በመጀመሪያዎቹ 4 የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ 4 ያልተለመዱ ስሞች
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ራዕይ መጽሐፍ 4 ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የተጠቀሱ ስሞች በለዓም፣ ኤልዛቤል፣ ኒቆላውያን፣ እና ጴርጋሞን (በግሪክ ጴርጋሞስ)።
First published on the 18th of June 2021 — Last updated on the 31st of July 2021በለዓም። ኤልዛቤል። ኒቆላውያን። ከዚያም ደግሞ በግሪክ ጴርጋሞስ የምትባለዋ ጴርጋሞን። ሶስተኛዋ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት የግሪክ ስም ያላት።
ራዕይ ምዕራፍ 2 ውስጥ ከተጠቀሱ አራት ቤተክርስቲያን ሶስቱ ለምንድነው በነዚህ ያልተለመዱ ስሞች የተጠሩት? ከስማቸው ምን እንማራለን?
54-0512 ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት
… የኒቆላውያን ክሕነት እዚያው ኤፌሶን ውስጥ ነው የሚጀምረው። ያ የቤተክርስቲያን ዘመንም የሚወድቀው እዚያው ነው … ፈጽሞ ከመጥፋቱ በፊት ኒቆላውያን የራሳቸውን አስተምሕሮ ጀመሮ፣ ይህም የወንድማማች ክሕነት ነው።
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን በ170 ዓ.ም አካባቢ ነው የተጠናቀቀው። ብዙዎቹ ሐዋርያት በ70 ዓ.ም አካባቢ ተገድለው ስላለፉ የሐዋርያት ተጽእኖ እየተዳከመ ነበር። ከዚያ በኋላ ሰባኪዎች ራሳቸውን ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ የሆኑ ካሕናት አድርገው መሾም ጀመሩ። ድርጅታዊ አሰራር እና ማዕረጎች ቤተክርስቲያንን ተቆጣጠሩዋት።
ይህን ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ለማሳየት በክረምት የወንዝ ውሃ በጎርፍ ሲሞላ ከኬይስተር ወንዝ የሚመጣ ደለል አፈር የኤፌሶንን ወደብ እየሞላው ነበር። በ40 ዓመታት ውስጥ ወደቡ በሰባት ሜትር ጥልቀት ባለው ደለል ተሞልቶ ነበር።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በ170 ዓ.ም በተጠናቀቀ ጊዜ በየከተማው ውስጥ ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ የአንድ ከተማ ቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ተሹሞ ማየት የተለመደ ሆኖ ነበር። በዚያ ጊዜ ሽማግሌዎችን ከጳጳሱ እንደሚያንሱ አድርጎ ማየት ተጀመረ። የሽማግሌዎች ስልጣን እየተናቀ ነበር። የቤተክርስቲያን መሪነትን ቦታ ማዕረግ እና ስም ያላቸው ሰዎች መያዝ ጀመሩ። ቤተክርስቲያን እራሷን ልክ እንደ ሮማ መንግስት ዓለም አቀፍ ድርጅት አድርጋ ማየት ጀመረች። ቤተክርስቲያን የእድገት አቅጣጫዋን የአካባቢዋ ሥርዓት እንዲወስነው ፈቀደች።
ቤተክርስቲያን ለማሕበራዊ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ድርጅት ሆነች። ቤተክርስቲያን ኢየሱስን የሚወዱ ሰዎች ስብስብ መሆኗ ቀርቶ የሰዎችን ትዕዛዝ የሚያከብሩ ሰዎች ድርጅት ሆና ቀረች፤ ደግሞም እንደ ጥምቀት፣ የጌታ እራት፣ እግር መተጣጠብ የመሳሰሉ ሥርዓቶች እና በቃሉ ላይ ያላቸው እምነት አንድ ያደርጋቸው ነበረ ግን ይህም ቀረ።
ሮማውያን በአስተዳደር ስራ የተካኑ አስተዳዳሪዎች ነበሩ፤ ስለዚህ ድርጅቶች በሙሉ የሮማውያንን የተቀላጠፈ አስተዳደራዊ አሰራር ተከትለዋል።
ሰው ሰራሽ ሕጎች በዙና እውነት ጠፋች።
ቤተክርስቲያን እንደ ድሆችን ማብላት ከመሳሰሉ ድርጅታዊ አሰራሮች አንጻር ይበልጥ ሮማዊ መልክ እየያዘች ሄደች።
በተለያዩ ባሕሎች ውስጥ የተለያዩ ልማዶች ሳይለወጡ ተጠብቀው መቆየት ነበረባቸው። ስለዚህ ተመሳሳይ ስርዓቶችን የሚያስጠብቁ በተለያዩ ቡድኖች መካከል የሚንቀሳቀሱ ወኪሎች ያስፈልጉ ነበር።
በ170 ዓ.ም እያንዳንዱ ማሕበረሰብ የተወሰነ ማዕረግ ባላቸው ባለ ስልጣኖች ይመራ ነበር፤ ከእነዚህም ባለ ስልጣኖች በላይ ጳጳሱ ነበረ። ጳጳሱ ደግሞ ማሕበረሰቡን በሙሉ ይወክላል። ሁሉም ማሕበረሰቦች የአንዲት ዓለም አቀፋዊ ወይም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አካላት ሆኑ (“ካቶሊክ” ማለት ዓለም አቀፋዊ ሲሆን ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው ኢግናሽየስ ነው)። የጳጳሳት መማክርት ጉባኤዎች ስብሰባ እየተቀመጡ የብዙ ማሕበረሰቦችን ሃሳብ ወክለው ይወያዩ ነበር። ቀስ በቀስ እነዚህ ምክር ቤቶች የሚያወጧቸው ትዕዛዛትና ውሳኔዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ማፈንገጥ ጀመሩ።
54-0513 የአውሬው ምልክት
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የጀመረው የኒቆላውያን አስተምሕሮ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ተቀባይነት አግኝቶ ጸንቶ ቀረ። እነርሱም እንዲህ ብለው ማሰብ ጀመሩ፡- “በቃ ይህ ነው እውነቱ።” እናንተ ሁላችሁ መጽሐፍ ቅዱስ የምታነቡ ሰዎች ግን እንዴት እንደመጣ ታውቃላችሁ።
የጀመረው በ306 ዓ.ም ኮንስታንቲን ክርስትናን ተቀበለ በሚሉበት ዘመን ነው። እርሱ ግን አልተለወጠም ነበር። ይህ ሰው ይሰራቸው ከነበሩ ክፉ ሥራዎቹ አልተመለሰም።
… እንግዲህ የኒቆላውያን ሥራ መጀመሪያ አስተምሕሮ ሆነ፤ ቀጥሎም ስደት ሆነ።
ሰውን ከፍ ማድረግ ሁልጊዜም ከፍ የተደረገውን ሰው የሚቃወሙትን ማሳደድ ያስከትላል።
ከፍ የተደረገውን ፓስተር ብትቃወሙ ከቤተክርስቲያን ትባረራላችሁ።
63-0319 ሁለተኛው ማሕተም
ኒቆላዊነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የክርስቶስ ተቃዋሚ ተብሏል፤ ምክንያቱም የመጀመሪያውን የክርስቶስ ትምሕርት እና ሐዋርያቱን የሚቃወም ነው።
… ሲጀመርም እርሱ የኒቆላዊ መንፈስ ነው። ከዚያም በኋላ በሰው ውስጥ ስጋ ለብሶ ተገለጠ፤ ቀጥሎም ዘውድ ጫነ፤ ዙፋን ላይ ተቀምጦም ነገሰ።
ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ በ860 ዓ.ም አካባቢ ነጠላ ዘውድ ተጭኖለት ተሾመ። ከ1305 በኋላ ይህ ዘውድ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ሆነና እስከ 1963 ድረስ ይጠቀሙበት ነበር። በ1963 ወንድም ብራንሐም ራዕይ ምዕራፍ 6 ውሰጥ ከተጻፉት ሰባት ማሕተሞች ስድስቱን የገለጠ ጊዜ ፖፑ እና ካቶሊክ የነበረው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኬኔዲ ሁለቱም በአንድ ጊዜ ሞቱ። ፖል 6ኛ የተባለው አዲሱ ፖፕ የተሾመ ጊዜ ዘውድ ጫነ ግን ባለ ሶስት ድርቡን ዘውድ አይደለም፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፖፑ ባለ ሶስት ድርቡን ዘውድ መጫን አቆመ። ይህ ዘውድ ችግር እንዳለበት ገብቷቸዋል። ማሕተሞቹ በመፈታታቸው የተለቀቀው ብርሃን በካቶሊክ ጨለማ ሥርዓት ላይ ታላቅ ነውጥ አምጥቷል።
61-0806 የዳንኤል ሰባኛው ሱባኤ
… እግዚአብሔር በፊት አሁንም የተደራጀ ሐይማኖትን እንደሚቃወም እናውቃለን።
አዎን አለቃዬ። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ኒቆላውያንን እጠላለው።” “ኒቆ” ማለት “ምዕመናንን መግዛት መጨቆን” ነው። ምዕመናን ማለት ቤተክርስቲያን ወይም አካሉ ማለት ነው። “ኒቆ” ማለት “ማሸነፍ መግዛት” በሌላ አነጋገር … አንድን ቅዱስ ሰው ከሌሎች በላይ ስልጣን ሰጥቶ መሾም ነው። ነገር ግን ሁላችንም ልጆች ነን፤ ሁላችንም አንድ ንጉስ አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው። ለሁላችንም አንድ ቅዱስ ጌታ አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው። አሜን። እርሱም በመንፈስ ቅዱስ መልክ በመካከላቸን ነው። እርሱ ነው ቅዱስ።
… ከዚያ ቀጥሎ የመጣው የአስተምሕሮ ነገር ነው። ከዚያ በኋላ ደግሞ የኒቆላውያን ቤተክርስቲያን ጋብቻ እና ቅዱሳንን ማሰደድ ተከተለ።
… ይህ የኒቆላዊነት ሥርዓት እየተስፋፋ ሲሄድ አዩ፤ ከዚያ አንድ ቅዱስ ሰው ወስደው ሊሾሙት አሰቡ። ምን ብለው? ፖፕ።
… አሁን አይሁዶች ወደ ሃገራቸው ገብተዋል፤ ስለዚህ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያው ላይ ደርሷል፤ ይህም የኒቆላውያን ዘመን -- ወይም የሎዶቅያውያን ዘመን ነው፤ ስለዚህ የጌታ ምጻት፣ የሁሉ ነገር መጨረሻ፣ የዚህ ዘመን ፍጻሜ፣ የንጥቀት ቀን ምን ያህል ቀርቧል?
በሎዶቅያውያን የመጨረሻ የቤተክርስቲያን ዘመን በኒቆላውያን መንፈስ ላይ ብዙ ትኩረት አለ፤ ይህም መንፈስ ሰዎችን እንደ ፈላጭ ቆራጭ እና የቤተክርስቲያን መሪዎች አድርጎ ከፍ ያደርጋቸዋል።
“ኒቆ” (ድል) እና “ላዎስ” (ሕዝብ)።
ኒቆላውያን ማለት “ሕዝቡን ድል የሚነሱ” ነው።
1960 12 07 የጴርጋሞን ቤተክርስቲያን ዘመን
አስተምሕሮውን የሚከተሉ ሰዎችን ታግሰሃቸዋል … (ድሮ በዚያ ዘመን ኤፌሶን ውስጥ የኒቆላውያን ሥራ ነበር የሚባለው አሁን “አስተምሕሮ” ሆኗል) … የኒቆላውያን ትምሕርት … (ከዚህ በፊት ባስተማርኳችሁ መሰት እዚህ ሁሉ እንዴት እንደደረሰ ታስታውሳላችሁ? ኤፌሶን ውስጥ የነበረው ሥራ አሁን “አስተምሕሮ” ሆነ) … እኔ የምጠላው የኒቆላውያን ትምሕርት።
ንሰሃ ግባ፤ አለዚያ በቶሎ እመጣብሃለው፤ እነርሱንም እዋጋቸዋለው (እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን አይደለም)
… ወደ ክሕነት እያዘነበለ የነበረው ክርስትና ሰዎችም በቤተክርስቲያናቸው የክሕነት ሥርዓትን ይፈልጉ ስለነበረ በኤፌሶን ቤተክርስቲያን ጥናት እንዳየነው የኒቆላውያን ትምሕርት ቀስ በቀስ ተቆጣጠራቸው፤ ይህን ወደፊት በሰምርኔስ እና በሌሎቹም ቤተክርስቲያኖ እናየዋለን።
… አስታውሱ፤ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ከጥንትም ጀምሮ ከትልቆቹ ጉባኤዎች መካከል ተገፍታ የምትወጣዋ ትንሽዬ ሕብረት ናት። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን እንደ ድርጅት ተደራጅታ አታውቅም ምክንያቱም ድርጅት ሳትሆን ሕያው የሆነች የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ናት። ይህች አካል በምድር ላይ ትኖራለች በውስጧም መንፈስ ቅዱስ ይንቀሳቀሳል። ስለዚህ ክርስቶስን ማደራጀት አትችሉም፤ አይሆንም። ስለ ሎዶቅያውያን ዘመን በምናጠናበት ጊዜ ይህንን እንድታስታውሱ እፈልጋለው። ደግሞ አስታውሱት፤ ይዛችሁም ጠብቁት ምክንያቱም የምናገረው ቃል በሙሉ በቴፕ ተቀርጾ ተቀምጧል።
… ስለዚህ ኮንስታንቲን በልቡ ግዛቱን የማጠናከር ሃሳብ ይዞ በመነሳት (ሮም ሁልጊዜ ግዛቷን ማጠናከርና ዓለምን ሁሉ መቆጣጠር ፍላጎቷ ነበር) ከባዕድ አምልኮ የሰበሰባቸውን ሃሳቦች ይዞ በመምጣት የክርስትና ሃሳቦችንም ጨምሮ በመያዝ በአንድነት አዋህዷቸው አጣምሯቸው ለራሱ ከሁሉም የሚበልጥ መንግስት ሊመሰርት ፈልጎ ነበር። አያችሁ? ምክንያቱም እርሱ … ይህ ሁሉ እራሱን በምድር ላይ ከነበሩ ነገስታት ሁሉ ታላቅ ለማድረግ ፈልጎ ነው።
የኮንስታንቲንን መለወጥ በተመለከተ፡- እርሱ ፖለቲከኛ ነበረ እንጂ አንዳንዶች የእግዚአብሔር ቅዱስ ተከታይ ነው እንደሚሉት አልነበረም። በፍጹም አልነበረም!
