ከ2,300 ቀናት በኋላ መቅደሱ ነጻ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
እግዚአብሔር ከአብራሃም ዘር ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን። ከፍጥረታዊው ዘር ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ እስከ መንፈሳዊው ዘር እስከ ኢየሱስ ሞት ድረስ።
- ከፍጥረታዊው ዘር ከይስሐቅ እስከ መንፈሳዊው ዘር እስከ ኢየሱስ
- ሐጥያት በሰማይ ስለተጀመረ ሰማይም መንጻት ያስፈልገዋል
- የአሕዛብ 69 ዓመታት ከአይሁድ 70 ዓመታት ጋር እኩል ናቸው
- እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ ጋር ቃልኪዳን አደረገ
- ቃልኪዳኑ 3 ዓመት በሞላቸው በ3 እንስሳት አማካኝነት ነው የተፈጸመው
- ቃልኪዳኑ በተደረገ ጊዜ አብርሃም ከባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበር
- ቀራንዮ ሙሉ በሙሉ በይስሐቅ ሕይወት ውስጥ ታይቷል
- ቃልኪዳኑ ከብዙ መከራና መገፋት ጋር ነው የሚመጣው
- ከኢየሱስ ሞት ጀምረን ወደ ኋላ 2,300 ዓመታት እንቆጥራለን
- ከይስሐቅ ጀምሮ አይሁዳውያን ከግብዝ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ 691 ዓመታት አልፈዋል
- እስራኤሎች በጠላቶቻቸው የተገዙባቸውን ዓመታት አይቆጥሯቸውም
ከፍጥረታዊው ዘር ከይስሐቅ እስከ መንፈሳዊው ዘር እስከ ኢየሱስ
አብራሐም የቃልኪዳን ልጆቹ ፍጥረታዊው ልጅ ይስሐቅ እና መንፈሳዊው ልጅ ኢየሱስ ናቸው።
ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ሞት ድረስ 2,300 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት አልፈዋል።
ዳንኤል 8፡14 እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።
የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ጥቅስ ኢየሱስ የአብራሐም መንፈሳዊ ልጅ መሆኑን በማሳየት ይጀምራል።
ማቴዎስ 1፡1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
መቅደሱ የነጻው በ33 ዓ.ም የአብርሃም መንፈሳዊ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ መስቀል ላይ ሞቶ ከሞት ሲነሳ ነው። ከሐጥያት ማንጻት የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
ይህ ትንቢት የአብርሃም የተስፋ ቃል ልጅ ፍጥረታዊው ይስሐቅ ሲወለድ ነው።
እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃልኪዳን አደረገ፤ ይህም ቃልኪዳን ለዘሩ ጭምር የሚሆን ነው።
እግዚአብሔርም ይህንን ቃልኪዳን በክርስቶስ ሞት አጸናው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
በአብርሃም ወገብ ውስጥ ሶስት ትውልዶች ነበሩ።
ስለ አብርሃም የልጅ ልጅ ልጅ ስለ ሌዊ ሲናገር ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡-
ዕብራውያን 7፡10 መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና።
ስለዚህ ከአብርሃም ጋር የተደረገው ቃልኪዳን በቀጥታ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ፣ እና የ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ራስ ለሆኑን ለ12ቱ የያዕቆብ ልጆች ሁሉ ይሰራ ነበር።
ይህ ግን የሚሰራው ፍጥረታዊ በሆነችዋ የተስፋ ምድር እስራኤል ይኖሩ ለነበሩ ለፍጥረታዊ የአይሁድ ሕዝብ ነበር።
ከዚያ ወዲያ ግን ቃልኪዳኑ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ አማካኝነት ጠለቅ ባለ መንፈሳዊ ደረጃ ለአብራሃም መንፈሳዊ ልጆች ሁሉ ጸና።
ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል የሆነው ቃልኪዳኑ ለዓለም ሁሉ ተደረገ።
ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።
ሐጥያት በሰማይ ስለተጀመረ ሰማይም መንጻት ያስፈልገዋል
ለሐጥያት መፍትሄ መፈለግ በመጀመሪያ ለእግዚአብሔር በጣም ውስብስብ ሥራ ነበረ፤ ምክንያቱም በሐጥያት ምክንያት የተበላሸችው የኤድን ገነት ብቻ ሳትሆን ሰው እና መላው ፍጥረታት ሁሉ ነበሩ።
በተጨማሪ ሰማይም ጭምር መንጻት ያስፈልገው ነበር ምክንያቱም ሰይጣን እርኩሰቱን ሐጥያቱን የጀመረው ሰማይ ውስጥ ሊቃ መላእክት በነበረ ጊዜ ነው። ይህም ማለት ሳይረገምና የአጋንንት አለቃ ሳይሆን በፊት ነው።
በሰማይ ውስጥ ምንም ደም አልፈሰሰም፤ ስለዚህ በሰይጣን ተሸንግለው የወደቁ መላእክት ምንም የመዳን ዕድል የላቸውም። ወደ አጋንንትነት ወይም ሐጥያተኛ መናፍስት ተለውጠዋል።
የወደቁ መላእክት ሐጥያተኛ መናፍስት ናቸው። እነዚህ የወደቁ ሐጥያተኛ መናፍስት ምንም የመዳን ዕድል ስለሌላቸው ሰዎችም ሞተው መንፈሳቸው ከስጋቸው ከተለየ በኋላ የመዳን ዕድል የላቸውም። ስለዚህ በሕይወት ሳለን መዳን ያስፈልገናል።
የመጀመሪያውን ሐጥያት እጅግ ከባድ ያደረገው ሔዋን ማርገዟ እና የሚሞት ሕይወት መውለዷ ነው።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
ይህ እርግዝና ከቧላ አልነበረም፤ ከባሏ ቢሆን ኖሮ ሐጥያት አይሆንም ነበር።
እባቡ ከእንስሳት ሁሉ ብልህ ወይም ብልጥ እንስሳ ነበረ (ሰዎች እንደሚሉት አጥቢ እንስሳ)። ሰዎች እንደሚያስቡት መሬት ላይ በደረቱ እየተሳበ የሚሄድ እንስሳ አልነበረም፤ ነገር ግን በሰው እና በዝንጀሮ መካከል የነበረ ብልህ ፍጡር ነበር። ከሔዋን ጋር መነጋገር እና ማሰብ ይችል ነበር። ሰይጣን እንስሳ አፍ አውጥቶ እንዲናገር ማድረግ እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።
ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
ስለዚህ ከእንስሳት ሁሉ ብልጡ እንስሳ ከአጋንንት ሁሉ ብልጡ ጋኔን (ሰይጣን) ገብቶበት ሐጥያትን ወደ ምድር አመጣ።
የታላቅነት ፍቅር አደገኛ የሆነው ለዚህ ነው። ሰይጣን ታላቅ መሆን የሚፈልጉ ሰዎችን ነው የሚጠቀመው፤ ለምሳሌ ሐዋርያው ይሁዳ እና ንጉስ ሔሮድስ። ጲላጦስ ገዥ ነበረ። ሐይማኖት፣ ፖለቲካ፣ እና ገንዘብ በፈጠሩት እርኩስ ጥምረት ነው ኢየሱስን የገደሉት።
ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።
እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ የፈረደውን ዓይነት ፍርድ ነው እባቡ ላይ የፈረደበት። እግዚአብሔር እባቡን ከረገመው በኋላ በደረቱ እየተሳበ የሚሄድ ተራ እንስሳ አደረገው።
የአጥንቶቹ አወቃቀር ሙሉ በሙሉ ነው የተለወጠው። ሳይንቲስቶች በሰው እና በዝንጀሮ መካከል የጠፋ ማገናኛ አለ የሚሉትን ማግኘት የማይችሉት ለዚህ ነው። እባቡ ከመረገሙ በፊት የነበረው ቁመናውና ቅርጹ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ አሁን የምናውቀውን እባብ ሆነ።
እባብ መንታ ምላስ (ይህም እውነትን ከሐሰት ጋር የመቀላቀል ምልክት ነው) እንዲሁም አፉ ውስጥ መርዝ አለው ሐሰተኛ ትምሕርቶች የሚያመጡትን መንፈሳዊ ሞት ያመለክታል።
እባቡ ለሔዋን፡- “ዓይኖቻችሁ ይከፈታሉ” አላት። ስለዚህ እግዚአብሔር እባቡ ከረገመው በኋላ የዓይን ቆብ እንዳይኖረው አደረገ። የእባብ ዓይኖች ብርሃን በሚያሳልፍ ቅርፊት ስለሚሸፈኑ እንጂ ሁልጊዜ እንደተከፈቱ ናቸው።
እባብ በሆዱ እንዲንፋቀቅ ተደረገ። ሆድ ማለት የስጋዊ ፍላጎታችን ምሳሌ ነው። ሔዋን ስታረግዝ ሆዷ አበጠ። እምብርታችን በስጋችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ነው። የሚያመለክተውም እንደምንሞት ነው። እግዚአብሔር አዳምን እና ሔዋንን ሲፈጥራቸው ሆዳቸው ላይ ጠባሳ አድርጎ አልፈጠራቸውም። ዛሬ ብዙ ሰባኪዎች የሚያሳስባቸው ምግባቸው እንጂ የቃሉ እውነት አይደለም። ልክ እንደ ሐዋርያው ይሁዳ የብዙ ሰባኪዎች የውድቀት መነሻ ገንዘብ ነው።
የሚያስፈራው ነገር “አፈር ትበላለህ” የሚለው ቃል ነው። እባቦች እንቁራሪትና አይጥ ነው የሚበሉት እንጂ አፈር አይደም፤ ስለዚህ አፈር ትበላለህ የተባለው በቀጥታ ሳይሆን በምሳሌ ነው። ሰዎች የተሰሩት ከአፈር ነው። ስለዚህ ሳንድን ከሞትን “የእባብ ምግብ” እንሆናለን ምክንያቱም የእባቡ ረጅም አካል ተንሸራትተን የምንገባበት የሲኦል ምሳሌ ነው።
ምድር የተረገመችው አዳም ለፍቶ ላቡን አንጠፍጥፎ እንዲበላ ነው።
አዳም የመጣው ከአፈር ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር አዳም የመጣበትን አፈር ረገመ። ይህም ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ እባቡ የሚበላው አፈር እራሱ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ጣልቃ ባይገባ ኖሮ ሰው ሁሉ ሲኦል እንዲወርድ ተረግሞ ነበር።
ዘፍጥረት 3፡17 አዳምንም አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
ዘፍጥረት 3፡19 ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።
ላባችን እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ለፍተን መስራት አለብን። የሐጥያተኞች ትልቁ እርግማን ስራ ፈትነት ነው።
ሕዝቅኤል 16፡49 እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፤ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ …
የአዳም አካል የተሰራው ከአፈር ነው።
ስለዚህ የአፈር ምንጭ የሆነችዋን ምድር መቤዠት ከአፈር የተሰሩ ፍጡራን የሆኑ ሰዎችን ከመቤዠት እኩል አስፈላጊ ነው።
ሮሜ 8፡22 ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን ያዘጋጀው እቅድ ምድርን መቤዠት እንዲሁም ሰማይን ማጽዳትን ያጠቃልላል።
