የክርስቶስ ተቃዋሚ በመጀመሪያዎቹ 800 ዓመታት ውስጥ እንዴት እንዳደገና እንደተከናወነ - ክፍል 1

በዚህ ርዕስ ዙሪያ በእርግጠኝነት ምን እናውቃለን? የክርስቶስ ተቃዋሚ ምን ወይም ማን እንደሆነ ያለህ ግንዛቤ በእምነትህ ላይ ሥር ነቀል ውጤቶችን ያስከትላል። ይህ ጽንሰ ሐሳብ የእምነትንህ ጉልህ በሆነ መንገድ ቅርጽ ያስይዘዋል።

 

1ኛ ዮሐንስ 2፡18 ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
19 ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።

 

የክርስቶስ ተቃዋሚ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጊዜ ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን አካል የነበሩ ሲሆን፤ የራሳቸውን እምነት ለመከተልና አማራጭ ወይም ተቀናቃኝ የቤተክርስቲያን ስርዓት ለመመስረት ሲሉ ከቤተክርቲያን ተለይተው ወጡ፡፡ እንደ ይሁዳ ሁሉ ስተው እስኪጠፉ ድረስ የክርስቶስ ተከታዮች ነበሩ፤ ይሁዳን ወደ ስህተት የመራር የገንዘብ ፍቅር ነበር በመሆኑም የሐብታም ቤተክርስቲያን ድርጅቶች ለክርስቶስ ተቃዋሚ ስርዓት ዓይነተኛ እጩ መሆን ይችላል፡፡ በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ሃብትን የሚከታተሉ ሲሆኑ ቁሳዊ ብልፅግናን የእግዚአብሔር በረከት ማረጋገጫ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን ግን ያላትን ሐብት ለሌሎች ትሰጥ ነበር፡፡ ይህም አንድ ሰው ቆም ብሎ እንዲያስብ ያስገድደዋል፡፡

 

የሐዋርያት ሥራ 2፡44 ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤
45 ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።

 

የምዕራቡ ዓለም በቁሳዊ ስኬት መለከፉ ጥሩ ነገር አይደለም።

የማቴዎስ ወንጌል 19፡24  ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።
ማስጠንቀቂያ አልተሰጠንም ነበር እንዳትሉ።

 

“ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች” ማለት ብዙ ስህተቶች ማት ነውይናገራሉ፡፡ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከተነሳ ቢያንስ የ2000 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን፤ ይህ ተቃዋሚ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሐርን ቃል የሚቃወም (ክርስቶስ ቃሉ ስለሆነ) “ክርስቲያናዊ” እምነትና አስተምህሮ ነው፡፡ ይሁን እንጂ 2000 ዓመታት ተሻግሮ በመምጣት ይህጸረ ክርስቶስ እምነት ዕድሜ ጠገብ እና የበለጸገ የቤተክርስቲያን ትምሕርት ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህ የእምነት ስርዓት በስም የሚታወቅ ግለሰብ መሪ ሊኖረውም ይችላል፡፡ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚለው መጠሪያ ስርዓትን ወይም ግለሰብን ሊወክል ይችላል። ናዚዝም ጀርመንን ያስተዳድራት የነበረውን የናዚ ስርዓት ወይም የዚህን ስርዓት መሪ አዶልፍ ሂትለርን ይወክላል፡፡
የዚህ ፀረ-መፅሐፍ ቅዱስ ስህተት ምንጭ ማን እንደሆነ ለማወቅ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ፍንጭ ማግኘት እንችላለን?
እስኪ ታላቁ ነብይ ዳንኤልን እንጠይቀው።

 

ዳንኤል 9፡26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።

 

የአይሁድ ቤተመቅደስ እጅግ አስደናቂ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሰው ሰራሽ ነበር፡፡ ይህ ሰው ሰራሽ ቤተመቅደስ አይሁድ በ33 ዓ.ም. ኢየሱስን አንቀበልም ካሉ በኋላ በ70 ዓ.ም. በሮማውያን እጅ ከመጥፋት አላዳናቸውም፡፡ አሁንም ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አንቀበልም ብንል እኛ ያበጀነው ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን ስርዓት ከሚመጣው መከራ ሊያድነን አይችልም፡፡

 

ኤፌሶን 2፡2 በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።

 

ሁለት ዋነኛ አለቆች አሉ። መሲሕ የተባለው አለቃ (እግዚአብሔር የተገለጠበት ኢየሱስ የተባለው ሰው) እና በመጨረሻው ዘመን ልክ ከዚህ በፊት በይሁዳ እንዳደረገው ሰይጣን ሊገለጥበት የሚፈልገው ሰው፡፡

 

ዮሐንስ 13፡27 ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት። እንግዲህ ኢየሱስ፡- የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ አለው።

 

በዘመን መጨረሻ ላይ ሰይጣን ወደ ሰው ውስጥ (የክርስቶስ ተቃዋሚ ስርዓት መሪ የሚሆነው ሰው ውስጥ) በመግባት አጭር ጊዜ በሚቆየው የታላቁ መከራ ወቅት ዓለምን የሚገዛ ልዕለሰብ ያደርገዋል፡፡

ነገር ግን ለዚህ የመጨረሻው ዘመን ልዕለሰብ መንገድ የሚጠርግ ፀረ ክርስቶስ የሐይማኖት ስርዓት ላለፉት 2000 ዓመታት ሲዘጋጅ ቆይቷል፡፡
ይህ ልዕለሰብ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ “የሚመጣው አለቃ” ይሆናል፡፡ ስለዚህ የእርሱ ሕዝብ እነማን ናቸው? ወደ ስልጣን መንበር የሚያመጡት እነማን ናቸው? የአይሁድን መቅደስ ያፈረሱት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሮማውያን ነበሩ፡፡ ከ66 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ዓመታት በቆየ ጦርነት አይሁድ ሮማውያንን ተቋቁመው ቆይተዋል፡፡ በ66 ዓ.ም. ብቃት በሌለው አመራር ስር የነበሩትን ሮማውያን አይሁድ አሸንፈዋቸዋል፡፡ በመቀጠልም ሮማውያን ቬስፓሲያን በተባለው ብቃት ያለው የጦር ጄነራልና በልጁ በታይተስ የሚመራ አራት ክፍለ ጦር አዘመቱ፡፡ እርሱም ያለምንም ርህራሄ እያሸነፈ የገጠሩን ክፍል ተቆጣጠረ፡፡ ንጉሰ ነገስቱ ኔሮ በ68 ዓ.ም. ሲሞት ሮማዊው ጄነራል ጦርነቱን አቆመ ምክንያቱም ኔሮ በመሞቱ ምክንያት ጦርነቱን ለመቀጠል ከአዲሱ ንጉስ ዘንድ ፈቃድ ማግኘት ያስፈልገው ነበር፡፡ ነገር ግን ጋልባ፣ ኦርቶ እና ቪቴሊየስ የተባሉ ሦስት ጄነራሎች ለጥቂት ወራት ያህል ለአጭር ጊዜ ስልጣን ነጥቀው ተቆጣጥረው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ቬስፓሲያን ትዕዛዝ እየተጠባበቀ ሳለ ከአይሁዳውያን ጋር የሚየደርገውን ጦርነት ለጊዜው ገትቶ ነበር፡፡ በመቀጠልም የቬስፓሲንያ ወታደሮች እርሱ ንጉሰ ነገስት እንደሆነ አወጀው አነገሱት፡፡ ስለዚህ በ70 ዓ.ም. ሥልጣን ለመያዝ ወደ ሮም ሲመለስ በሮም ውስጥ እንደ ድል አድራጊና አዲስ ንጉሰ ነገሰት የሚኖረውን ድርሻ ከፍ ለማድረግ ፈጣንና ጭካኔ የተሞላበት ድል በአይሁዶች ላይ ማግኘት እንደሚፈልግ ለልጁ ለታይተስ ነገረው፡፡ ታይተስም ኢየሩሳሌምን በመክበብ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲራቡ ካደረገ በኋላ በመጨረሻ ኢየሩሳሌምን በሚያወድሙበት ጊዜ 1 100 000 አይሁዳዊያንን ጨፈጨፈ፡፡ በዚህም ጊዜ መቅደሱ በዕሳት ተያያዘ፤ በመቅደሱ ውስጥ የሚገኙት የወርቅ እቃዎች እየቀለጡ በድንጋዮች ስንጥቆች ውስጥ ፈሰሱ፡፡ ሮማውያኑም እነዚህን ወርቆች ለመውሰድ የመቅደሱን ድንጋዮች ፈነቃቀሉ፡፡ ታላቁ እስክንድር የዓለም ገዥ የነበሩትን ፋርሶችን 50 000 ወታደሮችን በማዝመት ከአራት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አንበርክኮዋቸዋል። ሮማውያን ወደ ከሃገራቸው ራቅ ወዳለችው የእስራኤል ግዛት 80,000 ወታደሮች የላኩ ሲሆን ጦርነቱም ለአራት ዓመታት ፈጅቷል፡፡ ይህ ደግሞ ሮማውያን በዓለም ፊት መሳቂያ መሳለቂያ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በአይሁዶች እጅግ በመበሳጨታቸው 1.1 ሚሊዮን አይሁዶችን በመፍጀት ለአይሁዳውያን ትምህርት ለመስጠት መቅደሱን ሙሉ በሙሉ አፈራርሰው ባድማ አደረጉት፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዳውያንም በባርነት ወደ ሮም ተወስደው ታይተስ ከቤተመቅደሱ በዘረፈው ሐብት በሙሉ ኮሎሲየም የተባለውን ትርኢት ማሳያ ቦታ እንዲገነቡ ተደርገዋል፡፡ ኮሎሲየም በኋላ ክርስቲያኖች ከአውሬ ጋር እየታገሉ እንዲበሉ የተደረገበት ቦታ ነው፡፡

