7ቱ ማሕተሞች ተገልጠዋል ግን አልተፈቱም
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች ከመፍታቱ በፊት ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት አስቀድሞ መገለጥ ይልካል።
First published on the 5th of December 2021 — Last updated on the 5th of December 2021እኛ ሰዎች ስንማር ጊዜ ይፈጅብናል፤ ስለዚህ ብዙ ነገር በአንድ ጊዜ መረዳት አንችልም። የሆነ ነገር ሲፈታ በውስጡ ያሉትን ዝርዝሮች በሙሉ ታውቃላችሁ፤ ይህም የመረጃ ወይም የእውቀት ብዛት በአንድ ጊዜ ለመሸከም ይከብደናል። ስለዚህ ከሚመጡት ክስተቶች ዋና ዋናዎቹን ታውቁ ዘንድ መጀመሪያ መገለጥ አለበት። ከዚያ ወዲያ መገለጡን ተከትሎ ሁሉ ነገር ሲፈታ በተገለጡት ዋና ዋና ክስተቶች መካከል ያሉትን ዝርዝሮች ሁሉ አንድ በአንድ ያሳውቃችኋል። ዝርዝሮቹን ሁሉ ማዋቅ ከመገለጥ አልፎ ማሕተሞቹ ስለመፈታታቸው ማረጋገጫ ነው።
ማርች 1963 ዓ.ም ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ ስለ ማሕተሞቹ ሊታወቅ የሚገባውን ዝርዝር በሙሉ ማወቅ አለባችሁ፤ ነገር ግን ስለማታውቁ ብዙ ችግሮች ያጋጥሟችኋል።
አሞጽ 3፡7 እግዚአብሔር አስቀድሞ ሚስጥሩን ለባሪያዎቹ ለነብያት ሳይገልጥ በፊት ምንም ነገር እንደማያደርግ ይናገራል።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
ስለዚህ ማሕተሞቹ አስቀድሞ አንድ ነብይ ሳይገልጣቸው በፊት አይፈቱም። የሰባቱ ማሕተሞች መጽሐፍ ርዕሱ “Revelation of the Seven Seals” የሚል ነው። ዊልያም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች መግለጥ የሚችል ብቸኛው ነብይ ነበር።
ሰባቱ ማሕተሞች በተገለጡ ጊዜ የመፈታታቸውን መገለጥ ብቻ ማግኘታችንን እስካልዘነጋችሁ ድረስ ማሕተሞቹ ተፈተዋል ብላችሁ መናገር ትችላላችሁ።
ማሕተሞቹ በሚፈቱ ጊዜ ምን እንደሚፈጠር ዋና ዋናውን ነገር አውቀናል።
ነገር ግን በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔርን ያገለገሉ ሰዎች እንዲሁም እግዚአብሔርን የተቃወሙ ሰዎች ምን እንዳነሳሳቸው እና ስለ ነበሩበት ሁኔታ በጣም ውስብስብ ከሆኑት ዝርዝሮች ውስጥ ብዙዎቹን አናውቃቸውም። ለምሳሌ ታማኝ ስለሆነው ሰማዕት ስለ አንቲጳስ እናውቃለን። ነገር ግን ስለ እርሱ እና ስለ ኖረበት ሁኔታ እና የምናውቀው ምንም ዝርዝር የለም።
ወሳኝ ጥያቄ፡- ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የተሰበከው ይህ ስብከት የማሕተሞቹ መፈታት ከሆነ ወንድም ብራንሐም በመጽሐፉ ሽፋን ላይ ርዕሱን የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ብሎ የሰየመው ለምንድነው?
በ1964 ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ከሰበከ ከአንድ ዓመት ከግማሽ በኋላ ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም ብሎ ተናገረ።
64-0719M የመለከት በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።
ስለ ሰባተኛው ማሕተም ማርች 24 ቀን 1963 ሰብኳል ግን ሰባተኛው ማሕተም ተፈቷል ብሎ አልተናገረም። ስለዚህ ማሕተሙ አልተፈታም።
ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም ምን እንደሚወክል እየገለጠልን ነበር።
63-1110M አሁን በወህኒ ያሉ ነፍሳት
ሰባተኛው ማሕተም ጌታን ወደ ምድር መልሶ ያመጣዋል።
ስለ ሰባተኛው ማሕተም ማርች 24 ቀን 1963 ተሰብኳል። ደመናው ከዚያ ቀን አንድ ወር ያህል ቀድሞ ፌቭሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከምድረ 43 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ፎቶግራፍ ተነስቷል።
ስለዚህ ደመናው የጌታ ምጻት አልነበረም ምክንያቱም ጌታን ወደ ምድር የሚያመጣው ሰባተኛው ማሕተም ነው። ደመናው ወደ ምድር አልወረደም፤ ለ28 ደቂቃ ሰማይ ውስጥ በታላቅ ከፍታ ተንሳፎ ነው የቆየው። ሰባተኛው ማሕተም ግን አልተፈታም። ስለዚህ ጌታ እስካሁን ድረስ አልመጣም።
በ1965 ደመናው ታይቶ ዓመታት ካለፉ በኋላ ወንድም ብራንሐም የጌታን ምጻት ሲጠባበቅ ነበር።
65-0725E በተራራው ላይ ያለው መስህብ ምንድነው?
ከምስራቅ የባሕር ዳርቻ እስከ ምዕራብ የባሕር ዳርቻ ድረስ በክርስቶስ ወገኖቻችን ለሆኑት ሁሉ አሁን ለሚያዳምጡን ሰላምታችንን እንልካለን። ሳን ሆዜ ውስጥ ላሉት ወንድሞች በዚያም ላለው ሕብረት ሰላምታችንን እንልካለን። በፕሬስኮት አሪዞና ተራሮች ውስጥ ላለው ወንድም ሊዮ መርሲየ እና ለወገኖቹ እዚያው ሆነው የጌታን ምጻት በሚጠባበቁበት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። በታክሰን ውስጥ ሆነው ዛሬ ማታ ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። ሂውስተን ቴክሳስ ውስጥ ሆነው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም ሰላምታ እንልክላቸዋለን። ቺካጎ ውስጥ ሆነው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። በምስራቅም ደግሞ ኒው ዮርክ እና ኮኔቲከት በታላቅ ጉባኤ ተሰብሰበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁ ሰላምታ እንልክላቸዋለን። እነርሱ ሁሉ ወደዚህ ቢመጡ የሚቀመጡበት ቦታ አይገኝም፤ ስለዚህ መልእክታችንን በስልክ ነው የምንልክላቸው። ለወንድም ጁንየር ጃክሰን እና በክላርክስቪል ለተሰበሰቡ ወገኖቹ ሰላምታ እንልክላቸዋለን። ለወንድም ራድል እና ለወገኖቹም የጌታን ምጻት እየተጠባበቁ ባሉበት ሰላምታ እንልክላቸዋለን። እኛ ደግሞ በዚህ ተሰብስበን የጌታን ምጻት እየተጠባበቅን ነን።
ስለዚህ ጌታ በ1963 አልመጣም። ይም ገና ወደ ፊት ይመጣል ማለት ነው።
በ1963 ወንድም ብራንሐም ሰባተኛው ማሕተም እንዳልተፈታ ተናግሯል። ለምን? ምክንያቱም ሰባተኛው ማሕተም የጌታን ምጻት ሚስጥር የሚገልጥ ማሕተም ነው። ይህም ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው። የጌታ ምጻት የዓለማችን ሁሉ ታላቅ ሚስጥር ነው። ይህ ሚስጥር ለማንም አልተገለጠም።
ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ አይችልም፤ ቢፈታማ ኖሮ ጌታ መች እንደሚመጣ ልናውቅ እንችል ነበር። ነገር ግን የሰባተኛውን ማሕተም መገለጥ አግኝተናል። ሰባተኛው ማሕተም ስለ ጌታ ምጻት የሚናገር መሆኑን አውቀናል። የሰባተኛው ማሕተም ዝምታ የጌታ ምጻት ሚስጥር እንዳይታወቅ ሚስጥሩን ይጠብቃል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ዝም ባለበት እኛም ዝም ማለት እንዳለብን ያስተምረናል።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
አሁን ልብ በሉ። በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምንኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ። አያችሁ?
ወንድም ብራንሐም ለእስራኤል ተልከው የሚመጡት ሁለቱ ነብያት ስድስተኛውን ማሕተም ይፈቱታል ብሏል። ስለዚህ አሁን በእኛ ዘመን ሊፈታ አይችልም። ለዚህ ነው ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ መለከቶች እና ስለ ሰባቱ ጽዋዎች ያልሰበከው። እነዚህ ሚስጥራት የታላቁን መከራ ዘመን የሚመለከቱ ናቸው፤ እኛም ስለነርሱ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።
ስለዚህ ሰባቱ ማሕተሞች መች ነው የሚፈቱት? ማሕተሞቹ የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ ሄዳ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ከቆመች በኋላ በሰማይ ነው። ማሕተሞቹ በተፈቱ ጊዜ መፈታታቸውን ለራሳችሁ ታያላችሁ፤ ታላላቅ እውቀቶች እና ማስተዋሎችም ይሰጡዋችኋል። አሁን ትልቅ ልዩነት እናያለን። በዚያ የሙሽራይቱ አካላት አዲስ አካል ይለብሳሉ፤ በሌላ መንፈሳዊ ደረጃ ማሰብ የሚችል አዲስ አእምሮ ይቀበላሉ። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሚገለጠውን እጅግ ብዙ የሆነ እውቀት፣ በታሪክ ውስጥ ያለፉ ክስተቶችን ዝርዝር ሁሉ ማወቅ ይችላሉ። ሙሽራይቱ በዚያ ጊዜ አሁን ማሰብ ከምንችለው ባለፈ ከፍ ባለ ደረጃ ማሰብ በመቻሏ ሙሽራይቷ ሞት፣ መከራ፣ አደጋዎች፣ እና በታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ አሰቃቂ ክፋቶች ሁሉ እንዴት ከአጠቃላዩ የእግዚአብሔር እቅድ ጋር እንደሚገጥሙ መረዳት ትችላለች።
2ኛ ቆሮንቶስ 12፡3 እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለው፣ በሥጋ እንደሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም፣ እግዚአብሔር ያውቃል፤
4 ወደ ገነት ተነጠቀ፣ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።
አሁን በለበስነው አካል ውስጥ ሆነን ሰማይ ውስጥ ምን እየተደረገ እንዳለ መረዳት አንችልም። በሰማያት ያሉት ሃሳባቸው ከእኛ ሃሳብ እጅግ የመጠቀና ከፍ ያለ ነው። ስለዚህ የእኛ ሃላፊነት ወንድም ብራንሐም ቀለል አድርጎ የገለጠልንን ዋና ዋናዎቹን ሃሳቦች ማመን ነው። ወደ ሰማይ ከሄድን በኋላ ብቻ ነው ውስብስብ የሆኑ ታሪካዊ ዝርዝሮች ሁሉ በዋናው ሃሳብ ውስጥ እንዴት እንደሚገጥሙ መረዳት የምንችለው።
ሰባቱ ማሕተሞች ለወንድም ብራንሐም በተገለጡ ጊዜ ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ ሄዶ ወደፊት ሊሆን ያለውን ነገር ልክ በወደፊቱ ዘመን ውስጥ እንደኖረ ሆኖ ተመለከተ። ብዙ ዝርዝር ሳያይ የወደፊቱን ክስተቶች ዋና ዋና ነገር ተመለከተ። እኛ ግን ምንም ስላላየን እርሱ በነገርን ነገር ላይ ተመስርተን ነው የምንማረው።
በሰማይ ሰባቱ ማሕተሞች ሲፈቱ ታላቁ መከራ በምድር ላይ ይጀምራል፤ ለእስራኤል ተልከው የሚመጡት ሁለቱ ነብያት ለዚህ ነው ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት የሚችሉት፤ ምክንያቱም ማሕተሞቹ የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ነው።
አራተኛው ማሕተምም ችግሮችን ይፈጥራል። ቁጥር 7 ውስጥ የንስሩን ድምጽ እናገኛለን። የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ እናገኛለን፤ ይህም እኛን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመልሰን የዊልያም ብራንሐም ድምጽ ነው። ይህም መልካም ነው።
ቁጥር 8 ግን ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ሞት የተባለው ይህ ፈረሰኛ ማነው? የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን ሰውየው ማነው? ማን እንደሆነ በፍጹም አናውቅም። ፖለቲካን፣ ሐይማኖትን፣ እና ገንዘብን አጣምሮ በመጠቀም በዓለም ላይ በአምባገነንነት የሚነግሰው እንዴት አድርጎ ነው? ይህንንም አናውቅም። ደግሞም የአስር አምባ ገነን መሪዎችን ወታደራዊ ኃይል ወስዶ ይጠቀምባቸዋል። እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች እነማን ናቸው? አናውቃቸውም። በታሪክ ውስጥ ነገሮች እስከ ምን እንደደረሱ እናያለን፤ ነገር ግን ወደፊት ምን እንደሚሆኑ አናውቅም። በአሁኑ ሰዓት ያለው ፖፕ ፍራንሲስ ደግ እና ሩህሩህ ሰው ነው። ታዲያ ወደፊት እንዴት ሆኖ ነው ይህ ሁሉ የሚለወጠው? ምንም አናውቅም።
የትራምፕን መመረጥ አስቡ። በቀላሉ የሚስቱት የሜሴጅ አማኞች ጥቅሶችን ወስደው ጠምዝዘው ተረጎሙና በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሒላሪ ክሊንተን ትመረጣለች ብለው ተናገሩ፤ ግን አልተመረጠችም። ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ስለሚፈጸሙ ነገሮች የሜሴጅ አማኞች ምን ያውቃሉ? ብዙም አያውቁም። ስለዚህ ሶስቱን ፈረሰኞች አንድ ስለሚያደርጋቸው ስለ መጨረሻው ፈረሰኛ ምን ያውቃሉ? ስለዚህም የባሰ ምንም አያውቁም። የአራተኛው ማሕተም ሚስጥር ግማሹ ያህል አልተገለጠልንም ምክንያቱም ሞት የተባለው ፈረሰኛ ከታለቁ መከራ ዘመን ጋር የተያያዘ ነው። የሜሴጅ ሰባኪዎች እንኳን ስለ ታላቁ መከራ ዘመን ይቅርና ከሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር የተያያዙ ክስተቶችን እንኳ በቅጡ አያውቁም።
ምዕራፍ 6 ቁጥር 1 እስከ 7 ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል። እያንዳንዱ ቁጥር አንድ የቤተክርስቲያን ዘመን ነው። ቁጥር 7 አሁን እኛ የምንኖርበት የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ነው። ቁጥር 8 አዲስ ስርዓት ነው። እርሱም ታላቁ መከራ ነው። ስለ ታላቁ መከራ የምናውቀው ነገር በጣም ጥቂት ነው።
የሜሴጅ አማኞች ስለ ትራምፕ መመረጥ ከሳቱት የስሕተት ብዛት አንጻር ስለ ሰባተኛው ዘመን ብዙም እውቀት እንደሌላቸው አሳይተዋል። ለምን?
አንዲት ቆንጅዬ ነገር ግን ክፉ ሴት አሜሪካን እንደምትመራ የተነገረውን ጥቅስ ጠምዝዘው በመተርጎም ቆንጅዬ ያልሆነችው እንዲሁም ክፉ ያልሆነችው ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች አሉ። ከዚህ የበለጠ ስሕተት ምን አለ? የሰውን ንግግር ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ አድርገዋል። ኒቆላዊነት የክፋቱ መጨረሻ ይህን ያህል ነው። ኒቆላዊነት እግዚአብሔር የሚጠላው ነገር ነው።
እነዚህን ጥቅሶች ወስደው ወደተሳሳተ ድምዳሜ መድረሳቸው የእነርሱን የጥቅስ አተረጓጎም ማመን እንደማንችል ያሳየናል። በዚህም መንገድ እግዚአብሔር ትምሕርት ሊያስተምረን ፈልጓን።
“የተቀጠቀጠው እባብ” በሚለው ስብከቱ ወንድም ብራንሐም ወደ ትንሽ የውሃ ኩሬ ውስጥ ሱገባ የነበረ እባብን በጥይት ተኩሶ አቆሰለው።
61-0611 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 1
… ከጥቂት ሌሊቶች በፊት ለማረጋገጥ ይሆነኝ ዘንድ ከጌታ ዘንድ ጉብኝት ተደርጎልኝ ነበር። እኔም ቢጫ እና ጥቁር የሆነ እባብ አየሁ፤ እባቡም እግሬ ላይ ነደፈኝ። ነገር ግን በውስጤ የነበረው ደም እጅግ የበለጸገ ከመሆኑ የተነሳ የእባቡ መርዝ ምንም ሊያደርገኝ አልቻለም። እኔም እግሬን ተመለከትኩ፤ የተነደፍኩበት ቦታ በፊትም ተነድፌ የነበረበት ቦታ ነው። እኔም ወዲያው ዞር ብዬ እባቡን በጠመንጃ ተኩሼ መታሁት፤ ጥይቱም መሃሉ ላይ መታው።
አንድ ወንድም እንዲህ አለ … እኔም ዘወር ብዬ ጭንቅላቱን በጥይት ልመታው ስል እንዲህ አለ፡- “በጥይት አትምታው፤ አጠገብህ መሬት ላይ ያለውን በትር አንሳ።” እኔም በትሩን ለማንሳት ዘወር ስል እባቡ እየተውረገረገ ትንሽዬ የውሃ ኩሬ ውስጥ ገባ።
የሜሴጅ ሰባኪዎች በአንድ ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ላይ ማለትም በዓለም ላይ ትልቁ የፕሬዚዳንታዊ ስልጣን ላይ ለመውጣት በሚደረግ ውድድር ላይ የተመረኮዘ ትንቢት ይተነብያሉ። ይህ ትንቢታቸው በምን ላይ የተመሰረተ ነበር? የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ የሌላቸው ጥቂት የሰው ንግግር ጥቅሶች። የዚህ ዘመን የሜሴጅ ተከታዮች ስብከት ይህን የሚመስል ነው። ትንሽዬ የጥቅሶች ኮሬ ብቻ። ነገር ግን ጠምዝዘው ከተረጎሙዋቸው ጥቅሶች ተነስተው የደረሱበት ድምዳሜ የሕይወት ውሃ ወንዝ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የጸና አይደለም።
ጥቅሶችን ጠምዝዘው በመተርጎም ሒላሪ ክሊንተን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ታሸንፋለች ብለው አላዋቂነታቸውን ካሳዩ በኋላ ሃፍረታቸውን ለመሸፋፈን ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል ስለዚህ ሚስጥራትን በሙሉ እናውቃለን አሉ። ነገር ግን የመጨረሻዎቹን አራት ማሕተሞች ጠለቅ ያለ ዝርዝር ትርጉም ሊነግሩን አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ሎዶቅያ ዕውር መሆኗን ተናግሯል። ትራምፕ በምርጫ ማሸነፉ ለዚህ እውነት አሳዛኝ ማስረጃ ነው።
ይህ ለሁላችንም የሚሆን ማስጠንቀቂያ ነው። በሰዎች ንግግር ጥቅስ ላይ ተመስርታችሁ አስተምሕሮ አታዘጋጁ። አስተምሕሮዋችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ የተመሰረተ ይሁን።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የእባቡ ትርጉም ምንድነው?
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ ዓይነት ደብዳቤዎች ደርሰውኛል፤ ከልዩ ልዩ ስፍራዎች ብዙ ስልክ ተደውሎልኛል፤ አንተ ክርስቶስ ነህ እያሉ ይጠይቁኛል። ወንድሞች ይህ አስነዋሪ፣ መጥፎ የሰይጣን ውሸት ነው። አያችሁ? እኔ ወንድማችሁ ነኝ። እንዲህ ዓይነቱን ውሸት የሰማ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ሮጦ ይጠፋል። ክርስቶስን የሚወድ ሰው ሁሉ ከዚያ ቦታ ሮጦ ያመልጣል።
… መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ራሱ ተቀጥቅጦ በፍጥነት እንደሚሞት ተስፋ አደርጋለው፤ ስለዚህ ወደ አገልግሎቴ መመለስ እችላለው።
ያ እባብ የሚወክለው ወንድም ብራንሐምን ወደ መለኮትነት ደረጃ ከፍ በማድረግ የእርሱን ንግግር ከመጽሐፍ ቅዱስ የማስበለጥ አስተምሕሮን ነው። ስብከቶቹን “የእግዚአብሔር ድምጽ” ማለት። ይህ ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይቃረናል፤ ደግሞም በዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደምንሰማ ተስፋ አልተሰጠንም። የሜሴጅ ሰባኪዎች ግን ዊልያም ብራንሐም የተባለውን ሰው ያለ ልክ ከፍ ከማድረጋቸው የተነሳ ከተናገራቸው ቃሎች ጥቂቱ ተጠምዝዘው የጥቅስ ኩሬ በመሆን አሁን ትንቢታዊ እውነት ተደርገው እየተቆጠሩ ናቸው። ነገር ግን እንዲህ ያደረጉ ሁሉ ተሳስተዋል።
የሜሴጅ ሰባኪዎች በዚህ ትንቢት ከተሳሳቱ በኋላ ተጠራጣሪ ሰዎች እንዴት እያሳቱን እንዳሉ በመጠቆም ያላግጣሉ። ይህ የተሳሳተ ትንቢት እኛን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለመመለስ ታስቦ በተዘጋጀው በእውነተኛው መልእክት ላይ ታላቅ ጉዳት አድርሶበታል። ወንድም ብራንሐም ሐሰተኛ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሁን እንደ ማስረጃ የሚጠቀሙበት ነገር አግኝተዋል ምክንያቱም ይህ የተሳሳተ ትንቢት እርሱ በተናገረው ቃል ላይ ተመስርቶ ነው የተነገረው።
በሰው ንግግር ላይ ተመስርተን አስተምሕሮ ስናዘጋጅ እንዲህ ዓይነት አደጋ ውስጥ እንወድቃለን። በአስተዋይነታቸው ሊያስደንቁን ሲፈልጉ የሜሴጅ ሰባኪዎች በትንቢታዊ የማስተዋል ብቃታቸው ሊያስገርሙን ፈለጉ። ነገር ግን ወንድም ብራንሐምን መለኮት ሊያደርጉት እየሞከሩ ናቸው፤ እርሱ ግን ይህንን መለኮት የመሆን አስተምሕሮ በጥይት መቶ ሊገድል የሞከረ ሰው ነው። ወንድም ብራንሐም ይህንን ክፉ እባብ ሊገድል ሲሞክር ጌም እየተጫወተ አልነበረም።
ትራምፕ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፉ ይህ በሰው ንግግር ጥቅስ ላይ ተመስርቶ የመስበክ ልማድ ትልቅ ስሕተት መሆኑን ግልጽ ማሳያ ነው።
ጥቅሶቹን መልሳችሁ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መውሰድ እና አስተምሕሮዋችሁን በሰው ንግግር ላይ ጥገኛ ሳትሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ማጽናት ያስፈልጋኋል።
ማቴዎስ 23፡1 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦
2 ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ ምኩራቦችን ይመሩ የነበሩ ሐይማኖተኞቹ ፈሪሳውያን እንዲህ ሲሉ ነበር፡- “ነብዩ ሙሴ እንዳለው …” በማለት አይሁዶችን አንገት አስደፍተው የእነርሱን እምነት እንዲከተሉ ተጽእኖ ያደርጉባቸው ነበር። ነገር ግን ነብዩ ሙሴ ምን ማለቱ እንደነበር አንዳችም የተረዱት ፍንጭ አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እርሱ የተናገራቸውን አንዳንድ ጥቅሶች ቢጠቅሱም እንኳ የእግዚአብሔርን “ትልቅ ሃሳብ” አልተረዱም፤ ከዚህም የተነሳ ሙሴ ሲናገርለት የነበረው መሲህ የመጣ ጊዜ አላወቁትም። ሙሴን አዘውትረው እየጠቀሱ፤ ታላቁ ነብይ በተናገረው ቃል ሱስ እንደያዘው ሰው ተጠምደው ቢቆዩም እንኳ በስተመጨረሻ ኢየሱስን አንቀበለውም አሉ።
ይህ አሳዛኝ ነገር በኢየሱስ ዳግም ምጻትም ይደገማል። ፊት ፊት የሚሮጡት የሜሴጅ ሰባኪዎች እንዲህ ማለታቸውን ይቀጥላሉ፡- “ነብዩ ዊልያም ብራንሐም ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል ብሏል፤ እኛም ሚስጥራቱን በሙሉ እናውቃለን”። እነዚህ ጥቅሶች የሚከተሉትን አሉባልታዎች ለማሰራጨት ያገለግላሉ፡- ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደተናገሩ እናውቃለን፤ አዲሱን የኢየሱስ ስም እናውቃለን፤ ደግሞም የ1963ቱ ታላቅ ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር መምጣት ነው። ሌሎች ደግሞ ደመናው የጌታ መገለጥ ወይም ዳግም ምጻት ነው ብለው ያምናሉ። ከዚህም በተጨማሪ ሰባቱ ማሕተሞች ስለተፈቱ “በጉ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ስለተነሳ ለሙሽራይቱ ካልሆነ በቀር ምሕረት አብቅቷል”
ነገር ግን አሁንም ሐይማኖተኞቹ “የሜሴጅ” መሪዎች ወንድም ብራንሐም የተናገረውን ቃል ይጠቅሳሉ፤ እርሱ ከተናገረው ውስጥ ለሃሳባቸው የማይስማማቸውን ጸጥ ብለው ያልፋሉ፤ ከዚያም በላይ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ይቃረናሉ ወይም አንቀበላቸውም ይላሉ። በሎዶቅያውያን (በመጨረሻዋ) የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ በቤተክርስቲያኖች በዲኖሚኔሽናዊም ይሁን በሜሴጅ ቤተክርስቲያን ሁሉ በር ላይ ቆሟል፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኖች ሁሉ አንፈልግህም ብለውጥ አስወጥተውታል። ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ተወግዘዋል። ዛሬ ትምሕርታቸው ትክክል መሆኑን ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያረጋግጡ ቤተክርስቲያኖች የሉም። የሰው ንግግር ጥቅሶች መጽፍ ቅዱስን ተክተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ዕውር ናቸው ይላል። ይህ አስፈሪ ነገር ነው። ቤተክርስቲያኖቻችን ጨለማ ብቻ ነው መሆን የሚችሉት ምክንያቱም በመንገዳችን ላይ ሊያበራልን የሚችል ብርሃን ከመጽሐፍ ቅዱስ እየወሰድን አይደለንም። ስለዚህ ሁላችንም ችግር ውስጥ ነን። ቤተክርስቲያኖች ወይም የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለመከተል እምቢ ቢሉም እንኳ ኢየሱስ በየቤተክርስቲያኑ ውስጥ ግለሰቦች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያምኑ ለማድረግ እየሞከረ ነው።
የሰባቱ ማሕተሞች ሚስጥራዊ መፈታት ምን ማለት እንደሆነ ይበልጥ ለመረዳት መንግስተ ሰማያትን ይበልጥ መረዳት ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም ሰባቱ ማሕተሞች በራዕይ ምዕራፍ 4 እስከ 8 እንደተጻፈው በመንግስተ ሰማያት ውስጥ ነው የሚፈቱት።
ስለ መንግስተ ሰማያትና ስለ ሲኦል እንደ ቀላል ነገር እናወራለን፤ ነገር ግን ከምድር ጋር ያላቸው ግንኙነት ምንድነው? የት ናቸው?