ከአዳም ውድቀት በኋላ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የመጀመሪያውን ሚና የተጫወተው ኖህ ነው፤ ይህም ሰው አዳም ሐጥያት ከሰራ ከ1,656 ዓመታት በኋላ ምድርን በሙሉ የሚያጠፋ ውሃ በመጣ ጊዜ ከጥፋት ዳነ። ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ ጥፋት ውሃ ድረስ ያለው ታሪክ ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ በአምስት ምዕራፎች ብቻ ነው የቀረበው። ቀጣዮቹ አራት ምዕራፎች ስለ ኖህ ነው የሚተርኩት።
ማስታወሻ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ዓመት ማለት 360 ቀናት ናቸው ምክንያቱም እያንዳንዱ ወር 30 ቀን ነው።
ዘፍጥረት 7፡11 በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፥ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ፤
ዘፍጥረት 8፡4 መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።
ከ17/2 እስከ 17/7 ድረስ አምስት ወራት ናቸው ያለፉት።
ይህም 150 ቀናት ተብሎ ነው የተጻፈው።
በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ ወር 30 ቀን ነው ማለት ነው።
ዘፍጥረት 7፡24 ውኃውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።
ከጥፋት ውሃ በፊት የአንድ ዓመት ርዝመት 360 ቀናት ነበር።
መርከቢቱ ውሃው ላይ የተንሳፈፈችው ለአንድ ዓመት ያህል ነው። የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ምደር ከነበረችበት ዛቢያ ፈቀቅ ብላ ወደ ሕዋ ቅዝቃዜ ውስጥ ተጠጋች። የምድር ዋልታዎችም ወደ በረዶነት ተለወጡ። ይህም የመጨረሻው የበረዶ ዘመን ሆነ። በደቡብ ዋልታ ከሰሜን ዋልታ በአስር እጥፍ የሚበልጥ በረዶ አለ። ይህም ልዩነት ምድር በምሕዋርዋ ላይ ስትዞር እንድትወዛወዝ በማድረጉ የተነሳ ምሕዋርዋ ከበፊቱ ጥቂት ረዘም ስላለ ከዚያ ወዲያ አንድ ዓመት ለመጨረስ 365.2422 ቀናት መፍጀት ጀመረች።
አሁን ለአንድ ዓመት የምንቆጥረው 365 ቀን ሔኖክ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ እስኪወስደው ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር ለተመላለሰበት 365 ዓመት ምስክር ነው፤ ይህም ቤተክርስቲያን ጌታ ሲመጣ ልትቀበለው በአየር ላይ እንደምትነጠቅ የሚያሳይ ምሳሌ ነው።
ዘፍጥረት 5፡23 ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ።
24 ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።
ዳንኤል አራት የአሕዛብ መንግስታትን የሚወክሉ አራት አውሬዎችን በራዕይ አየ።
ዳንኤል በራዕይ ካያቸው አውሬዎች መካከል አራተኛው አውሬ “ከሌሎቹ ሶስት መንግስታት የተለየ” የሮማ መንግስት ነው ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፖፕ መንግስት ወደ መሆን ተለውጧል፤ ይህችም ቤተክርስቲያን የዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ወይም የዲኖሚኔሽናዊ ክርስትና እናት ናት። ሰዎች የክርስቶስ አካል ከመሆን ይልቅ የቤተክርስቲያን አባላት ሆነዋል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ የሚሉ ሰባኪዎችን ያምናሉ።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ሳይሆን ቤተክርስቲያን የምትለውን ያምናሉ።
ዲኖሚኔሽናዊ ክርስትና ቤተክርስቲያንን በ45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ከፋፍሏል፤ ሕዝቡንም እንደ ባሪያ እየረገጠ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ለቤተክርስቲያን መሪዎች እንዲታዘዝ አድርጓል።
ዳንኤል 7፡23 እንዲህም አለ፦ አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፤ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል።
ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።
“ዘመናትን ይለውጥ ዘንድ”። ሮም ካላንደር ላይ ለውጥ እንደምታደርግ ዳንኤል አስቀድሞ አይቷል።
ፖፑ እራሱን “ቪካሪየስ ክሪስቲ” ብሎ ይጠራል፤ ይህም “በክርስቶስ ቦታ ነኝ” ማለት ነው። እዚህ ፖፑ ራሱን ከፍ የሚያደርግባቸው የትዕቢት ቃላት ናቸው።
በ1302 ዓ.ም ፖፑ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን የለም ብሎ አወጀ። ስለዚህ ለመዳን ሰው ሁሉ ለፖፑ መገዛት አለበት አሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ቃላት ፖፑን እና የሮማ ከቶሊክ ቤተክርስቲያንን ያለ ልክ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ትልልቅ ቃላት ናቸው። ደግሞም ማዳን የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ከመሆኑ አንጻር የፖፑ አዋጅ የእግዚአብሔርንም ቃል ይቃረናል።
በፖፑ ሃሳብ አልስማማም ያሉ ከአስር ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች በጨለማው ዘመን ውስጥ እና በ1500ዎቹ ደግሞ የሉተርን ተሃድሶ ለማዳፈን በተከፈተ ጸረ ተሃድሶ ዘመቻ ውስጥ ተገድለዋል።
የአሕዛብ 69 ዓመታት ከአይሁድ 70 ዓመታት ጋር እኩል ናቸው
“ዘመናትን ይለውጣል”። ካላንደርን የለወጡ ሮማውያን ናቸው።
በ46 ዓመተ ዓለም ሮማዊው አምባ ገነን ዩልየስ ቄሳር በ45 ዓመተ ዓለም ላይ 90 ቀናትን በመጨመር በአንድ ዓመት ውስጥ ያሉትን የቀናት ብዛት 365.25 ቀናት አደረጋቸው፤ ይህን ያደረገው የካላንደር ቀኖች በዓመቱ ውስጥ ከሚፈራረቁ ወቅቶች ጋር እንዲገጥሙ ብሎ ነው። ይህ አቆጣጠር ትንሽ ስሕተት አለው፤ ምክንያቱም ትክክለኛው የዓመት ርዝመት 365.2422 ቀናት ነው። ይህ ለውጥ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከ1,600 ዓመታት በኋላ ካላንደሩ ከእስፕሪንግ ኤክዊኖክስ ጋር በ10 ቀናት መዛነፉ አይቀርም።
ኤክዊኖክስ ማለት የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት እኩል 12 ሰዓት የሚሆንበት ቀን ነው።
በ1582 የሮማ ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው የካላንደሩን ዓመት ወደ 365.2425 ቀናት ለወጠው። በዚያ ጊዜ ከትክክለኛው የአንድ ዓመት ርዝማኔ ጋር የተፈጠረው ልዩነት እምብዛም ነበረ።
ስለዚህ የካላንደሩን ዓመት ይለውጡ ዘንድ እግዚአብሔር ለሮማዊው አውሬ (ማለትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ለአረማዊው የሮማ መንግስት) ፈቀደለት። ይህም ለውጥ ወቅቶቹ ከወራቱ ጋር ይበልጥ መጋጠም እንዲችሉ አስፈላጊ ነው።
ይህ ለውጥ ሰይጣን የአውሬውን ኃይል መልሶ ያስነሳበት ዘዴ ነው።
በ476 ዓ.ም የሮማ መንግስት በባርቤሪያውያን ጭፍራዎች እጅ ለሞት በሚያበቃ ቁስል ተመታ። ሮም ውስጥ ከነበሩ የመጀመሪያ ተራሮች መካከል አንዱ የሆነው ካፒቶል ተራራ ላዩ ላይ የጁፒተር ቤተመቅደስ ነበረበት፤ ይህም የመንግስት እና የሐይማኖት ማዕከል ነበረ። ባርቤሪያውያን ይህንን ቤተመቅደስ አልተጠቀሙበትም ምክንያቱም በእነርሱ ዓይን ቤተመቅደሱ ኃይሉንም ስልጣኑንም አጥቷል። ነገር ግን ዋና ጽሕፈት ቤቷን በካኤልያን ተራራ ላይ በላተራን ቤተመንግስት እና ባሲልካ (ትልቅ ቤተክርስቲያን) አድርጋ የነበረችዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የወደቀውን የሮማ መንግስት ስልጣን ተክታ ተነሳች። ካኤልያን ተራራም ከመጀመሪያዎቹ ሰባት የሮም ተራሮች አንዱ ነው። ወድቆ በነበረው የሮማ መንግስት ስልጣን ቦታ ፖፑ ተተካበት።
አሁን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዓመት ርዝመት እንመለስ፤ አንድ ዓመት በመጽሐፍ ቅዱስ አቆጣጠር ሰላሳ ቀናት ያሉዋቸው 12 ወራት ማለትም 360 ቀናት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻ ስለሚመጣው የታላቁ መከራ ሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ሲናገር 1,260 ወይም 42 ወራት ነው የሚለው።
ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
1260 / 42 = 30 ቀናት፤ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ወር ሰላሳ ቀን ነው።
ስለዚህ በየ69 ዓመቱ እኛ የምንከተለው ባለ 365.24 ቀኑ ዘመናዊው የሮማውያን ካላንደር ከባለ 360 ቀኑ የአይሁዳውያን 70 ዓመት ጋር እኩል ይሆናል።
በየዓመቱ የሚገኘው 5.24 ትርፍ ቀን ተጠራቅሞ በ69 ዓመታት ውስጥ የሚሰጠን ውጤት 5.24 x 69 = 361 ትርፍ ቀናት፤ ማለትም አንድ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመት (ይህም ስሌት ላይ ጉልህ ችግር የማያመጣ ከአንድ ፐርሰንት ያነሰ ስሕተት ነው)።
ስለዚህ ረዘም ያሉት የእኛ ዓመታት በ69 ዓመት ውስጥ ከ70 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት ጋር እኩል ናቸው።
የመጽሐፍ ቅዱስ የዓመት አቆጣጠር ከእኛ ዘመናዊ የአሕዛብ አቆጣጠር ጋር እንዲገጥምልን ከፈለግን እነዚህን ትርፍ የአይሁድ ዓመታት መቀነስ አለብን።
ከአዳም ውድቀት ጀምሮ እስከ ጥፋት ውሃ ድረስ 1,656 ዓመታት ነበሩ።
1,656/70 = 24
ስለዚህ በዚህ ዘመን በምንጠቀምበት አቆጣጠር መሰረት 1,656 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት በ24 ይቀንሳሉ።
ስለዚህ 1,656 – 24 = 1,632 የአሕዛብ ዓመታት።
ስለዚህ በአሁኑ አቆጣጠራችን መሰረት የጥፋት ውሃ የመጣው ከውድቀት ጀምሮ 1,632 ዓመታት ካለፉ በኋላ ነው።