ሮማዊያን ኢየሩሳሌምንና ቤተመቅደሱን ያጠፉ ከመሆናቸው አንፃር የሚመጣው የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚነሳበት ሕዝቦች ናቸው፡፡
እስኪ ከዳንኤል ሌላ ፍንጭ እንፈልግ

 

ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።

 

“ዘመናትን ይለውጣል”
ጊዜ እጃችን ላይ በምናስረው ሰዓት አማካኝነት (የቀን ሰዓት) የምንለካበት ወይም በቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) የወሩን ቀናት ወይም የዓመቱን ወራት የምንለካበት መለኪያ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቁርባን ወይም የጌታ እራት (በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ) ተብሎ የሚጠራው ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ የቂጣ በዓለን ካከበሩ በኋላ ኢየሱስ የደነገገው ሥርዓት ነው፤ የቂጣ በዓልም የፋሲካ በግ ከታረደበት ምሽት በፊት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማታ የሚበላ እራት ነው። ኢየሱስ ይህንን ያደረገው በምሽት ጊዜ ሲሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን ይህ ሥርዓት ሚፈጸምበትን ሰዓት ወደ ቀን አዙራዋለች። ከዚያም ፕሮቴስታንቶች ይህንን የካቶሊኮች ምሳሌ በመቅዳት ቁርባኑን የሚወስዱት ሰዓት አድርገዋል፡፡

 

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡23 ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ

 

ሥርዓቱ ጠተፈጸመው በምሽት ቢሆንም ዛሬ ግን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ የምትለውን ሥርዓት በጠዋት መፈጸም ልማዷ አድርጋዋለች፡፡ ፕሮቴስታንቶችም የነርሱን ምሪት በመከተል ቁርባን ወይም የጌታ እራት የሚሉትን ስርዓት በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ለማከናወን ደስተኞች ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ስርዓቱን የጌታ እራት ሳይሆን የጌታ ቁርስ ያደርገዋል፡፡

 

ዮሐንስ 13፡2 እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ፥

 

ኢየሱስ ቁርባን የተባለውንና የእግር ማጠብ ስርዓቶችን ያከናወነው ከእራት በኋላ ነበር። (አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች እግር ማጠብን ትተውታል።)

ይህ ስርዓት የሚከናወንበት ጊዜ ከማታው ወደ ጥዋቱ ክፍለ ጊዜ ተቀይሯል፡፡ ክርስቲያኖች ይህ ምንም ለውጥ አያመጣም በማለት ይቀበሉታል፡፡ ስለዚህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቁርባንን (የቅዳሴን) ጊዜ ከምሽቱ ወደ ቀኑ ክፍለ ጊዜ ቀይራዋለች፡፡ ይህንን በማድረጋቸውም ይህ ስነስርዓት የሚፈጸምበትነ ጊዜ ለውጠዋል፡፡

እንደ ባለ አእምሮ ስናስብ ጊዜን መቀየር የክርስቶስ ተቃዋሚ ምልክት ነው፡፡
የእኛ ሥራ የኢየሱስን ምሳሌ መከተል እንጂ እርሱ ያደረገውን ነገር ለእኛ ወደሚመቸን ሌላ ነገር መለወጥ አይደለም፡፡ ክርስትና ማለት አብዛኛውን ጊዜ ከምቾትና ከመደላደል ይልቅ መስዋዕትነት ማለት ነው፡፡ የእግር ማጠብ ስነስርዓቱም በአብዛኞቹ ክርስቲያኖች የተተወበት ምክንያትም ይኸው ነው፡፡ ይህ ስነስርዓት ለሰው ብዙ የሚመች አይደለም፡፡

የሮማ ቤተክርስቲያን ወሩንና የወሩንም ቀን ለውጣዋለች፡፡ ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን እና ወር ማንም አያውቀውም፡፡ እግዚአብሔር የልደት ቀኖች አያሳስቡትም፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት የልደት ቀኖች ሁለት ብቻ ሲሆኑ እነዚህም የሄሮድስና የፈርኦን ናቸው፡፡ ደግሞ ሁለቱም ሰዎች በልደታቸው ቀን ሰው ገድለዋል፡፡ እኛ የሰው ልጆች ለልደት ቀን ትልቅ ትኩረት እንሰጣለን፤ ለኢየሱስም የልደት ቀን በመፍጠር እግዚአብሔርን ማስደነቅ የምንችል ይመስለናል፡፡ ስለዚህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የማናውቀውን ቀን (ክርስቶስ የተወለደበትን ትክክለኛውን ቀን) ወስዳ በመለወጥ በቋሚነት ዲሴምበር 25 እንዲሆን አድርገዋለች፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስ በዲሴምበር ወር ስለመወለዱ ምንም ዓይነት ማስረጃ አናገኝም፡፡ ነገር ግን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የማይታወቀውን የክርስቶስን የልደት ቀን ወደ ዲሴምበር ወር ለውጣዋለች፡፡

ፋሲካ በእርግጥ ልናውቀው የምንችለው ቀን ነው፡፡ ፋሲካ ከማርች ወር መጨረሻ ወይም ከአፕሪል ወር መጀመሪያ አንስቶ የመጀመሪያዋ ሙሉ ጨረቃ በምትታይበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ቀን በሳምንቱ በየትኛውም ቀን ላይ ሊውልና ይችላል፤ በየዓመቱም ይለዋወጣል፤ አይሁድም የፋሲካ በዓል የሚውልበትን ቀን የሚያሰሉት እንዲህ ነው። ይሁን እንጂ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀኑ ሙሉ ጨረቃ ከምትታይበት ቀን ቢርቅም ሁሌ አርብ እንዲውል አድርጋ ለውጣዋለች፡፡ ሙሉ ጨረቃን ተከትሎ ከማስላት ይልቅ የሳምንቱን የመጨረሻ ቀን ለፌሽታ አመቺ በመሆኑ ለአርብ ትኩረት ሰጥተውታል፡፡ አሁንም ፕሮቴስታንቶች ይህንን የካቶሊክ ምሳሌነት ተከትለውታል፡፡

 

የካቶሊክ ኢንሳይክሎፒያኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን ዲሴምበር 25 እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመዝግቦ የተገኘው በሮም ውስጥ ሲሆን ጊዜውም 354 ዓ.ም. (በፊሎካሊያን ካላንደር በ354 ዓመት) ሲሆን፤ ይህም መዝገብ የማትሸነፈዋ ፀሐይ የልደት ቀን እና የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ዲሴምበር 25 እንደሆነ ይጠቅሳል፡፡ ይህ ሰነድ በ336 ዓ.ም በነበረው የቀን መቁጠሪያ ላይ የተመሰረተ ነው (Herman Wegman, Christian Worship in East and West, New York: Pueblo Publishing, 1985, 103)፡፡

 

የጊዜ መቁጠሪያው በዓመት ውስጥ የሚከበሩ የተለያዩ የሰማዕታትን ክብረ በዓላት ቀን የሚያትተው የሮም ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት ሰነድ ነው፡፡

በ350 ዓ.ም. የሮም ጳጳስ የነበረው ጁሊየስ ዲሴምበር 25ን ተቀብሎታል፤ ምክንያቱም ይህ ቀን አሕዛብ አስቀድመው የሚያመልኩትን የፀሐይ አምላክን ልደት የሚያከብሩበት ታዋቂ ቀን ነበረ፡፡

በመሆኑም ሮማውያን የወሩን ቀን ሁለት ጊዜ ለውጠውታል፡፡ ዲሴምበር 25ን በተመለከተ የማናውቀውንና ቀን አሁን ግን እናውቀዋለን ብለን የምንጠራውን የኢየሱስን የልደት ቀን ብለው ለውጠውታል፡፡ ፋሲካን በተመለከተ ደግሞ የምናውቀውን የሙሉ ጨረቃ ቀን ሁል ጊዜ አርብ እንዲሆን ለውጠውታል፡፡ አርብና ሙሉ ጨረቃ የሚገጥሙት እጅግ በጣም አልፎ አልፎ ነው፡፡

ካላንደር ጊዜን የሚለካልን በረጅሙ ነው፡፡ ካላንደሩን ማን ነው የቀየረው? ሮም ነች፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ46ኛው ዓመት ከሮማውያን መካከል እጅግ ታዋቂ የነበረው ዩሊየስ ቄሳር ወሮቹን ከወቅቶቹ ጋር ለማገጣጠም በዓመቱ ላይ 90 ቀናትን ጨመረ፡፡ ከዚህ ትልቅ ማስተካከያ በኋላ የዓመቱን ርዝመት 365 ቀናት አድርጐ በማስቀመጥ በየአራት ዓመቱ አንዴ ደግሞ በፌብሩዋሪ ወር ላይ በሊፕይር አንድ ቀን ጨመረ፡፡ ምንም እንኳን በጣም ትክክል ቢሆንም ይህ የጁሊያን የቀን መቁጠሪያ በ400 ዓመታት አንዴ ሦስት ቀናትን የሚጨምር ሲሆን ቀስ በቀስም ከትክክለኛው የዓመቱ ወቅቶች ጋር እየተዛነፈ ይሄዳል፡፡