እኛ የምንኖረው በሶስቱ ዳይሜንሽኖች ማለትም በርዝመት፣ ስፋት፣ እና ከፍታ በተወሰነ ዓለም ውስጥ ነው የምንኖረው። የቦታን ዳይሜንሽኖች ከእኛ ተነስተው ወደ ሁሉም አቅጣጫ እንደተዘረጉ አድርገን ነው የምናያቸው።
አራተኛው ዳይሜንሽን ጊዜ ነው። ጊዜ ከቦታ በላይ ከፍ ያለ ዳይሜንሽን ስለሆን በትክክል ልንገልጸው አንችልም፤ ደግሞም ጊዜ እራሱ ምን እንደሆነ በትክክል አናውቅም ምክንያቱም ጊዜን አይተነውም አናውቅም። ነገር ግን ከጊዜ ጋር በውስጣችን በስሜት ግንኙነት መፍጠር እንችላለን። በሆነ ጉዳይ ተመስጠንና ተደስተን ከሆነ የግል ጊዜያችን ይፈጥናል። ስንሰላች ደግሞ ጊዜ ይንቀራፈፍብናል። ሰውነታችንም በውስጡ ይለወጣል፤ ስለዚህ ልጆች አድገው ትልቅ ይሆናሉ፤ ይህም መልካም ነው፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ ጊዜ ያስረጀናል፤ ፊታችንም የጊዜን ምልክት ያሳያል። ጊዜ በውስጡ የዓለማችንን ሶስት ዳይሜንሽን የያዘ የቧምቧ ግድግዳ ይመስላል።
በሕይወት ስንኖር በጊዜ ቧምቧ ውስጥ እየፈሰስን እንኖራለን። ነገር ግን በሆነ መንገድ ጊዜ በአሁኑ ሰዓት ላይ የራሱን መጋረጃ ይጋርድበትና የወደፊቱን እንዳናይ እንዲሁም ያለፈውንም በጥቂቱ እንድንረሳ ያደርገናል።
ስሜቶቻችን የሚፈጠሩት በውስጣችን ባለው የሕይወት መንፈስ ነው። ስለዚህ ጊዜ በውጫዊው የቦታ ዓለም እና በውስጣዊው ዓላማ፣ ተስፋ፣ ፍርሃት እንዲሁም ያለማቋረጥ እምነት እና ጥርጣሪ በሚጋጩበት የመንፈስ ዓለም መካከል የሚገኝ ውስብስብ አገናኝ ነው። ስንሞት ነፍሳችን በጊዜ ግድግዳ ውስጥ ታልፋለች።
ቀጥሎ ደግሞ የጊዜን ቧምቧ የሚከብብ ከጊዜ በላይ ከፍ ያለ አምስተኛ ዳይሜንሽን አለ፤ እርሱም የጠፉ ሰዎች የሚኖሩበት መንፈሳዊ ክልል ነው። ይህ ክልል ያልዳኑ ነፍሳት እና ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ያላቸው አጋንን የሚኖሩበት ነው። ከሰይጣን የሚመጡ ሃሳቦች ወደኛ የሚደርሱት ከዚህ “ጎረቤታችን” ከሆነው ክልል ነው። ጠንቋዮችና አስማተኞች እንደሚያደርጉት የጊዜን ግድግዳ ጠርምሰን ብናልፍ ከአጋንንት ጋር መነጋገር እንችላለን። የአጋንንቱ ዓለም የእውነት አለ። አጠገባችን በሚገኘው ዳይሜንሽን ውስጥ የሚኖሩ የቅርብ ጎረቤቶቻችን ናቸው። ይህ መልካም እና ክፉ የሚኖርበት መንፈሳዊ መኖሪያ ጊዜያዊ ነው ምክንያቱም በስተመጨረሻ የእሳት ባሕር ውስጥ ተቃጥሎ ይጠፋል። ከዚያ በኋላ ጊዜ ራሱ ያበቃል።
ስለዚህ ጊዜ በፍጥረታዊው ዓለማችን እና ከጊዜ ቧምቧ ውጭ ካለው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ዓለም መካከል እንደ ግድግዳ ወይም መጋረጃ ሆኖ የቆመ ዳይሜንሽን ነው።
አንድ ያልዳነ ሰው ሲሞት የዚያ ሰው ነፍስ በጊዜ ግድግዳ ውስጥ አልፎ ወደ አምስተኛው ዳይሜንሽን ይገባል።
ኢየሱስ ግን በቀራንዮ መስቀል ላይ የማምለጫ መንገድ ስላዘጋጀ በእግዚአብሔር ቃል የሚያምኑ የዳኑ ነፍሳት የጠፉ ሰዎች የሚኖሩበትን ክልል አልፈው ከዚያ ከፍ ወዳለ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ስድስተኛ ዳይሜንሽን ይገባሉ፤ ይህም የመላእክት እና የዳኑ ሰዎች መኖሪያ ክልል ሲሆን መንግስተ ሰማያት ይባላል። መንግስተ ሰማያት ውስጥ ጊዜ የሚባል ነገር የለም። ማንም አያረጅም። ሕምም የለም፤ ሐዘን የለም፤ ጸጸትም የለም። መንግስተ ሰማያት ከገባን በኋላ ዘላለማዊ እንሆናለን።
63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ
መጽሐፉን በእጁ ከያዘው ከበጉ ይህንን በሰባት ማሕተም የታተመ መጽሐፍ ይገልጥልን ዘንድ ምሕረቱንና ጸጋውን በእኛ ላይ እንዲደርግ እንጠይቃለን፤ ሲገልጥልንም ከጊዜ መጋረጃ ጀርባ ጥቂት አሻግረን እናያለን።
ነብይ ብቻ ነው በመንፈስ ከፍ ብሎ በመነሳት ከጊዜ መጋረጃ በስተጀርባ አልፎ ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን በራዕይ ማየት የሚችለው። ነብይ የወደፊቱን አሁኑኑ በራዕይ ያያል፤ ያያቸው ክስተቶች ግን የሚፈጸሙት ወደፊት ብዙ ቆይተው ነው።
57-0728 ሕይወትን መጠማት
ወንድሜ ሆይ እግዚአብሔር ከጊዜ መጋረጃ በስተጀርባ አሻግሮ የማየቱን ዕድል በሰጠህ። አሁን በዚህ ጉባኤ ውስጥ ተቀምጠህ መንፈስ ይመጣና ወደ ሌላ ዳይሜንሽን ይዞህ በመሄድ የሚያሳይህን ዓለም በጭራሽ አያውቀውም።
55-0109M ታላቁ አለቃ እና ንጉስ የሆነው መልከጼዴቅ
… ይህንን ከፊታችን የተጋረደውን መጋረጃ ማንሳት ብንችል (ስጋ ስላሳወረን) መጋረጃውን እንዲህ ቅድድ አድርገን ብናስወግደውና ከጊዜ መጋረጃ በስተጀርባ ምን እንዳለ ማየት ብንችልና ዓይተንም ብንጠይቅ
63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ
ይህ አሁን የምንነጋገርበት ጉዳይ በዚህ በሰባት ማሕተሞች በተዘጋው መጽሐፍ ውስጥ ተገልጾአል። የቤዛነት መጽሐፍ እዚህ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተገልጾአል። ክርስቶስ በመጨረሻ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከፈቀደ በዚሁ ሳምንት በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ይገለጥልናል። አያችሁ? ችግር የለም፤ ይገለጥልናል።
ክርስቶስ በሰማይ በመጨረሻ ሰባቱን ማሕተሞች ከመክፈቱ በፊት መጀመሪያ በምድር ላይ ለእኛ የሰባቱን ማሕተሞች መከፈት ሊገልጥልን ይገባል፤ ይህንንም የሚያደርገው ለመረጠው ነብይ የማሕተሞቹን መከፈት በራዕይ በማሳየት ነው።
እኛ ዘንድ ያለው ትልቅ ስሕተት ወንድም ብራንሐም ወደፊት የሚፈቱትን ማሕተሞች በራዕይ ማየቱን የእውነትም ማሕተሞቹ እንደተፈቱ አድርገን መቁጠራችን ነው። ነገር ግን አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት ቀድመን እንዘጋጅ ዘንድ ነገሩ ሳይሆን በፊት ለነብይ ይገለጥለታል።
63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያመጣውም
ኦ የዘላለም ሕይወት የሚቀበሉ ሰዎች ምንኛ አስደናቂ እንደሚሆኑ በቁጥር ቢያንሱም እንኳ! እንዲህ ይላል፡- “በሰራዊት መካከል ይሮጣሉ፤ ቅጥሩንም ይዘላሉ።” አዎ፤ የሞት ሰራዊት ሊይዛቸው አይችልም፤ በመካከሉ ሮጣ ታልፋለች። በፍጥረታዊው እና በልዕለ ተፈጥሮአዊው መካከል ያለውን “ግድግዳ” ዘላው ታልፈዋለች፤ ከዚያም ወደዚያ ታላቅ ዘላለማዊነት ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ትገባለች። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ እናመሰግንሃለን። ጊዜው በጣም እየቀረበ መሆኑን እናውቃለን።
እየቀረበ ያለው ምንድነው? በዳግም ምጻት ጊዜ የሚፈጸመው የቤተክርስቲያን መነጠቅ።
ከጊዜ ወጥተን ወደ ዘላለማዊነት መግባት እንድንችል ስጋዊ አካላችን ይለወጣል። ልክ ኤልያስ እና ሔኖክ እንዳደረጉት አስቀድመን መሞት ሳያስፈልገን ከጊዜ ቧምቧ ወጥተን እንሄዳለን።
58-0309M በግድግዳው ላይ የመጣው የእጅ ጽሐፈት
ከዚያ ወዲያ ጊዜ አይኖርም። ጊዜ በዘላለማዊነተ ይዋጣል።
ሙሽራይቱ በውስጡ ደም የሌለው አዲስ የማይሞት አካል ስትቀበል እያንዳንዱ ሰው ከጊዜ ዓለም ይወጣና የዘላለማዊነት አካል ይሆናል። ስለዚህ ለነዚህ ሰዎች ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም። አካላቸውም ከዚያ ወዲያ ምንም ዓይነት ለውጥ አይለወጥም። ከዚያ ወዲያ ማርጀት እና መታመም ያቆማሉ።
ለዳኑት ቤተክርስቲያኖች (ወደ ኋላ የሚቀሩት እንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት) እንዲሁም ላልዳኑት ሰዎች እና ለአይሁዶች ጊዜ ሳይቋረጥ ይቀጥላል ምክንያቱም እነርሱ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።
በዚያም ታላላቅ ለውጦች ተጽእኖ ያደርጉባቸዋል። እንቅልፍ የተኙት ቆነጃጅት ማለትም “ቤተክርስቲያን ወዳዶቹ” ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ወደጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ለመመለስ እምቢ ያሉት ክርስቲያኖች በሙሉ በታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ።
የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ፡ የፍጥሞ ራዕይ ምዕራፍ 2 - በጌታ ቀን በመንፈስ
… ዮሐንስ ለሁለት ዓመታት እነዚያን ራዕዮች እየተቀበለ በመንፈስ ነበረ። በእርግጥ የሆነው ነገር ዮሐንስ በመንፈስ ተነጥቆ በመሄድ ወደ ጌታ ተጉዞ ነበረ፣ የጌታ ቀንም ገና ሊመጣ ያለው ቀን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጌታ ቀን ሲናገር ወደፊት እንደሚሆን ነው የሚያመለክተው፤ ዮሐንስ ግን በነበረበት ዘመን ሆኖ የዚያን ገና ወደፊት የሚመጣውን የጌታን ቀን ነገር ቀድሞ ያይ ነበር።
… መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ በምሳሌዎች ነው የተጻፈው
ነብይ በመንፈስ ተነጥቆ በመሄድ ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን አሁኑኑ እንደሆኑ አድርጎ ያያል።
ሰይጣን ሰዎችን የሚያሞኛቸው እንዲህ ነው። ራዕዩ እራሱ የነገሩ ክስተት ነው ብለው እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል።
የተታለሉ ክርስቲያኖች በራዕዩ የታዩ ክስተቶች ለወደፊት የሚሆኑ ናቸው እየተባለ እነዚያ የወደፊት ክስተቶች ሆነው እንዳለፉ አድርገው ያምናሉ።
የጌታ ቀን እግዚአብሐየር በታላቁ መከራ ውስጥ የምድራችንን እና የዘመናችንን ቀሻሸ ከምድር ላይ ጠርጎ የሚያጠፋበት ጊዜ እና ኢየሱስ ምድርን ለ1,000 ዓመት ለሚገዛበት መንግስት ምድርን የሚያነጻበት ዘመን ነው።
ኢሳይያስ 13፡6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
ኢሳይያስ 13፡9 እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
ኤርምያስ 46፡10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።
በታለቁ መከራ መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር እስራኤል ላይ ጥቃት የሰነዘሩትን የራሺያ ጦር ሰራዊት እና አጋሮቻቸውን ያጠፋቸዋል። ራሺያ ማለት የሰሜኑ ንጉስ ነው። እነዚህ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰራዊት በጥላቻ መሰዊያቸው ላይ አይሁዶችን በመግደል መስዋእት ሊያቀርቡ ይመጣሉ። እግዚአብሔር ደግሞ እነርሱን እንደ መስዋእት አድርጎ ይገድላቸዋል።
ትንቢት ምነድነው?
ነብይ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተነጥቆ ይሄድና “ከጊዜ ግድግዳ” ወይም “ከዘመን መጋረጃ” በስተጀርባ አሻግሮ በራዕይ ያያል። ራዕዩ ከዘመን መጋረጃ አሻግሮ ይወስደውና ወደፊት የሚሆኑ ክስተቶችን አሁን እየሆኑ እንዳሉ ያህል ጥርት አድርጎ እንዲያይ ያስችለዋል።
ከዚያም በኋላ ነብዩ እኛ አሁን ወዳለንበት ዘመን ይመለስና በራዕይ የተመለከታቸው ክስተቶች እንዴት እንደሚፈጸሙ ያስረዳናል።
እንደዚህ ወደፊት የሚሆኑ ክስተቶችን አሁን እንደተፈጸሙ ያህል በራዕይ አስቀድሞ ማየት እነዚህ ክስተቶች ሆነው አልፈዋል ማለት ነው ብላችሁ በማመን አትሳቱ።
64-0705 ማስተርፒስ
ሌላ መጽፍ እንክፈትና ስለ ታላቁ ቀራጺ እናንብብ፤ እርሱም ሁሉን ቻይ አምላክ ነው። እርሱም ዓለም ከመፈጠሯ በፊት፣ መሰረቷም ከመመስረቱ በፊት የሚፈልገውን በአእምሮው አይቶ ነበር፤ የፈለገውም ሰውን በራሱ መልክ መፍጠር ነበር። እርሱ በልቡ ሃሳብ ውስጥ ያሰበውን በራዕዩ ውስጥ የነበረውን ሃሳብ በገሃድ ገልጦ ሊሰራው ፈለገ።
እርሱ በአእምሮው ውስጥ አስቦት የነበረውን ነገር በመፍጠር ወደ መኖር ማምጣት የሚችል አምላክ ነው።
ወንድም ብራንሐም ነብይ እንደመሆኑ መጠን የወደፊት ክስተቶችን አስቀድሞ ማየት ችሏል። ስለተሰጠውም መገለጥ ሊነግረን ችሏል። ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው በራዕይ የታዩትን ክስተቶች በዚህ ዓለም ውስጥ ወደ መሆን ሊያመጣቸው የሚችለው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
ስለዚህ ሰባቱ ማሕተሞች የእውነት ከመፈታታቸው በፊት እግዚብሔር አስቀድሞ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት መገለጥ ሊልክልን ይገባል።
ስለዚህ መርሳት የሌለብን ሁለት ወሳኝ ነጥቦች አሉ።
እግዚአብሔር የወደፊቱን ዘመን በተመለከተ ራዕይ ወይም “ቪዲዮ” ያሳያል፤ ይህም ራዕይ ወደፊት ሊሆኑ ያሉ ክስተቶችን ይገልጣል።
ከዚያም ጊዜ እያለፈ ሲሄድ እነዚያ ክስተቶች ዘመናቸውን ጠብቀው በገሃዱ ዓለም ይፈጸማሉ።
ሰዎች ትልቅ ስሕተት የሚሰሩት እዚህ ጋ ነው።
ማርች 1963 ወንድም ብራንሐም ጌታ በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሱትን ማሕተሞች ሲፈታቸው በራዕይ አየ፤ ይህ ግን የሚፈጸመው በራዕይ ምዕረፍ 4 እንደተጻፈው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች ተሳስተው ሰባቱ ማሕተሞች በ1963 ተፈተዋል አሉ።
ሰባቱ ማሕተሞች ሲፈቱ የታየበት ራዕይ በ1963 ነበረ። ነብዩ ወደፊት ስለሚሆኑ ክስተቶች የተናገረውም መስማት እንችላለን። ነገር ግን ማሕተሞቹ የእውነት የሚፈቱት ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው። ከዚያ በኋላ ክስተቶች በፊታችን ሲፈጸሙ እናያለን።
ስለ ክስተቱ የተሰጠውን የራዕይ መገለጥ መስማታችንን (ነብይ በራዕይ አይቶ ከዚያ በኋላ የነገረንን መስማታችንን) ወደፊት ሁላችንም የምናየው ክስተት እራሱ ነው በማለት አንሳሳት።
54-1205 ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን
አሁን ቆሜ የሆነ ሰውን እያየሁ ነኝ፤ ራዕዩ እዚህ ላይ ያበቃል፣ እናንተም ታያላችሁ። ምን እየተከናወነ እንዳለ ታያላችሁ። ነገር ግን ወደ ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚወስዳችሁ አታውቁም።
አሁን ቢመጣ ምናልባት ከሕንጻቸው ውስጥ ገፍተው ያስወጡታል ዛሬም እንደሚያደርጉት። ልጄ እስከሚበቃ ድረስ በተጠንቀቅ ቆመህ ተመልከት። ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ ዓለም ይዞኝ ይገባል፤ ይለውጠኛል። እስቲ አስቡ። እዚሁ ቆሜ ወደ ኋላ አርባ ዓመታት ሄጄ በዚያ ዘመን ከነበረ ሰው ጋር ስነጋገር ያደረገውን ሁሉ ስመለከት፤ ድምጼ ግን አሁን እዚህ እየተሰማ፤ ሆኖም ግን አርባ ዓመታት ወደ ኋላ ሄጃለሁ። ወይም ደግሞ ከአሁኑ ዘመን ብዙ ዓመታት ወደፊት ሄጄ ምን ሊመጣ እንዳለ ለሰዎች ስነግራቸው አስቡ…
ወንድም ብራንሐም ያያቸው ራዕዮች ወደ ሌላ ዓለም ይዘውት ይሄዳሉ፤ እርሱም እኛ በዓይናችን ልናየው የማንችለው መንፈሳዊ ዓለም ስድስተኛ ዳይሜንሽን ነው። በዚህ ሰማያዊ ዳይሜንሽን ውስጥ በሚገባ ጊዜ “ከጊዜ ቧምቧ” ውጭ ነው፤ ስለዚህ በዘመናት ወደ ኋላ ማየት ይችላል ደግሞም በተቃራኒው አቅጣጫ በመመልከት በቀላሉ የወደፊቱን ዘመን ማየትም ይችላል።
62-0601 ከኢየሱስ ጋር መወገን
አሁን ከጥንቷ ቤተክርስቲያን እንጀምራለን፤ ለአምስት ደቂቃ ወደ ራሳችን ዘመን አምጥተናት እናያታለን፤ የሰሩትን ሁሉ በዝርዝር እንመለከታለን፤ ከዚያ በኋላ ስለ ወደፊቱ ዘመን የተቀበልኩትን ራዕይ አሳያችኋለው።
ስለ ወደፊቱ መገለጥ ልናገኝ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ራዕይ በማየት ነው። ያው ራዕይ ነብዩ በመንፈስ ተነጥቆ “ከጊዜ ቧምቧ” ውጭ በሚወጣበት ጊዜ ያለፈውንም ዘመን ይገልጥለታል፤ ምክንያቱም ነብዩ ከጊዜ ዓለም ሲወጣ ያለፉ ክስተተችንም ሆነ ወደፊት የሚመጡትን ማየት ይችላል።
ነገር ግን ወደፊት የሚሆነውን ነገር ስለ ወደፊቱ ከሚገልጠው ራዕይ ጋር አትቀላቅሉት።
የቤተክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመተንበይ ቤተክርስቲያንን ለዛሬው ሁኔታዋ ያበቃትን ያለፈ ታሪኳን ማወቅና መረዳት አስፈላጊ ነው።
ሰዎች ወደፊት ስለሚቀበሉት ፈውስ ሊያሳምናቸው ብሎ በሕይወታቸው ውስጥ ያለፈ ታሪካቸውን ይገልጥላቸው ነበር።
63-1216 ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናል
መንፈሳዊ ሕልም ሲተረጎም፣ በትክክል ሲተረጎም ከራዕይ በምንም አይለይም። ራዕይስ ምንድነው? ራዕይ ወደፊት የሚፈጸሙ ክስተቶች ትንበያ ነው፤ ራዕይ አንድ ነገር ከመሆኑ አስቀድሞ ይናገራል።
ስለዚህ ራዕይ እንደ ቪዲዮ ነው። የወደፊት ክስተቶችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ባለ ሶስት ዳይሜንሽን ቪዲዮ ልታዩ ትችላላችሁ፤ የምታዩትም እነዚህ ክስተቶች ከመፈጸማቸው ረጅም ዘመን አስቀድሞ ነው።
65-1205 ሊሆኑ ያሉ ነገሮች
ከሶስት ዓመታት በፊት ክርስቲያን ነጋዴዎችን ከጊዜ መጋረጃ ባሻገር ታያላችሁ። እኔስ ከዚህች ሌሊት በኋላ በሕይወት ላልኖር እንደምችል አውቃለሁ። ከእንግዲህ በኋላ በሕይወት ሆኜ ላላያችሁ እችላለው ግን ይህ እውነት ነው። ይህንን ራዕይ ወይም ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም።
ራዕዩ ወንድም ብረንሐም ከጊዜ መጋረጃ ባሻገር የሰማይን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ዳይሜንሽን እንዲያይ አስችሎታል።
“ሁለተኛው ማሕተም” ማክሰኞ ማርች 19 ቀን 1963 የተሰበከ
አሁን ይህን ልብ በሉ። “እግዚብሔር አስቀድሞ ለነብያቱ ሳይገልጥ በፊት አንዳችም ነገር አያደርግም” አለ አሞጽጽ ከዚያም በኋላ እኛ ሥራውን እናያለን
ስለዚህ አሁን እየገለጠ ያለውን ነገር ሊፈጽመው እያሰበ መሆን አለበት።
እግዚአብሔር አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት (ሰባቱን ማሕተሞች ከመፍታቱ በፊት) አስቀድሞ የማሕተሞቹን መፈታት ይገልጣል።
ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት ሲናገር ነበር። በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት ሲገልጥለት ነበር፤ ይህም ከተወሰኑ ዘመናት በኋላ እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች በተጨባጭ ይፈታቸዋል ማለት ነው።
ማሕተሞቹ ሊፈቱ የሚችሉት እግዚአብሔር ለነብዩ ከገለጣቸው በኋላ ብቻ ነው።
ስለዚህ ሰባቱ ማሕተሞች ወንድም ብራንሐም የማሕተሞቹን መፈታት መገለጥ ተቀብሎ እስኪጨርስ ድረስ ሊፈቱ አይችሉም።
የሜሴጅ አማኞች የሰሩት ትልቅ ስሕተት ማርች 1963 በምድር ላይ የተሰበከውን የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት በራዕይ መገለጥ የማሕተሞቹ መፈታት ነው ብለው ማመናቸው ነው፤ ነገር ግን ማሕተሞቹ የሚፈቱት በራዕይ ምዕራፍ 4፣ 5፣ 6፣ 7 እና 8 መሰረት ሙሽራይቱ በሰማያት ወደተዘጋጀው ሰርግ ልትታደም ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ብቻ ነው።
ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የተጻፈው መጽሐፍ ርዕሱ፡- “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ” የሚል ነው።
እስቲ ኤልያስ ከኤልዛቤል ሸሽቶ ሄዶ በምድር ላይ እግዚአብሔርን የሚያመልክ እርሱ ብቻ እንደነበረ ወዳሰበበት ወደ 900 ዓመተ ዓለም እንመለስ።
63-0321 አራተኛው ማሕተም
ተመልከቱ ኤልያስ አንዳቸውም እንኳ እንደዚያ እንደሆኑ አላወቀም። እግዚአብሔር ማሕተሙን ፈቶ የመጽሐፉን ሚስጥር እስከሚገልጥለት ድረስ የዳነ ሰው እርሱ ብቻ እንደሆነ ያስብ ነበር፤ ለበዓል ያልሰገዱ ሰባት መቶ ሰዎች እንደነበሩ አላወቀም። እግዚአብሔር መጽሐፉን ለኤልያስ በከፈተለት ጊዜ እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- “ልጄ ሆይ አንድ ጊዜ ስማኝ፤ የሆነ ቦታ ተሰውረው የተቀመጡ ሰባት መቶ ሰዎች አሉኝ፤ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ስማቸው በእኔ ዘንድ በመጽሐፍ ተጽፏል። እነርሱ የእኔ ናቸው።”
ይህ በዚያ ዘመን የሰባቱ ማሕተሞች እውነተኛ መከፈት ሊሆን አይችልም። እግዚአብሔር ለኤልያስ ራዕይ ወይም ከማሕተሞቹ የአንዱን መከፈት እያሳየው ነበር።
በዚህ ትምሕርት ውስጥ ያለው ቁጥር 1 ችግር ማሕተሞቹ ተከፍተዋል ከተባለ ክርስቶስ ሰባቱን ማሕተሞች ከመክፈቱ በፊት ከምሕረት ዙፋን ላይ ተነስቷል ማለቱ ነው።
የመጀመሪያው ማሕተም ማርች 1963 ዓ.ም ሲገለጥ ኢየሱስ ከምሕረት ዙፋኑ ከተነሳ ከዚያ ወዲህ ላለፉት 54 ዓመታት በምሕረት ዙፋኑ ላይ ደም አልነበረም ማለት ነው። ከዚያ ወዲህ የተወለዱ ነፍሳት ሁሉ የምሕረት ዙፋኑ ላይ ደም ሳይሆኖር ነው የሚድኑት፤ ይህም ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ሃሳብ ነው። በፍርድ ዙፋን ላይ ደም ካለ ያ ዙፋን የምሕረት ዙፋን ነው።
1. ነገር ግን ስለ ማሕተሞቹ በሰበከ ጊዜ ዊልያም ብራንሐም ክርስቶስ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ተነስቷል፤ ደግሞም አማላጅነቱን አቁሟል አላለም። ስለዚህ ሲናገር የነበረው ነገሩ መፈጸሙን ሳይሆን ስለ ወደፊቱ ያየውን ራዕይ ነው።
2. ኢየሱስ ገና ወደፊት የሆነ ቀን የሚመጣ ከሆነ ለምንድነው ከ50 ዓመት በፊት ከምሕረት ዙፋኑ የተነሳው?
3. በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የነበሩ አማኞች ክርስቶስ በምሕረት ዙፋን ላይ እንዳለ ነው ያመኑት፤ እኛ ወደ እነርሱ እምነት የምንመለስ ከሆነ እነርሱ ያመኑት ነው ማመን ያለብን። የስንዴ ፍሬ ወይም የበቆሎ ፍሬ በመጨረሻ የሚታጨደው በመጀመሪያ የተዘራውን ዘር ሲመስል ብቻ ነው።
63-0321 አራተኛው ማሕተም
ልብ በሉ በዚያ ዘመን የአውሬ ልብ ይሰጠዋል፤ ሰይጣንም ራሱን በስጋ ይገልጣል፤ ምክንያቱም ቤክርስቲያን ወደ ሰማይ ስትነጠቅ ሰይጣን ወደ ምድር ይወድቃል። አያችሁ? የዚያን ጊዜ ያበቃል። የሰይጣን ክስ በሙሉ ያበቃል። አያችሁ?
አሁንም ልብ በሉ፤ ስለ እኛ የሚማልደው በዙፋኑ ላይ እስካለ ድረስ ሰይጣን በዚያ ቆሞ መክሰስ ይችላል ምክንያቱም የተቃራኒው ወገን ጠበቃ ነው። እርሱ የክርስቶስ ባለጋራ ነው። ክርስቶስ ደግሞ … እርሱ በዚያ ቆሟል … ባለጋራው እዚያ ቆሞ እንዲህ ይላል፡- “ቆይ አንዴ፤ አዳም ወደቀ። አዳም ይህን አደረገ። እኔም አሸነፍኩት። ሚስቱ ውሸትን እንድታምን አደረግሁ፤ አንተም ውሸትን ከማመኗ የተነሳ ይፈረድባታል አልክ። ገብቶኛል።”
ነገር ግን ጠበቃችን በዚያ ቆሟል (አሜን።) እርሱም ወገናችን የሆነው ቤዛችን ነው (አሜን።) የእርሱ ደም እጅግ ክፉ የሆነውን ሐጥያተኛ ልብ ወስዶ ይለውጠዋል። ስለ እኛ የሚማልደው በዙፋኑ ላይ ነው። አዎን።
ሰይጣን እንዲህ አለ፡- “ግን እኮ ሐጥያተኞች ናቸው።”
ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “የለም፤ አይደሉም።”
ይህ የተከፈተው አራተኛው ማሕተም ነው፤ አራተኛው ማሕተም እስኪከፈት ድረስ ሁሉ በጉ በምሕረት ዙፋኑ ላይ ነው። ስለዚህ ይህ ዕውን የማሕተሙ መከፈት ሊሆን አይችልም ምክንያቱም በጉ የመጀመሪያውን ማሕተም ከመክፈቱ በፊት ከምሕረት ዙፋኑ መነሳት አለበት። ስለዚህ ይህንን ወደፊት የሚፈጸም ክስተት ወንድም ብራንሐም በራዕይ እያየ ነው፤ ራዕይም የወደፊቱን ማየት የምንችልበት ብቸኛ መንገድ ነው።
63-0320 ሶስተኛው ማሕተም
የታረደ በግ ደም እንደሚፈስሰው እናውቃለን። ታርዷል። ከታረደ በኋላ ከሙታን ተነስቶ በዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፤ ከዙፋኑ በስተኋላ እንደዚህ ቆሞ ወደ እርሱ ስለሚመጡ ነፍሳት ሁሉ ይማልዳል። ከዚያም በኋላ የመጨረሻው ነፍስ ወደ መንግስቱ ከገባ እና ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ እግዚአብሔር የቤዛነትን መጽሐፍ በእጁ ይዞ ይታያል።
የመጨረሻው ሰው እስኪገባ ድረስ በጉ በዙፋኑ ላይ ይቆያል። ይህ መሰረታዊው የወንጌል መልእክት ነው፤ ስለዚህ ደሙ ላለፉት 50 ዓመታት በዙፋኑ ላይ አልነበረም በሚል ሌላ መልእክት መለወጥ የለበትም። የዛሬውን ሐጥያታችንን ለማንጻት የዛሬው ደሙ ያስፈልገናል።
የዚህ ትምሕርት ችግር ቁጥር 2 ማሕተሞቹ ዕውን ተከፍተዋል ማለቱ ነው፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው ፈረሰኛ እስካሁንም ልዩ ልዩ ፈረሶቹን እየጋለበ ነው የሚል ትርጉም ያመጣል። ስለዚህ ያለፉት ማሳሳቻዎቹ ተገልጠዋል ነገር ግን የወደፊት ማሳሳቻዎቹ አልተገለጡም። ሰይጣን ሊያታልለን ብሎ አዳዲስ ማሳሳቻዎችን እየፈጠረ ነው። ተጠንቀቁ።
በነጭ ፈረስ የተመሰለው ሐይማኖታዊ ማሳሳቻው ሙሉ በሙሉ አልተገለጠም ምክንያቱም የሚጠቀምባቸው ስሕተቶች መልካቸውን እየቀየሩና እየተለወጡ ነው የሚመጡት፤ ስለዚህ እኛ በዚህ ጊዜ ወደፊት ሊጠቀምባቸው ስላሰባቸው መጽሐፍ ቅዱስን የማጣመሚያ ዘዴዎቹ ንቁ መሆን አለብን። ብልጥ የሜሴጅ ሰባኪዎችና ዲኖሚኔሽናዊ ሰባኪዎች አዳዲስ ማራኪ አሳሳች ሃሳቦችን ስለሚያፈልቁ በፍጹም ልባችን መጽሐፍ ቅዱስን ካልተከተልን በቀር ልንታለል እንችላለን። ስለዚህ በየጊዜው የሰው ንግግር ጥቅሶችን ከመተርጎም የሚመጡ አዳዲስ የተሳሳቱ ትምሕርቶች ስላሉ ልንመረምራቸውና ልንዋጋቸው ያስፈልጋል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
በጉ ማሕተሙን በፈታ ጊዜ ወዲያ የነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ። ነጎድጓዱ ምን ገለጠ? ሙሉ በሙሉ ራሱን አልገለጠም …
ይህ በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የተገለጠው ያልታወቀ ፈረሰኛ ማነው? ማነው? እስቲ እናስብበት። ማነው ይህ ያልታወቀ ፈረሰኛ በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ መጋለብ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ በመሄድ ወደ ዘላለማዊነት ሰተት ብሎ የሚገባ። ሁለተኛው ማሕተም ይመጣና እስከ መጨረሻው ድረስ ቀጥ ብሎ ይሄዳል። ሶስተኛው ማሕተም ይመጣና እስከ መጨረሻው ድረስ ቀጥ ብሎ ይሄዳል። አራተኛው፣ አምስተኛው፣ ስድስተኛው፣ ሰባተኛው፤ እያንዳንዳቸው እስከ መጨረሻው ድረስ ይዘልቃሉ …
[የመጀመሪያው ማሕተም “ሙሉ በሙሉ ራሱን አልገለጠም”። ለምንድነው ያልገለጠው? እያንዳንዱ ፈረስ መጋለብ የጀመረው በፊት ነው ነገር ግን እስከ ዛሬም ድረስ እየጋለበ ይገኛል፤ ወደፊትም ይቀጥላል። የሐይማኖት አሳሳችነት የጀመረው በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ነው፤ ዛሬም የሰው ንግግር ጥቅስ እየተጠቀሙ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጣምሙና የሚቃረኑ ሰዎችን እያሞኘና እያታለለ ቀጥሏል። ይህ ዘዴ ሰይጣን የሰባኪዎችን አእምሮ የሚያታልልበትና የሚቆጣጠርበት አዳዲስ ተንኮሎችን እየፈጠረ በሄደ ቁጥር ወደፊትም ይቀጥላል።]
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ልክ በጉ ማሕተሙን እንደፈታው የነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ። ማሕተሙ ሲፈታ ምን ተገለጠ? ሙሉ በሙሉ አይደለም የተገለጠው። መጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ ቀጥሎም ምልክት ነው፤ ከዚያ በኋላ ይገለጣል፡ ሶስት ነገሮች ናቸው። አያችሁ? ከዙፋኑ ነው የሚመጣው። መጀመሪያ ሊታይም ሊሰማም የሚችል ነገር የለም። ታትሟል። የበጉ ደም ዋጋውን ከፍሏል። እርሱ ሲናገር ነው የነጎድጓድ ድምጽ የመጣው። እርሱም በተናገረ ጊዜ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ፈረሰኛ እየጋለበ ወጣ። ይህም ምልክት ነው።
… አሁን ልበ በሉ። በመጨረሻው ቀን በግልጽ ይታወቃል ብሏል፤ ነገር ግን በቤተክርስቲያን ተምሳሌት ሆኖ ነው የሚመጣው። ገብቷችኋል ወይ ቅዱሳን? በቤተክርስቲያን ተምሳሌት ሆኖ ነው የሚመጣው፤ ማሕተም እንዳለም ያውቃሉ፤ ነገር ግን በትክክል ምን እንደሆነ አያውቁም፤ ምክንያቱም በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ፈረሰኛ ነው።
ደግሞም ይህ ማሕተም በሚፈታበት ጊዜ በመጨረሻው ቀን ብቻ ነው የሚገለጠው። ማሕተሙ የሚፈታው ለማነው? መቸም ለክርስቶስ አይደለም፤ ለቤተክርስቲያን ነው እንጂ… ሙሽራ ብዬ እጠራችኋለው። (አያችሁ?) ይህን መረዳት ትችላላችሁ።
[መወሰን አለባችሁ፡
ይህ ዕውን በሰማይ የማሕተሞቹ መፈታት ነው ወይስ የማሕተሞቹን መፈታት ወንድም ብራንሐም በራዕይ ማየቱ ነው?
1. እግዚአብሔር የሰባቱን ማሕተሞች መፈታትና ትርጉሞቻቸውን ለነብይ ሳይገልጥ በፊት ሰባቱን ማሕተሞች አይፈታቸውም።
2. ወንድም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች ፈትቶ ቢሆን ኖሩ የሆነ ሰው ከእርሱ በፊት የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ማምጣት ነበረበት፤ ነገር ግን የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ያመጣ ማንም ሰው የለም። ይህን ማድረግ የሚችሉ ነብያትም አልነበሩም።
ዮሐንስ የነጭ ፈረሰ ምሳሌ በራዕይ አየ። የተቀመጠበትም ፈረሰኛ ደጋን ይዟል ግን ቀስት አልነበረውም። ዘውድ ጭኖ ድል እየነሳ ወጣ። ደጋን የያዘ ሰው አደገኛ ይመስላል ነገር ግን ደጋን ቢይዝም ቀስት ከሌለው ሰውየው እየቀለደ ነው። ወንድም ብራንሐም ጠለቅ ያለ ራዕይ አየ፤ በዚህም ራዕይ ውስጥ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ፈረሰኛ የሐይማኖት አሳሳች አሰራር መሆኑን ተረዳ፤ ማለትም ዲኖሚኔሽናዊ ክርስትና ከእግዚአብሔር ቃል እየራቀ መሄዱ ነው። የሐይማኖት አሳሳችነት ሲጀምር በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንና ዘውድ በጫነው የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ነበር፤ መጨረሻው ደግመፐ የእግዚአብሔር ቃል ማለትም ኢየሱስ ተገፍቶ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ሲቆም ነው።
ቀጥሎም የተምሳሌቱ መገለጥ ዕውን የሚፈጸም እውነታ መሆን አለበት።
ሰዎች ግራ የተጋቡት በዚህ ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ታሪክ ወደ ኋላ ተመልሰን ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጀምሮ በማጥናት እንዲሁም የሮማ መንግሰት በፈራረሰ ጊዜ ሳትፈርስ የቆየችው ብቸኛዋ የሮማ ተቋም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሆኗን በማየት ነጩን ፈረስ በታሪክ ውስጥ ተከታትለን እናየዋለን።
ይህ የሐይማኖት አሳችነት መገለጥ ከመጀመሪያው ጀምሮ መታየቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጀመሪያ ሰው ራስ የሆነበት የክርስቲያን ዲኖሚኔሽን እንደምትመሰርት ለማመልከት ነው (ይህም ኒቆላዊነት ነው ማለትም አንድን ቅዱስ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ከፍ ማድረገ ማለት ነው።) የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰው የቤተክርስቲያን ራስ የሆነባት የመጀመሪያዋ ተቋም ስትሆን በሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን በመቃወም የምትታወቅ ብቸኛዋ ድርጅት ሆናለች። ይህ የሐይማኖት አሳሳችነት መገለጥ ቀጥሎ በ860 ዓ.ም ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ ዘውድ ጫነና ታላቁ የቤተክርስቲያን ራስ ሆነ። ይህ መንፈስ በእያንዳንዱ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባቱ ፓስተሮች በየቤተክርስቲያናቸው ራስ ካልሆንን እንዲሉ አድርጓቸዋል፤ ቢቻላቸው የሌሎች ቤተክርስቲያኖችም ራስ መሆን ይፈልጋሉ።
የእናት ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጀመረው የሰው መሪነት ስሕተት ወደ ልጆቿ ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ተላለፈ። ዛሬ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም በሰው መሪ እየተገዙ ነው የሚኖሩት፤ መሪያቸው ፓስተሩ ነው። ነገር ግን “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሰ ሲሆን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስድስት ጊዜ ተወግዟል። ስለዚህ ፓስተር ቤተክርስቲያንን እንዲገዛ አንዳችም የተሰጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን የለም።
ይህ ሁሉ ታሪክን በመመርመር ሊደረስበት ይችላል፤ ነገር ግን የመጀመሪያው ማሕተም መጨረሻው ይህ አይደለም፤ ምክንያቱም የሐይማኖት አሳሳችነት ዛሬም በዘመናችን ይሰራል፤ እስከመጨረሻውም ድረስ ይቀጥላል። ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችም በኒቆላዊነት ተወርሰዋል ምክንያቱም የሚተዳደሩት በፓስተር ነው። ከዚህም በተጨማሪ ብዙ የሜሴጅ አማኞች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ተታለዋል፤ ደግሞም የሰው ንግግር ጥቅሶች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እየተኩ ሲሄዱ ብዙዎች ይስታሉ። በዚህ ምክንያት ነው በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች መካከል ብዙ ልዩነቶች ሊኖሩ የቻሉት። በመካከላቸው ልዩነት ካለ ሁላቸውም ትክክለኞች ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ ከዚህ በፊት የነበሩ ስሕተቶችና ሽንገላዎች ተጋልጠዋል፤ ነገር ግን የወደፊቶቹ ሽንገላዎች በሙሉ ገና አልተጋለጡም፤ ምክንያቱም ለሰው ንግግር የሚሰጡ አተረጓጎሞች በራሳቸው ብዙ የተሳሳቱ ትምሕርቶችን እየወለዱ ናቸው።
ስለዚህ የመጀመሪያው ማሕተም ሙሉ በሙሉ አልተፈታልም፤ ሰይጣንም ዘመን ሲያልፍ አዳዲስና የረቀቁ የማታለል ዘዴዎችን እየፈጠረ ይመጣል።
የሐይማኖትነ ሽንገላን ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መምርምሮ መግለጥ የመጀመሪያው ማሕተም ሙሉ መገለጥ አይደለም።
ገና ወደፊት የሚመጣ ብዙ አዲስ የሐይማኖት ስሐተት አለ።
አዳዲስ ስሕተቶች በታላቁ መከራ ዘመንም ይፈለፈላሉ።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ኢየሱስ ማሕተሞቹን በሚፈታ ጊዜ በምድር ላይ ታላቁ መከራ ይጀምራል፤ ኢየሱስም በዚያ ጊዜ ነው እንቅልፍ የተኙትን ቆነጃጅት አንቀላፍተው እንዲቀሩና ንጥቀት እንዲያመልጣቸው የሚያደርጓቸውን የሐይማኖት ሽንገላ አስተምሕሮዎችን በሙሉ በዝርዝር ገልጦ ሊነግረን የሚችለው። ብርሃን ስላልነበራቸው መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው መረዳት አልቻሉም። በታላቁ መከራ ውስጥ ዛሬ የማናውቀው ዓይነት ብዙ የስሕተት ጎርፍ ይመጣል።
ስለዚህ የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት መገለጥ አጠቃላይ የሆነ እይታ ማግኘት እንድንችል ረድቶናል። ነገር ግን አዲስ ዝርዝሮች በየጊዜው ብቅ ይላሉ። የዚህ ዘመን ፈሪሳውያን ማለትም የቤተክርስቲያን መሪዎች ክርስቲያኖችን ያሳሳቱበት የስሕተት ትምሕርት ከነሙሉ ዝርዝሩ የሚገለጠው በሰማይ ብቻ ነው።
ሰይጣን ወደፊት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲክዱ የሚያደርግበትን ብዙ የረቀቁ ሽንገላዎች አሁን አናውቃቸውም። ሰይጣን ግን ከእኛ ይልቅ ብልጥ ነው። ለደቂቃ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ፈቀቅ ብትሉ ሰይጣን በቀላሉ ያጠምዳችኋል። የሰው ንግግር አተረጓጎማችሁ ምርጥ ስለሆነ መንግስተ ሰማያት የምትገቡ አይምሰላችሁ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተጣብቃችሁ ብትኖሩ ብቻ ነው መንግስተ ሰማያት የምትገቡት።
የሰይጣን ሽንገላዎች ረቂቅነታቸው የሚገለጠው የሜሴጅ አማኞች የሰው ንግግር ጥቅስ ትርጓሜያቸውን እየፈጠሩ ሲጨምሩበት ነው። ይህ በዘመናችን ትልቅ ጥቃት የሚፈጸምበት ነገር ነው። ክርስቲያኖች ወደ እውነት እየተጠጉ ሲሄዱ ጠላትም እነርሱን በመዋጋት እየበረታ ይሄዳል።
የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በፊት ከነበሩበት ይልቅ ዛሬ በልዩነታቸው እየበዙ ሄደዋል። የሚጠቀሙዋቸው የሰው ንግግር ጥቅሶች ልዩ ልዩ ትርጓሜ እስከ አሁን ካላሳታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነገር ግን ተጠንቀቁ ምክንያቱም አዳዲስና ይበልጥ የረቀቁ ሽንገላዎች እንደ ቫይረስ እየተባዙ ናቸው። ሰዎች በጣም ብልጥ እየሆኑ ነው፤ ሃሳቦቻቸውም በጣም አሳሳች እየሆኑ ናቸው።
ስለዚህ የመጀመሪያው ማሕተም ሙሉ በሙሉ አልተገለጠም፤ ምክንያቱም እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች ገና ወደፊት በሚመጡ አስተምሕሮአዊ ወጥመዶች ይፈተናሉ፤ እነዚህም ፈተናዎች ከሰዎች ፍልስፍና ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የሚመጡና በወንድም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶች ላይ በሚሰጡ ልዩ ልዩ ትርጓሜዎች አማካኝነት የሚመጡ ናቸው።
አንድ ምሳሌ እንመልከት።
ወንድም ብራንሐም “ሰባቱ ነጎድጓዶች ተናግረዋል” ብሎ አያውቅም።
ነገር ግን የተለያዩ የነጎድጓድ አስተምሕሮዎች ሁሉ የተመሰረቱት በዚህ ትርጓሜ ነው።
ስለዚህ የሜሴጅ ተከታዮች ወንድም ብራንሐም ያልተናገረውን ተናግሯል ብለው ነው የሚያምኑት፤ ነገር ግን መልእክተኛው የተናገረውን ብቻ እንጠቅሳለን ይላሉ።
“ፈሪሳውያን እና ጻፎች በሙሴ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ።” እነዚህ ሰዎች ነብዩን ሙሴን እየጠቀሱ ኢየሱስን አንቀበልም አሉ።
የሜሴጅ ፓስተሮች በዊልያም ብራንሐም ወንበር ላይ ይቀመጣሉ። ይህንን ነብይ እየጠቀሱ ከዚያም እርሱ የተናገረውን ቃል እየጠመዘዙ መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም ይላሉ።
የሜሴጅ አማኞች ከዚህ በታች ያለውን ጥቅስ ሲያዩ በጉ ከምሕረት ዙፋን ላይ ተነስቷል ብለው ያስባሉ።
63-0818 የመጀመሪያው ማሕተም
… ድምጹ ነጎድጓድ ነው። ድምጹ የመጣው ከየት ነው? በጉ አማላጅነቱን ትቶ ከተነሳበት ከዙፋኑ። አሁን የሚገባውን ሥፍራ ለመያዝ በዚህ ቆሟል። ነገር ግን ነጎድጓዱ ከዙፋኑ ውስጥ ነው የመጣው። በጉ ደግሞ ከዙፋኑ ውጭ በዚያ ቆሞ ነበር። በጉ የአባቱን ዙፋን ትቶ በመነሳት የራሱን ዙፋን ለወስድ በሄደበት ነው ነጎድጓዱ የሚመጣው።
ወንድም ብራንሐም የወደፊቱን በራዕይ በመመልከት ኢየሱስ የመጀመሪያውን ማሕተም ሲፈታ ያያል። የሚያየው ወደፊት የሚፈጸም ራዕይ ስለሆነ ራዕዩን ሲከታተል ወደፊት ራዕዩ በሚፈጸምበት ዘመን ኢየሱስ የምሕረት ዙፋኑን ትቶ ሲነሳ ያያል፤ ስለዚህ በዚያ ዘመን ምሕረት ያቆማል።
… አንድ ቀን ከአባቱ ዙፋን ላይ ይነሳል፤ ከዚያም ወደ ራሱ ዙፋን ይሄዳል። አሁን አገልጋዮቹን ሊጠራ ይመጣል። እንዴት ነው አገልጋዮቹን የሚጠራቸው? የቤዛነት መጽሐፍ በእጁ ነው ያለው…
“አንድ ቀን”። ይህ ማለት ወደፊት ነው። ስለዚህ በራዕይ የታየው ነገር የሚፈጸመው ወደፊት አንድ ቀን ነው። ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ ይገልጣቸዋል።
… ኦህ በጣም ይደንቃል። እስቲ አሁን በሰማያዊ ሥፍራ ስለመቀመጥ አስቡ፤ ምን ዓይነት ነገር ይሆን? የምንነጠቅበት ጊዜ ከመምጣቱ በፊት እዚህ ምድር ላይ አሁን ባለንበት ሁኔታ ተቀምጠን እንዲህ የሚሰማን ከሆነ፤ በግድግዳዎች መካከል ቆመን ወይም ዝናብ ውስጥ ቆመን ደስ የሚለን ከሆነ በዚያ በዙፋን ላይ የተቀመጠውን እርሱን ስናየው ምነኛ ደስ ይለን ይሆን? ኦ እንዴት ድንቅ ነው። የታላቅ ክብር ጊዜ ነው የሚሆነው።
እኛ አሁን “በሰማያዊ ሥፍራ ተቀምጠናል”። ወደፊት ሊሆን ያለው ሲገለጥ መንፈሳችን በዚህ መገለጥ ወደሰማይ ይነጠቃል። በአሁኑ ሰዓት ወደፊት የሚፈጸሙ ክስተቶችን ነብዩ ወደ በራዕይ ተነጥቆ ሲያያቸው እኛ ደግሞ ስለ ክስተቶቹ መስማት ብቻ ነው የምንችለው። እኛ የንጥቀት ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ወደ ሰማይ መሄድ አንችልም፤ ምክንያቱም በዚያ ጊዜ ብቻ ነው ወደ ሰማይ የምንነጠቀው። ከዚያም ሰማይ ከገባን በኋላ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ “በሰማያዊ ሥፍራ እንቆማለን” የተነገሩን ክስተቶችም ሲፈጸሙ በቀጥታ እናያለን።
… የመጀመሪያው ማሕተም በተምሳሌት መልኩ ሲፈታ ነጎድጓድ መጣ። አሁን ደግሞ የእውነት ሲፈታ ምን ይመጣ ይሆን?
የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ ዮሐንስ ባየ ጊዜ የነጎድጓድ ፍንዳታ ድምጽ ተሰምቷል። ከሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ በፊት ሰባት መላእክት ወደ ወንድም ብራንሐም የመጡ ጊዜም ፍንዳታ ነበረ።
በጉ ዕውን ማሕተሞቹን ለመፍታት ከምሕረት ዙፋን ላይ የሚነሳው መች ነው? ይህ የሚሆነው ወደፊት ነው። በዚያ ጊዜ የነጎድጓድ ድምጽ ይሰማል።
-0319 ሁለተኛው ማሕተም
ለመነጠቅ የሚያበቃንን ጸጋ መቀበል እንፈልጋለን። ያ ሚስጥራዊ ነጎጓድ ከወዲያ ማዶ ሲያንጎደጉድ፤ ቤተክርስቲያንም ወደ ላይ ስትነጠቅ፤ ጌታ ሆይ በዚያ ጊዜ ይህንን ጸጋ መቀበል እንፈልጋለን።
አንድ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ገና ወደፊት ይመጣል። የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ በራዕይ ነጎድጓድ ታይቷል። ነገር ግን የዚህ ነጎድጓድ ፍጻሜ ገና ወደፊት ነው። ሳንሴት ተራራ ላይ መላእክቱ ወደ ወንድም ብራንሐም ሲመጡ እርሱ አደን ላይ እያለ የተፈጠረው ፍንዳታ ይህ ስብከት ከመቅረቡ አንድ ሳምንት ቀድሞ ነው የሆነው። እርሱ ግን ገና ወደፊት ስለሚመጣ ነጎድጓድ ነበር የሚናገረው።
ወንድም ብራንሐም የአራተኛውን ማሕተም መፈታት በገለጠ ጊዜ በጉ እስዚያ ሰዓት እንኳ ከምሕረት ዙፋኑ እንዳልተነሳ ተናግሯል። ስለዚህ ሲናገር የነበረው ነገር እነዚህ ነገሮች ወደፊት እንደሚፈጸሙ በራዕይ ማየቱን ነው።
63-0321 አራተኛው ማሕተም
በሙሉ ልቤ የማምነው ዙፋኑ እስካሁን ማንም እንደሌለበት ነው። እስካሁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ እንዳለ አምናለው፤ ነገር ግን በጣም በቅርቡ ከዚህ ዙፋን ላይ ይነሳል፤ ከዚያም በምድር ላይ የተቤዣቸውን ሊወስድ ይመጣል። ሩት እየተጠባበቀች ሳለ እርሱ የዘመድ ቤዛነትን ሥራ እየሰራ ነው። ነገር ግን በቅርቡ እንደምታውቁት ቦኤዝ የዘመድን ሥራ ከሰራ በኋላ መጥቶ እርሱ የሆነውን ይወስዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቶስም ልክ እንደዚሁ ነው የሚናገረው።
መጣና መጽሐፉን ወሰደ፤ በዚያን ጊዜ ምልጃ ያቆማል። ከዙፋኑ ላይ ይነሳል። ከዚያ በኋላ በምሕረት ዙፋን ላይ ደም አይኖርም፤ ከዚያ ይህ ዙፋን ምን ዓይነት ዙፋን ነው የሚሆነው? የፍርድ ዙፋን።
የመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች ከተፈቱ በኋላም ኢየሱስ በዙፋኑ ላይ ነበረ። ወደፊት ከሆነ ጊዜ በኋላ ከዙፋኑ ይነሳል። ይህ የሚፈጸመው ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀችና የሙሽራይቱ አካላት የሆኑ አማኞች አዲሱን አካላቸውን ከለበሱ በኋላ ነው፤ ምክንያቱም በአዲሱ አካል ውስጥ ሲሆኑ ብቻ ነው ማሕተሞቹ ሲፈቱ ቆመው ማየት የሚችሉት።
ወደፊት የሚሆነውን በሚያሳይ ራዕይ ውስጥ ኢየሱ ከዙፋን ተነስቷል። በአሁኑ ዘመን እውነታ ውስጥ በአዳኝነቱ እስካሁን ዙፋኑ ላይ ነው።
65-1127B የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
ስጋዊ አካሉ ተነስቶ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ሄዷል፡ ያም መንፈስ የነበረበት ዙፋን ነው፤
አሁን ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው በዙፋኑ የተቀመጠው።
በወንድም ብራንሐም የአገልግሎት የመጨረሻ ዓመት 1965 ድረስ ኢየሱስ በዙፋኑ ላይ ነበረ።
ስለዚህ ማርች 1963 ወንድም ብራንሐም የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት መገለጥ ያመጣበት ጊዜ ነበር፤ በዚያ ዓመት በሰማይ ማሕተሞቹ አልተፈቱም ምክንያቱም ከዚያ ዓመት በኋላ በ1965 መጨረሻ እንኳ ኢየሱስ በዙፋኑ ላይ ነበረ።
ሰባቱ ማሕተሞች እውን የሚፈቱት ክርስቶስ ከምሕረት ዙፋን ላይ ሲነሳ ብቻ ነው።
ኖቬምበር 1965 ድረስ በዙፋኑ ላይ ስለነበረ ማርች 1963 ከዙፋኑ አለመነሳቱ ግልጽ ነው።
63-1110M አሁን በወኅኒ ያሉ ነፍሳት
እርሱ የሞተለት ሁሉ መጽሐፉ ውስጥ ተጽፏል፤ እርሱም ሙሉ በሙሉ እስኪቤዥ ድረስ ከአማላጅነት ዙፋኑ ላይ ሊነሳ አልቻለም። እርሱም በመስቀሉ ላይ ሆኖ ሊቤዥ አልቻለም ምክንያቱም እነርሱ በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ላይ አስቀድመው ተጽፈዋል፤ ስለዚህ እርሱም በዙፋኑ ተቀምጦ ያ የመጨረሻው ሰው ተዋጅቶ እስከሚያልቅ ድረስ ይቆያል። ክብር ለጌታ ይሁን!
… በዚያ መጽሐፍ ላይ ከተጻፉ ስሞች የመጨረሻው በተዋጀ ጊዜ በጉ መጣና መጽፉን ወሰደ፡- “ይህን ያደረግሁት እኔ ነኝ!”
ይህ የሆነው ስለ ማሕተሞቹ መፈታት በመገለጥ ከሰበከ በኋላ ነው። ንሰሃ ሳትገቡ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሳትጠመቁ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሳትሞሉ ልትዋጁና የሙሽራይቱ አካል ልትሆኑ አትችሉም፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው የዘመን መጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን እምነት ወደምትመለስበት ወደ ሙሉው እውነት ሊመራችሁ የሚችለው።
ይህም ለመጨረሻው የሙሽራይቱ አካል በተፈጸመ ጊዜ ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ መነሳት ይችላል።
በዚያ ጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚሰብኩ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች አይኖሩም፤ ስለዚህ ኢየሱስ በሜሴጅ ቤተክርስቲያን ውስጥ ወዳሉ አማኞች መድረስ አይችልም፤ ምክንያቱም እነርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ቤተክርስቲያኖቻቸውንና ፓስተራቸውን ይወዳሉ።
አሁንም ሰዎች ወደፊት የሚሆነው ክስተት በመገለጥ ሲሰበክ እራሱ ክስተቱ መፈጸሙ ነው ብለው ይሳሳታሉ።
ኢየሱስ የምሕረት ዙፋንን ለ50 ዓመታት ሁሉ ትቶ መቆየት አይችልም። የመጨረሻው ነፍስ ለንጥቀት ዝግጁ እስኪሆን ድረስ በምሕረት ዙፋኑ ላይ መቆየት አለበት።
የዚህ ትምሕርት 3ኛው ችግሩ ማሕተሞቹ ተፈተዋል ማለቱ ነው፤ ማሕተሞቹ ተፈተው ቢሆን ኖሩ ታላቅ የነጎድጓድ ድምጽ ከሰማይ በመጣ ነበር (ከዚህ ከፍጥረታዊው ሰማይ ላይ)፤ ይህን በተመለከተ ወንድም ብራንሐም ሲናገር ሁልጊዜ ወደፊት እንደሚሆን አድርጎ ነው የተናገረው።
ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማሕተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፣ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጎድጓድ በሚመስል ድምጽ፡- መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ ከሰማይ የነጎድጓድ ፍንዳታ ድምጽ ነበረ።
ወንድም ብራንሐም ግን ገና ወደፊት ስለሚመጣ የነጎድጓድ ፍንዳታ ድምጽ ነው ሲናገር የነበረው። ማሕተሞቹ ተፈተው አልፈው ከሆነ ያ አንድ ነጎድጓድ ወደፊት ድምጹን ሊያሰማ አይችልም። ሰባቱ መልእክት በ1963 ወደ ወንድም ብራንሐም በመጡ ጊዜ የነጎድጓድ ድምጽ ተሰምቶ ነበር (ይህም የሆነው ማሕተሞቹን በራዕይ ለመፍታት ነው)። ነገር ግን እርሱ ገና ወደፊት ሊመጣ ስላለ የነጎድጓድ ድምጽ ይናገር ነበር (ይህም ማሕተሞቹ እውን ሲፈቱ የሚሆን ነው)።
65-0822M ክርስቶስ በራሱ ቃል ውስጥ ይገለጣል
የዚያን ጊዜ ያ ሰው እና እነዚያም ሰዎች ምን ሲያልሙ እንደነበር ታውቃላችሁ፤ እነዚህም ነገሮች ሁሉ ይፈጸማሉ፤ አያችሁ፤ የተገለጡት ነገሮች ምን እንደሆኑ ታስተውላላችሁ፤ እነዚያ ታላላቅ ነጎድጓዶች ከሰማይ ሲመጡ። ለነገሩ ሁላችሁም ይህ ምን ማለት እንደሆነ እንደማውቅ ታውቃላችሁ። ነገር ግን ጊዜው እስኪደርስ እንጠብቅ፤ በተፈጸመም ጊዜ በራሱ ጊዜ ሲሆን ይበልጥ የተሻለ ይሆናል።
1965. በአገልግሎቱ የመጨረሻ ዓመት ላይ ወደፊት ከሰማያት ስለሚመጣው ስለዚያ ታላቅ ነጎድጓድ ሲናገር ነበር።
“መስማነትን ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች፤” ኖቬምበር 27 ቀን 1965 የቀረበ ስብከት
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ይህ ኖቨምበር 1965 ሲሆን ጊዜው እርሱ ሰባቱን ማሕተሞች ከገለጠ ረጅም ጊዜ አልፎ ነው፤ በዚህም ጊዜ እንኳ ገና ወደፊት ሊመጣ ስላለው አንድ ነጎድጓድ ይናገር ነበር። ይህም ከትንሳኤ ጋር የተያያዘ አንድ ነጠላ ነጎድጓድ ነው።
“ንጥቀት፤” ዲሴምበር 4 ቀን 1965 የቀረበ ስብከት
አንድ ቀን ከሰማይ ታላቅ ድምጽ ይመጣል፤ “በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ቀድመው ይነሳሉ።”
ከመሞቱ በፊት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ጊዜ ስለዚህ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ገና ወደፊት እንደሚመጣ ነው የተናገረው።
ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል የሚለው የዚህ ትምሕርት ችግር ቁጥር 4 ሰባተኛውን ማሕተም እና ስድስተኛውን ማሕተም በትክክል ተረድተን እናውቃለን፤ የመጽሐፍ ቅዱስንም ሚስጥራት በሙሉ እናውቃለን ማለቱ ነው። ነገር ግን አናውቅም።
1. ወንድም ብራንሐም ሰባተኛውን ማሕተም ፈትቼዋለው አላለም። ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው ብሎ ነው የተናገረው።
2. ወንድም ብራንሐም ሁለቱ የእስራኤል ነብያት ስድስተኛውን ማሕተም ይፈታሉ ብሎ ነው የተናገረው።
3. ድግሞም ሰባቱን መለከቶችም መግለጥ አልችልም ብሎ ተናግሯል፤ ምክንያቱም ሰባቱ መለከቶች ድምጻቸው የተሰማው በስድስተኛው ማሕተም ስር ነው፤ ደግሞም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ እስራኤልን ብቻ የሚመለከቱ እናጂ ሙሽራይቱን የሚመለከቱ አይደሉም።
4. ወንድም ብራንሐም ሰባቱ ነጎድጓዶች ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆናቸውን ነው የተናገረው፤ ምክንያቱም ነጎድጓዶቹ የተናገሩት ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም።
5. የኢየሱስን አዲስ ስም አላውቅም ብሏል።
6.
1965 የፊልድልፍያ ቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ - ምዕራፍ 8
አዲሱን ስሜን እጽፍበታለሁ።” አዲሱ ስሜ። ሁሉ አዲስ በሚሆንበት ጊዜ እርሱም አዲስ ስም ለራሱ ይወስዳል፤ ያ ስም ደግሞ የሙሽራይቱም ስም ይሆናል። ያ ስም ማን እንደሆነ ማንም ሊገምት አይድፈር። ማንም ሊክደው እንዳይችል በመንፈስ የሚሰጥ መገለጥ መሆን አለበት። ያለ ምንም ጥርጥር እርሱ ይህንን ስም ሊገልጥ እስከወሰነበት ቀን ድረስ ይጠብቃል። ለጊዜው መገመት ከምንችለው በላይ እጅግ አስደናቂ ይሆናል ብለን ማረፍ ይሻለናል።
ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ያልገለጣቸው ሚስጥራት እነዚህ ናቸው።
ከዚህም የተነሳ “ሚስጥራትን ሁሉ እናውቃለን” ማለት አንችልም።
ታድያ እርሱ የገለጣቸውና ልናውቃቸው የምንችለው ሚስጥራት የትኞቹ ናቸው?
1. ወደ ኋላ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ እንችል ዘንድ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የጠፉትን “ሚስጥራት በሙሉ” ገልጧል። በመከር የሚታጨደው ፍሬ መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር ፍጹም መመሳሰል አለበት።
2. ለጌታ ዳግም ምጻት ለመዘጋጀት ይረዱን ዘንድ ማወቅ የሚያስፈልጉንን ሚስጥራት ሁሉ ገልጧል። ከመጀመሪያው ሰዓት ጀምሮ ከሰራው ሰራተኛ እኩል ክፍያ የተሰጣቸው የአስራ አንደኛው ሰዓት ሰራተኞች ምሳሌ። ለዚህ ነው ኢየሱስ መጀሪያውም መጨረሻውም የሆነው፤ አልፋ እና ኦሜጋ። የመጀመሪያው ዘመን እና የመጨረሻው ዘመን አንድ ዓይነት መሆን አለባቸው።
እስቲ ቀጥለን የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት እንመልከት።
ብዙ ጥቅሶች “ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል” ይላሉ።
ስለዚህ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ሁሉን ነገር የምናውቅና የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በሙሉ የምናውቅ ይመስላል።
63-0728 ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሚስጥር መገለጥ ነው
እርሱም ወደ ኋላ ተመልሶ እነዚህ ሰዎች ትተው የሄዱትን በመጨረሻው ቀን ያነሳል፤ በቅዱስ መንፈሱም አማካኝነት የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር ይገልጣል።
63-1229E ወደ ኢየሱስ ተመልከቱ
ደግሞም ሰባቱን ማሕተሞችም ይፈታቸዋል፤ ሚስጥሩንም መልሶ ያመጣዋል፤ ከዚያም ከዘመን መጀመሪያ ጀምሮ የተሰወረውን የእግዚአብሔርን ነገር ይገልጠዋል።
64-0726M ዘመናችሁንና መልእክቱን ማስተዋል
ማሕተሞቹ ተከፍተዋል። ለእኛ ተገልጦልናል።
ስለዚህ ሰባቱም ማሕተሞች በሙሉ የተፈቱ ይመስላል። ይህም ትክክለኛ ድምዳሜ ይመስላል።
ይህ ከሆነ ግን ያለ ምንም መረዳት ጥቅሶችን እንደ ገደል ማሚቶ እየደገምን ነን ማለት ይሆን?
መንግስተ ሰማይ ውስጥ ምንም የገደል ማሚቶ እንዳልተጠቀሰ ልብ በሉ።
ስለዚህ እስቲ ጥቂት ተጨማሪ ጥቅሶች እንመልከት።
በድንገትና ማንም ሰው ባልጠበቀበት ሰዓት ሰባተኛው ማሕተም አለመከፈቱን ይናገራል።
64-0719M የመለከት በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።
ጌታ ገና ስላልመጣ ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም።
ሰባተኛው ማሕተም የጌታን ምጻት ነው የሚገልጠው። ስለ ጌታ ምጻትም አንዳች የምናውቀው ነገር የለም። ስለዚህ የምናውቀው ነገር ቢኖር ሰባተኛው መለከት ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዘ መሆኑን ብቻ ነው። ነገር ግን የጌታ ምጻት ደግሞ የዓለም ሁሉ ታላቅ ሚስጥር ነው፤ ስለዚህ ስለ ጌታ ምጻት ምንም ነገር አናውቅም።
ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም እንኳን በዕውን ይቅርና በመገለጥም አልተፈታም።
ሚስጥር ሆኖ የታተመ ነገርና ያልተገለጠ ነገርን አውቃለው ማለት አትችሉም።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
አሁን ተመልከቱ፤ በዚህ በሰባተኛው ማሕተም መከፈት ሰዓት የሆነውን አስተውላችሁ እንደሆን ሶስት ድርብ ሚስጥር ነው። ይህ እኔ ያለኝ … ይናገራል፤ ደግሞም ተናግሯል፤ እርሱም የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥረ ነው። በሰማይ ያሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን ሚስጥር ይገልጡታል። እርሱም ልክ በክርስቶስ ምጻት ጊዜ ይሆናል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም ብሎ ተናግሯል …
የሰባተኛው ማሕተም በዕውን መፈታት ሚስጥር ነው። ሰባተኛውን ማሕተም ለመፍታት መሞከር ሌሎች ሶስት ሚስጥራትን ያካትታል። ለዚህ ነው ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ የማይችለው። ሰባተኛው ማሕተም ከመፈታቱ በፊት መፈታት ያለበት አንዱ ሚስጥር የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥር ነው።
62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ድምጹ የት እንደነበረ ተመልከቱ፤ መብረቁ ባለበት። በሰማይ አይደለም፤ በምድር ነው! ነጎድጓዶቹ ከሰማይ አልተናገሩም። የተናገሩት ከምድር ነው።
አንድ ጥቅስ ሰባቱ ነጎድጓዶች በሰማይ ነው ያሉት ይላል፤ ሌላ ጥቅስ ደግሞ ከምድር ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት ይላል። ስለዚህ ይህ በቀላሉ ልንረዳው የማንችለው ርዕስ ነው። ጥቅስን ይዞ መደጋገም መረዳትን አያመጣልንም። ሰባቱ ነጎድጓዶች የሙታን ትንሳኤ እስኪፈጸም ድረስ ባንነካካው የሚሻል ሚስጥር ነው። ከዚያ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ይናገራሉ።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
በዚይም ክፍል ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚመጣው መገለጥ (እንደ ሌሎቹ ሁሉ) እንደ ሌሎቹ … ከዚያ ማሕተም [ ሰባተኛው ] ሚስጥራት አንዱ፤ ያልተገለጠበት ምክንያት ድምጻቸውን ያሰሙት ሰባቱ ነጎድጓዶች ስለሆኑና ምንም እንከን በሌለበት መንገድ ስለተናገሩና ማንም ስለነሱ ስለማያውቅ ነው፤ ደግሞ ምን እንደተናገሩም አልተጻፈም።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ ስላልተጻፈልን ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደተናገሩ በፍጹም ልናውቅ አንችልም። የሰባቱ ነጎድጓዶች ዓላማ ጌታ በሚመጣ ጊዜ ሙሽራይቱ እንድትነጠቅ ሊያዘጋጁዋት መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደሆኑ፣ ምን እንደሚሰሩ ወይም ምን እንደተናገሩ አንዳችም የምናውቀው ነገር የለም።
ከዚህ [ ሰባተኛው ] ማሕተም በታች የተሰወረው ይህ ሚስጥር ምን እንደሆነ እኔ አላውቅም። አላውቀውም። ላየውም አልቻልኩ፤ ምን እንደሆነና ምን እንደሚል አላውቅም። ነገር ግን እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ተከታትለው ድምጻቸውን እንዳሰሙ አውቃለው። ሰባት ጊዜ የተለያዩ መልእክቶችን በድምጻቸው አሰምተዋል፤ ይህም አንድ ያየሁትን ነገር ሆኖ ተገለጠ።
ከዚያ እኔም ባየሁት ጊዜ በዚያ ያለፈውን ትርጓሜውን ፈለግሁ፤ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም።
… ሳቢኖ ኬንዮን ውስጥ እንዲህ አለ፡- “ይህ ሶስተኛው መልእከት ነው።” ደግሞም አብረውት የሚሄዱ ሶስት ትልልቅ ነገሮች አሉ፤ ከነዚህም አንዱ ዛሬ ተገልጧል፣ ወይም ትናንት፤ ሌላኛው ዛሬ ተገለጠ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አለ፤ እርሱንም ልተረጉመው አልችልም ምክንያቱም በማይታወቅ ቋንቋ ነው የተነገረው።
የሰባተኛው ማሕተም መፈታት እጅግ ውስብስብ ስለሆነ ከእኛ አእምሮ በላይ ነው። ሰባተኛው ማሕተም ከሰባቱ ነጎድጓዶች ጋር የተያያዘ ነው፤ ሰባቱ ነጎድጓዶችም ስላልተጻፉ በወንድም ብራንሐም አማካኝነት ሊገለጡ አይችሉም። ሰባቱ ነጎድጓዶች በውስጣቸው በማይታወቅ ቋንቋ የተነገረ መልእክት አለ፤ ይህም ከአእምሮዋችን በላይ ነው። ከራዕዩ ውስጥ ይህንን ክፍል መረዳት አይቻለም።
ሶስተኛውም መልእክት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። የሜሴጅ አማኞች ሶስተኛውን መልእክት የተረዱ ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን ወንድም ብራንሐም ማንም ሊያውቀው አይልም ብሏል። ስለዚህ ለመረዳት በመሞከር ጊዜያችንን ማቃጠል የለብንም።
62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልከት ነውን
ከዚያም እንዲህ አለ፡- “እንግዲህ ሶስተኛ ነገር ይመጣል፤ ነገር ግን ምን እንደሆነ ለማብራራት አትሞክሩ።”
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
ወደዚያ ወደላይ በወሰደኝ ጊዜ ምን እንዳለኝ ታስታውሳላችሁ፡- “ይህ ሶስተኛው ነገር ነው፤ እርሱንም ማንም አያውቀውም።” ይህን ታስታውሳላችሁ? ራዕዮች በፍጹም አይሻሩም። ፍጹም የሆኑ እውነቶች ናቸው።
ስለዚህ ሶስተኛውን መልእክት ማስረዳት ይቅርና መረዳትም አንችልም፤ አብረውት ያሉትን ሶስቱን ሚስጥራትማ እንኳን መረዳት ቀርቶ ስለ መረዳት ልናስብም አንችልም፤ እነዚህም የሰባተኛው ማሕተም መፈታት የሚመለከቱ ሶስጥ እጥፍ ድርብ ሚስጥራት ናቸው።
ስለዚህ ሰባተኛውን ማሕተም ለመረዳት መሞከሩ ቢቀርብን ይሻላል። ደካማው አእምሮዋችን ሰባተኛውን ማሕተም ለመረዳት ብቁ አይደለም። ነገር ግን አስተዋዮች መስለን ለመታየት ስንፈልግ ትዕቢት በተሞላው ልባችን ተነስተን ሰባተኛውን ማሕተም ለመተርጎም ያልሆነ ነገር በመናገር ሙከራ ልናደርግ እንችላለን።
… ስለዚህ አስታውሱ፤ ሰባተኛው ማሕተም ያልተከፈተበት ምክንያት (አያችሁ?) ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ማንም ሊያውቀው ስለማይገባ ነው።
… ደግሞም ስድስቱንም ማሕተሞች ገልጧቸዋል፤ ነገር ግን ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አይናገርም። የመጨረሻው ዘመን ማሕተም መከፈት ሲጀምር መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው የሚሆነው። ያንን ከማወቃችን በፊት … ደግሞ አስታውሱ፤ ራዕይ 10፡1-7 በሰባተኛው መልአክ መልእክት መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ሚስጥሮች በሙሉ ይታወቃሉ። እኛ አሁን የምንኖረው በመጨረሻው ዘመን ነው፤ እርሱም ሰባተኛው ማሕተም የሚከፈትበት ዘመን ነው።
1. ስለዚህ አንድ ችግር ያጋጥመናል። ስድስት ማሕተሞች ተገልጠዋል፤ ሰባተኛው ግን አልተገለጠም።
2. “ሚስጥራትን በሙሉ” ሊገልጥ የመጣው ሰባተኛው መልአክ ሰባተኛውን ማሕተም አልገለጥኩም ብሏል። ታድያ “ሚስጥራትን ሁሉ” ሲል ምን ማለቱ ነው?
65-0822 ክርስቶስ በራሱ ቃል ውስጥ ይገለጣል
ሰዎች ከኖሩባቸው ዘመናት መካከል ከሁሉ ይልቅ በሚያስፈራው ዘመን ውስጥ እያለፍን ነን። እኔም ሁላችን ጊዜ አግኝተን የምንሰበሰብበትን ሰዓት እየተጠባበቅሁ ነኝ… ሁላችንም ዕድል አግኝተን፣ እናንተም ከሥራ እረፍት አግኝታችሁ በአንድ ሥፍራ ብንሰባሰብ የሆነ ቦታ ተሰብስበን ስለ መቅሰፍቶቹ እነግራችሁ ነበር እንዲሁም በመጨረሻዎቹ ቀናት ስለሚፈጸሙ ነገሮች እነግራችኋለው፤ ሁለት ወይም ሶስት ሳምንት ያህል ጊዜ ብናገኝ፣ ጌታም እኔ እንዳስተምር ቢፈቅድና በሕይወት ቢያቆየኝ እነዚያ ነገሮች እንዴት እንደሚገለጡ እነዚያ ነጎድጓዶች እንዴት እንደሚመጡ እናይ ነበር።
1966 - በአገልግሎቱ የመጨረሻ ዓመት ላይ ሰባቱን ነጎድጓዶችና ሰባቱን መቅሰፍቶች ከሰባቱ ጽዋዎች ሊገልጥ ሲጠባበቅ ነበር።
ስለዚህ እነዚህን ሁለት ርዕሶች አልገለጣቸውም። ታድያ “ሁሉንም ሚስጥራት” ስለመግለጥ በተናገረ ጊዜ ምን ማለቱ ነው?
“ሚስጥራት ሁሉ” የሚለው ንግግር ሰባተኛውን ማሕተም፣ ሰባቱን የመቅሰፍት ጽዋዎች፣ እና ሰባቱን ነጎድጓዶች አያካትትም።
ወንድም ብራንሐም የስድስት ማሕተሞችን መገለጥ ተቀበለ። ስለዚህ የሚናገረው ስለ ስድስቱ ማሕተሞች ውስጥ ስላለው የእግዚአብሔር ሚስጥር ነው።
ሁለት ትልልቅ ጉዳዮች፡-
1. ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም የማያውቅ ከሆነ እንዲሁም ስለ ባለ ስድስት ማሕተሙ የእግዚአብሔር ሚስጥር የሚናገር ከሆነ ሰባቱ ማሕተሞች እንዴት የዕውን ሊፈቱ ይችላሉ?
2. ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውን ማሕተም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ሁለቱ የአይሁድ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው የሚፈቷቸው ብሎ ከናገረ ሰባቱ ማሕተሞች እንዴት ዕውን ሊፈቱ ይችላሉ?
