊጵስዩስ የተሰየመችው በመሰረታት የታላቁ አሊግዛንደር አባት ፊሊፕ ስም ነው)፡፡ አሊግዛንደር ፐርሺያኖችን ለማንበርከብ ወደ ምስራቅ የዘመተ ምዕራባዊ ንጉስ ነበር፤ እርሱም ሁሉን በራሱ ፈቃድ ስር ለማስገዛት ፈለገ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሊግዛንደር እንደ አምላክ የተመለከ የመጀመሪያው ምዕራባዊ ሰው ነበር፤ በመጀመሪያ በምሥራቅ ከዚያም በምዕራብ ተመለከ። ሁሉን ማንበርከክና እንደ አምላክ መመለክ የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ መገለጫዎች ሆኑ፡፡

ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች የጻፈው መልዕክት የፊልጵስዩስ መልዕክት ይባላል፡፡

ነገር ግን በዚሁ ለፊልስዩስ ከተማ ክርስቲያኖች በተጻፈው መልዕክት ጳውሎስ “ኤጲስ ቆጶሳት” ብሎ በበዙ ቁጥር ነው ኤጲስ ቆጶሳትን የተቀሰው።

 

ፊልጵስዩስ 1፡1የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤

 

በመሆኑም ጳውሎስ በአንድ ዓርፍተ ነገር በከተማይቱ ከአንድ በላይ ኤጲስ ቆጶሳት እንደ ነበሩ በማመልከት አንድ ኤጲስ ቆጶስ አንድ ከተማን ይምራ የሚለውን አስተሳሰብ ውድቅ አድርጐታል።

በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ፕሮቴስታንቶችም ጭምር በአንድ ከተማ ውስጥ መጀመሪያ ቤተክርስቲያን የመሰረተ ሰው የከተማይቱ ኤጲስ ቆጶስ ነው፤ ስለዚህ ሌሎች አማኞች ሁሉ ለእርሱ መታዘዝ አለባቸው ይላሉ፡፡ “ወደ እኔ ቤተክርስቲያን ተቀላቀል” የሚለው በብዙ ክርስቲያኖች ዘንድ የተለመደ ግብዣ ድብቅ መልዕክቱ “የመጋቢዬ አገዛዝና አመለካከት ተገዥ ሁን” ማለት ነው፡፡

ኢግናቲየስ ፖሊካርፕን “የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ” ብሎ ቢጠራውም ፖሊካርፕ ግን እራሱን “ፖሊካርፕና አብረውት ያሉ ሽማግሌዎች” ብሎ ነው የሚጠቅሰው (ለፊልጵስዩስ ሰዎች የተፃፈ መልዕክት)።

ፖሊካርፕ እራሱን የሰንርኔስ ኤጲስ ቆጶስ ብሎ አልጠራም፡፡

ፖሊካርፕ ከብዙ መሪዎች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን “ንጉሳዊ” የሚባል ኤጲስ ቆጶስ በፊልጵስዩስ ውስጥ አልነበረም (ኤቨሬት ፈርገሰን፤ Early Christains Speak 175)

 

ፖሊካርፕ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል የሚያከብርና ጳውሎስን የሚታዘዝ ሰው ነበር፡፡

ኢግናቲየስ የጳውሎስን መልዕክት መቃረኑ ሳያንሰው በአንድ ከተማ ውስጥ የቤተክርስቲያን ገዥ አንድ ሰው ይሁን የሚል ልማድ እንዲመሰረትና በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ያለው አሰራር እንዲሆን አድርጓል። በ200 ዓ.ም. አንድ ከተማ በውስጧ ላለችው ቤተክርስቲያን የበላይ ሆኖ የሚገዛት አንድ ኤጲስ ቆጶስ መሆኑ ተቀባይነት አግኝቶ የተደላደለ አሰራር ሆነ።

 

ራእይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

 

በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ዘመን የነበረው የኒቆላውያን ስራ በሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ዋነኛ አስተምህሮ ለመሆን በቅቷል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምሕርት ትተን የሰዎችን አሰራርና ልማድ ስንከተል ሁል ጊዜ የሰዎች መንገድ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሆኖ ይቀራል።