እግዚአብሔር ከኖህ እና ከምድር ጋር ቃልኪዳን አደረገ። የቃልኪዳኑ ምልክት ቀስተ ደመና ነው። ቀስተ ደመና ውስጥ እርስ በርሳቸው የተደራረቡ ሰባት ጉልህ ቀለሞች አሉ።
ዘፍጥረት 9፡13 ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
ይህም (አስተምሕሮን እና ብዙ ሕዝብን የሚወክለው) ውሃ ሁለተኛ ተመልሶ ምድርን እንደማያጠፋት ነው።
በመንፈሳዊ ሚስጥር ደግሞ ቀስተ ደመናው ከዚያ በኋላ የመጡትን ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል።
እያንዳንዱ የቀስተ ደመና ቀለም አንድ የቤተክርስቲያን ዘመንን ይወክላል።
7ቱ ቀለሞች በአንድነት ሲዋሃዱ ነጭ ቀለም ይሰጣሉ።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በአንድ ሲጣመሩ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል ይሰጣሉ።
ሰይጣን ሁልጊዜ የማያምኑ ሰዎችን እና እንደሚያምኑ የሚያስመስሉ ሰዎችን ሰብስቦ ከራሱ ጋር ብዙሃኑን ያሰልፋል። እነርሱም በሐሰተኛ ትምሕርታቸው አማካኝነት በየዘመናቱ የተገለጡ እውነቶችን አፍነው ለማስቀረት ይሞክራሉ። ስሕተት ሁልጊዜ በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። ነገር ግን ለየዘመናቱ ከተላኩ የእግዚአብሔር መልእክተኞች አገልግሎት የተነሳ እግዚአብሔር እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ነውጥ ውስጥ እየመራ ያሳልፋታል።
እግዚአብሔር ብዙሃኑ በስሕተቶቻቸው የጥቂቱን እምነት እንዲያደናቅፉና እንዲያጠፉ አይፈቅድም።
በኖህ ዘመን 8 አማኞች በምድር ላይ ከሚኖሩ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች ጋር ነበር የተፋጠጡት። የማያምኑ ሰዎች በቁጥር በጣም ይበልጣሉ
ኢሳይያስ 59፡19 እርሱ የእግዚአብሔር ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።
ቀስተ ደመናው የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ያመለክታል፤ ይህም ተስፋ በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የሚያሰምጥ የአለማመን ጎርፍ ቢመጣም እንኳ እጅ የማይሰጡ አማኞች እንደሚኖሩ ነው።
እግዚአብሔር ምድርን ለመቤዠት የወሰደው የመጀመሪያው እርምጃ በኖህ ዘመን ምድርን በውሃ መሸፈን ነው።
ይህም የውሃ ጥምቀት ተምሳሌት ነው። አማኞችም ሲጠመቁ ልክ እንደ ምድር ሙሉ በሙሉ በውሃ መሸፈን አለባቸው።
ከዚያ ምድርን ለመቤዠት ሁለተኛው እርምጃ ደም ነው።
ከጥፋት ውሃ አንስቶ 2,600 የአሕዛብ ዓመታት ካለፉ በኋላ አይሁዶች ኢየሱስን እጅግ ከመጥላታቸው የተነሳ ከከተማ አውጥተው ቀራንዮ የተባለ ቦታ ሰቀሉት። ሲሰቅሉትም ደሙ ወደ ምድር ተንጠባጠበና ምድርን ዋጃት።
የኢየሱስ ደም የነካውን ነገር ሁሉ ይቤዠዋል ወይም ይዋጀዋል።
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው የሐጥያትን ቆሻሻ ከሰው፣ ከምድርና፣ ከሰማይ ሊያስወግድ የሚችለው።
ቀራንዮ የሰዎች መዳን የተከናወነበት ወሳኝ ሰዓት ነው። ይህ ቀን በትንቢት የተነገረው 2,300 ቀን የሚያበቃበት ቀን ነው (መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመት ነው)።
ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሲጠይቅ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው።
ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።
ከቀራንዮ መስቀል ወዲህ 2,000 ዓመታት አልፈዋል፤ አሁን ደግሞ የኑክሊየር ቦምብ የሚፈነዳበት እና ከምድር ውስጥ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የሚጀምርበት የ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ከፊታችን እየመጣ ነው።
ውሃ፣ ደም፣ እሳት።
ምድር በነዚህ ሶስት ነገሮች ከነጻች በኋላ ኢየሱስ እና ሙሽራይቱ ለሚነግሱበት ለ1,000 ዓመት የሰላም መንግስት ምቹ መናገሻ ትሆናለች።
እግዚአብሔር ለምድር ያሰበላት ይህ ነው።
የጥፋት ውሃው ካበቃ በኋላ እግዚአብሔር ከአንድ ሰው እና ከዘሮቹ ጋር አዲስ ቃልኪዳን አደረገ።
ከጥፋት ውሃ በኋላ የክፋት አሰራር ኃይሉን አሰባስቦ በአንድ ናምሩድ በተባለ ሰው በኩል የባቢሎን ግንብ አካባቢ ተገለጠ። ይህ ግንብ የተሰራበት ቦታ ነው ኋላ የባቢሎን ከተማ የተቆረቆረችው። ናምሩድ የመጀመሪያውን የሰው መንግስት ሊመሰርት ሰዎችን ሁሉ ሲያንበረክክ ከዚያ ቦታ ጀምሮ ጣኦት አምልኮ፣ ሐሰተኛ አስተምሕሮዎች እና ብዙ አማልክትን የማምለክ ልማዶች በዓለም ዙርያ ሁሉ ተሰራጩ።
ዘፍጥረት 10፡9 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፦ በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።
ሰዎች እግዚአብሔር ከተናገረው ቃል የበለጠ ለናምሩድ ቃል ትልቅ ቦታ ሰጡት። የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች መሰረታዊ ስሕተታቸው ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ለሰው ቃል ስፍራ መስጠታቸው ነው።
ዘፍጥረት 10፡10 የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።
በአንድ መንግስት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መሪያቸውን መታዘዝ አለባቸው።
ስለዚህ ምን እንደሚያደርጉ እና ምን እንደሚያስቡ የሚነግራቸው መሪያቸው ነው። መሪያቸው ሃሳባቸውን ይቆጣጠራል።
በራሳቸው ጭንቅላት ማሰብ አይፈቀድላቸውም። መሪያቸው ከሚያውቀው ውጭ ማሰብ አይፈቀድላቸውም።
መሪያቸው ላይ ባለው ውስንነት እነርሱም ውስን እንዲሆኑ ይደረጋሉ።
ስልጣን የሚወድ ሐይማኖታዊ መሪ ሰው ሁሉ ለእርሱ እንዲታዘዝለት እና ሁሉም እንዲገዙለት ያስገድዳቸዋል።
ሰዎች ማየት የሚችሉት ራሳቸው ላይ ባደረጉት ውስንነት መጠን ነው።
አስቀድመው ባረደጉት የሃሳብ ገደብ ውስጥ ብቻ ነው ማየት የሚችሉት።
ከእነርሱ ሐይማኖታዊ ስርዓት ውጭ የሆነ ሰው ሁሉ ተሳስቷል ማለት ነው ብለው ይደመድማሉ።
የሐይማኖት መሪዎች ትኩረታቸውን የሚያደርጉት የራሳቸውን መንግስት በመገንባት ላይ እንጂ የእግዚአብሔርን መንግስት አይደለም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ቀጣዩን ታላቅ ሚና የሚጫወት ሰው ጠራ፤ እርሱም አብርሃም ነው። አብርሃም ከጥፋት ውሃ 290 ዓመታት በኋላ ነው የተወለደው። የክፋት አሰራር ማዕከሉን በጤግሮስ እና በኤፍራጥስ ወንዝ መካከል አቋቋመ። የዚያ አካባቢ ሰዎች እንደ ግብጻውያን ብዙ አማልክትን አመለኩ።
አብርሃም ከአባቱ ከታራ ጋር ሆኖ ከኡር ተነስቶ ወደ ካራን ሄደ። ታራ ሲሞት እግዚአብሔር አብርሃምን በቀጥታ ማናገር ጀመረ (ስሙ አብራም ነበረ)፤ ዕድሜው 75 ዓመት ሲሆን እግዚአብሔር ውጣ ብሎ አዘዘው። እግዚአብሔር አብርሃምን የጠራው ለእርሱ እና ለልጅ ልጆቹ የተስፋይቱን ምድር ሊሰጣቸው ነው፤ እርሷም የዛሬዋ ኢየሩሳሌም ባለችበት ዙርያ የምትገኘው ምድር ናት። አብርሃም በኖረበት ዘመን ኢየሩሳሌም ገና አልተቆረቆረችም ነበር። ከላይ ባለው ካርታ ውስጥ አረንጓዴው መስመር የሚያሳየው እግዚአብሔር አብራሃምን በጣኦት አምልኮ እና በባዕድ እምነቶች ከተዋጠው ሥፍራ በጠራበት ዘመን አብራሃም የተንቀሳቀሰባቸውን ቦታዎች ነው።
የአብርሃምን የልጅ ልጆች ለመዋጀት እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ ጋር አዲስ ቃልኪዳን አደረገ።
ፍጥረታዊው ቃልኪዳን የተደረገው ለእስራኤል የተስፋ ምድር ለአብርሃም እና ለፍጥረታዊ ዘሮቹ (ብዙ ቁጥር) እንዲሰጥ ነው፤ እነርሱም አይሁድ ተብለው የሚጠሩት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚያምኑ ሰዎች ናቸው።
ቃልኪዳኑ ግድ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና መጽናት ያስፈልገው ነበር፤ ኢየሱስ የአብርሃም መንፈሳዊ ዘር (ነጠላ ቁጥር) ነው። ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተሰጠው መሲህ ኢየሱስ ነው።
ዘፍጥረት 12፡7 እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
የአብርሃም ዘር ጊዜውን ጠብቆ ተስፋውን ይወርሳል።
ዘፍጥረት 17፡7 ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ዘፍጥረት 17፡21 ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።
ዘፍጥረት 21፡5 አብርሃምም ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ የመቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።
ቃልኪዳኑን ለማጽናት አብርሃም (አባትየው) መስዋእት ሆኖ መቅረብ የሚችል የተስፋ ቃል ልጅ ያስፈልገዋል፤ እርሱም ይስሐቅ ነው።
ይስሐቅ በተሰዋ ጊዜ ቢሞትም እንኳ እግዚአብሔር መልሶ ከሞት እንደሚያስነሳው አብርሃም አምኗል። እግዚአብሔር ግን ይስሐቅ እንዲሞት አልፈቀደም።
ይህም ሐሳብ የአብርሃም መንፈሳዊ ልጅ በሆነው በኢየሱስ ተፈጽሟል። ኢየሱስ ሞቶ ከዚያ ከሞት ተነስቷል።
ቃልኪዳኑ መጽናት የሚችለው የአብርሃም መንፈሳዊ ልጅ በሆነው በኢየሱስ ብቻ ነው።
ይህ የተፈጸመው የአብርሃም ፍጥረታዊ ልጅ ይስሐቅ ከተወለደ ከስንት ዓመት በኋላ ነው?
አብርሃም ፍጥረታዊ ልጁን ይስሐቅን ካልወለደ በቀር እስራኤል የሚባል ሕዝብ ሊፈጠር አይችልም።
የእስራኤል ሕዝብ የአብርሃምን መንፈሳዊ ልጅ መሲሁን እስካልወለዱ ድረስ በዓለም ዙርያ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ልትፈጠር አትችልም።
ስለዚህ ከተስፋው ልጅ ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ እስከ ክርስቶስ መስቀል ድረስ የአይሁድን ሕዝብ ለስንት ዓመት ሲመራ ነው የቆየው?