… ስለዚህ መንግስቱን ለማጠናከር ይጠቅመዋል። ይህንንም ለማድረግ የአረማውያን ሥርዓቶችን ወደ ኒቆላውያን ቤተክርስቲያን አምጥቶ አስገባቸው። ይህም በሰዎች ስርዓት የተመሰተው ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ጅማሬ ነው። ኮንስታንቲን ወደዚህች ኒቆላዊት ቤተክርስቲያን የጣኦት አምላኪዎችን ልማዶች አስገባ፤ ይህም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጅማሬ ነው።
… ይህ ሃሳቡ እንዲሳካለት የአረማውያንም የክርስቲያኖችም ትኩረት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲሳብ ለማድረግ ኮንስታንቲን ብዙ ዓለማዊ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን አዘጋጀ።
… ስለዚህ ኮንስታንቲን የተጠቀመው ዘዴ በለዓም የተጠቀመው ዘዴ ራሱ ነው። በምክር ቤታቸው ካደረጉት ስብሰባ በኋላ ባስተላለፉት ውሳኔ ጳጳሳትን በቤተክርስቲያኖች ላይ አለቃ አድርገው አስቀመጧቸው፤ ምዕመናንን ከእነርሱ በታች ተገዢዎች እንዲሆኑ አደረጓቸው።
“ምዕመናን አንዳችም ነገር በራሳቸው እንዳያስቡ ተደረጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስንም በራሳቸው አንብበው መረዳት ተከለከሉ።” ይህ ሁሉ የተፈቀደው ለቄሶች ብቻ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ማብራራት የሚችሉት ቄሶች ብቻ ናቸው ተባለ።
… “ካሕኑ ብቻ ነው መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚችለው፤ ስለዚህ ጉባኤው መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብም አያስፈልገውም፤ ምንም ነገር ማድረግ የለበትም፤” ከዚያም በላይ ግን ጳጳሱ ሆን ብሎ ጉባኤው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እንዳይኖራቸው አደረገ።
ይህም አሰራር መልካም መስሎ ታያቸው፤ ስለዚህ በራሳቸው ፈቃድ ባደረጉት ውሳኔ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማስረዳት ለካሕናቱ ብቻ ተባለ።
እነርሱም ሃብታሞች ስለነበሩ ይህ ሃሳብ መልካም ይመስል ነበር፤ ኮንስታንቲን ጳጳሳቱን ወደዚህ ታላቅ ስብሰባ በጠራቸው ጊዜ ትልልቅ ሕንጻዎችን እንደ ስጦታ አበረከተላቸው። ብዙ ገንዘብና … ትልልቅ ሕንጻዎችን ለቤተክርስቲያን ሰጠ። ሕጻዎቹ ሁሉ ታላላቅ እና ውብ ሕንጻዎች ነበሩ፤ እርሱም ለቤተክርስቲያን ሰጣቸው።
…
ከዚያም በተጨማሪ ጳጳሶቹን በሙሉ ትልልቅ የካሕናት ልብስ አለበሳቸው። ከዚያም በተጨማሪ ትልልቅ መቆሚያ ስፍራ አዘጋጀላቸውን ልክ እንደ ጣኦት ከፍ ብለው እንዲቆሙ አደረገ። እነርሱ ከሚቆሙበት በታች የእምነ በረድ መሰዊያዎች አዘጋጀ። ይህንን ሁሉ ሃሳብ ከጣኦት አምልኮ ያመጣው ነው፤ እርሱ ወደ ክርስትና ተለወጠ በተባለ ጊዜ ይህንን የጣኦት አምልኮ ልማድ ወደ ቤተክርስቲያን ይዞ ገባ። አያችሁ፤ የተቀረጸ ምስል ጣኦትን አውርደው በቦታው ጳጳሱን ተኩ። ለጳጳሱ መሰዊያ ተዘጋጀለት፤ ከጣኦት ጋር ተመሳሳይ ነገር፤ ደግሞም ጳጳሱን አምላክ አደረጉት። ጳጳሱን ወደ ስልጣን ስፍራ ከፍ አደረጉት፤ ሁሉም ነገር የሚደረገው እርሱ ሲፈቅድ ሆነ፤ እርሱንም አምላክ እንዲመስል አደረጉት። ከአሕዛብ አማልክት አንዱን እንዲመስል በማድረግ ፈንታ ኢየሱስ የሚለብሰውን ዓይነት ልብስ እንዲለብስ አደረጉ። አያችሁ? በተቀመጠበትም ልክ ጣኦት እንዲመስል አደረጉት።
አሕዛብም ይህን ባዩ ጊዜ ምን እንዳሉ መገመት ትችላላችሁ፡- “ይህንማ መቀበል እንችላለን፤ ስናናግረው መልሶ የሚያናግረን አለ። እስካሁን መናገር የማይችል ጣኦት ፊት ስንጸልይ ነበር፤ ይህ ሰው ግን መናገር ይችላል።”
… ስርዓቶች። የት? ባፕቲስቶች፣ ፕሬስቢተሪያኖች፣ እንዲሁም ጴንጤቆስጤዎች ዘንድ ሁሉ ሐይማኖታዊ ሥርዓት ሥር ሰደደ። የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ፒያኖ መጫወት ወይም ሌላ ዓይነት ሙዚቃ እየመቱ መዝለል ነው፤ ልክ ፒያኖው ጸጥ ሲል፤ ከዚያ ወዲያ ወጥተው መስረቅ፣ ማጭበርበር፣ መዋሸት እና ሌላም ክፉ ነገር ማድረግ ነው ሥራቸው። ነገር ግን እውነተኛው … ከዚያው ስለ ሁሉም ነገር እና ስለ ሁሉም ሰው ማውራት ብቻ። ሜተዲስቶች ብቻ አይምሰሉዋችሁ፤ ባፕቲስቶች፣ ፕሬስቢተሪያኖች፣ ካቶሊኮች፣ ጴንጤቆስጤዎችና በሎዶቅያውያን ዘመን የሚኖሩ ሁሉ።
… ኒቆላውያን በዚያን ጊዜ በድርጅታዊ ሥርዓት ነበር የሚንቀሳቀሱት፤ እነርሱም ከአረማውያን ቤተክርስቲያን ጋር ተጋቡ፤ የጣኦት አምላኪዎችን መሰዊያዎች የክርስቲያን መሰዊያ አደረጉ። የማይናገረውን የአሕዛብ አምላክ አምጥተው በጳጳስ መልክ የሚናገርና የሚያወራ አደረጉት። ቦታ ሰጥተውት አስቀመጡት፣ ልብስ አለበሱትና አምላክ እንዲመስል አደረጉት። አያችሁ? በውጭ ያለው አይደለም ዋናው፤ በውስጥ ያለው ነው። እነዚያ ሁለት የበቆሎ ፍሬዎች አንድ ዓይነት ይመስላሉ። ነገር ግን ዋናው ውጭው አይደለም፤ ውስጡ ነው እንጂ። ውስጡ ማለት ሕይወቱ ነው።
የእግዚአብሔር በጎች ድምጹን ያውቁታል፤ በትክክል ያውቃሉ። መጀመሪያ ማግኘት አለባችሁ … ማንም ሳያውቃችሁ ትወጣላችሁ ከዚያም … ምን ታደርጋላችሁ? ከሌላው ጊዜ ሁሉ የበለጠ ትጎዷቸዋላችሁ።
… ስለዚህ ምን አደረገ? በለዓም ቅጥረኛው ነብይ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ገንዘብን የሚወደው ነብይ ወደ ጳጳሱ ወይም ወደ ፖፑ ላከ። ንጉሱ ባላቅም እንዲህ አለው፡- “ወደዚህ ወጥተህ እነዚህ ሕዝብ ብትረግማቸው ታላቅ ሰው አደርግሃለው።” እግዚአብሔርም በለዓምን ተናገረው። ዛሬ በዚህ ዓለም ውስጥ ስንት በለዓሞች ያሉ ይመስላችኋል? ሜተዲስት አገልጋዮች፣ ባፕቲስት አገልጋዮች፣ ካቶሊክ አገልጋዮች (ማረን!) የእግዚአብሔርን ሃሳብ … ይህንን ታሪክ ብታነቡ እኔ ያነበብኩትን መጽሐፍ ብታነቡ። “በለዓም!”
… አሁን ግን የተናገረውን ልብ በሉ፡- “ጀርባውን ከሁሉ የከፋውን በኩል ጀርባውን ተመልከቱ።” በለዓም እንዲህ አለ፡- “አሁን ጀርባቸውን ችግር ያለበትን ጀርባቸውን ማለትም የሚያደርጉትን አያለው። የማደርገው ይህ ነው -- ተራነታቸውን አያለው፤ የማይረቡ ሰዎች ናቸው።” ድክመታቸውን እንመልከት ካላችሁ ሰዎቹ መጥፋታቸው ነው። ምክንያቱም በሕጉ የተጠቀሱ ሐጥያቶችን ሁሉ አድርገዋል። ነገር ግን እርሱ ማየት ያልቻለው ነገር ነበረ፤ ያም ስለ እነርሱ የተመታውን ዓለት፣ የናሱን እባብ፣ በመካከላቸው ያለውን የንጉስ እልልታ፣ ፈውስ፣ ምልክቶችና ድንቆች፣ ከላያቸው ያለው የእሳት ነበልባል፤ እነዚህን ማየት አልቻለም።
ያ ዓይኑ የታወረ ነብይ ይህን ማየት አልቻለም። ነገር ግን ቆሻሻነታቸውን አጉልቶ እያሳየ ነበረ፡- “የሌላ ሰው ሚስት ይዞ የሄደ ሰው አውቃለው። ይህኛው ደግሞ ገንዘብ መስረቁን አውቃለው።” አዎ። አዎ። ይህን አውቃለው። እነርሱ በመካከላቸው መልካም ነገር ነበረ፤ እርሱ ግን ድክመታቸውን ብቻ እያየ ነበር። አያችሁ?