63-0803E ተጽእኖ
በሰማይ ታላላቅ ምልክቶች፤ መላእክት እንደ ከዋክብት በዝተው ሲመጡ! ሳይንቲስቶችም ቀና ብለው ሲመለከቱ፤ ነገር ግን ከመፈጸሙ ወራት አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር። ይኸው። መጽሔት ላይ ታትሞ ማየት ይቻላል። ነገር ግን ከመፈጸሙ ወራት አስቀድሞ ተነግሯል። ሰባት መላእክት ወረዱና እንዲህ አሉ፡- “ባለ ስድስት ማሕተሙ የእግዚአብሔር ሙሉ ሚስጥር ይገለጣል።” ያው ልክ እንደተናገረው አስቀድሞ ከመሆኑ በፊት እንደተነበየው ተፈጽሟል።
በሰባቱ መላእክት አማካኝነት የተፈጠረው፣ ዶ/ር ጄምስ ማክዶናልድ በተባለው ሳይንቲስት ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ፎቶግራፍ የተነሳውና በላይፍ መጽሔት ሽፋን ላይ የታተመው ታላቁ ደመና “በሰማይ ላይ የታየ ታላቅ ምልክት” መባሉን አስተውሉ።
የመላእክቱ ደመና የኢየሱስ ምጻት ነው አልተባለም፤ ደግሞም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ነውም አልተባለም። እንዲሁ በሰማይ የታየ ታላቅ ምልክት ብቻ ነው የተባለው (ሰማይ ማለት ከጭንቅላታችን በላይ የምናየው ፍጥረታዊ ሰማይ ነው)።
ኢዩኤል 2፡30 በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።
ታክሰን አሪዞና አጠገብ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም ፎቶግራፍ የተነሳው አንድ ደመና ብቻ አልነበረም።
ፌብሩዋሪ 29 ቀን 1963 በመካከላቸው በ20 ማይልስ ርቀትና ከምድር ደግሞ 43 ኪሎ ሜትር ከፍ ብለው ሲንሳፈፉ የነበሩ ፎቶግራፍ የተነሱ ሁለት ደመናዎች ናቸው የነበሩት። ለዚህ ነው ጄምስ ማክዶናልድ የተባለው ሳይንቲስት ትልቁ ደመና ከየት እንደመጣ ማብራራት ያቃተው። በተለይም ደግሞ አየር ኃይል በዚያ ከፍታ ላይ ሮኬት አፈንድቶ እንደማያውቅ መናገሩ ነገሩን ይበልጥ አወሳስቦታል። ሁለት ደመናዎች ያን በሚያህል ከፍታ ላይ እንዴት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ አንዳችም ተፈጥሮአዊ ማብራሪያ አልተገኘም፤ ይልቁንም ደግሞ ታናሹን ደመና ምን እንዳመጣው ባለማወቁ ምን መሆኑን መግለጥ አልቻለም።
ቆይተው አየር ኃይሎች ሚስጥራዊ ከሆነው ፖይንት ሙጉ ከተባለው በቫንደንበር የካሊፎርኒያ ጠረፍ ከሚገኘው አየር ጣቢያቸው የተወነጨፈ ሮኬት ብዙ ጠጣር ነዳጅ ይዞ ከመስመር በመውጣቱ ሆን ተብሎ 43 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ እንዲፈነዳ መደረጉንና ሁለት የጭስ አምዶች መፍጠሩን ቆይተው ይፋ አድርገዋል። እነዚህ ከከባቢ አየራችን በላይ ከፍ ያሉ የነፋስ ሞገዶች ምን እንደሆኑ መረዳት አንችልም። ከደመናዎች ሁሉ በላይ ከፍ ብለው የሚንሳፈፉ ደመናዎች በክረምት ዋልታዎች አካባቢ በ25 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ የሚንሳፈፉ ናክሪየስ የተባሉ ደመናዎች ናቸው። ደመናዎችን የሚፈጥረው የውሃ ትነት 99 በመቶው የሚገኘው ከ20 ኪሎ ሜትር ከፍታ በታች ነው። ስለዚህ ሮኬት በድንገት ማፈንዳት ከዚህ የውሃ ትነት ከማይደርስበትና ደመና ከማይፈጠርበት ከፍታ በላይ የሚታይ የጭስ ደመና እና ስበርባሪ እንዲፈጠር ማድረጊያ ብቸኛው መንገድ ነው።
በዚህ የሮኬት ፍንዳት ሳይንስ የመጀመሪያውን ደመና ፈጠረ፤ ነገር ግን ከዚህ ሰው ሰራሽ የጭስ አምድና ደመና ፊት ለፊት በሃይ ማይልስ ርቀት ተለቅ ያለ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና በሰባት መላእክት አማካኝነት ተፈጠረ። በሮኬት ፍንዳታ የተፈጠረው የመጀመሪያው ደመና በዚያ ከፍታ ላይ በነበረው ውስብስብ የነፋሳት ሞገድ ወዲያው ተበታትኖ ጠፋ። ነገር ግን ሁለተኛው ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና አልጠፋም።
ከሮኬቱ ፍንዳታ የተፈጠረው ሰው ሰራሹ የጭስ አምድ እንዲሁም ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና የፈጠሩት ሰባቱ መላእክት ስለ ሁለቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል። ከዚህም የተነሳ የደመናዎቹ መፈጠር ትልቅ ክስተት ነው። በእነዚህ ደመናዎች አማካኝነት እግዚአብሔር የሰዎችን ትኩረት ወደ ቃሉ እየሳበ ነው።
ኢዩኤል 2፡30 በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።
ከሁለቱ ደመናዎች ትንሹ ደመና በጢስ ጭጋግ ነው የተፈጠረው።
65-0718M የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። ዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል። እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የምድር መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማያት ላይ ይታያል። ”
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
ታላቁ ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወደ ምድር መውረድ አልነበረም፤ ከዚያ ይልቅ በሰማያት የተገለጠ የሰው ልጅ ምልክት ነበር። ታክሰን አጠገብ በበረሃው ላይ በ43 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ እየተንሳፈፈ አለፈ እንጂ ወደ ምድር አልወረደም።
64-0112 ሻሎም
ነገር ግን ሰባቱ ማሕተሞች ከመገጣቸው በፊት፣ እዚህ ታክሰን ፍላግስታፍ እኛ በምንኖርበት ከተማ ሰማይ ላይ ያ ታላቅ ምስጢራዊ ብርሃን ከመታየቱ በፊት … ከዚያም በኋላ ደግሞ ሌላ መልአክ ሲወርድ አየ፣ እርሱም እዚህ መልእክት የተሰጠው ምድራዊው መልአክ አይደለም፤ ነገር ግን (ሌላ) ብርቱ መልአክ ከራሱ በላይ ቀስተደመና ያለው መልአክ መጣና እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ አሳረፈ፤ ለዘላለም በሚኖረውም ምሎ እንዲህ አለ፡- “ከዚህ በኋላ ዘመን አይኖርም።” አያችሁ? ነገር ግን እነዚያን ሰባት ማሕተሞች ሊገልጣቸው ከመክፈቱ በፊት ተዓምራዊ መሆናቸውን ሊያሳይ መጀመሪያ በሰማያት ገለጣቸው።
በዚያ ቀን በደቡባዊ ዩናይትድ እስቴትስ እና ሜክሲኮ ውስጥ ፎቶ ሲያነሱ ነበር። ፎቶግራፉም እስካሁን ላይፍ መጽሔት ውስጥ አለ፤ ምን ማለት እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል። እርሱ ግም በምድር ሳይፈጽመው በፊት በሰማይ ያውጀዋል። ይህን ሁልጊዜ ነው የሚያደርገው። በመጀመሪያ ምልክቶቹን በሰማይ ያሳያል።
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የታየው ደመና በሰማያት ላይ የተገለጠ ምልክት ነው።
ደመናው በ43 ኪሎ ሜትር ከምድር ወደ ላይ በጣም ከፍ ከማለቱ የተነሳ ፀሃይ ከተራሮች ኋላ ከጠለቀች በኋላ እንኳ የፀሃይን ብርሃን ያንጸባርቅ ነበር። ስለዚህ ሌሎች ደመናዎች ሁሉ በጨለማ ከጠቆሩ በኋላ እንኳ ይህኛው ደመና ግን የፀሃይዋን ብርሃን ያንጸባርቅ ነበር። በዚህም ምክንያት ደመናው ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ በሰማይ ከፍታ ላይ የሚያበራ ብርሃን ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ይህ ደመና የታየው ማርች 1 ቀን 1963 የአደን ወቅት ከመከፈቱ አንድ ቀን አስቀድሞ እና ሰባቱ መላእክት ወንድም ብራንሐምን ሊጎበኙ ከመምጣታቸው አንድ ሳምንት አስቀድሞ ነው። በዚያ ጊዜ ወንድም ብራንሐም ከማርች 5 ቀን 1963 እስከ ማርች 10 ቀን 1963 ድረስ ለአደን ወጥቶ ነበር። ሰባቱ መላእክት እንዲሄድና ሰባቱን ማሕተሞች እንዲገልጥ ነገሩት። ማርች 4 ቀን 1963 ወንድም ብራንሐም ሂውስተን ውስጥ ሲሰብክ ነበር። ከዚያ በኋላ ለአደን ወጣ። እርሱ ማሕተሞቹን መግለጡን ማርች 24 ቀን 1963 ከጨረሰ በኋላ ብቻ ነው መጽሐፉ ተከፍቷል ሊባል የሚችለው፤ ደግሞም መጽሐፉ ከተከፈተ በኋላ ብቻ ነው የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ የተከፈተውን መጽሐፍ በእጁ ይዞ ወደ ምድር ሊወርድ የሚችለው።
ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
መልአኩ የተከፈተ መጽሐፍ ነው የያዘው። ስለዚህ ማሕተሞቹ ሁሉ ከተፈቱ በኋላ ነው ወደ ምድር ሊወርድ የሚችለው። መልአኩ መጽሐፉን ሊከፍት አይደለም ወደ ምድር የሚወርደው። ወደ ምድር የሚወርደው መጽሐፉ ከተከፈተ በኋላ ብቻ ነው።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ሌላም ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፣ እርሱም ደመናን ተጎናጽፎ ነበር፡ … በእጁም ትንሽ የተከፈተ መጽሐፍ ይዞ ነበር (አሁን እዚህ እንደምናየው ማሕተሞቹ ተፈተዋል። አሁን ማሕተሞቹን እየፈታናቸው ነን፤ ይህ ነገር ግን ተፈቷል።) … እርሱም ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ አደረገ፤ ግራ እግሩንም በምድር ላይ አደረገ።
ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን በመፍታት ተጠምዶ ነበር። መልአኩ ወደ ምድር በሚወርድበት ጊዜ ማሕተሞቹ በሙሉ ተፈተዋል።
ስለ ማሕተሞቹ ከመሰበኩ በፊት በሰማይ ላይ በደመና የታዩት ሰባቱ መላእክት ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጠቀሰው ማሕተሞቹ ከተፈቱ በኋላ ወደ ምድር ይወርዳል የተባለለት አንድ መልአክ ነው ብሎ መናገር ትልቅ ስሕተት ነው።
64-0719M የመለከት በዓል
አስታውሱ መለከቶች ሁሉ ድምጻቸውን የሚያሰሙት በዚህ በስድስተኛው ማሕተም ነው። ስድስተኛው ማሕተም ሚስጥሩን ሁሉ ይጨርሳል፤ በስድስተኛው ማሕተም ስር ልክ ሰባተኛው ከመከፈቱ በፊት።
ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም በሚስጥር የተሞላ ነው እኛም ልንፈታው አንችልም።
ስለዚህ ሚስጥራቱ የተገለጡት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች ነው።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
ይህን ታላቅ ክስተት በተመለከተ የሚናገሩ፤ በቤዛነት መጽሐፍ ስድስተኛ ማሕተም ስር ስላለው ስለዚህ ታላቅ ሚስጥር የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን አነጻጽሩ።
ደግሞ ልብ በሉ፤ እነዚህ የተሰወሩ ሚስጥራት ናቸው። ስድስተኛው ማሕተም ደግሞ ራሱን የቻለ አንድ ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ማለትም ስድስት ጥቅልሎች በአንድ ላይ ሆነው ነው፤ ሲፈታም የቤዛነትን መጽሐፍ በሙሉ ይገልጠዋል። ምድር በሙሉ የተዋጀችው እንዲህ ነው።
ስድስተኛው ማሕተም በተፈታበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር ሙሉ በሙሉ ታውቋል።
64-0816 ቃሉን መፈተን
ሰባተኛው መልአክ የተላከው ባለ ስድስት ማሕተሙን መጽሐፍ ለመክፈት ነው
65-1125 የክርስቶስ ሙሽራ ስውር አንድነት
እግዚአብሔር በዚህ ሳይንሳዊ ዘመን ሁሉም እንዲሞት አደረገ፤ ስለዚህ ምን ሊያደርግ ይችላል? ባለ ሰባት ማሕተሙን ሚስጥር ከዲኖሚኔሽን ውጭ ለሆነችዋ ሙሽራ ይከፍተዋል።
ባለ ሰባት ማሕተም ሚስጥር ካለ እንዴት ሙሉ በሙሉ የተፈታ ባለ ስድስት ማሕተም ሚስጥር እንዴት ሊኖር ይችላል? ይህ ሊሆን የሚችለው ሰባተኛው ማሕተም በጭራሽ ሊታወቅ የማይችል ፍጹም ሚስጥር ከሆነ ነው፤ ስለዚህ ስድስቱ ማሕተሞች ማወቅ የሚያስፈልጉንን ሚስጥራት በሙሉ ይገልጡልናል።
ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም ወንድም ብራንሐም የገለጣቸው ሚስጥራት አካል አይደለም። ለምንድነው ያልሆነው?
62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?
እነዚህ ማሕተሞች በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ነው ያሉት። “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን በሚያሰማበት ጊዜ በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት በሙሉ ይፈጸማሉ።”
ሰባተኛው መልአክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራትን ብቻ ነው መግለጥ የሚችለው።
ሰባተኛው ማሕተም ዝምታ ነው። ምንም አልተጻፈም። ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ሊገልጠው አይችልም።
64-0719M የመለከት በዓል
የሆነ ሰው እንዲህ አለ፡- “ወንድም ብራንሐም፤ መቸም ሰባቱ ማሕተሞች የሚገለጡት በመጨረሻው ቀን ነው፤ እንዴት ነው ወደ እግዚአብሔር የምንቀርበው፤ ትልቅ ሚስጥር አይደለምን?” በፍጹም፤ ሊሆን አይችልም።
“ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቃል የሚያጎድል ወይም አንድም ቃል የሚጨምርበት ሰው ቢኖር ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እድሉ ይጎድልበታል።” ይህ ምንድነው፤ እዚያ በፊት የጎደለውን ነገር የሚሞላ መገለጥ ነው። አስቀድሞ እዚህ ተጽፏል። እዚህ ውስጥ ነው ያለው። ስለዚህ አስቀድሞ የተጻፈውን ለመግለጥ ነው። አያችሁ? ምክንያቱም ከውስጡ አንድም ነገር ማጉደል አትችሉም፤ አንዳችም ልትጨምሩበት አትችሉም።
ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን መግለጥ ብቻ ነው የሚችለው። በአገልግሎቱ ላይ የተደረገው ገደብ ይህ ነው።
የእርሱ ሚስጥረ የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ ድሮ ይታወቁ የነበሩ ነገር ግን ኋላ የጠፉ አስተምሕሮዎችን መግለጥ ነው፤ እነዚህ አስተምሕሮዎች የጠፉት በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ክርስቲያኖች ሰዎችን እንደ መሪ ተቀብለው ከፍ ባደረጓቸውና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ከመከተል ፈቀቅ ባሉ ጊዜ ነው፤ በዚህም መንገድ ሰዎች ወደ ተደራጁ ሐይማኖታዊ ተቋማት እየተሳቡ በመሄድ የሰው ሰራሽ አመለካከቶችና የልማዶች እስረኛ ሆነው ቀሩ። መሪያቸውን በመጥቀስ ተጠመዱና መጽሐፍ ቅዱስን ጣሉት።
64-1221 ለምንድነው እረኞች የሆኑት
እነዚያ ሰባቱ ሚስጥራት … ባለፉት ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሰባት የተሰወሩ ሚስጥራት ነበሩ። ስለነዚህ ሚስጥራት መጽሐፍ እየጻፍኩ ነኝ። ከጥቂት ጊዜ በፊት አንድ ታላቅ የስነ መለኮት ምሑር እንዲህ አለኝ፡- “ወንድም ብራንሐም …” ሰይጣን እንዴት ከመንገድ ሊያስወጣችሁ እንደሚሞክር አያችሁ? እንዲህ አለ፡- “ወንድም ብራንሐም፣ ምን መሰለህ? ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብን ጌታ ይገልጥልሃል ብዬ አምናለሁ። እርሱም… ከነዚህ ሰባት ማሕተሞች ስር የተሰወረ ታላቅ ሚስጥር ነው።”
264 እኔም እንዲህ አልኩ፡- “የለም፤ ወንድሜ በፍጹም እንደዚያ አይደለም።”
265 እርሱም እንዲህ አለ፡- “ቃሉ ውስጥ እንኳ ያልተጻፈ የሆነ ነገር ነው የሚሆነው።”
266 እኔም እንዲህ አልኩ፡- “የለም! የለም! “ማንም ከዚህ ቢያጎድል ወይም ቢጨምርበት” የሚለውን ቃል ረስተሃል። አያችሁ፤ አስቀድሞ በቃሉ ውስጥ ተጽፏል፤ ነገር ግን የተሃድሶ መሪዎች አላዩትም፤ ማየት እስከሚችሉ ድረስ በቂ እድሜ አልኖሩም።”
64-0726M ዘመናችሁንና መልእክቱን ማስተዋል
እንደ ታረደ በግ የሆነው መጣ፤ እርሱም መጽፉን ወሰደ፤ ሊወስድ የተገባው ነበረና፤ ማሕተሞቹንም ፈታቸው። እኛም መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት ይገልጥልን ዘንድ ዛሬ እርሱን በተስፋ እየጠበቅነው ነን፤ ምክንያቱመ መጽሐፉ የቤዛነት መጽሐፍ ነው። የተዋጁ ሁሉ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈዋል።
65-1204 ንጥቀት
እነዚህም በዚያ መጽሐፍ ውስት የተጻፉት ሰባት ማሕተሞች ለሰዎች ሚስጥር ናቸው፤ በዚያ ቀን ሊገለጡ ይገባል። እርሱም ሊገልጥ ተስፋ ሰጥቷል። በተገለጠ ጊዜ አንዳችም ነገር ከቃሉ ውጭ አይመጣም፤ ምክንያቱም ቃሉ ላይ መጨመርም አይቻልም፤ ከቃሉ ማጉደልም አይቻልም። ሁልጊዜ ቃሉ ብቻ በቂ ነው። መገለጡ ግን በውስጡ የተሰወረውን እውነት ማውጣትና ከቀሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በትክክል እንዲገጥም ማድረግ ነው። እግዚአብሔርም ቃሉ እውነት መሆኑን ማረጋገጫ ይሰጣል። አያችሁ?
እውነትን የምታውቁት በምታጠኑት ርዕስ ላይ የተጻፉ የመጽፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በሙሉ አገናኝታችሁ ስታዩ ብቻ ነው።
ማንኛውም መገለጥ መመስረት ያለበት በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ምክንያቱም እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሚተረጎመው በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብቻ ነው። ስለዚህ የሰው ንግግር ጥቅስ አስፈላጊ አይደለም። ከሰው ንግግር ጥቅስ ሃሳቡን ማግኘት ትችላላችሁ ነገር ግን ሃሳቡ እውነት መሆኑን የምታረጋግጡት ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
64-0419 ፈተናው
“በዚያ ቀን ይህ መልአክ ድምጽ ሲያሰማ የእግዚአብሔር ሚስጥሮች በሙሉ ይገለጣሉ።”
የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ - ጴርጋሞን - ምዕራፍ 5 - ሽልማቶች
ነገር ግን እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ዘመን መገለጥን ይሰጥ ነበር፤ ይህም በራዕይ 10፡7 ውስጥ የተጻፈው የተሰወረው የመጨረሻው ቀን እስኪደርስ ድረስ፤ በዚያን ጊዜ ነብይ ይመጣል፤ ሚስጥራትን ሁሉ ይገልጣል፤ ከዚያም ጌታ ይመጣል።
ሚስጥራትን ሁሉ ይገልጣል? መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ሚስጥራትን በሙሉ እናውቃለንን?
በፍጹም አናውቅም። እውቀታችን ገደብ አለው። ስለዚህ የምናውቀውን አጥርተን አትኩረን እንወቅ።
65-0221 ይህ መልከጼዴቅ ማነው
ራዕይ 10፡1-7 መሰረት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት በሙሉ በተሃድሶ መሪዎች ዘመናት ውስጥ ተሰውረው የቆዩት ሚስጥራት ሁሉ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልአክ አማካኝነት ይገለጣሉ። ይህ ትክክል መሆኑን የምታውቁ ስንት ናችሁ? ትክክል ነው፤ ሚስጥራቱ ይገለጣሉ። የዚህ ሚስጥራዊ መጽሐፍ ሚስጥራት በሙሉ በሎዶቅያ ዘመን ለሚነሳው መልእክተኛ ይገለጣሉ።
የመጀመሪያው ገደባችን።
ማወቅ የምንችለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡2 መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉት ሚስጥራት የትኞቹ ናቸው?
1. ሰባቱ ነጎድጓዶች
ዮሐንስ እንዳይጽፋቸው ተነግሮታል።
ራዕይ 10፡4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።
2. የሰባተኛው ማሕተም መከፈት
ዝምታ ብቻ ነው የነበረው። ስለ ሰባተኛው ማሕተም የሚነግረን አንዳች ነገር አልተጻፈም።
ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።
3. የጌታ ምጻት
ይህ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ጌታ መች ነው የሚመጣው የሚለው ጥያቄ ማንኛውም አማኝ እንዲጠይቅ ያልተፈቀደለት ጥያቄ ነው።
የሐዋርያት ሥራ 1፡6 እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት።
7 እርሱም፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤
ማርቆስ 13፡32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።
ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ ሰው እንደመሆኑ አላወቀም። እኛም እርሱ ካወቀው የበለጠ ልናውቅ አንችልም።
4. የኢየሱስ አዲስ ስም
ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
ይህንን ስም ማንም ሊያውቅ አይችልም። ከተለወጣችሁና የማይሞት አካል ከለበሳችሁ በኋላ ብቻ ነው ልታውቁት የምትችሉት።
ሁለተኛው ገደብ
ሁለተኛው ውሱንነታችን ማወቅ የሚያስፈልገን ለጌታ ዳግም ምጻት ለመዘጋጀት የሚጠቅመንን ብቻ መሆኑ ነው።
እነዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን የምታውቃቸው ነገር ግን በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የጠፉ ሚስጥራት ናቸው።
65-0725M በዘመን መጨረሻ የተቀቡት
ሰባቱ ማሕተሞች “ሊፈጸሙ የሚገባቸው” ሚስጥራት ሲከፈቱ።
የሚፈጸሙት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት በሙሉ አይደሉም፤ ይልቁንም ሊፈጸሙ የሚገባቸው ብቻ እንጂ። የሚፈጸሙት ሚስጥራት ሙሽራይቱ ለኢየሱስ ዳግም ምጻት እንድትዘጋጅ የሚያስፈልጓት ብቻ ናቸው።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
63-1112 ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን
… አንድ ችግር አለ። ደግሞ ሁሉም ያውቀዋል። አንድ ትልቅ ነገር እንደተጋፈጥን አምናለው፤ ደግሞም ከፊታችን የተጋፈጥነው ታላቅ ነገር የጌታ ኢየሱስ ዳግም ምጻት መሆኑን በልቤ ሙሉ አምናለው። ደግሞም መንፈሱን በላያችን ላይ እንደሚያፈስስ አምናለው፤ ለምጻቱ እንድንዘጋጅ ማድረግ የሚያስፈልገንን ነገር ይገልጥልናል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
በጴንጤ ቆስጤያዊው ዘመን ማብቂያ ላይ ያልተቋጩ ነገሮችን ሁሉ የሚሰበስብ መልእክተኛ ልንቀበል ይገባናል … ያልተቋጩትን ነገሮች ሰብሰብ አድርጎ ቤተክርስቲያን ለመነጠቅ ትዘጋጅ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሚስጥራት በሙሉ ይገልጣል።
63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም
ከዘመናት በፊት ያለፉ ሚስጥራትን በሙሉ ይገልጣል፤ ሁሉንም ይገልጣል፤ ራዕይ 10፡1-7። ይህ ነው የሚሆነው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ብዙ እውነቶችን ታውቅ ነበር፤ እነዚህም እውነቶች ጠፉ። ስለዚህ እኛ የጥንቶቹ አማኞች ያውቁ ወደነበረው እውቀት መመለስ አለብን።
64-0119 ሻሎም
እነዚያ መላእክት አሁን በፍጥረታዊ ዓይናችሁ እንደምታዩኝ እዚህ ቆሙ፤ ወደ ቤቴ እንድመለስ ነገሩኝ፤ በዘመናት ውስጥ ያለፉት የተሃድሶ መሪዎች ሳያዩ ያለፉዋቸው ሚስጥራት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት፣ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ የተሰወሩት ሚስጥራት ይገለጣሉ አሉኝ።
ሰባቱ ማሕተሞች የሚገልጡት ሚስጥር በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሊታወቁ ይችሉ ነበር፤ ነገር ግን በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚስጥራቱ እውቀት ጠፋ።
ሶስተኛው ገደብ
ሶስተኛው ውስንነታችን በታላቁ መከራ ውስጥ ከእስራኤል ጋር የተያያዙትን ጠለቅ ያሉ ሚስጥራት ማወቅ የማያስፈልገን መሆኑ ነው። ስለዚህ እነዚያን ሚስጥራት አናውቃቸውም።
64-0726M ዘመናችሁንና መልእክቱን ማስተዋል
ከዚያም በኋላ ስለ ሰባቱ መለከቶች እንድሰብክ አልፈቀደልኝም። እኔስ ስለ ሰባቱ መለከቶች ልሰብክ ተዘጋጅቼ ነበር፤ አዳራሾችንና ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጅቼ ነበር … መንፈስ ቅዱስ ግን ለምን እንደሆነ በማላውቀው ምክንያት አልፈቀደልኝም።
… እኔም በትሕትና በእግዚአብሔረ ፊት ለጸሎት ተንበረከክሁ። እርሱም እነዚያ ሰባት መለከቶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት በስድስተኛው ማሕተም ስር መሆኑን ገለጠልኝ፤ እኔም ከዚያ ወዲያ በመለኮታዊ ኃይል ሰብኬዋለው። አያችሁ፤ ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር እጅ ነው። ከእስራኤል ጋር የተገናኘ ነገር ነው፤ እኛም ከስድስተኛው ማሕተም ስር አገኘነው፤ ይህን የተረዳችሁ ሁሉ የአይሁዳውያን ስደት ምን እንደሚመስል አስቡ።
እኛ አሕዛቦች በታላቁ መከራ ውስጥ እስራኤል ጥቃት በሚሰነዘርባት ጊዜ፣ በምትሰደድበት ጊዜ እና ሁለቱ ነብያቶቿ ጥበቃ በሚያደርጉላት ጊዜ ስለሚፈጸሙ ነገሮች እውቀት አለን፤ ነገር ግን ዝርዝር እውቀት የለንም። ለምን?