በመሆኑም በ1582 የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ የነበረው ግሪጐሪ 13ኛው (50 ሺህ ፕሮቴስታንቶች በባርቶሎሜው እንዲጨፈጨፉ ትዕዛዝ የሰጠው ሰው) የቀን መቁጠሪያውን በድጋሚ ከወቅቶቹ ጋር ለማስተካከል ከዓመቱ ላይ 10 ቀናትን አስወገደ፡፡ በጥቂቱ ዓመቱን ለማሳጠር ጳጳሱ ግሪጐሪ 13ኛው ከእያንዳንዱ ለ400 ሊካፈል ከማይችል አዲስ ክፍለ ዘመን ላይ ሊፕይሮችን አስወገደ፡፡ ስለዚህ 1600 ዓ.ም ሊፕይር ሲኖረው ነገር ግን 1700 ወይም 1800 ወይም 1900 ሊፕይር አይኖራቸውም፡፡ 2000 ዓመት ሊፕይር ነበረው፡፡ እስካሁን የምንጠቀምበት ግሪጎሪ ያዘጋጀው ግሪጎሪያን የዘመን መቁጠሪያ በየ2,800 ዓመታት አንድ ጊዜ ብቻ የአንድ ቀን ስህተት የሚፈጥር ስለሆነ በጣም ትክክለኛ አድርገን ልንቀበለው ችለናል፡፡

ይህ በዩሊየስ ቄሳር ዘመን የነበሩት ጣኦት አምላኪዎችና በሮማ ካቶሊክ ክርስቲያኖች መካከል ልዩ አንድነት ያሳየናል፡፡ እነዚህ ሁለቱም ሮማዊ ቡድኖች ከወቅቶች ጋር እንዲገጥምላቸው ብለው ካላንደሩን ወይም የቀን መቁጠሪያውን በመቀየሩ ረገድ አብይ ሚናዎችን ተጫውተዋል፡፡

 

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤

 

ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች ማለትን ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ እንድትሆን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነች፡፡ በራዕይ 17 ላይ አውሬው ላይ ስለምትቀመጥና ስለምትቆጣጠር ሴት (ቤተክርስቲያን) እናነባለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አውሬው የሆነ የሥልጣን ዓይነትን ይወክላል፡፡ በምድር ላይ ካሉት ጠንካራ ሥልጣኖች አንዱ ጀግና የሆነ ሰውን ማምለክ ነው፡፡ ሰውን ማምለክን ስንመለከት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በወንድ መልክ የሚመለክ ጀግና ማለትም ጳጳሱን በሴት መልክ የምትመለክ ደግሞ ማርያምን አዘጋጅታለነች፡፡

 

ራእይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
4 ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤

በ1825 ጳጳሱ ሊዮ 12ኛው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በሴት የሚወክል ኒሻን ወይም ሜዳሊያ አሰራ፡፡ መዳሊያው ላይ የተቀረጸው ምስል አንዲት ሴት (እናት ቤተክርስቲያን) በእጇ ጽዋ ይዛ ያሳያል፤ ይህም ጽዋ አስተምሕሮን ይወክላል፤ ምክንያቱም ጽዋ የመገለጥ እውቀት መነቃቃትን የሚገልጸውን ወይንን ይወክላል፡፡

 

ራእይ 17፡9 ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው፡ ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥
ራእይ 17፡18 ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።

 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴት ቤተክርስቲያንን ነው የምትወክለው ሲሆን እዚህ ቃል ውስጥ ግን ሴቲቱ ከተማ ሆናለች፡፡

ከመጀመሪያው በሰባት ተራሮች ወይም ኮረብቶች ላይ የተገነባችና ኃይለኛ በሆነች ቤተክርስቲያን ቁጥጥር ስር ስላለች ከተማ ሰዎች ሲያስቡ ወዲያው ወደ አእምሮዋቸው የምትመጣ ከተማይቱን የምትቆጣጠር ቤተክርስቲያን አለችን? እንዲህ ያለች ከተማ በእርግጥ አለች፡፡ ይህች ከተማ የሰባቱ ኮረብቶች ታዋቂ ከተማ ሮም ነች፡፡

 

ራእይ 17፡8ያየኸው አውሬ (የሐይማኖታዊ ስርዓቱ ዋነኛ መሪ) ቀደም ሲል ነበረ፤ አሁን ግን የለም (መሪው ይሞታል) በኋላም ከጥልቁ ጉድጓ ይወጣል፡፡ (የካቶሊክ እምነቶች አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የላቸውም፡፡ ዝም ብለው እንደ ቅዳሴ፣ የገና ቀን፣ የገና ዛፍ፣ መቁጠሪያ፣ ካርዲናል፣ ሊቀ ጳጳስ፣ ዋና ጳጳስ፣ መነኮሳት፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ስርዓቶች፣ ለማርያምና ለሞቱ ቅዱሳን ጸሎት ማቅረብ፣ ሕፃናትን በመርጨት ማጥመቅ፣ ሥላሴና ሌሎች ልዩ ልዩ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ቃላትና ልማዶችን ያምናሉ፡፡) ወደጥፋቱም ይሄዳል፡፡ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ስማቸው በሕይወት መፅሐፍ ተፅፎ ያልተገኘ የምድር ነዋሪዎች አውሬው ቀድሞ የነበረ (የሚገዛው ጳጳስ)፣ አሁን ግን የሌለ (የሞተው ወይም ሥልጣኑን የለቀቀው ጳጳስ)፣ በኋላም የሚመጣ (አዲስ ጳጳስ ይመረጣል) መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ባላት እጅግ ብዙ ሐብት እና እጅግ በርካታ በሆኑት የተከታዮቿ ቁጥር እንዲሁም ጳጳሱ ባለው ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ)፡፡

 

ስርዓቱ እንዲቀጥል የሚያደርገው ይህ ነው፤ ምክንያቱም የቀድሞው በሚሞትበት ጊዜ አዲስ ጳጳስ መምረጥ ይችላሉ፡፡ ጳጳሳቱ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ሳይቋረጥ ለረጅም ጊዜ የቀጠለ የገዢዎች ሀረግን ይወክላሉ፡፡ ሰዎች አንድ ድርጅት እንዴት ለዚህን ያህል ረጅም ዘመን መቆየትና በአሁኑ ዓለም ላይም ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪና ሐብታም ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ይደነቃሉ፡፡ ጳጳሳት አያገቡም፤ በመሆኑም አባቱን ተከትሎ የሚሾም ብቃቱ የሌለው የጳጳስ ልጅ ይተካል የሚል ስጋት አይኖርም፡፡ የካርዲናሎች ምክር ቤት ከፍተኛ ብቃት ያለውን በወቅቱ የሚገኝ ሰው ለመምረጥ ነፃ ነው፡፡

IMG_7178 (Small)

 

ራእይ 17፡4 ሴቲቱም (ቤተክርስቲያኒቷ) ሐምራዊና ቀይ ልብስ ተጐናፅፋ ነበር (ጳጳሳት ሐምራዊ እንዲሁም ካርዲናሎች ደግሞ ቀይ ልብስ ይለብሳሉ)፤ ደግሞም በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቁዎች አጊጣ ነበር (እጅግ ሐብታም የሆነች ቤተክርስቲያን)፤ በእጅዋም የወርቅ ፅዋ ይዛ ነበር (ለዓለም የምታቀርባቸው አስተምህሮዎች፡፡ በጽዋ ውስጥ ያለው ወይን ይህ የሚያመጣውን የመገለጥ መነቃቃት ይወክላል፡፡ በበዓለ ሃምሳ ቀን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ጥመቀት የተነሳ ባገኙት የመገለጥ መነቃቃት የተነሳ ሰክረው ተንገዳግደዋል፡፡)

 

የሐዋርያት ሥራ 2፡13-15 ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፡- ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ።
14 ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፡- አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ።
15 ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤

 

ራእይ 17፡4 ...በእጅዋም የሚያፀይፍ ነገርና የዝሙቷ እርኩሰት የሞላበትን የወርቅ ፅዋ ይዛ ነበር፡፡ “ዝሙት” ማለት ያላገባች ሴት ከወንዶች ጋር ስትተኛ ማለት ነው፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን ክርስቶስን አላገባችም፡፡ የክርስቶስ ሙሽራ ብትሆን ኖሮ በዝሙቷ ትፀፀት ነበር፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን አትሰብክም፤ ነገር የሰዎችን ወግ እና ልማድ ታስተምራለች፡፡ “ገና” የሚለው ቃልም ሆና ዲሴምበር 25 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም። “ክሪስማስ” የሚለው ቃል አመጣጡ “ክራይስት” እና “ማስ” ከሚባሉ ሁለት ቃላት ሲሆን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፈጠረችውን ማስ (ቅዳሴ) የሚባል ስርዓትን የሚገልጽ ነው።

ሰብዓ ሰገል የገቡት ወደ በረት ውስጥ ሳይሆን ወደ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ያዩትም ኢየሱስና ማርያምን ሲሆን ዮሴፍን ግን አላዩትም፡፡

 

ወንጌል 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

 