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለ፡- “እኔ የተናገርኩትን ብቻ ትናገራለህ።” በለዓምም በመንፈስ ሆነ፤ ተመስጦ ውስጥ ገባ፤ ከዚያም እስራኤልን በመርገም ፈንታ ባረካቸው።
… ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ከዲኖሚኔሽን ጋር ያጋባች ጊዜ ሙት ሆነች።
… መንፈሳዊው ግልሙትና “ክርስቲያን” ነኝ እያላችሁ እንደ ዓለም ስትኖሩ ነው።
… ስለዚህ ኮንስታንቲንም ያዘጋጀው ድግስ ልክ እንደ በለዓም ነው። ልብ በሉ። በለዓም እንዳዘጋጀው የአሕዛብ ግብዣ ኮንስታንቲንም የአሕዛብ ግብዣ አዘጋጀ። ጴርጋሞን ተጋበዘች።
… የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ጳጳስ የሆነው ቦኒፌስ 3ኛው ነው … እርሱም በእነርሱ ዘንድ በሰው መልክ የተገለጠ አምላክ ሆነ።
ፖፕ ቦኒፌስ 3ኛው ዓለም አቀፍ ጳጳስ ተደርጎ ከተሾመ በኋላ ውድ የሆኑ የካሕን ልብሶችን ለብሶ የክርስቶስ ምትክ በመሆን በዙፋን ላይ በክርስቶስ ቦታ ተቀመጠ፤ እርሱንም ቪካሪየው ክሪስቲ (VICARIVS CHRISTI) አሉት።
[WIKIPEDIA ቦኒፌስ 3ኛው 606-607 ሌላኛው ታዋቂ ድርጊቱ የመነጨው ከንጉስ ፎካስ ጋር ከነበረው ቅርበት ነው። እርሱም ከንጉስ ፎካስ ዘንድ አዋጅ አጻፈ፤ ይህም አዋጅ በድጋሚ እንዲህ የሚል ነበር፡- “የብጹዕ ሐዋርያ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያኖች ሁሉ ራስ ትሁን”። ይህም አዋጅ “የዓለም ሁሉ ጳጳስ” የሚለው ማዕረግ የሮም ጳጳስ ብቻ ብቻ የሚጠራበት ማዕረግ እንዲሆን አደረገ፤ ከዚህም የተነሳ “የዓለም ጳጳስ” ለመሆን ጥረት ሲያደርግ የነበረው የኮንስታንቲኖፕሉ ጳጳስ ሳይሪያከስ ጥረቱን እንዲተው አደረገው።]
60-1211 አሥሩ ቆነጃጅት እና መቶ አርባ አራት ሺዎቹ አይሁዶች
“የእግዚአብሔር ልጅ ተወካይ።” በሌላ አነጋገር “ልክ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በዚህ ምድር ላይ የተቀመጠ” እና “መጽሐፍ ቅዱስን እንዳሻው ለመለጥ ስልጣን ያለው ሰው” ማለት ነው። ስለዚህ “እመቤታችን ማርያም ሆይ” ብለን እንጸልይ ይላል። ፖፑ ምን ይላል? “እመቤታችን ማርያም ሆን ብለን እንጸልያለን!” ይላል። እርሱ ካለ አለ ነው። ሌላም ነገር ደግሞ “እንዲህ ወይም እንዲያ ያለ ነገር እናደርጋለን፤” በተባለ ጊዜ ፖፑ ምን ይላል ተብሎ ይጠየቃል። ፖፑ ካለ ፖፑ እንዳለ ነው የምናደርገው ተብሎ ጸንቶ ይቀራል። “በእግዚአብሔር ልጅ ፈንታ ተወካዩን ይሰሙታል።” በቅርቡ ደግሞ “ማርያም አልተቀበረችም” የሚል ትምሕርታቸውን አመጡ (ከዚያም መቃብሯን እና ተቀብራ የነበረችበትን ቦታ ምልክት አደረጉ)። ከዚያም እንዲህ አሉ፡- “ከሞት ተነስታለች” አሉ። ፖፑ እንዲህ አለ፡- “አዎ እርግጥ ነው።” ስለዚህ ማርያም ከሞት መነሳቷ እርግጥ እውነት ተደርጎ ተወሰደ፤ ምክንያቱም ፖፑ “የእግዚአብሔር ልጅ ተወካይ” ብሎታል።
ራዕይም ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ የተጠቀሱትን ሰባት ቤተክርስቲያኖች አብዛኞቹ የዛሬ ክርስቲያኖች ጥንት በታሪክ ውስጥ የነበሩ ሰባት ቤተክርስቲያኖች ብቻ አድርገው ነው የሚቆጥሯቸው።
ይህ አረዳድ ትክክል ቢሆን ኖሮ አንዳንድ የተጠቀሱ ስሞች ትርጉም አይኖራቸውም ነበር።
ለምሳሌ እንደ ኒቆላውያን፣ ኤልዛቤል፣ በለዓም፣ እና አንቲጳስ።
በታሪክ ውስጥ አንድም ክርስቲያን በነዚህ ስሞች ተጠርቶ አያውቅም።
ስለዚህ እነዚህ ስሞች አማኞችን ለማሳሳት ወደ ቤተክርስቲያን ስለገቡ ልማዶች የሚያስደሩ ናቸው።
ከዚያ ሌላኛው እንቆቅልሽ ደግሞ ጴርጋሞን የሚለው ስም ነው።
ስድስቱ ቤተክርስቲያን በተለመደ ስማቸው ነው የተጠቀሱት፤ ሶስተኛዋ የጴርጋሞን ቤተክርስቲያን ግን በግሪክ ስሟ ጴርጋሞስ ተብላ ነው የተጠቀሰችው። የኤፌሶን ግሪክኛ ስሟ ኤፌሶስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን አንድም ጊዜ ኤፌሶስ የተባለውን ግሪክኛ ስም አይጠቀምም።
ከሰባቱ ቤተክርስቲያኖች ስሟ በግሪክኛው ቅርጽ የተጠቀሰው የጴርጋሞን ቤተክርስቲያን ብቻ ናት። ለምንድነው?
ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ደቀመዛሙርት ማቴዎስ ምዕራፍ 24 ውስጥ ኢየሱስን ሲጠይቁት የሰጣቸው የመጀመሪያው መልስ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” የሚል ነበር።
እነዚህ ሁሉ ያልተለመዱ ስሞች ከአሳሳቾች ጋር የተያያዙ ናቸው። የሐይማኖት አሳሰችነው በግሪክ ፍልስፍና ሲታገዝ አሳሳችነቱ ይጨምራል። የግሪክ ምሑራን የተሳሳተ ሃሳብን በክርክራቸው ትክክል እንዲመስል በማድረግ ችሎታቸው የታወቁ ነበሩ። እነርሱ ከእውነት ይልቅ የሚያስደስታቸው በፍልስፍናቸው መራቀቅ ነው።
ከ70 ዓ.ም እስከ 120 ዓ.ም የነበረው ጊዜ ስለ ጥንቷ ቤተክርስቲያን አንዳችም ታሪካዊ ማስረጃ ያልተገኘበት ዘመን ነው።
እነዚህ ሚስጥራቸውን ደብቀው የያዙ የዝምታ ዓመታት ነበሩ።
እነዚህን የዝምታ ዓመታት በተመለከተ የታሪክ ምሑራን እንደ ማስረጃ የሚጠቀሙት ዓመታቱ ካለፉ በኋላ ሰዎች የጻፏቸውን ጽሑፎች ነው። ከዚህም የተነሳ አፈታሪኮች ከታሪክ ጋር ተቀላቀሉ።
ጴጥሮው ወደ ሮም ሄዶ ሲኖር ቆይቶ እዚያ ነው የተገደለው የሚለው ወሬ ታሪካዊ ማስረጃ የለውም። ሆኖም ግን ዛሬ 1.4 ቢሊዮን ካቶሊኮች ይህን አፈ ታሪክ እውነት ነው ብለው ያምኑታል። ሐሰተኛ ታሪኮች ዛሬም እንደ ጥንቱ ብዙዎችን የማሳት ኃይል አላቸው።
ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ እግዚአብሔር እያንዳንዷን አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሽማግሌዎች ሕብረት እንዲያስተዳድሯት እና ለሐዋርያት ትምሕርት ታማኝ እንዲያደርጓት ፈለገ። ነገር ግን ቀስ በቀስ “ጳጳስ” የሚለው ቃል ከቤተክርስቲያን ራስ ጋር ተያይዞ አዘውትሮ ይጠቀስ ጀመር።
የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት ሐዋርያት ከሞቱ ከሁለት ትውልድ በኋላ ሚስጥራዊና ለማንም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ጳጳሱ ቀስ ብሎ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ተገለጠ።
የአሕዛብ ቤተመቅደሶች ሁሉ የጉባኤያቸው ራስ የሆነ አንድ ካሕን አላቸው።
ክርስቲያኖችም ቀስ በቀስ ይህንን የአሕዛብ ምሳሌነት መከተል ጀመሩ።
አንጾኪያ የተከበረ የቤተክርስቲያን ታሪክ ያላት ከተማ ነበረች። የአንጾኪያው ኢግናሺየስ የአንጾኪያ ጳጳስ ነኝ አለ። ደግሞም በከተማ ላይ ጳጳስ ሆኖ የሚያገለግል ሰው በምድር ላይ የእግዚአብሔር ወኪል ነው በማለት እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “ጳጳሱን ማየት ያለብን ልክ እንደ ጌታ ነው።”
አንድ ጳጳስ የአንድ ከተማ ቤተክርስቲያን ራስ መሆኑ ለዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ትኩረት የሚስብ አዲስ ሃሳብ ነበረ።
ይህም ብዙሃኑ የሚቀበሉት መንገድ ሆኖ ተገኘ። እንዲህ ዓይነቱ አንድ ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ከፍ የማድረግ ልማድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ አሰራር ነው።
ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ ማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ ከዚያም ደግሞ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ማድረግም ትክክል አይደለም። ክርስቲያኖችም ይህ ስሕተትን ለመከላከል የሚጠቅም መንገድ ነው ብለው በማመን ሳያውቁት ለኒቆላውያን ሥራ ድጋፍ እየሰጡ ነበር። የኒቆላውያን ሥራ አንድን ቅዱስ ሰው በቤተክርስቲያን ውስጥ ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ ነው።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጳጳሶች ከሽማግሌዎች ይበልጣሉ ብሎ ማሰብ ተጀመረ።
በእግዚአብሔር እና በጉባኤው መካከል የሚቆም የአሮን ዓይነት ክሕነት ተጀመረ።
ቤተክርስቲያን ቸልተኝነት ከማብዛቷ የተነሳ ይህ ስሕተት ሲመጣ ወዲያ አላስወገደችውም። ክርስቲያኖች ቸልተኝነት ከማብዛታቸው የተነሳ የእምነታቸውን ትምሕርት ሐዋርያት ካስተማሩት አንጻር ጠናማነቱን በጥንቃቄ አልጠበቁም።
ሰው መሪ ይሁን የሚለው ሃሳብ ቀስ በቀስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ስር ሰደደ። ከጥቂት ዘመን በኋላ ሐዋርያት የተናገሩትን በመርሳት (ወይም እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሾ ለማግኘት በመስነፍ) ቤተክርስቲያኖች ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ተቀበሉ። ልክ ዛሬ እንደሆነው ማለት ነው።
ንጉስ ኔሮ ሮም ከተማ ላይ በ64 ዓ.ም የእሳት አደጋ ከደረሰባት ጊዜ ጀምሮ እርሱ በ68 ዓ.ም እስኪሞት ድረስ ክርስቲያኖችን አሳደደ። በዚያን ጊዜ ከዮሐንስ በቀር ሐዋርያት በሙሉ ሞተው አልቀዋል። ዮሐንስ ሁለት ጊዜ ለብዙ ዓመታት በፍጥሞ ደሴት ታስሮ ነበር። ዮሐንስ ሮማዊው ገዥ ኔሮ በዙፋን ላይ በነበረበት ሰዓት የፍጥሞ ደሴት ላይ ከ64 እስከ 68 ዓ.ም ድረስ በእሥር ቤት ነበረ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ዶሚቲያን የተባለው ንጉስ ክርስቲያኖ ከ68 እስከ 96 ዓ.ም አሳደደ። ስለዚህ ዮሐንስ ፍጥሞ ደሴት ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ታሰረ።
በ69 ዓ.ም የተወለደውን ታዋዊውን ክርስቲያን ፖሊካርፕን አስቡ።
ከ70 ዓ.ም በኋላ ስለ ቤተክርስቲያን የተጻፉ መረጃዎች ካለመኖራቸው የተነሳ የመጀመሪያዎቹ የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ሰማዕት ሆነው መሞታቸው ከተመዘገበ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተመዝግቦ የምናገኘው በ156 ዓ.ም በ86 ዓመቱ እንጨት ላይ በእሳት ተቃጥሎ የሞተውን ፖሊካርፕ ነው። የፖሊካርፕ መሞት የተመዘገበው እርሱ እንደሞተ ወዲያው ነው እንጂ ሞቶ ብዙ ዓመታት ካለፉ በኋላ አይደለም።
ፖሊካርፕ በምድር ላይ 86 ዓመታት ያህል ቢኖርም እንኳ እርሱ ጽፎ የምናገኘው ለፊልጵስዩስ ሰዎች የጻፈውን አንድ ደብዳቤ ብቻ ነው።
ደብዳቤውም ፖሊካርፕ እራሱ የጻፈው መልእክት በመሆኑ ጠንካራ ማስረጃ ነው።
ከዚያ ውጭ ስለ ፖሊካርፕ የምናውቀው ሁሉ በቀጥተኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ አይደለም። የምናገኘው ሌሎች ሰዎች ስለ እርሱ የተናገሩትን ነው። እንደዚህ ዓይነቶቹ መረጃዎች ደግሞ ብዙውን ጊዜ የአስተላላፊዎቹን ስሕተት ለመደገፍ እንዲመች ተጨማምሮባቸው ተለውጠው ነው የሚደርሱን።
ይህንን የስላሴ ስዕል ተመልከቱ። ፖፑ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ስለጫነ ሰዓሊው እግዚአብሔር አብን ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ አድርጎበት ነው የሳለው ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ ስዕል በዚያ ዘመን በነበሩ ካቶሊኮች ዘንድ ተቀባይነት ስለሚያገኝ ነው። ሁልጊዜም ቢሆን ማስረጃዎች የጊዜውን አመለካከት እንዲደግፉ ይለወጣሉ። ልክ እንደዚሁ ሐይማኖታዊ አመለካከቶች እና ትምሕርቶች ሚዛናቸውን ያልጠበቁ ስለሚሆኑ ከእውነታው ለይተን ልናያቸው ይገባል።
ስለ ፖሊካርፕ የወጣትነት ዘመን የምናውቀው ሁሉ አፈታሪክ ውስጥ ማለትም ከዘመኑ የተገኙ ማስረጃዎች የጎደሏቸው ታሪኮች ውስጥ ነው የሚገኘው።
አንዳንዶች የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የሰምርኔስ ጳጳስ አድርገው ሹመውታል ይላሉ። ይህ ግን ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፐሊካርፕ በተወለደ ጊዜ ከሐዋርያት መካከል አብዛኞቹ ቀድመው ሞተዋል።
የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ማንንም የቤተክርስቲያን ፓስተር አድርገው አልሾሙም።
(ፓስተር የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንዴ ብቻ ነው የተጠቀሰው)።
የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት አንድ ሰውን የአንድ ከተማ ጳጳስ አድርገው ሹመውም አያውቁም። ፊልጵስዩስ 1፡1 ውስጥ ጳውሎስ መልእክቱን ለፊልጵስዩስ ኤጲስ ቆጰሳት እንደጻፈ እናያለን። ኤጲስ ቆጶሳት ማለት ሽማግሌዎች ማለት ነው።
ፊልጵስዩስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት - 1
በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ከሽማግሌ የሚበልጥ አገልጋይ ካለ በመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ? አዎ፤ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነጻ ሕብረት ናት።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
ሶስቱ ዋና ዋና የአገልግሎት ዘርፎች ሐዋርያት፣ ነብያት፣ እና አስተማሪዎች ናቸው። አጥቢያ ቤተክርስቲያኖችን ለመትከል የሚያስፈልጉ እነዚህ ሶስቱ ነበሩ።
ፓስተሮች ደግሞ በዚህ ቃል ውስጥ ጭራሽም አልተጠቀሱም።
ሐዋርያት አዲስ ኪዳን ውስጥ በጻፉዋቸው መልእክቶችና ወንጌሎች ላይ የተመሰረተ ጤናማ ትምሕርት ከመለኮታዊ የተዓምራት እና የፈውስ ስጦታዎች እንዲሁም ከልሳን ስጦታዎች የበለጠ ዋጋ ይሰጠው ነበር። ነብያት ሁልጊዜ ስለ ወደፊቱ በትክክል በመተንበይ አማኞች ሊመጣ ላለው እንዲዘጋጁ ይረዱዋቸው ነበር።
ነገር ግን ብዙዎቹ ሐዋርያት በ70 ዓ.ም ከሞቱ በኋላ የተጻፉ ማስረጃዎች ባለመገኘታቸው የተነሳ ከ70 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 120 ዓ.ም ድረስ ያሉት ዓመታት የጸጥታ ዘመን ሆነው ቀሩ።
ቀስ በቀስ እና በጸጥታ ቤተክርስቲያን ላይ የመጣባት ጥላ እየተስፋፋ ሄደ።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የመከተል የቀደመ ፍቅራቸው ሲቀዘቅዝ እና ቸልተኞች ሲሆን አንድ ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ የአንድ ከተማ ክርስቲያኖች ራስ ነው የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ሃሳብ ወደ ቤተክርስቲያን ሾልኮ ገባ። ጥንቃቄያቸውን ጣሉ፤ የሚሰሙትንም ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መመርመር አቆሙ።
ኤፌሶን ማለት ዘና ብሎ መተኛት ማለት ነው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ቀስ በቀስ እየተንሸራተተች የሰው አመራር ባሪያ ወደ መሆን ወደቀች።
የአንጾኪያ ጳጳስ ተብሎ የሚታወቀውን ኢግናሺየስ አስቡ። (የከተማ ጳጳስ የሚለው ማዕረግ በሐዋርያት ዘንድ እውቅና የሌለው እንግዳ ማዕረግ ነው)። ሪቻርድ ፕሬቮ የተባለው የታሪክ ምሑር እንደጻፋ ኢግናሺየስ የሞተው በ135 እና 140 መካከል ነው። ሆኖም ከ314 ዓ.ም በኋላ የጻፈው የካቶሊክ የታሪክ ምሑር ዩሰቢየስ እንዳለው ኢግናሺየስ የሞተው በ108 ዓ.ም ነው። ዩሰቢየስ ግን ማስረጃ አላቀረበም። ዩሰቢየስ በኖበት ዘመን የከተማ ጳጳስ የሚለው ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ቆይቷል። ስለዚህ የቂሳሪያ ማርቲማ ጳጳስ የነበረው ዩሰቢየስ የከተማ ጳጳስ የሚለውን የተሳሳተ ሃሳብ 30 ዓመታት ያህል ወደ ኋላ በመግፋት ሃሳቡን እንደምንም ብሎ ከሐዋርያት ጋር ለማገናኘት ሞክሯል። ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ የተፈጸሙ ነገሮች የተፈጸሙበትን ዓመት ለማወቅ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደሚያይ ሰው ነው ማየት የምንችለው እንጂ በእርግጥ ማወቅ አንችልም። በዚያ ዘመን የተፈጸሙ ታሪኮች በሙሉ ቀኖቻቸው በውል አይታወቁም። በአንቲዮክ ከተማ የነበረው ኢግናሺየስ አምስት ደብዳቤዎች ጽፏል። ከደብዳቤዎቹ አንዱ ስለ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ትኩረት ይሰጣል።
ኢግናሺየስ እንዲህ ብሎ ጻፈ፡- “ልክ ኢየሱስ ክርስቶስ አብን እንደተከተለ እናንተም ጳጳሱን ተከተሉ፤ ሐዋርያትን እንደምትከተሉ ደግሞ ሽማግሌዎችንም ተከተሉ፤ ዲያቆናትን ደግሞ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች አክብሩ። ከቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ ማንም ሰው ያለ ጳጳሱ ፈቃድ አንዳችመ አያድርግ”።
1965 የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ - የኒቆላውያን ትምሕርት
ይህ አስተምሕሮ በመጀመሪያው ዘመን ውስጥ እንደ ሥራ ነበረ የተጀመረው። ልብ ብለን ስናጤነው ችግሩ ያለው በሁለት ቃላት ላይ ይመስላል፡ “ሽማግሌዎች” (ፕሬስቢተርስ) እና “ጳጳሳት” (ጳጳሳት)። መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በርከት ያሉ ሽማግሌዎች መኖራቸውን ቢያሳይም አንዳንዶች (ኢግናሺየስን ጨምሮ) ጳጳስ በክብር እና በስልጣን ከሁሉም የሚበልጥ እና በሽማግሌዎችም ላይ አለቃ ነው የሚል ሃሳብ ይዘው ማስተማር ጀመሩ።
እውነታው ግን “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ሰውየው ማን እንደሆነ የሚናገር ሲሆን “ጳጳስ” የሚለው ቃል ግን የዚህኑ ሰው አገልግሎት የሚገልጽ ቃል መሆኑ ነው። ሽማግሌ ማለት ሰውየው ነው። ጳጳስ ማለት ደግሞ የሰውየው አገልገሎት ወይም ሥራው ነው። “ሽማግሌ” ሁሌም የሚገልጸው አንድ ሰው በጌታ ሆኖ ስንት ዓመት እንዳስቆጠረ ነው። ሽማግሌ የሆነው ስለተመረጠ ወይም ስለተሾመ አይደለም፤ በጌታ ቤት በኖረበት ዕድሜ ከሌሎች ስለሚበልጥ ነው። ይህ ሰው የበሰለ፣ የገባው እንጂ አዲስ ክርስቲያን ወይም ጀማሪ አይደለም፤ በክርስትና ሕይወት ልምድ እና መልካም ምስክርነትም ስላለው በባህሪ አስተማማኝ ሰው ነው።
በዚያ ዘመን አንድ ሰውን ከምዕመናን ወይም ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ ቀስ በቀስ ወደ ቤተክርስቲያን ገባ።
ይህ ነው “የኒቆላውያን ሥራ”። በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሰዎች አመራር ነጻ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ መተካት ጀመረ። ስለዚህ ኒቆላውያን ማለት የሰዎችን አመራር በሕዝቡ ላይ የሚጭኑ ማናቸውም ሰዎች ናቸው። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው።
ከሕዝቡ በላይ ከፍ ሊል የሚገባው ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 12፡32 እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።
ስለ ሐጥያታችን መስቀል ላይ ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስ ላይ ነው ትኩረት ማድረግ ያለብን።
አስራታችሁን ለእኔ ስጡ የሚል ሰውን እንደ መሪ ከፍ ማድረግ የለብንም።
የሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታላቅ ክርስቲያን የነበረው አይሬንየስ በ120 እና 140 ዓ.ም መካከል ነው የተወለደው። የዚያ ዘመን ታሪክ ጥርት ያለ ማስረጃ ስለሌለን እርግጥ የሆኑ ዓመታትን ማስቀመጥ አንችልም። ዕድሜው 30 ዓመት ያህል በነበረ ጊዜ ሲጽፍ የጻፈበት ጊዜ በ170 ዓ.ም አካባቢ ነው፤ ይህም አብዛኞቹ ሐዋርያት ከሞቱ ከ100 ዓመታት በኋላ ማለት ነው። ታሪክ በአፍ እየተደገመ ነበር የሚተላለፈው፤ ብዙ ጊዜ ተደጋግመው የተነገሩ ታሪኮች ደግሞ ከጊዜው ጋር እየተለወጡ ሄደው “እውነታዎች” ሆነው ይቀራሉ።
የታሪክ ምሑራን የትያጥሮንን ታሪክም በተመለከተ ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸዋል።
ዮሐንስ ከፍጥሞ ደሴት ከተለቀቀበት ከ96 ዓ.ም በፊት ትያጥሮን የምትባለዋ ቤተክርስቲያን መኖሯን ለማረጋገጥ የሚበቃ አንዳችም የታሪክ ማስረጃ የለም።
ስለዚህ ዮሐንስ በዘመኑ ለነበረች ትያጥሮን ለምትባል አንዲት ቤተክርስቲያን አልነበረም የጻፈው። ስለዚህ ለትያጥሮን ቤተክርስቲያን ተብሎ የተጻፈው መልእክት ትንቢታዊ ነው። ዮሐንስ የራዕይ መጽሐፍ ከተጻፈ በኋላ ስለምትመጣ ቤተክርስቲያን ባህሪ ዘርዝሮ በመግለጽ ነበር የጻፈው። ንጉስ ዶሚቲያን በ96 ዓ.ም ሞተ። አንድ የሮማ ገዥ በሞተ ጊዜ ሁሉ የፖለቲካ እሥረኞች ይፈቱ ነበር።
እግዚአብሔር የትያጥሮንን ቤተክርስቲያን ሲናራት እንዲህ አለ፡-
ራዕይ 2፡22 እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤
ከትያጥሮን ቤተክርስቲያን ጋር የተያያዘ የሆነ ነገር ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባቱ አይቀርም።
ትያጥሮን ውስጥ የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ግን በ1922 ጠፋች፤ በዚያን ጊዜ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኞች በሙሉ ተባረው ወደ ግሪክ ሄዱ።
ከ1914 እስከ 1922 ቱርክ ውስጥ የተፈጸመው የክሪክ ኦርቶዶክስ አማኞች ጭፍጨፋ ከቱርክ ሸሽተው እንዲወጡ አደረጋቸው።
ይህ ሽሽት ከ923 ጀምሮ የጸና ሆነ።
ቱርክ ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ግሪክ ኦርቶዶክሶች ስደተኞች ተባሉና ወደ ግሪክ እንዲመለሱ ተደረጉ።
በ1923 በሎዛን ከተማ ስዊዘርላንድ ውስጥ ግሪኮች እና ቱርኮች በሃገራቸው ያሉ ሕዝቦችን ወደየሃገራቸው እንዲመልሷቸው የሚያስገድድ ስምምነት ተፈረመ።
400,000 ሙስሊሞችም ስደተኞች ናችሁ ተብለው ከግሪክ ወደ ቱርክ እንዲመለሱ ተደረጉ።
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ወደ ታላቁ መከራ የምትገባ ቤተክርስቲያን ትያጥሮን ውስጥ የለችም።
ራዕይ 3፡10 የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
የፊልደልፊያ ቤተክርስቲያን ደግሞ ምድርን ሁሉ ሊፈትን ከሚመጣው ፈተና ጥበቃ እንደሚደረግላት ቃል ተገብቶላታል።
ይህ የተስፋ ቃል ፊልደልፊያ ከተማ ውስጥ ለነበረችው ቤተክርስቲያን አልተፈጸመላትም፤ ምክንያቱም ከተማይቱ ልክ እንደ ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በምድር መንቀጥቀጥ እና በሙስሊሞች ወረራ ተጎድታለች። ነገር ግን ዓለምን ሁሉ የሚመለከት ፊልደልፊያ ላይ የተፈጸመ ነገር የለም።
ፊልደልፊያ ከመከራው ትተርፋለች፤ ሰምርኔስ ግን አታመልጥም። ይህ በአንድ ጊዜ ሊፈጸም አይችልም። ስለዚህ ይህ የሚያሳየን በታሪክ ውስጥ ሁለት የተለያዩ ዘመናትን ነው።
በሁለቱም ከተሞች ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች አሕዛብ በሆኑ ሮማውያን ገዥዎች እጅ ተሰድደዋል፤ በሁለቱም ከተማ ያሉ ክርስቲያኖች በምድር መንቀጥቀጥ ተጎድተዋል፤ በሙስሊሞች ተወርረዋል፤ ሙስሊሞቹም እስከ ዛሬ ድረስ ገዢዎቻቸው ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚናገረው በታሪክ ውስጥ ሰለሚታወቅ ሌላ ዘመን ነው።
ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን የሆነው የፊልደልፊያ ቤተክርስቲያን ዘመን አሁን በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያኖች ወደ አንድነት እያሰባሰበ ካለው ኢክዩሜኒካል እንቅስቃሴ ተጠብቋል። የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ግን ለ130 ዓመታት ያህል ሄደ መጣ ሲል የቆየው በክርስቲያኖች ላይ የነበረ ስደት ሊያበቃ 10 ዓመታት ሲቀሩ በሚነሳው የአስር ዓመት መራራ ስደት ውስጥ ትፈተናለች።
ሰምርኔስ ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው፤ በዚህም ዘመን ቤተክርስቲያን በአሕዛብ ሮማውያን ገዥዎች ስደት ደርሶባታል፤ በስተመጨረሻም ከ302 እንከ 312 ዓ.ም ድረስ ለአስር ዓመታት እጅግ መራራ የሆነ ስደት በንጉስ ዲዮክሌቲያን እጅ ደርሶባታል።
ራዕይ 2፡10 … እነሆ፥ እንድትፈተኑ … አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።
የአስር ቀን ስደት የአስር ዓመታትን ስደት ሊወክል ይችላልን?