በቀራንዮ መስቀል የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ሲፈስስ መቅደሱ በደሙ ነጽቷል።
የመሲሁ መምጣት ተስፋ ወይም የአብርሃም መንፈሳዊ ልጅ መወለድ እግዚአብሔር ለአብርሃም ፍጥረታዊ ልጅ እንዲወልድ ከሰጠው ተስፋ ጋር የተያያዘ ነው።
ከተስፋው ልጅ ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ሞት ድረስ የተቆጠሩት ዓመታት 2,300 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት ናቸው።
አብርሃም በፍጥረታዊ ልጁ በይስሐቅ መወለድ ተባርኳል።
በመንፈሳዊ ልጁ በኢየሱስ ሞት ደግሞ ዓለም በሙሉ ይባረካል።
መንፈሳዊ የሆነው የኢየሱስ ቃልኪዳን ለአብርሃም የተደረገውን ፍጥረታዊ ቃልኪዳን ከፍ ከፍ ያደርገዋል፤ ለአብርሃም የተሰጠው ፍጥረታዊ ቃልኪዳን የተስፋይቱ ምድር ለአይሁዶች መኖሪያ ሆና እንድትሰጥ ነው። የአብርሃምን ቃልኪዳን ጠለቅ ባለ መንፈሳዊ መንገድ ማጽናት በዓለም ዙርያ ሁሉ ላሉ ዳግመኛ ለተወለዱ አሕዛቦች ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ወደ እውነት ሁሉ በሚመራቸው በመንፈስ ቅዱስ ቢያምኑ በር ይከፍትላቸዋል።
ቃሉ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቲያኖች የተስፋ ምድር ነው። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ባሳየቸው መንገድ እና ዘይቤ ይኖሩበታል።
የክርስቲያኖች ተስፋ ለሚኖሩበት ዘመንና ሁኔታ የተመደበላቸውን ቃሉን የሚገልጥላቸው መንፈስ ቅዱስ ነው።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።
የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል መንፈስ ቅዱስን መላክ ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
ተስፋው መንፈስ ቅዱስ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ እውነት ይመራናል፤ ይህም ሃሳባችን እና እምነታችን የሚያምኑትና የሚኖሩበት መንፈሳዊ ምድር ነው።
ከአብርሃም ጋር የተደረገውን ቃልኪዳን የሚያመለክቱ ፍጥረታዊ ምልክቶች በሙሉ ጠለቅ ያሉ መንፈሳዊ እውነታዎችን የሚወክሉ ናቸው፤ እነዚህም ሁሉ እውነታዎች ኢየሱስ ቃልኪዳኑን በሚያጸናበት ጊዜ በተግባር የሚፈጸሙና ለአብዛብ ቤተክርስቲያን መዳን የሚሆኑ ናቸው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ኢየሱስ በምድር ላይ ለ1,000 ዓመት በሚነግስበት የሰላም መንግስት ከታላቁ መከራ የተረፉ አይሁዳውያን ምድርን በሚገዙበት ዘመን የተስፋይቱ ምድር ይህንን ነው የምትመስለው።
ኤፍራጥስ የባቢሎን መንግስት ድንበር ነበረ። ይህ መንግስት የባቢሎናውያን ሚስጥራት መፍለቂያ ነው፤ እነዚህ ሚስጥራት ከባቢሎን ተነስተው በፋርስ እና በግሪክ መንግስታት በኩል አልፈው ወደ ሮማ መንግስት ከገቡ በኋላ በስተመጨረሻ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልከው ገብተዋል።
ስለዚህ ባቢሎን የሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ተምሳሌት ሆነች። ግብጽም የፀሃይ አምልኮ መነሻ እንደመሆኗ የዓለማዊነት ተምሳሌት ናት። እግዚአብሔር ከዓለማዊነት እና ከሰው ሰራሽ ሐይማኖቶች ነጻ የሆነች የተስፋ ምድር ነው ለአይሁዶች ያዘጋጀላቸው። ከዚያ ብዙ ዘመናት ካለፉ በኋላ እግዚአብሔር ከዓለማዊነትን እና ከሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽናዊ እምነቶች የጸዳች ቤተክርስቲያን ፈለገ።
እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ ጋር ቃልኪዳን አደረገ
በእግዚአብሔር እና በአብርሃም መካከል የተደረገው ፍጥረታዊ ቃልኪዳን እንደ ምልክት ሶስት እንስሳትን ያካትታል፤ እነርሱም ለሁለት ለሁለት ተሰንጥቀዋል። እንስሳቱ ከተሰነጠቁ በኋላ የተሰነጠቁት አካላቸው ጎን ለጎን ተቀምጠዋል። እነዚህ ፍጥረታዊ እንስሳት ጥልቅ የሆኑ ሚስጥራትን ነው የሚወክሉት። እነዚህም ሚስጥራት ኢየሱስ በቀራንዮ መስቀል ላይ ሲሞት ብቻ የሚፈጸሙ ናቸው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም … ቃል ኪዳን አደረገ፦
ዘፍጥረት 15፡9 እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው።
በጉ የሚወክለው የጌታ ኢየሱስን መምጣት ነው።
አብርሃም ይስሐቅን ሊገድለው ሲል እግዚአብሔር አስቆመውና በይስሐቅ ቦታ እንዲሞት በግ ሰጠው።
ዘፍጥረት 22፡13 አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፥ በልጁም ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው።
በጉ ሊያመልጥ አልቻለም። ቀንዶቹ ሐረግ ውስጥ ተጠምጥመው ስለተያዙ ለአንድ ሰው ብቻ ማለትም ለይስሐቅ መሞት ነበረበት። ስለዚህ የአብርሐም ልጅ ከሞት ዳነ።
የአብርሃም መንፈሳዊ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ከይስሐቅ ይልቅ እጅግ ታላቅ ነው። እርሱ ሌሎችን ለማዳን የራሱን ሕይወት ሰጠ። እራሱን ሊያድን አልሞከረም።
ልክ እንደ በጉ ኢየሱስም ሊያመልጥ አልቻለም። መስቀል ላይ በሚስማር ተቸነከረ፤ ንስሐ ለሚገቡ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሐጥያት ሞተ፤ እነዚህም በብዛት አሕዛብ ናቸው።
ስለዚህ ኢየሱስ ቃልኪዳኑን ባጸና ጊዜ የቃልኪዳኑ ውጤታማናት ይበልጥ ጎልቶ ታየ።
ገላትያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።
17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።
ቀድሞ በነበረ ሐይማኖት ሥርዓት ማለትም በአይሁድ ሕግ ላይ ተመስርቶ የተጀመረ ብቸኛ ሐይማኖት ክርስትና ነው። ከዚህም የተነሳ በአይሁድ ሕግ ውስጥ የሚገኙ ምልክቶች በትኩረት ሲጠኑ ጠለቅ ያለ መረዳት ይሰጣሉ።
ኢሳይያስ 42፡21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።
አይሁዳዊው ይስሐቅ በሕይወት በመኖሩ ክብር ተሰማው።
እኛ አሕዛብ ኢየሱስ ስለሞተልን ነው ክብር ያገኘነው። ስለዚህ እኛ የተሻለ ቃልኪዳን አለን።
ሁለተኛው ተምሳሌት ፍየል ነው። እርሱም ሐጥያታችንን ከእኛ ወስዶ ተሸክሞ ወደ ሩቅ ቦታ የሚሄደው ሸክም ተሸካሚ ነው።
አይሁዶች ሁለት ፍየሎችን መርጠው ይወስዳሉ። አንዱ ፍየል ለአይሁድ ሕዝብ ሐጥያት ይታረዳል፤ ሁለተኛው ፍየል ደግሞ የሕዝቡን ሐጥያት ተሸክሞ ምድረበዳ ውስጥ ሩቅ ቦታ ይሄዳል።
አብርሃም ከዚህ ግማሹን ብቻ ነው ማቅረብ የቻለው፤ እርሱም የሞተው ፍየል ነው። ስለዚህ ከአብርሃም ጋር የተደረገው ፍጥረታዊ ቃልኪዳን መልካም ነው ግን ሙሉ አይደለም።
ኢየሱስ ግን ቃል ኪዳኑን ሲፈጽመው ሙሉውን ስራ ነው የሚያከናውነው።
ኢየሱስ መፈጸም ያለበት ሁለት ስራዎች ነበሩት። ልክ እንደ መጀመሪያው ፍየል ሐጢያታችንን ተቀብሎ ሞተ። ቀጥሎ ደግሞ በውስጡ የነበረው ታላቅ ቅዱስ መንፈስ ከአካሉ ወጥቶ ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል ወርዶ የሐጥያት አባት በሆነው በሰይጣን ላይ አራገፈው። ስለዚህ ለነዚህ ሁሉ ሐጥያቶች ተጠያቂው ሰይጣን ነው።
ስለ ሐጥያታችን መሞት እና ሐጥያታችንን ተሸክሞ ከእኛ ማራቅ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። ዋነኛው የሚለቀቀው ፍየል እረሱ ነው።
ዘሌዋውያን 16፡8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ።
“ዕጣ የሚጣለው” የትኛው ፍየል እንደሚሞት ለመምረጥ ነው። አይሁዳውያን ማን እንደሚሞት ለመወሰን በኢየሱስ እና በነፍሰ ገዳዩ በበርባን መካከል ምርጫ ቀረበላቸው።
ዘሌዋውያን 16፡9 አሮንም የእግዚአብሔር ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል።
ዘሌዋውያን 16፡10 የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ፥ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል።
ሁለተኛው ፍየል ሳይታረድ በሕይወት ይቀርና ወደ ምድረበዳ ይለቀቃል። ይህም መንፈስ ቅዱስ ሐጥያታችንን ይዞ ወደ ሩቅ ቦታ ወስዶ እንደሚጥለው የሚገልጥ ተምሳሌት ነው።
መንፈስ ቅዱስ በቀራንዮ አልሞተም። ሞት ማለት የመንፈስ ከስጋ መለየት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ሲሞት በውስጡ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ከስጋው ወጥቶ ወደ ሲኦል ወረደና ሰይጣንን ፊት ለፊት አግኝቶ ድል ነሳው።
ንጹህ መስዋእት የሆነች ቀይ ጊደር በእሳት ከተቃጠለች በኋላ አመዷ እርኩሰት የሚያነጻ ውሃ ላይ ይበተናል፤ ሕዝቡንም ከሐጥያታቸው ይለያቸዋል።
ዘኁልቁ 19፡2 እግዚአብሔር ያዘዘው የሕጉ ትእዛዝ ይህ ነው፤ መልካሚቱን፥ ነውርም የሌለባትን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ቀይ ጊደር ያመጡልህ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።
ቀንበር አንድ እንስሳ ለሰዎች እንዲታዘዝ ያስገድደዋል። ይህች ቀይ ጊደር ግን ሰዎችን እንድትታዘዝ ተገድዳ አታውቅም። እኛም በፍጹም የቤተክርስቲያን ልማዶችን ለመታዘዝ መገደድ የለብንም።
ዘኁልቁ 19፡3 እርስዋንም ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጣላችሁ፥ እርስዋንም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወስዳታል፥ አንድ ሰውም በፊቱ ያርዳታል።
ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በሆነው ቀራንዮ የተባለ ቦታ ተገደለ። ሊቀ ካሕናቱ ቀያፋ በሐሰት ፈረደበትና ሌላ ሰው ማለትም ጲላጦስ በቀያፋ ፊት እንዲገድለው አደረገ።
ዘኁልቁ 19፡4 ካህኑም አልዓዛር ከደምዋ በጣቱ ይወስዳል፥ ከደምዋም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል።
ሰባት ጊዜ የሚለው ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል፤ በነዚህም ዘመናት ውስጥ ሚሽነሪዎች ወንጌልን በዓለም ዙርያ ይዘው ሲሄዱ የኢየሱስ ደም በዓለም ሁሉ ላይ ይረጫል።
ዘኁልቁ 19፡5 ጊደሪቱም በፊቱ ትቃጠላለች፤ ቁርበትዋም ሥጋዋም ደምዋም ፈርስዋም ይቃጠላል።
ያቃጥላል። ኢየሱስ መዳናችንን እውን ለማድረግ በሲኦል እሳት ላይ እየተራመደ ሄዶ ሰይጣንን፣ ሞትን፣ ሲኦልን እና መቃብርን ድል ነስቷል።
ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥
በእሳት መቃጠል ያለባቸው ሌሎች ሶስት ነገሮችም አሉ።
ዘኁልቁ 19፡6 ካህኑም የዝግባ እንጨት ሂሶጵም ቀይ ግምጃም ወስዶ ጊደሪቱ በምትቃጠልበት እሳት መካከል ይጥለዋል።
ዝግባ መስቀሉን የሚወክል ቀይ እንጨት ነው። ይህም እንደ እሳት የሚለበልበውን የኢየሱስ መከራ ይገልጻል።
ሂሶጵ ትንሽዬ ተክል ነው። ይህ ተክል የትም ቦታ ሊገኝ ይችላል። ስለዚህ እምነትን ይወክላል። ሁላችንም እምነት አለን፤ ለምሳሌ ምግባችን ወይም ውሃችን ውስጥ መርዝ እንደሌለ እናምናለን። መኪና ስንነዳ ሌሎቹ መኪኖች መስመራቸውን ጠብቀው እንደሚሄዱ እናምናለን። እምነት ሁሌም በሰዎች ውስጥ አለ። መማር ወይም መልመድ የሚያስፈልገን እምነትን ከእግዚአብሔር ወይም ከቃሉ ጋር ማገናኘትን ነው። አይሁዶች ሂሶጵን የተጠቀሙት የፋሲካ በግ ከታረደ በኋላ ደሙን በቤታቸው በር መቃን እና ጉበን ላይ ለመቀባት ነው። ይህም ወደ ሰማይ መግቢያ በር መስቀሉ መሆኑን ያመለክታል።
ዘጸአት 12፡22 ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ
እንደ ሕጻን ልጅ ያልተወሳሰበ እምነት ሲኖረን እምነታችን በመስቀሉ ላይ የፈሰሰውን የኢየሱስ ደም ተቀብሎ ልባችንን ከሐጥያት ያነጻበታል።
ቀይ ቀለም እኛን ከሐጥያታችን የሚያድነን የኢየሱስ ደም ቀለም ነው። ረአብ ኢያሪኮ ውስጥ ከቤቷ መስኮት ላ ቀይ ጨርቅ ሰቀለች። በዚህም እርሷ እና ቤተሰቧ ከሞት ድነዋል፤ ምክንያቱም የኢያሪኮ ግምብ ሲወድቅ የእርሷ ቤት ብቻ ነው ያልፈረሰው።
ኢያሱ 2፡18 እነሆ፥ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው፤ አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብስቢ።
የእግዚአብሔር ቃል ከሐጥያት የሚያነጻንና ከሐጥያት ለይቶ የሚያኖረን ውሃ ነው።
ዘኁልቁ 19፡9 ንጹሕም ሰው የጊደሪቱን አመድ ያከማቻል፤ ከሰፈሩም ውጭ በንጹሕ ስፍራ ያኖረዋል፤ ርኵሰትም ለሚያነጻ ውኃ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ይጠበቃል፤ ከኃጢአት ለማንጻት የሚሆን ነው።
ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ብቻ ነው ከሐጥያት ሊያነጻንና ከሐጥያት ሊለየን የሚችለው። አመድ አይበሰብስም፤ ደግሞም በጊዜ ሂደት ውስጥ አይለወጥም። የእግዚአብሔር ቃል ጥንት በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንደነበረው ዛሬም ያድነናል። ቃሉ አይለወጥም፤ አይበሰብስም፤ ኃይሉም አይደክምም።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
ቃሉ ዘላለማዊ ነው፤ እኛንም ከሐጥያት እና ከአለማመን ይለየናል።
አብርሃምም ሶስት እንስሳት ወሰደና ሰነጠቃቸው፤ እነዚህም ክርስቶስ ሊያደርግ ያሰበውን ነገር ይወክላሉ። የተሰነጠቁትንም ጎን ለጎን አስቀመጣቸው።
ቀራንዮ ላይ እግዚአብሔር ክርስቶስን ለሁለት ሰነጠቀው።
ከስጋው ውስጥ መንፈስ ቅዱስን ቀዶ አወጣውና መንፈሱን ወደ ሲኦል ልኮ ስጋውን ወደ መቃብር አወረደው።
ቀጥሎም ስጋውን ከመቃብር አውጥቶ አስነሳውና በአካል ወደ ሰማይ ወስዶ ዙፋን ላይ አስቀመጠው። ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ይኖር ዘንድ የክርስቶስን መንፈስ ወደ ምድር መልሶ ላከው።
ታላቁ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ልክ ክርስቶስ በሰማይ እንደሚኖረው እንድትኖር እና እንድታምን ያደርጋታል።
እግዚአብሔር ለሁለት “ሲሰነጠቅ”።
እግዚአብሔር ለመስዋእትነት በተዘጋጀው በክርስቶስ አካል ውስጥ ሲኖርና በሰማይ በምሕረት ዙፋን ሲቀመጥ።
ይኸው እራሱ እግዚአብሔር በምድር ላይ በሰዎች ልብ ውስጥ ደግሞ ይኖራል።
ቃልኪዳኑ 3 ዓመት በሞላቸው በ3 እንስሳት አማካኝነት ነው የተፈጸመው
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም … ቃል ኪዳን አደረገ
ዘፍጥረት 15፡9 እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው።
ለምንድነው ለቃልኪዳኑ ሶስት እንስሳት የተሰነጠቁት?