ስጦታም ለክርስቶስ ሰጡ እንጂ እርስ በእርስ አልተሰጣጡም፡፡ በመሆኑም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሰብዓ ሰገልን ታሪክ በመለወጥ ወደ በረት እንደገቡ ብላ አስተምራለች፡፡ ለኢየሱስ ልደትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ቀን ሰይማለች፡፡ ዲሴምበር 25 የፀሐይ አምላክ ልደት እንዲሆን ፀሐይን ያመልክ የነበረው ሮማዊው ንጉሰ ነገስት ኦሬሊያን በ274 ዓ.ም አውጆ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ይህ ቀን እውቅና ያለው ቀን አልነበረም፡፡ የገና ዛፎችም ከአሕዛብ የተኮረጁ ናቸው፡፡

 

ኤርሚያስ 10፡2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና።
3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እንጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።

 

የሮማ ካቶሊክ በዚህ የገና በዓል አማካኝነት የአሕዛብን ባህል ኮርጃለች (ኢየሱስ በክረምት አጋማሽ ማለትን በዲሴምበር አልተወለደም፤ በክረምት ቢወለድ ኖሮ በዚያ ምሽት ከቤት ውጭ የነበሩ እረኞችና በጎች በቅዝቃዜ ይሞቱ ነበር፡፡)፤ ከዚያም ፕሮቴስታንቶች ይህንኑ ቀን እናት ቤተክርስቲያን ከሆነችው ከካቶሊክ ኮረጁ፡፡

 

ራእይ 17፡5 በግንባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፡-ታላቂቱ ባቢሎን የጋለሞታዎችና የምድር ርኩሰት እናት ተብሎ ተጻፈ፡፡ (ፕሮቴስታንቶች በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እግዚአብሔርን ለማምለክ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተለይተው ወጡ፤ ነገር ግን ወዲያውኑ እነርሱም በሰዎች ባህል መጠላለፍ ጀመሩ፡፡ ከወንዶች ጋር የምትወሰልት ሴት ሁሉ ጋለሞታ ነች፡፡ ስለዚህ ፕሮቴስታንቶችም የካቶሊክን ያህልበግልሙትና ተጠያቂ ናቸው፡፡ እነርሱም የሰውን አመለካከት ከመፅሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ያከብራሉ፡፡ ስለዚህ ሁሉም በተመሳሳይ ፍርድ ውስጥ ናቸው፡፡)

 

ራእይ 17፡6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።

አንድ ሐብታም ቤተክርስቲያን እንዴት እንደዚህ ብዙህ ክርስቲያኖች ልትገድል ትችላለላለች? ሮማውያን ነገስታት የአረማውያን ጀነራል ኦዳሴር በ476 ዓ.ም አካባቢ ሥልጣን እስኪነጥቃቸው ድረስ በቆዩበት ጊዜ ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጉ ክርስቲያኖችን ገድለዋል፡፡ የሮም ጳጳሳት የአሳዳጆች ቁንጮ በሆነው በኦጋገስተን ጽሑፎች ቅስቀሳ ከእነርሱ ጋር የማይስማሙ 68 ሚሊየን የሚሆኑ ክርስቲያኖችን ገድለዋል፡፡ ይህ በማንኛውም መለኪያ ቢታይ ከልክ ያለፈ ቁጥር ነው፡፡ ይህ ልቅ ባህርይ የስካር መገለጫ ነው፡፡

 

ራእይ 13፡3 ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥

 

የአውሬው ሰባት ራሶች (ወይም ሥልጣን) ሮም በመጀመሪያ የተገነባችባቸውን ሰባቱን ኮረብቶች ይወክላሉ፡፡ በካፒቶላይን ኮረብታ ላይ የተመሠረተው ዋና ከተማ የንጉሳዊ መንግስቱ ሕጐች የሚወጡበት የንጉስ መናገሻ መሆኑ ታውጆ ነበር፡፡ በመቀጠልም የሄሩሊ ጐሳ መሪ የሆነው ኦዳሴር ንጉሰ ነገስቱን አውግስጦስን በመገልበጥ በእርሱ ቦታ ተተክቶ ይገዛ ነበር፤ ነገር ግን ዋና መቀመጫውን በካፒቶላይን ኮረብታ አላደረገም፡፡ በመሆኑም ይህ የሥልጣን መቀመጫ የነበረው ኮረብታ ግዛቶቹን የማስተዳደር ሥልጣኑን አጣ፡፡ የሮም ዘመነ ግዛትም በዚሁ አከተመ፤ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ከአውሬው ራሶች በአንዱ ላይ የደረሰው ለሞት የሆነ ቁስል ባርቤሪያኖች በካፒቶላይን ኮረብታ ላይ የሰነዘሩት ጥቃት ሲሆን እርሱም የሮም ገዢነት ማክተሙን አመላካች ነው። የሮማ ግዛትም በወራሪ ባርቤሪያኖች ተከፋፈለ፡፡ ከዚያም በኋላ የሮማ ቄሳሮች ሁለተኛ ገዢ ሊነግሱ አልቻሉም፡፡

ነገር ግን ከነዚህ ባርቤሪያን ጐሳዎች መካከል የሮም ጳጳስ በሥልጣን ከፍ ማለት ጀመረ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ንጉስ ኮንስታንቲን ወደ ምስራቅ ሄዶ ኮንስታንቲኖፕልን ለመገንባት ፈለገ፡፡ ስለዚህ እርሱ ወደ ኮንስታንቲኖፕል በሄደበት በሮም ውስጥ የንጉሱ ቀኝ እጅ ይሆንለት ዘንድ ኮንስታንቲን ለሮማው ጳጳስ እጅግ በርካታ ገንዘብና ሐብት ሰጠው፡፡ ይህም የሮማው ጳጳስ ታላቅ ከበሬታ እንዲኖረው አደረ፡፡ በ311 አካባቢ ንጉስ ኮንስታንቲን የላተራን ቤተሰብ ንብረቶችን ወስዶ ሚልቲያደስ ለተባለው ጳጳስ ሰጠው፤ የላተራን ቤተመንግስት አንዳንድ ሰዎች እንደሚገልጹት በተለያዩ ጊዜያት ተቃጥሎወድሞ በድጋሚ ከመገንባቱ በፊት በዓለም ላይ ከነበሩ ቤተመንግስቶስ ሁሉ እጅግ ያማረ ቤተመንግስት ነበር፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ የተገነባው ቤተመንግስት እስዛሬ ድረስ የሚገኝ ሲሆን በውበቱ እና በግርማ ሞገሱ ግን ከበፊቱ እጅግ ያነሰ ነው፡፡ ኮንስታንቲን አዲሲቱን የኮንስታንቲኖፕል ከተማ ለመገንባት ወደ ምስራቅ በሄደ ጊዜ፤ ለሮማው ጳጳስ እጅግ ብዙ ሐብት እና ፖለቲካዊ ሥልጣን ሰጥቶት ሄደ፤ ይህን ያደረገበት ምክንያትም ጳጳሱ የንጉሱ የቅርብ ወዳጅ ስለነበረ ነው፡፡

ከላተራን ቤተመንግስት አጠገብ ባሲልካ ነበረ (ባሲልካ ቅምጥል ሆኖ የተሰራውን የቤተክርስቲያን ሕንጻ ለመግለጽ የሚያገለግል ቅምጥል ቃል ነው)። ሲልቬስተር የተባለው ቀጣዩ የሮም ጳጳስ ኮንስታንቲን በሰጠው ገንዘብ ባሲልካውን ገነባ፡፡ የተሰጠውም ገንዘብ ሲልቬስተርን እጅግ ሐብታም አደረገው። ፖለቲካዊ መሪው ኮንስታንቲን በብዙ የገንዘብ ስጦታው የሮሙ ጳጳስን ታማኝነት ገዛ፡፡ ኮንስታንቲን የቤተክርስቲያኒቷ ሐይማኖታዊ መሪ መሆን ይፈልግ ስለነበር የሮማውን ጳጳስ ድጋፍ ይፈልግ ነበር፡፡ በዚህም መንገድ ኮንስታንቲን የሮማ ግዛት ውስጥ ፖለቲካዊም ሐይማኖታዊም መሪ ሆነ፡፡ በ476 ዓ.ም. የሮማው ንጉሰ ነገስት ኦጋስተለስ ከሥልጣን ተወግዶ በባርቤሪያኑ ጀነራል ኦዳሴር ተተካ፡፡ የሮም ጳጳሳት (እራሳቸውን ጳጳሳት ብለው የሚጠሩ) ጥበቃ ፍለጋ ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ በሚኖረው የምስራቅ ሮም ንጉሰ ነገስት መተማመን ጀመሩ፡፡ (ኮንስታንቲኖፕል ዛሬ ኢስታንቡል ተብላ ነው የምትጠራው)

 

ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ ያለው ንጉስ ኢጣሊያን ከጥቃት መከላከል ሲያቅተው፤ ጳጳሳቱ ከባርቤሪያኖች ነገስታት ጋር ወዳጅነት ጀመሩ፡፡