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ሊወክል ይችላል።
ያዕቆብ የላባን ልጅ ራሔልን ሊያገባ በፈለገ ጊዜ ላባ ምን እንዳለው አንብቡ።
ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።
ሰባት ቀናት ያሉት ሳምንት ሰባት ዓመታትን ይወክላል። ስለዚህ አንድ ቀን አንድ ዓመትን መወከል ይችላል።
ይህ አሰቃቂ ስደት በስተመጨረሻ የቆመው በ312 ዓ.ም በተነሳው አዲስ ንጉስ ኮንስታንቲን ነው።
ሰይጣን ቤተክርስቲያንን ከውጭ ማጥቃቱን አቆመ ምክንያቱም በ33 ዓ.ም እና በ312 ዓ.ም መካከል 3 ሚሊዮን ክርስቲያኖች ቢገደሉም እንኳ ቤተክርስቲያን ማደጓን ቀጥላለች። ስለዚህ ከውጭ የሚሰነዘር ጥቃት ቤተክርስቲያን እንድታድግ እያገዛት ነበረ።
ከዚያም ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጴርጋሞን (ሙሉ በሙሉ የተጋባች ማለት ነው) ሲመጣ ሮማዊው ንጉስ ኮንስታንቲን የሮማውን ጳጳስ ቅጥረኛ አደረገው፤ ቅጥረኛ ያደረገውም እጅግ በጣም ብዙ ገንዘብ እና ውብ የሆነውን የላተራን ቤተመንግስት ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት እንዲሆን ስጦታ በማበርከት ነው።
የሰው አመራር በቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍ ሲደረግ የሚያስከትለው የመጨረሻ ክፉ አደጋ ይህ ነው።
ሲልቬስተር የተባለው ይህ የሮማ ጳጳስ በፖለቲካዊ አመራሩ ያመቻመቸውን የጨካኙን ገዥ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ብኩርናውን ሸጠ። የላተራን ቤተመንግስት እስከ ዛሬ ድረስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ጽሐፈት ቤት ነው፤ ፖፑም በዚያ ተቀምጦ ከፍ ባለው ስልጣኑ በዓለም ዙርያ ሁሉ የተስፋፋችዋን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያስተዳድራታል።
ራዕይ 13፡1 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
አውሬው በዓለም ዙርያ ያለችዋን ቤተክርስቲያን ሁሉ ለመቆጣጠር የቫቲካንን ከተማ እስኪመሰርት ድረስ አውሮፓ ውስጥ በስልጣን የተነሳው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሕብረት ነው። ፖፑ የአውሬው መታወቂያ ነው፤ በአሁኑ ዘመን ባለችው አውሮፓ ውስጥ ፖፑ ብቸኛ አምባ ገነን መሪ ሆኖ ይመራል።
ባሕር ማለት እረፍት የሌለው ብዙ ሕዝብ ነው።
ሰባቱ ራሶች የሮም ከተማ መጀመሪያ የተመሰረተችባቸው ሰባቱ ኮረብታዎች ናቸው።
ሰባት መንደሮች በራሳቸው ዙርያ ግምብ አጥር ሰርተው ከተማ ሆኑ። የሰባት ኮረብታዎች ከተማ።
የስድብ ስም የተባለው “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” የሚለው አነጋገር ነው።
እነዚህ የእግዚአብሔርን ስም ተክተው የተቀመጡ ሶስት ማዕረጎች ናቸው። ከዚህም የተነሳ ስሳሴ ብለው የሚያመልኩት አምላክ ስም የለውም።
የስድብ ስም ሌላኛው ገጽታው ደግሞ ቤተክርስቲያንን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብሎ መጥራት ነው። ከዚያ ወዲያ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው በመጥራት ፈንታ ሮማን ካቶሊክ ብለው መጥራት ጀመሩ።
ዲኖሚኔሽን የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
አስሩ ቀንዶች የመጨረሻው ፖፕ የ3½ ዓመታት መከራ ሊያስጀምር እና ዓለምን በሙሉ ሊገዛ ሲነሳ ወታደራዊ ኃይላቸውን የሚሰጡት አስር አምባገነን መሪዎች ናቸው።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
እንደ ነገስታት “ሥልጣን” ይቀበላሉ። እነዚህ ዘውድ አልጫኑም ግን የንጉስ ሥልጣን አላቸው። ስለዚህ ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
የመጨረሻው ፖፕ ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ገንዘብ እና ሐይማኖታዊ ኃይል የራሱ ያደርጋል። አይሁዶች እስቶክ ኤክስቼንጅ ገበያ ውስጥ ያላቸውን ገንዘብ ለመጠቀም ብሎ ከእነርሱ ጋር ቃልኪዳን ያደርጋል። ነገር ግን የቤተክርስቲያን ሰው አንደመሆኑ ዓላማውን የሚያስፈጽምበት ወታደራዊ ኃይል የለውም። ይህንንም ወታደራዊ ኃይል ከአስሩ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ያገኛል።
ዳንኤል 8፡23 በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቈቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል።
ይህ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ነው። ስሙም ፖፕ ጴጥሮስ 2ኛው ተብሎ ይጠራ ይሆናል።
ዳንኤል 8፡24 ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም፤ በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል፤ ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል።
የዚህ ፖፕ ወታደራዊ ኃይል የሚመጣው ከቤተክርስቲያን ሳይሆን ከአስሩ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ነው።
ሮም የተመሰረተችው ሮሙለስ በተባለ ሰው ነው። የሮማ መንግስት የመጀመሪያ ገዥ አውግስጦስ ነበረ።
የመጨረሻው የሮም ገዥ ስሙ ሮሙለስ አውግስጦስ ነበር።
ስለዚህ የመጀመሪያዎቹ መሪዎች ከመጨረሻው መሪ ጋር ስማቸው አንድ ዓይነት ነበር።
በዚህ መንገድ ሮም ኢየሱስን በመኮረጅ “ፊተኛ እና ኋለኛ” ለመሆን ሞክራለች።
ካቶሊኮች ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነበረ በማለት ይዋሻሉ። ስለዚህ የመጨረሻውም ፖፕ ጴጥሮስ የሚባለው ነው የሚሆነው። ፖፕ ጴጥሮስ ዳግማዊ።
ራዕይ 13፡2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።
ነብሩ በ325 ዓ.ም ከተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ጀምሮ የግሪክ ፍልስፍና ቤተክርስቲያን የወረረበትን ፍጥነት ይወክላል። አረማዊው የግሪክ ፍልስፍና ቤተክርስቲያን ባዕድ የሆኑ እምነቶችን በቀላሉ እንድትቀበል አደረገ።
ድቡ ደግሞ ሰው ሰራሽ ደኖሚኔሽናዊ ድርጅቶች ያላቸውን የመርገጥና የማድቀቅ ኃይል ይወክላል። ፋርሶች እጅግ የተዋጣለት ድርጅታዊ አሰራር ጥበብ ስለነበራቸው የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ መንግስት መስርተው መምራት ችለዋል። በዚህ መዋቅራቸው ውስጥ አንድ ግለሰብ ትልቅ ማሽን ውስጥ እንደተገጠመ ብሎን ነው። ሰዎችም ለመሪዎቻቸው ያለምንም ጥያቄ እንዲታዘዙ አእምሮዋቸው ተለውጧል።
አንድ ጊዜ ሐይማኖታዊ ድርጅት ከተመሰረተ በኋላ ሰይጣን መሪዎች ሕዝባቸውን እንዲያስቱ እና የሰውን የተሳሳተ ሃሳብ እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነት አድርገው እንዲያስተምሩ ያደርጋቸዋል። ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰዎች ሐይማኖታዊ ውሸትን ያመኑ ጊዜ ከእነርሱ በኋላ ሌሎች ሰዎች አሳማኝ በሆነው የውሸት ትምሕርታቸው በቀላሉ ይማረኩበታል።
ራዕይ 13፡2 ያየሁትም አውሬ … ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።
ዘንዶው ዲያብሎስ ነው። ካኤልያን ኮረብታ ላይ ያለው ላተራን ቤተመንግስት በሮማው ንጉስ ኮንስታንቲን ነው ለፖፑ የተሰጠው። በዚያም የቅዱስ ጴጥሮስ ዙፋን አለ፤ ይህም ዙፋን ለፖፑ በቤተክርስቲያን ላይ ስልጣን እና ኃይል እንዲኖረው አስችሎታል።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡8 በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
ኢየሱስ የይሁዳ ነገድ አንበሳ ነው። ሰይጣን እራሱን የእውነት አንበሳ በማስመሰል ኢየሱስን ሊኮርጅ ይሞክራል።
ነገር ግን ሰይጣን ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ ሆኖ አይኖርም። ሰይጣን ሁልጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያፈነግጣል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ይለውጣል ወይም ቸል ይላል።
ስለዚህ ሰይጣን እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሚመስሉ የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ሰዎች እየተጠቀመ በእነርሱ አማካኝነት ሐሰተኛ የሆኑ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ውጭ የሆኑ ሃሰቦችን በማስተማር በሐይማኖት ሰዎችን ያስታል።
እነዚህም ፓስተሮች እናንተ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመጠቀም ሃሳባቸውን የምታፈርሱ ከሆነ ወዲያው ይጠሏችኋል።
ራዕይ 13፡3 ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥
ሮም መጀመሪያ የተመሰረተችው በሰባት ኮረብታዎች ላይ ነበር።
ካፒቶላይን ኮረብታ ላይ ያለው የጁፒተር ቤተመቅደስ የሮማ መንግስት ዋነኛ ማዕከል እና ሕግ ተደንግጎ የሚታወጅበት ቦታ ነበረ። በ476 ዓ.ም የሄሩሊ ጀነራል ከወጣቱ ሮሙለስ አውግስጦስ ስልጣንን ሲረከብ በሮማ መንግስት ላይ የደረሰው ለሞት የሆነ ቁስል ያ ነው። ከዚያ ወዲያ የሮማ መንግስት ተመልሶ ወደ ስልጣን አይመጣም።
ካፒቶላይን ኮረብታ ፖለቲካዊ ስልጣኑን በተቀማ ጊዜ ለሞት የሚያበቃ ቁስል ቆሰለ።
የሮማ መንግስት ሲወድቅ በተፈጠረው ሁካታ ውስጥ ባርቤሪያን ነገዶች አውሮፓን ተቆጣጠሩ። በነዚያም ረጅም የመከራ ዓመታት የሮማ ጳጳሳት ኢጣልያ ውስጥ አብዛኛውን ፖለቲካዊ እና የገንዘብ ስለጣን ተቆጣጠሩ። በ754 ዓ.ም ፖፕ እስቲቨን ዳግማዊ ፔፒንን የባርቤሪያውያን ፍራንኮች ንጉስ አድርጎ ዘውድ ጫነለት፤ ፍራንኮችም ከባርቤርያውያን ነገዶች መካከል ኃይለኞች ነበሩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፖፑ ባርቤሪያዊ መሪን ንጉስ አድርጎ መሾም በመቻሉ በስልጣን ከፍ አለ።
ከዚያ በኋላ ፖፑ ለፔፒን ሲሞት የመንግስተ ሰማያትን በር ሊከፍትለት የሚችለውና ቁልፍ ያለው ጴጥሮስ ብቻ መሆኑን ነገረው። ጴጥሮስ ደግሞ ለፔፒን የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍትለት ፔፒን የጴጥሮስ ተተኪ ለሆነው ለፖፑ መሬት እና ገንዘብ ሲሰጠው እንዲሁም ጥበቃ ሲያደርግለት ብቻ ነው። ባርቤርያውያን ጴጥሮስን ማስደሰት ከፈለጉ ለፖፑ መታዘዝ አለባቸው።
በዚህም መንገድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሕዝቡ ወደ ኢየሱስ ማየትን ትተው ወደ ጴጥሮስ እና ወደ ማርያን እንዲመለከቱ እና እንደ አማላጅ ተስፋ እንዲያደርጉባቸው አስተማረች። የሐሰተኛ ሐይማኖት አውሬ በዚህ መንገድ እያደገ ሄደ።