ታላቁ መከራ እኛን አይመለከተንም፤ ስለዚህ ስለ ታላቁ መከራ በዝርዝር ማወቅ አስፈላጊያችን አይደለም። ከታላቁ መከራ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ነገሮች ሚስጥር ሆነው መቆየት አለባቸው፤ አለዚያ ሰይጣን የራሱን ሥራ ለመስራት እንዲመቸው ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል። እነዚህ ሚስጥራት ማለትም ሰባቱ መለከቶች እና ሰባቱ ጽዋዎች፣ እንዲሁም የዳንኤል ትንቢቶች ለምሳሌ ምዕራፍ 11 እና 12 እና ከሕዝቅኤል ትንቢቶች የተወሰኑት የሚገለጡት ታላቁ መከራ በምድር ላይ ሲጀምር ነው።
በብዙዎች ዘንድ በ1963 ስለ ታየው ታላቅ ደመና ትልቅ የተሳሳተ መረዳት አለ።
ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የታየው ታላቅ ደመና ማለቂያ የሌለው ስሕተትና ግራ መጋባት መንስኤ ሆኗል።
በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው “የሜሴጅ እምነት” ደመናው የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ወደ ምድር መውረድ ነው ይላል።
ይህ ሃሳብ ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ አርቀው የሚወስዱ ብዙ አመለካከቶችን ያስከትላል።
በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከዲኖሚኔሽናም ሆነ ከሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በር ውጭ መቆሙን አስታውሱ። ለምን? እምነታችንን የመሰረትነው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሳይሆን በሰዎች ጥቅስ ትርጓሜ ስለሆነ ነው። ይህም የሜሴጅ አማኞች አንዳንድ ጥቅሶች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉና ሌሎች ጥቅሶችን ቸል እንዲሉ አድርጓቸዋል።
ይህንን ብርቱ መልአክ በተመለከተ የተጻፉ ጥቂት ጥቅሶችን እንመልከት። ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጠቀሰው ይህ መልአክ ለምንድነው ወደ ምድር የሚወርደው?
1. ሙታንን ለማስነሳት።
2. ይህ መልአክ ወደ ምድር የሚወርደው በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያኖች የጠፉባቸውን ሚስጥራት ዊልያም ብራንሐም ከገለጠ በኋላ ነው።
3. ዘመንን ለማስቆም ነው የሚመጣው። ሰዓታችሁን ባያችሁና ቀን በቆጠራችሁ ጊዜ ሁሉ ይህ መልአክ እስካሁን እንዳልመጣ እየመሰከራችሁ ናችሁ።
63-0320 ሶስተኛው ማሕተም
ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ባሰማ ጊዜ ድምጹን በማሰማቱ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ይጠናቀቃሉ። ከዚያም ከተገለጠ በኋላ ብርቱው መልአክ ከሰማይ ይወርዳል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው (ይህ መልአክ በምድር ላይ የሚኖር መልእክተኛ እንደሆነ አስተውሉ)። ክርስቶስ ወደ ምድር ይወርዳል (ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ታዩታላችሁ)፤ ከዚያም አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን ደግሞ በባሕር ላይ ያኖራል፤ ከራሱ በላይ ቀስተደመና አለ፤ እግሮቹ -- እግሮቹ እንደ እሳት ወዘተ. ፤ እርሱም እጆቹን አንስቶ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖው ምሎ ከዚያ ወዲያ ጊዜ እንደማይኖር ይናገራል።
የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ሚስጥራት ሁሉ ከተገለጡ በኋላ ለሙሽራይቱ ዘመን ማብቃቱን ለማብሰር ይወርዳል። ከዘመን ክልል መውጣት የምትችሉት አዲሱን የማይሞተውን አካላችሁን ስትለብሱ ብቻ ነው።
ደመናው የታየው ሚስጥራቱ ከመገለጣቸው በፊት ነው። ስለዚህ ደመናው መልአኩ አይደለም።
65-0124 የምጥ ጣር
ስለዚህ አንድ ቀን የእግዚአብሔር መለከት ድምጹ ይሰማል፤ በክርስቶስ የሞቱትም ይነሳሉ፤ ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ ይህንን ቃል ይመሰክራል።
64-0119 ሻሎም
ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
መልአኩ የሚወርደው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳንን ከሙታን ለማስነሳት ነው። ከዚያ በኋላ በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት የማይሞተውን አካላቸውን ለብሰው ይለወጣሉ። በዚያን ጊዜ ለጻድቃን ቅዱሳን ሁሉ ዘመን ያበቃል ምክንያቱም ወደ ዘላለማዊነት ውስጥ ይሻገራሉ።
ቀሪው ዓለም ግን የጊዜ እስረኛ ሆኖ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባል፤ ይህም በስድስተኛው ማሕተም ተገልጧል።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን የሚያሰሙት መልአኩ ወደ ምድር ከወረደ በኋላ ነው። መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ደግሞ ሚስጥራት ሁሉ ከተገለጡ በኋላ ነው።
63-0623M በክፍተቱ መካከል መቆም
የሰባተኛው መልአክ መልእክት በተሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ይገለጣሉ። ከዚያም ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ።
ስለዚህ ሰባቱ ማሕተሞች ከመገለጣቸው በፊት በሰማይ ላይ ከፍ ብሎ ያለፈው ደመና ሚስጥራቱ ሁሉ ከተገለጡ በኋላ የሚወርደው መልአክ ሊሆን አይችልም።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
ዮሐንስ የተናገረውን አሁን እናያለን፤ እርሱም እንዲህ አለ፡- “ስድስተኛውን ማሕተም በፈታ ጊዜ አየሁ፣ እነሆም ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ።” ከዚያም የተፈጥሮ ኡደቶች ሁሉ ተቋረጡ። አያችሁ? እግዚአብሔር በሽተኞችን እንደ መፈወስ፣ ዕውሮችን ማብራት የመሳሰሉ ታላላቅ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህ ቃል ውስጥ ግን የምናየው ተፈጥሮ እንደተዛባች ነው።
ምን እንደተፈጠረ ተመልከቱ፤ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ፀሃይ ጨለመች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አልሰጠችም፤ ከዋክብትም ተናውጠው ረገፉ፤ ይህ ሁሉ የሆነው ስድስተኛው ማሕተም በሚፈታበት ሰዓት ነው። ይህ የሚፈጸመው ስለ ሰማዕታቱ በታወጀ ጊዜ ነው። አያችሁ? ሰማዕታቱ አልቀዋል።
አያችሁ፤ አሁን ወደዚያ ሰዓት በጣም ቀርበናል። በማንኛውም ሰዓት ሊደርስ ይችላል (አያችሁ?) ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ልትበርር ቀርባለች። ነገር ግን አስተውሉ፤ እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበት ጊዜ ሙሽራይቱ እዚህ አትገኝም። ይህን አትርሱ፤ ሙሽራይቱ ትሄዳለች። ሙሽራይቱ በመከራዎቹ ውስጥ አታልፍም። ይህ ቤተክርስቲያን በመከራ ተፈትና የምትጠራበት ወቅት ነው። ይህ በቤተክርስቲያን ላይ የሆነባት
ስድስተኛው ማሕተም ገና አልተፈጸመም።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
… [ሁለቱ ነብያት] ውሃን ወደ ደም ለመለወጥ እና በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ምድርን በመቅሰፍ ለመምታት ስልጣን ይኖራቸዋል።
ምንድነው? ከቃሉ በቀር እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ማድረግ የሚችል ምንድነው? ተፈጥሮን እንደፈለጉ ሊያሽከረክሯት ይችላሉ። ተመልከቱ። ስድስተኛው ማሕተም እንዲፈጸም የሚያደርጉት እነርሱ ራሳቸው ናቸው። ማሕተሙን ይገልጡትና ይፈቱታል። ይህም እግዚአብሔር የተፈጥሮ ኡደት እንዲቋረጥ የሚያደርግበት ኃይል ነው። ተመለከቱ፤ ስድስተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ኡደት መቋረጥ ነው።
አሁንስ አስተዋላችሁን? ይኸው ማሕተሙ። ማነው የሚያደርገው? ንጥቀት ከተፈጸመ በኋላ ነብያቱ ናቸው የሚያደርጉት። በእግዚአብሔር ኃይል፣ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥሮ ላይ ይፈርዳሉ። የምድር መንቀጥቀጥ ማስነሳት ይችላሉ፤ ጨረቃን ወደ ደም መለወጥ ይችላሉ፣ ፀሃይ ልትወድቅ ወይም በእነርሱ ትዕዛዝ ማንኛውንም ነገር ልትሆን ትችላለች …
አሁንም አስተውሉ። በዝቶባችሁ እንዳያስጨንቃችሁ፤ ግን ያንን ማሕተም ማን እንደከፈተው ተመልከቱ፡ ነብያት ናቸው። አያችሁ? አሜን። ይኸው። በንስሩ ዘመን እየኖርን ነው ወንድሞች ሆይ፤ ራሶቻችን በደመናት መካከል ናቸው። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ከፈቱት። ለመክፈት ስልጣን አላቸው። እንግዲህ ስድስተኛው ማሕተም የሚከፈተው እንዲህ ነው።
ስለዚህ ሌላም ችግር አለ።
ስድስተኛው ማሕተም የሚፈታው በሁለቱ የእስራኤል ነብያት ነው። ለምን?
ስድስተኛው ማሕተም የተፈጥሮ ኡደት መቋረጥ ነው። ምድርን በፍርድ እና በመቅሰፍት የመምታት ኃይል ያለቸው ብቸኞቹ ሁለት ሰዎች ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው። ስለዚህ ስድስተኛውን ማሕተም ዕውን የሚፈቱት እነርሱ ናቸው። ስድስተኛው ማሕተም ስለ ታለቁ መከራ እንደሆነ የሚያስረዳ መገለጥ ስላገኘን ስለ ስድስተኛው ማሕተም ማውራት እንችላለን። ሁለቱ ነብያት ግን ስድስተኛውን ማሕተም በተግባር የፈቱታል። እስራኤልን ለማጥፋት የሚዘምቱትን የራሺያ እና የሙስሊም ሰራዊት እንዳይንቀሳቀሱ ያግዷቸዋል።
ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውን ማሕተም ስለገለጠ ሁለቱ ነብያት ወደፊት ሲመጡ ዕውን ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት ይችላሉ፤ ማሕተሙን በመፍታታቸውም የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው ፖፕ እስራኤልን ለማጥፋት የሚያደርገውን ሙከራ በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ያስቆሙታል።
ስድስተኛው ማሕተም ከዚህ በፊት ተፈቷል የምትሉ ከሆነ የተፈጥሮ ኡደትን በማስቆም የተፈጥሮ አደጋ የሚያስከትለውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል አሳዩን። ከአሕዛብ ክርስቲያኖች መካከልስ ይህንን ኃይል የሚፈልግ ማነው? እኛ ሰዎችን ለማዳን ነው የምንፈልገው እንጂ በፍርድ ልንረግማቸው አይደለም።
እነዚህ መቅሰፍቶች ፍርድ ናቸው፤ የሚመጡትም በታላቁ ፍርድ ዘመን ብቻ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን የፍርድ ቀን ነው።
ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱ ታላቅ የፍርድ ኃይል ቢኖር ይባክናል፤ ምክንያቱም ፍርድ የሚሆነው ሙሽራይቱ ከምድር ከተነጠቀች በኋላ ብቻ ነው።
ሰባተኛው ማሕተም
በዚህ ውስጥ የምናውቀው ስድስተኛው ማሕተም አሁን እየተከፈተ እንዳለ ነው።
በዚህ ጥቅስ ውስጥ ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውን ማሕተም እየፈታሁ ነኝ ይላል፤ ይህም እውነት ነው።
ነገር ግን ስድስተኛው ማሕተም አሁንም እንደገና ደግሞ ወደፊት በእስራኤል ነብያት፣ ሁለት ጊዜ ሊፈታ አይችልም።
ለዚህ መፍትሄው ቀላል ነው። ስድስተኛው ማሕተም የሚፈታው ወንድም ብራንሐም ወደፊት ስለሚሆነው ነገር በራዕይ የተቀበለው መገለጥ ሆኖ ነው። ወደፊት ምን እንደሚፈጠር ከጊዜ መጋረጃ በስተጀርባ አሻግሮ በመመልከት አየ። ከዚያም ወደፊት በሚሆነው በታላቁ መከራ ዘመን ምን እንደሚፈጸም ሊነግረን ተመለሰ።
ስለዚህ ስድስተኛው ማሕተም ለእኛ በራዕይ ተፈቶልናል። ስድስተኛው ማሕተም ዕውን በሚፈታ ጊዜ ምን እንደሚፈጠር በራዕይ መገለጥ አግኝተናል።
በታላቁ መከራ ዘመን ግን በሁለቱ ነብያት አማካኝነት ዕውን ይከፈታል።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
የስድስተኛው ማሕተም መሰረታዊ ሃሳብና በተፈታ ጊዜ የሚሆነውን ታላቁን መከራ በተመለከተ ጥቂት መረዳት አግኝተናል። ነገር ግን ዝርዝር እውቀት የለንም። የሰባቱ መለከቶች ትርጉም ምን እንደሆነ አናውቅም። ሁለቱ ነብያት ስድስተኛውን ማሕተም ሲፈቱ መቅሰፍቶቹ በሙሉ በዝርዝር ይገለጣሉ። እኛ የተሰጠን መገለጡ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ስለ መቅሰፍቶቹ አጠቃላይ መረዳት አለን። ነገር ግን ወደፊት መቅሰፍቶቹን በዝርዝርና በግልጽ እናያቸዋለን።
እውነታን ስለ እውነታ ከሚገልት ራዕይ ጋር አትቀላቅሉ።
ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች እየሰበከ በነበረ ጊዜ ስለ ዘመን ማብቃት ጥያቄ ተነስቶ ነበር።
64-0830M ጥያቄዎችና መልሶች - 3
ማሕተሞቹ ሲከፈቱ ጊዜ ቢያቆም፣ ጊዜ ከዚያ ወዲያ ባይኖር (ይቅርታ አርጉልኝ) ማሕተሞቹ ሲከፈቱ የዚያን ጊዜ የሺ ዓመቱ መንግሥትም ያበቃል አይደል?
አይደለም፤ አይደለም። ማሕተሞቹ ሲከፈቱ ጊዜ አላበቃም። ይህ የተሳሳተ መረዳት ነው። የሆነው ነገር ምን መሰላችሁ፤ ሚስጥራት ተገለጡ እንጂ ጊዜ አላቀመም። አያችሁ? ተመልከቱ። ልብ ብላችሁ በደምብ ተመልከቱ፤ ከቴፕ ሰምታችሁት ከሆነ ቴፑን እንደገና አጫውቱት። አያችሁ?
ጊዜ እስከ … ይህን ጥያቄ የጠየቀ ሰው ፖስት ሚሌኒሊስት ሊሆን ይችላል። ቤተክርስቲያን ወደ ቤቷ ከሄደች በኋላ አንድ ሺ ዓመታት አሉ፤ የዚያን ጊዜ ወደ ምድር ትመጣለች። ከዚያ በኋላ በአዲሱ ሰማይና በአዲሱ ምድር ውስጥ ጊዜ የሚባል ነገር ያቆማል።
የዘመን ማቆም እጅግ የተወሳሰበ ነገር ከመሆኑ የተነሳ የሰዎች አእምሮ ሊያስተውለው አይችልም። በከበረው አዲስ አካላችሁ ውስጥ ስትሆኑ ከጊዜ ውጭ ትሆናላችሁ፤ በዚያም ጊዜ ልክ እንደ ሃሳብ በነጻነት መንቀሳቀስ ስለምትችሉ በሰማይም በምድርም ውስጥ እንደ ልብ መመላለስ ትችላላችሁ።
ነገር ግን ሙሽራዋ ስትነጠቅ ንጥቀት ያመለጣቸው ሰዎች ጊዜ ውስጥ ይቆያሉ። በአርማጌዶን ጦርነት ውስጥ ሳይሞቱ ተርፈው ወደ ሺ ዓመቱ መንግስት የሚገቡ ሰዎች እነርሱም የጊዜ እስረኞች ናቸው። ስለዚህ ሁለት ዓይነት ሰዎች ይኖራሉ። እነርሱም የከበረው አካላቸውን ለብሰው ከጊዜ ነጻ የወጡ የሙሽራይቱ አካላት እና በምድር ላይ የሚኖሩ የጊዜ ባሪያዎች የሆኑ ሰዎች ናቸው።
የጠፉት ሰዎች በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ እሳት ባሕር ሲገቡ ይህ የመጨረሻው ፍርድ ይሆናል።
የጠፉ ነፍሳት የቅጣታቸው ዘመን እስኪያልቅ ድረስ በእሳት ባሕር ውስጥ ይቆያሉ፤ ከዚያ በኋላ ቅርንጫፍና ስር ሳይቀራቸው ተቃጥለው ይጠፋሉ። በዚያ ሰዓት የእነርሱ ጊዜ ያልቃል። በዚህ አስከፊ እስር ቤት ውስጥ ከሁሉም የበለጠ ረጅም ጊዜ የሚቆየው ሰይጣን ነው። ሰይጣን ተደምስሶ ሲጠፋ አምስተኛውም ዳይሜንሽን ይጠፋል፤ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ምንም አገልግሎት አይኖረውም።
ማቴዎስ 25፡41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
መልአክ መልእክተኛ ነው። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ቃል ይለውጣል፤ ይቃረናል። ከመጽሐፍ ቅዱስ የተለየ አንዳች ነገር ብናስተምር የሰይጣን መልአክ ወይም የሰይጣን መልእክተኛ ነን። እንዲህስ ከመሆን ቢቀርብን ይሻላል።
እሳቱ ዘላለማዊ ነው። ማለትም በጣም ለረጅም ጊዜ ይነድዳል። ነገር ግን ፍጻሜ የሌለው አይደለም። የእሳት ባሕር ለዘላለም ቢሆን ውስጡ የተጣሉ ሰዎችን በእሳት ባሕር ውስጥ ለማቆየት ሰዎቹ የዘላለም ሕይወት ያስፈልጋለቸዋል። የዘላለም ሕይወት ግን ኢየሱስ ሲያድነን የምንቀበለው ሕይወት ነው። ይህም የዘላለም ሕይወት ማለትም መንፈስ ቅዱስ ወደ መንግስተ ሰማይ ነው የሚወስደን እንጂ ወደ ሲኦል አይደለም።
እምነት የሚመጣው የመጽሐፍ ቅዱስን መገለጥ ወይም ራዕይ በመስማት ነው። ሲፈጸም ማየት ኋላ የሚሆን ነው።
የእግዚአብሔር ሃሳብ መጀመሪያ በራዕይ መልክ እንደ ኢሳይያስ ላሉ ነብያት ነው የተገለጠው፤ ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከድንግል ሴት በመወለዱ ዕውን ሆኖ ተፈጸመ።
ኢሳይያስ 7፡14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ድንግል ትጸንሳለች። የኢሳይያስ ራዕይ አጠቃላይ ሃሳቡን ይገልጣል ግን ዝርዝር ነገር የለውም።
እውነታው ከ700 ዓመታት በኋላ ሲፈጸም ስለ በረቱ፣ ስለ ቄሳር ግበር፣ ስለ መጠቅለያ ጨርቅ እና ስሙ ኢየሱስ ስለመሆኑ አወቅን። የድንግሊቱ ስም ማርያም ነበረ። ደግሞም ወደ ኤልሳቤት ስለመሄዷና መልአኩ ገብርኤል ወደ እርሷ ስለ መምጣቱ ተጨማሪ ዝርዝር አወቅን።
ነገር ግን አሁንም ሌላ የማናውቀው ሚስጥር አለ። ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን አናውቀውም። ከ500 ዓመታት በኋላ ዳዮናይሲየስ ኤክሲገስ የተባለ ገዳም ውስጥ የተቀመጠ መነኩሴ (በአጭሩ ዴኒስ ይባላል) የዘመን አቆጣጠር ካላንደርን ለወጠ። ኢየሱስ ዲሴምበር 25 ነው የተወለደው ብሎ አሰበ፤ ስለዚህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ኢየሱስ ከተገረዘበት ቀን ጀምሮ እንዲሆን አደረገ፤ ይህም ከተወለደበት ስምንተኛው ቀን ነው። ይህም ቀን ጃንዋሪ 1 ቀን 1 ዓ.ም ተባለ። በዚያ ጊዜ ምዕረባውያን ስለ ሒንዱዎች ዜሮ አላወቁም ነበር፤ ምዕራባውያን ስለ ዜሮ ቁጥር ያወቁት በ800 ዓ.ም አካባቢ ነው። ነገር ግን የዜሮ ጽንሰ ሃሳብ መምጣት ብዙ ውዝግብ ፈጥሯል ምክንያቱም ሰዎች ሁለተኛው ሺ ዓመት የተጠናቀቀው በ2000 ይሁን በ2001 እርግጠኛ ሊሆኑ አልቻሉም። ምሑራን እስከ ዛሬ ድረስ ኢየሱስ ስለተወለደበት ዓመት እየተጨቃጨቁ ናቸው፤ እኛም የተወለደበትን ወር እና ቀን አናውቀውም።
ስለዚህ ስለ አንድ ሚስጥር እናውቃለን ብለን ባሰብን ጊዜ ሚስጥሩ ሙሉ በሙሉ አይደለም የሚገለጥልን። ትንሽ እንኳ ከውስጡ የማናውቀው ነገር ካለ እውቀታችንን ድንግዝግዝ ያደርገዋል።
በዲሴምበር 25 የምታምኑ ከሆነ በ360 ዓ.ም ይህንን ቀን ኦሬልያን ከተባለ የሮማ ገዥ በኮረጀ የሮማ ጳጳስ ተታላችኋል፤ ኦሬልያን በ274 ዓ.ም ዲሴምበር 25ን ሶል ኢንቪክተስ ወይም የማይሸነፈው የፀሃይ አምላክ ቀን ብሎ አወጀ። ስለዚህ የፀሃይ አምላክ የልደት ቀኑን ታከብሩለት ዘንድ ማርኳችኋል ማለት ይሆን?
እቤታችሁ ውስጥ የገና ዛፍ የምታስገቡ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ትታችሁ ለአረማዊ ልማድ ተገዥ ሆናችኋል።
ሰብዓ ሰገል ወደ ግርግም ሲገቡ ሶስት ስጦታ ይዘው በመምጣታቸው እናንተ ደግሞ የገና ስጦታ የምታዘጋጁ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ በጣም ርቃችሁ ሄዳችኋል ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሰብዓ ሰገል ስጦታ ይዘው የገቡት ወደ ቤት ውስጥ ነው፤ በመጡም ጊዜ ኢየሱስ ትንሽ ልጅ ነበረ። እቤት ውስጥ ከእናቱ ጋር ነበረ፤ ዮሴፍ ግን በቤት አልነበረም። ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ወይም ወደ ግርግም አልመጡም። ስለዚህ የገና ዛፍ አናት ላይ የምትሰቅሉት ኮከብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ የኢየሱስን ልደት እንድናከብር አላዘዘንም።
ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
የክሪስማስ ጊዜ። 25ኛው ቀን። የታሕሳስ ወር። በየዓመቱ የሚደጋገም የልደት ቀን።
እንደምታዩት ጳውሎስ በዚህ ዘመን ቢኖር ኖሮ በፈጠርነው የክሪስማስ በዓል ቀን አይደነቅም።
ዲሴምበር 25። የክሪስማስ ዛፍ። የጥበብ ሰዎች በረት ውስጥ ስጦታ ይዘው ሲመጡ። እንደምታዩት ነጩ ፈረስ እስካሁን በምድር ላይ ሥራውን እየሰራ ነው፤ በሐይማኖታዊ ሽንገላው ብዙዎችን እየማረከ ነው።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
በመካከላችን ታላቅ የሚባል ሰው የለም። እኛ ታላላቅ ሰዎች ወይም ታላላቅ ሴቶች አይደለንም -- ሁላችንም ወንድሞችና እሕቶች ነን፤ ሁላችንም እኩል ነን። እኛ ታላቅ አይደለንም። አንድ ሰው ራሱን ከሌላው ሰው ማስበለጥ ወይም ታላቅ ማድረግ አይችልም። በፍጹም። ነገር ግን ሁላችንም ሰዎች ነን። ነገሮችን ለመተርጎም አትሞክሩ። ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን እና ምስጋናን እየሰጣችሁ ከመሆን በቀር ምንም ሌላ ነገር ለማድረግ አትሞክሩ …
ሰውን በዚህ ውስጥ ማስገባት አንፈልግም። ስለ እኔ የምታውቁትን ሁሉ እርሱት። እኔ ወንድማችሁ፣ እንደናንተው በጸጋ የዳንኩ ሐጥያተኛ ነኝ እንጂ መኖር የሚገባኝ ሰው አይደለሁም፤ ይህንን የምለው ትሁት ለመምሰል ፈልጌ አይደለም፤ እውነት ስለሆነ ነው እንጂ። በእኔ ውስጥ አንድም ነገር አንዳችም መልካም ነገር የለም።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋ እነዚህ ምስኪን ዓይኖቼ ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ አሻግረው ወዲያ ማዶ ያሉ ነገሮችን እንድመለከት አስችሎኛል፤ እኔም አይቼ ተመለስኩ …
እኔም ብዙ ነገር እንድመለከት እግዚአብሔር መርጦኛል (አያችሁ፣ አያችሁ?) ተመልክቼም እንድመለስና እንድገልጥ …
ወንድም ብራንሐም የወደፊት ክስተቶችን እንዲያይ ከጊዜ መጋረጃ በላይ ተነጥቆ ነበረ።
“ሰውን በሰው ትምሕርት አታሳድጉት።” በሰው ንግግር ጥቅስ ላይ አስተምሕሮ አትመስርቱ። ሰዎች የተናገሩትን ቃል ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስዳችሁ አስተምሕሮዋችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ መስርቱ።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
ሁሉን የሚችለው ይመጣና በዚህ ምሽት ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ አሻግረን እንድናይ ማሕተሙን ይከፍትልን ዘንድ።
63-0319 ሁለተኛው ማሕተም
አባት ሆይ ዛሬ ምሽት ወደዚህ ትመጣና ይህንን ስድስተኛ ማሕተም ትከፍትልን ዘንድ እንለምንሃለን። ባለ ቅኔው እንዳለው ከዘመና መጋረጃ በስተጀርባ አሻግረን እንመለከት ዘንድ። ጌታ ሆይ መሻታችን ይህ ነው፤ አሻግረን እንድንመለከትና ከፊታችን ምን እንዳለ እናይ ዘንድ። ደግሞም የታረደው በግ አሁን በመካከላችን እንዲመጣ እና ማሕተሙን ከፍቶ እንዲገልጥልን፣ ማየት የሚያስፈልገንን እንድናይ እንጸልያለን።
ይህንን ክስተት በራዕይ ለማየት ብሎ ይጸልያል፤ ክስተቱም ከጊዜ መጋረጃ ባሻገር ያለ ስለሆነ ገና ወደ ፊት የሚፈጸም ነው።
ወደፊት ምን እንደሚፈጸም በራዕይ ማየት ይፈልጋል።
ክስተቱ በዚያው ሰዓት ዕውን እየተፈጸመ ሳለ አይደለም የሚያየው። ክስተቱ ዕውን ከመፈጸሙ በፊት አስቀድሞ መገለጡ መምጣት አለበት፤ ይህም የሚሆነው በዕውን ከመፈጸሙ በፊት ቀድመን መዘጋጀት እንድንችል ነው።
የሜሴጅ አማኞች ግን የወንድም ብራንሐምን መልእክት ለውጠው እነዚህ ክስተቶች ተፈጽመው አልፈዋል ይላሉ፤ ወንድም ብራንሐም ግን ወደፊት የሚፈጸሙ ክስተቶችን ራዕይ ብቻ ነው ያየው።
58-1130 ጉበኛ ሆይ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?