ጳጳሳቱ የባርቤሪያኖቹን መሪዎች በየራሳቸው ነገዶች ላይ ነገስታት አድረገው ቀብተው ሾሙዋቸው፤ እነዚህም ነገስታት ጳጳሶቹንና ግዛታቸውን ከጠላት ለመጠበቅ ቃል ገቡላቸው፡፡ ባርቤሪያኖቹ ወደ ካቶሊክ እምነት ሲለወጡ ጳጳሳቱ በእነርሱም ላይ የገዢነት ሥልጣን ተጐናጸፉ፡፡ የባርቤሪያኖቹ በሁከትና ነውጥ የተሞላ፤አስቸጋሪና አጭር ሕይወት በሮማውያኑ እርጋታ፣ ጸጥታ እና የስልጣኔ እድገት እንዲገረሙና እንዲያከብሩዋቸው አድርጓቸዋል፡፡ በሂደትም የሮማ ጳጳሳት የሮም ቄሳሮች ያጡትን ፖለቲካዊ ሥልጣን መልሰው በእጃቸው ያስገቡ ሲሆን በዚህም “ለሞቱ የሆነው ቁስል ተፈወሰ” የሚለው ቃል ተፈጸመ፡፡ አረማዊቷ ሮም ወድቃ ከአመዷ ላይ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሆና አንሰራርታ የተነሳች ሲሆን የሮማ ካቶሊክ ሃይማኖትም ክርስትና የተነሳ አረማዊነት (ጣኦት አምላኪነት) ነው፤ ምክንያቱም አረማውያንን ለማስደሰት ብለው ብዙ አረማዊ የሐይማኖት ልማዶችን ወደ ክርስትና እምነት ውስጥ እንዲካተቱ አድርገዋል፡፡

 

ራእይ 13፡6 እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ (የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥላሴን በመፍጠር የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ስም ባልሆኑት አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ማእረጎች ተክታለች፡፡ ፕሮቴስታንቶችም ይህንን ምሳሌነት በመከተል ስሙ (ነጠላ ቁጥር፡- የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም) ማን እንደሆኑ ለመናገር ባይችሉም በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቃሉ።

 

፡፡ በእርግጥ ይህ ስም የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፡፡ አንድን ክርስቲያን የእግዚአብሔር ስም ማን ነው ብለህ ብትጠይቀው መመለስ አይችለም፤ ምክንያቱም ለሦስት አካላት የሚሆን አንድ ስም ለመጥራት ይቸገራል፡፡ የእግዚአብሔርን ማደሪያም አያውቁም፤ (ካቶሊኮቹ ቫቲካን ውስጥ ያሉትን ውብ ሕንጻዎች በምድር ላይ የእግዚአብሔር ማደሪያ ናቸው ብለው ያምናሉ። እግዚአብሔር ግን መኖር የሚፈልገው በወንዶች እና በሴቶች ልጆቹ ልብ ውስጥ እንጂ በሕንፃ ውስጥ አይደለም፡፡) “በሰማይም የሚያድሩትን” (ወደሞቱ ቅዱሳን ጸሎት ይጸልያሉ፤ ወደ ሙታን መጸለይ ግን ሙታን ሳቢነት ሲሆን ማርያምና የሞቱ ቅዱሳን እንደ አማላጅ ማየት ቅድመ አያቶችን ማምለክ፡፡)

 

ራእይ 9፡2የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።
3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ (አጥፊ የሆነ የአጋንንት ኃይልን ያመለክታል) የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።

 

የሲኦል ጉድጓድ ተከፍቶ አጋንንታዊ ተጽእኖዎች ምድርን ያጥለቀልቋታል፡፡ ጳጳሱ ሲመረጥት መመረጡን የሚያመለክቱት በጭስ አማካኝነት ነው፡፡ ካርዲናሎች በአዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው ምንም ዓይነት ውሣኔ ካልተላለፈ ጥቁር ጢስ እንዲጨስ ያደርጋሉ፤ በመጨረሻም በአዲሱ ጳጳስ ላይ ሲስማሙ ነጭ ጢስ ያቀጣጥላሉ፡፡

 

ራእይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።

 

የአጋንንቱ ዓለም ንጉስ አለው፤ እርሱም የጥልቁ መልአክ (መልዕክተኛ) ነው፡፡ ንጉስ ዘውድ እንደሚደፋ ፤ ጳጳሱም የሰማይ፣ የምድር እና የፑርጋቶሪ ንጉስ መሆኑን የሚያመለክት ባለ ሦስት ተደራቢ ጌጠኛ ዘውድ (አክሊል) ይደፋል፡፡ ኢየሱስ የደፋው የዕሾህ አክሊል ነበር፡፡ “ፖፕ”፣ “ባለ ሦስት ተደራቢ ዘውድ”፣ “ፑርጋቶሪ”፣ “ካርዲናሎች”፣ “በጭስ መምረጥ” ወዘተ የመሳሰሉት ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ አይደሉም፡፡ የምናምነው ሁሉ ምንጩ ከመጽሐፍ ቅዱስ አለዚያም ከጥልቁ ጉድጓድ ነው።

እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን (700-800 ዓ.ም) የሮማ ቤተክርስቲያን በጴጥሮስ ሊቀጳጳስነት ሹመት በመተካት የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳላት አላወጀችም ነበር፡፡ ይህ የተደረገው “የኮንስታንቲን ልገሳ” በተባለው ሐሰተኛ ሰነድ አማካኝነት ነበር፡፡ በመጀመሪያ ይፋ የተደረገው በ752 ዓ.ም. ማለትም ኮንስታንቲን (በ337 ዓ.ም.) ከሞተ ከአራት መቶ ዓመታት በኋላ ነበር፡፡ ሰነዱ የአራተኛውን ክፍለ ዘመን የታላቁ ንጉስ ኮንስታንቲንን ስም በሐሰት በመጠቀም፤ የሐዋርያት መተካካትን አስተምህሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ይዞ ከመምጣት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ vicarius filii dei የሚለውን ስም ፈልስፏል፡፡

የላቲንን ቋንቋ በሚገባባታውቁም እንኳ በኮንስታንቲን ልገሳ ላይ ከተቀመጠው የላቲን ጽሕፈት አንድ ዓረፍተ ነገር እንጠቅስላችሁዋለን፡፡ ይህ ወረቀት በቤተክርስቲያን ጉባዔ የተረጋገጠና በሮማ ካቶሊክ ቀኖና ውስጥ የተካተተ ሲሆን በኋላም በጳጳሱ ግሪጐሪ 13ኛው አማካኝነት ጸድቋል (የቀን መቁጠሪያውን የቀየረው ጳጳስ) እንዲሁም ሉሺየስ ፌራሪስ በተባለ የካቶሊክ ምሁርና ታሪክ ጸሐፊ አማካኝነት ሰነዱ ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

 

Ut sicut Beatus Petrus in Terris Vicarius Filii Dei fuit constitutus, ita et Pontifices eius successores in terris principatus potestatem amplius, quam terrenae imperialis nostrae serenitatis mansuetudo haber videtur” Lucius Ferraris, Prompta Biblietheca, (edition of 1890), art, “Papa,” II, Vol. VI, p. 43.

 

ትርጉሙ እንደሚከተለው ነው፡-
የተባረከው ጴጥሮስ በምድር ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ተወካይ (ምትክ) ተደርጎ እንደተሸመ ሁሉ የሐርያቱ አለቃ የሆነ የጴጥሮስ ተወካዮች የሆኑት ጳጳሳትም የምድራችን ግርማዊ ክብር የሚበልጥ ሥልጣንና ታላቅነት ከእኛ እና ከግዛቶቻችን ሁሉ ሊቀበሉ ይገባቸዋል፡፡
ክሪስቶፈር ቢ. ኮልማን፤ Treatise of Lorenzo Valla on the Donation of Constantine የኮንስታንቲንን ልገሳ በተመለከተ ሎሬንዞ ቫላ ከጻፈው ጥናት ገፅ 13

 

በእርግጥ ኮንስታንቲን የቀደመውን ሰነድ የእውነትም ጽፎት ቢሆን እንኳ ይህ አንዲት ቤተክርስቲያን በጳጳሷ ሹመት በሌሎች ላይ እንድትሰለጥን አያደርጋትም። ነገር ግን ይህ ሐሰተኛ ሰነድ የጳጳሶቹን የበላይነትና በጴጥሮስ ስም የማይሳሳቱ ተደርገው እንዲቆጠሩ ለማድረግ በመሣሪያነት አገልግሏል፡፡
ጳጳሱ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ስላለው ጴጥሮስን ማስደሰት ያስፈልጋል አለ፡፡ ለጳጳሳቱ የምታደርገው ለጴጥሮስ እንዳደረክ ይቆጠራል፡፡ ጳጳሳቱ ይህንን ልዩ ክብር ለራሳቸው የተጎናጸፉት ጴጥሮስን የሐዋርያት አለቃ አድርገው በመሾም እና ራሳቸውን ደግሞ የጴጥሮስ ወራሾች በማድረግ ነው፡፡ ጴጥሮስ እራሱ ጳጳስ ነኝ ብሎ አያውቅም፤ ወይም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መገለጫ ለሆነው የሐብትና የግዛት ፍላጐት መሻትም አልነበረውም፡፡ ይህ በአንድ ሰው በጴጥሮስ ላይ የሚደረግ ትኩረት እንዲሁም ጴጥሮስ Vicarius Filii Dei ነበር ብሎ ማስተማር ለእነርሱ ልዩ ዕድልን ይከፍትላቸዋል፡፡

 

Vicarius urbis Romae ማለት “በሮም ከተማ ፈንታ” ማለት ነው፡፡
ይህ ንጉሰ ነገስቱ ከሮም ወጥቶ በሚሄድበት ጊዜ በሮም ውስጥ ለንጉሰ ነገስቱ ተወካይ የሚሰጥ የማዕረግ መጠሪያ ነው፡፡
የላቲን ቋንቋ የተወሰኑ ፊደላትን እንደ ቁጥር ይጠቀማል፡፤