ኮንስታንቲን በ312 ዓ.ም. አካባቢ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ባቆመበት ወቅት የተጀመረው ሦስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጊዜም ከፍ ያለ ማዕረግ የተሰጣቸው ኤጲስ ቆጶሳት የከተማ ገዥ መሆናቸው ቤተክርስቲያን በይፋ የምትመራበት ሕግ እና ልማድ ለመሆን በቅቷል፡፡ ማንም ይህንን በመቃረን መሟገት አይችልም ነበር፡፡

ከዚያም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እየሰፋች ስትሄድ ኤጲስ ቆጶሳትን የሚቆጣጠሩ ሊቀ ጳጳሳት እንዲኖሩ ተደረገ (ሊቀ ጳጳስ የሚባል ማዕረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም)፡፡ በአንዳንድ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት ውስጥ እንኳ ሳይቀር ሊቀ ጳጳሳት አሉ፡፡ አማኞች ከፍ ተደርጐ በተሰየመ አንድ መሪ ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ የሚያደርገው ይህ ስሕተት እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ከዚያም ደግሞ ሊቀ ጳጳሳትን የሚቆጣጠሩ ካርዲናሎች ተሰየሙ (ካርዲናል ከባዕድ እምነቶች የተወሰደ ማዕረግ ነው)፤ በመጨረሻም የሥልጣን ተዋረዱ ሁሉ ቁንጮ “ፖፕ” ወይም ጳጳስ ይሾማል። ፖፕ የሚለው ቃል በኢጣሊያንኛ አባት የሚል ትርጉም አለው፡፡ “ፖፕ” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ማዕረግ ብቻ ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል የሚቃረን ጭምር ነው፡፡

 

ማቴዎስ 23፡9አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፡- አባት ብላችሁ አትጥሩ።

 

በፍጥረታዊ ሕይወትህ ውስጥ አንድ ብቻ ሥጋዊ አባት አለህ፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው መንፈሳዊ አባትህ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ዳግመኛ በተወለድክ ጊዜ የዘላለም ሕይወት መንፈስን ከኢየሱስ እንጂ ከሌላ ከማንም አልተቀበልክም፡፡ ይህም ኢየሱስን መንፈሳዊ አባትህና የቤተክርስቲያንም ራስ ያደርገዋል፡፡

 

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

 

በአሁን ጊዜ ቤተክርስቲያናት መጋቢው ለሚላቸው ነገሮችና ለእርሱ አገዛዝ ተገዢ ሆነዋል፤ መጋቢውም ይህንን ሥልጣን ከየት እንዳገኘ ማንም አይጠይቀውም፡፡ በእርግጠኝነት ይህ ሁሉ ሥልጣን ከመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም፤ መጋቢ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ይህም የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ ከአምስቱ አገልግሎቶች ውስጥ በአራተኛ ደረጃ ነው የተጠቀሰው፡፡

 

ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
12 ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።

 

እረኞች ወይም ፓስተሮች ሰዎችን በግል ችግሮቻቸውና በመንፈሳዊ እድገታቸው የመርዳት ሚና አላቸው፡፡ ነገር ግን አገልግሎታቸው በቤተክርስቲያን ላይ ብቸኛ ባለ ሥልጣን ሆኖ መግዛት አይደለም ፡፡

አስተማሪዎች መሰረታዊ አስተምህሮ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አስተምህሮ የማስተማሩን ሥራ ፓስተሮች ተቆጣጥረውታል፡፡

ሰዎች ማንን ማዳመጥ እንደሌለባቸው ወይም ወደ ቤታቸው ማንን መጋበዝ እንደሌለባቸው መንገር የፓስተሮች ሥራ አይደለም፡፡

ፓስተሮች የተሰየሙት ከእነርሱ ጋር በማይስማሙ ሰዎች በር እንዲዘጉ አይደለም፡፡ የፓስተሮች ጥሪ በቤተክርስቲያን ውስጥ ቀዳሚው ስፍራ መያዝ አይደለም፡፡

ዲዮጥራጢስ የተባለው ሰው ባህርያት እነዚህ ናቸው፡፡

 

3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።

 

በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስቲያን ሰውን የሚያባርር ማን ነው? ይህ ሰው ሰራሽ ሥልጣን የተሰጠው ማን ነው? ፓስተሩ ነው፡፡