ይህ አሰራር ለሶስት ቁጥር ትኩረት እንድንሰጥ ያደርገናል።
እግዚአብሔር የምድር ሕዝቦችን በሶስት ዘር ከፍሎ ነው የሚያያቸው (ከፊል አይሁድ፣ ከፊል አሕዛብ)፣ እና አሕዛብ።
ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳንን ያስገኘው በሶስተኛው ቀን ከሙታን በመነሳት ሞትን ሲያሸንፍ ነው።
እውነት ከምድር ላይ ፈጽማ ልትጠፋ በቀረበችበት በጨለማው ዘመን ውስጥ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን በቀሩት ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በመንፈስ ከሙታን እየተነሳች ናት።
ይህም ትንሳኤ የተጀመረው ሉተር በአምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ስለ ጽድቅ በማስተማሩ እና መዳን በስራ ሳይሆን በእምነት መሆኑን ስለገለጠ ነው።
ዌስሊ ያስተማረው ቅድስና እና የወንጌል ስብከት በስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ታላቅ የወንጌል ስርጭት እንዲጀመር አደረገ።
የጴንጤቆስጤ ኃይል እና የተሰወሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የተገለጡት በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን አማኞች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ ጥንታዊ አማኞች እና ሐዋርያት ወደነበሩበት እውነትና እምነት ይመለሱ ዘንድ ነው።
በመስቀል ላይ ከኢየሱስ ስጋ ውስጥ ሶስት ሕይወት ሰጭ ንጥረ ነገሮች ናቸው የፈሰሱት። እነርሱም ውሃ፣ ደም፣ እና መንፈስ ናቸው።
የቃሉ ውሃ፣ የኢየሱስ ደም፣ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና መገለጥ እውነተኛይቱን ሙሽራ ከአለማመን እና ከሐጥያት ያስነሷታል።
እግዚአብሔር አብ ነው (ከአይሁዶች በላይ)፤ ወልድ ነው (ከአይሁዶች ጋር አማኑኤል)፤ እንዲሁም (ዳግመኛ በተወለዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ሲኖር) መንፈስ ቅዱስ ነው።
ዘፍጥረት 15፡10 እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልከፈለም።
ወፎቹ ለመዳን እና ለፈውስ የሚያስፈልገውን እምነት ይወክላሉ፤ መዳን እና ፈውስ ሊሰነጠቁ አይችሉም። እግዚአብሔር ለማዳን ከሰዎች ጋር ቃልኪዳን ከገባ በዚሁ ቃልኪዳን ውስጥ ፈውስንም ያዘጋጃል።
ዘፍጥረት 15፡11 አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።
ቀኑ ሲጨልም አካባቢ ወፎችና አሞራዎች ስጋ ሊበሉ መጡ።
ነብዩ አብርሃም አሞራዎቹን አባረራቸው። የአብርሃም ቃልኪዳን ለአሞራዎችና ለጥምባንሳዎች አይደለም። ይህም የመጨረሻውን ዘመን ያመለክታል። የመጨረሻው ዘመን የምሽት ዘመን ነው።
ማቴዎስ 24፡27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤
የወንጌሉ ብርሃን ከፓለስታይን ምድር ጀምሮ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሲያበቃ ከቆየ በኋላ በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፋ።
ጠፍቶ የነበረው የወንጌል ብርሃን ማርቲን ሉተር በ1500ዎቹ ጀርመኒ ውስጥ የጽድቅን ትምሕርት ማስተማር ሲጀምር ተመልሶ በራ። ማርቲን ሉተር በእምነት መዳንን አስተማረ።
ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና እና ስለ ወንጌል አገልግሎት ባስተማረ ጊዜ ብርሃን ወደ እንግሊዝ ገባ፤ ይህን የወንጌል ስርጭት ዘመንን አስጀመረ።
ፐንቲኮስታል ስጦታዎች በ1904ቱ የዌልሽ መነቃቃት ላይ እንግሊዝ ውስጥ መገለጥ ጀመሩ፤ ከዚያም በ1906 ወደ ሎሳንጀለስ አሜሪካ ውስጥ አዙዛ እስትሪት ወደሚባል አካባቢ ተዛመቱ። በ1963 አሜሪካ ውስጥ ዊልያም ብራንሐም የተሰወሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገለጠ፤ ይህም የሆነው የመጨረሻው ዘመን ንስሮች ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እንዲመለሱ ለማስቻል ነው።
ማቴዎስ 24፡28 በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።
በትኩሱ የታረደው የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ንስሮችን ብቻ ነው የሚስባቸው፤ ጥምብአንሳዎችን ያባርራቸዋል።
ለዘመን መጨረሻ ከአሕዛብ መካከል የተመረጠው የዚህ ነብይ ትምሕርቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ዲኖሚኖሽናዊ እምነቶችን ሁሉ ያባርሯቸዋል። ልክ እንደ ጥንቷ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለማመን ፈቃደኛ ለሆኑት ነው የሚያስተምራቸው።
መንፈሳዊ ንስር ብቻ ነው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት የሚያበቃ እይታ ያለው።
መንፈሳዊ ወፎች ወይም አሞራዎች ግልጽ ያልሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አላስፈላጊ ዝርዝሮች ናቸው፣ ወይም በስሕተት የተተረጎሙ ናቸው፣ ወይም እርስ በርሳቸው ይጋጫሉ፣ ወይም ለመረዳት ከባዶች ናቸው፣ ወይም ደግሞ እነዚያን ጥቅሶች መለወጥ ወይም እንዳላዩ ማለፍ ሲፈልጉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ያልፋሉ።
ሙሽራይቱ “ማወቅ አለብን” ትላለች፤ ስለዚህ የሙሽራይቱ ቃላት ሚስጥር እንዲገለጥላቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በጥንቃቄ ይመረምራሉ።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት “ብናውቅስ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመረዳት ከባድ የሆኑ ጥቅሶችን ሲያገኙ በስንፍና እና በቸልተኝነት ያልፋሉ።
ዘፍጥረት 3፡1 “በውኑ እግዚአብሔር … አዝዞአልን?”
እባቡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ሲፈልግ ንግግሩን እንዲህ ብሎ ነው የጀመረው።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች በዚህ ንግግር ይስማማሉ።
ዕንባቆም 2፡3 ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፤ እርሱ አይዘገይም።
በስተመጨረሻ ግን መረዳታችን ሲያድግ የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥር ተፈጽሞ ይጠናቀቃል።
ቃልኪዳኑ በተደረገ ጊዜ አብርሃም ከባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበር
ይህም በራሳችን ስራ መዳን እንደማንችል ያመለክታል።
እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ቃልኪዳን የጀመረው አብርሃምን እንቅልፍ በማስተኛት ነው።
አብርሃም አንዳችም የሚያደርገው አስተዋጽኦ የለም። ቃልኪዳኑ በአብርሃም ስራ ላይ የተመሰረተ አይደለም።
ዘፍጥረት 15፡12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤
ፀሃይ ገባች የሚለው ጊዜ እየመሸ እንደነበረ ያመለክታል፤ ይህም የሰባተኛው ወይም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ ማለት ነው።
አብርሃም ከባድ እንቅልፍ አንቀላፋ።
ይህ ሁለት ትርጉሞች አሉት። የመጀመሪያው ትርጉም እግዚአብሔር በሚያደርገው ቃልኪዳን ውስጥ አብርሃም ምንም ሚና እንደማይጫወት ያመለክታል። እግዚአብሔር የሰው እርዳታ አያስፈልገውም።
አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳን ለማድረግ መስራት የሚችለው አንዳችም መልካም ሥራ የለም።
እንስሳቱን ለመስዋእት እንዲሆኑ ነው ያረዳቸው ነገር ግን የተሰዉት እንስሳት በሙሉ ክርስቶስ ሲመጣ ምን እንደሚያደርግ የሚያመለክቱ ነበሩ።
አብርሃም የተኛው ከባድ እንቅልፍ የሞተ ምሳሌ ነው፤ እርሱም የሐጥያተኛው እጣ ፈንታ ነው።
ድንጋጤውና ታላቁ ጨለማ የሐጥያት እና የአለማመንን ጨለማ ያመለክታሉ። ስለዚህ ወደ ጥልቅ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ መውደቅ ማለት ነው።
ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሲመላለሱ ብረሃን አያገኙም።
መዝሙር 119፡105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
ከዚያም እግዚአብሔር ብቻውን ቃልኪኑን አደረገ።
ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።
ጢስ። ጢስ ባለበት እሳት አለ። ይህም እሳት እጅግ የሚለበልብ እሳት ነው። የሲኦል እሳት ነው። ይህም የሐጥያተኛውን የመጨረሻ ጥፋት ያመለክታል።
አሁን ግን የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን ዋነኛ ሃሳብ እንመለከታለን።
በተሰነጠቁት እንስሳት መካከል ብርሃን አለፈ።
ከሐጥያት እና ከአለማመን ጨለማ ሊቤዠን የሚችለው ይህ ብርሃን ብቻ ነው።
ዮሐንስ 8፡12 ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤
ኢየሱስ የዓለም ብርሃን ነው።
ይህ ብርሃን የክርስቶስን መንፈስ ነው የሚወክለው። ኢየሱስ በሁለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል ሞተ፤ እነርሱም አዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን ናቸው።
መንፈሱም ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል ወረደ። እርሱም ሲኦል ውስጥ ባለው የእቶን እሳት ላይ እየተራመደ ሄዶ ሐጥያታችንን በሰይጣን ላይ አራገፈ።
ክርስቶስ ነጩን የዳኛ ዊግ ለብሶ ይታያል። ለሐጥያት ያለው ጥላቻ ዓይኖቹ ውስጥ እንደ እሳት እየነደደ ይታያል። እርሱ የለበው የዳኛው ዊግ እንደ በረዶ ነጭ ነው። ዳኛውም ፍጹም ሐጥያት የሌለብን እንድንሆን ይጠብቃል።
ራዕይ 1፡14 ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤
ስለዚህ ራሳችንን ማዳን አንችልም። መልካም የሆኑ ሃሳቦቻችን እንኳ በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ አይደሉም።
ኢሳይያስ 64፡6 ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤
እግሮቹ ደግሞ በእቶን እሳት ላይ እየተራመደ ባለፈ የጋለ ናስ ነው የተመሰለው።
ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥
ክርስቶስ ከሐጥያት ሊቤዠን የከፈለውን ዋጋ ታላቅነት ሙሉ በሙሉ መረዳት አንችልም።
ይህን ዓይነቱን ዋጋ መክፈል የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር በሐጥያት ላይ የተቆጣበትን የቁጣውን ወይን መርገጥ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው።
ኢሳይያስ 63፡3 መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤
ኢየሱስ ሲኦል ውስጥ ገብቶ ሰይጣንን ካሸነፈው በኋላ የሞትን እና የሲኦልን ቁልፍ ከሰይጣን እጅ ነጠቀ።
1ኛ ቆሮንቶስ 2፡8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤
ሰይጣን የሰራው ትልቅ ስሕተት ኢየሱስን መግደሉ ነው።
የሞተ ሰው መንፈስ የሙት መንፈስ ነው።
ዘፍጥረት 25፡8 አብርሃምም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካም ሽምግልናም ሞተ፤