 

IN PLACE OF               THE SON               OF GOD
ፈንታ                                      ልጅ                   የእግዚአብሔር

V I C A R I V S F I L I I D E I (ላቲን በU ፊደል ፈንታ Vን ይጠቀማል)
5 1 100 1 5 1 50 1 1 500 1 ( D = 500 C = 100 L = 50 V = 5 I = 1 )

 

እነዚህ ሁሉም ቁጥሮች ሲደመሩ 666ን ይሰጣሉ፤ እርሱም የአውሬው ምልክት ነው፡፡
ይህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለጴጥሮስ የሰጠችው ማዕረግ (ጴጥሮስ ለራሱ ተጠቅሞት የማያውቀውን) የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ቃል ጋር ያገጣጥማታል፡፡

 

ራእይ 13፡18 አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።

 

የአውሬው ምልክት ከሰው ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሐዋርያው ጴጥሮስን አገልግሎት ያጣመመችበት ልክ ስርዓቶቿን በሙሉ ከአውሬው ምልክት ጋር ሊያያዝ እስከሚችል ድረስ ነው፡፡

ይህ አይነቱ ክብር ይገባኛል ብሎ ስለማያውቅ ጴጥሮስ ለዚህ ስሕተት ተወቃሽ ሊሆን አይችልም፡፡ ጴጥሮስ አይሁድ ላልሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያ ነበርን? የአህዛብ ሐዋርያ ሆኖ ያውቃልን? አያውቅም፡፡ በዚህ ርዕስ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ግልፅ መልስ የሚሰጠን ሲሆን፤ ስለ ሐዋርያነትም የተወሰኑ አስገራሚ እውነታዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ልንማር እንችላለን፡፡

 

በመጀመሪያ፤ ጴጥሮስ የሮም ጳጳስ እንዳልነበረ እንረዳለን፤ ነገር ግን ጳውሎስ በግልፅ እንደጻፈው ጴጥሮስ የአይሁድ ሐዋርያ ነበር፡-

 

ተመልሰው ግን ጴጥሮስ ለተገረዙት (ለአይሁድ) የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠው እንዲሁ ለእኔ (ለጳውሎስ) ላልተገረዙት (ለአሕዛብ) የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠኝ አዩ፤ ለተገረዙት (ለአይሁድ) ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት (እግዚአብሔር)፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና። ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ (የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን) አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ (ጴጥሮስ) ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት (ወደ አይሁድ) ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን። ገላቲያ 2፡7-9

 

ከዊኪፒዲያ - ነፃ ኢንሳይክሎፔዲያ

በሴብቴምበር 24/768 ዓ.ም. የሞተው ፔፒን ወይም ፒፒን ታናሹ ከካሮሊንጂያን ሥርወ መንግስት የመጣ የመጀመሪያው የፍራንኮች ንጉስ ነበረ (752-768)፡፡ በ741 እርሱና ወንድሙ ካርሎማን አባታቸውን ቻርልስ ማርቴልን በመተካት የቤተመንግስቱ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በቀድሞው እና በተከታዩ ንጉስ መካከል በነበረው የስድስት ዓመታት ክፍተት ጊዜ የግዛቱ መሪዎች ሆኑ (737-743)፡፡ ካርሎማን ጡረታ ከወጣ በኋላ (747) ፔፒን የሜሮቬኒያኖችን የመጨረሻ ንጉስ ኪልደሪክ ለዙፋን ለማውረድ የጳጳሱን የዛካሪን ፈቃድ አገኘ፤ ከዚያም ዙፋን ላይ ተቀመጠ።

 

(የባርቤሪያን ፍራንኮች ንጉስ ለመሆን ፔፒን የጳጳሱ ድጋፍ ያስፈልገው ነበር።)

ጳጳሱ በበኩሉ ኢጣሊያን የወረራት የሎንባርድ ባርቤሪያኖችን ያባርርለት ዘንድ የፔፒንን እርዳታ ይፈልግ ነበር፡፡

ፔፒን እንደነገሰ የመጀመሪያ እርምጃው ወደ ሮም ግዛት የተስፋፋውን የሎንባርድ ንጉስ አይስቱልፍን መውጋት ነበር፡፡ ድልን ከተቀዳጀ በኋላ የሎንባርድ ንጉስ ከቤተክርስቲያን የዘረፋቸውን ንብረቶች አስመለሰ፡፡ ራቬና እና ፔንታ ፖሊስ (አምስቱ ከተሞች) የተባሉትን የፔፒን ስጦታ የሚባሉትን ከተሞች ለጳጳሳቱ መልሶ ሰጠ፤ በዚህም የጳጳሳቱ መስተዳድሮች ተመሰረቱ፤ ፖለቲካዊ የሆነ የጳጳሳት አገዛዝም ተጀመረ፡፡

ፔፒን ለጳጳሱ ድጋፍ የሰጠው ጴጥሮስ ወደ መንግስተ ሰማያት እንዲያስገባው ነው፡፡

የካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ከሮም አንስቶ ኢጣሊያን ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚያዳርሱ ፓፓል ስቴትስ የተባሉ ግዛቶች ባለቤት ሆነች።

ጳጳሱ በ752 ዓ.ም. ባርቤሪያኑን ፔፒን የፍራንኮች ንጉስ አድርጋ ሾመችው፤ እንዲሁም በ800 ዓ.ም. ልጁን ሻርለሜይንን አነገሰችው(ሻርለሜይን ከባርቤሪያን ነገዶች ሁሉ እጅግ ታዋቂው ንጉስ ለመሆን በቅቷል፡፡) በዚህ መሠረት ጳጳሱ በባርቤሪያኖች መካከል ንጉስ ሿሚ ሆነ፡፡ ባርቤሪያኖች ወደ ካቶሊክ እምነት ሲለወጡ ጳጳሱም መንፈሳዊ መሪያቸው ሆነ፡፡ የሮማ ቄሳሮች ከእጃቸው የጠፋውን ሥልጣን ጳጳሱ በእጁ እያስገባ ነበር፡፡

 

ራእይ 17፡2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።

 

ጳጳሱ ከንጉሶችና ከዓለም መሪዎች ጋር አብሮ ለመስራት በቂ ሥልጣንና የተለየ መብት አግኝቷል፡፡

“አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” (ማቴዎስ ምዕራፍ 16 ቁጥር 16)

ከደቀመዛሙርት ሁሉ ጴጥሮስ ብቻ ነበር ኢየሱስ ማን እንደሆነ የጠራ መገለጥ ያገኘው፡፡

ኢየሱስም አለ “አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዓለት ላይ (ኢየሱስ ማን እንደሆነ ያወቀበት የመገለጥ ዓለት) ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉዋትም፡፡ (ማቴዎስ ምዕራፍ 16 ቁጥር 18)

ጴጥሮስ ዓለት ነው በማለት ጳጳሱ ይህንን እውነት ለውጦታል፡፡ ይህ ጴጥሮስ እራሱ ግን ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ክዶታል፡፡

 

ማቴዎስ 26፡33 ጴጥሮስም መልሶ፡- ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም አለው።
34 ኢየሱስ፡- እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው።

 

ጴጥሮስ (በግሪክ ፔትሮስ) ድንጋይ ወይም ጠጠር ብቻ ማለት እንጂ ዓለት አይደለ፡፡

 

ገላትያ 2፡11 ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።
12 አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ።

 

እንግዲህ ጴጥሮስ አሕዛብ በአይሁድ ሕግ እንዲኖሩ ይፈልግ ነበር፡፡ ጳውሎስ ጴጥሮስን በማረም ጴጥሮስ የሮማ ቤተክርስቲያን እንደምትለው ዋናኛው ሐዋርያ እንዳልሆነ ገልጧል። ጴጥሮስ በትምሕርቱ ተሳስቶ ስለነበረ የመጀመሪያው የሮማ ጳጳስ ሊያደርጉት የሚፈልጉ ሰዎች ፍጹም የማይሳሳት አድርገው ቢቆጥሩትም አይደለም፡፡

 

ማርቆስ 1፡29 ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።
30 የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ወዲያው ነገሩት፡፡

ማርቆስ 3፡16 ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤

 

ስምዖን ጴጥሮስ ሚስት ነበረው፡፡ ስለዚህ ጴጥሮስየመጀመሪያው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ አልነበረም፤ ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከካህናት ጀምሮ እስከ ጳጳሳት ለአገልጋዮችዋ ማግባት ትከለክላለች፡፡

 

1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡1 መንፈስ ግን በግልጥ። በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ …
3 እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፥

 

ስለዚህ ካህናትና ጳጳሳት ማግባት አይችሉም የሚለው ሕግ በእርግጠኝነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡

 

ማቴዎስ 16፡19የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

 

በበዓለ ሃምሳ ቀን ጴጥሮስ የመጥምቁ ዮሐንስን ጥምቀትን አሰረ፤ ስለዚህ ከዚያ ቀን በኋላ የዮሐንስ ጥምቀት አስፈላጊነቱ አበቃ፡፡ ዮሐንስ ለንሰሃ ብቻ ያጠምቅ ነበር እንጂ፤ የመስዋእቱን በግ፣ በደሙ ከኃጥያት የሚያነጻውን የአዳኙን ስም አልጠቀሰም ነበር፡፡