እርሱም [ጉበኛው] በማማው ላይ ነበረ፣ ማማውም ከቅጥሮች በላይ ከፍ ብሎ ነበር የተሰራው። በዚህ ማማ ውስጥም የስነ ከዋክብት መጽሐፎችና ሌሎች መጽሐፎች ነበሩት፤ ከዋክብትን እያየ ሰዓቱ ስንት እንደሆነ ይቆጥራል። በቀን ውስጥ በየትኛውም ጊዜ ስንት ሰዓት እንደሆነ ያውቃል። ደግሞም መሬት ላይ ማንም ማየት ከሚችለው በላይ አርቆ ማየት ይችላል። በቅጥሩ ላይ ካሉ ሰዎችም ሁሉ የበለጠ አርቆ ማየት ይችላል ምክንያቱም ከእነርሱ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ነው የቆመው።
ወደ ላይ ከፍ ባላችሁ ቁጥር በጣም ሩቅ ማየት ትችላላችሁ። እየመጡ ያሉ አደጋዎችንም በምድር ላይ ዝቅ ብለው ከቆሙ ሰዎች ቀድማችሁ ታያላችሁ።
ኢሳያስ በዘመኑ እግዚአብሔር ጉበኛ አድርጎት ነበር። እግዚአብሔር ነብያቱን በንስር ይመስላቸዋል። ስለ ንስሮች ብዙ ጊዜ እንደሰበክሁት ንስር ከወፎች ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ መብረር የሚችል ወፍ ነው። ስለዚህ ለሚበርርበት ከፍታ የሚመጥን ተደርጎ ነው የተሰራው።
63-1214 ለምን ትንሽዋ ቤተልሔም
የሆነ ቀን አንድ ሰው እንዲህ አለ- “አንተ ነብይ እንደሆንህ እናምናለን።”
እኔ ግን እንደዚያ አላልኩም፤ እኔ አልናገርም። እኔ ነብይ አይደለሁም፤ እኔ እውነትን ለመናገር የምሞክር የእግዚአብሔር ባሪያ ነኝ።
ወንድም ብራንሐም እነዚህን ሁሉ ራዕዮች ቢያይም እንኳ እራሱን ነብይ ነኝ ብሎ አላወጀም። እነዚህ ራዕዮች አስደናቂዎች ናቸው፤ ግን ቁምነገሩ እሱ አይደለም። እርሱ ትኩረት ያደረገው ራዕዮቹ በገለጧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ላይ ነው። ያያቸው ራዕዮች ተዓማኒነት ሊያገኙ የቻሉት መጽሐፍ ቅዱስን ሊገልጡ በመቻላቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ትርጉም እየነገረን እንዲሁም ራዕዮቹን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ በማመሳከር ወንድም ብራንሐም የኤልያስን ሚና ተጫውቷል፤ ማለትም ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መልሶናል። የሜሴጅ ሰባኪዎች የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ሰባኪዎች ግን ትምሕርቶቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው አያረጋግጡም። ወንድም ብራንሐም ነብይ ነበር፤ ነብይ መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን እርሱ ደግሞ በነብይነቱ ላይ ትኩረት እንድናበዛ አልፈለገም፤ በሰው ላይ ትኩረት መደረግ የለበትም። እርሱ የፈለገው ያቀረባቸውን መልእክቶች እርሱ ስላቀረባቸው ሳይሆን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደን መርምረን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትክክለኛነታቸው ስለመሰከረላቸው እንድናምን ነው የፈለገው።
64-0823 ጥያቄዎችና መልሶች - 1
ቃሉን በሙላት መቀበል የሚችሉ ግን እኔ ስለሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ይቀበላሉ። የሚቀበሉ ሁሉ ለመቀበል ነጻ ናቸው ምክንያቱም ቃሉ እውነት መሆኑ ተረጋግጧል።
65-0725M በዘመን መጨረሻ ላይ የተቀቡት
ስለዚህ ይህንን ወደፊትና ወደ ኋላ እየተመላለስን በቃሉ መርምረን እናረጋግጣለን፤ እንጂ በሆነ ሰው ቲዎሪ ወይም በሆነ ሰው ሃሳብ አይደለም።
ማንም ይሁን ማን ጉዳዬ አይደለም፤ እኔም ልሁን ወይም ሌላ ሰው፤ “እንደ ሕጉ እና እንደ ነብያቱ ካልተናገረ በውስጡ ብርሃን ስለሌለው ነው።” አያችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረው ይህንን ነው። “የሰው ሁሉ ቃል ሐሰት ይሁን የእኔ ብቻ እውነት ይሁን” ማንም ይሁን ማን።
ሌላ ትልቅ ችግር እንመልከት።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራትን በሙሉ እናውቃለን ካልን ለምንድነው ወንድም ብራንሐም አላውቅም ያላቸው ብዙ ነገሮች የኖሩት?
ሰባተኛ ማሕተም
1. “መች ነው የሚሆነው፣ ወንድም ብራንሐም?” እኔ አላውቅም። እኔ ምንም አላውቅም …
2. ይኸው አሁን ስድስተኛው ማሕተም ተከፍቶልናል፤ አሁን እናየዋለን፤ ሰባተኛው ማሕተም ግን ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ለሕዝብ ሊከፈት እንደማይችል እናውቃለን …
ከዚህ ማሕተም በታች የተሰወረው ይህ ሚስጥር ምን እንደሆነ እኔ አላውቅም። አላውቀውም። ላየውም አልቻልኩ፤ ምን እንደሆነና ምን እንደሚል አላውቅም። ነገር ግን እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ተከታትለው ድምጻቸውን እንዳሰሙ አውቃለው። ሰባት ጊዜ የተለያዩ መልእክቶችን በድምጻቸው አሰምተዋል፤ ይህም አንድ ያየሁትን ነገር ሆኖ ተገለጠ።
ከዚያ እኔም ባየሁት ጊዜ በዚያ ያለፈውን ትርጓሜውን ፈለግሁ፤ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም።
3. … ያ ሰባተኛ ማሕተም። አያችሁ ግን የተሰወረ ሚስጥር ነው። ማንም አያውቀውም። ነገር ግን እርሱ እንደተናገረው፡ የሚመጣበትን ቀን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ደግሞ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥርም ማወቅ አይችሉም። ስለዚህ አያችሁ፤ የተያያዘ ነገር ነው…
4. … ዛሬ ይህን ያህል ነው መረዳት የቻልነው፤ ምክንያቱም የቀረው በሙሉ ተገልጧል፤ ይህኛው ግን አልተገለጠም። እቤቴ ውስጥ ተቀምጬ ይህንን ሰማሁ -- ወይም አልሰማሁም ብል ይሻላል፤ ከመስማት ይልቅ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሲገለጥ አየሁት። ስለዚህ አሁን መሄድ የምንችለው ይህን ያህል ነው …
… ሳቢኖ ኬንዮን ውስጥ እንዲህ አለ፡- “ይህ ሶስተኛው መልእከት ነው።” ደግሞም አብረውት የሚሄዱ ሶስት ትልልቅ ነገሮች አሉ፤ ከነዚህም አንዱ ዛሬ ተገልጧል፣ ወይም ትናንት፤ ሌላኛው ዛሬ ተገለጠ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አለ፤ እርሱንም ልተረጉመው አልችልም ምክንያቱም በማይታወቅ ቋንቋ ነው የተነገረው። እኔም በዚያ ቆሜ ቀጥ ብዬ አየሁት፤ ይህም የሚመጣው ሶስተኛው መልእክት ነው። የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስም … ኦ አምላኬ። ሰማይ ሁሉ ጸጥ ያለበት ምክንያት ይህ ነው።
5. ይህ ሶስተኛው መልእክት ይሆናል፤ እናንተም ለማንም አትነግሩትም።
እንዲህ አለ፡- “ይህን ለማብራራት አትሞክር።” እንዲህ አለ፡- “ይህ ሶስተኛው መልእክት ነው፤ ነገር ግን እዚያው አገኝሃለው …
ወደ ላይ ወስዶኝ የተናገረኝን ታስታውሳላችሁ፡- “ይህ ሶስተኛው መልእክት ነው፤ ደግሞም ማንም አያውቀውም።” …
6. ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በአንድ ላይ አሰሙ፤ የሆነ መልእክት ሊያስተላልፉ የፈለጉ ይመስላሉ። ልብ በሉ፤ በዚያ ጊዜ ዮሐንስ ሊጽፍ ፈልጎ ነበር፤ እርሱ ግን አለው፡- “አትጻፈው።” ኢየሱስ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ተናግሮ አያውቅም። ዮሐንስ ሊጽፍ አልቻለም። መላእክት ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ምንም አያውቁም።
ወንድም ብራንሐም ሰባተኛው መልአክ ነበረ፤ ነገር ግን ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች እርሱም ምንም እንደማያውቅ ተናግሯል።
ምን ይሆን? ኢየሱስ የተናገረው ነገር ነው፤ የሰማይ መላእክት እንኳ አንዳች የሚያውቁት ነገር የለም። አያችሁ አያችሁ? እርሱ ራሱ አላወቀውም፤ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው አለ …
ሰባት ነጎድጓዶች በመደዳ ተራ በተራ ቃላቸውን መናገራቸው አይደለም … አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት። እንደዚያ ቢሆንማ ሰማያት ሊጽፉ አይችሉም። ሰማያት ምንም ሊያውቁ አይችሉም፤ ምክንያቱም ምንም መነሻ የሚሆን ነገር የለም። የእረፍት ጊዜ ነው። ከመላእክት ተሰውሮ እስኪቆይ ድረስ ታላቅ ነበር። አሁንስ ምን?
ይህንን ሚስጥር ሰይጣን ቢያገኘው ታላቅ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል። እርሱ አንድ የማያውቀው ነገር አለ። ምንም ነገር በራሱ መተርጎም አይችልም፤ የትኛውንም ስጦታ ኮርጆ ማስመሰል አይችልም (እየተማራችሁ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለው)። ይህንን ሊያውቅ አይችለም። ይህ ሚስጥር ቃሉ ውስጥ እንኳ አልተጻፈም። ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። መላእክትም ሆኑ የትኛውም ፍጥረት አያውቁትም። ቢያውቁና አንድ ነገር ትንፍሽ ብለው ቢናገሩ ሚስጥሩን ሊያባክኑ ይችላሉ፤ ስለዚህ ምንም ባለማወቃቸው የተነሳ ምንም መናገር አይችሉም…
የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ዝም አሉ። እግዚአብሔር በሰማይ ያደረገውን ነው በምድር ማድረግ ያለብን። ሰባተኛው መልአክ ሰባተኛውም ማሕተም በተመለከተ ዝም አለ። ስለዚህ ከዚህ በፊትም ይሁን ወደፊት ጌታ መች ወይም እንዴት ወይም የት እንደሚመጣ ሊያብራራ የሚሞክር ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ እየሰራ አይደለም። እኛ ሰዎች በቀላሉ እግዚአብሔር ያልፈለገውን ሥራ የመስራት ዝንባሌ አለን። ደመናው የጌታ ምጻት ነው ብሎ መናገር የሐሰት ዜና ስለሆነ የሚያስከትለው ብዥታ እና ግራ መጋባት ብቻ ነው። ስለ ጌታ ምጻት ምንም ነገር ልናውቅ አንችልም። የጌታ ምጻት ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው።
7. እንግዲህ ሰባተኛውን ማሕተም በከፈተው ጊዜ መልሶ እንደገና አጠፋው። አያችሁ? ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ማየጥ እንችላለን፤ ስለዚህ እነዚህ ሚስጥራት የሚገለጡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ስለዚህ እስከዚህ ደርሰናል፤ የቀረው ሁሉ ኢየሱስ ለሙሽራይቱ ተመልሶ ምድር ላይ በሚገለጥበት ጊዜ ይታወቃል ወይም በዚያ ጊዜ በሚከሰተው በማንኛውም ነገር አማካኝነት …
[የኢየሱስ መገለጥ ገና ወደ ፊት ነው። ስለዚህ ደመናው የጌታ መገለጥ አይደለም።]
… እስቲ ስለዚህ ስለ ሰባተኛው ማሕተም እንነጋገር። ትልቅ ትኩረት የሚስብ ነገር ነው። እኛም ደግሞ …. ሰባተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ገና አናውቅም ምክንያቱም እንዲፈታ አልተፈቀደም …
… ከዚያ [ከሰባተኛው] ማሕተም ሚስጥራት አንዱ ያልተገለጠበት ምክንያት የተናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች ስለሆኑ ነው፤ እስካሁንም ማንም አያውቀውም ምክንያቱም ስለሱ የሚያውቅ ማንም የለም፤ ደግሞም አልተጻፈም …
… መላእክት አያውቁትም፤ ጌታ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም። ነገር ግን የሰባቱ ነጎድጓዶች ሰባት ድምጾች በዚያ ጊዜ ታላቁን ሚስጥር ይገልጣሉ።
ስለዚህ እኔ የማምነው የማናውቀው ከሆነ፤ ደግሞም ያ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ልናውቀው አንችልም፣ ነገር ግን በዚያ ቀን ይገለጣል፤ ሊገለጥ በሚገባው ሰዓት ነው የሚገለጠው።
… ስለዚህ አስታውሱ፤ ሰባተኛው ማሕተም ያልተገለጠበት ምክንያት (አያችሁ?) ለማንም ያልገለጠበት ምክንያት ማንም ሊያውቀው ስለማይገባ ነው …
ሌሎቹን ስድስቱንም ማሕተሞች ገልጧቸዋል፤ ነገር ግን ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አልተናገረም። የዘመን መጨረሻው ማሕተም ሲጀምር መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው የሚሆነው …
በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ዝምታ ሆነ። በዚህ ግማሽ ሰዓት ውስጥ ይህ የሰባተኛው ማሕተም ሚስጥር በቤዛነት መጽሐፍ ውስጥ ሲከፈትየሰማይ ሰራዊት ሁሉ ዝም አለ፤ ። አስቡት፤ ነገር ግን ተከፍቷል። በጉ ይከፍተዋል። አንድ ነገር ልንገራችሁ? በጣም ተደነቁ። አላወቁም። ነገር ግን ሲገለጥ ዝም አሉ …
64-0830E ጥያቄዎችና መልሶች - 4
8. መለከቶች ከሙሽራይቱ ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ነገር እንደሌለ መንፈስ ቅዱስ ነግሯኋል። ሰባቱ ጽዋዎች ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር አለ?
መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ ይገልጠው እንደሆን ጠብቄ አያለሁ። ለጊዜው ግን አላውቅም።
እንደምታዩት ብዙ ጊዜ ደጋግሞ “አላውቅም” ብሏል። ስለዚህ ወንድም ብራንሐም የተናገረውን እየተናገርኩ ነኝ ብሎ ሚስጥራትን ሁሉ አውቃለው የሚል ማነው? ከራሱ አፍ ከተናገረው ቃል አንጻር ዊልያም ብራንሐም እነዚህን ሚስጥራት አለማወቁ ግልጽ ነው።
ሌላ ትልቅ ችግር እንመልከት።
ሰባተኛው ማሕተም ዕውን ተፈቶ ከሆነ ሁሉም ነገር መጠናቀቅ አለበት።
1. ሰባቱ መለከቶች መጠናቀቅ አለባቸው። ነገር ግን ሰባቱ መለከቶች ድምጻቸው የሚሰማው ወደፊት በሚመጣው በታላቁ መከራ ውስጥ ብቻ ነው።
2. ሰባቱ ጽዋዎች መጠናቀቅ አለባቸው። ነገር ግን ጽዋዎቹ የሚፈስሱት ወደፊት በታላቁ መከራ ውስጥ ብቻ ነው።
3. የሺው ዓመት መንግስት ጅማሬ መጠናቀቅ አለበት።
4. ለዚህችም ዓለም ዘመን መጠናቀቅ አለበት።
5. ለፍጥረትም ሁሉ ትግል ማብቃት አለበት። የምድር መናወጥ፣ የጎርፍ አደጋ፣ ድርቅ፣ አውሎ ነፋስ ሁሉ መጥፋት አለባቸው። የአየር ጠባይ ለውጥ ወይም የዓለም ሙቀት መጨመር ሁሉ መጥፋት አለበት።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
ይህን አስተውሉ [ሰባተኛው ማሕተም] የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ነው። የሰባቱ ማሕተሞች መጨረሻ ነው። የመለከቶቹ መጨረሻ ነው። የጽዋዎቹ መጨረሻ ነው፤ እንዲሁም የሺ ዓመት መንግስት መጨረሻም ነው፤ ይህ ሰባተኛው ማሕተም ነው።
ልክ ሮኬት ወደ አየር ላይ እንደመተኮስ ነው፤ ያም ሮኬት እዚህ ይፈነዳል፤ ወደላይ ይሄዳል፤ ከዚያም እንደገና ይፈነዳል። አምስት ኮከቦችን ከውስጡ ያወጣል። ከነዚያ ኮከቦች አንዱ ይፈነዳና ከውስጡ አምስት ኮከቦችን ያወጣል፤ ከዚያም ከነዚያ ከዋክብት አንዱ ይፈነዳና አምስት ኮከቦችን ያወጣል (አያችሁ?) ከዚያም ኮከቡ ይጠፋል። ሰባተኛው ማሕተም እንዲህ ነው፤ በሰባተኛው ማሕተም የዓለም ዘመን ያበቃል። የዚህን ዓለም ዘመን ይቋጨዋል። የዚህንም፤ የዚያንም የሁሉንም ዘመን ይቋጫል። ዘመንን ይቋጫል … ሁሉም ነገር የሚጠናቀቀው በዚያ በሰባተኛው ማሕተም ነው።
ስለዚህ እንዴት አድርጎ ነው የሚሰራው? ይህንን አናውቀውም፤ አይደል? አናውቅም። እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚሆኑበትና የሺ ዓመት መንግስቱ የሚጀመርበት ጊዜ ነው …
ይህ ሰባተኛ ማሕተም ለሁሉ ነገር ማብቂያ መሆኑን ማወቅ አለብን። እውነት ነው። በሰባቱ ማሕተሞች በታተመው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉ ነገሮች (ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ በቤዛነት መጽሐፍ ውስጥ ታትመው የተቀመጡ ነገሮች) በውስጡ የተጻፉ ነገሮች አንድ በአንድ ይጠናቀቃሉ። መጨረሻቸው ነው፤ በትግል ውስጥ የምትኖረዋ ዓለም መጠናቀቂያዋ ነው። የፍጥረት ትግል ማብቂያ ነው። የሁሉ ነገር መጨረሻ ነው። በዚያ የመለከቶቹ ማብቂያ ይሆናል። በዚያ የጽዋዎቹ ማብቂያ ይሆናል። የምድር መጨረሻ ነው። የ… እንደውም የጊዜም ጭምር መጨረሻ ነው። ጊዜ ያበቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህ እንደሚሆን ተናግሯል።
ራዕይ ምዕራፍ 10 ቁጥር ከ1 እስከ 7። ጊዜ ያበቃል። መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ጊዜ አይኖርም” ይህ የሚሆነው እነዚህ ትልልቅ ነገሮች በሚፈጸሙ ጊዜ ነው። በሰባተኛው ማሕተም መጨረሻ ላይ በዚህ ዘመን ውስጥ ያለ ሁሉም ነገር ያበቃል።
የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ መውረድ ወደፊት “የሚፈጸም ታላቅ ክስተት” ነው። ስለዚህ ከዚህ ቀደም ታይቶ ያለፈው ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ሊሆን አይችልም።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
ከዚያም እንዲህ አሰብኩ፡- “ጌታ ሆይ ይህ ምንድነው?” ከዚያም ቤቴ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃ ወዲያ ወዲህ ተንጎራደድኩ። ተንበርክኬ ጸለይኩ፤ ተመልሼ መጽሐፍ ቅዱሴን ከፈትኩ፤ ተቀመጥኩ፤ አነበብኩ፤ ወዲያ ወዲህ ተራመድኩ። ከዚያም በጸጥታ ውስጥ ስሆን ድንገት በአንድ ጊዜ ተገለጠልኝ። ከዚያም እስክሪፕቶዬን ይዤ በፍጥነት እጽፈው ጀመርኩ፤ ያየሁትንና የተገለጠልኝን በሙሉ ልቅም አድርጌ ጻፍኩ። ከዚያም ይዤው እሄድና ቀኑን ሙሉ የጻፍኩት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሙሉ በሙሉ ይስማማ እንደሆን ስመረምር እውላለው። ከዚያም … “ሁሉን ፈትኑ” ይል የለ። አያችሁ?
ይህን ደግሞ ተቀበልኩ። “የሚገርማችሁ ራዕይ ያዩ ብዙ ሰዎች አሉ። ብዙዎች መገለጥ ተቀብለዋል።” ከቃሉ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ጣሉት። አዎን፤ አትቀበሉት።
ወንድም ብራንሐም ያየውን ራዕይ ጻፈው፤ ከዚያም ትክክለኛነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ አረጋገጠ። ስለዚህ እውነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው እርሱ የተቀበላቸውን መገለጦች ከመጽፍ ቅዱስ በማረጋገጥ ብቻ ነው።
64-0719M የመለከቶች በዓል
ምክንያቱም በሰባተኛው መለከት ሰዓት ዝምታ ነበረ። “ማንም አላወቀም፤ ያም ክርስቶስ የሚመጣበት ሰዓት ወይም ደቂቃ ነው፤” ለእኛ እንደገለጠልን …
የዚያ ማሕተም ሚስጥራት አንዱ ያልተገለጠበት ምክንያት የተናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች ስለሆኑ ነው፤ እስካሁንም ማንም አያውቀውም ምክንያቱም ስለሱ የሚያውቅ ማንም የለም፤ ደግሞም አልተጻፈም …
ሰባቱ ነጎድጓዶች እና ሰባተኛው ማሕተም እንድናውቅ ያልተፈቀዱልን ጉዳዮች ናቸው። ወዳልተፈቀደልን ቦታ ለመግባት አንሞክር። ሁለቱም አልተጻፉም።
63-0324E ሰባተኛው ማሕተም
እንግዲህ አሁን በመጠናቀቂያው በእግዚአብሔር ቸርነት የስድስቱንም ማሕተሞች ሚስጥራት አግኝተናል፤ ደግሞም ሰባተኛው ማሕተም ለሕዝብ እንደማይገለጥ ይፋ እንደማይደረግ እናውቃለን።
63-1110M አሁን በወኅኒ ያሉ ነፍሳት
ሰባቱ ማሕተሞች መጠናቀቃቸውን አስታውሱ፤ እነዘያ ሰባት የተገለጡ እውነቶችም …
ከእነርሱ አንዱ እንድናውቅ አልፈቀደልንም። እኛም … ሰባቱ ማሕተሞች ሲገለጡ የነበራችሁና የሰማችሁ ስንቶች ናችሁ? ሁላችሁም የነበራችሁ ይመስለኛል። አያችሁ፤ ሰባተኛውን ማሕተም እንድናወቅ አልፈቀደልንም።
ለሕዝብ አልተገለጡም ብሏል። ደግሞም “እኛ” አናውቃቸውም ብሏል። ስለዚህ ሕዝቡ ማለት እኛ ነን።
63-0324 ሰባተኛው ማሕተም
8ኛው ምዕራፍ የሰባተኛውን ማሕተም መቼት ይገልጣል፤ በዚያም ከሰባተኛው ማሕተም በቀር ሌላ ምንም አልተገለጠም። ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም የተገለጠ ነገር የለም። ደግሞም ከራዕይ ምዕራፍ 7 ጋር የሚያያይዘው ምንም ነገር የለም። የሰባተኛውን ማሕተም መገለጥ በተመለከተ ፍጹም የሆነ ጸጥታ ብቻ ነው ያለው …
ኢየሱስ እራሱ ስለ መጨረሻው ዘመን ሲናገር ስለ ስድስቱ ማሕተሞች ተናገረ፤ ሰባተኛውጋ ሲደርስ እርሱም ዝም አለ …
… ኢየሱስ የተናገረው ይፈጸማል። እኛስ ይህን እንዴት ልናውቅ እንችል ነበር? ይኸው በትምሕርቱ ወይም በስብከቱ (እዚያ በሰበከ ጊዜ) ስለ ስድስቱ ማሕተሞች በደምብ ገልጦ አስተማረ፤ ስድስቱንም ማሕተሞች ገለጠ፤ ነገር ግን ሰባተኛውጋ ሲደርስ ዝም አለ። አያችሁ?
ከዚያም ማሕተሞቹ በተከፈቱ ጊዜ እግዚአብሔር (ልብ በሉ) ስለ ሰባተኛው ማሕተም አንዳችም ነገር እንኳ ሳይገልጥ ተወ። አያችሁ? ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተያዘ ፍጹም ሚስጥር ነው…
ወንድም ብራንሐም በዚህ መንገድ የሰባተኛውን ማሕተም ሚስጥር ገለጠ። ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ የማይችል ማሕተም ነው። ትልቅ ሚስጥር ነው።
ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም ተፈቷል የምትሉ ከሆነ እንዲሁም ምን ማለት እንደሆነ እናውቃለን የምትሉ ከሆነ ራሳችሁንም የሚሰሙዋችሁንም ሰዎች እያታለላችሁ ናችሁ።
63-1127 ዓለም እንደገና እየወደቀች ነው
መንፈስ ቅዱስ እራሱ ይመጣል፤ የተጻፈውን ቃል ይገልጣል እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን ያሳያል!