የሞቱ ሰዎች መንፈስ ብቻ ነው ወደ ሲኦል መውረድ የሚችለው። ክርስቶስ በሕይወት ሳለ ቅዱስ የሆነው መንፈሱ ወደ ሲኦል ሊወርድ አይችልም። ነገር ግን ክርስቶስ በሞተ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ከአካሉ ወጥቶ ሄደና አካሉ ሞቶ በመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ ሳለ መንፈሱ የሙት መንፈስ ሆኖ ወደ ሲኦል መውረድ ቻለ። በተጨማሪ ኢሱስ ሐጥያታችንን ተሸክሞ ነበር፤ ስለዚህ ቅዱስ የሆነው መንፈሱ ሐጥያታችንን ስለተሸከመ ወደ ሲኦል መግባት ይችላል።
ከዚያም ኢየሱስ የሐጥያታችንን ዋጋ በመስቀል ላይ ስለከፈለ መንፈሱ ወደ ሲኦል ሲገባ ሐጥያታችንን ወስዶ ሰይጣን ላይ አራገፈው። ሰይጣን ዋጋውን አገኘና የሞት እና የሲኦልን ቁልፍ ከእጁ ተነጠቀ።
ራዕይ 1፡18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
ኢየሱስ ሞተ፣ ሰይጣንን፣ ሞትን፣ ሲኦልን እና መቃበርን ድል ነስቶ ለዘላለም ሕይወት ከሞት ተነሳ።
ቀራንዮ ሙሉ በሙሉ በይስሐቅ ሕይወት ውስጥ ታይቷል
ዘፍጥረት 22፡1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ፡፡ አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ አለ።
2 የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ።
አብርሃም እንደ አባት ሆኖ ይስሐቅን እንደ ልጅ ሊሰዋ ታዘዘ።
አንድ ቀን ቤተመቅደሱ ወደሚሰራበት ወደ ሞሪያ ተራራ እየወጡ ሳለ አብርሃም አብረውት የነበሩትን ሰዎች የሆነ ቦታ እንዲጠብቁት ነገራቸው።
ዘፍጥረት 22፡5 አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው፦ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን።
አብርሃም ይስሐቅን ሊሰዋው እየሄደ መሆኑን አውቆታል። ሆኖም ግን ይስሐቅ ከእርሱ ጋር አብሮ እንደሚመለስ ነው የተናገረው። ስለዚህ አብርሃም እግዚአብሔር የተስፋ ልጁን ይስሐቅን ከሞት እንደሚያስነሳለት ሙሉ እምነት ነበረው።
ዘፍጥረት 22፡6 አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
ይስሐቅ የአብርሃም ፍጥረታዊ ልጅ እንደመሆኑ እንጨቱን ተሸከመ።
ኢየሱስ ደግሞ የአብርሃም መንፈሳዊ ልጅ እንደመሆኑ መስቀሉን ተሸከመ።
ይስሐቅ ግን ስለ አንድም ሰው ሐጥያት መሞት አይችልም። ይስሐቅ ቢሞትም እንኳ የእርሱ ሞት ምንም ዋጋ አይኖረውም። ስለዚህ እግዚአብሔር የይስሐቅን ሞት አልፈለገም።
ስለዚህ የይስሐቅ መወለድ የ2,300 ዓመታቱ ትንቢት የጀመረበት ቀን ነው።
የይስሐቅ መወለድ ለሣራ ሳቅ እና ደስታ አምጥቶላታል።
ከአብርሐም እና ከይስሐቅ ጋር የተደረገው ፍጥረታዊው ቃልኪዳን ለአይሁዶች የተስፋይቱን ምድር ሰጣቸው።
ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞቱ ፍጥረታዊ የነበረውን ቃልኪዳን ጠለቅ ባለ መንፈሳዊ ደረጃ እንዲጸና በማድረጉ መንፈሳዊ በሆነ መንገድ በተስፋ የሆነው የአብርሃም ዘር ኢየሱስ መሆኑን አረጋግጧል።
ኢየሱስም ግዴታ የሆኑትን ሞት እና ትንሳኤ ፈጸማቸው ምክንያቱም ከእርሱ ውጭ እነዚህን ሊያደርግ የሚችል የለም። የኢየሱስ ሞት ለሚሊዮኖች ሳቅ እና ደስታ አመጣላቸው።
ስለዚህ ትንቢቱ ተፈጽሞ የተጠናቀቀው በኢየሱስ ሞት ነው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
እግዚአብሔር በመጀመሪያ ከአብርሃም ጋር ትንሽዬ ፍጥረታዊ ምድር ለመስጠት ፍጥረታዊ ቃልኪዳን አደረገ። የእስራኤል ምድር ከጠቅላላው የምድር ስፋት ከአንድ መቶኛ በታች ናት።
እግዚአብሔርም ይህንን ቃልኪዳን ኋላ በክርስቶስ ሊያጸናው አሰበ። በክርስቶስ የሚጸናው ቃልኪዳን ከፍ ይልና ምድርን በኢየሱስ ደም ያነጻል፤ ደግሞም በዓለም ዙርያ ሁሉ የሚኖሩ አሕዛብንም ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳን አድርጎ ያካትታቸዋል። ነገር ግን የባቢሎን ዲኖሚኔሽናዊ እምነቶች እና የግብጽ ዓለማዊነት ወደ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባት የለባቸውም።
ዘፍጥረት 15፡13 አብራምንም አለው፦ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ፤ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።
ቃልኪዳኑ ከብዙ መከራና መገፋት ጋር ነው የሚመጣው
ቃልኪዳኑ ግን ከዋጋ ጋር ነው የመጣው። ብዙ መከራ ይኖራል። ብዙ ስሕተቶችን አሸንፎ ማለፍ ይጠይቃል።
ብዙ መገፋት እና ብዙ ስደት ይሆናል።
ኋላ ግን ቤተክርስቲያን ዲኖሚኔሽኖች ያመጡዋቸውን ሰው ሰራሽ እምነቶች እና ልማደች ተቀበለች። ከዚህም የተነሳ ዛሬ 45,000 ዓይነት ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ እምነቶች አሉን። በእንግሊዝኛ ብቻ ከ100 በላይ የተለያዩ ትርጉሞች አሉ። በዛሬው ዓለም ውስጥ ባሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ እውነትን ለማግኘት መሞከር በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ብዙ ልዩ ልዩ አመለካከቶችና መረዳቶች አሉዋቸው።
ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
ግለሰቦች መጽሐፍ ቅዱስን እየመረመሩ የእግዚአብሔርን እውነት መፈለግ አለባቸው፤ ምክንየቱም እውነት በቤተክርስቲያኖች ውስጥ አትገኝም።
የአንድን ጥቅስ ትርጉም ማግኘት የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ጥቅሱን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከብዙ ሌሎች ጥቅሶች ጋር በማገናኘት ነው።
የኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ የብሉይ ኪዳንን ቃልኪዳን አጸና፤ እንዲሁም የአዲስ ኪዳንን ቃልኪዳን መጀመር አበሰረ።
ኤርምያስ 31፡31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤
32 ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
በኖህ ዘመን የመጣው የጥፋት ውሃ ከአዳም ውድቀት በኋላ የተከሰተ ታላቅ ክስተት ነው።
ነገር ግን ከጥፋት ውሃ በፊት ፍጹም የነበረው ኖህ የወይን ጠጅ ጠጥቶ በመስከር ከጥፋት ውሃ በኋላ የመጀመሪያው ሐጥያተኛ ሆነ።
ዘፍጥረት 6፡9 የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ።
ይህ የሆነው ከጥፋት ውሃ በፊት ነው።
ዘፍጥረት 9፡20 ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ።
21 ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ።
ይህ የሆነው ከጥፋት ውሃ በኋላ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎችን ለመቤዠት የተሻለ እቅድ ማዘጋጀት ጀመረ።
እግዚአብሔር አብርሃምን መረጠውና ከእርሱ ጋር የብሉይ ኪዳን ቃልኪን አደረገ።
አዲስ ኪዳን የሚጀምረው አብርሃምን ከኢየሱስ ጋር በማገናኘት ነው።
ማቴዎስ 1፡1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
ስለዚህ አብርሃም ከኢየሱስ ጋር በዘር ለመገናኘት ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።
ለአብርሃም በተስፋ ቃል ከተሰጠው ከይስሐቅ መወለድ አንስቶ ለአብርሃም በተስፋ እስተሰጠው መንፈሳዊ ልጅ እስከከ ኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ ድረስ ልዩ የሆነ ዘመን እንዲኖር ተደርጓል።
(እግዚአብሔር ለዚህ ነው የኢየሱስን ልደት እንድናከብር ያልጠየቀን።)
ይህም ዘመን ዳንኤል በትንቢት 2,300 ዓመታት ብሎ የተናገረው ነው።
ኢየሱስ የትንሳኤ አስተምሕሮ እውነት መሆኑን ለማሳመን ሲከራከር ስለ አብርሃም ተናግሮ ነው ያስረዳው።
ማቴዎስ 22፡31-32 ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን፦ እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።
አብርሃም ስለ ትንሳኤ ከልቡ አጥብቆ ነበር የሚያምነው። ለዚህ ነው ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት ያላመነታው። እግዚአብሔር ለአብርሃም ዘሩ የተስፋይቱን ምድር እንደሚወርስ ተስፋ ሰጥቶት ስለነበረ ይስሐቅ ተሰውቶ ቢሞት እንኳ ከሙታን እንደሚያስነሳው አብርሃም አምኗል።
እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ ለራሱ የጎልማሳ ሰው አካል ፈጥሮ የተገለጠበት ጊዜም አብርሃምን ፊት ለፊት ለማግኘት ነው።
ዕብራውያን 7፡1 የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤
2 ለእርሱም ደግሞ አብርሃም ከሁሉ አስራትን አካፈለው። የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው።
3 አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።
እግዚአብሔር ከምድር አፈር ለራሱ ጊዜያዊ አካል አዘጋጀና እራሱን መልከጼዴቅ ብሎ ጠራ። ከዚያም አብርሃምን ሊገናኘው መጣ። መልከጼዴቅ ከአብርሃም ጋር የነበረውን ጉዳይ ከጨረሰ በኋላ አካሉ እንደገና ወደ አፈር ተመለሰ።
መልከጼዴቅ እንደ ሕጻን ልጅ ሆኖ አልተወለደም፤ ደግሞም ለሐጥያታችን ደሙን አፍስሶም አልሞተም። በተጨማሪ በምድር ላይ ስለሚያደርገው አገልግሎትም የተነገሩ ትንቢቶች አልነበሩም። ከዚያ ውጭ መልከጼዴቅ የእግዚአብሔር አካላዊ መገለጥ ስለነበረ እርሱ ልጅ እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንደ ኢየሱስ ነበረ።
እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከፍጥረታዊ ዘሩ ከአይሁድ ሕዝብ ጋር ቃልኪዳን አደረገ።
እንደ መልከጼዴቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንዴ ካሕንም ንጉስም መሆን የቻለው እግዚአብሔር ነው።
እነዚህን አገልግሎቶች በአንድ ላይ አጣምሮ እንዲይዝ ለማንም ሰው ተፈቅዶለት አያውቅም፤ ምክንያቱም ለአንድ ሰው በጣም ይበዛበታል። ስልጣን ሲበዛ ያባልጋል።
ከዚያ በኋላ በኢየሱስ እግዚአብሔር ሕጻን ልጅ ሆኖ ተወለደና ጎልማሳ ሰው እስኪሆን ድረስ አደገ። ከመልከጼዴቅ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ካሕንም ንጉስም መሆን የቻለው ሰው ኢየሱስ ነው።
ስለዚህ የአብርሃም መንፈሳዊ ዘር በሆነው በኢየሱስ ከመጀመሪያው የተሻለ ቃልኪዳን ጸና።
ከሐጥያት መንጻት ወይም ስርየት ሊደረግ የሚችለው ደም ሲፈስስ ብቻ ነው።
ዕብራውያን 9፡22 እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።
ሰይጣን በሰማይ መልአክ በነበረ ጊዜ ስለሆነ ሐጥያት የሰራው በሰማይ ያለው መቅደስም መንጻት ያስፈልገው ነበር።
ዕብራውያን 9፡23 እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መስዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ።
ድንኳኑ እና ቤተመቅደሱ በሰማይ ላለው መቅደስ ጥላዎች ናቸው። በምድር ያሉት ድንኳንና መቅደስ በእንስሳት ደም ነበር የሚነጹት። ነገር ግን በሰማይ ያለችው እውነተኛ መቅደስ በኢየሱስ ደም ነው የነጻችው።
ዕብራውያን 9፡24 ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።
ዕብራውያን 9፡11 ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥
ይህ የእግዚአብሔር ሰማያዊ መቅደስ ነው። ይህ መቅደስም በክርስቶስ ደም ነጽቷል።
ዕብራውያን 9፡12 የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።
የኢየሱስ ደም ወደ ሰማይ ሄዷል፤ ይህም ሰይጣን ትቶ ያለፈውን የሐጥያት ዱካ በሙሉ ለማጥፋት ነው።
ሐጥያታችን ይቅር ሊባል የሚችልበት ብቸኛው መንገድ በምሕረት ዙፋኑ ላይ ያለው የኢየሱስ ደም ነው።