 

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፡- ንስሐ ግቡ (ከኃጢአት የምንፈታበት መንገድ ይህ ነው)፤ ኃጢአታችሁም ይሰረይ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ (እግዚአብሔር ማን መሆኑ እንደገባን እና በሰዎች አመለካከት እንዳልተታለልን ማረጋገጫ ነው፡፡ በዚህ ዓለት ላይ ማለት የኢየሱስ ማንነት መገለጥ ነው፡፡ እርሱ እግዚአብሔር አብ፤ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ በተባለው ሰው ውስጥ ያደረው ያ ታላቅ ቅዱስ መንፈስ ነው፡፡ እንደ አብ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከአይሁድ በላይ ነበር፡፡ እንደ ወልድ እግዚአብሔር ሰው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ አማኑኤል ሆኖ ተመላለሰ፤ አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው፡፡ እንደ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በሕዝቡች ልብ - በቤተክርስቲያን - ውስጥ ለመኖር ተመልሶ መጣ።) የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡

 

ስለዚህ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በንስሐ ድና፤ በበጉ ደም ታጥባለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም መሆኑን ያውቁ ነበር፡፡ ይህ ጥምቀት የእግዚአብሔርን ማንነት እውቀት በሕዝቡ ላይ ለቀቀ፡፡ በብሉይ ኪዳን ላይ የተጠቀሰው ያህዌ የአዲስ ኪዳኑ ኢየሱስ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም፡፡

ጴጥሮስ የመጀመሪያው ጳጳስ ከሆነ በዚህ ምክንያት ፍጹም የማይሳሳት ሰው ነው ካልን እንግዲህ በኢየሱስ ስም ማጥመቁን ልብ በሉ፡፡ ታዲያ ለረጅም ዘመናት የእርሱ ተተኪዎች ነን ያሉት ጳጳሶች እርሱ ያደረገውን ለምን አላደረጉም? ሁሉም በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃሉ፤ ስሙ ማን እንደሆነ ሊነግሩን ባይችሉም፡፡

ጳጳሱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን አለኝ ብሏል፤ በእነርሱ አባባል የኃጥያት ይቅርታን የመስጠት እና የመንፈግ ሥልጣን ነው። ነገር ግን ይህን ስልጣን ጳጳሳቱ በመካከለኛው ዘመን ከፖለቲከኞች ጋር በሚገጥማቸው ግጭት ውስጥ ይጠቀሙበት ነበር፡፡

 

ማቴዎስ 16፡22 ጴጥሮስም ወደ እርሱ (ኢየሱስን) ወስዶ፡- አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።

 

ቁልፍ ተሰጥቶትም ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር በመቃረን በቀጥታ ወደ ስህተት ገብቷል፡፡

 

23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፡- ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።

 

ይህ አስደንጋጭ አነጋገር ነው፡፡ መክፈቻዎቹ የጴጥሮስ ሐሳብ ሰይጣናዊ እንዳይሆን አላደረጉም፡፡ እንግዲህ የጴጥሮስ ሥልጣን አለን ብለው የሚያውጁት ጳጳሳትስ?

ሐዋርያዊ ትውፊት ማለት ጳጳሳቱ የጴጥሮስ ተተኪዎች ነን ብለው ማወጃቸውና በዚህም ኃጢአትን ይቅር ማለት ሲፈልጉም ይቅርታን መከልከል እንደሚችሉ ማመናቸው ነው፡፡

ጳጳሱ ቦኒፌስ (418-22) መንግስትና ክርስቶስ ለጴጥሮስ አደራ የሰጣት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ለጴጥሮስ ተተኪዎች ማለትም ለሮም ጳጳሳት እንደተላለፈችና የጳጳሳቱም አገዛዝ የማይቀለበስ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ደግሞም ቦኒፌስ እንዲህ አለ፡- ለጳጳሳቱ የማይታዘዝ ሁሉ የክርስቲያን ማሕበረሰብ አባል ሆኖ ሊቆይ አይችልም ወይም የመዳን ተስፋ የለውም፡፡

(የጴጥሮስን ስህተት ያረመው ጳውሎስስ?)

ጳጳሱ ገላስየስ (492-96) ጳጳሱን ቪካሪየስ ፔትሪ (የጴጥሮስ ምትክ) እንዲሁም ይባስ ብሎ ቪካሪየስ ክሪስቲ (የክርስቶስ ምትክ) ብሎ ለመጥራት የመጀመሪያ ነበር፡፡

“ቪካሪየስ ፔትሪ” ማለት የጴጥሮስ ተተኪ ማለት ነው፡፡ ጳጳሱ በምድር ላይ የጴጥሮስ ተወካይ ነው፡፡

 

2ኛ ተሰሎንቄ 2፡4 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ (ጳጳስ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ስላለው ኃጥያትን ይቅር እያለ እና ሲፈልግ ይቅርታን እየከለከለ) በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ (ውቧ እና ሃብታሟ ቫቲካን ውስጥ)፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።

 

በሮም የአገዛዝ ዘመን የሮም ንጉሰ ነገስት ከሮም ወጥቶ በሚሄድበት ጊዜ የሮማው ጳጳስ የንጉሰ ነገስቱ ተወካይ ወይም ተጠሪ ነበር፡፡

ስለዚህ የሮማው ጳጳስ “ቪካሪየስ ኡርቢስ ሮሜ” (በሮም ከተማ ምትክ) ነበር፡፡ ባርቤሪያውያን ጎሳዎች ንጉሳዊ ግዛቱ ላይ ስጋት በሚፈጥሩበት ጊዜ የሮማው ጳጳስ በኢጣሊያ ውስጥ መሪ እና የንጉሰ ነገስቱ ተጠሪና ሆኖ ቆሟል፡፡ ከዚያም ጳጳሱ ቪካሪየስ ፔትሪ ወይም የጴጥሮስ ተወካይ ነኝ አለ። ከዚያም ደግሞ ጳጳሱ ጴጥሮስ የክርስቶስ ተወካይ ነው ብሎ አወጀ፡፡ (ቪካሪየስ ፊሊ ዴይ) ይህንን የማዕረግ ስም የሰጡት ለጴጥሮስ ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ይህንን ማዕረግ ለራሱ የሚጠቀም ጳጳስ ይኖር እንደሆን ምንም ዓይነት ግልፅ ማስረጃ አይገኝም፡፡ ጴጥሮስም እንደዚህ ዓይነት ማዕረግ ለራሱ አልወሰደም፡፡

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቪካሪየስ ፊሊ ዴይ (666) የሚለውን ማዕረግ እስከዛሬ ለአንድ ሰው ብቻ ተጠቅማዋለች፤ ማለትም ለጴጥሮስ፡፡ ጴጥሮስ ይህ ይገባኛል ብሎ የማያውቅ ከመሆኑ አንፃር በዚህ ጉዳይ በፍጹም ሊወቀስ አይችልም፡፡

የጴጥሮስን ሥልጣን ከፍ ለማድረግ እና ለማጣመም ሙከራ ያደረገችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ናቡከደነፆር የቅዱሱን ሰው የዳንኤልን ሐውልት ሰርቶ አቆመ፤ ዳንኤልም ለራሱ ምስል አልሰግድም ያለበት ምክንያት ይህ ነው፡፡ ለሐውልቱ ዳንኤል ተጠያቂ አይደለም፡፡

ዮሐንስ ሁለት ጊዜ ለመለአክ ሊሰግድ ነበር፤ ይህም መልአክ ነብይ ነበር፡፡

 

ራእይ 19፡10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፡- እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።
ራእይ 22፡8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
9 እርሱም፡- እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

 

እኛ ሰዎች በቀላሉ ቅዱስ የሆነ ሰውን ከፍ ከፍ እናደርጋለን፡፡

 

ራእይ 13፡18 አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።

 

ጴጥሮስ ይህንን ማዕረግ ይገባኛል ብሎ አያውቅም፡፡ ጴጥሮስ ለየትኛውም የሮማ ጳጳስ ምንም ዓይነት ሥልጣን አልሰጠም፡፡
ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን እንዴት መተዳደር እንዳለባት ምክር ሲሰጥ ለሽማግሌዎች እንጂ ለየትኛውም ጳጳስ አልጻፈም።

 

1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን (ሃብታም ለመሆን ሳይሆን) ጐብኙት፤
3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ። (ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ጰጳስ አትሁኑ) ጴጥሮስ በቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው ገዥ በሚሆንበት አሰራር በፍፁም ተስማምቶ አያውቅም፡፡

 

የሮማ ጳጳሳት አንድ ካህን ብቻ ቤተክርስቲያንን እንዲቆጣጠር ይፈልጋሉ፡፡ ጳጳሱ ካህናትን ከተቆጣጠረ ቤተክርስቲያንንም በቀላሉ ተቆጣጠረ ማለት ነው፡፡ ፕሮቴስታንቶችም ይህንኑ የካቶሊክ ልማድ በመከተል አንድ ፓስተር ወይም መጋቢ በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ ገዥ እንዲሆን ፈቅደዋል፡፡

እግዚአብሔር እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ቡድን እንድትመራ ይፈልጋል፡፡

በሮሜ መፅሐፍ መጨረሻ ላይ ጳውሎስ ለሮማውያን ደብዳቤ ሲጽፍ ሁሉንም በስም እየጠቀሰ ሰላምታ ሲያቀርብላቸው ጴጥሮስን ግን አንዴ እንኳ አልጠቀሰም፡፡