የፖፑ ዋና ጽሕፈት ቤት የላተራን ቤተመንግስት እና (ባሲልካ የሚባለው) የፖፑ ልዩ የላተራን ቤተክረስቲያን ያለበት የካኤልያን ኮረብታ ላይ ነው።
ስለዚህ ካኤልያን ኮረብታ ላይ የተቀመጠው ፖፕ የሮማ መንግስት በአውሮፓ ላይ ይዞት የነበረውን ነገር ግን ኋላ ያጣውን ስልጣን በሙሉ አስመለሰ።
የባርቤሪያኖች ሰይፍ በባደረሰው ለሞት የሆነ ቁስል የደመሰሰው የካፒቶላይን ኮረብታ ስልጣን ኋላ ተፈወሰ።
ጴርጋሞስ፤ የሶስተኛዋ ቤተክርስቲያን ስም ትርጉሙ “ሙሉ በሙሉ የተጋባች” ማለት ነው።
ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ312 ዓ.ም ኮንስታንቲን ክርስቲያኖችን ማሳደድ ሲያስቆም ተጀምሮ በ606 ዓ.ም ፖፑ የቤተክርስቲያኖች ሁሉ ዓለም አቀፍ ጳጳስ በሆነ ጊዜ ነው የተጠናቀቀው፤ ይህም ፖፕ እርሱን የሚቃወሙ ክርስቲያኖችን በሙሉ ያሳድድ ነበር።
በዓለም ላይ ባሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ይህንን ታላቅ ስልጣን ለመያዝ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ፣ የአሕዛብ ልማዶች፣ እና ከዓለማዊነት ጋር መጋባት ግድ ሆኖባታል።
የባቢሎን ሚስጥራት ሁልጊዜ በአስገራሚ የቅዳሴ ስርዓቶች፣ እንቅስቃሴዎች እና ደመቅ ባሉ ልብሰ ተክህኖዎች የታጀቡ ነበሩ።
የሚያብረቀርቀው የቫቲካን ሃብት፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ስዕሎቻቸው እና ቅርጻ ቅርጾቻቸው፣ እንዲሁም ማራኪ የሆነው ስርዓተ ቅዳሴያቸው የዓለምን ሁሉ ቀልብ ይማርካሉ። እነርሱ የሚያሳዩት ሐይማኖታዊ ትዕይንት ወደር የለውም። ነገር ግን ትርኢት ነው እንጂ ሕይወት የለውም። በሲስቲን ቻፕል ኮርኒስ ላይ የተሳሉት ራቁታቸውን የሚታዩ ሰዎች ስዕሎች ብዛት ብቻውን አእምሮን ያዞራል።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሚያስተምረን ስለ ቅድስና እና በጨዋነት ገላን ስለመሸፈን ነው።
የግሪክ ፍልስፍና እርቃንን ገልጦ በማሳየት በግብረ ሰዶማዊነት የሚያምን ሲሆን የቅድስና መገለጫ እርቃን ገላ ነው ይላል።
የሲስቲን ቻፕል ውስጥ ግን የግሪክ ፍልስፍና ያመጣው እርቃን ገላ አሸነፈ። በዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ እየተነሳ ያለው የግብረ ሰዶማውያን መብት ጥያቄ የግሪክ ፍልስፍና ቤተክርስቲያንን እየወረራት ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።
ኮንስታንቲን ክርስቲያኖች እና አሕዛቦች መስማማት አለባቸው አለ።
የሮማ ጳጳስ ለአሕዛብ እምነቶች እና ልማዶች ክርስቲያናዊ ስሞችን በመስጠት ቀደሳቸው።
ታላቁ የታሪክ ምሑር ጊቦን እንደ ጻፈው፤ ቤተክርስቲያን ክርስትና የተነሳች ጣኦት አምልኮ ሆነች።
በ274 ዓ.ም አሕዛብ የሆነው የሮማ ንጉስ ኦሬሊያን ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ ልደት ቀን ነው ብሎ አወጀ። በ352 ዓ.ም ልክ እርሱ ከመሞቱ በፊት ዩልየስ 1ኛ ዲሴምበር 25 የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ቀን ነው ብሎ አወጀ።
መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናከብር አልጠየቀንም። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን ይህንን በዓል ክሪስ-ማስ ብላ ጠራችው። ይህም “ማስ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ አይገኝም።
ፕሮቴስታንቶች “ማስ” የሚባለውን ስርዓት አንቀበልም አሉ። ሆኖም ግን ሁሌ የሚያከብሩት አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ማስ አለ። እርሱም ክሪስማስ ነው።
በኮንስታንቲን ትዕዛዝ በ325 የተደረገው የኒቅያ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን የስላሴ አስተምሕሮ እንዲያጸድቅ ተገደደ።
ንጉስ ኮንስታንቲን (የጥነታዊው የሞዓብ ንጉስ የባላቅ ምሳሌ የሆነው) መንፈሳዊ መሪ ለሆነው ለፖፑ (የሐሰተኛው ነብይ በለዓም ምሳሌ ለሆነው) ጉቦ ከፍሎ ታዛዥ አደረገው። ከዚያ በኋላ ፖፑ እና ኮንስታንቲን 318 ያህል የሚሆኑ ጳጳሳትን በኒቅያ ጉባኤ የስላሴ አስተምሕሮን እንዲቀበሉ አስገደዱዋቸው፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ስላሴ” የሚል ቃል የለም። ጳጳሳቱ በሙሉ ወደየከተሞቻቸው ተመልሰው በየከተሞቻቸው ያሉ ቤተክርስቲያኖች በስላሴ እንዲያምኑ አስገደዱ። በዚህም መንገድ ይህ መንፈሳዊ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው እየተጋባ ተዛመተ፤ አውሮፓን ሁሉ አዳርሶ እስከ ምድር ዳርቻ ተሰራጨ።
ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች እና ቤተክርስቲያኖች አሉ፤ ሁላቸውም እምነታቸው የተለያየ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ስላሴ የተባለው ትምሕርት በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን ከገባ በኋላ እርሱን ተከትለው ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል። ቤተክርስቲያኖች “ስላሴ ተብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም ግን እውነት ነው” ሲሉ አያፍሩም። “ስለዚህ “ክሪስማስን” ጨምሮ ማንኛውም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃልም እውነት ነው።” ይህ በጣም ከባድ ችግር ያለበት አስተሳሰብ ነው።
ዛሬ ከ100 በላይ ልዩ ልዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ፤ ይህ ሁሉ የሆነው “ስላሴ” ከሚለው ቃል የተነሳ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በትክክል መጽሐፍ ቅዱስን ስለመከተል ምንም ግድ የሌላቸው ስለሆኑ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ሲተረጉሙ ማንኛውንም ቃል ቢጠቀሙ የሰዎችን አስተሳሰብ እስከደገፈላቸው ድረስ ምንም ችግር የለባቸውም።
ስለዚህ በኮንስታንቲን ዘመን ፖፕ ሲልቬስተር ሐሰተኛ ነብይ ሆነ። ምክንያቱም የሐሰተኛ ሐይማኖት ነብይ ሆኗል።
ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆኑ ብዙ ቃላት በር ከፈተ።
እነዚህም ቃላት ዲኖሚኔሽን፣ የሐዋርያት የሐይማኖት መግለጫ፣ ፑርጋቶሪ፣ ኩዳዴ፣ መነኮሳት፣ ሲኖዶስ፣ ካተኪዝም፣ ማርያም አማላጅ ናት፣ መቁጠሪያ፣ “ጸጋ የሞላብሽ እመቤታችን ማርያም ሆይ” ብሎ መጸለይ። የሞቱ ቅዱሳን እንዲማልዱልን መጸለይ፤ ይህም መናፍስት ጠሪነት ነው። ኮንፈርሜሽን፣ ስልጣነ ክህነት፣ ስርዓተ ቅዳሴ፣ ሐጥያታችሁን ለማስተስረይ በገንዘብ የስርየት ወረቀት መግዛት፣ ፖፕ፣ ፖንቲፍ፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናል፣ ክሪስማስ፣ የክሪስማስ ዛፍ፣ ዲሴምበር 25። ፖፑ የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ነው። ለፖፑ ታዛዥ ከሆናችሁ ብቻ ነው ስትሞቱ ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን ደጅ የሚከፍትላችሁ።
እነዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ቃላት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለመገኘታቸው ሐሰተኛ ትምሕርቶች ናቸው።
ሐሰተኛ ትምሕርት ልክ ጥቅም እንደሌለው ጣፋጭ ምግብ የሰዎችን ቀልብ ይስባል።
የሮማ ካቶሊክ ዲኖሚኔሽን በሐሰተኛ ዜናዎች የተሞላ አሸዋ ላይ የተገነባ ቤት ነው፤ እነዚህም ሐሰተኛ ወሬዎች ምንጫቸው የግሪክ ፍልስፍና እና እንደ ፕሮፓጋንዳ የሚጠቀሙዋቸው የባቢሎን ሚስጥራት ናቸው።
ቤተክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አለመከተልን ከመላመዳቸው የተነሳ እግዚአብሔር የለም የሚሉ የኤቮሉሽን እና ቢግ ባንግ ቲዎሪዎች እንኳ ሳይቀሩ ቤተክርስቲያን በሚሄዱ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል። እንደውም ከመቀበል አልፈው የሚሟገቱላቸውም አሉ። የግብረ ሰዶማውያን መብት እና ጽንስ ማቋረጥም ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው ገብተዋል። እንደ ትንሽ ጅረት የመጣው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነው የስላሴ ትምሕርት ያለማመን ጎርፍ ሆነ። መንፈሳዊ አረንቋ።
ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አነጋገር አስቡ።
“አንድ አምላክ በሶስት አካላት”።
ይህ አነጋገር መሰረቱ የግሪክ ፍልስፍና ነው። የቤተክርስቲያንንም ትኩረት በአንድ ጊዜ ተቆጣጠረ።
ምንም ማለት እንደሆነ ማንም በውል አያውቅም ግን የቤተክርስቲያን ሰባኪዎች ታላቅ የእውነት ሚስጥር የተገለጠላቸው ይመስል በኩራት ያውጁታል።
ከግሪክ ፈላስፎች መካከል እጅግ ጠቢብ የሆኑት ተጠርተው እንዲሰበሰቡና እያንዳንዳቸው አምላክ የሆኑ ሶስት የተለያዩ አካላት የሚለውን ትምሕርት በዝርዝር እንዲያዘጋጁ ተጠየቁ። ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ ብቻ ነው።
ይህ ለአእምሮ የማይጨበጥ ፍልስፍና ተብራርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ብዙ ዓመታትን እና የብዙ ሰዎችን ነፍስ ፈጅቷል፤ የሚቃወሙት ተገድለዋል።
ታላላቅ ሰባኪዎች እንኳ እስከ ዛሬ ድረስ ሶስት አካላት፣ በአንድ መለኮት የሚለውን ሃሳብ በግልጽ አልተረዱትም።
ስለዚህ የስላሴ ጽንሰ ሃሳብ እስከ አሁን ድረስ ተብራርቶ አልተጠናቀቀም።
በስላሴ የሚያምኑ ሰዎች እስካሁንም ድረስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምሕርታቸውን ለመጨበጥ ሲሉ የማይጨበጥ ጥላ እያሳደዱ ይኖራሉ። ይህንም ለማድረግ ሲጥሩ በፊት ከነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላት ላይ በየጊዜው አዳዲስ እየጨመሩባቸው ነው።
ሶስት አካላትነ ከአንድ አምላክ ጋር ለማያያዝ ተቸግረዋል፤ ስለዚህ አሁን የሚሞክሩት ሶስት አካላትን ከአንድ መለኮት ጋር ለማገናኘት ነው።
ይህን ሁሉ የሚያደርጉት በእግዚአብሔር እና በመለኮት መካከል ልዩነት ያለ መስሏቸው ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የጨዋታ መጽሐፍ ይመስል በቃላት ይጫወታሉ።