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጀመረችው ከፍ ተደርጐ ለተቀመጠ የቤተክርስቲያን መሪ ፈቃድና ሥልጣን መገዛት ባህል በአሁኑ ወቅት ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናትም ገብቷል፡፡

የሥላሴ አስተምህሮ ማለት እግዚአብሔር አንድ ስም የለውም ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ጥምቀጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አይደረግም፡፡ ፕሮቴስታንቶች ይህንንም ልማድ ተከትለውታል፡፡

 

የሐዋርያት ሥራ 2፡38ጴጥሮስም፡- ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
የሐዋርያት ሥራ 8፡12ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።

 

ፊሊጶስ የአብ፣ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን ስም በጭራሽ አልሰበከም፡፡

 

የሐዋርያት ሥራ 19፡4ጳውሎስም፡- ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው።
5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
ሮሜ 6፡3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?

 

ወልድ ብቻ ነው የሞተው እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይደለም፡፡ እና የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም ኢየሱስ ካልሆነ በቀር የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ከኢየሱስ ሞት ጋር አንድ ለመሆን ከመጠመቅ ጋር ምን ያገናኘዋል?

 

ቆላስይስ 3፡17እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።

 

ጥምቀት በሥራ የሚተገበር ስለሆነ በኢየሱስ ስም መደረግ አለበት፡፡

የሰው ከፍ ያለ አመራር የጥንቷን ቤተክርስቲያን አበላሻት ነገር ግን በሰዎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን አገኘ፡፡

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህንን ሞዴል ተቀብላ በሕዝብ ዘንድ በስፋት ተቀባይነትን እንዲያገኝ ደግሞ ብዙ የሚስቡ የአረማውያን እምነቶችን ለማጣፈጫነት ጨመረችበት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ክደዋል፤ ነገር ግን ከፍተኛ ዝና እና ሐብት ትክክል ተደርገው ተቀባይነት እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡

ይህ የጥንት ሮም መንፈስ ነው፡፡ የሮም መንፈስ ነጻ በነበሩ ሰዎች ላይ የመገዛትን ቀምበር ይጭናል፡፡ የሮማ መንግስት ምክር ቤት በአንጃዎች ተከፋፍሎ የነበረ ቢሆንም ለንጉሰ ነገስቱን በመለማመጥ ግን አንድነት ነበረው፡፡ ለአንድ ሰው ፈቃድ መገዛት የስኬት ቁልፍ ሆነ፡፡ በቂ ሥልጣን በሚሰጠው ጊዜ ታማኝ ሰው እንኳን መቅለስለስ ይጀምራል፡፡ ለሰው ፈቃድና ልማዶች መገዛት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለንን የግል ግንኙነት ያበላሻል፡፡

ይህ ጥናት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እንዴት አንቴናውን አስረዝሞ ከቀድሞዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወጥተው ለማምለጥ በሞከሩት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ዘልቆ መግባቱን አሳይቶናል፡፡ እኛ ለሰው ሕጐችና ልማዶች ባሪያ ነን ወይስ መጽሐፍ ቅዱስን ለመከተል ነፃነት ያለን ሰዎች ነን?

በዚህ ብትስቱ ታላቁ መከራ ይጠብቃችኋል፡፡ ታላቁ መከራ ለእንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት ማለትም ለበርካታ ክርስቲያኖች የማንቂያ ደወል ሆኖ ይመጣል፡፡

 

ማቴዎስ 24፡21በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።

ራእይ 2፡22እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤

ራእይ 7፡9ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤

ራእይ 7፡13ከሽማግሌዎቹም አንዱ ተመልሶ፡- እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ? አለኝ።
14 እኔም፡- ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፡- እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።

 

የሰዎች ግምትና አመለካከት እንዲሁም በሌሎችን ላይ ጌታ ለመሆን ያላቸው ፍላጎት በዘመናት ውስጥ ምንም የማይነቀንቀው አስተምህሮ ወደ መሆን ደርሷል። እነዚህም ትክክል ያልሆኑ አስተምህሮዎች እንዳይጠፉ ጥበቃ የሚያደርጉላቸው ቡድኖች አሉ። አመለካከታቸው ወይም እምነታቸው ግልጽ ውይይትን የሚከላከሉ ጽኑ ሃይማኖታዊ ግድግዳዎች ሆነው ቀርተዋል።