ጴጥሮስ ሮም ሄዶ ስለማወቁ እንኳ አንዳች ታሪካዊ ማስረጃ የለም፡፡

ጳውሎስ ያገቡ ሽማግሌዎችን በኃላፊነት ቦታ ላይ ስለመሾም ተናግሯል፤ ስለዚህ ሽማግሌ ጳጳስ ነው ማለት ነው፡፡ ጳጳሶች ማግባት ይችላሉ፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማግባትን አትፈቅድም፡፡

 

ቲቶ 1:5-7 ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤
6 የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።
7 ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥

 

ስለዚህ ጳጳሳት ወይም ኤጲስ ቆጶሳት ነቀፋ የሌለባቸው ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ ሽማግሌ ሰው ሲሆን ኤዺስቆስ ማዕረጉ ነው፡፡
ሽማግሌዎች ሁልጊዜ በብዙ ቁጥር ነው የሚጠቀሱት፡፡ ጴጥሮስ ለአይሁድ ሐዋርያ ነበር፡፡

“ኢንተርፕረተር” የሚለው ቃል ከ“ፔትር ሮማ” የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “ታላቁ አስተርጓሚ” ማለት ነው፡፡ ጣኦት አምላኪ አሕዛብ ይህ ታላቅ ሰው የአማልክቶቻቸውን ፈቃድ ለነርሱ መተርጐም ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡

ባርቤሪያውያን ወደ ሮም ሲመጡ “ፔትር ሮማ” “የሮማው ጴጥሮስ” ነው ብሎ እነርሱን ለማሳመን ቀላል ነበር፡፡ ስለዚህ ካቶሊካዊነት የተመሰረተው በጴጥሮስ ዝና ላይ ነው፡፡ ነገር ግን በጴጥሮስ ላይ ተመስርቶ የሚደረግ መተካካት ከመጀመሪያውም ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት ኢየሱስ ጴጥሮስን ሰይጣን ብሎ ጠርቶታል፡፡

ጴጥሮስ ፈጽሞ ጳጳስ ነኝ ብሎ አያውቅም፡፡ ጴጥሮስ ያገባና በኢየሱስ ስም የተጠመቀ ሰው ነው፡፡ ጴጥሮስ ንስሐን ሰብኳል፡፡ በአንድ ወቅትም፡- “ብር እና ወርቅ የለኝም” ካለ በኋለ ብር እና ወርቅ በመስጠት ፈንታ ለማኙን ፈውሶታል፡፡

 

የሐዋርያት ስራ 3፡6 ጴጥሮስ ግን። ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።

 

ጳጳሳት ሐብታም ናቸው፤ ሚስት አያገቡም በእግዚአብሔርም ስም ፈንታ “አብ፣ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን የእግዚአብሔር “ስም” ፈጥረዋል፡፡ ሦስት ማዕረጎች እንዴት አንድ ስም ሊሆኑ ይችላሉ? በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ኢየሱስ ሁለተኛ ሰው ሆኑ ዝቅ የሚልበትን ሥላሴን ፈጠሩ፡፡ ጳውሎስ ደግሞ ተቃራኒውን አድርጓል፡፡ የመለኮት ሙላት ሁሉ በክርስቶስ ውስጥ ነው ብሎ ጻፈ፡፡

 

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።
ማቴዎስ 23፡9  አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ።

 

የካቶሊክ ቀሳውስት አባ ተብለው ይጠራሉ፡፡
“ፖፕ” የሚለው መጠሪያ “ፓፓስ” ከሚለው የኢጣልያንኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜውም አባት ነው፡፡

 

1 ኛ ቆሮንቶስ 11፡4 ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋርዳል።

 

ጳጳሱ ራሱ ላይ ቆብ ሳይደፋ የተነሳውን ፎቶ አይተህ ታውቃላህ? በአደባባይ ላይ በሚወጣበት ጊዜ ሁሉ ባለ ሦስት ድርብ ዘውዱን ባይደፋ እናኳ የሆነ ዓይነት ቆብ ወይም የራስ መሸፈኛ ከመጠቀም አይቆጠብም፡፡

ለምን? ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ወይም ፖንቲፍ የባቢሎያዊያን ምስጢራዊ ሊቀ ካህናት ሲሆን የክህነት ተግባሩን በሚያከናውንበት ጊዜ ሁሉ ዘወትር ራሱን ይሸፈናል፡፡ ጳጳሳቱም ይህንን ማዕረግ በመውሰድ እራሳቸውን ይከናነባሉ፡፡

Caesar
ቄሳር

የመጀመሪያው የሮም ንጉሰ ነገስት አውግስጦስ እራሱን እንደ ፖንቲፍ በቁጠር አናቱን ይሸፈን ነበር፡፡

የንጉሰ ነገስቱ የአውግስጦስ ሐውልት (አውግስጦስ ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ወይም ፖነቲፍ የተባለው እንዲሁም የባቢሎናውያን ምስጢር ሊቀካህን የነበረው) የተወሰነው የልብሱ ክፍል ራሱን እንደሚሸነው ያሳያል፡፡

pope
ጳጳስ

ዘመናዊው ጳጳስ ወይም ፖፕ ራሱን ለመሸፈን “ነጭ የራስ ቆብ” በራሱ ላይ ይደፋል፡፡

ጳጳሱ ባለ ሦስት ተደራቢ ዘውድ ይደፋል፡፡ ኢየሱስ ግን የእሾክ አክሊል ነበር የደፋው፡፡

የጥንታዊቷ ባቢሎን ምስጢራት ወደ ጴርጋሞስ ተስፋፍቶ ነበር፤ ከዚያም ጴርጋሞች በላይሲማከስ ተያዘች (የጥንት ባቢሎን ማለት ኒምሮድ በእግዚአብሔር ላይ ባመጸበት ዘመን ከጥፋት ውሃ በኋላ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ጠላት የነበሩት ናቸው።) ላይሲማከስ የግሪክን ዓለም አቀፍ ግዛት ከታላቁ እስክንድር ሞት በኋላ ለአራት ከከፈሉት የግሪክ ጀነራሎች አንዱ ነበር፡፡ የእርሱ መኖሪያ የነበረው የጴርጋሞስ ግዛት የምስጢራዊው ባቢሎን እርኩሰት የመኖሪያ ስፍራ ነበር፡፡ ከዚያም የጴርጋሞስ ግዛት እስከነ እርኩሳን ምስጢራቱ ንጉስ አታለስ ሦስተኛው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ133 በሞተ ጊዜ ለሮማውያን ተሰጡ፡፡ አታለስ ልጅ ስላልነበረውና በሚሞትበት ወቅት የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይፈጠር ብሎ ጴርጋሞስን ግዛት ለሮም ሰጠ፡፡ ጴርጋሞስ በጣም ሐብታም ሃገር ስትሆን ይህም ሐብት የሮማውያንን ባህሪ ብልሹ እንዲሆን ያደረገው የብልፅግና መጀመሪያ ነበር፡፡

ሜዶናዊው ዳርዮስ ባቢሎንን አሸንፎ በነገሰ ጊዜ የባቢሎንን ምስጢር ካህናት ለደህንነታቸው በመስጋት ሸሽተው የተወሰኑት ጴርጋሞስ ውስጥ ሰፈሩ፡፡

 

ራእይ 2፡12 በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል።
13 የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤

 

ጴርጋሞስ “የሰይጣን ዙፋን” ተብላ ከመጠራቷ አንጻር የአስከፊ ስህተቶች ምንጭ መሆኗ ግልፅ ነው፡፡

ኒምሮድ ከጥፋት ውሃ በኋላ የአስከፊ ስህተቶች ፈጣሪና የባቢሎንን መንግስት የመሰረተ እንዲሁም የባቢሎንን ግንብ የገነባ ሰው ነበር፡፡ ስለዚህ ስህተት ከባቢሎን ተነስቶ በጴርጋሞስ አድርጎ ወደ ሮም ገባ፡፡

የሮም ንጉሰ ነገስታት ፖንቲፍ የተባለውን የጣኦት አምላኪዎቹን ማዕረግ ወስደዋል፡፡ በ312 ዓ.ም ኮንስታንቲን ንጉሰ ነገሰት ከሆነ በኋላ በግዛቱ ውስጥ ክርስትና ተቀባይነት ያለው ሐይማኖት እንዲሆን አደረገ፡፡ ንጉሰ ነገስታቱ ክርስቲያኖች ቢሆኑም እንኳ ፖንቲፍ የሚለውን ማዕረግ ግን ይዘውት ቀርተዋል፡፡ በ378 ክርስቲያን የነበረው ቲዎዶሲየስ ሲነግስ ይህንን የአረማውያን ማዕረግ ተወው፡፡ እርሱ የጣለውን ማዕረግ የሮማ ጳጳሳት አንስተው መጠቀም ጀመሩ፤ ምክንያቱም ሮምን ያሸነፉት ባርቤሪያኖች ላይ ሥልጣንና ኃይል ለማግኘት ፖንቲፍ የሚለው መጠሪያ ያግዛቸው ስለነበር ነው፡፡ በዚህም መንገድ ጳጳሱ የባቢሎን ምስጢራት መሪ ሲሆን የሮማ ካቶሊካዊ እምነትም የባቢሎን ምስጢር ሆነች፡፡