ስለ እግዚአብሔርም ይሁን ስለ መለኮት የምታስቡት ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር እና መለኮት ሙሉ በሙሉ ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ በተባለው ሰው ውስጥ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
የካቶሊክ ምሑራን ሃሳባቸውን ለመግለጥ ሙሉ በሙሉ ከግሪክ ፍልስፍና በተወሰዱ ቃላት ነው የሚጠቀሙት፤ ለምሳሌ “ሂፖስታቲክ ዩንየን” ወይም የባህሪ አንድነት። ይህ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ የሌለ ቢሆንም እንኳ ከ533 ዓ.ም ጀምሮ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቷል።
መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸው ቃላት፣ ለምሳሌ፡- የመለኮት የመጀመሪያው አካል፣ የመለኮት ሁለተኛው አካል፣ የመለኮት ሶስተኛው አካል የስላሴን ትምሕርት ግልጽ ለማድረግ የተፈጠሩ ቃላት ናቸው።
የግሪክ ፍልስፍና እነዚህን ሶስት አካላት እኩል አድርጓቸዋል።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሌሎች ቃለትም ተጨመሩ፤ እነዚህም እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ናቸው።
“እግዚአብሔር ወልድ” ተብሎ የተጠራው ብቸኛው ሰው ናምሩድ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ላይ ያመጸ የመጀመሪያ አመጸኛ ሰው ነው። ናምሩድ ስሙ “ኤል ባር” ወይም “እግዚአብሔር ወልድ” ነበረ።
ነገር ግን “እግዚአብሔር አብ” የሚል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እርሱም አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” የሚል የለም። የስላሴ አማኞች ይህ ለምን እንደሆነ መመለስ አይችሉም።
የግሪክ ፍልስፍና አብ እና ወልድ አንድ ባህሪ ናቸው ይላል (ይህ ምን ማለት እንደሆነ እንጃ)።
“ባህሪ” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝና ትርጉሙም የፈለጋችሁትን የሚሆንላችሁ ቃል ነው። ሆኖም “ባህሪ” የሚለውን ቃል በጣም ገልጣችሁ ልታብራሩት ካልሞከራችሁ በቀር ችግር አይገጥማችሁም።
ዘላለማዊ ልጅነት። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዴ እንኳ ያልተጠቀሰ አነጋገር ነው።
“ኢየሱስ የመለኮት አካል ነው”።
ይህ አነጋገር የመለኮት ሙላት ሁሉ በኢየሱስ ውስጥ በአካል ተገልጦ ይኖራል ከሚለው ከቆላስይስ 2፡9 ጋር ይጋጫል።
ዮሐንስ 14፡10 … ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
አብ ኢየሱስ በተባለው ሰው ውስጥ በሙላት የሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።
ስላሴ በሐሰተኛ እንደ አሸዋ አስተማማኝ ባልሆኑ የሰው ምናብ እና ሃሳቦች ላይ የተመሰረተ አሳሳች ትምሕርት ነው።
ስላሴያዊው አምላክ ስም የለውም ምክንያቱም ለሶስት አካላት የሚሆን አንድ ስም ማግኘት አይቻልም።
ከዚህም የተነሳ ሁልጊዜ “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ይላሉ፤ ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ በጭራሽ አያውቁም።
ስለዚህ ሶስት አካላት ያሉት የክርስቲያኖች አምላክ ስም የለውም።
መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የለውም። ለዚህም የስላሴ አማኞች መልስ የላቸውም።
ስለዚህ ጴርጋሞን ስሟ ወደ ግሪክኛው ጴርጋሞስ ተለወጠ፤ ይህም የሆነው ስነ መለኮታዊ መራቀቅን የሚወደው የግሪክ ፍልስፍና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለውን የስላሴ አምላክ ለማብራራት ወደ ቤተክርስቲያን በመግባቱ ነው።
ይህ ዓይነቱ ወጥመድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሰው ጥበብ ጉድፍ ስር እንዲቀበር አደረገ።
በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላትን በማምጣት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን ለመቆጣጠር እና ስላሴያዊ አምላክ ለሚለው ሃሳብ ሰው ሁሉ እንዲሰግድ ለማድረግ ዲኖሚኔሽናዊ ስርዓትን መሰረተች (ዲኖሚኔሽን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል ነው)።
ስለዚህ አራተኛዋ የትያጥሮን ቤተክርስቲያን (ትያጥሮን ገዥ ሴት ማለት ነው) ፖፑ በ606 ዓ.ም እራሱን ዓለም አቀፋዊ ጳጳስ ብሎ ከሾመ በኋላ የጨለማው ዘመን የነበረበት 900 ዓመታት ውስጥ ነው የኖረችው። ፖፑ የቤተክርስቲያኖች ሁሉ ራስ ነኝ አለ።
የስላሴ አስተምሕሮ ከእግዚአብሔር ስሙን ሰረቀበት፣ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ውስጠ ተሰራጨ። የመጨረሻው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ዕውር የተባለበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው።
ስለዚህ ከኒቅያ ጉባኤ የተጀመረው የስላሴ አስተምሕሮ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች እንዲሁም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆኑ እምነቶች እንደ ቆሻሻ ማቃጠያ ሆኖ ወደ ተዘጋጀው ወደ ታላቁ መከራ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።
ሮማን ካቶሊኮች መጽሐፍ ቅዱስን እንደፈለጉ ተጫውተውበት ለወጡት። የብርሃን ምንጭን ብትጫወቱበት ብርሃኑ ይጠፋል።
ስለዚህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን በሙሉ ይዛ ወደ ጨለማው ዘመን ገባች።
ራዕይ ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ ሰባት ቤተክርስቲያኖች ተጠቅሰዋል።
1 2 3 4 5 6 7
አራት በ1 እና በ7 መካከል ነው የሚገኘው።
ስለዙህ አራተኛዋ ቤተክርስቲያን የአውሮፓ ታሪክ ውስጥ የመካከለኛውን ዘመን ትወክላለች።
ይህ መካከለኛ ዘመን ሌላ ስሙ የጨለማው ዘመን ሲሆን በዚያ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ ማዕቀብ ተጥሎበት፤ ሰዎችም በእጃቸው መጽሐፍ ቅዱስ ከተገኘ የሚገደሉበት ዘመን ነበር።
ትያጥሮን ማለት ጨቋኝ ሴት ናት።
ሴተ ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ናት።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጨለማው ወይም በመካከለኛው ዘመን አውሮፓን በሙሉ ስትጨቁን ነበር። የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት ከ904 ዓ.ም እስከ 963 ዓ.ም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምትመራው በጋለሞታዎች ነበር።
ራዕይ ምዕራፍ 17 የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ጋለሞታ ይላታል።
ቤተክርስቲያን የምትሄድ ሴት ኤልዛቤል ተብላ አታውቅም፤ ስለዚህ ይህ ስም የሚገልጸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ነው።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኤልዛቤል ምስኪኑን ናቡቴን በመግደሏ ጭካኔዋ ተገልጧል። ይህ ጭካኔ በጨለማው ዘመን ውስጥ አይሁዶች፣ ሙስሊሞች፣ የኮንስታንቲኖፕል ክርስቲያኖ እና ደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ አልቢጀንስ እና ዋልደንስ የተባሉ ክርስቲያኖች የተገደሉበትን አሰቃቂ የግድያ ዘመቻ ይገልጻል። ከዚያ በኋላ ደግሞ እስፔይኖች እና ፖርቹጋሎች በገዙዋቸው ጊዜ በደቡብ እና በመካከለኛው አሜሪካ ውስጥ የተገደሉት ኢንዲያኖች እልቂት በታሪክ ተመዝግቧል። ከዚያ ቀጥሎ ዌስት ኢንዲስ ውስጥ የሸንኮራ ማሳ ላይ እንዲያገለግሉ የተወሰዱት 11 ሚሊዮን አፍሪካውያን ባሪያዎች በደቡብ ቦሊቪያ አደገኛ ሜርኩሪ በመጠቀም ብር እንዲያወጡ በተገደዱ ጊዜ በአሰቃቂ ሞት አልቀዋል።
ራዕይ 2፡20 ዳሩ ግን፦ … ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤
በካቶሊክ “የስርዓተ ቅዳሴ መስዋእት” መሰረት እነርሱ በመሰዊያ ላይ ከሚበሉት ክብ ሕብስት ጋር ክርስቶስ ስለሚሞት ሕብስቱ እና ወይኑ ትክክለኛዎቹ የክርስቶስ ስጋ እና ደም ናቸው ይላሉ። ጉባኤው ወይኑን መጠጣት አይፈቀድለትም። ጉባኤው ሕብስቱን ብቻ ነው የሚበላው።
ካሕኑ ብቻ ነው ወይኑን የሚጠጣው። ይህም ስርዓት ካሕኑን ከምዕመናኑ ለይቶ ከፍ ያደርገዋል። ይህ የኒቆላውያን ሥራ ነው።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉት የክርስቶስ፣ የማረያም፣ የሐዋርያት እና የተለያዩ ቅዱሳን ሃውልቶች የተነሳ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጣኦታት ተሞልታለች።
ፖፑ እና ማርያም ለካቶሊኮች ዘንድ ጣኦት ሆነዋል።
ይህን የካቶሊክ ስርዓት ቅዳሴ ለፍራንኮች ያስተዋወቀው በ754 ፔፒንን የፍራንኮች ንጉስ አድርጎ ሊሾም ወደ ፓሪስ የሄደው ፖፕ እስቲቨን ዳግማዊ ነው። ፔፒንም በተራው ሮምን እያጠቁ የነበሩ የሎምባርድ ነገዶችን በማባረር ለፖፑ ግዛቶች ተጨማሪ መሬቶችን አበርቷል። ፖፑ አስቀድሞ ካርታው ላይ የምታዩትን ቢጫ ቦታ ይገዛ ነበር፤ ፔፒንም ለራሱ መንግስተ ሰማያት ውስጥ ቦታ ለመግዛት ፈልጎ ለፖፑ የሰጠው መሬት ደግሞ በቀይ ቀለም የተመለከተው ነው። ይህ ስግብግብነት፣ አታላይነት፣ እና ጭካኔ ነው።
ከዚያም በኋላ ፖፑ ለፔፒን ፔፒን ሲሞት ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር እንዲከፍትልህ አደርጋለው አለው። ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር እንዲከፍትልን ፖፑን የጴጥሮስ ተተኪ አድርጎ በመቀበል ለፖፑ መታዘዝ የሚለው አስተምሕሮ የሮማ መንግስትን በተቆጣጠሩት የባርቤሪያ ነገዶች መካከል በፍጥነት ተሰራጨ።
በዚህም መንገድ ፖፑ የሮማ መንግስትን አሸንፈው የነበሩ የባርቤሪያ ነገዶችን ገዛቸው።
ፕሮቴስታንቶች በካቶሊክ ማስ አናምንም ይላሉ።
ሆኖም ግን ተታለው ክሪስማስ ወይም የክርስቶስ ማስ ያከብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናከብር አላዘዝንም። ፕሮቴስታንቶች በተጨማሪ በካቶሊክ ተታለው በስላሴ ያምናሉ። ስለዚህ ከሮም ነጻ ወጥተናል ብለው የሚያስቡትን ፕሮቴስታንቶች እስካሁን ሮም ትገዛቸዋለች። ዛሬ ፕሮቴስታንቶች ራሳቸውን ዲኖሚኔሽናል ይላሉ፤ በተጨማሪም እንደ አንግሊካን፣ ሜተዲስት፣ እና ባፕቲስት፣ ወዘተ. በተባሉ የስድብ ስሞች ራሳቸውን ይጠራሉ። ይህም ልክ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንዳደረገችው ነው።
ሳርዲስ፡- በተሃድሶው ምክንያት ያመለጡ።