54-0515 ጥያቄዎችና መልሶች
ከእርገት በኋላ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ በኋላ፣ ከመስቀሉ እንዲሁም መቅደሱ ከነጻ በኋላ፤
64-0629 በፊታችን የተገለጠው ታላቁ አምላክ
መጋረጃው በቀራንዮ በተቀደደ ጊዜ የምሕረት ዙፋኑ ቁልጭ ብሎ ታየ። ነገር ግን ምንድነው የተከናወነው? በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ደም እያንጠባጠበ ነበር። መቅደሱን በየዓመቱ ለማንጻት ደም እንደሚወስዱ ሁሉ የምሕረት ዙፋኑ ላይ ደም በሚረጩበት ሰዓት እግዚአብሔር በታላቅ ነጎድጓዳዊ ኃይሉ ያንን ጥንታዊ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ድረስ ቀደደው፤ የዚያን ጊዜ የምሕረት ዙፋን ግልጥ ሆኖ ታየ።
ትክክለኛው እውነተኛው የእግዚአብሔር በግ፣ እውነተኛው የምሕረት ዙፋን በቀራንዩ በግልጽ ተሰቅሎ ታይቷል፤ እግዚአብሔር እራሱ የሐጥያትን ዋጋ ከፈለ፤ ከእኛ አንዱ ሆነ፤ እራሱንም የሰው ልጅ አድርጎ ገለጠ፤ ይህን ያደረገው ከእኛ ጋር ለመተዋወቅ እንዲሁም እኛ ከእርሱ ጋር እንድንተዋወቅ ነው። በዚያ በታላቁ የስርየት ቀን የምሕረት ዙፋኑ በእስራኤል ሁሉ ፊት ግልጥ ሆኖ ታይቷል።
61-0618 ራዕይ ምዕራፍ አምስት. 2
… መቅደሱ መንጻት ከጀመረበት ከመጀመሪያው ቀን ወይም ክርስቶስ ወደ ቀራንዮ ከሄደበት ቀን ጀምሮ ወደ ሰማይ እስካረገበት ቀን ድረስ 40 ቀናት ነበሩ።
ዳንኤል 8፡14 እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።
የአብርሃም እምነት የተመሰረተው በትንሳኤ ነው።
አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሴፍ ሁላቸውም የተስፋይቱ ምድር ውስጥ ነው መቀበር ያለብን ብለው ጽኑ አቋም ያዙ። በዚያች ምድር ውስጥ ትንሳኤ እንዳለ ገብቷቸዋል። ልክ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በሙሉ ከሞት ተነስተዋል።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
ኢየሱስ እራሱ በትንሳኤ ከሞት ከተነሳ በኋላ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንንም ከሞት አስነሳቸው።
የተስፋይቱ ምድር ውስጥ ትንሳኤ እንደሚመጣ በመረዳት አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሴፍ ሁላቸውም እዚያ መቀበር ፈለጉ።
ያዕቆብ ሲሞት ወስደውት አብርሃም እና ይስሐቅ በተቀበሩበት ቦታ የተስፋይቱ ምድር ውስጥ እንዲቀብሩት ልጆቹን አዘዛቸው።
ዘፍጥረት 49፡29 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ፤ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤
30 እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።
31 አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ፤ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ፤ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት፤
ዮሴፍ ፈርኦንን እንዲህ ብሎ አናገረ።
ዘፍጥረት 50፡5 አባቴ አምሎኛል እንዲህ ሲል፦ እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።
ዘፍጥረት 50፡13 ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፤ እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።
ዘፍጥረት 50፡24 ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ፦ እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል።
25 ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፦ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው።
ዘጸአት 13፡19 ዮሴፍም፦ እግዚአብሔር ሳይጎበኛችሁ አይቀርም፥ አጥንቶቼንም ከዚህ ከእናንተ ጋር ታወጣላችሁ ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና ሙሴ የእርሱን አጥንቶች ከእርሱ ጋር ወሰደ።
ኢያሱ 24፡32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በግ በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት፤ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።
ጳውሎስ በመልእክቱ “ዘር” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር እንደተጻፈ አጉልቶ በማሳየት ቃልኪዳኑ የሚያመለክተው ወደ ኢየሱስ ነው ብሎ ያብራራል።
ገላትያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።
17 ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።
እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃልኪዳን አደረገና ኢየሱስ ሐጥያትን ድል በነሳ ጊዜ ቃልኪዳኑን በክርስቶስ አጸና፤ በደሙ ሰማያዊውን መቅደስ አነጻ፤ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንንም ከሙታን አስነሳ።
እግዚአብሔር ከአብርሃም እና በአብርሃም ወገብ ውስጥ ከነበሩ ሶስት ትውልዶች ጋር ቃልኪዳን አደረገ። እነርሱም ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እና 12ቱ የያዕቆብ ልጆች ናቸው። ይሁዳ የነገስታት ዘር ሃረግ ሲሆን ሌዊ ደግሞ የካሕናት የዘር ሃረግ ነው። የትኛውም ሰው ቢሆን አንድ ሰው ሆኖ ንጉስም ካሕንም መሆን አይችልም። ስልጣን ሲበዛ ያባልጋል።
ዕብራውያን 7፡9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤
ሌዊ የአብርሃም የልጅ ልጅ ልጅ ነው።
አብርሃም አንድ ሰው ሆኖ ቀጣዮቹን ሶስት ትውልዶች በወገቡ ይዞ ነበር።
በአንድ ጊዜ ንጉስም ካሕንም መሆን የሚችለው ሰው ኢየሱስ ብቻ ነው። በመልከጼዴቅ ሹመት አዲስ የክሕነት ቃልኪዳን በመቀበሉ የአሮንን ክሕነት አስረጅቶታል። ደግሞም ከይሁዳ ነገር ንጉስ ሆኖ ተወልዷል።
መልከጼድቅ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ከምድር አፈር ለራሱ የትልቅ ሰው አካል ፈጠረ። ያም አካል ኋላ እግዚአብሔር አካል በማይፈልግበት ሰዓት ወደ ምድር አፈር ይመለሳል።
እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ የአይሁድ ሕዝብ እንደሚወለዱ ከአብርሃም ጋር የተስፋ ቃልኪዳን አድርጓል።
ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው። እርሱም ለሐጥያታችን ዋጋ ለመክፈል እራሱን መስዋእት አደረገ።
አብርሃም እና ልጆቹ በኢየሱስ እና በመልከጼዴቅ መካከል አገናኝ ሆኑ። ይህም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ የንጉስንም የካሕንንም አገልግሎት አጣምሮ የያዘበት ብቸኛው አጋጣሚ ነው።
ይህንን ታዋቂ ቀን የሚጠቅሰውን ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነ ጥቅስ እንደገና እንመልከት።
ዳንኤል 8፡14 እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።
ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ሞት ድረስ 2,300 ዓመታት እንዳለፉ ማሳየት እንችላለንን?
የአይሁድ ሕዝብ በተስፋ የተሰጠ የአብርሃም መንፈሳዊ ዘር የሆነውን ኢየሱስ ን በቀራንዮ መስቀል ላይ ሰቀሉት። ከዚያ ወዲያ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ሕዝብ መስራቱን አቆመ። ከዚያ በኋላ አሕዛብ ሲድኑ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር በግለሰብ ደረጃ መስራት ጀመረ።
አብርሃም የወለደው የመጀመሪያው የተስፋ ቃል ልጅ ይስሐቅ ነው፤ እርሱንም የወለደው ዕድሜው 100 ዓመት ሲሞላ ነው።
እግዚአብሔር አብርሃምን ሲጠራው አብርሃም 75 ዓመቱ ነበረ፤ አባቱ ታራ ደግሞ በዚያ ጊዜ ካራን ውስጥ ሞተ።
ዘፍጥረት 11፡32 የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።
ዘፍጥረት 12፡4 አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ።
ከኢየሱስ ሞት ጀምረን ወደ ኋላ 2,300 ዓመታት እንቆጥራለን
ስሌታችን ትክክል መሆኑን ለማጣራት ከታሪክ ምሑራን የተገኘውን ግምታዊ ቀን እንመልከት።
የተለያዩ የታሪክ ምሑራን ሰለሞን ወደ ዙፋን የወጣበትን ዓመት በ960 ዓመተ ዓለም ወይም በ970 ወይም 986 ወይም 992 ዓመተ ዓለም ነው ይላሉ። ቁርጥ ያለ ዓመት መወሰን ከባድ መሆኑን ያምናሉ። ይህም ካስቀመጡዋቸው በ30 ዓመታት ውስጥ ከተበታተኑ ቀኖች ግልጽ ሆኖ ይታያል።
እኛ ደግሞ አሁን ይስሐቅ የተወለደበትን ዓመት ካገኘን በኋላ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖችን ደምረንበት ሰለሞን መንገስ የጀመረበትን ዓመት ለማግኘት ሙከራ እናደርጋለን።
ይህ ከተሳካልን ይስሐቅ የተወለደበት ዓመት ብለን ያሰላነው ስሌት ትክክል ነው ማለት ነው።
ዓመታት የሚቆጠሩት ብዙውን ጊዜ አንድ ንጉስ መንገስ በጀመረበት ጊዜ ላይ ተመስርተው ነበር።
አውግስጦስ ከሮማውያን ገዥዎች ሁሉ ዝነኛ ነበረ፤ እርሱም በ12 ዓ.ም ሞተ። ይህ ቀን ትክክለኛነቱ በታሪክ የተረጋገጠ ቀን ነው።
አውግስጦስ በማደጎ ያሳደገው ጢባርዮስ የተባለ ልጁ የሮማ መንግስት ምክር ቤት እውቅና በሰጠው ጊዜ በ14 ዓ.ም ነገሰ።
ሉቃስ 3፡1 ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥
2 … የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ መጣ።
14 + 15 = 29። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ መስበክ የጀመረበት ዓመት 29 ዓ.ም ነው።
የተወሰኑ ወራት ካለፉ በኋላ ኢየሱስ ሊጠመቅ ወደ ዮሐንስ መጣ። ኢየሱስ ሊጠመቅ በመጣበት ጊዜ የ29 ዓ.ም ወራት ብዙዎቹ አልፈዋል።
ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር
ቀኖቹ በትክክል ይጋጠማሉ። ልክ 30 ዓ.ም ሲመጣ ኢየሱስ 30 ዓመት ሞላው።
ስለዚህ ኢየሱስ ተወለደው በዜሮ ዓ.ም መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል። የእኛ ካላንደር የሚጀምረውም ኢየሱስ በተወለደበት ዓመት ነው።
ኢየሱስ የመጣው እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ ጋር ያደረገውን ቃልኪዳን ለማጽናት ነው።
ኢየሱስ ለ7 ዓመታት ሊያገለግል ነበር የመጣው። ነገር ግን ከሶስት ዓመት ከግማሽ በኋላ አይሁደች አንቀበልህም ብለው ገደሉት።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤
አንድ ሳምንት ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ አቆጣጠር ሰባት ዓመት ሊሆን ይችላል።
የአይሁድ ሰላዮች የተስፋይቱን ምድር ለ40 ቀናት ሲሰልሉ ቆይተው ተስፋ ቆረጡ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሊቀጣቸው በምድረበዳ 40 ዓመታት እንዲዞሩ አደረገ።
ዘኁልቁ 14፡34 ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ ስለ አንድ ቀንም አንድ ዓመት፥ ኃጢአታችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ ቍጣዬንም ታውቃላችሁ።
የኢየሱስ አገልግሎት የጀመረው በ30 ዓ.ም ከሆነ እና ለ3½ ዓመታት ከዘለቀ የሞተው በ33 ዓ.ም ነው ማለት ነው።