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
መንፈስ ቅዱስ መገኘት ማረጋገጫው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች መግለጥ መቻሉ እና ወደፊት ሊሆን ያለውን ነገር መተንበይ መቻሉ ነው።
65-0725
እምነት ምንድነው? እምነት የሚገለጥላችሁ ነገር ነው፤ ነገር ግን ገና ያልተፈጸመ፤ እናንተ ግን እንደሚፈጸም ታምናላችሁ። እምነት የእግዚአብሔር ፈቃድ መገለጥ ነው።
63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ
አሁን ይህ [ብርቱው መልአክ] በዚህ በ10ኛው ምዕራፍ ውስጥ ተመልሶ ይመጣል፤ ከዚያም ከሚመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሚስጥራት ሁሉ ይፈጸማሉ፤ ማሕተሞቹ በሙሉ ይፈታሉ፤ ከዚያም በኋላ ጊዜ የሚባል ነገር እንደማይኖር ያውጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር ሚስጥራቱ ሁሉ ይጠናቀቃሉ፤ ብርቱውም መልአክ ይገለጣል። ወደዚያ ጊዜ ቀርበናል፤ እውነት ነው።
ዲሴምበር 1965 ሚስጥራቱ ሙሉ በሙሉ በተገለጡ ጊዜ ከዚያ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ወደ ምድር ሊመጣ የሚችለው። እስከ ማርች 17 ቀን 1963 ድረስ መልአኩ አልመጣም ነበር። ወንድም ብራንሐም የመልአኩ መምጫ በጣም ቅርብ እንደሆነ ይሰማው ነበር፤ ስለዚህ እስከዚያ ቀን ድረስ የመልአኩ መምጣት ገና ወደ ፊት ነበር። ቀድሞ መጥቶ ያለፈው ደመና መልአኩ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም የመልአኩ መምጣት ከደመናውም በኋላ ገና ወደፊት ነበረ።
63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ
… ምስጢራቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ እግዚአብሔር ቃል ሆነው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ሙሉ መገለጥ ለሰው ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ሚስጥር እና ሌላው ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል። ሚስጥራቱ በሙሉ፤ የእባቡ ዘር እና ሌላው ሊገለጥ ያለው ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል።
…ማሕተሞቹ ሲፈቱ እና ሚስጥራቱ ሲገለጡ የዚያን ጊዜ መልአኩ ይወርዳል፤ መልእክተኛው ማለትም ክርስቶስ ይመጣና እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ ያሳርፋርል፤ ከራሱም በላይ ቀስተደመና ይታያል።
እንግዲህ ልብ በሉ፤ ይህ ሰባተኛ መልአክ በዚህ ምጻት ጊዜ በምድር ላይ ነው።
“በዚህ ምጻት”። በነጠላ ቁጥር ነው የተገለጸው። አንድ ምጻት ብቻ። የትኛው ምጻት? የመልአኩ ምጻት ወይስ የሚስጥራቱ ምጻት?
አሁን ይህ [ብርቱው መልአክ] በዚህ በ10ኛው ምዕራፍ ውስጥ ተመልሶ ይመጣል፤ ከዚያም ከሚመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሚስጥራት ሁሉ ይፈጸማሉ፤ ማሕተሞቹ በሙሉ ይፈታሉ፤ ከዚያም በኋላ ጊዜ የሚባል ነገር እንደማይኖር ያውጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር ሚስጥራቱ ሁሉ ይጠናቀቃሉ፤ ብርቱውም መልአክ ይገለጣል። ወደዚያ ጊዜ ቀርበናል።
ሰባተኛው መልአክ የሚስጥራቱ መገለጥ በሚመጣ ጊዜ ተቀብሎ ይገልጥና ያስተምር ዘንድ በምድር ላይ መሆን አለበት።
ከዚያም ሚስጥራቱ ከተጠናቀቁ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው (ሚስጥራቱ የተጠናቀቁት ወንድም ብራንሐም ሲሞት ነው)።
ስለዚህ ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ መልአኩ አልወረደም።
ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ያገለግል በነበረ ጊዜ ሚስጥራቱ ብቻ ናቸው ከሰማይ የወረዱት።
እነዚህን ሁለት መውረዶች አትቀላቅሉ።
መጀመሪያ ሚስጥራቱ ወደ ምድር ይመጣሉ፣ ከዚያም ከፈተጸሙ በኋላ መልአኩ ወደ ምድር የሚመጣበት ጊዜ ይሆናል፤ ሲመጣም ሙታንን ያስነሳቸዋል።
ጠፍተው የነበሩ ነገር ግን የሚመለሱ ሚስጥረትን በጥቂቱ እንመልከት፡-
62-1230E ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ይህ መልአክ ከሚያጠናቅቃቸው ሚስጥራት መካከል ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው፤ “ሚስጥራቱ” በሙሉ፣ የእግዚአብሔር ሚስጥራት በሙሉ።
1. በዘመናት ውስጥ ሁሉ ሚስጥር የነበረው የእባቡ ራስ።
2. የተገለጠው ጸጋ፤ እውነተኛው ትክክለኛው ጸጋ
3. ለዘላለም የሚነድ ሲኦል የለም። ሐጥያተኞች ለብዙ ሚሊዮን ዓመታት ይቃጠላሉ። ነገር ግን ዘላለማዊ የተባለ ነገር ሁሉ ጅማሬም ፍጻሜም የለውም፤ ሲኦል ደግሞ የተፈጠረ ነገር ነው።
እነዚህ ሁሉ ሚስጥራት!
4. የመንፈስ ቅዱስ ሚስጥር፤ ይህም የሰውን ትኩረት የሚስብ እንቅስቃሴ ሳይሆን ክርስቶስ በውስጣችሁ የሚራው የራሱ ሥራ ነው።
5. የውሃ ጥምቀት ሚስጥር። የስላሴ አስተማሪዎች ጥምቀትን “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” አድርገውታል። የመለኮት ሚስጥር “በኢየሱስ ክርስቶስ” ስም በሚደረገው ሚስጥር ተፈጽሟል፤ የዮሐንስ ራዕይ እንደሚናገረው ይህን ሚስጥር ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን ተቀብላዋለች።
ከሚስጥራቱ ጥቂቱ እነዚህ ናቸው።
6. የእሳት አምድ ተመልሶ መምጣት። አሜን! ሊፈጸም ያለው ነገር ይህ ነው፤ እኛም አሁን እናየዋለን።
በጣም ድንቅ ነው፤ ሚስጥራቱን ማጥናት ድንቅ ነው።
61-0618 ራዕይ ምዕራፍ አምስት - 2
7. … በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል።” እግዚአብሔር ማን እንደሆነና እንዴት እንደተገለጠ፤ ያ ማሕተም በተከፈተ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዴት እንደምንረዳ፤ እርሱም እራሱ እግዚአብሔር በስጋ መገለጡ ነው፤ ይህም የማንነቱ መገለጥ ነው፤
8. የቤተክርስቲያን ዘመን ሚስጥራት በሙሉ ሲጠናቀቁ፣ የቤዛነት ሚስጥራት ሁሉ ሲጠናቀቁ
65-0418M ይህ የንጋት ፀሃይ መውጣት ነው
9. … እነዚያን ሚስጥራት መስማት። ጋብቻ፣ ፍቺ፣ የእባቡ ራስ
የጥንቷ ቤተክርስቲያን እነዚህን ሁሉ አስተምሕሮዎች ታውቃቸው ነበር። ነገር ግን በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የእነዚህ አስተምሕሮዎች እውቀት ጠፋ።
ሰባቱ ማሕተሞች ሁሉም ተፈተው ከሆነ ምዕራፍ 4፣ 5፣ 6፣ 7 እና 8 ለወደፊት ለእኛ ምንም ትርጉም የላቸውም፤ ምንም መልእክት የላቸውም ማለት ነው።
እነዚህ ምዕራፎች የሚያካትቷቸው ክስተቶች ምን ምን እንደሆኑ እንይ፤ ከዚያም ወንድም ብራንሐም ስለነርሱ ምን እንዳለ እናያለን።
በሰማይ ሰባቱ ማሕተሞች የሚፈቱበትን ትዕይንት አስቡ።
1. ራዕይ ምዕራፍ 3 ስለ ሰባተኛው ወይም ስለ መጨረሻው የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ነው የሚናገረው።
2. ራዕይ ምዕራፍ 4 ከመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በኋላ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከምትነጠቅበት ጊዜ ይጀምርና በሰማይ የሚከናወኑ ክስተቶችን ይተርካል። ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ የምትነጠቅበት ጊዜ ዓለም ወደ ታላቁ መከራ የምትገባበትና የቤተክርስቲያን ዘመን የሚያበቃበት ጊዜ ነው። እግዚአብሔርም በሰማይ ነዋሪዎች ተከብቦ በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
3. ራዕይ ምዕራፍ 5 በዙፋኑ መካከል የተቀመጠውን በጉን ይገልጻል፤ እርሱም በዘመናት ውስጥ ወደ ኋላ ተመልሶ በማየት የሰራው የማዳን ሥራ ሙሉ በሙሉ መልካም መሆኑን አይቶ የቤዛነትን መጽሐፍ ለመውሰድ በዘመን ወደፊት ተሻግሮ ይሄዳል። እኛ ሰዎች በዘመን ወደ ኋላ እና ወደፊት መንቀሳቀስ ስለማንችል በጉ የሚያደርገው ነገር ለእኛ አእምሮ ከባድ ነው። እኛ አሁን በተባለው የጊዜ ፍሰት አማካኝነት መጓዝ ብቻ ነው የምንችለው። ይህ የሰማይ ራዕይ ውስብስብ ነው ምክንያቱም ክርስቶስን በሁለት ዓይነት ማዕረግ ያሳየናል፡- ክርስቶስን እንደ ፈጣሪ ያሳየናል (የፍጥረት ባለቤት እርሱ መሆኑን)፣ እና አዳኝ መሆኑን ምክንያቱም እርሱ በጉ ነው።
ነገር ግን ሁለት የተለያዩ አካላት በአንድ ዙፋን ላይ ሊቀመጡ አይችሉም።
ኢሳይያስ 43፡1 አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
11 እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
ስለዚህ በሰማ ከእግዚአብሔር ጎን የቆመ ወይም የተቀመጠ አዳኝ ሊኖር አይችልም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።
በዚህ ጊዜ ሙሽራይቱ በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ነች።
ስለዚህ እናንተ በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን እስክትቆሙ ድረስ ሰባቱ ማሕተሞች ሊፈቱ አይችሉም።
በዘመን ቅደም ተከተል ምዕራፍ 5 የሚመጣው ከምዕራፍ 4 በኋላ ነው፤ ስለዚህ ነገሮችን በቅደም ተከተላቸው እየተመለከትናቸው ነን።
4. ራዕይ ምዕራፍ 6 የመጀመሪያዎቹን ስድስት ማሕተሞች መፈታት ይገለጻል።
እነዚህ ስድስት ማሕተሞች የሚገልጡት የቤተክርስቲያን ዘመናትን እና አይሁዶችን ነው፤ በመጨረሻም ምድር ለሺ ዓመቱ መንግስት እንድትዘጋጅ በሚያጠራት በታላቁ መከራ ይጠናቀቃሉ። ስለዚህ ስድስተኛው ማሕተም የሚከፈተው በታላቁ መከራ ዘመን ነው፤ ሁለቱ ነብያትም ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት የሚችሉት ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም አልግሎታቸው ያለው በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የተፈጥሮን ኡደት መቋረጥ ነው።
5. ራዕይ ምዕራፍ 7 ስለ 144,000ዎቹ አይሁዶችና ስለ እንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት ይናገራል፤ እንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት የዳኑ ነገር ግን የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን በማመናቸው ተታልለው ታላቁ መከራ ውስጥ የገቡ ክርስቲያኖች ናቸው። እነዚህ በታላቁ መከራ አማካኝነት መንጻት ያለባቸው ሁለት ቡድኖች ናቸው፤ እነርሱም የአውሬውን ምልክት አንቀበልም ባሉ ጊዜ ይገደላሉ። በጣም ያሳዝናል። ከታላቁ መከራ በፊት ፓስተራቸውን ለመቃወም ወኔ አልነበራቸውም። በታላቁ መከራ ውስጥ ግን የክርስቶስ ተቃዋሚውን አንቀበልም ስላሉ ይገደላሉ። እንዲህ ዓይነቱን ድፍረት አስቀድመው ማጣታቸው አሳዛኝ ነገር ነው፤ መጀመሪያም ወኔው ቢኖራቸው የሙሽራይቱ አካል መሆን ይችሉ ነበር።
ይህ ምዕራፍ ሰባት የተጻፈው ሰባተኛውን ማሕተም ከሌሎቹ ስድስት ማሕተሞች ለመለየት ነው። ለምን?
ስድስቱ ማሕተሞች ሚስጥራዊ ነበሩ የተገለጡትና የተብራሩት ወንድም ብራንሐም ስለ ማሕተሞቹ ራዕይ ባየ ጊዜ ነው፤ ይህ ራዕይ ለወንድም ብራንሐም የተገለጠው በ1963 ያንን ታላቅ ደመና የሰሩት ሰባት መላእክት ባሳዩት ጊዜ ነው።
ሰባተኛው ማሕተም ግን ከሌሎቹ ስድስት ማሕተሞች ይለያል፤ የሚለየውም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር በመሆኑ ነው፤ ስለዚህ ልናውቀው አንችልም። ለምን?
6. ራዕይ ምዕራፍ 8 በሰማይ ውስጥ በሚታይ ትዕይንት ይጀምራል፤ ከዚያም በታላቅ ጸጥታ ይቀጥላል።
ይህ ሚስጥር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ሚስጥራት ሁሉ በላይ ታላቅና ውስብስብ ሚስጥር ነው። ዝምታን ልትተረጉሙ አትችሉም።
1. ይህ ሚስጥር ከዘመን ጋር የተያያዙ ነገሮች ሁሉ የሚያበቁበት ነው።
እግዚአብሔር የዘመንን ሚስጥራዊ ዳይሜንሽን ይፈታዋል፤ ስለዚህ በሰማይ ያለችዋ ሙሽራ እና ተገድለው ከሞቱ በኋላ ከሙታን የተነሱት 144,000ዎቹ አይሁዳውያን ከጊዜ ነጻ ይወጣሉ፤ ነገር ግን ቀሪው ዓለም ደግሞ በጊዜ እስር ቤት ውስጥ ይቆያል።
2. ሰባተኛው ማሕተም ከእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ ፍጻሜ ጋር የተያያዘ ነው፤ በዚህ ዕቅድ ፍጻሜ ላይ በጉ በሰማይ ከምሕረት ዙፋን ላይ ይነሳል፤ በምድር ግን ትንሳኤ እና ንጥቀት በሆኑ ጊዜ ነው ምሕረት ያበቃው ምክንያቱም ከሙሽራይቱ አካላት የመጨረሻው ለንጥቀት ተዘጋጅቷል ከእንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት የመጨረሻው ድኗል። ሆኖም ግን እኛ መረዳት በማንችለው ሚስጥራዊ መንገድ ኢየሱስ አይሁዶችን በታላቁ መከራ ማዳን ይችላል። ከዘመን ውጭ የሆኑትን የሙሽራይቱን አካላት እና በዘመን ውስጥ ያሉትን ቀሪውን ሕዝብ በአንድ ጊዜ ለመረዳት መሞከር ነገሮች ከሚከሰቱበት ቅደም ተከተል አንጻር ውስኑ አእምሮዋችን መረዳት ከሚችልበት አቅም በላይ ነው።
3. ነገር ግን ከትንሳኤ በኋላ የሙሽራይቱ አካላት አዲሱ አካላቸውን እና አሁን ካለን አእምሮ እጅግ የላቀውን አእምሮዋቸውን ሲቀበሉ እነዚህን ክስተቶች ሁሉ መረዳት ይችላሉ።
ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን እንቆቅልሽ ለመፍታት ፍንጭ ይሰጣሉ። ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትንሳኤ በኋላ አዲሱን አካላችንን ከለበስንና አዲስ አእምሮ ከተቀበልን በኋላ ነው፤ ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከአሁኑ የበለጠ እጅግ አስተዋዮች እንሆናለን።
63-0321 አራተኛው ማሕተም
ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን መስማት የሚችል ሕዝብ ሲመጣ እስኪያሰሙ ድረስ ጠብቁ። የእግዚአብሔር ቃል ስለታም ሰይፍ ነው፤ ይቆርጣል። እነርሱም ሰማያትን መዝጋት ይችላሉ፤ የፈለጉትን መዝጋት የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።
ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ለአይሁዶችም የሚናገሩት መልእክት አላቸው።
በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ኤልያስ ለሶስት ዓመት ተኩል ዝናብ እንዳይዘንብ ያደርጋል። ሙሴ መቅሰፍቶች እንዲመጡና የተፈጥሮ ኡደቶች እንዲቋረጡ ያደርጋል።
4. ሌላው የሚሆነው ነገር ደግሞ ምድር በላይዋ ላይ ከተሰራው ሐጥያት ትጠራለች፤ ትነጻለች። ታላቁ መከራ ለሺ ዓመቱ መንግስት መወለድ የመጨረሻው የምጥ ጣር ነው።
ወንድም ብራንሐም ስለነዚህ የወደፊት ክስተቶች ምን እንደሚል እንይ።
63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ
እነዚያ ማሕተሞች ሲፈቱ እንዴት ያለ የታላቅ ደስታ ጊዜ ይሆን። ዮሐንስ ተመልክቶ ከዘመን መጋረጃ ባሻገር ሳያይ አይቀርም፤ ስለዚህ እንዲህ አለ፡- “ያውልህ ዮሐንስ።” በጣም ደስተኛ ነበር።
ነብዩ ዮሐንስ ከዘመን መጋረጃ በስተጀርባ አሻግሮ በመመልከት እራሱን ከ24ቱ ሽማግሌዎች መካከለ አየ። የወደፊቱን አስቀድሞ እያየ ነበር።
60-1231 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 1
አሁን 4ተኛውን ምዕራፍ እንጀምራለን፡
ከዚያ በኋላም አየሁ፣ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፤ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምጽ፡- ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለው አለ።
ከዚያ በኋላም (ከቤተክርስቲያን ዘመን በኋላ)
ይህ ሁሉ ከዚያም በኋላ የተባለው ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ በምድር ላይ የሚፈጸም ነው። አያችሁ፤ ከቤተክርስቲያን መነጠቅ በኋላ።
60-1231 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 1
የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ሁሉም ነገር ከተዘጋጀ በኋላ የአራተኛው ምዕረፍ ክስተቶች ሁሉ በተዘጋጁ ጊዜ የቤተክርስቲያን ዘመን አብቅቷል። እርሱም ምድርን ለቅቆ ሄዷል፤ አያችሁ።
60-1231 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 1
ደግሞ ልብ በሉ፤ ዮሐንስ ከቤተክርስቲያን ዘመን በኋላ ወዲያው ወደ ላይ ተነጥቆ መሄዱ የቤተክርስቲያን መነጠቅ ተምሳሌት ነው። ይህ የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያው መነጠቅ ይሆናል። ልክ ዮሐንስ ተነጥቆ እንደሄደው ሁሉ ቤተክርስቲያንም ትነጠቃለች፤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ትሄዳለች።
60-1231 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 1
ይህ ጊዜው ነው፤ የፍርድ ሰዓት ቀርቧል። ዮሐንስ ያየው ከቤተክርስቲያን ዘመን በኋላ ምን እንደሚሆን ነው።
61-0101 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 2
“ከዚህም ነገር በኋላ” የሚለውን ቃል እናገኛለን። ከዚያ በኋላ ማለት “የቤተክርስቲያን ዘመን ካበቃ በኋላ” ማለት ነው።
ከዚያ በኋላ ዮሐንስ “ወደላይ እንዲወጣ” ተጠራ ትርጉሙም ከዚህ ከምድራዊው ዓለም ወደ ሰማያዊው ዓለም ከፍ ማለት ነው። በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የሚሆነውን ሁሉ አሳየው። ከዚያም የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ዮሐንስ በክርስቶስ ተጠርቶ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የሚሄዶ አማኞች ሁሉ ጥላ መሆኑን እናያለን። ገብቷችኋል? “ወደዚህ ውጣ” ተብሎ ተጠራ።
61-0108 ራዕይ ምዕራፍ አራት - 3
ራዕይ 4፡1፤ ቤተክርስቲያን ከሄደች በኋላ … ዮሐንስ ወደ ላይ ወጣ። ይህም ቤተክርስቲያን ተነጥቃ መሄዷን ነው የሚያሳየን።
ዮሐንስ በመንፈስ ወደ ላይ ወጣ፤ ወደ ሰማይ ተወስዶ እግዚአብሔር ሊያደርግ ተስፋ የሰጠውን ነገር ሁሉ ተመለከተ፤ ለደቀመዛሙርትም እንዲህ አለ፡-“እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?” እርሱም የጌታን ምጻትና ምን እንደሚፈጸም አየ። በምድር ሳለ በቤተክርስቲያን መነጠቅ ጊዜ ምን እንደሚፈጸም አየ፤ ከዚያም ወደ ላይ ተነጥቆ ሄዶ ከሺ ዓመት መንግስት በኋላ እንኳ ምን እንደሚፈጸም ተመለተከተ።
ወደ ሰማይ መነጠቅ ወደፊት የሚሆነውን ማየት ያስችላችኋል።
63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ሚስጥራት መካከል ያለው ቅርንጫፍ
… የራዕይ መጽሐፍ በተለይ 4ኛው ምዕራፍ ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ከሄደች በኋላ የሚፈጸመውን ነገር ይገልጣል፤ ቤተክርስቲያን በራዕይ መጽሐፍ በ3ኛው ምዕራፍ ውስጥ ተነጥቃ ትሄዳለች፤ ከዚያም እስከ ራዕይ መጽሐፍ 19ኛው ምዕራፍ ድረስ አትመለስም።
የቤተክርስቲያን መጽሐፍ ምዕራፍ 1 - ሰላምታው
ዮሐንስም ሲመለከት ዙፋኑ ላይ “አንድ” ብቻ ነው ያየው። በራዕይ 4፡2-3 እና 9-10 እንደምናየው በጉ መጽሐፉን በዙፋን ላይ “ከተቀመጠው” እጅ ሲወስድ የምናየው ከራዕይ 5፡6-8 በፊት አይደለም (እርሱም በጊዜ ቅደም ተከተል ራዕይ 4፡2-3ን ተከትሎ ነው የሚሆነው)።
63-0324M ማሕተሞቹን በተመለከተ ጥያቄዎችና መልሶች
በራዕይ ከቁጥር 5 እስከ 9 ድረስ በጉ መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ የሚዘምሩት እናማን ናቸው … እነዚህ የተነጠቁ ቅዱሳን ናቸውን?
አይደሉም፤ ራዕይ 5፡9 አይደሉም። ልብ ብላችሁ ብታዩ እነዚህ ቅዱሳን አይደሉም። እርሱ ገና ንብረቱን አልተረከበም። አያችሁ? እነዚህ ቅዱሳን አይደሉም። ካስተዋላችሁ ሽማግሌዎች እና አውሬው ናቸው፤ እነርሱም ይዘምራሉ።
አንድ ችግር አለ። አንድ ችግር አለ። ስለ ጉዳዩ የተባለው ይህ ብቻ ነው። የሆነ ነገር ተፈጽሟል። አያችሁ? የሆነ ቦታ የሆነ የተበላሸ ነገር አለ። ሁላችሁም ደህና ናችሁ? የታመመ ወይም ሌላ ችግር ያለበት ሰው የለም? [ከጉባኤው መካከል አንድ ሰው ወንድም ብራንሐም ራዕይ 5፡9ን እንደገና እንዲያነብ ጠየቀው - ኤዲተር]
… መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማሕተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና … (ይኸውና። እዚህ ላይ ተሳስቼ ነበር። አያችሁ?) … በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ …
… ነገር ግን አያችሁ እዚያ ላይ እንዳስቆመኝ … “ከሕዝብ፣ ከወገንን ከቋንቋም ሁሉ ዋጅተህ” ብለው የዘመሩት መዝሙር። በእርግጥ እነርሱ ናቸው።
ስለዚህ ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ በጉ ማሕተሞቹን ከመፍታቱ በፊት ተነጥቀው የሄዱ ቅዱሳን በእግዘአብሔር ዙፋን ዙርያ ይቆማሉ። ሰባቱ ማሕተሞች ዕውን የሚከፈቱ ጊዜ መፈታታቸውን ለማየት በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ትቆማላችሁ።
63-0317E በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ
“የታለ ያ የዘመን ቤዛ? ማነው ሊወስድ የሚችል?
ከአዳም ጀምሮ እስከ ሐዋርያት ድረስ፤ እስከ ነብያት እና በትውልዶች ሁሉ ውስጥ ቢፈለግ ማንም አልተገኘም። ስለዚህ ምን ይደረግ? በሰማይ ማንም፣ በምድር ማንም አልተገኘም … ኤልያስ በዚያ ቆሞ ነበር። ሙሴም በዚያ ቆሞ ነበር። ከዚህ በፊት የሞቱት ሐዋርያቱ በሙሉ በዚያ ቆመው ነበር፣ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ ቆመው ነበር፤ ኢዮብ፣ እና ሽማግሌዎች ሁሉ። ሁሉም በዚያ ቆመው ነበር፤ ነገር ግን መጽሐፉን ሊወስደውና ሊፈታው ይቅርና ሊመለከተው ሊያየው እንኳ ብቁ የነበረ ሰው አልተገኘም።
ሐዋርያት ሁሉ በዚያ ተገኝተዋል፤ ስለዚህ ይህ የሚሆነው ትንሳኤ ካለፈ በኋላ ነው።
መደምደሚያ
ሰባተኛው ማሕተም አልተከፈተም። ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑ ነው የተገለጠው።
ስድስተኛው ማሕተም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ በሁለቱ ነብያት አማካኝነት ይከፈታል።
ማሕተሞቹ በሚፈቱበት ጊዜ ሙሽራይቱ ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ጋር ሆና በዙፋኑ ዙርያ ትቆማለች።
ስለዚህ ማግኘት የምንችለው የስድስቱን ማሕተሞች መገለጥ ነው ምክንያቱም ስድስቱ ማሕተሞች ሊተረጎሙ የሚችሉ ምልክቶች አሉዋቸው።
“ሰባቱ ማሕተሞች ተፈተዋል፤ ስለዚህ አሁን ሚስጥራትን ሁሉ አውቀናል”። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ አለባችሁ።
በቀቀን የምትባለዋ ወፍ የሰዎችን ንግግር አስመስላ መድገም ትችላለች ግን የተናገረቻቸውን ቃላት መረዳት አትችልም፤ ስለዚህ እንደ በቀቀን የሰው ንግግር ጥቅስ አትድገሙ።
ዘመናችን የንስር ዘመን ነው። ንስር በጥራት የማየት ብቃት ስላለው የተሻለ መረዳትን ይሰጠናል።