ራዕይ 3፡1 … ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ ሞተህማል።
እንደ ክርስቲያን በእምነት ዳናችሁ፤ ከዚያ በኋላ ግን ራሳችሁን ሉተራን፣ ካልቪኒስት፣ እና አናባፕቲስት እያላችሁ ትጠራላችሁ። እነዚህ ሁሉ ሙታን ስሞች ናቸው።
በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ኒቆላውያን ሰዎችን የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆኑ ከፍ የሚያደርግ ሥራ ሰሩ። በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ግን የኒቆላውያን ሥራ አስተምሕሮ ሆነው ተደላደሉ። አንድ አካባቢ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሊከፈት ከሆነ ቤተክርስቲያኒቱ ራስ ይሆናት ዘንድ አንድ ቄስ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ውስጥ የተማረ ፓስተር ማስመጣት ግዴታዋ ነው፤ ምክንያቱም ራስ መሆን የሚችለው እንዲህ ዓይነቱ ሰው ብቻ ነው። ይህ ሰው ሰራሽ መመሪያ ወዲያው አስገዳጅ ሆነ። የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆችን የሚቆጣጠሩ ሰዎች በቤተክርስቲያኖችም ውስጥ የሚሰጡትን ትምሕርቶች ይቆጣጠሩ ነበር። እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች ውስጥ ተምረው የወጡ ፓስተሮች አዳዲስ ሃሳቦች ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳይገቡ ተቆጣጣሪ ሆኑ። ስለዚህ ሉተር መዳን በእምነት ብቻ ነው ምንም መልካም ሥራ አይጠይቅም የሚለውን መገለጥ ያገኘ ጊዜ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተባረረ። ይህንን አዲስ መገለጥ ሊቀበሉት አልቻሉም። ይህ ዓይነቱ ችግር ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ውስጥ ገባ። ሜተዲስቶች ድነው፣ ስለ ቅድስና ተምረው አልኮል መጠጥ መጠጣት አቆሙ፤ ነገር ግን ውሃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመቀበር መጠመቅን ሊቀበሉ አልቻሉም።
አንዲት ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን የእምነት አቋሟን ካዘጋጀችበት ጊዜ ጀምሮ የቤተክርስቲያን መሪዎች በሙሉ እነዚያን የእምነት መግለጫዎች እንዲጠብቁ እና አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጦችን እንዲከላከሉ ስልጠና ይሰጣቸዋል።
በኤፌሶን የተደረገው የኒቆላውያን ሥራ ጊዜ ሲያልፍ በጴርጋሞን ደግሞ የኒቆላውያን ትምሕርት ወደ መሆን አደገ።
ሥራዎች ወደ ልማዶች፣ ልማዶችም ቆይተው ጊዜ ሲያልፍ ወደ ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች ይለወጣሉ።
ቤተክርስቲያን በአዲስ ሃሳቦች ከተከፈተች በኋላ ሃሰቦቿ ቋሚ ልማዶች ሆነው ይቀራሉ። ድግግሞሽ ሲበዛ እነዚህ ልማዶች የቤተክርስቲያኒቱ አስተምሕሮዎች ሆነው ይጸናሉ።
የአንጾኪያው ኢግናሺየስ እና እርሱን የመሳሰሉ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ጳጳስ የሁሉ ታላቅ ነው የሚለውን ሃሳብ ማሰራጨት ጀመሩ። ሃሳቡም ተቀባይነት አግኝቶ ከረጅም ጊዜ በኋላ ቋሚ ልማድ ሆነ። ከዚያ በኋላ ሁሉ ሊታዘዙት የሚገባ ጽኑ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ሆነ።
የሮም ጳጳስ ቅዱስ ጳውሎስ የሞተው ሮም ውስጥ ነው አለ። ይህም እውነት ነው። ጴጥሮስ ግን የመንግስተ ሰማያት መክፈቻዎች ተሰጥተውታል። ፖፑ እኔ የጴጥሮስ ተተኪ ነኝ ስላለ ይህንን ስልጣን ለራሱ ፈልጎታል። ስለዚህ ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ጴጥሮስ ሮም ውስጥ የመጀመሪያው ፖፕ ነበር እያለ ደጋገመ። ይህም ውሸት ብዙ ጊዜ ከተደጋገመ በኋላ እንደ እውነት ተቀባይነትን አገኘ።
በ600ዎቹ አካባቢ ሙስሊሞች እርስ በራሳቸው የሚፎካከሩትን የአንጾኪያ፣ ኢየሩሳሌም፣ እና የአሌግዛንድሪያ ቤተክርስቲያኖች በጦርነት አሸነፏቸው። ከዚህም የተነሳ በምዕራብ የነበረው የሮማው ፖፕ ያለ ምንም ተፎካካሪ ቀረ። ስለዚህ ፖፑ የምዕራብ አውሮፓ ብቸኛ ጳጳስ ሆነ። በ1453 ሙስሊሞች ኮንስታንቲኖፕልን በተቆጣጠሩ ጊዜ ሮም ታላቋ ቤተክርስቲያን ሆና አውሮፓን ትገዛ ነበር።
ኤልዛቤል የምትባል የቤተክርስቲያን ሴት ኖራ አታውቅም። የዚህች ሴት ስም የሚገልጸው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ባህሪ እና ድርጊቶች ነው።
እርሷም እድል ፈንታዋ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው።
ይህ በራዕይ ምዕራፍ 17 እና 18 ውስጥ በተገለጠው መሰረት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጣ ፈንታ ነው።
በ1922 በትያጥሮን ይኖሩ የነበሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሕዝብ ከትያጥሮን ተባረሩ። ከዚያ በኋላ በከተማይቱ ሙስሊሞች ብቻ ቀሩ።
ዛሬ ወደ ታላቁ መከራ የምትገባ ቤተክርስቲያን ትያጥሮን ውስጥ የለችም።
ደግሞም በቤተክርስቲያን ውስጥ በለዓም የሚባል ሰው ተገኝቶ አያውቅም።
ኤልዛቤል ሴት እንደመኗ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። ይህች ቤተክርስቲያን ጣኦት አምላኪ፣ ግፈኛ እና ጨካኝ ስለሆነች ልክ ኢዩ ኤልዛቤልን እንደ ገደላት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ልተጠፋ ተወስኖባታል። በስተመጨረሻ አስር ፈላጭ ቆራጮች በራዕይ ምዕራፍ 17 እና 18 መሰረት ቫቲካን ላይ ቦምብ ይጥላሉ።
ራዕይ 17፡16 ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል።
ራዕይ 18፡9 ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤
10 ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው፦ አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።
ለምንድነው በሩቅ የሚቆሙት? ለምንድነው ወደ ውስጥ ገብተው እሳቱን የማያጠፉት? የኑክሊየር ቦምብ በመሆኑ ከፍተኛ ጨረር ስለሚያመነጭ ሰው ሊያጠፋው አይችልም። ያም የሮም መጨረሻዋ ነው።
የክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ከሮም ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ አስሩ ፈላጭ ቆራጮች ቫቲካንን በኑክሊየር ቦምብ ወይም በሚሳኤል እንዲያጋዩ ያዛቸዋል።
ባላቅ የሞዓባውያን ንጉስ ነበረ። እርሱም ነብዩ በለዓም ሙሴን እና አይሁዶችን እንዲረግማቸው ገንዘብ ከፈለው።
በለዓም እውነተኛ የነብይነት አገልግሎት ውስጥ ነበረ፤ ነገር ግን ገንዘብ ተከፍሎት አይሁዶችን ማሳት ፈለገ።
የዲኖሚኔሽን አገልጋዮች በተሳሳቱ እምነቶች ሕዝባቸውን ለማሳሳት ገንዘብ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ።
እርሱም በብኤልፌጎር ድግስ አዘጋጅቶ አይሁዳውያንን ከሞዓባውያን ሴተኛ አዳሪዎች ጋር አስተዋወቃቸው። አይሁዶች ከእነዚህ ሴቶች ጋር በዝሙት ወድቀው በሺዎች የሚቆጠሩት ሞቱ።
የዳኑ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ በሚመሩዋቸው ሰዎች ላይ ከሚደገፉ ቤተክርስቲያኖች (ሴቶች) ጋር ይተባበራሉ።
ስለዚህ በለዓም የሚወክለው በ312 በጀመረው በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበረውን ሁኔታ ነው፤ በዚያ ጊዜ ንጉስ ኮንስታንቲን ልክ እንደ ባላቅ ለሮም ጳጳስ እንዲታዘዝለት ብሎ ገንዘብ ከፈለው (ይህም የሮም ጳጳስ ኋላ ፖፕ ሆነ)። ፖፑም በኒቅያ ጉባኤ በተዘጋጀው ሐይማኖታዊ ድግስ ውስጥ የስላሴ አስተምሕሮ በቤተክርስቲያኖች ላይ በግዳጅ እንዲጫንባቸው አደረገ። ራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ የሮም ቤተክርስቲያን ጋለሞታ ተብላለች። ስለዚህ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ትተው በመሄድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ጋር ዝሙት ፈጽመዋል።
እነርሱም ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር እንዲከፍትልን የሚያደርገው ፖፑ ብቻ ነው ብለው ስላሰቡ ሕዝቡ ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስርዓቶች ሁሉ ተገዢ ሆኑ፤ ይህ ታዛዥነት ግን ያመጣባቸው መንፈሳዊ ሞት ነው።
በለዓም (ፖፑን የሚወክለው) ሙሴን ተቃወመ፤ አይሁዶችንም ወደ ጣኦት አምልኮ ይዟቸው ሄደ።
በለዓም ማለት “ምናልባት” ማለት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን መቀየር እንችላለን፤ ያም “ምናልባት” ችግር ላይፈጥረ ይችላል። ይህ ትልቅ ስሐተት ነው።
ዘኁልቁ 31፡16 እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።
በለዓም ስጦታ ያለው ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ግን ስጦታውን ለክብር እና ለገንዘብ ብሎ ሸጠ። እርሱም በስተመጨረሻ አይሁዶችን አሳስቶ የሎጥ እና የሴት ልጁ ዲቃላ ልጆች ከሆኑት ሞአባውያን ጋር በማጋባት አስገድሏል።
ዘኁልቁ 25፡1 እስራኤልም በሰጢም ተቀመጡ፤ ሕዝቡም ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ጀመር።
ዘኁልቁ 25፡2 ሕዝቡንም ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ጠሩ፤ ሕዝቡም በሉ፥ ወደ አምላኮቻቸውም ሰገዱ።
ኮንስታንቲን እና ፖፑ በ325 ዓ.ም በተጠራው የኒቅያ ጉባኤ ቤተክርስቲያኖች የክርስትና መልክ ለተሰጣቸው የአሕዛብ ስላሴያዊ አማልክት እንዲሰግዱ አደረጉ።
የግብጾች ስላኤ
የቤተክርስቲያን ስላሴ።
ተመሳሳይነታቸውን ልብ በሉ። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጀመሪያ መሰረታዊውን የአሕዛብ ሃሳብ ኮረጀች፤ ከዚያ ክርስቲያናዊ ቃላት ነሰነሰችበት።
ነገር ግን ለዚህ ስላሴያዊ አምላክ የሚሆን አንድ ስም አልተገኘም።
ዘኁልቁ 25፡3 እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።
2ኛ ጴጥሮስ 2፡15 ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዓመፃን ደመወዝ ወደደ፥
ገንዘብ ተቀብሎ የዲኖሚኔሽን ስሕተትን መስበክ።
ይሁዳ 1፡11 ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።
በለዓም የሚለው ስም ሁልጊዜም የሚያያዘው ለገንዘብ ብሎ ከመስበክ ጋር ነው። ሆድን ለመሙላት ብሎ መስበክ።
አይሁዶች በስተመጨረሻ በለዓምን ገደሉት።