2,300 / 70 = 33
ስለዚህ እኛ የምንጠቀምበት የአሕዛብ ካላንደር ከመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት በ33 ዓመት ወደ ኋላ ቀርቷል።
2,300 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት ማለት 2,300 – 33 = 2,267 የአሕዛብ ዓመታት ማለት ነው።
ከቀራንዮ መስቀል ወደ ኋላ ኢየሱስ ወደተወለደበት ዓመት ለመድረስ 33 ዓመታት ቀንሱ።
2,267 – 33 = 2,334
ይስሐቅ የተወለደው በ2234 ዓመተ ዓለም ነው ብለን እናስብ።
(ይህን ማብራሪያ ቀለል ለማድረግ ባለ 360 ቀኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመት እንጠቀማለን። ከዚያም ዓመታታን በሙሉ ደምረን ውጤቱን ወደ ዘመናዊው የአሕዛብ ካላንደር እንቀይረዋለን።)
ከይስሐቅ ጀምሮ አይሁዳውያን ከግብዝ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ 691 ዓመታት አልፈዋል
ዘፍጥረት 25፡26 ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ስለዚህ ያዕቆብ ሲወለድ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበር።
ቀጣዮቹ ዓመታት ብዙም ግልጽ አይደሉም።
ዘፍጥረት 41፡46 ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፥ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
ዮሴፍ ከ7 መልካም የጥጋብ ዓመታት በኋላ 7 የረሃብ ዓመታት እንደሚመጡ ትንቢት ተናገረ።
ዘፍጥረት 41፡47 በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ።
48 በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመት እህል ሁሉ ሰበሰበ፥ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ።
ሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ሲያልቁ ዮሴፍ 30 + 7 = 37 ዓመቱ ነበረ።
ዘፍጥረት 41፡29 እነሆ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ፤
30 ደግሞ ከዚህ በኋላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል፥ በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል፤ ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል፤
ረሃቡ ከጀመረ በኋላ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ፍለጋ ወደ ግብጽ መጡ። ዮሴፍም ረሃቡ ሊያበቃ ገና 5 ዓመታት ይቀራሉ አለ።
ዘፍጥረት 45፡11 የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና።
ሁለት የረሃብ ዓመታት አልፈዋል፤ ስለዚህ ዮሴፍ 37 + 2 = 39 ዓመቱ ነበረ።
ከዚያ ወዲያ ወንድማማቾቹ አባታቸውን ያዕቆብን ሊያመጡ ሄዱ፤ እርሱም ፈርኦን ፊት በቀረበ ጊዜ እድሜዬ 130 ዓመት ነው አለ።
ዘፍጥረት 47፡8 ፈርዖንም ያዕቆብን፦ የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው? አለው።
9 ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤
ስለዚህ ዮሴፍ 39 ዓመት ሲሆነው ያዕቆብ 130 ዓመቱ ነበር።
ማለትም ዮሴፍ ሲወለድ ያዕቆብ 91 ዓመቱ ነበር።
ያዕቆብ ሲወለድ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበረ።
ዮሴፍ ሲወለድ ደግሞ ያዕቆብ 91 ዓመቱ ነበር።
ይስሐቅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዮሴፍ እስከተወለደበት ጊዜ 60 + 91 = 151 ዓመታት ተቆጥረዋል።
ዘፍጥረት 50፡26 ዮሴፍም በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ፤ በሽቱም አሹት፥ በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።
ይስሐቅ ከተወለደበት ዓመት ዮሴፍ እስከ ሞተበት ዓመት 151 + 110 = 261 ዓመታት አልፈዋል።
እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ ጋር ቃልኪዳን ባደረገ ጊዜ በአብርሃም ወገብ ውስጥ ከነበሩ ትውልዶች የመጨረሻው ዮሴፍ ነበረ። ስለዚህ ቃልኪዳኑ በቀጥታ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሴፍን የሚመለከት ነበረ።
ዮሴፍ የሞተ ጊዜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ያደረገው ቃልኪዳን ተጠናቀቀ።
ዘፍጥረት 15፡13 አብራምንም አለው፦ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ፤ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።
አይሁዶች ዮሴፍ በሕይወት ሳለ በባርነት ውስጥ አልነበሩም።
ባሮች የሆኑት ዮሴፍን የማያውቅ ንጉስ በተነሳ ጊዜ ነው። ይህም የሆነው ከ30 ዓመታት በኋላ ነው።
ዘጸአት 1፡8 በግብፅም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ።
ዘጸአት 1፡11 በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤
ዘጸአት 12፡41 እንዲህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ሠራዊት ሁሉ ከግብፅ ምድር ወጣ።
አይሁዶች ከግብጽ ከመውጣታቸው በፊት ግብጽ ውስጥ ለ30 ዓመታት በሰላም ለ400 ዓመታት ደግሞ በመከራ ኖረዋል።
261 + 430 = 691
ይስሐቅ ከተወለደበት ጀምሮ አይሁዶች ከግብጽ እስኪወጡ ድረስ 691 ዓመታት አልፈዋል።
እስራኤሎች በጠላቶቻቸው የተገዙባቸውን ዓመታት አይቆጥሯቸውም
ሰሎሞን በነገሰ በአራተኛው ዓመት ነው ቤተመቅደሱን መስራት የጀመረው።
1ኛ ነገሥት 6፡1 የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
ስለዚህ ከግብጻውያን ጭቆና ነጻ ከወጡ ከ480 ዓመታት በኋላ ቤተመቅደሱን መገንባት ጀመሩ።
በመሳፍንቱ ዘመን ግን ለ111 ዓመታት በጠላቶቻቸው ማለትም በዙርያቸው በነበሩ ጣኦት አምላኪ ነገዶች ተገዝተውና ተጨቁነው አሳልፈዋል። በነዚህ ዓመታት ውስጥ በግብጽ እንደነበሩት ተመልሰው በጭቆና ስር ወድቀው ነበር።
በነዚህ ዓመታት ጠላቶቻቸው እየገዙዋቸው ስለነበረ እግዚአብሔር እነዚህን ዓመታት አልቀጠራቸውም።
ከዚህ አንጻር አይሁዶች በራሳቸው ሕግ እየኖሩ አልነበሩም። ከባርነት ቀንበር ስር ሆነው ጣኦት በሚያመልኩ ጠላቶቻቸው እጅ እየተጨቆኑ ነበር የሚኖሩት።
ስለዚህ 480 ዓመታት ላይ 111 ዓመታት ስንደምር የምናገኘው 591 ዓመታትን ነው።
እስቲ እነዚህን ያልተቆጠሩ 111 ዓመታት እንደምራቸው።
መሳፍንት 3፡8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በመስጴጦምያ ንጉሥ በኵሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኵሰርሰቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት።
መሳፍንት 3፡14 የእስራኤልም ልጆች ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎም አሥራ ስምንት ዓመት ተገዙለት።
መሳፍንት 4፡3 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሀያ ዓመት ያህል እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።
መሳፍንት 6፡1 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
መሳፍንት 10፡7 የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በፍልስጥኤማውያንና በአሞን ልጆች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
8 በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።
መሳፍንት 13፡1 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
8 + 18 + 20 + 7 + 18 + 40 = 111 ዓመታት።
እነዚህ ዓመታት በጠላቶቻቸው እየተበዘበዙና እየተገዙ የኖሩባቸው የመከራ ዓመታት ስለሆኑ ነጻ ሆነው በእግዚአብሔር ሕግ ስር በተስፋይቱ ምድር እንደኖሩ ተደርገው አይቆጠሩም።
አሁን አይሁዶች ከግብጽ ወደ ወጡበት ጊዜ እንመለስ።
1ኛ ነገስት 6፡1 የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
ይስሐቅ ከተወለደ 691 ዓመታት በኋላ አይሁዶች ግብጽን ለቀው ሄዱ።
ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ ቤተመቅደሱ እስከተጀመረበት ዓመት ድረስ 691 + 591 = 1,282 ዓመታት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታትን ወደ አሕዛብ ዓመታት ስንቀይር 1,282/70 = 18 ዓመታት እንቀንሳለን።
1,282 – 18 = 1,264 የአሕዛብ ዓመታት።
ይስሐቅ የተወለደው በ2,234 ዓመተ ዓለም ከሆነ ሰሎሞን ቤተመቅደሱን መስራት የጀመረው 2,234 – 1,264 = በ970 ዓመተ ዓለም ነው።
ስለዚህ ሰሎሞን መቅደሱ ከተጀመረበት 4 ዓመታት ቀድሞ መንገስ የጀመረው በ974 ዓመተ ዓለም ነው።
ብዙ የታሪክ ምሑራን ሰሎሞን መንገስ የጀመረው መች ነው ሲባሉ በ960 ዓመተ ዓለም እና በ992 ዓመተ ዓለም መካከል የተለያዩ ዓመታትን ይጠቅሳሉ።
ስለዚህ እኛ ሒሳብ ሰርተን ያገኘነው ዓመት ማለትም 974 ከታሪክ ምሑራኑ ግምት ጋር በደምብ ይገጥማል።
2,300 ዓመታቱ ከይስሐቅ መወለድ ጀምሮ በቀራንዮ በፈሰሰው በኢየሱስ ደም መቅደሱ እስከመንጻቱ ድረስ ያሉትን ዓመታት ይሸፍናሉ።
ይህም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በፍጥረታዊ ደረጃ ያደረገውን ቃልኪዳን ኢየሱስ ጠለቅ ባለ መንፈሳዊ ደረጃ ያጸናበት ጊዜ ነው።
ዘፍጥረት 14፡18 የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።
ካሕን እና ንጉስ የሆነው መልከጼዴቅ ለአብርሃም እንጀራ እና ወይን ሰጠው።
ዮሴፍ እስር ቤት ውስጥ ከዳቦ ጋጋሪ እና ከወይን ጠጅ አሳላፊ ጋር ነበረ።
በመልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካሕናት የሆነው ኢየሱስ በመጨረሻው እራት ላይ ለደቀመዛሙርቱ እንጀራ እና ወይን ሰጣቸው።
ኢየሱስ እንጀራውን ቆረሰ። ዳቦ ጋጋሪውን ፈርኦን ገደለው።
ሮማውያን በ70 ዓ.ም አይሁዶችን ከተስፋ ምድራቸው አስወጥተው ካባረሩዋቸው በኋላ በመጨረሻው ዘመን አይሁዶች ተመልሰው የተስፋ ምድራቸውን እንደሚይዙ ትንቢት ተነግሯል።
ዘፍጥረት 14፡20 አብራምም (ለመልከጼዴቅ) ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።
አብርሃም አንድ ነገር እንዲደረግለት ብቻ ጠየቀ፤ ያም ኤስኮል ድርሻውን እንዲያገኝ ነው።
ዘፍጥረት 14፡24 ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ … አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።
አብራሃም አስራቱን አወጣ፤ ከዚያም ኤስኮል የራሱን ድርሻ እንዲወስድ ጠየቀ። ኋላ የአብርሃም የልጅ ልጅ ልጅ ሌዊ አስራት ሰብሳቢ ሆነ።
ከ4,000 ዓመታት በኋላ በ1967 ዓ.ም በተደረገው ጦርነት አይሁዶች ከተስፋይቱ ምድራቸው ውስጥ ብዙውን ክፍል መልሰው ተቆጣጠሩ። የእስራኤል ፕሬዚዳንትም ስሙ ሊቫይ ኤሽኮል ነበር።
አብርሃም ለሰጠው አስራት ሽልማቱን እስኪያገኝ ድረስ 4,000 ዓመታት ወሰደበት፤ ሆኖም ግን ተፈጽሞለታል። ኤሽኮልም ድርሻውን እንደገና ተቀበለ።
እንደ እግዚአብሔር ቃል እንከን የሌለበት ትክክለኛ ቃል የለም።
አብርሃምም አስራት በመክፈሉ አልተጸጸተም።